1 474
Subscribers
No data24 hours
-37 days
-2130 days
Posts Archive
"የከተማዬን ሰላም አስከብራለሁ ፣ፅዳቷንም እጠብቃለሁ"! በሚል መሪ ቃል በቂርቆስ ክፍለ ከተማ የፅዳት ንቅናቄ ተካሄደ።
የቂርቆስ ክ/ ከተማ የጽዳት አስተዳደር ጽ/ ቤት ከክፍለ ከተማው ሰላምና ጸጥታ ጽ/ ቤት ጋር በመተባበር ባዘጋጁት በዚሁ የጽዳት ንቅናቄ በወረዳ 2 የተካሄደ ሲሆን የፖሊስ መምሪያ ኃላፊ ኮሚሽነር ዳመና ተስፋዬን ጨምሮ የፖሊስና የትራፊክ ደህንነት አባላት፣ የደንብ ማስከበርና የሰላም ሰራዊት አባላት ተሳትፈዋል።
ፅዳቱን ያስጀመሩት የክፍለ ከተማው ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አብድልሃዲ ረሺድ የኮሪደር ልማቱ አዲስ አበባን የብልፅግና ተምሳሌት ለማድረግ በሚያስችል መልኩ እየተሰራ ሲሆን ይህ ታላቅ ስራ ያለ ምንም የፀጥታ ችግር እንዲከወን የፀጥታ ሀይሉ እያበረከተ ያለው አስተዋጽኦ በቃላት የሚገልፅ አይደለም ብለዋል።
ዛሬም ከፀጥታው ስራ ጎን የአካባቢያችሁን ፅዳት ለመጠበቅ በመውጣታችሁ ልትመሰገኑ ይገባል ብለዋል።
የሰላምና ፀጥታ ጽ/ቤት ኃላፊው አቶ ታዬ ሽፈራው በበኩላቸው የፀጥታ ሀይሉ ሰላምን ከማስከበር ባሻገር በማህበረሰብ አገልግሎት ላይ እንደሚሳተፉ ገልፀው የዛሬው የፅዳት ዘመቻም የዚሁ አካል ነው ብለዋል።
ሐምሌ 13/ 2016
Kirkos Communication-ቂርቆስ
ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ!
Facebook:-
👇👇👇👇
https://www.facebook.com/CITYMANAGER1
Telgram:-
👇👇👇👇
https://t.me/aacitymanager
Twitter:-
👇👇👇👇
https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r
YouTube:-
👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s
Tiktok
👇👇👇👇
https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager...
Website
👇👇👇👇
https://www.aacitymanger.gov.et
የየካ ክ/ከተማ አስተዳደር ስራ አስኪያጅ ፅ/ቤት የክረምት ወራት የጎርፍ አደጋን ለመከላከል የተሰሩ ስራዎችን ከባለድርሻ አካላት ጋር ገመገመ።
የየካ ክ/ከተማ አስተዳደር ስራ አስኪያጅ ፅ/ቤት በ2016 የክረምት ወራት የጎርፍ አደጋን ለመከላከል በወረዳዎች የተለዩ የአደጋ ስጋት ቦታዎች ዙሪያ የተሰሩ ስራዎችን ከወረዳ ስራ አስኪያጅ ፅ/ቤት ሃላፊዎች እና ባለድርሻ ፅ/ቤት ተወካዬች ጋር ገምግሟል፡፡
የየካ ክ/ከተማ ስራ አስኪያጅ ፅ/ቤት ሃላፊ አቶ ጫሊ ቤኛ በክረምት ወራት የተለያዩ ሰው ሰራሽ እና የተፈጥሮ አደጋዎች ተጋላጭ የሆኑ ቦታዎች በመለየት የቅድመ ጥንቃቄ ስራዎችን ለመከናወን ከዚህ ቀደም መግባባት ላይ መደረሱን ገልፀው ወረዳዎች የክረምት ወቅት ተጠናክሮ ሳይገባ ለአደጋ ተጋላጭ የሆኑ ቦታዎች ላይ የተለያዩ ስራዎችን እየሰሩ እንደሆነ እና በቀጣይም ከልየታ ባለፈ ለአደጋ ተጋላጭ የሆኑ የማህበረሰባችንን ክፍሎች መደገፍ ባለባቸው ልክ የመደገፍ ስራዎች እንደሚከናወኑ ገልፀዋል፡፡
በግምገማው ላይ ወረዳዎች በስራቸው ያሉ ተቋማትን በማስተባበር ግብረ ሀይል እንዳቋቋሙ እና የአደጋ ስጋት ያለባቸው ቦታዎች ላይ በመውረድ ችግሮችን የለዩ ሲሆን በወረዳ አቅም መፈታት የሚችሉ ችግሮችን በወረዳ እና የአካባቢውን ማህበረሰብ በማስተባበር በመፍታት ከወረዳ አቅም በላይ የሆኑትንም የማሳወቅ ስራዎች መስራታቸውን ገልፀዋል፡፡
በተጨማሪም የጎርፍ አደጋ ይፈጥርባቸዋል ተብለው የታሰቡ ቦታዎች ላይ ከህብረተሰብ ተሳትፎ እና በጎ ፍቃድ ማስተባበሪያ ፅ/ቤት ጋር በመቀናጀት የጎርፍ መቀልበሻ እንዲሁም አዳዲስ የዲች ግምባታ እና ነባር ዲቾችን የማፅዳት ስራዎች የተሰሩ ሲሆን እያንዳንዱ ተቋምም ከሚያከናውነው ስራ ጎን ለጎን አደጋዎችን ለመቀነስ እና የጎርፍ ስጋት እንዳይፈጠርም በጥንቃቄ እንዲሰራ መደረጉም ተገልፃል፡፡
Yeka Communication-የካ ኮሙኒኬሽን
ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ!
Facebook:-
👇👇👇👇
https://www.facebook.com/CITYMANAGER1
Telgram:-
👇👇👇👇
https://t.me/aacitymanager
Twitter:-
👇👇👇👇
https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r
YouTube:-
👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s
Tiktok
👇👇👇👇
https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager...
Website
👇👇👇👇
https://www.aacitymanger.gov.et
በአዲስ አበባ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ ሞገስ ባልቻ እና ምክትል ከንቲባ ጃንጥራር አባይ የተመራ የከተማ አስተዳደሩ አመራሮች የልዑካን ቡድን በሲንጋፖር ጉብኝት በማድረግ ላይ ይገኛል።
በጉብኝታቸውም በአረንጏዴ ልማትና የከተማ ውበት ስራዎች ፣ በመሰረተ ልማት ዝርጋታ ፣ በቴክኖሎጂ ሽግግር እንዲሁም በሌሎች ዘርፎች ዙሪያ ከሲንጋፖር ጋር የልምድ ልውውጥ በማድረግ ላይ ይገኛሉ።
ከዚህ ቀደም ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) እና ከንቲባ አዳነች አቤቤ በሲንጋፖር የስራ ጉብኝት ማድረጋቸው ይታወሳል።
ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ!
Facebook:-
👇👇👇👇
https://www.facebook.com/CITYMANAGER1
Telgram:-
👇👇👇👇
https://t.me/aacitymanager
Twitter:-
👇👇👇👇
https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r
YouTube:-
👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s
Tiktok
👇👇👇👇
https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager...
Website
👇👇👇👇
https://www.aacitymanger.gov.et
+6
የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት 3ኛ አመት የስራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ጉባኤ የተለያዩ ሹመቶችን በማጽደቅ ተጠናቅቋል፡፡
ምክር ቤቱ በሁለተኛ ቀን ውሎው በአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ የቀረቡ የተለያዩ ሹመቶችን አጽድቋል፡፡
በዚህም ፤-
1-አቶ ማሾ ኦላና- የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የመንግስት ዋና ተጠሪ ሆነው እንዲያገልግሉ ተሹመዋል፡፡
2-ወ/ሮ ይመኙሻል ታደሰ - የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የከተማ ውበትና የአረንጓዴ ልማት ቢሮ ኃላፊ
3-አቶ ያብባል አዲስ ጎበዜ -የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትራንስፖርት ቢሮ ኃላፊ
4-ወ/ሮ ቅድስት ወልደጊዮርጊስ - የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ
5-አቶ ቁሴ ለታ ዋቅጅራ- የአዲስ አበባ ዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤት ምክትል ዋና ኦዲተር
6-አንድነት ብዙሰው ታመነ- የአዲስ አበባ ዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤት ምክትል ዋና ኦዲተር
የስራ ኃላፊዎቹ በምክር ቤቱ ፊት ቀርበው ቃለ መሃላ ፈጽመዋል፡፡
በዛሬው የምክር ቤታችን ውሎ ለ2017 በጀት ዓመት 230.39 ቢሊዮን ብር በጀት አውጀናል።
ከዚህ ውስጥ 146.48 ቢሊዮን ብር (63.6%) ለካፒታል የተመደበ ሲሆን፣ 74.55 ቢሊዮን ብር (33.4%) ለመደበኛ ወይም ለአስተዳደርዊ ወጪ የተመደበ ነው።
ለካፒታል ከተመደበው ውስጥ 90.4 % ለድህነት ቅነሳ እና እድገት ተኮር ዘላቂ ልማት ለሆኑ ፕሮጀክቶች የተመደበ ነው።
ውድ የከተማችን ግብር ከፋዮች፤ ይህን በጀት ማሳካት የጋራ ርብርብ ይጠይቃል። በ2016 በጀት ዓመት ግብራችሁን በወቅቱ በፈቃደኝነት በመክፈላችሁ 146.8 ቢሊዮን ብር ግብር ሰብስበን 18,091 ፕሮጀክቶችን እና የኮሪደር ልማትን ተግብረን ከተማችንን እንደ ስሟ ውብ አበባ በማድረግ የጋራ አሻራችንን እያስቀመጥን ነው።
በዚህ ዓመትም እጅ ለእጅ ተያይዘን የበለጠ ለመስራት ሁላችንም ሃላፊነታችንን እንድንወጣ ጥሪዬን አቀርባለሁ።
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህቦቿን ይባርክ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ኤፍኤም ሬድዮ 98.1 ጋር በመተባበር "ይህ የሁላችንም ጉዳይ ነው!" በሚል ርእስ ዘወትር እሁድ ከምሽቱ 12 ስአት ጀምሮ በየሳምንቱ የሚተላለፈውን ፕሮግራም የመጀመሪያ ክፍል በማህበራዊ ሚዲያ ገጻችን ትከታተሉት ዘንድ እነሆ ብለናል።
See less
+8
የፕሮጀክቶች አፈፃፀምን በተመለከተ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከተናገሩት:-
"18,ዐ91 ኘሮጀክቶች ተጠናቅቀው ለህዝብ አገልግሎት ዝግጁ ተደርገዋል:: ፕሮጀክቶቹን በ24/7 ሌት ከቀን ወጪ ቆጣቢ በሆነና በተያዘላቸው እቅድ መሰረት ለአገልግሎት ማብቃት የተቻለ ሲሆን በበጀት አመቱ በመንግስትና በበጎ አድራጐት በአጠቃላይ 18,ዐ91 ኘሮጀክቶችን አጠናቀን ለህዝብ አገልግሎት ዝግጁ አድርገናል፡፡"
በተጠናቀቀው የ2016 በጀት ዓመት ቆሻሻን መልሶ በመጠቀም እና ጥቅም ላይ በማዋል ከ1 ነጥብ 4 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ ተገኘ።
በበጀት ዓመቱ ይህ ገቢ ሊገኝ የቻለው 90 ሺ 175 ቶን ቆሻሻ ለመልሶ ጥቅም ላይ በማዋል መሆኑን የጽዳት አስተዳደር ኤጀንሲ ጠቅሶ መልሶ ጥቅም ላይ ከዋለው ቆሻሻም 3 ሺህ 631 ቶን ያህሉ ኮምፖስት በማምረት ለገበያ እንዲውል የተደረገ መሆኑም ተመልክቷል፡፡
ኤጀንሲው በመልሶ መጠቀም ዘርፍ በመዲናችን በአጠቃላይ 354 ማህበራት እንዳሉ ገልጾ ከእነዚህ ማህበራት 54ቱ በኮምፖስት ማምረት ላይ የተሰማሩ ናቸው ብሏል፡።
በዘንድሮው ዓመትም በመልሶ መጠቀሙ ዘርፍ ለ1ሺህ 161 ዜጎች የስራ ዕድል መፈጠሩንም አስታውቋል።፡
ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ!
Facebook:-
👇👇👇👇
https://www.facebook.com/CITYMANAGER1
Telgram:-
👇👇👇👇
https://t.me/aacitymanager
Twitter:-
👇👇👇👇
https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r
YouTube:-
👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s
Tiktok
👇👇👇👇
https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager...
Website
👇👇👇👇
https://www.aacitymanger.gov.et
+6
የምክር ቤታችንን የዓመቱን ማጠቃለያ ስብሰባ እያካሄድን ነው። የ 2016 በጀት ዓመት የስራ አፈፃፀም ሪፖርት እንዲሁም የቀጣይ የ 2017 በጀት ዓመት ዋና ዋና የትኩረት አቅጣጫዎችን ለምክር ቤታችንን አቅርቤያለሁ።
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
