en
Feedback
Addis Ababa City Manager Office

Addis Ababa City Manager Office

Open in Telegram
1 474
Subscribers
No data24 hours
-37 days
-2130 days
Posts Archive
ከለውጡ በፊት የከተማዋ ነዋሪዎች ፅዱና ልምላሜን አካባቢ ለማዬት ሲፈልጉ ለጉብኝት ከከተማዋ ራቅ ብለው ወደሚገኙ አካባቢዎች ነበር የሚወጡት። ዛሬ እናንተ ወጣቶች ታድላችሁዋል።ፅዱና ልምላሜ ቦታዎች በመዲናችን ተፈጥሮላችሁዋል።" ሃጂ ሸምሱ አባስ የመዲናችን የፅዳት አምባሳደር

መንግስት የአዲስ አበባ ከተማን እንደ ስሟ ጽዱና ውብ እያደረገ ያለውን ተግባር ለማገዝ ነዋሪው ፍሳሽም ሆነ ደረቅ ቆሻሻን በአግባቡ መያዝና ማስወገድ እንዳለበት ተገለፀ። የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ጽዳት አስተዳደር ጽ/ቤት በቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ ዙሪያ በተለያየ መልኩ ግንዛቤ የማስጨበጥ ስራ መድረክ በማዘጋጀት፣ በቤት ለቤት፣ በሻይ ቡና ፕሮግራም፣ በንቅናቄ እና በተለያዩ ስልቶች ግንዛቤ እየተፈጠረ እንደሚገኝ ጽ/ቤቱ አሳዉቋል። የክፍለ ከተማው ጽዳት አስተዳደር ጽ/ቤት በተቀናጀ ደረቅ ቆሻሻ አስተዳደር ስርዓት፣መልካም አስተዳደርና አገልግሎት አሰጣጥ እንዲሁም ሁሉን አቀፍ የከተማ ጽዳትና የጎርፍ መከላከል ንቅናቄ ዕቅድ ዙሪያ ለብሎክ ካውንስል አመራሮች፤ለክፍለ ከተማና ለወረዳ የጽ/ቤት ኃላፊዎች፣አስተባባሪና ቡድን መሪዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ አካሂዷል። የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ማናየ ጫኔ በግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኩ መክፈቻ ንግግር ሲያደርጉ እንደገለጹት የሚሰጠውን ግናዛቤ ወደ ተግባር ላይ ማዋል እንደሚያስፈልግና በጽዳት ስራው የኃይማኖት ተቋማት፣ዕድሮች፣ድርጅቶችና ተቋማት በንቃት ልትሳተፉ ይገባል ሲሉ ተናግረዋል። የክፍለ ከተማው ጽዳት አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ በየነ ቱሉ እንደተናገሩት ቀደም ሲል በመኖሪያ አከባቢ በተቋማትና በብሎክ የጽዳት ንቅናቄ ስናካሄድ የቆየን ሲሆን መጪው ክረምት በመሆኑ የፍሳሽ መውረጃዎችን ማጽዳት ይገባል ብለዋል። በጽ/ቤቱ የግንዛቤና ህብረተሰብ ተሳትፎ ቡድን መሪ ወ/ሮ እቴነሽ አበራ እና አቶ ጌቱ ኩምሳ የክፍለ ከተማው ጽዳት ስራዎች አስተባባሪ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጥተዋል። በክፍለ ከተማው በሚፈጠር ግንዛቤ የህብረተሰቡ የቆሻሻ አያያዝ እና አወጋገድ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሻሻለ እንደመጣና ቆሻሻን የመለየትና መልሶ መጠቀም እየተለመደ መምጣቱን ያነጋገርናቸው ነዋሪዎች ገልጸዋል። ነዋሪዎቹ አያይዘውም መንግስት የአዲስ አበባ ከተማ ገጽታ ውብና ማራኪ እየደረገ ያለውን ተግባር ነዋሪውም በየአከባቢው የፍሳሽም ሆነ ደረቅ ቆሻሻን በአግባቡ መያዝና ማስወገድ ይገባል ብለዋል። በተጨማሪም ጨለማን ተገን በማድረግ ቆሻሻ በመነገድ ላይ የሚጥሉና የሚያዝረከርኩ ህገ ወጦችን መከታተልና የወጡ ህግና ደንቦችን ተግባራዊ በማድረግ በቅጣት ማስተማር ያስፈልጋል ብለዋል። ሚያዝያ 24/ 2017

የማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎቶች የምንላቸው የከተማችን ነዋሪዎች በእለት ተእለት የኑሮ እንቅስቃሴያቸው ጋር የተገናኙ መሠረታዊ አገልግሎቶች በመሆናቸው ህዝቡ በቂ ግንዛቤ ኖሮት በሂደቱ ሰፊ ተሳትፎ እንዲያደርግ የተለያዩ ሥራዎችን እያከናወን እንገኛለን። ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ በምክትል ከንቲባ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ

የመዲናችን የደረቅ ቆሻሻ አስተዳደር በይበልጥ ለማዘመን የሚያስችሉ አዳዲስ የአሰራር ስርአቶችና ስልቶችን በሳይንሳዊ ጥናት በማስደገፍ ተግባራዊ ማድረግ እንደሚገባ በም/ከንቲባ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ አስገነዘቡ። ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ ይህን ያስገነዘቡት ከስራ አስኪያጅ ጽ/ቤትና ከጽዳት አስተዳደር ኤጀንሲ የተውጣጡ አመራሮች በቅርቡ በጋና አክራ ተገኝተው በጽዳት ዘርፍ ባካሄዱት የልምድ ልውውጥ ያገኙትን ተሞክሮ ባቀረቡበት ወቅት ነው። የአመራር ቡድኑ መዲናችን አዲስ አበባ በደረቅ ቆሻሻ አሰባሰብና ማጓጓዝ፣ በአካባቢና በከተማ ፅዳት፣ እንዲሁም ዜጎችን በፅዳት ስራ ለማሳተፍ የሚካሄዱ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች ያላትን ምርጥ ተሞክሮ ትምህርት እንዲቀሰምበት ለጋና አክራ የዘርፉ አመራሮች አቅርበዋል። በጋና አክራ በኩል ደግሞ " ፅዱ ጋና" Clean Ghana initiative በመተግበር በደረቅ ቆሻሻ አስተዳደር ዘርፍ የግሉን ሴክተር ተሳትፎ ማሳደግን፣ በቴክኖሎጅ የታገዘ የቆሻሻ ልዬታ እና ወደ ሃብት የመቀየር ስራዎችን የመልሶ መጠቀምና የኮምፖስት ስራዎች ላይ በተግባር የተደገፈ ልምዳቸውን ማጋራተቸውን የአመራር ቡድኑ በሰነድ አስደግፎ አቅርቧል። ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ በዚሁ ወቅት በከተማችን አዲስ አበባ በደረቅ ቆሻሻ አሰባሰብ ላይ ያስመዘገብነውን ከፍተኛ ስኬት ቆሻሻን ወደ ሃብት በመቀየርና የቆሻሻ አወጋገድ ላይ የአፈፃፀም ውጤታማነትን በእጅጉ ለማሳደግ ይህን መሰል የልምድ ልውውጦች እገዛቸው የጎላ ነው ሲሉ ተናግረዋል።

ሚያዚያ 23 ቀን 2017 ዓ.ም አዲስ አበባ 44ኛ መደበኛ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ስብሰባ ውሳኔዎች የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 44ኛ መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ፡፡ 1. ምክር ቤቱ በቅድሚያ የተወያየው ከጣሊያን ሪፐብሊክ መንግሥት እና ከዓለም አቀፍ የልማት ማህበር ጋር በተፈረሙ ሁለት የፋይናንስ ድጋፍ ስምምነቶች ላይ ነው፡፡ ከጣሊያን ሪፐብሊክ መንግስት የተገኘው የ11,500,000 ዩሮ ለአካባቢያዊና አረንጓዴ ኢኮኖሚ ልማት የበጀት ድጋፍ ፕሮግራም ማስፈፀሚያ የሚውል ሲሆን የ16 ዓመት የችሮታ ጊዜን ጨምሮ በ30 ዓመት ተከፍሎ የሚጠናቀቅ ነው፡፡ ከዓለም አቀፍ የልማት ማህበር የተገኘው 38,100,000 ኤስ.ዲ.አር ለመማር ማስተማር ማጎልበቻ የትምህርት ዘርፍ ትራንስፎርሜሽን ፕሮግራም ማስፈፀሚያ የሚውል ሲሆን 0.75% የአገልግሎት ክፍያ የሚከፈልበት ሆኖ 6 ዓመት የችሮታ ጊዜን ጨምሮ በ38 ዓመት ተከፍሎ የሚጠናቀቅ ነው፡፡ ምክር ቤቱም ብድሮቹ ምንም አይነት ወለድ የማይታሰብባቸው እና ከአገራችን የብድር አስተዳደር ፖሊሲ ጋር የሚጣጣሙ መሆናቸውን በማረጋገጥ ረቂቅ አዋጆቹ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፉ በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡ 2. በመቀጠል ምክር ቤቱ የተወያየው በአፍሪካ ፋይናንስ ኮርፖሬሽን መቋቋሚያ ስምምነት ማጽደቂያ ረቂቅ አዋጅ ላይ ነው፡፡ ኮርፖሬሽኑ ትኩረቱን በመሠረተ ልማት፣ በተፈጥሮ ሀብት እና በኢንዱስትሪ ዘርፍ ልማት ላይ በማድረግ ለግል አልሚዎችና ለመንግሥት አካላት የፋይናንስና የቴክኒክ ድጋፍ ለመስጠት የተቋቋመ ነው፡፡ ሀገራችን በአባልነት መቀላቀሏ ለግሉ ዘርፍ ተጨማሪ የፋይናንስ ሀብት በማቅረብና የግል ዘርፉን የማይተካ የኢኮኖሚ አንቀሳቃሽነት ሚና በማሳደግ ቀጣይነት ያለው የኢኮኖሚ ዕድገት ለማፋጠንና ድህነትን ለመቀነስ ጠቀሜታ ያለው በመሆኑ ምክር ቤቱ በቀረበው ረቂቅ አዋጅ ላይ ከተወያየ በኋላ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፍ በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡ 3. ሌላው ምክር ቤቱ ለአፍሪካ አህጉራዊ ነጻ ንግድ ቀጣና ስምምነት የዕቃዎች ቀረጥ ምጣኔ ቅነሳን ለማስፈፀም በቀረበ ረቂቅ ደንብ ላይ ተወያይቷል። ስምምነቱ በአባል ሀገራት መካከል ንግድ እንዲስፋፋ፣ የገበያ ትስስሩ እንዲጠናከር፣ የእሴት ሠንሰለቱ እንዲጎለብት እና የኢኮኖሚ ትራንስፎርሜሽን ማበረታታት የሚያስችል ነው፡፡ በአባል ሀገሮች መካከል የሚደረጉ ግብይቶች በታሪፍ ምክንያት ሳይደናቀፉ የእቃዎች ፍሰት የተሳለጠ እንዲሆን ከአባል አገራት በሚመጡ እቃዎች ላይ የጉምሩክ ታሪፍ ምጣኔ ለይቶ መወሰን አስፈላጊ መሆኑን በመወያዬት ምክር ቤቱ ደንቡ በፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ተፈፃሚ እንዲሆን በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡ 4. ሌላው ምክር ቤቱ የተወያየው በትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር ለሚሰጡ አገልግሎቶች እና በኢ.ፌዲ.ሪ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለሥልጣን ለሚሰጡ አገልግሎቶች የሚከፈሉ የአገልግሎት ክፍያዎችን ለመወሰን በቀረቡ ሁለት ረቂቅ ደንቦች ላይ ነው፡፡ ተቋማቱ አገልግሎት ለመስጠት የሚያወጡትን ወጪ በመሸፈን፣ ገቢያቸውን አሳድገው ጥራት ያለው አገልግሎት በመስጠት የተገልጋይ እርካታ ማሳደግ የሚያስችል የደንበኞችን አቅም ባገናዘበ መልኩ የአገልግሎት ክፍያ መወሰን አስፈላጊ ይሆናል፡፡ ምክር ቤቱም በረቂቅ ደንቦቹ ላይ በስፋት ከተወያየ በኋላ በነጋሪት ጋዜጣ ታትመው ከወጡበት ቀን ጀምሮ በስራ ላይ እንዲውሉ በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡ 5. የውጭ ዜጎች የማይንቀሳቀስ ንብረት ባለቤት ወይም ባለይዞታ የሚሆኑበትን አግባብ ለመደንገግ የወጣው ረቂቅ አዋጅ ሌላው ምክር ቤቱ የተወያየበት አጀንዳ ነው፡፡ የዜጎችን የመሬት ይዞታ የማግኘትና የመጠቀም መብት በማያጣብብ መልኩ ለውጭ ዜጎች ህጋዊ አሠራር መዘርጋቱ የውጭ ካፒታል በሀገራችን ሥራ ላይ እንዲያውሉ ለማበረታታት፣ የቤት ልማት እና ተደራሽነትን ይበልጥ ለማነቃቃት፣ የመኖሪያ ቤት ፍላጎት እና አቅርቦት ሚዛን ለማስጠበቅ እና ለዜጎች የሥራ ዕድል ለመፍጠር ትልቅ ጠቀሜታ የሚኖራቸው በመሆኑ ምክር ቤቱ በረቂቅ አዋጁ ላይ በስፋት ከተወያየ በኋላ ወደ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፍ በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡ 6. በመጨረሻም ምክር ቤቱ የተወያየው ከኦስትሪያ መንግስት ጋር የተፈረመውን የአየር ትራንስፖርት ስምምነት ለማፅደቅ በቀረበ ረቂቅ አዋጅ ላይ ነው፡፡ የስምምነቱ መጽደቅ የሁለቱን ሀገራት የሁለትዮሽ ግንኙነት ይበልጥ የሚያጠናክር፣ ለአየር መንገዳችን ተጨማሪ የገበያ ዕድል የሚፈጥር ከመሆኑም ሌላ የሀገራችንን ንግድና ኢንቨስትመንት በማበረታታት፣ የውጪ ንግዱን በመደገፍ፣ ቱሪዝምን በማስፋፋት፣ የስራ ዕድል በመፍጠርና በውጭ ምንዛሪ ግኝት ረገድ ትልቅ ጠቀሜታ ያለው በመሆኑ ምክር ቤቱ በረቂቅ አዋጁ ላይ ከተወያየ በኋላ ወደ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፍ በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡ //

የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መልዕክት ዛሬ ጠዋት ከፕሬዝደንት ጁአዎ ማኑኤል ጎንካሌቭ ሎሬንቾ በልዩ መልዕክተኝነት መልዕክት ይዘው የመጡትን የአንጎላ ሪፐብሊክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቴቴ አንቶኒዮን በጽሕፈት ቤታችን ተቀብያለሁ።

በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ሥራ አስኪያጅ ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ ከምክር ቤት አባላት ለተነሱ ጥያቄዎች የሠጡት ምላሽና ማብራሪያ

ህዝብን በማዳመጥ ለተነሱ ጥያቄዎች ማብራሪያዎች እና ዝርዝር መረጃዎችን መስጠት የተጠያቂነት ስረአትን ግንባታ አካል ነዉ። ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ ከንቲባ አዳነች አቤቤ

ከለውጡ በፊት የከተማዋ ነዋሪዎች ፅዱና ልምላሜን አካባቢ ለማዬት ሲፈልጉ ለጉብኝት ከከተማዋ ራቅ ብለው ወደሚገኙ አካባቢዎች ነበር የሚወጡት። ዛሬ እናንተ ወጣቶች ታድላችሁዋል።ፅዱና ልምላሜ ቦታዎች በመዲናችን ተፈጥሮላችሁዋል።" ሃጂ ሸምሱ አባስ የመዲናችን የፅዳት አምባሳደር

ዉጤታማ የስራ አፈፃፀማችንን በማጠናከር ክፍተቶችን እየዘጋን የላቀ ዉጤት ለማስመዝገብ ተዘጋጅተናል። ከንቲባ አዳነች አቤቤ

የኮሪደርና መሰረተ ልማቶች ቅንጅት በ2ኛው ምዕራፍ የኮሪደር ልማት እየተከናወነ ያለው የመሰረተ ልማት ዝርጋታ በተናበበ እና ቅንጅታዊ አሰራርን ተከትሎ በፍጥነት እየተከናወነ ይገኛል፡፡… See more

በማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት ዙሪያ የህዝብ ተሳትፎን ለማጠናከር እየተሰሩ ያሉ የግንዛቤ ማስጨበጫዎችና የተግባቦት ስራዎች የፈጠሩትን የአመለካከት ለውጥ እና ያስገኙትን ውጤት ለማወቅ ለሚካሄድ ሳይንሳዊ ጥናት የኦሬንቴሽን መድረክ ተካሄደ። ሳይንሳዊ የዳሰሳ ጥናቱ በአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ፅ/ቤት ፣በተጠሪ ተቋማት እና እንዲሁም በክፍለ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት አስከ ወረዳ ድረስ ባለው መዋቅር ባሉ ሙያተኞች የሚካሄድ ሲሆን የጥናቱ ናሙናም የተለያዩ የከተማው የህብረተሰብ ክፍሎችን ስብጥር በጠበቀ መልኩ የሚከናወን መሆኑ ተገልጿል ። በቢሮ ሃላፊ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ ም/ዋ/ስራ አስኪያጅ እና የጥናትና ትግበራ ዘርፍ ሃላፊ ወ/ሮ ይመኙሻል ታደሰ በመሩት በዚሁ የኦሬንቴሽን መድረክ ላይ ከማዘጋጃ ቤታዊ የአገልግሎት አሰጣጥ ጋር ተያይዞ ከነዋሪው ጋር የሁለትዮሽ ተግባቦቱን ለማጠናከር በመላው መዋቅር በበጀት አመቱ 10 ወራት የተከናወኑ ስራዎች እና ያመጡት የአመለካከት ለውጥ ላይ ሳይንሳዊና ሙያዊ በሆነ ጥናት ማስደገፍ ለቀጣይ ስራዎች ወሳኝ እንደሆነ ተመላክቷል። የኦሬንቴሽን መድረኩ ዋነኛ አላማ የሚሰበሰበዉ መረጃን ጥራቱን የጠበቀ ለማድረግና በማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት የህበረተሰቡን የግንዛቤ ደረጃ ለመለካትና በዚህ መነሻነት የቀጣይ ስራዎችን አቅጣጫ ለማስቀመጥ እንደሆነም ተገልጿል። በዚህ መነሻነት የሚካሄደው የፋይዳ ጥናት በዋናነት የከተማችንን ነዋሪዎች በማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት ዙሪያ ያላቸውን የግንዛቤ ደረጃ በተጨባጭ እና ትክክለኛ መረጃ ላይ በመመስረት እና በመለካት ያሉ ጥንካሬዎችን አጠናክሮ ለማስቀጠልና ክፍቶችን በማረም ረገድ ከፍተኛ ሚና እንዳለዉም ተጠቁሟል።

ፋይዳ ለኢትዮጵያ " የጎዳና ላይ ሩጫ በአዲስ አበባ በመጪው እሁድ ግንቦት 3/2017ዓ.ም በመስቀል አደባባይ እንደሚከናወን ተገለፀ " ፋይዳ ለኢትዮጵያ " የጎዳና ላይ ሩጫ በአዲስ አበባ በመጪው እሁድ ግንቦት 3/2017ዓ.ም በመስቀል አደባባይ እንደሚከናወን በዛሬው ዕለት በሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ዋና መስርያ ቤት ከብሄራዊ መታወቂያ ፕሮግራም ጽ/ቤት እንዲሁም ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ጋር የጋራ መግለጫ ተሰጥቷል። በፋይዳ ምዝገባ ላይ ያለውን የህብረተሰብ ግንዛቤ እና አረዳድ በስፖርት ንቅናቅኔ ማጠናከረ በእጅጉ አስፈላጊ መሆኑ ስለታመነበት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ከብሄራዊ መታወቂያ ፕሮግራም ጽ/ቤት ጋር በመተባበር በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ቴክኒካል ድጋፍ " ፋይዳ ለኢትዮጽያ " በሚል መሪ-ቃል የጎዳና ላይ ሩጫ በመስቀል አደባባይ እሁድ ግንቦት 3/ 2017ዓ.ም ለማከናወን ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮናስ አለማየሁ በዛሬው ዕለት በኤጀንሲው ዋና መስርያ ቤት በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ተናግረዋል። የብሄራዊ መታወቂያ ፕሮግራም ጽ/ቤት ዋና ስራ-አስኪያጅ አቶ ዮዳሄ አርዓያ ስላሴ በመግለጫው እንደገለፁት ሩጫው የምዝገባ ንቅንናቄውን ያግዛል ተብሎ የታመነበትና የፋይዳ ምዝገባን በህብረተሰቡ ውስጥ በስፋት ለማስረፅ በሌሎች ክልሎች ይህ የስፖርት ንቅናቄ እንደሚቀጥል ገልፀዋል። አቶ ዮዳሄ የፋይዳ ምዝገባ እንደ ሃገር ጅማሮው መልካም የሚባል ቢሆንም በስፋት ከመመዝገብ አኳያ አሁንም የሁሉም አካላት ርብርብ እንደሚያስፈልግ አክለዋል። በጋዜጣዊ መግለጫው ቴክኒካል ገለፃ ያደረጉት የወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ሃላፊ አቶ በላይ ደጀን ሩጫው ግንቦት 3/2017ዓ.ም መነሻ እና መዳረሻውን መስቀል አደባባይ እንደሆነና በመርሃ-ግብሩ አትሌቶችን ጨምሮ ነዋሪዎች በስፋት በሩጫው እንደሚሳተፉ ገልፀዋል። ቢሮ ሃላፊው ለሯጮች የሚሰጠው ቲ-ሸርት ነፃ መሆኑን እና ሁሉም ተወዳዳሪዎች ሜዳልያ ሽልማት እንደሚኖር የገለፁ ሲሆን ለወንዶች ፣ በሴቶች እና በፓራ ለሚወዳደሩ አሸናፊ አትሌቶች በየደረጃው ሽልማት እንደተዘጋጀ ጠቁመዋል። በሩጫ መርሃ ግብሩ ነዋሪዎች፣ ሰራተኞች ፣ ታዋቂ ሰራተኞች፣ አትሌቶች ፣ አመራሮች ፣ የውጭ ዲፕሎማቶች እና ተጋባዥ እንግዶች የሚሳተፉ ይሆናል። የብሄራዊ መታወቂያ ፕሮግራም ጽ/ቤት ከየሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት ምዝገባ ኤጀንሲ የፋይዳ ምዝገባ በጋራ ለመምራት መግባብያ ስምምነት ከተፈራረሙ በኋላ በከተማው ባደረጉት ንቅናቄ 2.3 ሚልዮን አዲስ ተመዝጋቢዎችን ላለፉት ወራት መመዝገባቸውን በዛሬው ዕለት ያስታወቁ ሲሆን ይህም በከተማው ላለፉት ሁለት ዓመት ከተመዘገበው ቁጥር አንፃር በአጭር ግዜ ከግማሽ በላይ ብልጫ እንዳለው ተነግሯል።

ዛሬ በኢትዮጵያ ጉብኝት በማድረግ ላይ ካሉት የእሥራኤል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌድዮን ሰአር ጋር በኢትዮ-እሥራኤል ግንኙነት ላይ ፍሬያማ ውይይት አካሂደናል። ሁለቱ ሀገሮቻችን በታሪክ ሥረ መሠረት ላይ የተገነባ ረዥም ዘመን የቆየ ግንኙነታቸውን ዛሬም ቀጥለዋል። ዛሬ ትብብራችን በኢኮኖሚያዊ፣ በፖለቲካዊ፣ በዲፕሎማሲያዊ፣ በማኅበራዊ እና በሌሎችም መስኮች ላይ ተጠናክሮ ቀጥሏል። Har'a walittidhufeenya Itoophiyaafi Israa'el irratti Ministira Dhimma Alaa Israa'el, Geediyoon Sa'aar Itoophiyaa daawwataa jiran waliin marii bu'a-qabeessa gooneerra. Biyyoonni keenya lachan walittidhufeenya yeroo dheeraa bu'ura seenaafi hidhataa duriii irratti hundaa'e qabu. Har'as walta'insi keenya dameewwan dinagdee, siyaasa, dippiloomaasiifi hawaasummaatiin cimee itti fufeera. Had productive discussions today on Ethio-Israeli relations with Israeli Minister of Foreign Affairs, Gideon Sa’ar, during his visit to Ethiopia. Our two nations continue to share a long-standing relationship grounded in historical roots and ancient connections. Today, our partnership spans economic, political, diplomatic, and social spheres, among many others.