en
Feedback
Addis Ababa City Manager Office

Addis Ababa City Manager Office

Open in Telegram
1 474
Subscribers
No data24 hours
-37 days
-2130 days
Posts Archive
በመዲናችን አዲስ አበባ የማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት አሰጣጥ የነዋሪዎቿን አዳጊ ፍላጎት ያረካ እንዲሆን ቀጣይነት ያለው የተቋም ግንባታ ሪፎርም ስራችን ተጠናከሮ መቀጠል ይኖርበታል ሲሉ በም/ ከንቲባ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ አስገነዘቡ። ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ ይህን ያስገነዘቡት የ2018 በጀት አመት የመጀመሪያ ሩብ አመት የእቅድ አፈፃፀምን ከተቋሙ የጠቅላላ ካዉንስል አባላት ጋር በዛሬዉ ዕለት በገመገሙበት ወቅት ነው። ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ በመሩት በዚሁ የግምገማ መድረክ ላይ በበጀት አመቱ የ1ኛ ሩብ አመት የተከናወኑ የዝግጅት ምእራፍ ስራዎች ማለትም የክረምት ወራት ንቅናቄዎች፣ የቅድመ አደጋ መከላከል፣በተለይም (የጎርፍና የመሬት መንሸራተትን መከላከል ስራዎች) የጽዳትና ውበት፣ የማንነት መለያ ስርአትን የማጠናከርና የመብራትና የኤሌክትሪክ አገልግሎት አሰጣጥ ስራዎችን እንዲሁም በሌሎች ማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት ረገድ የተከናወኑ ስራዎች የአፈፃፀም ሪፖርት ቀርቦ ውይይት ተካሂዶበታል። በመድረኩ ላይ ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ የተቋም ግንባታና የአገልግሎት አሰጣጥ ወጤታማነትን በማሳደግ የተገልጋይ እርካታን መጨመር፣የ90 ቀናት ልዩ የንቅናቄ ስራዎች ፣የተቋማት ሪፎርም፣ የሰዉ ሀብት አጠቃቀም፣በቴክኖሎጂ ስራዎችን ከመከወን፣የአቅም ግንባታና ፣የመልካም አስተዳደርን ና የግንዛቤ አሰጣጥና ግልፅነትን የመፍጠር ስራዎችን ከማጎልበት አንፃር የተከናወኑ ስራዎች መልካም የሚባል አፈፃፀም እእንዳላቸው ገልፀዋል። አክለዉም በፅ/ ቤቱ በ1ኛው ሩብ ዓመት ላይ የተመዘገቡ ዉጤቶችን በተሻለ አፈፃፀም የማጠናከር፣ የተቋማት ቅንጅትን የማሳደግ እንዲሁም በማዘጋጃ ቤታዊ ዘርፍ የሚሰጡ አገልግሎቶች ከተማዋ የደረሰችበትን የእድገት ደረጃ የሚመጥን እና የህብረተሰቡን የአገልግሎት እርካታ ደረጃ ያሟሉ መሆኑን የመፈተሽና እንዲሁም ችግር ፈቺ መሆናቸዉን በጥናት የማረጋገጥ ጉዳይ በትኩረት ሊሰራበት ይገባል ሲሉም ተናግረዋል። በተጨማሪም በመጀመሪያው ሩብ አመት የተመዘገቡ ጥንካሬዎችን አጠናክሮ በማስቀጠል የታዩ የአሰራር ክፍተቶችን ከማሟላትና የአገልግሎት ተደራሽነትን ከማስፋት እንዲሁም ከማዘመን አንፃር በሁለተኛው ሩብ አመት ከዚህ የተሻለ አፈፃፀምና የአገልግሎት አሰጣጡንም ማጠናከር በልዩ ትኩረት ሊፈፀም እንደሚገባ ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ አቅጣጫ አስቀምጠዋል። ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች https://linktr.ee/aacitymanager

እንኳን ለ2018 ዓ.ም የኢሬቻ ሆረ ፊንፊኔ በዓል አደረሳችሁ ! Happy 2018 Irreechaa Holiday! በም/ከንቲባ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ

የሆረ ፊንፊኔ ኢሬቻ በዓል እና በርካቶችን ተጠቃሚ ያደረገው የፕላስቲክ ጠርሙስን መልሶ የመጠቀም ተግባር "ብዙ የሰበሰበ ብዙ አገኝ" የሚለው መርህ ትላንት መስከረም 24/ 2018 ዓ.ም በመዲናችን በተከበረው የሆረ ፊንፊኔ የኢሬቻ በዓል ላይ ተግባራዊ ሆኖ ታይቷል። በአዲስ አበባ ከተማ በብዙ ሚሊዮኖች ተሳታፊነት በታላቅ ድምቀት በተከበረው በዚህ ባህላዊ በዓል፣ በደረቅ ቆሻሻ መልሶ መጠቀምና ዑደት ስራ ላይ የተሰማሩ ማህበራት በመልሶ መጠቀም የተለያዩ ግብአት መስሪያነትና ሃብት ለመፍጠር የሚውሉ ያገለገሉ የፕላስቲክ ጠርሙሶችን በመሰብሰብ ከፍተኛ ገቢ ማግኘት ችለዋል። በደረቅ ቆሻሻ መልሶ መጠቀምና ዑደት ማድረግ ዘርፍ የተሰማሩ አካላት እንዳሉት፣ በአግባቡ የተያዘ ደረቅ ቆሻሻ ለጤና ጠንቅ ከመሆን ይልቅ ዋና የገቢ ምንጭ እና ሀብት ሊሆን ይችላል። ይህ በዓሉ በተከበረባቸው አካባቢዎች በተለይ በኢሬቻ ፓርክ እና አካባቢው ጎልቶ ታይቷል ብለዋል። ከበዓሉ ዋዜማ ጀምሮ፣ በከተማው አስተዳደር ስር የተደራጁ የደረቅ ቆሻሻ መልሶ መጠቀም ማህበራት በተለይም 'ሀይላንድ' ውሃ ጠርሙሶችን ለመሰብሰብ በትጋት ሲሰሩ ውለዋል። እነዚህ ማህበራት ህጋዊ ባጆችን በመጠቀም የበዓሉ ታዳሚዎች የሚጠቀሙባቸውን ያገለገሉ የፕላስቲክ ጠርሙሶች ወዲያውኑ በመሰብሰብ ከፍተኛ መጠን ያለው ቆሻሻ ወደ መልሶ ማምረቻ ግብዓትነትነት እንዲለወጥ አድርገዋል። በአንድ ድንጋይ ሁለት ወፍ እንዲሉ የማህበራቱ አባላት ይህን ሥራ በማከናወን ሁለት ዋና ጥቅሞችን አስገኝተዋል። አንደኛ፣ የተሰበሰበውን ፕላስቲክ ለፋብሪካዎች በመሸጥ ለራሳቸው ከፍተኛ ገቢ በማስገኘት ኑሯቸውን አሻሽለዋል። ሁለተኛ፣ በርካታ ሰዎች በተሰበሰቡበት የኢሬቻ በዓል አካባቢዎች የከተማዋ ፅዳት እንዳይጓደል እና የአካባቢ ብክለት እንዳይፈጠር ወሳኝ ሚና በመጫወት ለከተማው አስተዳደር የፅዳት ጥረት ትልቅ እገዛ አድርገዋል። ይህ አሰራር በዓላት ባህላዊ እና ሃይማኖታዊ ፋይዳቸው እንደተጠበቀ ሆኖ፣ ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታቸው ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱን ከሚያሳዩ ተጨባጭ ምሳሌዎች አንዱ ሆኗል። በአጠቃላይ የማህበራቱ ጥረት የደረቅ ቆሻሻን ችግር ወደ ሃብትነት በመቀየር ወደ ብልፅግና ዕድል ለመቀየር በተደረገው ጉዞ ስኬታማ ምሳሌ ነው። መስከረም 25/2018 ዓ.ም ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች https://linktr.ee/aacitym

የምስጋና መልዕክት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመብራት አገልግሎት አስተዳደር ባለስልጣን የኢሬቻ ሆረ ፊንፊኔ በዓል ውብ፣ ደማቅና ሰላማዊ በሆነ መልኩ እንዲጠናቀቅ በተመደባችሁበት የክትትልና ቁጥጥር የስምሪት መንገዶች ላይ ቀንና ሌሊት ያለ ምንም እረፍት የመንገድ መብራት አገልግሎቱ በተሟላ መልኩ ያለምንም መስተጓጎል በማብራት ትልቅ አስተዋፅኦ ላበረከታችሁ የባለስልጣን መ/ቤታችን አመራሮችና ሰራተኞች፤ ህዝብ በዓሉን ለመታደም በምሽት ለነበረው እንቀስቃሴ ምቹ፤ ሰላማዊና ያለምንም ስጋት መንገዶች በቂ ብርሀን እንዲሰጡ በማድረግ በዓሉ ደማቅ ሆኖ እንዲከበር ከባለድርሻ አካላት ጋር ተቀናጅተን በጋራ መስራት በመቻላችን ለነበረው ውጤታማ ስራ በራሴና በባለስልጣኑ ስም ምስጋናዬን ከልብ አቀርባለሁ። በድጋሚ መልካም የኢሬቻ በዓል ሰብስብ ሁሴን ዋና ዳይሬክተር ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች https://linktr.ee/aacitymanager

የኢሬቻ በዓል በፅዱና ውብ በሆነ ስፍራ እንዲከበር ላደረጉ አካላት ምስጋና ቀረበ የአዲስ አበባ ከተማ ፅዳት አስተዳደር ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ ገዛኸኝ ዴሲሳ "ኢሬቻ ለሀገር ማንሰራራት!" በሚል መሪ ቃል በድምቀት የተከበረውን ሆረ ፊንፊኔ የኢሬቻ በዓል ፅዱና ውብ በሆነ አካባቢ ተከብሮ እንዲጠናቀቅ ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ 24/7 በፅዳት ስራው ላይ ለተሳተፉ አመራሮች፣ ባለሙያዎችና አጠቃላይ ለከተማው ህብረተሰብ ክፍል ምስጋና አቅርበዋል። በዓሉ ከመከበሩ በፊትና በኋላ ዘርፈ ብዙ የሆነ የጽዳት ንቅናቄ ስራዎች የተሰሩ ሲሆን በፅዳት በሂደቱ ውስጥ ከፍተኛ አመራሮችን ጨምሮ፣ የሀይማኖት አባቶች፣ አባ ገዳዎች፣ ሃደ ስንቄዎች፣ የፅዳት አምባሳደሮች፣ አርቲስቶች፣ የፀጥታ አካላት፣ የተለያዩ አደረጃጀቶች ፣ ወጣቶች እና ልዩ ልዩ የህብረተሰቡ ክፍሎች ተሳትፎ ማድረጋቸውን ዋና ዳይሬክተሩ ገልጸዋል። አቶ ገዛኸኝ አክለውም የፅዳት ስራው ስኬታማ እንዲሆን በቂ የሰው ሀይልና ቁሳቁስ በሁሉም አቅጣጫ መቅረቡን አብራርተዋል። የጽዳት ስራው በሁሉም ክ/ከተሞች በአራት ክላስተር በመክፈል አመራሮችንና ባለሙያዎችን በመመደብ ከበዓሉ ዝግጅት ምዕራፍ ጀምሮ በጥብቅ ድስፕሊን እንዲመራ ከመደረጉም በተጨማሪ ከተማዋ ባሏት አምስት የእንግዶቿ መግቢያና መውጫ በሮች ሁሉ ፅዱ እንዲሆኑ ተደርጓል ብለዋል። በመጨረሻም ዋና ዳይሬክተሩ በዚህ የፅዳት ስራ ላይ ለተሳተፉ አካላት በድጋሚ ምስጋና ያቀረቡ ሲሆን፣ በቀጣይም የከተማዋን ፅዳትና ውበት የመጠበቅ ስራው ግለቱን ጠብቆ መቀጠል እንዳለበት አሳስበዋል። ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች https://linktr.ee/aacitymanager

በአዲስ አበባ አለም አቀፍ እና አህጉራዊ ኩነቶች ፣ የአደባባይ ክብረ በአሎች በተከታታይ ከፍ ባለ ስነ-ስርአት ፣ ደማቅ ፣ ዉብ ፣ ፍፁም ሰላማዊ እና ስኬታማ ሆነዉ መከናወናቸዉ የከተማዋን የትኛዉንም ኩነት በብቃት የማስተናገድ ችሎታዋ እያደገ መምጣቱን ያሳያል ። አዲስ አበባ የአደባባይ በአሎችንና ትላልቅ ኩነቶችን የማስተናገድ አቅሟ እያደገ የመጣ እና በአለም አቀፍ ደረጃ የሚቀመጥ መሆኑን የከተማዉ አስተዳደር ከፍተኛ አመራር ገምግሟል ፣ ለአብነትም በከተማዋ የተካሄዱት የአፍሪካ የአየር ንብረት ጉባኤ ፣ የአፍሪካ ካረቢያን መሪዎች ጉባኤ፣ የህዳሴ ግድብ ግንባታ መጠናቀቅ ህዝባዊ ሰልፍ ፣ የመስቀል ደመራ ፣ ኢሬቻን ጨምሮ በሚሊዮኖች የሚቆጠር ህዝብ በነቂስ ወደ አደባባይ ወጥቶ ያለ አንዳች ኮሽታ ፣ አንድም መሰረተ ልማት ሳይበላሽ ፣ በታላቅ ስነስርአት ፣ ደማቅና ዉብ ሆነዉ እንዲስተናገዱ ማስቻል ትልቅ ትርጉም የሚሰጠዉ ነው ። ለዚህም በከተማዉ የተሰሩ የልማት ስራዎችና መሰረተ ልማቶች ወደ አደባባይ ለሚተመዉ ነዋሪና ጎብኚ የሚፈጥሩት ተጨማሪ ዉበት እና ምቾት አዲስ አበባን የስህበት ማዕከል ማድረጉን የተገመገመ ሲሆን በከፍተኛ ሁኔታ ኢኮኖሚዉን ያነቃቃና የአለም አቀፍና የአገር ዉስጥ ጎብኚዎች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩንም አንስቷል ። በዋናነት የከተማው ህዝብ በሀላፊነት ስሜት ፣ በሃይማኖት ፣ በብሄር ፣ በፓለቲካ አቋም ሳይለያይ ፣በወንድማማችነትና እህትማማችነት መንፈስ ከመንግስት ጋር በሁሉም መስክ መስራቱ ፣ የሆቴልና የአገልግሎት ሰጪ ተቋማት ፣ በከፍተኛ ዝግጅት አገልግሎት ማቅረባቸዉ ፣ እንዲሁም ምርቶቻቸዉን በከፍተኛ ሁኔታ ወደ ገበያ በማቅረብ የምርት እጥረት እና የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ከፍተኛ ሚና የተጫወቱ የአምራች ኢንዱስትሪዎች ፣ የግብርና ምርት አቅራቢዎች ፣ የፓለቲካ አመራሩ እና የፀጥታ ተቋማት በቅንጅት የተሰራ ስራ ዉጤት ስለሆነ ለሁሉም አካላት ከልብ ምስጋና ይገባቸዋል ። በመተባበርና በመደጋገፍ የተመዘገበው ስኬት ለኢትዮዽያ ትልቅ የአብሮነትና የማንሰራራት መሰረት ስለሆነ ይበልጡን አጠናክረን እናስቀጥላለን ብሏል የከተማው ከፍተኛ አመራር። ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች https://linktr.ee/aacitymanager

የ2018 የሆራ ፊንፊኔ ኢሬቻ በዓል በማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት በድምቀት እንዲከበር በተደረገ በቂ ቅድመ ዝግጅት ጽዱና ውብ በሆነች መዲናችን የአገልግሎት መስተጓጎል ሳያጋጥምና ምንም አይነት የአደጋ ክስተት ሳይኖር በሰላም መጠናቀቁን በም/ከንቲባ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ አመለከቱ። ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ የበአሉን መጠናቀቅ አስመልክተው ባስተላለፉት መልእክት በአሉ በተሟላ ማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት ያለምንም የአደጋ ክስተት እንዲከበር ቅንጅታዊ ስራን በማጠናከር በትጋት፣ በታታሪነትና በሙሉ ቁርጠኝነት የሰሩ የተቋማት፣ የክፍለ ከተማና የወረዳዎች አመራሮችና ባለሙያዎች እንዲሁም ባለድርሻ አካላትና መላው የከተማችንን ነዋሪዎች አመስግነዋል። አክለውም በማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት በኩል ለሆራ ፊንፊኔ ኢሬቻ በአል ውበትና ድምቀት አስቀድሞ የአደባባዮች፣የዋና ዋናና የውስጥ ለውስጥ መንገዶች የመብራት መሠረተ ልማት ጥገናና የማልማት ስራዎች ሲካሄድ መቆየቱን ገልፀው የኤሌክትሪክ መቆራረጥ እንዳያጋጥምና የቅድመ አደጋ መከላከል ዝግጁነትን የሚያጠናክሩ ሰፋፊ ተግባራት መከናወናቸውንም አውስተዋል። እንዲሁም መዲናችንን ጽዱና ውብ የማድረግ ስራዎች ካለፈው ነሃሴ ወር ጀምሮ በተጠናከረና ተቋማዊ ቅንጅትን ባጠናከረ አግባብ ሲሰራ መቆየቱን አስታውቀዋል። የፅዳት ስራው አሁንም በመዲናችን በሁሉም አካባቢዎች ከተማዋን የማፅዳት ተግባር በመላው መዋቅራችን ልዩ ቅንጅትና በትኩረት አየተሰራ እንደሆነ የገለፁት ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ በበአሉ የመነጩ ተረፈ ምርቶችን በዘመናዊ መንገድ የመሰብሰብና የማስወገድ ተግባር ስታንዳርዱን በጠበቀ መልኩ እየተካሄደ እንደሆነም አመልክተዋል። ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች https://linktr.ee/aacitymanager

የሆረ ፊንፊኔ ኢሬቻ አከባበር ባህላዊ እሴቱን ጠብቆ እጅግ በደመቀና ባማረ ሁኔታ ተጠናቅቋል ። የሆረ ፊንፊኔ እሬቻ ክብረ በዓል የኦሮሞ ህዝብ ብቻ ሳይሆን በርካታ ብሔር ብሔረሰቦች፣ የተለያዩ አገራት ጎብኚዎች፣ የባህልና ታሪክ ተመራማሪዎች በታደሙበት በልዩ ሁኔታ ደምቆ ፍፁም ሰላማዊ ሆኖ ተጠናቅቋል ። በኮሪደር እና በወንዝ ዳርቻዎች ልማት ያማረችዉ አዲስ አበባችን ለአደባባይ ክብረ በዓላት፣ ለበዓሉ ታዳሚያንና ከመላዉ ዓለም ለሚመጡ ቱሪስቶች ተጨማሪ ድምቀት እና ምቾት ሆናለች ። በዓሉ እጅግ ባማረ፣ ደማቅና ሰላማዊ በሆነ መልኩ እሴቱንና ቱፊቱን ጠብቆ እንዲጠናቀቅ ላደረጋችሁ አካላት ሁሉ ፣ በተለይም ለከተማችን ነዋሪዎች የላቀ ምስጋናዬን አቀርባለሁ ። ፈጣሪ ኢትዮዽያንና ሕዝቦቿን ይባርክ ከንቲባ አዳነች አቤቤ

የገዳ ስርዓት አካል የሆነው የሆራ ፊንፊኔ ኢሬቻ በዓል እሴቱን ጠብቆ በስኬት መከበሩን የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ገለፀ፡፡ *** በርካታ ታዳሚዎች፣ ልዩ ልዩ ብሔር ብሔረሰቦች፣ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች፣ የውጭ ሀገር ዜጎችና ቱሪስቶች የታደሙበት "ኢሬቻ ለሀገር ማንሰራራት" በሚል መሪ ቃል የተከበረው የዘንድሮ የሆራ ፊንፊኔ የኢሬቻ በአል በደማቅ ስነ-ስርዓት በስኬትና በሠላም መከበሩን የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አስታውቋል፡፡ በያዝነው አዲስ ዓመት በርካታ ህዝብ ወደ አደባባይ በመውጣት ያከበራቸው ኃይማኖታዊና ሕዝባዊ በዓላት ፍፁም በስኬት ተከብረው መጠናቀቃቸውን የአዲስ አበባ ፖሊስ ገልፆ የሆራ ፊንፊኔ ኢሬቻ በዓል ባህላዊ ይዘቱን ጠብቆ በድምቀትና ፍፁም ሰላማዊ ሆኖ እንዲከበር አባገዳዎች፣ አደ ሲንቄዎች፣ ፎሌዎች፣ የከተማው ነዋሪ እንዲሁም በየእርከኑ የሚገኙ የአስተዳደር አካላት ላደረጉት አስተዋፅኦ እና ኃላፊነታቸውን በአግባቡ ለተወጡ የፀጥታና የደህንነት ተቋማት አመራሮችና አባላት የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ በፀጥታና ደህንነት ተቋማት ስም ምስጋናውን አቅርቧል፡፡ ጠቅላይ መምሪያው አያይዞ እንደገለፀው በነገው እለት በቢሾፍቱ ከተማ የሚከበረው የሆራ አርሰዴ የኢሬቻ በአል በሰላም እንዲጠናቀቅ የፀጥታ ተቋማት ዝግጅታቸውን አጠናቀው ወደ ተግባር የገቡ ስለሆነ ህዝቡ የተለመደ ትብብሩን አጠናክሮ እንዲቀጥል የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ መልዕክቱን አስተላልፏል፡፡ Addis Ababa Police ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች https://linktr.ee/aacitymanager

አንዳችን የሌላው ውበት ነን፤ ኢትዮጵያዊነት መገለጫው ይህ ነው! ብሔር ብሔረሰቦች በሆር ፊንፊኔ… See more