1 474
Subscribers
No data24 hours
-37 days
-2130 days
Posts Archive
ባለስልጣኑ የደንብ ጥሰት የፈጸመውን የከተማ አውቶቢስ አሽከርካሪ መቅጣቱን አስታወቀ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለስልጣን በቂርቆስ ክፍለ ከተማ በለገሀር አከባቢ የከተማ አውቶቢስ ሹፌር ከመኪናው የጠረገውን ደረቅ ቆሻሻን አስፓልት ላይ በመጣሉ በደንብ ቁጥር 167/2016 መሰረት አምስት ሺህ ብር በመቅጣት ለመንግስት ገቢ ማድረጉን አስታወቀ ።
ድርጊቱን የፈጸመው ግለሰብ በጊዜው ተሸከርካሪዉን ይዞ ከቦታዉ ቢሰወርም በተደረገዉ ክትትል በዛሬዉ እለት የካ
ክፍለ ከተማ ወረዳ 6 ላይ ሹፈሩን ከነተሸከርካሪው በቁጥጥር ሰር በማዋል መንገድ በማቆሸሸ ለተላለፈዉ የደንብ ጥሰት የገንዘብ ቅጣት በመቅጣት ህጋዊ እርምጃ ተወስዷል ።
ባለስልጣኑ ህብረተሰቡ ለሰጠው ጥቆማ ከልብ እያመሠገነ ለማንኛውም የደንብ መተላለፎች መረጃ በ9995 ነፃ የስልክ መስመር ጥቆማ እንዲሰጥ ጥሪውን ያቀርባል።
ትውልድ በመምህራን ይቀረፃል ፤ ሀገር በትምህርት ይበለፅጋል "በሚል መሪ ቃል ዉይይት እያደረጉ የሚገኙ የመዲናችን መምህራንና የትምህርት አመራሮች የከተማዋን የልማት ስራዎች ጎብኙ… See more
ፋይዳ፣ ፋይዳው የጎላ፣ እያንዳንዱ ዜጋ ሊኖረው የሚገባ ነገር ነው ብዬ አስባለው።”
የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ “Tech Talk with Solomon” ያደረጉትን ቃለ መጠይቅ ክፍል 2 ዛሬ ከምሽቱ 2:30 በኢቢኤስ ቴሌቪዥን ይከታተሉ።
ደረቅ ቆሻሻ የሃብት ምንጭ እንጅ የጎርፍ መንስኤ ሊሆን አይገባም" በሚል መሪ ቃል በመጪው ክረምት ሊከሰት የሚችል የጎርፍ ጉዳትን አስቀድሞ ለመከላከል እንዲቻል የተዘጋጀ የፍሳሽ መውረጃ መስመሮችና የቦዮች የፅዳት ንቅናቄ ማስጀመሪያ መርሐግብርን አስመልክቶ የNBC Ethipia ቴሌቪዥን ዘገባን በቀጣዩ ቪዲዮ ይመልከቱ 👉👉
በመዲናዋ ደረቅ ቆሻሻን ወደ ኃይል የሚቀይርና መልሶ ጥቅም ላይ የሚያውል የ500 ሚሊዮን ዶላር ኢንቨስትመንት ስራ ላይ ሊውል ነው
በአዲስ አበባ ደረቅ ቆሻሻን ወደ ኤሌክትሪክ ኃይል የሚቀይርና ቆሻሻን መልሶ ጥቅም ላይ የሚያውል የ500 ሚሊየን ዶላር ኢንቨስትመንት ስራ ላይ ሊውል መሆኑን በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ ገለጹ።
የነዋሪነትና ሲቪል ምዝገባ፣ የእሳትና ድንገተኛ አደጋ፣ የደረቅ ቆሻሻና የመንገድ ዳር ኤሌክትሪክ አገልግሎቶች በመዲናዋ ለስራ አስኪያጅ ጽ/ ቤት ተጠሪ የሆኑ ተቋማት ናቸው።
ተቋማቱ በትብብርና በቅንጅት መስራታቸው የለውጥ ስራዎቹ ውጤት እንዲመዘገብባቸው ማድረጉም ተገልጿል።
በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ ለኢዜአ እንደገለፁት በመዲናዋ 500 ሚሊዮን ዶላር በሚፈጅ ኢንቨስትመንት ደረቅ ቆሻሻን ወደ ኃይል መቀየር የሚያስችል ፕሮጀክት ተግባራዊ ይደረጋል።
ፕሮጀክቱን ተግባራዊ ማድረግ የሚያስችለው ስምምነት የተፈፀመው ከቻይናዎቹ ሻንዥን ኢነርጂ ግሩፕ፣ ከቻይና ብሔራዊ ኤሌክትሪክ ኢንጅነሪንግ እና ከጀርመኑ ኮቬናንት ኢንጅነሪንግ ድርጅት ጋር ሲሆን አጠቃላይ ግንባታው ከሁለት እስከ ሶስት ዓመት እንደሚፈጅ ጠቅሰዋል፡፡
ለፕሮጀክቱ የሚውለው ወጪ በውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት የሚሸፈን ሲሆን ከተማ አስተዳደሩም ለዚሁ የሚሆን መሬት እንደሚያቀርብ አስረድተዋል።
በመዲናዋ ደረቅ ቆሻሻን የመሰብሰብ አቅም 96 በመቶ ደርሷል ያሉት ኢንጂነር ወንድሙ ቆሻሻን ከማስወገድ ባሻገር ወደ ሃብት የመለወጥ ስራም ትኩረት የተሰጠው መሆኑን አንስተዋል።
በተጨማሪም ባለፉት ሁለት ዓመታት በመዲናዋ የተካሄዱ ሁለንተናዊ የለውጥ ስራዎች ውጤት ማስገኘታቸውን አስታውቀዋል።
በመዲናዋ ባሉ 119 ወረዳዎች የሚሰጡ አገልግሎቶች ዲጂታላይዝ በመደረጋቸው ለውጥ እንደተመዘገበም አብራርተዋል።
አዲስ አበባን ስማርቲ ሲቲ ማድረግ የሚያስችሉ ቴክኖሎጂዎች ተግባራዊ መደረጋቸው በተቋማቱ ለውጥ እንዲመዘገብ አስችሏል ብለዋል ።
በመዲናዋ አገልግሎት ከሚሰጡ ተቋማት መካከል የሲቪልና ነዋሪነት ምዝገባ አንዱ መሆኑን ጠቅሰው ቢሮው ባለፉት 10 ወራት የ870ሺህ ዜጎችን መረጃ/ባዮሜትሪክ ዳታን/ መውሰድ መቻሉን ጠቁመዋል።
ከዚሁ ጎን ለጎን በሀገር አቀፍ ደረጃ ተግባራዊ በተደረገው የፋይዳ ምዝገባ በአዲስ አበባ ብቻ እስካሁን ከ5 ሚሊዮን በላይ ነዋሪዎችን ተደራሽ ማድረግ ተችሏል ነው ያሉት።
"ትምህርት በመምህራን ይቀረፃል ፤ ሀገር በትምህርት ይበለፅጋል "በሚል መረሃሳብ የአዲስ አበባ ትምህርት ማህበረሰብ ውይይት እየተደረገ መሆኑ ተገለፀ::
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ አመራሮች እና የከተማችን ከፍተኛ አመራሮች ጋር በመሆን የውይይት መድረኮቹን አካሄድ ተዘዋውረው የተመከቱ እና ሂደቱን ያበረታቱ ሲሆን ፤ ለሀገር እድገት የሚጠቅሙ ሀሳቦች ይነሳሉ ተብሎ እንደሚጠበቅም ተናግረዋል።
በውይይቱ ላይ በሁሉም የመንግስት ትምህርት ቤቶች ውስጥ የሚያስተምሩ መምህራንና የትምህርት አመራሮች የተሳተፉ ሲሆን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ እና የከተማችን ከፍተኛ አመራሮች በአንደኛ እና 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ላይ ተዘዋውረው ምልከታ አድርገዋል::
ውይይቱን አስመልክተው ማብራሪያ የሰጡት ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ ከመምህራንና ከትምህርት አመራሮች ጋር በየአመቱ መሰል ውይይቶች እንደሚካሄድ ገልፀው ውይይቶቹ ለስራ ውጤታማነት ትልቅ እገዛ እንደነበራቸው ያብራሩ ሲሆን እየተካሄደ የሚገኘውም ውይይት የጋራ መግባባት ለመፍጠር እንደሚያግዝ ተናግረዋል።
የትምህርት ልማት ስራ የሁሉንም ባለድርሻ አካላትን ርብርብ ይጠይቃል ያሉት ሀላፊው ትውልድን በመቅረፅ ስራ ውስጥ በቅንጅት ስራዎች ከተለያዩ አካላት ጋር እየተከናወኑ ይገኛሉም ብለዋል።
አዲስ አበባ እንደ ስሟ ፤ዉብ፤ሳቢ እና ፍንትዉ ብለዉ የሚታዩ አዳዲስ ገፅታዎችን በመላበሷ መልኳተቀይሯል፡፡" ከንቲባ አዳነች አቤቤ
ከንቲባዋ ይህን ያሉት በካዛንቺስ የኮሪደር ልማትና መልሶ ማልማት ተገኝተዉ በሰጡት ማብራሪያቸዉ ነዉ፡፡
የአዲስ አበባ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በካዛንቺስ የኮሪደር ልማትና መልሶ ማልማት ስራዎችን አስመልክተዉ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡
የካዛንቺስ ኮሪደር ልማት ስናነሳ ስፋቱን ማየት መልካም ነዉ ያሉት ከንቲባ አዳነች አቤቤ በአጠቃላይ ወደ 1ሺ ሄክታር መሬት የሸፈነ ይህም እስከ አዋሬ፤ቤይለር፤ ቀበና ድረስ የሚገጥም ነዉ ብለዋል፡፡
በተጨማሪም የካዛንቺስ ኮሪደር ልማት ብለን የምንጠራዉ ቸርቸር ጎዳናን ይዞ በለገሃር፤በሜክሲኮ እድርጎ በ4 ኪሎ የሚመጣዉን ጭምር የኮሪደር ልማት ዉስጥ ተካቶ እንዲለማና እኩል ደረጃ ላይ እንዲመጣ የተደረገ ነዉም ሲሉ ገልፀዋል፡፡
ኮርደር ልማቱን በምንሰራበት ሰዓት አንዱ ትልቁ መሰረተ ልማቶቻችንን ማገኛኘት ወይም ኔትዎርክድ ማድረግ በመሆኑ በቀበና ስንሄድ ከኮሪደር 1 ጋር ፤ወደ አዋሪ ስንሄድ ወደ 4ኪሎ ፤በእንደራሴ በኩልም ቀጥታ ሂዶ ካዛንቺስ ቶታል ጋር የሚገኛኙ መሆኑን ጠቅሰዉ በመለስ ፋዉንዴሽን ሲኬድም ቀጥታ ወደ ቤተ መንግስቱ ከሚሄደዉ መንገድ እና ካዛንቺስ ቶታል ጋር ተመልሶ የሚገናኝና መስቀለኛ መንገዶቹም በተመሳሳይ ወደ ቦሌ እና ወደ መገናኛ በሚያመጣዉ መገናኛ ናቸዉ ብለዋል፡፡
አያይዘዉም አዲስ አበባ ላይ መንገድ ለተሸከርካሪ ብቻ ነበር ያዉም ጠባብ መንገዶች ያሉት ከንቲባ አዳነች አቤቤ አሁን ግን መንገድ ለእግረኛ ፤ለሞተር አልባ እና ለሌሎች ተሸከርካሪዎች አገልግሎት እንዲዉሉ ተደርጓል ብለዋል፡፡
56 የሚደርሱ ከቴክኖሎጂ ጋር የተቆራኙና ባህልን የሚያንፀባርቁ ልዩ ትኩረት ተሰጥቷቸዉ የተሰሩ የህዝብ መዝናኛ ፓርኮች መኖራቸዉን ጠቁመዉ በሁሉም ቦታዎች ላይ በማንኛዉም ደረጃ ላይ ያሉ የማህበረሰብ ክፍሎች ለተለያዩ አገልግሎቶች በጋራ የሚጠቀሙበት፤የሚዝናኑበት እና የሚያርፉበት እድልን የፈጠረ የልማት መሆኑን ገልፀዋል፡፡
አዲስ አበባን ስማርት ከተማ ከማድረግ ህልማችን ጋራ አያይዘን በጣም ከመሬት በታችም የመብራት የቴሌኮም፤የዉሃ፤የፍሳሽ እና የአይቲኤስ ወሳኝ የሆኑ መሰረተ-ልማቶች ተገንብተዋልም ብለዋል፡፡
በመጨረሻም አዲስ አበባ እንደ ስሟ ፤ዉብና ሳቢ ፍንትዉ ብለዉ የሚታዩ አዳዲስ ገፅታዎችን በመላበሷ መልኳ ተቀይሯል ያሉት ከንቲባዋ በዚህም ጠቅላይ ሚኒስተራችን የሚያነሱት የትስስር ልማት ፅንሰ ሃሳብ ወደ ተግባር ተለዉጦ ተጨባጭ ለዉጥ የታየበት የኮሪደር ልማት ስራችን ነዉ ሲሉ ገልፀዋል፡፡
የቀጣይ 5 ወራት የፅዳት ንቅናቄ ማስጀመሪያ መርሃ-ግብር ተካሄደ፡፡
በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ የቀጣይ 5 ወራት የፅዳት ንቅናቄ ማስጀመሪያ መርሃ-ግብር የጽዳት አምባሳደሮችና የተለያዩ ባለድርሻ አካላት አመራሮች በተገኙበት ውይይት ተካሂዷል፡፡
ስራና ክህሎት ጽ/ቤት፣ ጽዳት አስተዳደር ጽ/ቤት፣ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት፣ መንገዶች ባለስልጣን፣ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት፣ ትራንስፖርት አገልግሎት፣ ህብረተስ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት፣ አካባቢ ጥበቃ ጽ/ቤት፣ ከተማ ውበትና አረንጓዴ ልማት ጽ/ቤት፣ ደንብ ማስከበር እንዲሁም የፅዳት አምባሳደሮች በጋራ በመሆን በቀጣይ 5 ወራት የፅዳት ንቅናቄ ስራ የሚሰራ መሆኑ ተገልጧል፡፡
የክፍለ ከተማው ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚና የስራ ክህሎት ጽ/ቤት ሃላፊ ወ/ሮ ሰላማዊት ከበደ በቀጣዩ ወራት ክፍለ ከተማችንን ውብ፣ ፅዱና ማራኪ ለማድረግ የሚካሄደው የንቅናቄ ስራ ስኬታማ እንዲሆን በቅንጅት መስራት ይገባል ብለዋል፡፡
የክፍለ ከተማው ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ደረሰ ፈጠነ በበኩላቸው ጽዳትን ባህሉ ያደረገ ማህበረሰብ ለመፍጠር የሚደረገው ጥረት ውጤታማ እንዲሆን የንቅናቄ ስራውን በስኬታማነት ማስኬድ ይገባል ሲሉ ተናግረዋል፡፡
የጽዳት አስተዳደር ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ድሪባ ጉለማ በበኩላቸው ንቅናቄው ዘውትር ቅዳሜ በየሳምንቱ የሚካሄድ በመሆኑ መላው ህዝባችን አካባቢውን በማፅዳት አስፈላጊውን ትብብር ማድረግ ይጠበቅበታል ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
ግንቦት 5 ቀን 2017
"ስማርት ማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት
ለስማርት ሲቲ አዲስ አበባ" - በም/ ከንቲባ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ ከ#AMN ጋር ያደረጉትን ቆይታ ሙሉ ቃለ ምልልሱን
ዛሬ ግንቦት 5/ 2017 ዓ.ም ማክሰኞ ምሽት ከ3 ስአት ጀምሮ ይከታተሉ።
