cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ሥለ ፍቅር እና ሥነ-ግጥም

"ሁሉም ሠው የራሱ የሆነ አመለካከት እና ችሎታ አለው ማንም ሠው ምንም የመሆን መብት አለው" ❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤ ፈታ በሉልኝ።ሀሣብ አስተያየት ካለ ከታች ባለውሊንክ በውስጥ አውሩኝ @Jovaniye ❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤

Show more
Finland2 397Amharic9 686The category is not specified
Advertising posts
243
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

😍😍😍😍😍😍😍😍😍😍 ዋ ጌታዬ የኔ ጌታ ጌታዬዋ ፤ በመስቀልህ ባርከኝ ፤ በስልጣንህ ባርከኝ ፤ እድሌንም ባርከው ፤ ተመለጠ እራሴ እየቆጨኝ ባከው ። 😔😔😔😔😔😔😔😔😔😔 ጆን የእናቱ ልጅ 😀😀😀😀😀😀😀😀😀😀
Show all...
😍😍😍😍😍😍😍😍 ............................................... #ውዴ ............................................... ተይ አንወቃቀስ አንግባ ኩነኔ ፤ ................................................ ትርፍ ቃል ለምንሽ ትርፍ ቃል ለምኔ። ................................................
Show all...
Photo unavailableShow in Telegram
🔰 BAGA NAGAAN DHUFTAN 🔰 Itiyoo-Teleekom tamsaasa telegramaa sa'aati guutuu afaan oromoodhan jalqabuu ilaalchisee hordoftoota horachuuf badhaasa qopheessera. Linkii armaan gadii fayyadamuudhan galmaa'uu keessaniif qarshii 1000 ni badhaafamtu. Namoota 30 yemmuu affeertan immoo dabalataan qarshii 3000, tokkoon tokkoon namoota affeertanif qarshii 100 badhaafamtu. Liinkii affeerraa ·٠•●♥️ Jovaniye ♥️●•٠·. 🔽 https://t.me/Ethiotelecom_Afaan_Oromoo_bot?start=r0825903657 Liinkii affeerraa keessaani argachuudhaaf liinkii affeerraa ·٠•●♥️ Jovaniye ♥️●•٠·tiin galmaa'aa. JOIN | ETHIOTELECOM - AFAAN OROMOO
Show all...
ገደል ግቢ በሏት... ይህችን ቃል ንገሯት... ተፈርዶብኝ እንጅ መለየት ተስኖኝ ጥሬውን ከብስል ሃገሬ ምድር ላይ እሷ ብቻ ቆንጆ የቀረች ይመስል ዞር ባለች ቁጥር አትራቂኝ እያልኩኝ የምለማመጣት ልቻለው ብየ እንጅ ምሳሌ ከመሆን አፍቅሮ ከማጣት ገደል ግቢ በሏት። ይኸው ደግሞ ዛሬ ይኸው ደግሞ ዛሬ ገላዋን በሙሉ አወደችው ሎሽን ጸጉሯን አጎፈረች ደመቀች በሽንሽን ከንፈሯን ምን ይሆን ደግሞ የቀባችው የእጇን አይበሉባ በቄንጥ አቆናጥራ ሰዓቷን አየችው ገና ነው መሰለኝ ጊዜን ታዘበችው 'ባፏ ሸብረክ አርጋ እየገረመመች መንቀር አለችና እግሯን አመሳቅላ መስታውት ፊት ቆመች ደግሞ ፈገግ አለች ጥርሷ ይርገፍና ማርያምን ታምራለች። መከርኳት በወዳጅ ዘከርኳት በዘመድ ቀለበት አይጠቅማት አሰርኳት በገመድ ገደል ግቢ በሏት ልቧን ከጋረደው ወዳጅ ከከለላት ስውር አይነ ጥላ እንዲህ ካማረባት መሄድ ከጀመረች አፍቃሪ ሰው ጥላ ልክ እንደገላዋ ይለስልስ መንገዱ ፍጹም አይጎርብጣት አየሩ በሙሉ ፍክት ይበልላት እንደ ጥርሷ ንጣት እያልኩኝ መርቄ እያልኩኝ መርቄ እንደገጣሚ ቃል ልቤን አልጀነጅን የታባቷንና በጸበል ካልወጣች ትረሳለች በጅን። የታባቷንና እንዲህ የሚያምርባት የትናቷንና እንዲህ ሚደምቅባት ልንገራት እስከጥግ ልርገማት የልኳን እንዲህ ምታደርገኝ ጠባቂዋንና ተማምና አድል መልኳን የታባቷንና እንዲህ የሚያምርባት የትናቷንና እንዲህ ሚደምቅባት እስከመቸ ድረስ እስከመቸ ድረስ ስቀባ እኖራለሁ ጉድፍ ልቧን ስኩል ገደል ግቢ በሏት እኔ ገደል ስር ነኝ ድንገት ከወደቀች በቆሻሻው በኩል።
Show all...
በስማችሁ ግጥም እንድፅፍ የምትፈልጉ '' comment '' ላይ ስማቹን አስቀምጡ ። Join us @Jovaniyee Like&share
Show all...
😍😍😍😍😍😍😍😍😍😍 አንቺ የጀግኖች መቅደስ ታሪክን አዋቂ፤ የነገስታትን ደም በላይሽ አርቃቂ፤ በከፍታሽ አድማሽ ባለሽ ግርማ ሞገስ ፤ ታሪክ አመሥጥረሽ ትውልድ የሚያኮራ ጀግንነት የሚያላብስ፤ ፈለገ ብዙ የቴዎድሮስ ማረፊያ ጥይት የጠጣብሽ፤ 🙄 ስለ ሀገር ሞቶ መኖር ያስተማረሽ ፤ ❤ አትሞ ያኖረብሽ የታሪክ መሀላ ፧7, አንቺው ነሽ መቅደላ ።😍 ❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤
Show all...
አምሳለ ቴዎድሮስ አናተ ተራራ ልብሽ አምሳለ ጥይት ጠጡኝ ባይ ምትጣራ
Show all...
በእግሬም አልኳትን መቅደስን ፍለጋ 🚶‍♂🚶 አይኔም አይጓዝም ሰውም አላወጋ 🙈🙊 የናፍቆቴ መንፈስ ጆሮዬ ስር ናቸው 🧟‍♂🧟‍♂ ነጠላ አጣፍቼ የማላበራቸው 👳‍♀👳 ልክ እንደ መናፍስት ልክ እንደዛር ውላጅ 😏😏 መቅደስ ሲባል ብቻ ከስሬ ማጣቸው😍 ❤️
Show all...
በራስ ሃሳብ ማበድ _//__ "ኧረ ባሏ ባሏ - የፊተኛው ባሏ እስኪ ልጠይቅህ ምንድን ነው አመሏ?" ብዬ ብጠይቀው የፊተኛው ባልሽ፣ "ደግ ሴት ናት" አለኝ፤ "ኩሩ ሴት ናት " አለኝ ፤ "ብልህ ሴት ናት" አለኝ፤ ቀንቼ ነው መሰል ራሴን አመመኝ። ለተፈታች ሴት ለገባች ከሌላ፣ አቅፋ ለምታድር የሌላ ሰው ገላ ፣ እንዴት የድሮ ባል በጎ ይናገራል? መጠርጠር አለብኝ... በመካከላችሁ አንድ እውነት ይኖራል። _________ ደሱ ፍቅርኤል ተይው ፖለቲካውን ዝም ብለሽ ሳሚኝ
Show all...
➛➛ተፈጥሮን ደጅ ልጥና➛➛ " እኔ ልሙትልሽ" እያልኩኝ አልምልም ቃላቴን መንዝሬ፣ለሞት ቀብድ አልከፍልም ያኔ ትዝ ይልሻል? "ራስህን ግደል" ብለሽ በረኪና የላክሽልኝ ጊዜ እድሜ ለስጦታሽ፣ ታጠበ ሸሚዜ። ገደብ ጫፍ በሌለው፣ በልቤ መጋዘን ቢታጨቅ መከራ፣ ቢጠራቀም ሀዘን "ባለፈልኝ" እንጂ "በሞትኩ" ብየ አላቅም ካልጋ ላይ ነው እንጂ፣ ከፎቅ ላይ አልወድቅም። በሀኪሙ ስተት ፣በቁሜ ብከፈን በወርድ በቁመቴ፣ ሳጥኔ ቢደፈን ከጭስ እቀጥናለሁ፣ እኔ መውጫ አላጣም በጠጅ በወይን አገር፣ሽጉጤን አልጠጣም። የተመደበልኝ ዘመን ከባከነ የተሰፈረልኝ ፣ቀን አልቆ ከሆነ ተፈጥሮን ደጅ ልጥና ባዲስ መንገድ ትስራኝ፣ባዲስ የፍጥረት ውል መስኮትሽ ላይ ሆና ስትዘምር የምትውል ድንቢጥ ወፍ ታድርገኝ ብኖር አንቺን አየሁ፣ ከመሞት ምን ሊገኝ? ➛ገጣሚ ፦በእውቀቱ ስዩም
Show all...