cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

የፍልስፍና አለም

“የማያነብ ሰው እና ማንበብ የማይችል ሰው ልዩነት የላቸውም” ይህ ቻናል ማንኛውም ፍልስፍና ተኮር የሆኑ ጽሑፎች የሚቀርቡበት ነው ። ፍልስፍናን እንደነብሴ እወዳለሁ ያለ ሁሉ ይቀላቀለንና አብሮን ፍልስፍናን ይኮምኩም... @Philosophyworld1 ፧ ግሩፓችንን መቀላቀል ለምትፈልጉ @Philosophyworldd ለአስታየት እና ለCross @fear121

Show more
Advertising posts
2 152
Subscribers
No data24 hours
-137 days
-3630 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

ታኦኢዝም (ከላይኛው የቀጠለ) 📜📖📜 በቻይና ታኦኢዝምን የሚከተሉ እምብዛም አይደሉም ። በምንም ማመንና "ምንም" መከተል ይከብዳል ይላሉ ። የጃፓኑ ዜን ግን በታኦኢዝም አስተሳሰብ ተወስዶ እንደነበር እንረዳለን ። ለዚህም ነው የጃፓን ቅርፃ ቅርጽ የሰው እጅ ሳይነካቸው በተፈጥሮ ቅርፃቸው ብቻ መደነቅን እንዲያተርፉ አድርጎ አልፏል የሚባለው ። 📖📜📖 የታኦኢስት ዋነኛ መገለጫቸው ባላቸው ነገር ረክተው መገኘታቸው ነው ።ይኸ ደግሞ ኮንሺፊየዝምን የሚቃወሙበት ዋነኛው ነገር ነው ። ከዚሁ ጋር የተገናኘ የአንድ የኮንፊሽየስ አስተሳሰብ ተከታይ የሆነ ሰዓሊን ታሪክ ቻይናውያን ይነግሩናል ። ይኽ ሰዓሊ የእባብ ስዕልን መሳል ይጀምርና ስዕሉ በእውነታው የምናየውን እባብ አልመስል እያለ ያስቸግረዋል፤ ይኸን ግዜ ሰዓሊው ለእባቡ አራት እግሮች ማበጀት ይጀምራል ፦ "ለእባብ እግር መሳል" ይላሉ ታኦኢስቶች "የሌለን ነገር እንደማሳየት(መግለጽ) ነው ፤ አልያም ተፈጥሮን በሥልጣኔ እንደመተካት ተደርጎ ሊወሰድ ይችላል" ይላሉ ። በሕፃንነት የጀመርነውን ሕይወት በሕፃንነት እንጨርሰው እንደማለት ነው ። 📜📖📜 ታኦኢስቶች ለራስ መብቃት እምነታቸው ነው ። "ዉ ዊ" ይሉታል ። "የምድርን አበቦች ተመልከቱ ... አያርሱም፣ አይዘሩም... ሰለሞን እንኳን በዚያ ሁሉ ክብሩ እንደ እነሱ አላጌጠም" ። ይኽን ምክር ታኦኢስቶች የሚቀበሉት በከፊል ነው ። " አትረስ ፣ አትዝራ... " ይላሉ ታኦኢስቶች " ነገር ግን ይኸን የማታደርገው የሰማዩ አባት ስለሚያቀርብልህ አይደለም፤ አንተ ለራስህ ማቅረብ ስለምትችል እንጂ ። የምታርሰውና የምትዘራው ሁሉ ለአንተ መታሰርያ ነው፤ ይልቁንስ ታኦ ነፃና ግልጽ እንዲሁም ባዶ ነውና በዚያ ተመላለስ ...." ይላሉ ። 📖📜📖 በመጨረሻም ስለሰው ልጅ ይመክሩናል ፦ "የሰው ልብ እንደተወጠረ ሽቦ ነው ፤ ብትጫነው ተመልሶ ይዘላል ። እናም ሰውን ከመጨቆን ራቅ " ነው ምክራቸው ። ዳሩ ታኦ ስትሆን አንተስ ሰው ጋ ምን ልታደርግ ትደርሳለህ? ፧ ለዚህም ነው ቻይናውያን ከሁለቱ አስተሳሰቦች አንዳንድ ነገር ወስደዋል የሚባለው ፦ " ቻይናዊ ሲሳካለት ኮንፊሽየስ ፤ ሲወድቅ ደግሞ ታኦኢስት ይሆናል " ይባላል ። 📜📖📖📜 ምንጭ 👉 ጥበብ ከጲላጦስ ቅጽ ፩(4ቱን በ1) ደራ ሲ 👉 ኃይለጎርጊስ ማሞ ከገጽ 44-46 ካለው የተወሰደ ፧ ስለ ኮንፊሽየስ አስተምህሮዎች ሌላ ግዜ የምናቀርብላችሁ ይሆናል ። For any comments:- @fear121 JOIN US 👇👇👇👇👇👇👇👇 @Philosophyworld1 @Philosophyworld1 ☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️ Join our group:-👇👇👇👇👇👇@philosophyworldd @philosophyworldd የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊
Show all...
📜
የጥበብ ቅምሻ... ፧ ታኦኢዝም 📗📒📕 በቻይናውያን ፍልስፍና ከኮንሺፊየኒዝም ቀጥሎ ሁለተኛውን መስመር የያዘው ታኦኢዝም ነው ። የታኦኢዝም ፍልስፍና በላኦትዙ ትምህርት ላይ የተመሠረተ ነው ። ላኦትዙ ማለት "Old Master" ማለት ነው የሚሉ አሉ ። በእርግጥም ከጥንታዊነቱ ጋር ሲነፃፀር ትርጉሙ ተቀባይነትን ሊያገኝ ይገባዋል ። ላኦትዙ በኮንፊሽየስ ዘመን የነረም ነበር ይባላል ። በአንዳንድ አፈታሪክ ላኦትዙና ኮንፊሽየስ በመንገድ ላይ ተገናኝተውም ነበር ይላሉ ፤ ይሁንና አንዳቸው ለአንዳቸው የሚያወሩት ስላልነበራቸው በዝምታ ተላልፈዋል ይባላል ። 📜📖📜 የላኦትዙ ተቀዳሚና ዋነኛ ፍልስፍናዊ እሳቤና ሥራ ደግሞ "ታኦ ቲ ቺንግ ይባላል" ። "መንገዱና የመንገዱ ኃይል" እንደማለት ነው ይላሉ ። ይኽ እሳቤ ከኤሽያ ፍልስፍናዎች ሁሉ ጣፋጭና የተዋበው ነው የሚሉም ምዕራባውያን ፈላስፎች አልጠፉም ። ከእነዚህም አንዱ ጆርጅ ሳንታያና ነው ። እንደሌላው ፍልስፍና ሁሉ የታኦኢዝም መሠረቱ ውስጣዊ ማንነታችን ነው ። ታኦ ምክንያታዊና ሞራላዊ የሆነው ተፈጥሮአዊ አስተሳሰባችን ሲሆን ይኸ አስተሳሰብ ደግሞ በውስጡ "ባዶነትን" ያዘለ ሆኖ እናገኘዋለን ። 📖📜📖 ታኦ ምንም እንኳን ሲተረጎም "መንገድ" እንደማለት ቢሆንም ይኽ መንገድ ግን ራሱን ወደ ባዶነት (ምንምነት) መውሰጃ ነው ። በብዙዎች የቻይና መልክዓምድራዊ ሥዕሎች ውስጥ የምናየው ባዶነት የታኦኢዝም ፍልስፍና ተፅዕኖ ነው የሚሉ አሉ ። ታኦኢስቶች ከሰው ተነጥለው ወደተራራ ጫፍ ይወጡና በደመና መካከል ይቀመጡ ነበር ይባላል ። ባዶነትን ፍለጋ ነው ። ታኦኢስቱ ቹ ኦንግ ዙ ይመክረናል ፦ "ሌሎችን ለባልንጀራነት የሚፈልግ እሱ ለዘላለም በሰንሰለት እንደታሰረ ሰው ነው፤ በሌሎች አጥብቆ የሚፈለግ ደግሞ እሱ ለዘላለም እንዳዘነ ይኖራል፤ ሰንሰለቱን አውልቀህ ጣል ፤ ማዘንህንም አስወግድ ፤ ከታኦም ጋር በታላቁ የባዶነት መንግስት ውስጥ ተመላለስበት ።" ይኽን የሰሙ ምዕራባውያን ፈላስፎች " ታኦኢስት ማለት ለማንም የትም እንደማይሄድ ፈጽሞ ቃል የማይገባና ፤ ነገር ግን የሚሄድበትም የሌለው ነው " ይላሉ.. ፧ ይቀጥላል... በንባብ አብራችሁን መሆናችሁን እቺን 👉 (📜) በመጫን አሳዩን... For any comments:- @fear121 JOIN US 👇👇👇👇👇👇👇👇 @Philosophyworld1 @Philosophyworld1 ☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️ Join our group:-👇👇👇👇👇👇@philosophyworldd @philosophyworldd የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊
Show all...
📜
ፍቅር በፍልስፍና እይታ ፧ ንፅረተ-ፍቅር 📖📜📜📖 አብዛኞቻችን "ፍቅር" ሲባል ከሰማን እዝነልቦናችን ላይ የሚመጣብን በወንድና በሴት መካከል ያለው የመቀራረብ ስሜት ነው ። በእርግጥም እንዲህ ያለው ፍቅር ተጨባጭና ለተመልካች ግንዛቤ የማያዳግት ነው ። ተጨባጭነቱንና ግልፅነቱን ያገኘው በቴአትሮች ፣ በሆሊውድ ፊልሞች ወይም በፍቅር ልቦለዶች ብርታት ነው ማለት አይቻልም ። በነባሩ ባህል ውስጥ ስንመለከት የኖርነው እንዲህ ያለው የወንድና የሴት ፍቅር ወደ አንድ አካልና አንድ አምሳልነት ሲያመራ ነው ። 📖📜📖 ፍቅር አይነቱ ብዙ ነው ። በፆታዊ ፍቅር ብቻ አይገደብም ። የመጽሐፍ ቅዱሱ ንጉስ ዳዊት ቤርሳቤህን በማፍቀር ብቻ እሷን አግኝቶ አልተገታም ። በህይወቱ ውስጥ ሌላም አይነት ፍቅር እንዳለ አሳይቷል ። ለምሳሌ ለዮናታን ከፍተኛ ፍቅር ነበረው ከዚህም ባሻገር ልጁ አቢሴሎም ሲሞትም "አቢሴሎም ልጄ ልጄ" ሲል በተሰበረ ልብ ፍቅሩን ገልጿል ። ስለዚህ የጓደኝነትና የስጋ ዝምድና ፍቅር እንዳለ በዚህ እንረዳለን ። በፕሌቶና በሶቅራጥስ እንዲሁም በኢየሱስና በደቀመዛሙርቱ መካከል የነበረው ደግሞ እውቀትን ወይም ሃይማኖትን ተንተርሶ የሚመጣውን ፍቅር ይገልፅልናል ። በዚህ አይገታም የሰው ልጅ አገሩን፣ ወገኑን ፣ አቋሙን ፣ ቤተሰቡን ፣ አምላኩን በማፍቀር የተለያየ ፍቅር መኖሩን አሳይቷል ። 📖📜📖 የተለያዩ ግንኙነቶችን እራሳቸውን አስችለን የምንወክልበት መጠርያ ስለምናጣላቸው በጋራ ስያሜ የምንደፈጥጥበት ግዜ ብዙ ነው ። ፍቅርም አይነቱ ብዙ ቢሆንም አንዱን ካንዱ የሚለይ ስም ግን ሲውጣለት አይታይም ። ይሄንን ክፍተት ተመልክተው ለፍቅር አይነቶች ሶስት መጠርያ ያዘጋጁ ግሪኮች ናቸው ። "ፊልያ" (Philia) ፣ "ኢሮስ" (Eros) ፣ እና "አጋፔ" (Agape) ይሏቸዋል ። ምናልባት በጥሬው ብንተረጉማቸው "የወዳጅነት" ፣ "የምኞት" እና "የልግስና" የፍቅር አይነቶች ልንላቸው እንችላለን ። ፊልያ በንጉስ ዳዊትና በዮናታን መካከል የነበረውን የጓደኝነት ፍቅር ይወክላል ። ኢሮስ ደግሞ አፍቃሪው ተፈቃሪውን በማግኘት እርካታን የሚቃብዝበት አይነቱ ነው ። በወንድና በሴት መካከል የሚከሰተውን ማለታችን ነው ። አጋፔ ደግሞ መንፈሳዊ ፍቅር ሆኖ በሰውና በፈጣሪው ወይም በሰዎች መካከል ይከሰታል ። በቅዱሳት መጻህፍት አማካኝነት አምላክ ለሰው ልጆች ያሳየው ፍቅር በአጋፔ ውስጥ የሚጠቃለል ነው ። በአፀፋው ሰዎች ስለፈጣሪያቸው የሚቀበሉት መከራና ሞት የዚሁ የፍቅር አይነት ውጤት ነው ። 📖📜📖 ምኞት ያለበት ኢሮስን ጨምሮ ሶስቱም አይነት ፍቅሮች የተሸጋጋሪነት ጠባይ አላቸው ። ስለዚህ ፍቅር ሁልግዜም ከአንዱ ወደ ሌላው የሚያነጣጥር ጥልቅ ስሜት ነው ለማለት ተገደናል ። ነገር ግን እራስ አፍቃሪነትስ? የት ይመደባል? "ባልንጀራህን እንደራስህ አድርገህ ውደድ" የሚለው የአምላክ ትእዛዝ ለእራስ አፍቃሪነት እውቅና አይሰጥም? የስነ-ምግባር ሰዎች እና የስነ-ልቦና ምሁራን እራስን ማዕከል ያደረገ ፍቅርን ጤናማ ያልሆነ ስሜትና ያለመብሰል ምልክት አድርገው በመፈረጅ ያጥላሉታል ። የሃይማኖት ጉባኤዎችም ለራሳችን እራሳችን የምናሳየውን ፍቅር ያወግዙታል ፧ ምንጭ 👉 " የፍልስፍና አፅናፍ " ደራሲ 👉 ዶክተር ሞርቲመር ጄሮም ትርጉም 👉 ደራሲ ዓለማየሁ ገላጋይ ፧ ፨ በነገራችን ላይ ባሁን ሰአት ግሪኮች ከላይ ከጠቀስናቸው ሶስቱ የፍቅር አይነቶች በተጨማሪ አራተኛ ስተሪጅ(Sturige) ወይም "ቤተሰባዊ ፍቅር" የሚሉት አይነት ፍቅር እንዳለም ያምናሉ አንዳንድ መጽሀፍትም በዛ መነሻነት ፍቅርን በአራት ከፍለው ይገልጹታል ። ፧ For any comments:- @fear121 JOIN US 👇👇👇👇👇👇👇👇 @Philosophyworld1 @Philosophyworld1 ☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️ Join our group:-👇👇👇👇👇👇@philosophyworldd @philosophyworldd የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊
Show all...
Photo unavailableShow in Telegram
💡'እኔ ማን እንደሆንኩኝ አታውቅም, ግን እኔ ማን እንደሆነች አውቃለሁ' 'She doesn't know who I am, but I know who she is 💎 የ85 አመት አዛውንት ናቸው ከ 60 ዓመት በላይ ከባለቤታቸው ጋር በትዳር ኖረዋል, ባለቤታቸውን በሄዱበት ሁሉ እጃቸውን አጥብቃ እንድትይዛቸው ባለመሰልቸት ይጠይቋታል, ስትቆም ቆመው ስትቀመጥ ተቀምጠው ስታስቸግር አብረው ተቸግረው . . . ሳይሰለቹ የድሮ ፍቅራቸውን ሳይቀንሱ በ 85 ዓመት የአዛውንት ጉልበታቸው አሁንም በትዕግስት አብረዋት አሉ :: ሰዎች ሚስታቸው ምን ሆና እንዲህ እንደሆነች ይጠይቃሉ “አልዛይመርስ' የመርሳት በሽታ አለባት” ሲሉ ይመልሱላቸዋል 💡እና ምንም አታስታውስም ? ምንም !ያን ሁሉ ዓመት የሕይወት ውጣውረዳችንን,ደስታችንን ሀዘናችንን ወልደን ኩለን መዳራችንን ዘመድ አዝማድን ኧረ እኔንም ዘንግታኛለች እናም "ሚስትህ እጅህን ብትለቅህ ትጨነቃለህ ማለት ነው ?" ለምን አልጨነቅም ምንም ነገር ማንንም አታስታውስም እኮ በዚህ ዓለም ያላትን ነገሮች ሁሉ ረስታለች እኔንም ጭምር , ለብዙ አመታት አላወቀችኝም እና ያለኔ ማን አላትና ነው የማልጨነቀው ?! 💎 "እናም አንተን ባታውቅህም በየቀኑ መንገድ ላይ እየመራሃት ትቀጥላለህ" ማለት ነው , ፈገግ አሉና አይኖቼን እምባ ባቀረሩ አይናቸው እየተመለከቱ. "እኔ ማን እንደ ሆንኩኝ አታውቅም ግን እኔ ማን እንደሆነች አውቃለሁ " ውዷ ከ 60 ዓመት በላይ ብዙ ነገር የሰጠችኝ ሕይወቴ ናት " እናም ሕይወቴን ሙሉ በሄደችበት ሁሉ አብሪያት አለሁ , ሰው ካለ ህይወቱ ምን ሕይወት አለው .. እከተላታለሁ። መልካሞችን ሁሌም ያብዛልን። ውብ አዳር❤️ For any comments:- @fear121 @Philosophyworld1 የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊
Show all...
💫አፍርሰህ አትገነባም. የሄደ ነገር ተመልሶ ይመጣል። ሰብረህ ያጠፍኸው የመሰለህ ነገር ይዘገይ ይሆናል እንጂ አይቀርምና አፀፍውን መልሶ ሊያስታቅፍህ ምንአልባትም እጥፍ ድርብ አድርጎ ደጃፍህ ላይ ቆሞ በርህን ያንኳኳል። ኃላፊነት በንግግር፣ ተግባርና ሁሉም መስክ ላይ እንዲንፀባረቅ የተገባው በእዚህና መሰል ምክንያቶች ነው። 💡እርግጥ ነው ኃላፊነትን በፀጋ መቀበል እና ሳይሸራርፉ በተጨባጭ መወጣት ፈታኝ ነው። አስተዋይ አእምሮ እና ቅን ልቦና በምርጫና መንገድህ ካልተለየህ ግን በድል ትወጣዋለህ። ድሉም ከበደል የፃዳ ይሆናል። ድሉ ከራስህ አልፎ አለምን ስለሚጠቅም መልካሙ ስርህ ሄዶ ዞሮ ሲመለስ በጎ ምላሽ ማግኘትህ አይቀሬ ነው። ወርቅ ለሰጠ ወርቅ እና ጠጠርም ለሰጠ ጠጠር ማግኘት ተፈጥሯዊ ህግና የህይወት ነባራዊ እውነታ ነውና። 💎መልካምነት ከማንም በላይ ላራስ ነው ጥቅምና ፍይዳው። ቅን ሀሳብ አሳቢውን ይባርካል። ሴራ፣ ተንኮል እና ክፍት ህሊናና ልብህን ከሞላው ግን ሌላው ይቅርና መልካም እንቅልፍ እንኳ ብርቅ እና ሩቅ እንደሚሆኑብህ ልነግርህ እችላለሁ። 🔆አዳርህ በመባነን እና መበርገግ ይሞላል። ቀን ያሳደድከው በህልምህ መግቢያና መሸሸጊያ ጥግ ያሳጣሀል። ቀን ከሌት የዘራሀቸው ክፋቶች ሌሎችን ብቻ ሳይሆን የአንተን የገዛ ራስህንም ገላም ይቧጥጣሉ። ከአንተ የመነጨና ተንደርድሮ የተተኮሰ ኃይል በእኩል መጠን እና ልክ አጥፊ እንደሆነ ራስህንም ያጠፍል፤ አልሚ ከአደረከው ደግሞ ቅድሚያ አንተን እና የእኔ የምትለውን ሁሉ ባርኮ ለሌሎች ይተርፋል። ✨ይህ የህይወት ሀቅ ከፊዚክስ action/reaction ተፈጥሮአዊ ህግ ጋር ይመሳሰላል። አፍርሰህ አትቆምም። ጠልተህ ፍቅርን አታተርፍም። ወደህ ላትከበር፣ ትህትናን ሰጥተህ ልትናቅ፣ አሳቢና አስታዋሽ ሆነህ ሳለ ልትረሳ አትችልም። ምክንያቱ ደግሞ ምዕራባዊያን እንደሚሉት የሄደ ነገር ተመልሶ ይመጣልና ነው (what goes around comes around)። አበውም አሳ ጎርጓሪ ዘንዶ ያወጣል፣ የሰው ፈላጊ የራሱን ያጣል፤ በቆፈሩት ጉድጒድ መቀበር አይቀርም ወዘተረፈ ብለውናል። ✍ ነጋሽ አበበ ሰናይ ቀን ይሁንልን❤️ For any comments:- @fear121 JOIN US 👇👇👇👇👇👇👇👇 @Philosophyworld1 @Philosophyworld1 ☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️ Join our group:-👇👇👇👇👇👇@philosophyworldd @philosophyworldd የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊
Show all...
<<<<አርስቶትል>>>> የቀጠለ……… 📖📖📖📖📖📖📖📖 በግሪክ ይኸው አባባል ትልቅ ቦታ ተጥቶት ሲገለፅ፦ "ህይወት የተፈጥሮ ስጦታ ስትሆን፣የተዋበች ህይወት ግን የጥበብ ስጦታ ነች" ይላሉ። አሌክሳንደርም መምህሩ ለነበረው አርስቶትል በፃፈለት ደብዳቤ፦ "በስልጣኔና በሀይሌ በልጬ ከመታየት ይልቅ መልካም በሆነው ጥበብና እውቀት ልቄ መታየትን እሻለሁ" ብሏል። አርስቶትል ይህን ያልተገራ ወጣት ለመግራት ተቸግሯል ወይም አልተሳካለትም። ለዚህም ይመስላል አሌክሳንደር ከአርስቶትል ጋር የቆየው ለሁለት አመታት ብቻ ሲሆን ከዛ በኋላ የፍልስፍናን ነገር እርግፍ በመተው በስልጣንና በሀይል ወደመጋለብ ተሸጋገረ። በዚህ መንገድ በእርግጥም ተሳክቶለት የአለምን አንድ ሶስተኛ በቁጥጥሩ ስር ለማድረግ የቻለ ሰው ሲሆን ይኸው ስራውም ታላቁ አሌክሳንደር እስከመባል አድርሶታል። 📒📒📒📒📒📒📒📒📒📒 ይሁንና እስክንድርን የታላቅነቱን አላማ ያስጨበጠው ለደረሰበት ዝና ያበቃውን ራዕይ የሰነቀው ለጥቂት አመታት መምህሩ የነበረው አርስቶትል በውስጡ ካስቀመጠው ነገር የተነሳ ነው የሚሉ ብዙዎች ናቸው። 📖📖📖📖📖📖📖📖 አርስቶትል በአቴና ውስጥ በትልቁ የሚነገርለትን የፍልስፍና ትምህርት ቤት ከፍቶ ማስተማር የጀመረው በአምሳ ሶስት አመቱ ነበር። የነገስታት ንጉስ ታላቁ እስክንድርን አስተማሪ ለነበረ ሰው በአቴና ተማሪ ለማግኘት ብዙም የሚከብደው ነገር አልሆነበትም። እንዳውም የተማሪው ቁጥር እጅግ በመብዛቱ ምግቡን የሚመገብበት ጊዜ በማጣት በመቸገሩ ከተማሪዎቹ ጋር አዘውትሮ ይበላ እንደነበር ታሪኩ ይናገራል። አርስቶትል በትምህርት ቤቱ ይበልጥ አትኩሮቱን ያደረገው በተፈጥሮ ሳይንስ ጥናት ላይ ነበር። እንዳውም ባንድ ወቅት ታላቁ አሌክሳንደር የአርስቶትልን አትኩሮት ተረድቶ አንድ ሺህ የሚደርሱ ሰዎችን ረዳት በማድረግ መድቦለት ነበር። እንዚህን ሰዎች አርስቶትል በግሪክና ኤሽያ በመላክ ለምርምር ስራው የሚረዳውን ናሙና እንዲሰበስቡለት አድርጓል። አርስቶትል የአቴናን ከርበርቴ ልጅ አግብቶ የተደላደለ ኑሮውን የሚመራ ሰው ከመሆኑም በላይ አሌክሳንደርም ለምርምር ስራው እንዲሆነው በአሁኑ የገንዘብ ስሌት 4 ሚሊዮን ዶላር ሰጥቶት ስለነበር በአርስቶትል ዘንድ የገንዘብ ችግር አልነበረም። 📖📖📖📖📖📖📖📖📖 አርስቶትል የምርምር ስራውን ተከትሎ በፅሁፍ ትቶልን የሄደው ስራዎቹ አንዳንዶቹ ከ400 በላይ እንደሆኑ ሲናገሩ የተቀሩት ደግሞ ከሺህ በላይ እንደሆነ ይናገራሉ። ከእነዚህ ስራዎቹ ውስጥ (Øɽ₲₳₦ø₦) (₱ⱨɏ₴ł₵₴) (Ø₦ ₮ⱨɇ Ⱨɇ₳vɇ₦₴) (₲ɽø₩₮ⱨ ₳₦đ Đɇ₵₳ɽɏ) (Ø₦ ₮ⱨɇ ₴øʉⱡ) (Ɇ₮ⱨł₵₴) (₱øⱡł₮ł₵₴) (₥ɇ₮₳₱ⱨɏ₴ł₵₴) ወዘተ ሲገኙባቸው ብዙዎች የግሪክ የፍልስፍናው ጠበብት እጅግ ስህተት የበዛባቸውና ግራ አጋቢ ሀሳቦችንም የተሞሉ ናቸው በማለት ትችታቸውን ሲሰነዝሩባቸው ኖረዋል።እንዳውም አርስቶትል ሀሳቡን በብቃት የመፃፍ ክሂሉ የነበረው ሰው ባለመሆኑ ፍልስፍናውን የፃፉለት ተማሪዎቹ ናቸው የሚሉም አልታጡም። ይሁንና መፅሀፎቹ በማንም ይፃፉ ሀሳቡን የወለደው አርስቶትል እስከሆነ ድረስ ደራሲነቱም ለእሱው ሊበረከት ይገባል የሚሉ ብዙዎች ናቸው። 📖📖📖📖📖📖📖📖📖 አርስቶትል የመጀመሪያው ልዩ የፍልስፍና ስራው ተደርጎ የሚወሰድለት የሎጅክን ሳይንስ የፈጠረ ሰው በመሆኑ ነው። ሎጅክ በቀላል አገላለፅ "የምክንያታዊ አስተሳሰብ ጥበብና መንገድ" ተደርጎ ሊወሰድ ይችላል። ሎጅክን ሳይንስ የሚያደርገው የራሱ ህግና መንገድ ያለው በመሆኑ ነው፤ ጥበብ የሚያደርገው ደግሞ እሱን በመለማመድ የማሰብን ብቃት የሚጨምር በመሆኑ ነው። በአርስቶትል እሳቤ መሰረት የሚያስብ አዕምሮ ሙት ነው፤ አዕምሮ ያስብ ዘንድ ደግሞ በሎጅክ መታገዝ አለበት። ይቀጥላል……… For any comments:- @fear121 JOIN US 👇👇👇👇👇👇👇👇 @Philosophyworld1 @Philosophyworld1 ☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️ Join our group:-👇👇👇👇👇👇@philosophyworldd @philosophyworldd የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊 ምንጭ፦ ጥበብ ከጲላጦስ ሀይለጊዮርጊስ ማሞ
Show all...
……📖📖📖…አሪስቶትል…📖📖📖… አሪስቶትል የመቄዶንያ ዋና ከተማ በነበረችው ስታጂራ ውስጥ ከክርስቶስ ልደት በፊት በ384 ተወለደ። አባቱ የታላቁ አሌክሳንደር አያት የነበረው የንጉስ አሚንታስ የልብ ጓደኛና ሀኪም ነበር። ቤተሰባዊ እድገቱም ከህክምና ሙያ ጋር በተቆራኘ ቤተሰብ ውስጥ በመሆኑ የዚሁ ሙያ ተፅዕኖ በሰፊው እንዳደረበት ይነገራል። 📖📖📖📖📖📖📖📖📖📖 ይሁንና አርስቶትል ከልጅነቱ የተዋሀደው ሀሳበ ብኩንነት ብዙ ሙያዎችን እንዲረግጥ እንዳደረገውና በዚህም ምክንያት ወታደርነትን፣ ከዚያም ወደ ስታጂራ በመመለስ የህክምና ሙያን፣ እንደገና ወደ አቴና ተመልሶ ደግሞ በፕሌቶ ስር ፍልስፍናን ተምሯል። 📘📘📘📘📘📘📘📘📘 በሌላ አንፃር የተፃፈው የአርስቶትል ታሪክ እንደሚያትተው ደግሞ በ18 ዓመቱ ወደ አቴና በመሄድ በፕሌቶ ስር ፍልስፍና ማጥናቱንና በዚያም ምጡቅ አይምሮ ያለው ሰው ለመሆኑ ማስመስከሩን ይነግረናል። አርስቶትል ከፕሌቶ ስራ ፍልስፍናን ሲያጠና ከስምንት እስከ አስር ዓመት እንደቆየ የሚነግረን ታሪኩ የእሱ ደስተኛ ዘመናትም እኒሁ ጊዚያቶች እንደነበሩ አስፍሮ ይሁንና በአስተሳሰብ ደረጃ የሚጋጩባቸው ብዙ ፍልስፍናዊ እሳቤዎች እንደነበሩ እንረዳለን። ለዚህም ይመስላል ብዙዎች የፍልስፍናው ዓለም ሰዎች ስለሁለቱ ሲናገሩ"ከፍተኛ አስተሳሰብ ያላቸው ሁለት ጭንቅላቶች ሲጋጩ ታላቅ እሳት መጫሩ አይቀሬ ነበር"የሚሉት። 📖📖📖📖📖📖📖📖📖📖📖 ፕሌቶ እጅግ ከሚደነቅባቸው ጥቂት ሰዎች አንዱ አርስቶትል አንደነበር ሳይደብቅ ይናገር እንደነበር ብዙዎች ሲመሰክሩ በአንድ ወቅትም በአንደበቱ ስለዚሁ ሰው በሰጠው ምስክርነት "አዋቂነት ስጋ ለብሶ ሲንቀሳቀስ በእርግጥ አየሁ" በማለት እንደነበር ማረጋገጫ ያቀርባሉ። 📒📒📒📒📒📒📒📒 ምንም እንኳ የፕሌቶ ተማሪና በእውቀቱም ተደናቂ የነበረው አርስቶትል ከመምህሩ ከፍተኛ አድናቆትን የተቸረው ሰው ቢሆንም በአስተሳሰቡ ግን ከመምህሩ ጋር ጉልህ የሆነ ልዩነት አምጥቶ እንደነበርና እንዲያውም በአንዳንዶች እሳቤ በፕሌቶ የተንቀለቀለው የፍልስፍና እሳት በአርስቶትል ጭሱ ብቻ እንደታየ አድርገው የሚተቹትም ብዙዎች ነበሩ። አርስቶትልም ቢሆን ከማሰብ ይልቅ መፅሀፍን ብቻ ማንበብ ላይ መበርታቱ በራሱ በፕሌቶ ዘንድ እንዳስተቸው የሰፈረ ታሪክ አለ። 📘📘📘📘📘📘📘📘📘📘 በ356 እ.ኤ.አ የግሪክ ንጉስ የነበረው ፊሊፒ አርስቶትልን ወደቤተ መንግስቱ በመጥራት ልጁን በፍልስፍና ጥበብ እውቀት እንዲያኮተኩትለትና ለእሱም በትርፍ ጊዜው እንዲያስተምረው ጥያቄ ባቀረበለት መሰረት አርስቶትል የቤተ መንግስት የቅርብ ሰው ለመሆን በቅቶ ነበር። ይሁንና ንጉስ ፊሊፒ በዛው ዓመት በሰው እጅ በመገደሉ አርስቶትል በወቅቱ የአስራ ሶስት ዓመት ልጅ የነበረውን አሌክሳንደርን ማስተማር ጀመረ። 📖📖📖📖📖📖📖📖📖📖 ይህ አሌክሳንደር ገና በልጅነቱ ቀበጥባጣ፣ የአልኮል ፍቅር ያደረበትና በሚጥል በሽታ የተያዘ ሲሆን የደስታው ምንጭ አድርጎ ይዞት የነበረውም ለማዳ ያልሆኑ ፈረሶችን በመግራት አሰልጥኖ መያዝና መጋለብ ነበር። በዚህም ምክንያት በፍልስፍናው ጥበብ ብዙም ቦታ የሚሰጠው ሆኖ አልተገኘም። ስለዚህም ጉዳይ አንድ ቀን እስክንድር ተጠይቆ ሲናገር "አርስቶትል የሚያስተምረኝ መኖርን ነው፤ እኔ ደግሞ ማወቅ የምፈልገው የመኖርን ጥበብ ነው" ብሏል። 📖📖📖📖📖📖📖📖📖📖 👇👇👇👇 For any comments:- @fear121 JOIN US 👇👇👇👇👇👇👇👇 @Philosophyworld1 @Philosophyworld1 ☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️ Join our group:-👇👇👇👇👇👇@philosophyworldd @philosophyworldd የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊 👆👆👆👆 ይቀጥላል………… ምንጭ፦ ጥበብ ከጲላጦስ ከቁ.፪
Show all...
ዲዮጋን ፨፨፨ 📖 የታላቁ ፈላስፋ የዲዩጋን ምርጥ ምላሾች!! ❇️ በቆሻሻ ቦታ ሲዘዋወር የተመለከተው የአቴና ነዋሪ ወዳጁ ቢገስጸው፡- ‹‹አትሳሳት! ጸሀይ የማትወጣበት ቦታ የለም እስከዛሬ ግን አልቆሸሸችም ብሎታል››፡፡ ❇️ በሌላ ግዜም በገበያ ቦታ ላይ ሲበላ የተመለከቱት የአቴና ነዋሪዎች በዙሬያው ተሰብስበው ‹‹ውሻ ውሻ ! ›› በማለት ሲጮሁበት፡- ‹‹እኔ የማውቀው ሰው ምግብ ሲበላ በዙሪያው ከቦ የሚመለከትና የሚጮህ ብቻ ነው››በማለት መልሳል፡፡ ❇️ ሰዎች ለለማኝ እንጂ ለምን ለፈላስፋ ገንዘብ እንደማይሰጡ ሲጠይቁት ‹‹ምክንያቱም አንድ ቀን ለማኝ እንጂ ፈላስፋ እንደማይሆኑ ስለሚያውቁ ነው›› ብላቸዋል፡፡ ❇️ ምግብ ለመመገብ የተመቸ ሰአት የቱ እንደሆነ ተጠይቆ፡- ‹‹ሀብታም ከሆንክ ስትፈልግ'ድሀ ከሆንክ ደሞ ስትችል ምግብ ለመመገብ ጥሩ ሰአት ነው››ብላል፡፡ ❇️ ለዲዩጋን ምጽዋት የሚሰጡት ሰዎች ለምን እንደማያመሰግናቸው ሲጠይቁት ‹‹እናንተ በመስጠታችሁ ብቻ ሳይሆን እኔም የናንተን ምጽዋት በመቀበሌ ምስጋን ይገባኛል››ብላቸዋል፡፡ ❇️ ስለጸሎተኛ ሰው ሲጠይቁት ‹‹ጸሎተኛ ሰው የሚፈልገውን እንጂ መጠየቅ የሚገባው የማይጠይቅ ሰው ነው››ብላል፡፡ ❇️ ሲሞት እንዴት እንዲቀብሩት እንደሚፈልግ ሲጠየቅም ‹‹ፊቴን ወደታች ዘቅዝቃችሁ ቅበሩኝ ምክንያቱም ዝቅ ያለ ነገር ጥቂት ቆይቶ ከፍ ማለቱ እንደማይቀር ስለማውቅ ነው›› ብላቸዋል፡፡ ❇️ እንድ የአቴና አስተማሪ ስለህይወት ክፉነት ደጋግሞ ሲያስተምር ሰምቶ ‹‹ህይወት ክፉ ያደረጋት የሚኖራት እንጂ ህይወት በራሷ ክፉ አይደለችም››ብሎታል፡፡ ❇️ በባርነት የገዛው ዜነዲየስ ‹‹እኔን ልትታዘዝ የግድ ነው››አለው፡፡ ‹‹ምንም እንኮን ባሪያህ ብሆንም አዋቂና የነቃ ሰው በባርነትም ሆኖም ሊታዘዙት ያስፈልጋል››፡፡ For any comments:- @fear121 JOIN US 👇👇👇👇👇👇👇👇 @Philosophyworld1 @Philosophyworld1 ☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️ Join our group:-👇👇👇👇👇👇@philosophyworldd @philosophyworldd የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊
Show all...
ያንተ ጥንካሬ! አይንህ ወደ ብርሀኑ አቅጣጫ ከሆነ ሊጋርድህ የሚፈልግ ጥላ ከኋላህ ያርፋል፤ ሀሳብህ መልካም ነገር ላይ ብቻ ካረፈ መጥፎ ነገሮች አንተ ጋር ሳይደርሱ ከጀርባህ ይወድቃሉ። ጨለማው ላይ ማፍጠጥ ብርሀን አይሰጥም፤ ድክመትህን ብቻ አጉልተህ አትይ! አንተ ባትሆን የማታልፋቸው ብዙ ችግሮች ነበሩ፤ አንተ ግን ለዛሬ ደርሰሀል፤ ወዳጄ አሁን ያለህ ጥንካሬ የምታስበውን ሁሉ ለማሳካት ከበቂ በላይ ነው! ውብ ቀን ተመኘንላችሁ🙏 For any comments:- @fear121 JOIN US 👇👇👇👇👇👇👇👇 @Philosophyworld1 @Philosophyworld1 ☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️ Join our group:-👇👇👇👇👇👇@philosophyworldd @philosophyworldd የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊
Show all...
Photo unavailableShow in Telegram
Dreams of a life ብቸኝነት + መረሳት ስሟ ጆይስ ካርሎ ቪንሰንት ይባላል የ 38 አመት ወጣት ስትሆን ነዋሪነቷ የነበረው እንግሊዝ ውስጥ ለንደን ነው፡፡ ትኖር የነበረው አፓርትመንት ተከራይታ ሲሆን የቤቷ የኪራይ ውል በማለቁና ያለባትን የኪራይ ውዝፍ ልትከፍል ባለመቻሏ አከራዮቿ በ 2006 ለፓሊስ ያሳውቃሉ ፓሊሶቹም ወደ ቤቷ በመሄድ ሲያንኳኩ በር አይከፈትም ሰብረው ይገባሉ ሰብረው ሲገቡ ግን በህይወት ሳይሆን ሶፋ ላይ ቁጭ እንዳለች ሞታ ነበር ያገኟት እሷ የሞተችው ግን በ2003 ነበር ፡፡ ሞታ ለ ሶስት አመት ምናምን ያለ ጠያቂ በቤቷ ሶፋ ላይ ቁጭ እንዳለች ቆይታለች ፡፡ ከሞተች ከ 3 አመት በኀላም ቀናቸው ያለፈባቸው ምግብና መጠጦች ከፍሪጇ ውስጥ ፓሊሶች አግኝተዋል ሌላው ብዙዎችን ያሳዘነው ነገር ይሄን ሁሉ አመት ሞታ ቤቷ ስትቆይ ማንም የት ነሽ ወዴት ነሽ ያላት አለመኖሩ ነበር ፡፡ በ2011 GC በእውቋ እንግሊዛዊት ዳሬክተር ካርሎ ሞርሌ DREAMS OF A LIFE የተሰኘ አሳዛኝ ዶክመንተሪ ተሰርቶላታል፡፡ የሰለጠነው አለም ግላዊነት ከመጣባቱ የተነሳ ሁሉም በየራሱ ይኳትናል እንጂ አጠገቡ ስላለው ጎረቤት አይጨነቅም ፡፡ አብረከው ስለኖርክ ብቻ መጠጋጋትንና ቅርርብን አይፈቅድም ፡፡ ሀገራችን ውስጥ ምንም ቢሆን ከፋም ለማም ተጣላክም አልተጣላክም እንዴት ነው ወዴት ነው የሚል ደሞ ዛሬ ምነው ድምፁ ጠፋ ድምፇ ጠፋ የሚል ጎረቤት ሁሌም ቢሆን ይኖርሀል .... መኖርህ ነው የኑሮ መለኪያ እናም የሀገሬ እናቶች ተሰብስበው ስናያቸው ቡና ከመጠጣቱ በዘለለ የአብሮነት ድራቸውን አየፈተሉ እንደሆነ መገንዘብ ተገቢ ነው ፡፡ For any comments:- @fear121 JOIN US 👇 @Philosophyworld1 የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊
Show all...