en
Feedback
AVT - aviewtainment

AVT - aviewtainment

Open in Telegram

📈 Analytical overview of Telegram channel AVT - aviewtainment

Channel AVT - aviewtainment (@aviewtainment) in the Amharic language segment is an active participant. Currently, the community unites 12 687 subscribers, ranking 4 929 in the Sports category and 2 257 in the Ethiopia region.

📊 Audience metrics and dynamics

Since its creation on невідомо, the project has demonstrated rapid growth, gathering an audience of 12 687 subscribers.

According to the latest data from 25 December, 2024, the channel demonstrates stable activity. Although there has been a change in the number of participants by -237 over the last 30 days and by 0 over the last 24 hours, overall reach remains high.

  • Verification status: Not verified
  • Engagement rate (ER): The average audience engagement rate is 0%. Within the first 24 hours after publication, content typically collects N/A% reactions from the total number of subscribers.
  • Post reach: On average, each post receives 0 views. Within the first day, a publication typically gains 0 views.
  • Reactions and interaction: The audience actively supports content: the average number of reactions per post is 0.

📝 Description and content policy

Channel description not provided.

Thanks to the high frequency of updates (latest data received on 26 December, 2024), the channel maintains relevance and a high level of publication reach. Analytics show that the audience actively interacts with content, making it an important point of influence in the Sports category.

12 687
Subscribers
No data24 hours
-397 days
-23730 days
Posts Archive
አርሰናል በሞት ያጣው የቀድሞ ኮከብ ................................. አርሰናል የቀድሞ ኮከብ አጥቂው ኬቪን ካምፕቤልን በሞት አጥቷል። የቀድሞው የመድፈኞቹ፣ የኤቨርተንና ኖቲንግሃ
+3
አርሰናል በሞት ያጣው የቀድሞ ኮከብ ................................. አርሰናል የቀድሞ ኮከብ አጥቂው ኬቪን ካምፕቤልን በሞት አጥቷል። የቀድሞው የመድፈኞቹ፣ የኤቨርተንና ኖቲንግሃም ፎረስት ታሪካዊ ተጫዋች በህክምና ሲረዳ ቆይቶ ዛሬ በ54 አመቱ ህይወቱ ማለፉ ታውቋል። ከእግር ኳስ ህይወቱ በኋላ በኮሜንታተርነት ሲሰራ የቆየው ካምፕቤል ህይወቱ ከማለፉ አስቀድሞ ለሁለት ሳምንታት በሆስፒታል ህክምና ሲደረግለት መቆየቱን የእንግሊዝ ሚዲያዎች ዘግበዋል። አርሰናል የቀዶሞ ኮከቡን ህልፈተ ህይወት ተከትሎ በማህበራዊ ሚዲያው ባወጣው የሀዘን መግለጫ " የቀድሞ ኮከባችን በአጭር ጊዜ ህመም ህይወቱ ማለፉን በእጅጉ አስደንግጦናል፣ ኬቪን በክለቡ በሁሉም ዘንድ ተወዳጅ ነበር" ብሏል። ካምፕቤል ትውልዱ በለንደን ከተማ ነው። ለመጀመሪያ ጊዜ በትልቅ ደረጃ መጫወት የጀመረውም ለሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል 1998 ላይ ነበር። ከመድፈኞቹ ጋር ሁለት የውሰት አመታትን ጨምሮ ሰባት አመታትን አሳልፏል። በዚህም ቆይታው 1990-91 ላይ የመጀመሪያ ዲቪዚዮን ዋንጫን አርሰናል ሲያነሳ የቡድኑ አካል ነበር። መድፈኞቹ 1992-93 የኤፍ ኤ ካፕ ዋንጫ፣ 1993-94 ዩሮፒያን ካፕ አሸናፊዎች ዋንጫን ሲያነሱም ካምፕቤል የቡድኑ ቁልፍ ተጫዋች እንደነበር ይታወሳል። ካምፕቤል ከአርሰናል ጋር ከተለያየ በኋላ 1995 ላይ ወደ ኖቲንግሀም ፎረስት ነበር ያቀናው። ሦስት አመታትን ካሳለፈ በኋላም 1999 ላይ ወደ ኤቨርተን ተጉዟል። በጉዲሰን ፓርክ ባሳለፈባቸው ስድስት አመታትም በፕሪሚየርሊጉ 45 ግቦችን ከመረብ አሳርፏል። ይህም በፕሪሚየርሊጉ ለኤቨርተን በርካታ ግብ ያስቆጠረ አምስተኛው ተጫዋች ያደረገው ሲሆን ኤቨርተንን በአምበልነት መምራት የቻለ የመጀመሪያው ጥቁር ተጫዋች ሆኖም ይታወሳል።

አርሰናል በሞት ያጣው የቀድሞ ኮከብ June 15, 2024 Amen 👇ሊንክ በመጫን ሙሉውን ያንብቡ https://aviewtainment.com/?p=64296 ቤተሰብ ለመሆን👇ይጫኑ https://aviewtainment.com/?page_id=59503

የአውሮፓ ዋንጫና የጀርመን ትልቁ ፈተና June 14, 2024 Amen ከእግር ኳስ ተመልካቾች የስቴድየም ውስጥ መጠነኛ ፀብ እስከ ነውጠኛ ደጋፊዎች የለየለት አምባጓሮ እንዲሁም የሽብር ስጋት ያንዣበበ
የአውሮፓ ዋንጫና የጀርመን ትልቁ ፈተና June 14, 2024 Amen ከእግር ኳስ ተመልካቾች የስቴድየም ውስጥ መጠነኛ ፀብ እስከ ነውጠኛ ደጋፊዎች የለየለት አምባጓሮ እንዲሁም የሽብር ስጋት ያንዣበበት ይህ የአውሮፓ ዋንጫ በብዙ ምክኒያቶች ከፀጥታ ጋር በተያያዘ ውጥረት ነግሶበታል። ለዚህም ወቅታዊ የአለም የፖለቲካ ትኩሳቶች፣ ታሪክና ሌሎችም ምክኒያቶች ሰበብ ሆነዋል። 👇ሊንክ በመጫን ሙሉውን ያንብቡ https://aviewtainment.com/?p=64284 ቤተሰብ ለመሆን👇ይጫኑ https://aviewtainment.com/?page_id=59503

የአውሮፓ ዋንጫ አንዳንድ ነጥቦች… June 14, 2024 Amen 👇ሊንክ በመጫን ሙሉውን ያንብቡ https://aviewtainment.com/?p=64271 ቤተሰብ ለመሆን👇ይጫኑ https://aviewtainment.com/?page_id=59503

የአውሮፓ ዋንጫ አንዳንድ ነጥቦች… June 13, 2024 Amen በጉጉት የሚጠበቀው የአውሮፓ ዋንጫ ነገ ምሽት በአዘጋጇ ጀርመንና ስኮትላንድ የመክፈቻ ጨዋታ ይጀመራል። ወርቃማ ስብስብ ከያዘችው እንግ
የአውሮፓ ዋንጫ አንዳንድ ነጥቦች… June 13, 2024 Amen በጉጉት የሚጠበቀው የአውሮፓ ዋንጫ ነገ ምሽት በአዘጋጇ ጀርመንና ስኮትላንድ የመክፈቻ ጨዋታ ይጀመራል። ወርቃማ ስብስብ ከያዘችው እንግሊዝ እስከ አለም ዋንጫ የፍፃሜ ተፋላሚዋ ፈረንሳይና የክርስቲያኖ ሮናልዶ ፖርቹጋል የውድድሩ ድምቀቶች ይሆናሉ። 👇ሊንክ በመጫን ሙሉውን ያንብቡ https://aviewtainment.com/?p=64274 ቤተሰብ ለመሆን👇ይጫኑ https://aviewtainment.com/?page_id=59503

ፖርቹጋላዊው ኮከብ ክርስቲያኖ ሮናልዶ አገሩ ዛሬ በአቋም መለኪያ ጨዋታ አየርላንድን 3ለ0 ስትረታ በግራ እግሩ ሁለት አስደናቂ ግቦችን በ49' እና 60' ደቂቃ ላይ በማስቆጠር አነጋጋሪነቱ ቀጥሏል።
ፖርቹጋላዊው ኮከብ ክርስቲያኖ ሮናልዶ አገሩ ዛሬ በአቋም መለኪያ ጨዋታ አየርላንድን 3ለ0 ስትረታ በግራ እግሩ ሁለት አስደናቂ ግቦችን በ49' እና 60' ደቂቃ ላይ በማስቆጠር አነጋጋሪነቱ ቀጥሏል። የ39 አመቱ የግብ ማሽን በእግር ኳስ ህይወቱ 66ኛ፣ ለብሔራዊ ቡድኑ ደግሞ 11ኛ ሐትሪኩን ለመስራት ተቃርቦ ነበር። በቅጣት ምት ከርቀት የተኮሳትን ኳስ የግቡ አግዳሚ መልሶበታል። ያምሆኖ ከዛሬው ጨዋታ በፊት በ204 ጨዋታ ለብሔራዊ ቡድን 128 ግቦችን በማስቆጠር የአለምን ሪከርድ የያዘው የእግር ኳስ ፈርጥ ይህን ሪከርዱን ከአውሮፓ ዋንጫው አስቀድሞ ወደ 130 አሳድጎታል። ሮናልዶ በአጠቃላይ የእግር ኳስ ህይወቱ 900ኛ ግቡ ላይ ለመድረስም አምስት ግቦች ብቻ ይቀሩታል። ይህንን በዘንድሮው የአውሮፓ ዋንጫ ማሳካት ይችል ይሆን!?

ሳሙኤል ኤቶ:-🗣‼️ " ሀብታም ባለቤቴን ሳገኛት ድሃ ነበርኩ። ከባለቤቴ ጋር ስተዋወቅ አሁንም በፈረንሳይ አማተር እግር ኳስ ተጫዋች ነበርኩ። ኖንትስ ሊወስደኝ ፈቃደኛ አልሆነም ፣ ግን ባለቤቴ ሁል
ሳሙኤል ኤቶ:-🗣‼️ " ሀብታም ባለቤቴን ሳገኛት ድሃ ነበርኩ። ከባለቤቴ ጋር ስተዋወቅ አሁንም በፈረንሳይ አማተር እግር ኳስ ተጫዋች ነበርኩ። ኖንትስ ሊወስደኝ ፈቃደኛ አልሆነም ፣ ግን ባለቤቴ ሁል ጊዜ በእኔ እምነት ነበራት። እኔ ትንሽ የካሜሩንያን የንግግር ዘዬ አለቀቀኝም፣ እሷ በኖንትስ የፀጉር ቤት ነበራት። ዛሬ እሷ በአፍሪካ አህጉር ውስጥ በጣም የተከበረ የእግር ኳስ ተጫዋች ሚስት ነች፣ እኔ ደግሞ በዓለም ላይ በጣም ታጋሿ ሴት ባል ነኝ። ሕይወት የአጭር ርቀት ሩጫ ሳትሆን አገር አቋራጭ ሩጫ ናት!"

የሮናልዶን ልምምድ ለማየት 8መቶ ዩሮ! June 11, 2024 Amen ሮናልዶ ከብሔራዊ ቡድኑ ጋር አርብ ለሚያደርገው ልምምድ ለተመልካች የተዘጋጁ ስድስት ሺ ነፃ ትኬቶች በተወሰኑ መቶ ዩሮዎች በደቂቃ
የሮናልዶን ልምምድ ለማየት 8መቶ ዩሮ! June 11, 2024 Amen ሮናልዶ ከብሔራዊ ቡድኑ ጋር አርብ ለሚያደርገው ልምምድ ለተመልካች የተዘጋጁ ስድስት ሺ ነፃ ትኬቶች በተወሰኑ መቶ ዩሮዎች በደቂቃ ውስጥ ተሸጠው ተጠናቀዋል። እስከ 4መቶ ዩሮ ድረስ ለሽያጭ የቀረቡ በርካታ ትኬቶች ደግሞ kleinanzeigen በተባለ የጀርመን ድረ ገፅ በኩል እስከ ስምንት መቶ ዩሮ እየተቸበቸቡ እንደሚገኙ ተጠቁሟል። 👇ሊንክ በመጫን ሙሉውን ያንብቡ https://aviewtainment.com/?p=64267 ቤተሰብ ለመሆን👇ይጫኑ https://aviewtainment.com/?page_id=59503

የንስሮቹ ጥቁር ሳምንት June 11, 2024 Amen የናይጄሪያ እግር ኳስ በታሪኩ ሀዘን የተቀመጠበት ወቅት ቢኖር ይህ ሳምንት አንዱ ነው። ምክኒያቱም ሁለት የእግር ኳስ ጀግኖቹን ከስምንት አመት በ
የንስሮቹ ጥቁር ሳምንት June 11, 2024 Amen የናይጄሪያ እግር ኳስ በታሪኩ ሀዘን የተቀመጠበት ወቅት ቢኖር ይህ ሳምንት አንዱ ነው። ምክኒያቱም ሁለት የእግር ኳስ ጀግኖቹን ከስምንት አመት በፊት በሦስት ቀን ልዩነት በሞት ያጣበት ጊዜ ነውና። 👇ሊንክ በመጫን ሙሉውን ያንብቡ https://aviewtainment.com/?p=64263 ቤተሰብ ለመሆን👇ይጫኑ https://aviewtainment.com/?page_id=59503

ፈርናንዶ ቶሬስ በአሰልጣኝነት June 11, 2024 Amen አሁን ላይ የ40 ዓመት ጎልማሳ የሆነው ቶሬስ ቀደም ሲል የአትሌትኮ ማድሪድን ከ19 ዓመት በታች ቡድን ሲያሰለጥን የቆየ ሲሆን፣ አሁን ከፍ
ፈርናንዶ ቶሬስ በአሰልጣኝነት June 11, 2024 Amen አሁን ላይ የ40 ዓመት ጎልማሳ የሆነው ቶሬስ ቀደም ሲል የአትሌትኮ ማድሪድን ከ19 ዓመት በታች ቡድን ሲያሰለጥን የቆየ ሲሆን፣ አሁን ከፍ ብሎ የልጅነት ክለቡን ቢ ቡድን በዋና አሰልጣኝነት እንዲመራ ተሹሟል። 👇ሊንክ በመጫን ሙሉውን ያንብቡ https://aviewtainment.com/?p=64258 ቤተሰብ ለመሆን👇ይጫኑ https://aviewtainment.com/?page_id=59503

የማይረሳው የሻባላላ ግብና የፒተር ዱሪ ኮመንተሪ ........................................... "ሻባላላ ጎልልል!፣ ባፋና ባፋና ጎልል!፣ ደቡብ አፍሪካ ጎልልል!፣ የመላው አፍ
+1
የማይረሳው የሻባላላ ግብና የፒተር ዱሪ ኮመንተሪ ........................................... "ሻባላላ ጎልልል!፣ ባፋና ባፋና ጎልል!፣ ደቡብ አፍሪካ ጎልልል!፣ የመላው አፍሪካ ጎልልል...!" ይህ እውቁና ተወዳጁ የእግር ኳስ ኮሜንታተር ፒተር ዱሪ ከሚታወስባቸው አስደናቂ ታሪኮች አንዱ ሆኖ ይታወሳል። ከአስራ አራት አመታት በፊት ልክ በዛሬዋ እለት ጁን 11-2010 አፍሪካ ለመጀመሪያ ጊዜ በደቡብ አፍሪካ አማካኝነት ባዘጋጀችው የአለም ዋንጫ አስተናጋጇ አገር የመክፈቻ ጨዋታዋ ላይ የመጀመሪያዋን ግብ ኮከቧ ሻባላላ ከመረብ ማሳረፉን ተከትሎ ነበር ፒተር ዱሪ በማይረሳ ኮመንተሪው የሻባላላን ግብ የገለፀው። በዚያ ታሪካዊ የአለም ዋንጫ ደቡብ አፍሪካ በወቅቱ ጠንካራ ከነበረችው ሜክሲኮ ጋር 1ለ1 በተለያየችበት ፍልሚያ በሻባላላ አማካኝነት ታሪካዊቷን የመጀመሪያ ግብ ብታስቆጥርም በአለም ዋንጫ ከምድብ ጨዋታ የተሰናበተች የመጀመሪያ አዘጋጅ አገር ከመሆን አልዳነችም። ሁለተኛውን የምድብ ጨዋታ በዩራጓይ 3ለ0 ተሸንፋለች። ባፋናባፋናዎች የመጨረሻውን የምድብ ጨዋታ ፈረንሳይን 2ለ1 አሸንፈው ከውድድሩ ውጪ መሆናቸው ቢያስቆጭም አፍሪካውያን የጋና ብሔራዊ ቡድን እስከ ሩብ ፍፃሜ በተጓዘበት መንገድ ተክሰዋል። ሉዊስ ሱዋሬዝ በመጨረሻ ሰአት በእጁ ያወጣው ጎልና ዩራጓይን የታደገበት ክስተት እሱን ተከትሎም አሳሞአ ጂያን ያመከናት ፍፁም ቅጣት ምት በዚያ የአለም ዋንጫ ከማይረሱ ታሪካዊ ቅፅበቶች ዋነኞቹ ናቸው።

አወዛጋቢው የካሜሩናዊ ተጫዋች የእድሜ ጉዳይ June 11, 2024 Amen እድሜህ 42 ነው በሚል የተከሰሰው የቀድሞ የላዚዮ ተጫዋች አሁን ላይ 27 አመቱ ነው ተብሎ በመጫወት ላይ መገኘቱ ብዙዎችን
አወዛጋቢው የካሜሩናዊ ተጫዋች የእድሜ ጉዳይ June 11, 2024 Amen እድሜህ 42 ነው በሚል የተከሰሰው የቀድሞ የላዚዮ ተጫዋች አሁን ላይ 27 አመቱ ነው ተብሎ በመጫወት ላይ መገኘቱ ብዙዎችን እያነጋገረ ይገኛል። 👇ሊንክ በመጫን ሙሉውን ያንብቡ https://aviewtainment.com/?p=64252 ቤተሰብ ለመሆን👇ይጫኑ https://aviewtainment.com/?page_id=59503

የሶስት አገራት የአለም ዋንጫ ኮከብ! June 10, 2024 Amen በሶስት አለም ዋንጫዎች ለሶስት አገራት በመጫወት ብቸኛው ባለታሪክ ነው። ይህ የቀድሞ የኢንተር ሚላን ኮከብ በ1998 አለም ዋንጫ
የሶስት አገራት የአለም ዋንጫ ኮከብ! June 10, 2024 Amen በሶስት አለም ዋንጫዎች ለሶስት አገራት በመጫወት ብቸኛው ባለታሪክ ነው። ይህ የቀድሞ የኢንተር ሚላን ኮከብ በ1998 አለም ዋንጫ ለዩጎዝላቪያ ተጫውቷል፣ 2006 ደግሞ ለሰርቢያና ሞንቴኔግሮ እንዲሁም በ2010ሩ የአለም ዋንጫ ለሰርቢያ በመሰለፍ ልዩ ታሪክ አለው። 👇ሊንክ በመጫን ሙሉውን ያንብቡ https://aviewtainment.com/?p=64246 ቤተሰብ ለመሆን👇ይጫኑ https://aviewtainment.com/?page_id=59503

ሴፕ ብላተርና የዛሬዋ እለት June 8, 2024 Amen ብላተር በፕሬዘዳንታዊ ምርጫው ስዊድናዊ ተፎካካሪያቸው ሌናርት ጆሃንሰንን አሸንፈው ነበር የፊፋን መንበር የተቆናጠጡት። ከዚያም ጊዜ አንስቶ ነ
ሴፕ ብላተርና የዛሬዋ እለት June 8, 2024 Amen ብላተር በፕሬዘዳንታዊ ምርጫው ስዊድናዊ ተፎካካሪያቸው ሌናርት ጆሃንሰንን አሸንፈው ነበር የፊፋን መንበር የተቆናጠጡት። ከዚያም ጊዜ አንስቶ ነው ለአስራ ስምንት አመታት ፊፋን በመሩበት ዘመናት ከተለያዩ የሙስና ቅሌቶች ጋር ዛሬም ድረስ ስማቸው የሚነሳው። 👇ሊንክ በመጫን ሙሉውን ያንብቡ https://aviewtainment.com/?p=64240 ቤተሰብ ለመሆን👇ይጫኑ https://aviewtainment.com/?page_id=59503

ሲቲ የኦርቴጋን ውል አራዝሟል ....................... ማንችስተር ሲቲ የጀርመናዊውን ግብ ጠባቂ ስቴፈን ኦርቴጋን ኮንትራት ማራዘሙን ይፋ አድርጓል። ኦርቴጋ በኢትሃድ እስከ 2026 የሚያ
ሲቲ የኦርቴጋን ውል አራዝሟል ....................... ማንችስተር ሲቲ የጀርመናዊውን ግብ ጠባቂ ስቴፈን ኦርቴጋን ኮንትራት ማራዘሙን ይፋ አድርጓል። ኦርቴጋ በኢትሃድ እስከ 2026 የሚያቆየውን የአንድ አመት ተጨማሪ ኮንትራት መፈረሙን ቢቢሲ ስፖርት ዘግቧል፡፡ በፕሪምየር ሊጉ ማንችስተር ሲቲ ዋንጫውን ለማንሳት በነበረው ግስጋሴ በተለይም በቶትንሀሙ ወሳኝ ጨዋታ ኤደርሰን መጎዳቱን ተክተሎ ተቀይሮ ወደ ሜዳ የገባዉ ኦርቴጋ የሶን ሂንግ ሚኒን ጎል ያዳነበት መንገድ አስደናቂ እንደነበር አይዘነጋም፡፡ "ማንችስተር ሲቲ ውስጥ ለተጨማሪ አመት በመቆየቴ ተደስቻለሁ ፤ ይህ ክለብ ተጨዋቾች ምርጥ ለመሆን የሚያስፈልጋቸውን ነገር ማቅረብ የሚችል ነው።" በማለት ኦርቴጋ ኮንትራቱን ከፈረመ በኋላተናግሯል፡፡ ከሁለት አመት በፊት ከአርሜኒያ ቢየልፊልድ የኢታዱን ክለብ የተቀላቀለው ግብ ጠባቂ በተጠናቀቀው የውድድር አመት በፕሪምየር ሊጉ በ9 ጨዋታዎች ተሰልፎ ሲጫወት በኤፍ ኤ ካፑ ፍጻሜም ተሰልፏል፡፡ ከክለቡ ጋርም ሁለት የሊግ ፣ አንድ የቻምፒየንስ ሊግ እና አንድ የኤፍ ካፕ ዋንጫዎችን አሳክቷል።

የፍልስጤም የአለም ዋንጫ ግስጋሴ June 8, 2024 Amen በምድብ ዘጠኝ ከአውስትራሊያ ሊባኖስ እና ባንግላዲሽ ጋር የተደለደለው የፍልስጤም ቡድን ከሊባኖስ ጋር በዶሃ ጃስሚን ቢን ሃማድ ስታዲየም
የፍልስጤም የአለም ዋንጫ ግስጋሴ June 8, 2024 Amen በምድብ ዘጠኝ ከአውስትራሊያ ሊባኖስ እና ባንግላዲሽ ጋር የተደለደለው የፍልስጤም ቡድን ከሊባኖስ ጋር በዶሃ ጃስሚን ቢን ሃማድ ስታዲየም ያደረገው ጨዋታ ያለ ጎል ማጠናቀቁን ተከትሎ ለመጨረሻው ዙር ማጣሪያ ማለፉን አረጋግጧል። 👇ሊንክ በመጫን ሙሉውን ያንብቡ https://aviewtainment.com/?p=64236 ቤተሰብ ለመሆን👇ይጫኑ https://aviewtainment.com/?page_id=59503

አዲሱ ሰማያዊ ኮከብ June 7, 2024 Amen የ26 ዓመቱ አዳራቢዮ የክለቡ ከፍተኛ ተከፋይ እንዲሆን ፉልሃም ያቀረበለትን የውል ማራዘሚያ ጥያቄ ውድቅ አድርጎ ሰማያዊዎቹን መርጧል። 👇ሊንክ በመጫ
አዲሱ ሰማያዊ ኮከብ June 7, 2024 Amen የ26 ዓመቱ አዳራቢዮ የክለቡ ከፍተኛ ተከፋይ እንዲሆን ፉልሃም ያቀረበለትን የውል ማራዘሚያ ጥያቄ ውድቅ አድርጎ ሰማያዊዎቹን መርጧል። 👇ሊንክ በመጫን ሙሉውን ያንብቡ https://aviewtainment.com/?p=64230 ቤተሰብ ለመሆን👇ይጫኑ https://aviewtainment.com/?page_id=59503

ያልተቀደደው የፖግባ ኮንትራትና ጫማ የመስቀል ጉዳይ June 7, 2024 Amen ፈረንሳዊው የአማካኝ ስፍራ ተጫዋች ፖል ፖግባ በአበረታች ንጥረ ነገር (ዶፒንግ) ተጠቃሚነት ከእግር ኳስ ለአራት አመት
ያልተቀደደው የፖግባ ኮንትራትና ጫማ የመስቀል ጉዳይ June 7, 2024 Amen ፈረንሳዊው የአማካኝ ስፍራ ተጫዋች ፖል ፖግባ በአበረታች ንጥረ ነገር (ዶፒንግ) ተጠቃሚነት ከእግር ኳስ ለአራት አመት ከታገደ ወራት ተቆጥረዋል። ይሁን እንጂ ከክለቡ ጁቬንቱስ ጋር ያለው ኮንትራት አሁንም ድረስ አልተቀደደም። 👇ሊንክ በመጫን ሙሉውን ያንብቡ https://aviewtainment.com/?p=64226 ቤተሰብ ለመሆን👇ይጫኑ https://aviewtainment.com/?page_id=59503

ታማኙ ቀበሮ ኮንትራቱን አራዝሟል .............................. በሌስተር ሲቲ ውጣ ውረድ ከክለቡ ጋር ያልተለየው እንግሊዛዊ አጥቂ ጄሚ ቫርዲ ዛሬም በክለቡ ታማኙ ቀበሮ ሆኖ ቀጥሏል
ታማኙ ቀበሮ ኮንትራቱን አራዝሟል .............................. በሌስተር ሲቲ ውጣ ውረድ ከክለቡ ጋር ያልተለየው እንግሊዛዊ አጥቂ ጄሚ ቫርዲ ዛሬም በክለቡ ታማኙ ቀበሮ ሆኖ ቀጥሏል። የ37 አመቱ ኮከብ ቀበሮዎቹ የፕሪሚየርሊጉን ዋንጫ በታሪካቸው ለመጀመሪያ ጊዜ ሲያነሱ ቁልፍ ተጫዋቻቸው ነበር። በድንቅ አቋም ላይ በነበረበት ወቅት በርካታ ታላላቅ ክለቦች ፈላጊዎቹ ሆነው ቢመጡም እሱ በኪንግ ፓወር መቆየትን መርጧል። አምና ክለቡ ወደ ቻምፒዮንሺፕ ሲወርድም ቫርዲ አብሮ ወርዶ ታማኝነቱን እስከ ጥግ አሳይቷል። ሌስተር ከአመት በኋላ ወደ ፕሪሚየርሊጉ ዘንድሮ ሲመለስም ቫርዲ የቀበሮዎቹ አካል ነው። የ37 አመቱ የፊት መስመር ተጨዋች ዛሬ በሌስተር ሲቲ የሚያቆየውን የ1 አመት ኮንትራት ተፈራርሟል።

ራሽፎርድና የሮልስ ሮይሱ መዘዝ June 7, 2024 Amen ራሽፎርድ በቅንጡ መኪናው ከፍጥነት በላይ ማሽከርከሩን አምኗል ሲሉ የፍርድ ቤቱ ባለስልጣናት ዛሬ አረጋግጠዋል። በዚህም ከባድ ቅጣት እንዲሁ
ራሽፎርድና የሮልስ ሮይሱ መዘዝ June 7, 2024 Amen ራሽፎርድ በቅንጡ መኪናው ከፍጥነት በላይ ማሽከርከሩን አምኗል ሲሉ የፍርድ ቤቱ ባለስልጣናት ዛሬ አረጋግጠዋል። በዚህም ከባድ ቅጣት እንዲሁም እስከወዲያኛው መኪና እንዳያሽከረክር ሊታገድ እንደሚችል ዘገባዎች አመልክተዋል። 👇ሊንክ በመጫን ሙሉውን ያንብቡ https://aviewtainment.com/?p=64221 ቤተሰብ ለመሆን👇ይጫኑ https://aviewtainment.com/?page_id=59503