cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

"ግጥሞች"

በየዕለቱ አሪፍ አሪፍ ግጥሞች ይቀርቡበታል ከወቅቱ ጋር የሚሄዱ ግጥሞች ይለቀቁበታል መንፈሳዊ ግጥሞችም ምርጥ ምርጥ የፍቅር ግጥሞች ብቻ ምን አለፋቹ ገብተው ዕዩት ፡ ፡ ፡ ሀሳብ አስተያየት ካላቹ @abitanu @tarikachew #Cross @abitanu

Show more
The country is not specifiedThe language is not specifiedThe category is not specified
Advertising posts
241
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

አንቺ ከሄድሽ ወዲ . . አንቺ ከሄድሽ ወዲ ናፍቆት በሹል መርፌው እየጠቀጠቀ ለየዋሁ ልቤ ስቃይ እያረቀቀ እማላገኝሽን እማላገኝሽን አንቺን አምጣት አለኝ እሷን አምጣት አለኝ ቆራርጦ አፈራርሶ ካፈር ሊያዳቅለኝ እስትንፋሴን ነጥቆ ከጉድጓድ ሊጥለኝ አንቺ ከሄድሽ ወዲህ መሰለኝ መቃብር ያለሁበት ሰፈር ዘልዬ ቦርቄ ያደኩበት መንደር ደሞም ባከባቢው የሚወጣው ድምፀት የሚሰማው ጩኸት መሰለኝ የሲኦል ጫጫታ'ና ሁካታ፥ የአጋንንት ፉጨት የሐጣን ዋይዋይታ፥ የሐጥአን እሪታ... እንዲም አስባለሁ ሰፈርተኛው ሁሉ ሞልቶለት ሲዘክር ይመስለኛል የኔ የአርባዬ ተስካር የሰማንያ ተስካር ሙት አመቴን ማውሻ እኔን ማስታወሻ ደግሶ ማልቀሻ... አንቺ ከሄድሽ ወዲ አለሜ በሙሉ ተመሰቃቀለ ሁሉ በኔ አየለ ህሊናዬ ዛለ ዋለለ ቆሰለ መላው ሰውነቴም ነደደ ከሰለ ከሰለ . . እንደው ባጠቃላይ አንቺ ከሄድሽ ወዲ ምናለ ያልሆንኩት ምናል ያላረግሽኝ አንድ ጊዜ ሄደሽ አስሬ ገደልሽኝ!!! ማይክል ሰለሞን (የቡዜ ልጅ)
Show all...
ፍቅርን ❤️ ፩ብዬ ስጀምር ገና ከጥንስሴ በሆዴ የዘለልክ አንተ ነበርክ ፅንሴ:: በፍቅር❤️ ብወልድህ ከሆዴ ብትወጣ ከልቤ ካንተ መማር ፈለኩ ዙሪያህን ከብቤ:: አንተኮ❤️ የአፌ መፍቻ ነህ ሀ ሁ መጀመሪያ ሽፋሽፍቴን ስገልጥ ቀኔን ማሳመሪያ:: የጥርሴ ፈገግታ የሳቄ ጅማሬ ስትስቅ እያየሁኝ የምስቅ አብሬ:: ሳቅ እንደበፊቱ እንዳምና ካቻምና በሳቅህ የምስቅ የአብራክህ ነኝና:: ገና ስትፈግግ ነው ልቤ የሚዘለው ድምፅህን ሲሰማ ነው ደምስሬ ሚሠራው:: ያኔ መጀመሪያ❤️ ልቤ ውስጥ ስትገባ ስትበላው አንዠቴን መች እንዲህ መሠለኝ ሀሴት ምታለብሰኝ በእቅፍህ አዋዝተህ ደስታን ደረብክልኝ:: ታዲያ የኔ ፍቅር❤️ አመቴን አደለም እድሜዬን ውሰደው ዘላለሜን ወስደህ በፍቅር አንገላታው ባንተ ውስጥ መኖርን እንደ እድል ነው ማየው:: ብቻ ያቺን ቀን ባረኳት አንተን የሰጠችኝ በውስጤ ባካሌ እልፍ አመት ኑርልኝ:: @biscute
Show all...
sticker.webp0.29 KB
••●🍃 ኢትዮጵያዊ ነኝ! ●🍃 ,,,,,,,,,,,, ለሀገሬ ሞቼ ሀገር የማኖር ሞት ማልፈራ ከቶ ማልበገር ኢትዮጵያዊ ነኝ! ሞተ ሲሉኝ ምገኝ በደም አሻራ በአንጥንት ክስካሽ የድል ፍና ወጊ ሁሌ ፈጥኖ ደራሽ ኢትዮጵያዊ ነኝ! ሞተ ሲሉኝ ምገኝ የሰው ዘር መገኛ ቀደምት ስልጣኔ ችጋር ያበረታኝ የኖርኩ በጠኔ ኢትዮጵያዊ ነኝ! ሞተ ሲሉኝ ምገኝ አለም በጀግንነት ሞቼ የማይረሳኝ ህያው ሆኜ ምኖር ሁሌ የሚያወሰኝ ኢትዮጵያዊ ነኝ! ሞተ ሲሉኝ ምገኝ ክብሬ ሳይሆን ክብሯ ሚያስጨንቀኝ ✍ ቶፊቅ መሀመድ @Tufaw_muhe ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
Show all...
የተወደዳችሁ የቻናላችን ተከተያዮች እንደምን ከረማችሁ ራሳችሁን ከኮሮና ቫይረስ እየጠበቃችሁ እንደሆነ ተስፋ እያደረግን ልናዘጋጅ ባሠነብነው የግጥም ውድድር የናንተን ሀሣብ ልንሠማ ወደድን ፡፡ ይዘጋጅ እንሳተፋለን የምትሉ ወንድም እህቶቻችን ታች ባለው User name ላይ ይዘጋጅ ብላችሁ ላኩ ከኛ ጋር ስለሆናችሁ እናመሠግናለን፡፡ 😍😍😍😍 👇👇 @Abitanu
Show all...
መንግስት ብሆን ኖሮ በአስቸኳይ ግዜ አዋጅ የተደረገ አስቸኳይ የምርጫ ቅስቀሳ! (ሀይሌ አበባው አክሊሉ) . . . ቴዲ አፍሮ ድምፅ ሰቶኝ ፣ መንግስት ብሆን ኖሮ፤ ባገሩ አይሰማም ፣ እዬዬ እና እሮሮ ከቻልኩ በሪሞት ፣ ድምፁን ቀንሳለሁ ካልቻልኩ በፌደራል ፣ እደመስሳለሁ ወጣት ተብዬውም ፣ በመንጋ ተነድቶ ፣ እንደዚ አይፈነጭም ከታሪክ ፡ ድል እንጂ ፣ ቁጭት አይመነጭም፤ ።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።። ምርጫ አሸንፌ ፣ መንግስት ብሆንማ፣ አይኖርም ነበረ ፣ ሽብር እና አድማ ለውጥም እንዳቢዮት ፣ ልጇን አትበላም መንገድ ላይ አጋድማ፤ ማንም በዘር በዘር ፣ እንዲ አይደራጅም ሰፊ ሀገር ሳለችው ፣ በመንደሩ ጠቦ እንደዚ አይፋጅም፤ ........................................ ግድቡም እስካሁን ፣ አይንዘላዘልም ግብጥም ይሄን ያክል ፣ እኛ ላይ አትዘልም ጣናም እንደዛሬ ፣ እምቦጭ አይወርሰውም ህዝብ እንደዘንድሮ ፣ ሆዱን አይብሰውም :::::::::::::::: የምዬንም ሀውልት ፣ ማንም ሲነሽጠው ካላፈረስኩ አይልም ፣ የጅ ፡ የግሩን ስሰጠው ወስዳቹ ብትጥሉኝ ፣ እኔን አራት ኪሎ መንገድ አይዘጋም ፣ በክልል ጫጫታ ፣ ጦቢያ አትዘነጋም ንብረትም አይወድምም ፣ የለም ማፈናቀል ጅምላፍርድ ይቀራል ፣ ነውር ነው መበቀል ግፍ በግፍ አይገስፍም ጀግና አይቀሰፍም ምንም አይነት አርቲስት ፣ በእጆቹ ካልሆነ በሰው እጅ አይሞትም፣ ይንበርስቲ ህዳ ፣ ሴት አትታገትም ድንገት ቢሆን እንኳን ፣ ጉዳዩ በቶሎ አይፎረገትም፤ ለጠባቦች 'ሚሆን ሰፋ ያለ አዕምሮ ፣ ከቻይና አዛለሁ ተመራቂዎችን ፡ ስራ ቢጠፋ እንኳን ፣ ስራት አስይዛለሁ፤ ።።...።።።.....።።።።።።.....።።።።... እንግዲ ህዝቤ ሆይ ፣ ተግተህ ብትመርጠኝ ይሆናል እንደዚ፣ ካልመረጥከኝ ክላ ፣ ጥፋልኝ ፣ ሂድ ከዚ እኔ ካልተመረጥኩ ፣ ሀገር አትኖርም ዘራፍ!ዘራፍ! ብዬ ፣ ብዙም አልደነፋም በሻማ ቢፈለግ ፣ እንደኔ የሚሆን ባገር አንድ አይጠፋም። . . ህፃናት ከማይደርሱበት ደረቅ ቦታ ቁጭ ብለው ያንብቡት!! 💚💛❤ 💚💛❤ ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
Show all...
05፨2012 #001 መሠልጠን መሠይጠን😒😒 የዘመን ቱሩፋት ልቡን ያሣበጠው የአጀብ እልልታ ኮንኖ ያስኮፈሰው ግና ጉራ ብቻ እውቀት እንደው ባዶ ነገን ማያዘልቀው ከዚህ ቢሄድ ማዶ ቀስቅሶ ሚያነሣው የፌሽታ መንጠቆ ኀላ ሲጠፋበት ይቀራታል ማቆ መሠልጠን መሠይጠን ይኸው በሡ አየው ከፍ ዝቅ አድርጎ ራሡን ሲያረክሠው የመንፈሱን ክብር በብጫቂ የለካ በለቅሶ ዋይታ እሡ ግን ያስካካ ለማ መስሎት ይሆን ሚደልቁት ደረት ገና ሳይሞት በፊት የተላቀሱለት ሰዋዊነት ጠፍቶት መንፈሱ ቀለለው ሚያለቅሡት ለሡ ነው በድኑን ለቀረው እየላላ መጥቷል ያስተሳሰረው ድር ከጫንቃው አልወርድ አለ የሀጢአቱ ክምር ታዲያንስ ለዚህ ሠው ብልጭልጭ ለገዛው በስልጣኔ በር ከውስጥ ለታሠረው የአእምሮ ስካር ውስጥ ለሚወዛወዘው የህይወቱ አቋም ለተጠማዘዘው ምንድነው መፍትሄ ሚያድነው ምን ይሆን ከዚ ህይወት አውጥቶ ሚያሣየው ብርሀን ሚያድነው አንድ ነው ሀሳቡን ይሠብስብ ፀሎቱንም ያድርስ መልካምነት ያንግብ ይሄ ነው መፍትሄው የሡ መፈወሻ ጎትቶ ሚያወጣው ከዛ ከቆሻሻው ✍ ኮዜት_ዳንኤል
Show all...
።።።።።።። ምከሩኝ ።።።።።።።። ከውቢቷ ሸገር አስፓልት ዳር ቆሜ ፈዝዠ ቀረሁኝ አንድ ህልም አልሜ እንደሀገራችን እንደ አማርኛ ፊልም ስኮመኩም ነበር የማይሳካ ህልም አንዲት ቆንጆ መጥታ በውድ መኪና በፊትተኛው መብራት ነካ ታርገኝና እንደዚህ ደንግጣ ወስዳኝ ሆስፒታል ልትሰጠኝ ስታስብ ቻፓ በፔስታል እኔ ኮ ደህና ነኝ አይሆንም ስላልኳት እንባ በአይኗ ሞላ ከኔ ፍቅር ያዛት ወይ ደግሞ በድንገት የሞተው አባቴ ድክም ካለችው ከደሳሳ ቤቴ የድሮ ጓደኞቹ ለጋራ ሚሰሩት ከውጭ ይመጡና ድርሻውን ይዘውት ድንገት አግኝተውኝ በፎቶ አመሳስለው ሃምሳ ሚሊየን ብር ያባትህ ድርሻ ነው ብለው እንዲሰጡኝ ቆሜ ከአስፓልት ዳር ስጠብቅ ብቆይም እዛው ውሎና አዳር እንኳንስ የምትገጭ ፍቅር የሚይዛት ጎማዋ ተንፍሶ ወይ ነዳጅ አልቆባት በትሽ ጀሪካን ሮጨ አምጥቸላት ያዘጋጀሁት ቀልድ ምን ብዬ ላስቃት ልሄድ ይቅርና ስልክ ተቀብያት መብራት እንኳን ድንገት ትንሽ ሲያስቆማቸው መስታወቱ ዝግ ነው ድሃ እንዳያያቸው ወይም የኔ ቢጤ እንዳይለምናቸው እኔም አርቲስቶችን በጣም ታዘብኳቸው መሬት ላይ የለለን ምን አስተወናቸው እኔስ ተስፋ አልቆርጥም እቀጥለዋለሁ ደግሞ ህንድ ሄጄ አረጋግጣለሁ ድሃ የሚወዱ ብዙ አክተር አውቃለሁ ባዶ ኪሴን ሄጀ አፋጃቸዋለሁ ደስ የሚል ቀን ተመኘሁላቹ 😎@Dagiye1219 😎@Dagiye1219 😎@Dagiye1219
Show all...
05፨2012 #002 #ዓለም ተቀልብሳ!🙃 ይኸኛው ፅንሰ ሀሳብ፣ ያሁኑ ቲዎሪ፣ ጥንተ መሰረቱን፣ ያኛውን ሲጥለው፣ ያሁን መዳረሻ፣ ነባሩን ሲያፈርሰው፤ ይኼኛውም ጣዪ፣ ያኛውም ፈራሽ፣ ሁሉም በየጊዜው፣ ሁሉንም ቀልባሽ፤ ወይ አለመታደል፣ አወይ የኛ አበሳ፣ ዓለም ወድቃ ቀረች፣ ዓለም ተቀልብሳ፤ ጥንተመሰረቱን፣ ጠፍቶ የሚያነሳ። ዮናስ ኃ/ገብርኤል
Show all...
የአራዳ ጉርሻ (ናትናኤል መስፍን እንዳለ) ------------------------------------- በመዳፌ ሙሉ እንጀራ በሽሮ ባጎርሰው ጠቅልዬ አይን አይኑን እያየሁ ከሳህኑ ስጋ ያጎርሰኛል ብዬ እርሱ ግን አራዳ እንዳይሰጥ ሰስቶ እዳይተወኝ አፍሮ ጠቅልሎ አጎረሰኝ በሰፊው መዳፉ ከኔው ሳህን ሽሮ::
Show all...
Choose a Different Plan

Your current plan allows analytics for only 5 channels. To get more, please choose a different plan.