የፍሬ እይታዎች
ሲለኝ ያየሁትን፣ሲያሻኝ ያነበብኩትን ከዛ ውጪ ደግሞ ከራሴ የወጣውን እከትባለሁ✍️
Show moreThe country is not specifiedThe language is not specifiedThe category is not specified
189
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days
- Subscribers
- Post coverage
- ER - engagement ratio
Data loading in progress...
Subscriber growth rate
Data loading in progress...
⏱ ⏰ 🕰 ያለፈ ጊዜ ልክ እንደታሪክ ነው። በትውስታ ይወራል እንጂ አሁን አይኖርበትም።
⏳ ምርጥ ታሪክ የተጠቀምንበት ጊዜ ነው። ከልተጠቀምንበት ትረካ የሌለው ታሪክ ታሪክ አልባ ነው።
@freaneger
ማሸነፍ 🏆 የሚያረካው የውድድሩ ውጣውረድ ሲበዛና ተወዳዳሪዎችም ጠንክረው ሲገኙ ነው።
ፍቅር❤➡️ይቅርታ🙏➡️ሠላም🕊
የፍሬ እይታዎች 🌄
@freaneger
መልካምነት ለሠዎች ጥሩ እንዲሆንላቸው በመመኘት ውስጥ ያለ ባህሪ ነው።
ፍቅር❤➡️ይቅርታ🙏➡️ሠላም🕊
የፍሬ እይታዎች 🌄
@freaneger
ገበሬ ይዘንባል ብሎ ተስፋ በማድረግ መሬቱን ያርሳል። እምነቱም የጠነከረ ስለሆነ ፈጣሪውም አያሳፍረውም። ጅራፉን በበሬዎቹ አናት ላይ ባጮኸ ቁጥር የሚመግበውን የሠው መጠን ነው የሚያስበው። ስለ ሠው ይኖራል። ፍቅርን እንደ ገበሬ ማን ያውቃታል።🤔 ለዚህ ነው ገበሬ ደግ ነው የሚባለው። የደግ ሠው መገለጫው ገበሬ ነው። ገበሬ ደግሶ ያበላል። ሁሌም እንደደገሰ ነው።
ሁሌም በረከት ለደግ ነው።💜💜💜
ፍቅር❤➡️ይቅርታ🙏➡️ሠላም🕊
የፍሬ እይታዎች 🌄
@freaneger
ስኬት=አለማቅማማት ሲደመር አለመሰልቸት ሲደመር መጨረሻቸውን እያዩ መስራት ነው።!
ፍቅር❤➡️ይቅርታ🙏➡️ሠላም🕊
የፍሬ እይታዎች 🌄
@freaneger
ሰዎችን በጠላን ቁጥር ራሳችንንም በዛው ልክ እንጠላለን። ቂም ቁዋጥረን ከኖርነው መቶ አመት በፍቅር የዋልነው አንድ ቀን ይበልጣል። ይቅር ከመባባል የሚገኘውን ትርፍ የሚተካ የለም። ይቅርታ ልብ ላይ እንጂ መሬት ላይ አይወድቅም። ዴርቶጋዳ
ፍቅር❤➡️ይቅርታ🙏➡️ሠላም🕊
የፍሬ እይታዎች 🌅
@freaneger
አንዳንዴ................. ግዜ ሰጥተን ያሰብንላቸው፣ ከእኛ በላይ ለእነሱ የተጨነቅንላቸው፣ ምርጫችንን የተውንላቸው፣እረፍታችንን የሰጠናቸው፣ ሌሊቶቻችንን ያልተኛንላቸው እና በእያንዳንዱ ሀሳባችን ውስጥ የመጀመሪያውን እና ዋናውን የያዙት ሰዎች እኛ ለእነሱ ትርፍ እንደሆንን እንድንቆጥር ያደርጉናል። ቢያመን የማያገባቸው፤ ብንወድቅ ብንሰበር ስሜት የማይሰጣቸው፤ ብናዝን ብንከፋ የነሱ ደንታ እንዳልሆነ ያሳዩናል። ያኔ መለስ ብለነን ለእነዚህ ነበር ያን ሁሉ የሆንኩት?! ብለን ራሳችንን ጠይቀን በፀፀት እሳት ራሳችንን እንፈጃለን። ካለፈ በኋላ ደግሞ ለነሱ ነው ያለቀስኩት? ብለን የንዴት ሳቅ እንስቅና እንተወዋለን።.........
ግን እኔ ሳስበው ያከበርናቸው እንኳን ናቁን! የወደድናቸው እንኳን መልሰው አልወደዱን! ግዜ የሰጠናቸው እንኳን ነፈጉን ! አሉን ያልናቸው እንኳንም የኛ እንዳልሆኑ አሳዩን! እ!ሰ!ይ ከሠዎች የማንጠብቅ በራሳችን የምንተማመን ጠንካሮች አድርገውናል። ሠው ስለመጣ የማንፈነጥዝ ስለሄደ ደግሞ የማንፈዝ የማንደነዝዝ አድርገውናል። እንዲያውም ባለውለታዎቻችን ናችሁ እናመሰግናለን።🙏
ፍቅር❤➡️ይቅርታ🙏➡️ ሠላም 🕊
የፍሬ እይታዎች 🌄
@freaneger
@freaneger
@freaneger
@freaneger