cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

N̆̈ꫀw̥ͦ 🄻𝔦𝖋𝔢 ✞︎

አላማችን #ወንጌልን ለአለም መስበክ ነው። ከእኛ ጋር ወንጌልን ይማሩ ይስሩ። ፨ BIBIL STUDY ፨ መንፈሳዊ ነክ መፅሐፍ ፨ Spiritual Picture #worship songslemaget join us ጥያቄዎችን ፣ be @Newlifechanalbot lay yanagruge for more Join us @Newlifechanal @Newlifechanal

Show more
The country is not specifiedThe language is not specifiedThe category is not specified
Advertising posts
170
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

@Newlifechanal @Newlifechanal @Newlifechanal Share our chanal for ur friends
Show all...
Show all...
ለኢየሱስ ነው - ዘሪቱ ከበደ || Le Eyesus Newe - Zeritu Kebede

​​VALENTINE'S DAY ሼር በማድረግ ትውልዱን ከጥፋት እንታደግ❗ አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለኛ ቤዛ ሆኖ በፍቅሩ የገዛን እጃችንን ለጣኦት እንድንሰጥ አይደለም ብዙ ዋጋ የተከፈለብን እስከ ሞት እንከን በሌለው ፍቅሩ የወደደን መንግስቱን እንድንወርስ እንጂ እንድንጠፋ አይደለም። የቫላንታይ ቀን ድብቅ እውነታ ስንቶቻችን እናውቃለን? ይህን የቫላታይን ቀን (የፍቅረኛሞች ቀን) ብለን ስንቶቻችን ነን የምናከብረው ? ወይስ ሰው ስላከበረውና የስልጣኔ መገለጫ መስሎን ነው የምናከብረው ??? ከክርስቶስ ልደት በፊት በባቢሎን ፤ቤልዘቡል ፤በግሪክ ፓን ፤ ሮማ ሞሎቅ ፤ በላቲን ሳተርን ለሚባሉት ሰይጣኖች ያላገቡ ሴቶች ደም የሚፈስላቸው ቀይ ልብስ የሚለበስላቸው ጣኦቶች ናቸው ይህ ዛሬ ቫለንታይን ተብሎ የመጣው ማለት ነው። የሚገርመው ደሞ ሴቶቹ በዚህ ቀን ለመደፈር ብለው እራቁታቸውን ጫካ መግባታቸው ነው በዚህ ቀን የተደፈረች እና ደሟን ያፈሰሰች ሴትም ሆነ ወንድ በጣኦቱ የተመረጠ እና የተባረከ ነው መባሉ ነው ይበልጥ ነገሩን ሰይጣናዊ የሚያደርገው። ግሪክ አርኬዲያ ብለው በሚጠሩት አስቀያሚ ትርጉም ባለው ተራራቸው ላይ በዚህ ቀን ላይ ነው ያላገቡ ወንድ እና ሴቶቻቸውን ጣኦቱ ስር ወሲብ በመፈጸም ገላቸውን አርክሰው ለሰይጣን የሚገብሩት። ይህ የሰይጣን ቀን ነው ክርስትና ይሄን ትከለክላለች ታወግዛለች። (ሁሉም ቀን የእግዚአብሔር ነው ግብሩ ነው የሰይጣን የሚያደርገው) ኢየሱስ ክርስቶስ ከመውለዱ ከዘመናት በፊት አረማውያን ሮማውያኖች Feb 14 ማታ እና ለ Feb 15 ንጋት አጥቢያ የተኩላ አዱኚ ለሚሉት ሉፐርካልያ (luperkalya ) ጣኦት የሚዘጋች ክብረ በአል ነው፡፡ ንጉሥ ቆስጠንጢኖስ ክርስትና ተቀብሎ እውነተኛ የጽድቅ ሃይማኖት መሆኑን በማውጁ ማንኛውም የጣኦት አምልኮ እንዲቀር ቢያስጠነቅቅም የተውሰኑ የሮማውያን ሰዎች ግን በአሉን ማክበር አልተውም። እንዴት ይህ አረማዊ ባህል ቫለንታይን የሚል ሰያሜ ተሰጠው? ቫለንታይን የሚል ስም በሮማውያን ዘንድ የተለመደ ስያሜ ነው፡፡ ቫለንታይን የጥንታዊ ታዋቂው ሉፐርኩስ ጣኦት ነው። ሉፐርኩስ በግሪካዎያን ፓን (pan) ተብሎ ሚጠራው ከወገቡ በታች በግ አናቱ ላይ ቀንድ ያለው ጣኦት ነው። በጥንታውያን አይሁድ ደግሞ ይህ ፓን ባል (baal) በሚል ስያሜ ይታወቃል። ጥንታውያን ሮማውያን ከባቢሎናውያን የቀዱት አረማዊ የልብ (heart) ምልክት ይጠቁማሉ፡፡ በባቢሎናውያን ባል (bal) ልብ የሚል ፍች ነው ያለው፡፡ በአሁኑ ጊዜ ይህ አረማዊ የልብ ምልክት ለቫለንታይን ቀን (የፍቅረኛሞች ቀን) የምንለው መግለጫነት እንጠቀምበታለን። ባል የባቢሎናውያን ጣኦት ነበር። በዚህ የሃጥያት ቀን በትንቹ ይህ ይሆናል 1. በዚህ ቀን February 14 በብዙ የሚቆጠሩ እህቶቻችንን ክብረ ንጽህናቸውን (ድንግልናቸውን) ያጣሉ❗ 2. በርካታ ወጣቶች በስካር ምክንያት በሚያሽከረክሩት መኪና ህይወታቸውን እና አካላቸውን ያጣሉ❗ 3. በአለማችን ላይ በከፍተኛ ሁኔታ የአልኮል መጠጥ ሽያጭ የሚከናወንበት ቀን ነው በአጠቃላይ የዝሙት እና ስካር መንፈስ የሚነግስበት በከፍተኛ ሁኔታ ሰይጣን በደም የሚረካበት ቀን ነው። Valentine day ማለት ሰይጣን በጥልቅ እና ረቂቅ ሃሳብ ብዙዎችን የሚያጠምድበት ቀን ነው አስተውሉ ሰይጣን ከ7ሺህ አመት በላይ የክፋት ልምድ አለው። እንግዲህ ምርጫው ያንተ/ቺ ነው :- የእግዚአብሔር ወይም የሰይጣን ልጅ መሆን??? " ሕዝቤ እውቀት ከማጣቱ የተነሣ ጠፍቶአል፤ አንተም እውቀትን ጠልተሃልና እኔ ካህን እንዳትሆነኝ እጠላሃለሁ፤ የአምላክህንም ሕግ ረስተሃልና እኔ ደግሞ ልጆችህን እረሳለሁ። " (ትንቢተ ሆሴዕ 4 : 6) እግዚአብሔር አምላክ ማስተዋሉን ያድለን። @Newlifechanal @Newlifechanal @Newlifechanal
Show all...

BETHEL REGASA :SITTAN SIQAA..(live worship)
Show all...