cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ኦፍቲ ቲዩብ-ልበ ጥሞና

Show more
Advertising posts
240
Subscribers
No data24 hours
+17 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

የጌቱ በቀለ ሽልማት.aac48.02 MB
"በምንም የማይታለፉ አንዳንድ ጋሬጣዎች አሉ...ወግተው ከማድማትና አድምተው ከመጠዝጠዝ ባለፈ ተልዕኮ የሌላቸው። ተወርውረው ከመሰካት ሙላት ከማጉደል ሌላ እርባና የሌላቸው። በልካችን የተሰሩና በልካችን የተቀረጹ ጋሬጣዎች..... ...የሠው ልጅ ከማወቅ ይልቅ አለማወቁ ይበጀዋል። ባለማወቅ ብዙ አትርፈናል። በማወቅ ግን አለማወቃችንን እየገለጥን ነው። እየፈራን ያለነው ባወቅን ትንሽ ነገር ነው። አለማወቅ ነው ያኖረን...ድንቁርና ነው የደበቀን። ነገን ማወቅ ስጋታችንን ከመጨመር ባለፈ ለመኖራችን ዋስትና አይሰጠንም... ...ሙሉ መሆን ጊዜ ይወስዳል። ....በአእምሮ የተወደደ በልብ አይጠላም። በልብ የተፈቀረ በአእምሮ አይናቅም። በአይን የሆነ ነገር ሁሉ ግን ብላሽ ነው። እኔን ስትመርጡኝ፤ ሌላውንም ሰው ስትሹ በሌሎች ስትመረጡም በአእምሮ በኩል ይሁን... አእምሮ የህይወት ሚዛን ነው። ፍትህ ከነክብሯ በአእምሮ ቋት ውስጥ አለች....አእምሮ ጣልቃ ያልገባበት ምርጫ የቁጭት ሰፊ በር ነው። #ዝም! 👌 እጅግ የሚወደድ ድንቅ የአጫጭር ልብ ወለድ አዲስ 20ኛው የዘላለም የሳጥን ወርቅ መጽሐፍ። በየመጽሐፍት መደብሩ #ዝምን ጠይቁ። የአንባቢያን የመጀመሪያው ምርጫ ዝም። ቅዳሜ ኅዳር 15/2016ዓም በአፕድ አዳራሽ 4ኪሎ ከብሰማተሚያ ቤት ፊት ለፊት ከቀኑ 9:00ሰዓት ጀምሮ ይመረቃል🙏 ጊዜ ካላችሁ ሁላችሁንም ጋብዘናል👌❤ በዕለቱ ግዢ የምትፈጽሙ ከሆነ የመጽሐፉን ግማሽ ዋጋ ይሸፈንላችኋል🙏 ማንበብ አለማወቅን ይገልጻል። ከማማረር ማምረር።
Show all...
#የአፍሪካ ድንቃ ድንቅ ይመዝግብልኝ🙏❤ 👉ዘለዓለም የሳጥን ወርቅ በሰባት ዓመታት ግዜው 20 መጽሐፍትን አሳትሟል። በአማካይ በየዓመቱ 2.8 መጻሕፍትን ። 👌የመንፈሳዊ መጻሕፍትን የሚጽፈው እጅግ ምርጡ ጸሐፊዬ ዲያቆን አሸናፊ መኮንን ከ1998ዓም ጀምሮ 43 መጻሕፍትን በ17ዓመታት ውስጥ አሳትሟል። በዓመት 2.5 መጻሕፍትን ለአንባቢያን አቅርቧል ማለት ነው። የእነዚህን ሁለት ኢትዮጵያዊ ፀሐፊያንን ያህል በአማርኛ ሥነ-ፅሑፍ የመጻፍና የማሳተም ታሪክ ውስጥ የእነርሱን ያህል በወጣትነት ዕድሜያቸው በማያበረታታ አንባቢና እንደልብ የሚገኝ አድናቂና አበርች የህትመት ዎጋ ቅናሽና አማራጭ አቋራጮች በሌለበት ሀገር ላይ ጀብደኞቹ ደማማቅ ታሪክንና የህይወት ዘመን አሻራቸውን እየጣሉ ቀጥለዋል🙏❤💪! የኔ ጀግኖች ናቸው🙏❤ ዲ አሸናፊ ከዘለዓለም ጋር ሲነጻጸር ቢከተለው እንጂ በዓመታዊ ግመታ የማሣተም ንጽጽሩ/ሬሾው/አይደርስበትም🙏 ዘለዓለም በኢትዮጵያ የአማርኛ ድርሰቶች ታሪክ በወጣትነት ዕድሜው በሳል እና የመታተም ተከታታይነታቸው ሳይንገራገጭ በሰባት ዓመታት ውስጥ 20 መጻሕፍትን ለተደራሲው ማድረሱ እኔ ባለኝ መረጃ አስደናቂና ብቸኛው ባለታሪክ ያደርገዋል💪❤🙏 በነገራችሁ ላይ በሠይፉ ፋንታሁን ሾው ላይ ሲቀርብ በምናየው የአፍሪካ ድንቃ ድንቅ ላይ ሊመዘገብና ምስክር ወረቀት ሊሰጠው የሚገባው ድንቃይ ደራሲና ፀሐፊ ነው ዞላዬ💪❤ (ምርቃቱ ከመከወኑ በፊት በርካታ ተመልካች ባለው ሠይፉ ሾው ላይ ደራሲውን ዘላለምን እባካችሁ እንዲቀርብ ጠቁሙና ምስክር ወረቀቱን አሠጡልኝ?🙄❤👌🙏...እኔንም ሠይፈዲን ስለ ጀብደኛ ስራዎቼ እንዲጠይቀኝ አስደርጉ🙄😁😀 በነገራችን ላይ 🤔እኔምኮ የአፍሪካ ድንቃድንቅ ቢመዘግበኝ ይቻላል🙏🙄ግን ማን ነው[ልጎርርባችሁ እዚች ጋር] 53 ክህሎት/ችሎታ ያለው አፍሪካዊ? የራሱን ፊደል ያለውን ቋንቋስ የፈጠረ አለ?😂 እረ እኔንም አስመዝግቡና ከተመዝጋቢዎቹ እኩል አድርጉኝ🙏🙄😂 እናም ከዚህ ታሪከኛ ደራሲ ዘለዓለም የሳጥን ወርቅ ስራና የኔም የጎበዝ ተማሪዎች 16ኛው ዙር ሽልማት መርሐ ግብሬ በአንድ አዳራሽ 20ኛውን ዝም መጽሐፉ ምርቃት ጋር ሊከወን ኀዳር 15/2016ዓም በኢፕድ አራት ኪሎ ላይ ቀጠሮ ተይዟል። በዕለቱ እጁ ላይ ያሉትን የቀድሞ መጻሕፍቶቹንም ይዞላችሁ ይመጣል። ከረፋዱ 3:00ሰዓት ጀምሮ የምረቃና ሽልማት መርሐ ግብሩ 9:00ሰዓት እስኪጀመር ድረስ በሽያጭ ላይ ይቆያል🙏❤ መጽሐፍቶቹን እኔ ወድጄያቸዋለሁ። በርግጠኝነት አትቆጩበትም ምርጫዬን ተስማምታችሁ ብትወስኑ ፈጽሞ የቁጭት መንፈስ አይጎበኛችሁም💪🙏❤ እውነት❤! መርሐ ግብሩ ላይ እንድትገኙ ተጋብዛችኋል❤🙏 በዕለቱ የሚመረቀው መጽሐፍትን ለመግቢያነት የግማሹን ዎጋ በጌቱ በቀለ የጎበዝ ተማሪዎች ሽልማት ድርጅት ክፍያው ተፈጽሞላችኋል❤🙏 አንብቡ። እናብብ🙏❤ ማንበብ አለማወቅን ይገልጻል👌
Show all...
ዜና.aac12.04 MB
ምክረ ሀሣቤ #4 ይሄ ታሪክ በወጣት ዕድሜ ውስጥ ላላችሁት እጅግ አስገራሚውና ድንቁ ዜናችሁ ነው👌አንብቡልኝ🙏? ዘመናዊ የድርሰትና ስነ-ጽሑፍ ታሪክ ፈር ቀዳጆቹ ጎምቱ ስራዎች-በጉለሌው ሠካራም አጭር ልብ ወለድና ጦቢያ የረዥም ልቦለድ በተሠኙት ድርሰቶች ኢትዮጵያ ሠማይ ስር የደራሲነት ስራ ከተጀመረበት መቶ ምናምን ዓመታት ውስጥ እስከዛሬ በኢትዮጵያ የሥነ-ጽሑፍ ታሪክ ውስጥ ይህን አይነት ጀብድ የተገበረ አንድም ደራሲ አልታየም🙄🤔👌🙏 አንድም!👌 ደራሲ ዘለዓለም የሳጥን ወርቅ ብቻ አድርጎታል። ጀብዱ 🤔የወረቀት ዋጋው ...አንባቢ የለም በሚባልባት ኢትዮጵያ ሠማይ ስር ነው ይህ ጀብድ ባለፉት ሰባት የጠራራ ፀሐየ-ዓመታት ውስጥ ሲከወን ያመተዉ። ጀብደኛው ወጣት 20ኛውን -ዝምታ -የተሰኘ የአጫጭር ልብወለድ ድርሰቱን በ2016ዓም የጥቅምት ወር ለንባብ ያበቃል። እየመጣ ነው። በጉጉት እየጠበኩህ ነው ዞላዬ🙏 ከ100ምናምን ሚሊዮናት ሕዝባ-'ዳምወሔዋን ኢትዮጵያውያን ውስጥ ደራሲውን ከዛሬ በፊት ባሳተማቸው ስራዎቹ የምናውቀው አንድ መቶም አንሞላም አይደል? በሰባት ዓመታት ውስጥ በዓመት ከአንድ በላይ መጽሐፍ በተከታታይ ዓመታት ማሳተም ይከብዳል አይደል? ለዚያውም የደራሲያን ሞራል ያሳተሙትን ገዝተንላቸው አድንቀን በማናበረታታበት ሀገር ላይ? የዘለዓለም የሳጥን ወርቅ ብቻ ግን ችሎታል። አድርጎታል። ማናችንንም ሳይጠብቅ በሰባት ዓመታትና በወጣትነት ዕድሜው አስራ ዘጠኝ ድርሰቶች😍👌 አዎ ጽፏል። አምርቷል? እረ እንዴት ተቻለህ?🤔 በዚህ ወጣትነትን ተፈጥሮአዊ የዕድሜ ጥያቄና ብዙ ውጥንቅጥ አንቆ መላወሻ ባሳጣው ትውልድ ዘመን ላይ?😍 እኔ አስሮቹን ስራዎቹን አንብቤለት ተደምሜበታለሁ። በኢትዮጵያ የስነ ጽሑፍ ታሪክ ውስጥ እስከ ዛሬ ካነበብኳቸው ደራሲያን መካከል ሁለተኛው ቃላት የሚያሸረግዱለት የደራሲነት ዛር የሰፈረበት የጥበብ አዶከርቤ የሚያዛብረው አይደክሜና አይታክቴ የስነ ጽሑፍ ባለ አውሊያ አልታደልንም እንጂ እንደ አንበሳ ዙ ግቢ አበጃጅተንለት በትውልዱ እስከ ህቅታው ድርሰቱን እያመረተ ለአርዓያነት የምንጎበኘው የክፍለ ዘመናችን የኢትዮጵያውያን የስነ ጽሑፍ ትውልድ ሽልማታችን መሆኑን አምነን በተቀበልነው ነበር👌🤔😍🙏 ውድ አንባቢያን ከዛሬ በፊት ያወጣቸውን ከታች የተዘረዘሩትን አንብባችሁ ፍረዱኝ👍🙏🤔 1.እፀሳቤቅ 2007 2 .እፀጳጦስ 2008 3.እፀሲና 2008 4.ብኤልዜቡል 2008 5.ሊተቶስጥራ 2009 6.ሽርፍራፊ ልቦች 2010 7.ፍካት እና ንጋት 2010 8.የህይወት ዋጋ 2011 9.ሰውነት 2012 10.ፊት እና ኋላ 2012 11. አዳፋ ነፍሶች 2013 12.እንደፍቅር 2013 13 .አውነት 2013 14.አሁን2014 15.የነፍስ ዜማ2014 16.ጌጣም አልቦዎች2015 17.ልጃገረድ ልብ2015 18.የህይወት ህግ2015 19. ትርታ 2015ዓም በየመጽሐፍት መደብሩ ጠይቋቸው! ቪቫ ዞላ🙏💪👌😍
Show all...
ምክረ ሀሳብ #፫ ይድረስ የቁም ሬሳ ቃዣቴያም ሰው መሳይ በሸንጎ ለሆናችሁት ራሳቸውን በገዛ እጃቸው ለሞት አሳልፈው ለሚሰጡ የወደፊቱ ሟች የሁለት ዓለም ተሸናፊዎች። በርግጥ ሁለቱ በማስፈንጠሪያው ውስጥ ያኖርኳቸው ሟቾች ፍጻሜ ያሳዝናል💔😭 ግን ለምን ብዬም እጠይቃለሁ። መልስ እነርሱ አይሰጡኝም ለቁም ሬሶች ግን ለምኔን እንዳትረሱብኝ🙏🤔😘 ፈራጅና ኮናኝ ማን ነው? ክርስቶስ ኢየሱስ አይደለምን? የሚል የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ባውቅም... በሀይማኖት ተቋሜ ስሰበክ ከሰማኋቸው ትምህርቶች ውስጥ ሀሌታው"እኛ ሕንጻ እግዚአር ነን፣ የእኛነታችን ባለቤት ፈጣሪ ነው።... በእራሳችን ላይ እንኳን ግድያን መፈጸም ኃጢአት እንዲሰለጥንብን መፍቀድ ከኃጢአት ሁሉ የከፋው እና ባለቤቱን እግዚአርን ከመናቅ እኩል ነው...ወዘተ" ተብዬ ተምሬያለሁ። እኔ በበኩሌ የፈለገ ጨለማም የህይወት ጥጎች በኑረት ገጾቼ ላይ ለበረከቱ ጊዜያት ቢያልፍ እንኳ ራሴን ተሸናፊ በማድረግም እጅ ሰጥቼ በራሴ ላይ የሁለት ሞትን አዋጅ አላውጅም። በፍጹም። እጅ ልሰጥና ልሸነፍ ወደ ዓለም አልመጣሁም። ራሳችሁን ለማጥፋት ያኮበኮባችሁ ተስፋ የለኝም ባዮች አንድ ግዜ ይሄን መልዕክት አንብቡ🙏👌 አለም ረስቷችሁ ብቻችሁን ብትቀሩ እንኳ በፍጹም ተስፋ እንዳትቆርጡ። ዙሪያ ገባችሁ ተስፋ በሚያስቆርጡ ዝባንዝኬዎች ቢከበቡ እንኳ ጥቂት የማምለጫ ቀዳዳ ባለቤታችሁ እግዚአብሔር አዘጋጅቶ ይጠብቃችኋልና ለምን ተውከኝ ብላችሁ ቀና በሉና አነጋግሩት። ማምለጫችሁን ታገኙታላችሁና። እባካችሁ የእንዲህ ያለ ክፉ ቀን ማምለጫ ስንቃችሁም እንዲሆን ከመጋጊጫ እና ምግብ ወጪ ማውጣት ጎን ለጎን ለመጽሐፍት ሸመታም ዎጋ ክፈሉና አእምሮአችሁን መግቡት። ንባብና ጥበበ-ዕውቀትን የተራበና አሰስ ገሰስ የታጨቀበት አእምሮ ችግር ሲገጥመው ሁሌም የሚታየው አልቆልኛል። ተሸንፌያለሁ። እጅ ሰጥቻለሁና...ወዘተ የውድቀት ልዘናዎችን እንጂ የማሸነፊያና የማምለጫ ኮዶቹ የተቆለፉና መላ የለሽ ሆነውብት ነው። እባካችሁን የሚያጸኑንና የሚያጽናኑን አበርች እንዲሁም አይዞህ/ሽ ባይ ቃሎችን ከእምነትና ሌሎች የስነልቦና መጽሐፍቶች ውስጥ በደህናው ጊዜ አንብበን እንያዛቸው። ራሳቸውን የሚገድሉ ሰዎች ራሳቸውን የማያከብሩ አምላክን ያህል ሀብታምና መልካም አባት እንዳላቸው የማያውቁ የድንቁርና ሸረሪት ድር አእምሮአቸውን ተብትቦ የደፈነባቸው ሰው መሳይ በሸንጎዎች ናቸው። እኔ አባት አለኝ በሚገጥሙኝ ፈተናዎች ሁሉ ተምሬበት እንጂ ተሠብሬበት የትም እንዳልቀር ጎኔ በጠራሁት ጊዜ ሁሉ ጎኔ የሚቆም አባት። እግዚአር ይባላል ተዋወቁት❤💪🙏👌😍 እግዚአብሔሬ የማላልፈውን ተፈትኜ የምወድበትን ደቅቄ የምሞትበትን ፈተና እንድጋፈጠው ብቻዬን የፈተና ቦክስ ናዳ በሚወርድብኝ ሪንግ ውስጥ ብቻዬን ያለ ፎጣ አቀባይ ላብ አድራቂ አጋር ትቶኝ መቼም አይተወኝም። ትከሻዬን መታ እያደረገና እያሻሸኝ አይዞህ እያለ እንፋለምለት ባለድል ሆኜ እንደ ወርቅ ተፈትኜ ሊጥለኝ ሊገድለኝ የሚታገለኝን መከራዬን ድል አድርጌ አሸንፌ የድል አክሊሌን ሜዳሊያዬን ተሸልሜለት እንዳንጸባርቅለት እየቶፈዘ ያበረታታኛል እንጂ ለፈተናዬ ጥሎኝ እስካሸንፍለት የትም ንቅንቅ አይልም። ስፈተንም ጎሽ የኔ ጀግና ትችለዋለህ አሸንፈህ ትነሳለህ እንደወደቅክማ አትቀርም ብሎ ያጀግነኛል እንጂ ለፈተናዬ አሳልፎ ሰጥቶኝ እኔ ልጁን ውድ ሀብቱን ጥሎኝ የትም አይሄድም። https://www.facebook.com/100008399136504/posts/pfbid0swGDq2VLMgQP3DF9F7PNe4YnGzYBu638Cvt3haxCfC8xTqh1Cf2Vep7yi8apMVgwl/?app=fbl https://www.facebook.com/100003670681270/posts/pfbid02yvzDD6farfeA4NL3WDQbVmqFzU2EL8f4Qo2K42B4H8iTbpPb7GYkBAYTSQiTbiLbl/?app=fbl
Show all...
Log in or sign up to view

See posts, photos and more on Facebook.

የጓዳ ወሬ🤔❤ ዛሬ እኛ ቤት በጓዳችን ይህ ሆነ🙏 ፲፬ኛው ዙር የሰብ ንባበ-ሁለንታ ሕይወት ወርሐዊው የወሩ የመጀመሪያው ሰኞ መርሐ ግብራችን የልጅ ኦፍታናን ታሪከ-መጽሐፍ ነበር የገለጸው። ሸጋ ግዜን አሳልፈናል። ኦፍታና የ11ዓመት ታዳጊ ነው። እርሱም ታሪክ አለው። አልተጻፈለትም እንጂ። በቃሉ ዛሬ ነግሮናል
Show all...
14ኛው_ሰብ_ላይብረሪ_የልጅ_ኦፍቲ_ታሪክ.aac64.70 MB
Choose a Different Plan

Your current plan allows analytics for only 5 channels. To get more, please choose a different plan.