cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

✝️Orthodox✝️

ተዋህዶ ለዘላለም ትኑር 🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏

Show more
The country is not specifiedThe language is not specifiedThe category is not specified
Advertising posts
145
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

ገጣሚ፦ማኅሌት ዳንኤል ከ ቅዱስ ዮሀንስ አፈወርቅ ንግግር የተወሰዶ በማኅሌት ዳንኤል የተገጠመ @liyuzema
Show all...
2.77 KB
...........👇 ሰው በራሱ ደስታኛ ካልሆነ ነው ከብዙ ሰው ጋር እሚጣላው…አብዝቶ እሚከራከረው…ያለ ምክንያት እሚነጫነጨው… ሰው ከራሱ ጋር ሳይስማማ ሲቀር ነው ብዙ ስህተቶች መስራት እሚያበዛው…ሌሎችን መውቀስ እሚያበዛው… ለምን እንደሆነ እኔም አላውቅም…ግን እኔም ብዙ ጊዜ ደስ አይለኝም…ለዛም ነው መሰለኝ ስህተቴ የበዛው… @liyuzema
Show all...
ቡሄ ሆያ ሆዬ ልበል ልጨፍር ላዜመው ዱላዬን ሸክፌ ከእረኞቹ ጋራ እስቲ ላንጎርጉረው አውዳመት ነው ዛሬ "ቡሄ" ብርሀን በራ የጌታ መለኮት ለ አለሙ ይብራ ችቦውን ለኩሱ ፈልጉ ልጆቹን ሙልሙሉ በመያዝ ቃኙ እረኞቹን ጅራፍን አጩሁ መስክሩ እውነቱን የጌታን መገረፍ ስቅለት እና ሞቱን ድምፁንም አሰሙን ምስክርነቱን እኔም ልመስክረው የተረከብኩትን ከዘመን ዘመናት የመጣ ትውፊትን ልበል "ሆያ ሆዬ" በ "ሆ" ተቀበሉኝ ሙልሙሌን ወስጄ ልመርቃችሁኝ ገጣሚ፦ማኅሌት ዳንኤል @liyuzema @liyuzema
Show all...
"ከመጸለይህ በፊት ተመስገን በል። ስለሁሉም ነገር አመስግን...በረከቶችህን ቁጠር! ጠዋት ገና ከእንቅልፍህ ስትነቃ....አይኖችህን ስትገልጥ <<ተመስገን>> በል!!!...ሞተህ ልታድር ትችል ነበርና!!! ደግሞ ከአልጋህ ወርደህ መሬት ስትቆም……‹‹ተመስገን>> በል! በሆነ ምክንያት የአልጋ ቁራኛ ሆነህ ልትቀር ትችል ነበርና!!! በየትኛውም መንገድህ ላይ አመስግን። ምስጋና ቢስ አንደበቶች ልመናን ሲያሻግሩ ለዛቸውን ያጣሉ!" ደራሲ ስብአት ገብረ እግዚአብሔር Share share @liyuzema @liyuzema
Show all...
"የራስህን ኑሮ ለማስተካከል ብለህ የሌሉችን ኑር አታበላሽ ፤ . . .የራስህን ኑሮ ለማጣፈጥ ብለህ የሌሎችን ኑሮ ልክ እደ ጨው አትጠቀመው ፤ . . . በሰዎች ህይወት ውስጥ ጣልቃ አለመግባት በራሱ ሰዎችን እንደመርዳት ነው!" @leyuzema
Show all...
ኢትዮጵያዊነቴን እንዲነጥቀኝ ለማንም አልፈቅድም። ለኔ ብሔር እንደ ካልሲና ኮፍያ ተጨማሪ ጌጥ ነው አገር ግን ሙሉ ልብስ ናት ። ሰው በካልሲና ኮፍያ አደባባይ አይወጣም ። ብሄርም እንደዛው ነው ። አገሬን ለብሼ ግን ዓለምን እዞራለው። ( አትሌት ቀነኒሳ በቀለ ) 💚💛❤️ @liyuzema
Show all...
ቡሄ ማለት ምን ማለት ነው ? ችቦ ለምን እና መቼ ይበራል? ሙልሙል ልምን ይታደላል? በቡሄ ወቅት ጭራፍ ለምን ይጮሃል ? #ቡሄ ቡሄ ማለት ብራ፣ ብርሃን፣ ደማቅ ማለት ነው፡፡ ጌታችን ብርሃነ መለኮቱን የገለጠበት በዓል የሚዘከርበት እና ለበዓሉም ችቦ ስለሚበራ የብርሃን በዓል በማለት የቡሄ በዓል እንላለን፡፡ ወቅቱ የክረምት ፤ጨለማ አልፎ የብርሃን የሚወጣበት፤ ሰማይ ከጭጋጋማነት ወደ ብሩህነት የሚለወጥበት የመሸጋገሪያ ወቅት ነው፡፡ “ቡሄ ከዋለ የለም ክረምት፤ ዶሮ ከጮኸ የለም ሌሊት” እንዲሉ፡፡ በሌላ በኩልም “ቡኮ/ሊጥ” ተቦክቶ ዳቦ የሚጋገርበት “#ሙልሙል” የሚታደልበት በዓል በመሆኑ ቡሄ ተብሏል፡፡ #ጅራፍ በደብረ ታቦር በዓል በትውፊታዊ መልኩ የሚታየው ምስጢር፤ በኢየሩሳሌም ስለሚሆነው የጌታችን ምስጢራዊ ሞቱ ነው፡፡ ጅራፍ መገመድ(መጥለፍ) እና ጅራፍ ማጮኽ ሁለት ዓይነት ምስጢር የያዘ ትውፊታዊ ተግባር ነው፡፡ የመጀመሪያው ግርፋቱንና ሞቱን እናስብበታለን፡፡ ሁለተኛው ደግሞ ፤ድምፁን ስንሰማ የባሕርይ አባቱን የአብን ምስክርነት ቃል፤ እንደ ነጎድጓድ ድምፅ ያስታውሰናል፡፡ የጅራፍ ትውፊታዊነት /ውርስ/፣ መጽሐፋዊ ትምህርትና ምስጢር ጠብቆ ለትውልድ እንዲተላለፍ ለማድረግ ጨዋታውን በተራራማ አካባቢ፣ ከመኖሪያ ቤት ርቆና፣ በሜዳ ማድረጉ ጠቃሚ ነው፡፡ ጅራፍን #በርችት መቀየር የሚያመጣውን የምስጢር ተፋልሶ ብቻ መመልከት ከማኅበራዊ ጎጂ ገጽታው በላይ እንድናስወግደው ያስገድደናል #ችቦ ችቦ የጌታችንን ብርሃነ መለኮት መገለጥ የሚያመለክት ነው፡፡ በመሆኑም ችቦ ለኩሰን በዓሉን እናከብራለን፡፡ የዚህ ትውፊታዊ አመጣጥ በብርሃኑ ድምቀት የቀኑን መምሸት ያልተረዱ እረኞች በሜዳ ቀርተዋልና ወላጆች ከመንደር ችቦ ለኩሰው ልጆቻቸውን ፍለጋ ሔደዋልና ታሪኩን እያዘከርን በዓሉት እናከብራለን፡፡ የችቦው መንደድም ሌላ ትርጉም አለው፡፡ አንድ ምእመን ለሌላው ምእመን መካሪ አስተማሪ መሆኑን፣ መከራ እየተቀበለም አርአያ፣ ምሳሌ፣ ብርሃን መሆኑን ያሳያል፡፡ በሃይማኖትም አርአያ ምሳሌ ይሆንላቸዋል፡፡ ከዚህ ጋርም ተያይዘዞ ችቦ #በ13 ምሽት ይበራል ፣ብርሃኑ የተገለጠው በዚችው ዕለት ነውና ፡፡ #ሙልሙል በችቦ ብርሃን ልጆቻቸውን ፍለጋ የወጡ ወላጆች ዳቦ ጋግረው ይዘውላቸው ወጥተዋል፡፡ ስጦታው ቤተሰባዊነትን፣ ፍቅርንና መተሳሰብን መግለጫ ነው፡፡ ወደ ቤታችን “ ቡሄ ” እያሉ ለሚመጡ አዳጊዎችም፤ ዘምረው እንዳበቁ የሚሰጥ “ሙልሙል” ዳቦ አለ፡፡ ሕፃናቱም ሊዘምሩ ሲመጡ ዳቦ መስጠት ልማዳዊ ብቻ አይደለም፡፡ ሕፃናቱ የደቀመዛሙርት ምሳሌ ናቸው፡፡ መዝሙራቸው ደግሞ ሐዋርያት “የምሥራች” ይዘው የመምጣታቸው ምሳሌ ነው፡፡ ሐዋርያት በገቡበት አገር አስተምረው አጥምቀው የጸጋ ልጅነትን አሰጥተው በረከት አድለው እንደሚሔዱም፣ ልጆችም ዘምረው፣ አመስግነው፣ መርቀው “ውለዱ ክበዱ፣ ሀብት አግኙ፣ የመንግሥተ ሰማያት ወራሾች ያድርጋችሁ ….” ይላሉ በአጠቃላይ በዓለ ደብረ ታቦር ከእነዚህ ምስክር ካላቸው ትምህርቶቹ፣ ምሥጢር ከሚራቀቅባቸው ትርጓሜያቱና ከትውልድ ትውልድ በቅብብል በተላለፈው ቅዱስ ትውፊት ጋር ሃይማኖታዊ ባሕል ሆኖ ሊቀጥል ይገባዋል፡፡ ይህን ማድረግ የሚቻለው ግን አዳጊዎች ሃይማኖታዊ ትውፊቱን ይዘው እንዲያድጉ ጥቆማ በመስጠት፣ ግጥም በመግጠምና ምሥጢሩን በማብራራት የመጀመሪያዎቹ ባለድርሻዎች ወላጆች ናቸው፡፡ አንዳንድ ጊዜ የሚሰሙ ግጥሞች ስድብ፣ ፌዝና ሥላቅ የተቀላቀለባቸው ይሆናሉ፡፡ ሕፃናቱም ዝማሬውን ሲጀምሩ “ከሰጡን እንነሣ ከነሱን እናርዳ” ብለው ይጀምሩታል፡፡ ከሰጡን እንመርቃለን ካልሰጡን እንራገማለን በማለት፡፡ አሳሳቢው ነገር ደግሞ ሃይማኖታዊ ሥርዓቱን ወደ ገንዘብ ማግኛነት የቀየሩ ሁኔታዎች መታየታቸው ነው፡፡ ዳቦ /ሙልሙል/ ትምህርቱንም፣ ምስጢሩንም፣ ትውፊቱንም በአግባቡ ልንጠቀምበት ይገባል ከዚም ጋር ተያይዞ ሰንበት ት/ት ቤታችን ለበርካታ ዓመታት ሲወረድ የመጣውን የዝማሬ ሥርዓት ለአጥብያው ምእምን በየቤቱ በመሄድ የብሄን ዝማሬ ከነሥርዓቱ በመዘመር አገልግሎት ይሰጣል ፤የደብር ታቦርን በዓል በተመለከትም የወረቀት ጽሑፎችን ይበትናል በዝማሬ መኃል ያድላል ፡፡ ቤተክርስቲያን የምሥጢር ግምጃ ቤት ናት፤ የምታከናውነውን ሁሉ ከበቂ መረጃ ጋር ነው ተግባራዊ የምታደርገው ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇 •➢ ሼር // SHARE ✥┈┈•◦●◈◎❖◎◈●◦•┈┈✥ 💚 •✥• @liyuzema •✥•💚 💛 •✥• @liyuzema •✥•💛 💖 •✥• @liyuzema •✥• 💖
Show all...
ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ

✞ በየጊዜው አዳዲስ መንፈሳዊ ➢ ፅሁፎች ➢ መዝሙሮች ➢ ኦርቶዶክሳዊ መልእክቶች ➢ መንፈሳዊ ነገሮችን ሁሉንም ለማግኘት ከፈለጉ ተቀላቀሉን ✞ ❑• @Z_TEWODROS •❒ ➢ ሁሉም እንዲያነበው SHARE ያርጉ ! እናመሰግናለን ! • እንዲሁም ግሩፓችንን የኪዳነምህረት ልጆች ይቀላቀሉ ❤! • @kidanameherat16 •

Choose a Different Plan

Your current plan allows analytics for only 5 channels. To get more, please choose a different plan.