cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

Ethiopia news

ኢትዮጵያን መውደድ ባትችል አትጥላት ማክበር ባትችል አታዋርዳት ማራመድ ባትችል አታዘግያት መጠበቅ ባትችል አትበትናት። ይህን በማድረግ ታሪክ ባትሠራም ታሪክ አታበላሽም።

Show more
The country is not specifiedThe language is not specifiedThe category is not specified
Advertising posts
824Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

አብይ አህመድ አሊ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ተሰየሙ❗️ ኢትዮጵያን ለቀጣይ 5 አመታት ሊመሩ ዶ/ር አብይ አህመድ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ተሰይመዋል። 6ኛው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና የፌዴሬሽን ምክር ቤት የምስረታና የመክፈቻ ጉባኤ እየተካሄደ ይገኛል ። የምርጫ 2013 አሸናፊው የሆነው " ብልፅግና ፓርቲ " እጩ" አድርጎ ያቀረባቸው  የፓርቲውን ፕሬዝዳንት ዶ/ር አብይ አህመድ ነው   በዚህም መሰረት ከ2010 መጋቢት ወር ጀምሮ በጠቅላይ ሚኒስትርነት ሲያገለግሉ የቆዩት ዶ/ር አብይ አህመድ በምክርቤቱ ደንብ መሰረት በቀጥታ ተቀብሎ አጽድቆ የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ተሰይመዋል ። ዶ/ር አብይ አህመድ ኢትዮጲያን ለቀጣይ 5 ዓመታት ለመመራት ቃለ መሃላ ፈጽመዋል  ። #ዳጉ_ጆርናል
Show all...
በስድስተኛው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመክፈሻ ስነ ስርዓት ላይ አቶ ታገሰ ጫፎ ለኢፌዴሪ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ተደርገው ተሾሙ።በ419 ድምፅ እና በስድስት ድምፀ ተአቅቦ ተመረጡ #ዳጉ_ጆርናል
Show all...
ቃልኪዳን ገዛህኝ ሪከርድ ሰበረች❗️ በጄኔቫ በተካሄደው የ10 ኪሜ የጎዳና ላይ ውድድር ትውልደ ኢትዮጲያዊቷ ለባህሬን የምትሮጠው ቃልኪዳን ገዛህኝ የርቀቱን የዓለም ክብረ ወሰን አሻሽላለች። ያጠናቀቅችበት ሰዓት 29:35 ሲሆን ከቀድሞ ሪከርድ 5 ሰከንዶችን አሻሽላለች። በሚኪያስ ፀጋዬ #ጎል_ጆርናል
Show all...
በጌዴኦ ዞን ይርጋጨፌ ወረዳ በጣለው ከባድ ዝናብ የአንድ ሰው ሕይወት ሲያልፍ 39 አባወራዎች ከቤት ንብረታቸው ተፈናቀሉ! በጌዴኦ ዞን ይርጋጨፌ ወረዳ በሦስት ቀበሌ በጭቶ፣ በዶማርሶ እና ቡዱቅሳ በጣለው ከባድ ዝናብ የአንድ ሰው ሕይወት ማለፉን እና 39 አባወራዎች ከቤት ንብረታቸው መፈናቀላቸውን የይርጋጨፌ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ዮሐንስ ታደሰ ገልጸዋል። መስከረም 22 ቀን 2014 ዓ.ም በጣለው ከባድ ዝናብ ከ39 አባወራዎች 156 የቤተሰብ ብዛት እንደተፈናቀሉ አስተዳዳሪው ለዞኑ መንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ መረጃውን በስልክ አድርሰዋል። አደጋው የደረሰው መስከረም 22 ቀን 2014 ዓ.ም ከቀኑ ከ7:00 እስከ 10:00 ድረስ በጣለው ከባድ ዝናብ እንደሆነ የዶማርሶ ቀበሌ ነዋሪ አቶ ታምራት ብርሃኑ በስልክ በሰጡት መረጃ ገልጸዋል። ከቤት ንብረት የተፈናቀሉት አባወራዎች በቤተሰቦቻቸው እና በጎረቤት መጠለላቸውን አስተዳዳሪው መናገራቸውን ከጌዴኦ ዞን መንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። በአሁኑ ጊዜ የነፍስ አደን ሥራ እየተሠራ መሆኑ እና አደጋ በደረሰበት አከባቢ ያሉ ማኅበረሰብ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ አስተዳዳሪው መልዕክት አስተላልፈዋል። Via EBC
Show all...
በግጭት ምክንያት ተፈናቅለው ኮምቦልቻ ላይ ከሰፈሩ 320 ተፈናቃዮች ውስጥ 8 የሚሆኑ ነብሰ ጡር እናቶች በመጠለያ ጣቢያ ውስጥ መውለዳቸው ተነገረ! ከሰሜን ወሎ ሀራ ወረዳ ተፈናቅለው በኮምቦልቻ የሰፈሩ ተፈናቃዮች ቁጥር 321 መድረሱ ተነግሯል ። ከተፈናቃዮቹ ውስጥ 8 የሚሆኑት እናቶች በመጠለያ ጣቢያ ውስጥ የወለዱ ሲሆን በአሁን ሰራት 6 ለመውለድ የደረሱ እናቶች ናቸው ብስራት ሬድዮ በስፍራው ተገኝቶ እንደተመለከተው ከእነዚህ እናቶች በተጨማሪ 41 የሚሆኑት የሚያጠቡ እናቶች ናቸው ። የተፈናቃዮች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ እንደሚገኝም ተናግሯል ።ተፈናቃዮቹ ከሁለት ወር በላይ በመጠለያ ውስጥ አስቆጥረዋል ። የቢጂ አይ ኢትዮጲይ ኮምቦልቻ ፋብሪካ እነዚህኑ ፣በኮምቦልቻ ፣ ደሴ ከተማዋ እና ዙሪያዋ ለሰፈሩ ከመኖሪያ ቀዬአቸው ለተፈናቀሉ ዜጎች ድጋፍ አድርጓል። ናትናኤል ሀብታሙ
Show all...
በድሬዳዋ ዛሬ አዲስ መንግስት ይመሰረታል። የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት ዛሬ የምስረታ ጉባኤ ያካሂዳል። በምስረታ ጉባኤው ለቀጣይ 5 ዓመታት ከተማዋን የሚመራ አዲስ አስተዳደር ይመሰርታል፡፡ ጉባኤው የምክር ቤቱን አፈጉባኤዎች የሚመርጥ ሲሆን የከተማዋን ከንቲባ ይሾማል። በተጨማሪም ጉባኤው የካቢኔ አባላት ሹመትንም እንደ ሚያፀድቅ ይጠበቃል። @Skyline7777 @Skyline7777
Show all...
🔆መልካም ዜና ለወላጆች ለውድ ልጆ ዘመናዊ መማሪያ ወይም መተግበሪያ በስጦታ ያበርክቱ ከዘመኑ ጋር እኩል ያራምዱ ለልጆች ተብሎ የተሰራ ታብሌት 0913663777 🏷 የልጆች መማሪያ ታብሌት ▫️ Wifi መጠቀም የሚያስችል ▫️ ልጆች አልባሌ ነገር እንዳያዩ የራሱ ማቆጣጠሪያ ያለው ▫️የፊትና የኃላ ካሜራ ያለው ▫️ 16Gb. ያለው & 2ጂቢ ራም ▫️ ተጨማሪ ሚሞሪ እስከ 32ጂቢ የሚወስድ ▫️ 7 ኢንች ስክሪን እንዲሁም የራሱ ፕሮቴክተር ▫️ አንድሮይድ 8.1 የተጫነበት (kids software) ▫️ ሙሉ በሙሉ ተች ስክሪን የሆነ ▫️ ከ ዋስትና ጋር📌 ▫️አስተማማኝ ባትሪ🔋 3000mAh Free Gift :-3D Glass , Fan Pen , Stickers, earphone and more ...... ☑️ ለልጁ የተሻለውን ለሚመርጥ ወላጅ የቀረበ 💰ዋጋ - 3499 Birr Contact- 0913663777 አድራሻ : - ቦሌ bras Our telegram challenge 👇🏻👇🏻 https://t.me/zackcomputer0913663777
Show all...
Zack computer 0913663777

Sell and buy products freely in ethiopia For more 0913663777

የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን እና የቱርክ አቻቸው ረሲፕ ታይፕ ኤርዶሃን ዛሬ ሩሲያ ውስጥ ተገናኝተው ይነጋገራሉ። ሁለቱ መሪዎች ከሚመክሩባቸው ጉዳዮች መካከል የጦር መሳሪያ ግዢ እና የሶሪያ ጉዳይ ዋነኛ አጀንዳዎች ይሆናሉ ተብሏል። ቱርክ ከሩሲያ የጦር መሳሪያዎችን መግዛቷ ከአሜሪካ ጋር ውዝግብ ውስጥ እንድትገባ አድርጓታል። ቱርክ ከሩሲያ ለመግዛት ያሰብኩትን ጦር መሳሪያ በተመለከተ አሜሪካ ምንም አይነት ክልከላ ልታደርግ አትችልም ስትል የአሜሪካንን አቋም ተቃውማለች። የቱርኩ ፕሬዝዳንት ረሲፕ ታይፕ ኤርዶሃን ቱርክ በርካታ ቁጥር ያላቸው ስልታዊ የሚሳኤል ሥርዓቶችን ከሩሲያ ለመግዛት እቅድ እንዳላት አስታውቀዋል። ፕሬዝዳንት ኤርዶሃን አገራቸው ለሁለትኛ ዙር ኤስ-400 ከምድር ወደ ሰማይ የሚወነጨፉ ሩሲያ ሠራሽ ሚሳኤሎችን ለመግዛት በዝግጅት ላይ መሆኗ በታወቀበት ጊዜ አሜሪካ ተቃውሞ አሰምታለች። በዚህም ሳቢያ ቱርክ ከሰሜን አትላንቲክ የጦር ቃል ኪዳን ድርጅት ኔቶ አጋሯ አሜሪካ ጋር ውዝግብ ውስጥ የከተታት ሲሆን፣ ተጨማሪ ማዕቀብ ሊያስጥልባት ይችላል ተብሏል። አሜሪካ ሩሲያ ሰራሾቹ ኤስ-400 ሚሳኤሎች ለኤፍ-35 ተዋጊ ጄቶቼ ስጋት ናቸው ትላለች። ከዚህ በተጨማሪም ዋሽንግተን ሚሳኤሎቹ ለኔቶ የድንበር መከላከያ ሥርዓት አደጋ ናቸው ብላ ታምናለች። ቱርክ በበኩሏ፣ የአየር መከላከያ ሥርዓቶችን አጥጋቢ በሆነ መልኩ ከኔቶ አባል አገራት መግዛት እንዳልቻለች በማመልከት ከሩሲያ ጋር ስምምነት ላይ እንደደረሰች ገልጻለች።
Show all...
በከተማችን የምናካሄዳቸው ሁሉም የልማት ስራዎች በሂደታቸውም ሆነ በውጤታቸው ተጨባጭ ለውጥ እንዲያመጡ ለማድረግ በትኩረት እንሰራን ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ተናገሩ፡፡ በዛሬው እለት እየተካሄደ በሚገኘው የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት ምስረታ ስነ ስርዓት ላይ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ የከተማዋ ከንቲባ ሆነው ከተሾሙ በኋላ ባደረጉት ንግግር፤ በከተማዋ የምንሰራቸው ሁሉም ኢኮኖሚዊ እንቅስቃሴዎች በከታማችን ነዋሪዎች ላይ ተጨባጭ ለውጥን እንዲያመጡ እንሰራን ብለዋል፡፡ በከተማችን ላይ ምርትና አገልግሎት አቅርቦቶችን ለማሻሻል ሲባል በጥናት ለመለየት ይሰራል ያሉት ወ/ሮ አዳነች የከተማዋን የመልማት አቅም ለማጎልበት በትብብር እንሰራለን ሲሉ ተናግረዋል፡፡ ወ/ሮ አዳነች ይህንን የከተማዋን የኢኮኖሚ እድገት ለማፋጣን ደግሞ የመንግስት የኢኮኖሚ ተቋማት ላይ የማሻሻል ስራዎች እንደሚሰሩም ቃል ገብተዋል፡፡ በተለይም ደግሞ የከተማዋ የመሰረተ ልማቶች ተደራሽነት ላይ በትኩረት የሚሰሩባቸው ዘርፎች መኖራቸውንም እንዲሁ ጠቁመዋል፡፡ ከነዚህም መካከል፤ የመኖሪያ ቤት አቅርቦትን ለማሻሻል፤ የውሃ፤ የመብራትና የኮምንዩኬሽን እንዲሁም የትራንስፖርት ዘርፎችን ለማሳለጥ በልዩ ትኩረት የምንሰራባቸው ዘርፎች ይሆናሉ ብለዋል፡፡ ወ/ሮ አዳነች አክለውም ደሃ ተኮር መርሃ ግብሮቻችን ውጤታማ እንዲሆኑ ለማድረግ ወጣቶችና ሴቶች ላይ የስራ እድል እንዲያገኙ በልዩ ትኩረት እንሰራለን ነው ያሉት፡፡ ይህንን እውን ለማድረግ ደግሞ የኢንዱስትሪን ልማት እድገትና የሰራ ፈጠራ ዘርፎችን ለመደገፍ ሲባል አንዱ የትኩረት አቅጣጫችን ይሆናል ብለዋል ከንቲባዋ፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘ ወሮ አዳነች የሌብነትና የዝርፊያ ስራዎችን ለመከላከል ሲባልም አዳዲስ የስነ ምግባር እንዲሁም ተጠያቂ ለመሆን የሚያስችሉ ደንቦችን እንዲወጡ እናደርጋንም ብለዋል፡፡ [Ethio FM]
Show all...
ወ/ሮ አዳነች አቤቤ የአዲስ አበባ ከንቲባ ሆነው ተሾሙ። ወ/ሮ አዳነች አዲስ አበባ ከተማን ለቀጣይ አምስት ዓመት በከንቲባነት እንዲመሩ ምክር ቤቱ በሙሉ ድምፅ የደገፋቸው ሲሆን ቃለ መሃላም ፈፅመዋል።
Show all...