en
Feedback
AVT - aviewtainment

AVT - aviewtainment

Open in Telegram

📈 Analytical overview of Telegram channel AVT - aviewtainment

Channel AVT - aviewtainment (@aviewtainment) in the Amharic language segment is an active participant. Currently, the community unites 12 687 subscribers, ranking 4 929 in the Sports category and 2 257 in the Ethiopia region.

📊 Audience metrics and dynamics

Since its creation on невідомо, the project has demonstrated rapid growth, gathering an audience of 12 687 subscribers.

According to the latest data from 25 December, 2024, the channel demonstrates stable activity. Although there has been a change in the number of participants by -237 over the last 30 days and by 0 over the last 24 hours, overall reach remains high.

  • Verification status: Not verified
  • Engagement rate (ER): The average audience engagement rate is 0%. Within the first 24 hours after publication, content typically collects N/A% reactions from the total number of subscribers.
  • Post reach: On average, each post receives 0 views. Within the first day, a publication typically gains 0 views.
  • Reactions and interaction: The audience actively supports content: the average number of reactions per post is 0.

📝 Description and content policy

Channel description not provided.

Thanks to the high frequency of updates (latest data received on 26 December, 2024), the channel maintains relevance and a high level of publication reach. Analytics show that the audience actively interacts with content, making it an important point of influence in the Sports category.

12 687
Subscribers
No data24 hours
-397 days
-23730 days
Posts Archive
ልማደኞቹ‼️ ............ የቻምፒዮንስሊግ ኃያላኖቹ ሪያል ማድሪዶች ዛሬም ባለትልቁ ጆሮ ዋንጫ ጫፍ ደርሰው ባዶ እጃቸውን አልተመለሱም። የቻምፒዮንስሊግ ድል ልማደኞቹ ዳኒ ካርቫሃል 74ኛ፣ ቪኒ
ልማደኞቹ‼️ ............ የቻምፒዮንስሊግ ኃያላኖቹ ሪያል ማድሪዶች ዛሬም ባለትልቁ ጆሮ ዋንጫ ጫፍ ደርሰው ባዶ እጃቸውን አልተመለሱም። የቻምፒዮንስሊግ ድል ልማደኞቹ ዳኒ ካርቫሃል 74ኛ፣ ቪኒ ጁኒየር ደግሞ በዘጠኝ ደቂቃ ልዩነት ባስቆጠሯቸው ግቦች እንደተገመተው ዶርትሙንድን 2ለ0 በማሸነፍ 15ኛውን የቻምፒዮንስሊግ ዋንጫ ወደ ስፔን ማድሪድ ወስደዋል። የማይሞቃቸው የማይበርዳቸው ጣሊያናዊ ታክቲሺያን አሰልጣኝ ካርሎ አንቸሎቲ የመድረኩ መሃንዲስ መሆናቸውን በተግባር በማሳየት ከነጮቹ ጋር ትልቁን ዋንጫ ለሦስተኛ ጊዜ ስመዋል። የመጨረሻ ጨዋታውን ያደረገው የመኃል ሜዳው ሞተር ቶኒ ክሩስም ከነጮቹ ጋር 5ኛ የቻምፒዮንስሊግ ዋንጫውን አንስቶ ስንብቱ በድል ደምቆለታል። በተቃራኒው እድለ ቢሱ ማርኮ ሪውስ 12 አመታትን በታማኝነት አገልግሎ ዛሬ የመጨረሻ ጨዋታውን ለማድረግ በተሰለፈበት የዶርትሙንድ ማለያ ዋንጫ የማንሳት የመጨረሻ ተስፋው በልማደኞቹ ተጨናግፎበታል። የጀርመኑም ክለብ ከ11 አመት በፊት 2013 ላይ በዌምብሌ ስቴድየም ፍፃሜ በባየርሙኒክ 2ለ1ተሸንፎ ያጣው የቻምፒዮንስሊግ ዋንጫ ዛሬም በዌምብሌ ፊቱን አዙሮበታል። ቻምፒዮንስሊግን ባህላዊ ፍልሚያቸው ያደረጉት ልማደኞቹ ነጮች ግን ዘንድሮም ለአይነት እንኳን ለሌላ ክለብ የቻምፒዮንነት ቁልፉን አሳልፈው ሳይሰጡ ወደ ቤርናባው ይዘውት ተመልሰዋል‼️

ቲቡአ ኮርቱአ በውድድር አመቱ የቻምፒዮንስሊግ ጨዋታ የመጀመሪያውን ፍልሚያ ቋሚ ሆኖ ይጀምራል። ሪያል ማድሪድ ለዚህ ፍፃሜ ሲደርስ ድንቅ ብቃቱን ያሳየው አንድሪ ሉኒን በጉንፋን በመያዙ የተጠባባቂ ወን
ቲቡአ ኮርቱአ በውድድር አመቱ የቻምፒዮንስሊግ ጨዋታ የመጀመሪያውን ፍልሚያ ቋሚ ሆኖ ይጀምራል። ሪያል ማድሪድ ለዚህ ፍፃሜ ሲደርስ ድንቅ ብቃቱን ያሳየው አንድሪ ሉኒን በጉንፋን በመያዙ የተጠባባቂ ወንበር ላይ ለመቀመጥ ተገዷል። 😮

ክሎፕ የቀድሞ ክለባቸውን ዶርተመንድ እና በቻምፒየንስ ሊጉ ብዙ ጊዜ የፈተኗቸውን ቡድን የሆነውን ሪያል ማድሪድ የሚያረጉትን የፍፃሜ ጨዋታ ለመመልከት ዌንብሌ ይገኛሉ። በተመሳሳይ ጆዜ ሞሪኒሆም የቀድሞ
ክሎፕ የቀድሞ ክለባቸውን ዶርተመንድ እና በቻምፒየንስ ሊጉ ብዙ ጊዜ የፈተኗቸውን ቡድን የሆነውን ሪያል ማድሪድ የሚያረጉትን የፍፃሜ ጨዋታ ለመመልከት ዌንብሌ ይገኛሉ። በተመሳሳይ ጆዜ ሞሪኒሆም የቀድሞ ክለባቸው ሪያል ማድሪድን ለመደገፍ ዌምብሌ መገኘታቸውን የሚጠቁሙና ከማድሪድ ደጋፊዎች ጋር የተነሱትን ፎቶ ግራፍ የሚያሳዩ መረጃዎች በማሆበራዊ ሚዲያው እየተዘዋወሩ ይገኛሉ።

ሪያል ማድሪድ እና ቦሩሲያ ዶርትሙንድ ያለፉት 10 ጨዋታዎች፡- ⚪️ ማድሪድ አሸነፈ:- 4 🤝 አቻ፡-3 🟡 ዶርትሙንድ አሸነፈ:- 3 ⚽️ ግቦች:- 35 የቻምፒዮንስ ሊግ ዋንጫ ማን ይወስዳል? 🤔
ሪያል ማድሪድ እና ቦሩሲያ ዶርትሙንድ ያለፉት 10 ጨዋታዎች፡- ⚪️ ማድሪድ አሸነፈ:- 4 🤝 አቻ፡-3 🟡 ዶርትሙንድ አሸነፈ:- 3 ⚽️ ግቦች:- 35 የቻምፒዮንስ ሊግ ዋንጫ ማን ይወስዳል? 🤔

"ማድሪድ ዋንጫ ሲያነሳ ለማየት አልመጣንም!" የቦርስያ ዶርትመንዱ አሰልጣኝ ኤዲን ቴርዚች ቡድናቸው በምሽቱ የአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ ፍፃሜ ጨዋታ በከፍተኛ ደረጃ ለመፎካከር ዝግጁ መሆኑን ገልጸዋል።
"ማድሪድ ዋንጫ ሲያነሳ ለማየት አልመጣንም!" የቦርስያ ዶርትመንዱ አሰልጣኝ ኤዲን ቴርዚች ቡድናቸው በምሽቱ የአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ ፍፃሜ ጨዋታ በከፍተኛ ደረጃ ለመፎካከር ዝግጁ መሆኑን ገልጸዋል። "የመጣነው ማድሪድ ዋንጫ ሲያነሳ ለማየት አይደለም " ያሉት ቴርዚች ቡድናቸው ከቻምፒዮንስሊጉ ኃያል ሪያል ማድሪድ አንፃር ዋንጫውን የማንሳት ዝቅተኛ ግምት ቢሰጠውም ዌምብሌ ላይ የሞት ሽረት ትግል አድርገው በታሪካቸው ሁለተኛውን ባለትልቁን ጆሮ ዋንጫ ለማንሳት እንደሚፋለሙ ተናግረዋል። "ለመፎካከር ዝግጁ ነን " ያሉት አሰልጣኝ ኤዲን ቴርዚች ዌምብሌይ የተገኙት ሪያል ማድሪድ ተጨማሪ የቻምፒየንስ ሊግ ዋንጫ ሲያሸንፍ ለመመልከት አይደለም " ሲሉ ከ27 አመት በኋላ ዋንጫውን ለማንሳት ያላቸውን ፍላጎት ገልፀዋል።

ከታላቁ ዋንጫ በኋላ የሚሸኙት ከዋክብት June 1, 2024 Amen የዌምብሌ የቻምፒዮንስሊግ ፍፃሜ ዋንጫውን ማን ያነሳዋል ከሚለው ጉዳይ ባሻገር በተፋላሚዎቹ ሪያል ማድሪድና ቦሩሲያ ዶርትሙንድ በኩል
ከታላቁ ዋንጫ በኋላ የሚሸኙት ከዋክብት June 1, 2024 Amen የዌምብሌ የቻምፒዮንስሊግ ፍፃሜ ዋንጫውን ማን ያነሳዋል ከሚለው ጉዳይ ባሻገር በተፋላሚዎቹ ሪያል ማድሪድና ቦሩሲያ ዶርትሙንድ በኩል ሁለት ታላላቅ ተጫዋቾች ስንብት በምን መልኩ እንደሚቋጭ በጉጉት ይጠበቃል። አንዱ በእንባና በኃዘን ሌላው ደግሞ በጣፋጭ ደስታ መለየቱ ግድ ነው። 👇ሊንክ በመጫን ሙሉውን ያንብቡ https://aviewtainment.com/?p=64150 ቤተሰብ ለመሆን👇ይጫኑ https://aviewtainment.com/?page_id=59503

ዶርትሙንድ የ27 አመቱን ይደግም ይሆን? June 1, 2024 Amen ዶርትሙንድ በተዓምራት ከተሞላው ብቸኛ የቻምፒዮንስ ሊግ ድላቸው ከ27 ዓመታት በኋላ በሌላ ተመሳሳይ የፍፃሜ ፍልሚያ ላይ ደርሰዋል
ዶርትሙንድ የ27 አመቱን ይደግም ይሆን? June 1, 2024 Amen ዶርትሙንድ በተዓምራት ከተሞላው ብቸኛ የቻምፒዮንስ ሊግ ድላቸው ከ27 ዓመታት በኋላ በሌላ ተመሳሳይ የፍፃሜ ፍልሚያ ላይ ደርሰዋል። 👇ሊንክ በመጫን ሙሉውን ያንብቡ https://aviewtainment.com/?p=64142 ቤተሰብ ለመሆን👇ይጫኑ https://aviewtainment.com/?page_id=59503

በግለሰብ ፍላጎት የሚመሩ ተቋማት June 1, 2024 Amen ተቋማት የሚመሩት በህግና መርህ ሳይሆን ተቋሙን በሚመራው ግለሰብ ግላዊ ባህሪ ነው፡፡ ለዚህም ነው ለአንድ ተቋም ኃላፊ ሲሾም የሰውየው ግ
በግለሰብ ፍላጎት የሚመሩ ተቋማት June 1, 2024 Amen ተቋማት የሚመሩት በህግና መርህ ሳይሆን ተቋሙን በሚመራው ግለሰብ ግላዊ ባህሪ ነው፡፡ ለዚህም ነው ለአንድ ተቋም ኃላፊ ሲሾም የሰውየው ግላዊ ባህሪ የሚጠናው፡፡ ከተቋሙ መተዳደሪያ ደንብ ይልቅ የሰውየው ግላዊ ባህሪ ጉዳይ ይሆናል… 👇ሊንክ በመጫን ሙሉውን ያንብቡ https://aviewtainment.com/?p=64136 ቤተሰብ ለመሆን👇ይጫኑ https://aviewtainment.com/?page_id=59503

የጆዜ ያልተጠበቀ ማረፊያ May 31, 2024 Amen ጆዜ ከቱርኩ ክለብ ጋር ለ 2 ዓመታት የሚያቆያቸውን ኮንትራት ለመፈራረም የተስማሙ ሲሆን፣ በውሉ መሰረት ክለቡ አሰልጣኙን ለተጨማሪ ዓመት የማስፈ
የጆዜ ያልተጠበቀ ማረፊያ May 31, 2024 Amen ጆዜ ከቱርኩ ክለብ ጋር ለ 2 ዓመታት የሚያቆያቸውን ኮንትራት ለመፈራረም የተስማሙ ሲሆን፣ በውሉ መሰረት ክለቡ አሰልጣኙን ለተጨማሪ ዓመት የማስፈረም መብት ይኖረዋል ተብሏል። 👇ሊንክ በመጫን ሙሉውን ያንብቡ https://aviewtainment.com/?p=64133 ቤተሰብ ለመሆን👇ይጫኑ https://aviewtainment.com/?page_id=59503

ሁሉንም ተጫዋቾቹን ለገበያ ያቀረበው ክለብ! May 31, 2024 Amen ኤቨርተን የገባበት ችግር መቋጫው ቢጠፋው የሂሳብ መዝገቡን ለማመጣጠን(ባላንስ) ለማድረግ ሁሉንም የክለቡን ተጫዋቾች ለዝውውር
ሁሉንም ተጫዋቾቹን ለገበያ ያቀረበው ክለብ! May 31, 2024 Amen ኤቨርተን የገባበት ችግር መቋጫው ቢጠፋው የሂሳብ መዝገቡን ለማመጣጠን(ባላንስ) ለማድረግ ሁሉንም የክለቡን ተጫዋቾች ለዝውውር ገበያ አቅርቦ ገንዘብ መሰብሰብን አማራጭ ማድረጉ ተጠቁሟል። ቶፊዎቹ እስከ ሚቀጥለው ወር መጨረሻ የሂሳብ መዝገባቸውን የማመጣጠን ግዴታ አለባቸው። ይህም በርካታ ከዋክብቶቻቸውን ሳይወዱ በግድ በርካሽ ዋጋ ለመሸጥ እንዲገደዱ ሊያደርጋቸው ይችላል። 👇ሊንክ በመጫን ሙሉውን ያንብቡ https://aviewtainment.com/?p=64128 ቤተሰብ ለመሆን👇ይጫኑ https://aviewtainment.com/?page_id=59503

This is a test message

ኢትዮጵያውያን የነገሱበት የዳይመንድሊግ ምሽት ......................... የ2024 ዳይመንድሊግ 6ኛዋ መዳረሻ ከተማ የሆየችው ኦስሎ ዛሬ ምሽት ባስተናገደችው የወንዶች 5ሺ ሜትር ውድድር
ኢትዮጵያውያን የነገሱበት የዳይመንድሊግ ምሽት ......................... የ2024 ዳይመንድሊግ 6ኛዋ መዳረሻ ከተማ የሆየችው ኦስሎ ዛሬ ምሽት ባስተናገደችው የወንዶች 5ሺ ሜትር ውድድር አትሌት ሐጎስ ገ/ህይወት የርቀቱን የኢትዮጵያ ሪከርድ ሰብሯል። የርቀቱ የቀድሞው ክብረወሰን ልክ በዛሬዋ እለት ከ20 አመት በፊት 2004 ላይ በጀግናው አትሌት ቀነኒሳ በቀለ የተመዘገበ ሲሆን ሰአቱም 12:37.35 ነበር። በምሽቱ የዳይመንድሊግ ውድድር አስደናቂ ብቃት ያሳየው ሐጎስ 12:36.73 በማጠናቀቅ ሰብሮታል። ይህም ሰአት በርቀቱ በታሪክ ሁለተኛው ፈጣን ሰአት ሆኖ የተመዘገበ ሲሆን ሐጎስ የአለም ክብረወሰኑን ከዩጋንዳዊው አትሌት ጆሽዋ ቺፕቴጌ ለመረከብ ያደረገው ጥረት ለጥቂት ሳይሳካ ቀርቷል። የርቀቱ የአለም ክብረወሰን በዩጋንዳዊው አትሌት 12:35.36 በሆነ ሰአት 2020 ላይ ነበር የተመዘገበው። የኢትዮጵያውያን አትሌቶች የበላይነት በታየበት የኦስሎው ምሽት ዮሚፍ ቀጄል አስደናቂ ፉክክር አድርጎ የራሱን ምርጥ ሰአት በ12:38:95 በማስመዝገብ ሁለተኛ ሆኖ አጠናቋል። ባለፉት ጥቂት አመታት በርቀቱ ነግሰው የቆዩት ዩጋንዳውያን አትሌቶችም ኦስሎ ላይ ለኢትዮጵያውያኑ እጅ ሰጥተዋል። ዩጋንዳዊው የርቀቱ የቀድሞ የአለም ቻምፒዮን ጃኮብ ኪፕሊሞ 12:40:96 በሆነ ሰአት ሶስተኛ ሆኖ ሲያጠናቅቅ የርቀቱ የሪከርድ ባለቤትና የኦሊምፒክ ቻምፒዮኑ ጆሹዋ ቺፕቴጌ በ12:51:94 ሰአት ዘጠነኛ ሆኖ ፈፅሟል። ይህም ከሁለት ወራት በኋላ በሚካሄደው የ2024 የፓሪስ ኦሊምፒክ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች 2008 የቤጂንግ ኦሊምፒክ የቀነኒሳ ድል በኋላ የወርቅ ሜዳሊያ ተስፋ እንዲጣልባቸው አድርጓል።

ከከባድ ሀዘን እስካለመውረድ ትግል May 30, 2024 Amen ክርስቲያን አትሱን ጨምሮ 5 የክለቡን አባላት በመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ ያጣው የቱርኩ ክለብ ከሱፐርሊጉ ላለመውረድ በፅናት ተፋልሞ በመጨ
ከከባድ ሀዘን እስካለመውረድ ትግል May 30, 2024 Amen ክርስቲያን አትሱን ጨምሮ 5 የክለቡን አባላት በመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ ያጣው የቱርኩ ክለብ ከሱፐርሊጉ ላለመውረድ በፅናት ተፋልሞ በመጨረሻው ቀን ተርፏል። 👇ሊንክ በመጫን ሙሉውን ያንብቡ https://aviewtainment.com/?p=64116 ቤተሰብ ለመሆን👇ይጫኑ https://aviewtainment.com/?page_id=59503

የነጮቹ ትንሳዔ May 30, 2024 Amen ነጮቹ ወደ ፕሪሚየርሊግ ለማደግ የነበራቸው ተስፋ ከጨለመ ከቀናት በኋላ ጥሩ ዜና ሰምተዋል፡፡ በትንሽ በጀት ከሚንቀሳቀሱ ታሪካዊ ክለቦች አንዱ የሆነው ሊድ
የነጮቹ ትንሳዔ May 30, 2024 Amen ነጮቹ ወደ ፕሪሚየርሊግ ለማደግ የነበራቸው ተስፋ ከጨለመ ከቀናት በኋላ ጥሩ ዜና ሰምተዋል፡፡ በትንሽ በጀት ከሚንቀሳቀሱ ታሪካዊ ክለቦች አንዱ የሆነው ሊድስ ዛሬ የባለቤትነት አነስተኛ ድርሻው ጠንከር ያለ ገንዘብ ያለው ድርጅት እጅ ላይ ወድቋል፡፡ 👇ሊንክ በመጫን ሙሉውን ያንብቡ https://aviewtainment.com/?p=64111 ቤተሰብ ለመሆን👇ይጫኑ https://aviewtainment.com/?page_id=59503

ተማሪዎች ለምን ትምህርት ጠሉ? May 30, 2024 Amen መምህራን መንግስት ላይ ያላቸውን ቅሬታ የሚገልጹት ተማሪ ላይ ከሆነ ይሄ የእውቀት አባትነት ሳይሆን ጨለማን ማውረስ ነው፡፡ እርግጥ ነው የ
ተማሪዎች ለምን ትምህርት ጠሉ? May 30, 2024 Amen መምህራን መንግስት ላይ ያላቸውን ቅሬታ የሚገልጹት ተማሪ ላይ ከሆነ ይሄ የእውቀት አባትነት ሳይሆን ጨለማን ማውረስ ነው፡፡ እርግጥ ነው የሚከፈለው ክፍያ በቂ ነው ማለት አይደለም፡፡ በቂ አለመሆኑ ግን የተማሪዎችና የወላጆች ችግር አይደለም፤ የመንግስት ችግር ነው፡፡ ያንን ከመንግስት ጋር ነው መነጋገር፡፡ 👇ሊንክ በመጫን ሙሉውን ያንብቡ https://aviewtainment.com/?p=64105 ቤተሰብ ለመሆን👇ይጫኑ https://aviewtainment.com/?page_id=59503

ኦሎምፒያኮስ የኮንፈረንስሊግ አሸናፊ ሆነ አዮብ ኤል ካቢ በጭማሪ ሰላሳ አንድ መቶ አስራ ስድስተኛው ደቂቃ ላይ ያስቆጠራት ጎል ኦሎምፒያኮስ ተጋጣሚውን ፊዮረንቲና በመርታት የዩሮፓ ኮንፍረንስ ሊግ አሸ
ኦሎምፒያኮስ የኮንፈረንስሊግ አሸናፊ ሆነ አዮብ ኤል ካቢ በጭማሪ ሰላሳ አንድ መቶ አስራ ስድስተኛው ደቂቃ ላይ ያስቆጠራት ጎል ኦሎምፒያኮስ ተጋጣሚውን ፊዮረንቲና በመርታት የዩሮፓ ኮንፍረንስ ሊግ አሸናፊ እንዲሆን አድርጋለች። ኦሎምፒያኮስ የአውሮፓ መድረክ ዋንጫን በማንሳትም የመጀመሪያው የግሪክ ክለብ መሆን ችሏል። ፊዮረንቲና በበኩሉ ለሁለተኛ ተከታታይ የውድድር ዘመን ጊዜ ልብ በሚሰብር መልኩ የመድረኩን ዋንጫ ለማጣት ተገዷል።

እግር ኳስ ማቅ የለበሰበት ቀን ሲታወስ May 29, 2024 Amen ዘግናኝ ከሆኑ የስቴድየም አደጋዎች አንዱ ልክ በዛሬዋ እለት ከ39 አመት በፊት በሄይስል ስቴድየም የተፈጠረ ነበር። በዚያ ክስተት
እግር ኳስ ማቅ የለበሰበት ቀን ሲታወስ May 29, 2024 Amen ዘግናኝ ከሆኑ የስቴድየም አደጋዎች አንዱ ልክ በዛሬዋ እለት ከ39 አመት በፊት በሄይስል ስቴድየም የተፈጠረ ነበር። በዚያ ክስተት 39 ሰዎች ህይወታቸውን ሲያጡ 6መቶ የሚሆኑ ተጎድተዋል። 👇ሊንክ በመጫን ሙሉውን ያንብቡ https://aviewtainment.com/?p=64099 ቤተሰብ ለመሆን👇ይጫኑ https://aviewtainment.com/?page_id=59503

በጭቅጭቅ የሚቋጨው የፔዤና ምባፔ ጉዳይ May 29, 2024 Amen ምባፔ የፓሪሱን ክለብ መልቀቅ እንደሚፈልግ ካሳወቀ ጀምሮ ከክለቡ ጋር በተለይም ከፕሬዘዳንቱ ናስር አል ከሊፊ ጋር ያለው ግንኙነት
በጭቅጭቅ የሚቋጨው የፔዤና ምባፔ ጉዳይ May 29, 2024 Amen ምባፔ የፓሪሱን ክለብ መልቀቅ እንደሚፈልግ ካሳወቀ ጀምሮ ከክለቡ ጋር በተለይም ከፕሬዘዳንቱ ናስር አል ከሊፊ ጋር ያለው ግንኙነት ጤናማ እንዳልሆነ በተለያየ አጋጣሚ ታይቷል። የመጪው ዘመን ኮከብ በነፃ ዝውውር ክለቡን መልቀቁ በፕሬዘዳንቱ ዘንድ የተወደደ አይመስልም። 👇ሊንክ በመጫን ሙሉውን ያንብቡ https://aviewtainment.com/?p=64092 ቤተሰብ ለመሆን👇ይጫኑ https://aviewtainment.com/?page_id=59503

የላሊጋው የአመቱ ከዋክብት May 29, 2024 Amen በውድድር አመቱ የሪያል ማድሪድ አስደናቂ የላሊጋና የቻምፒዮንስሊግ ጉዞ ጎልተው የሚጠቀሱት አንጋፋው አሰልጣኝ ካርሎ አንቸሎቲ የአመቱ ምርጥ አሰ
የላሊጋው የአመቱ ከዋክብት May 29, 2024 Amen በውድድር አመቱ የሪያል ማድሪድ አስደናቂ የላሊጋና የቻምፒዮንስሊግ ጉዞ ጎልተው የሚጠቀሱት አንጋፋው አሰልጣኝ ካርሎ አንቸሎቲ የአመቱ ምርጥ አሰልጣኝ ተብለው አለመመረጣቸው ሙግት አስነስቷል። 👇ሊንክ በመጫን ሙሉውን ያንብቡ https://aviewtainment.com/?p=64088 ቤተሰብ ለመሆን👇ይጫኑ https://aviewtainment.com/?page_id=59503

የ5ሺ ሜትር ፈርጦች አጓጊ የዳይመንድሊግ ፍልሚያ May 29, 2024 Amen በርካታ ኢትዮጵያውያን ልምድ ያላቸውና ወጣት አትሌቶች በርቀቱ ከእጃቸው የወጣውን የበላይነት ለማስመለስ ባለፉት ጥቂት አመ
የ5ሺ ሜትር ፈርጦች አጓጊ የዳይመንድሊግ ፍልሚያ May 29, 2024 Amen በርካታ ኢትዮጵያውያን ልምድ ያላቸውና ወጣት አትሌቶች በርቀቱ ከእጃቸው የወጣውን የበላይነት ለማስመለስ ባለፉት ጥቂት አመታት ያደረጉት ጥረት ባይሳካም በዘንድሮው አመት የተሻለ ጥንካሬ እያሳዩ ይገኛሉ። 👇ሊንክ በመጫን ሙሉውን ያንብቡ https://aviewtainment.com/?p=64083 ቤተሰብ ለመሆን👇ይጫኑ https://aviewtainment.com/?page_id=59503