en
Feedback

Don't get caught by a cheater! Telemetrio finds and tags such channels 👉 If you want to see the tag, subscribe 👈

Addis Ababa City Manager Office

Addis Ababa City Manager Office

Open in Telegram
1 474
Subscribers
No data24 hours
-37 days
-2130 days
Posts Archive
ዛሬ የካቲት 19 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 9:33 ሰዓት ላይ በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ-ከተማ ወረዳ 2 ካራ ቆሬ በተለምዶ ቢቂላ መናፈሻ እየተባለ በሚጠራዉ አካባቢ ለፍራሽ መስሪያ የሚሆኑ ግብአቶች በተከማቹበት መጋዘን ላይ የእሳት አደጋ ተከስቷል። የእሳት አደጋዉን ሙሉ በሙሉ ለመቆጣጠር የአደጋ ጊዜ ሰራተኞችና የጸጥታ አካላት እንዲሁም የአካባቢዉ ህብረተሰብ በአደረጉት ርብርብ እሳቱ በአቅራቢያዉ ወዳለዉ መስኪድና ሌሎች መኖሪያና ንግድ ቤቶች እንዳይዛመት ማድረግ ተችሏል። በእሳት አደጋዉ በሰዉ ለይ የደረሰ ጉዳት የለም። ለእሳትና ለሌሎች ድንገተኛ አደጋዎች እንዲሁም ለአንቡላንስ አገልግሎቶች በ939 ፈጥነዉ ያሳዉቁ! ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ! Facebook:- 👇👇👇👇 https://www.facebook.com/CITYMANAGER1 Telgram:- 👇👇👇👇 https://t.me/aacitymanager Twitter:- 👇👇👇👇 https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r YouTube:- 👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s Tiktok 👇👇👇👇 https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager... Website 👇👇👇👇 https://www.aacitymanger.gov.et

የፕሮግራም ጥቆማ ዛሬ ምሽት ከ2:00 ጀምሮ በቀጥታ በሚተላለፈው ‘አገልጋይ’ ፕሮግራማችን የፅዳት አስተዳደር ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ከሆኑት ዶ/ር እሸቱ ለማ ጋር በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ቆይታ ያደርጋል ይጠብቁን! AMN-Addis Media Network

የፕሮግራም ጥቆማ ነገ ምሽት ከ2:00 ጀምሮ በቀጥታ በሚተላለፈው ‘አገልጋይ’ ፕሮግራማችን የፅዳት አስተዳደር ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ከሆኑት ዶ/ር እሸቱ ለማ ጋር በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ቆይታ ያደርጋል ይጠብቁን!… See more

የፕሮግራም ጥቆማ ነገ ምሽት ከ2:00 ጀምሮ በቀጥታ በሚተላለፈው ‘አገልጋይ’ ፕሮግራማችን የፅዳት አስተዳደር ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ከሆኑት ዶ/ር እሸቱ ለማ ጋር በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ቆይታ ያደርጋል ይጠብቁን!… See more

በአዲስ አበባ ከተማ የደረቅ ቆሻሻ መልሶ መጠቀምና ኡደት ማድረግ ዙሪያ በጽ/ ቤቱ በተካሄደ ጥናት ከባለድርሻ አካላት ጋር የተካሄደ ውይይት ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ! Facebook:- 👇👇👇👇 https://www.facebook.com/CITYMANAGER1 Telgram:- 👇👇👇👇 https://t.me/aacitymanager Twitter:- 👇👇👇👇 https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r YouTube:- 👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s Tiktok 👇👇👇👇 https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager... Website 👇👇👇👇 https://www.aacitymanger.gov.et See less

መዲናችን አዲስ አበባ ጽዱ፣ ውብ እና ማራኪ እየሆነች ትገኛለች። ይህም በአለምዓቀፍ መድረኮችም እውቅና እየተሰጠው ነው።ሰሞኑንም በጃፓን በተካሄደው የጃይካ አለምአቀፍ ፎረም ላይ በጽዱ ከተሞች ኢኒሼቲቭ ፎረም ተሳታፊዎች በአዲስ አበባ በጽዳት መስክ የመጣው ለውጥ አድናቆት ተችሮታል። ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ! Facebook:- 👇👇👇👇 https://www.facebook.com/CITYMANAGER1 Telgram:- 👇👇👇👇 https://t.me/aacitymanager Twitter:- 👇👇👇👇 https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r YouTube:- 👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s Tiktok 👇👇👇👇 https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager... Website 👇👇👇👇 https://www.aacitymanger.gov.et See less

የህብረተሰቡን የአገልግሎት ጥያቄ ለመመለስ የተጠሪ ተቋማትን ድጋፍና ክትትል የማጠናከር ስራ መሰራቱን የኮልፌ ክፍለ ከተማ ስራ አስኪያጅ ፅህፈት ቤት አስታወቀ፡፡ የፅዳት አስተዳደር የሲቪል ምዝገባና ነዋሪዎች አገልግሎት እንዲሁም ስራ አስኪያጅ ፑልን የሚመራው የክፍለ ከተማው ስራ አስኪያጅ ፅህፈት ቤት በዛሬው እለት የ2017 በጀት ዓመት የ6 ወር አፈጻጸም ተጠሪ ተቋማት፣የወረዳና የክፍለ ከተማ የዘርፍ ባለሞያና አመራሮችና ባለድርሻ አካላት የእውቅና የምስጋና መርሀ ግብር አካሔዷል። በመድረኩ ፅህፈት ቤቱ ፅዳት አስተዳደር ፣የሲቪል ምዝገባና ነዋሪዎች አገልግሎት፣የፋይናንስ ፑልን ተጠሪ ተቋምነት እንዲሁም የውሃና ፍሳሽ፣ኤሌክትሪክ፣የእሳትና ድንገተኛ አደጋ ስጋት፣የትራፊክ ማኔጅመንትና የመንገድ ትራንስፖርት ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤቶች በ2017 በጀት አመት 6 ወር የተሰሩ ስራዎች ቀርበው ውይይት ተደርጎበታል፡፡ የክፍለ ከተማ ስራ አስኪጅ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ዳኛቸው አበበ ተቋሙ የአቅም ግንባታ ስልጠናዎችን በማስጠት፤ድጋፍና ክትትል ተግባራትን የማጠናከር ስራዎች መስራቱንና ከተጠሪ ተቋማት ጋር ቅንጅታዊ አሰራርን በማጠናር ለህብረተሰቡን የሚሰጠውን አገልግሎት ማቀላጠፍ መቻሉን ገልፀዋል፡፡ ኃላፊው አክለውም የህብረተሰቡን የአገልግሎት ጥያቄ ለመመለስ የተጠሪ ተቋማትን ድጋፍና ክትትል በማጠናከር ተቋማት የሚነሳባቸውን ችግር እንዲፈቱ በቅርበት ውይይት በማድረግ መፍታት መቻሉን አስታውቀዋል፡፡ በመርሀ ግብሩ የተሻለ አፈፃፀም የነበራቸው ቡድኖች ባለድርሻ አካላት፣ተጠሪ ተቋማትና ወረዳዎች እውቅናና ሽልማት የተሰጠ ሲሆን በተደረገው የ3 ተቋማት ማለትም ስራ አስኪያጅ፣የፅዳት አስተዳደር፤የሲቪል ምዝገባና ነዋሪዎች አገልግሎት አማካን ውጤት ወረዳ 04፣ 11 እንዲሁም ወረዳ 1 ከ1ኛ እስከ 3ኛ በመውጣት ሰርተፊኬት ተሸላሚ ሆናሆናል። Kolfe Keranio Communication /ኮልፌ ቀራኒዮ ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ! Facebook:- 👇👇👇👇 https://www.facebook.com/CITYMANAGER1 Telgram:- 👇👇👇👇 https://t.me/aacitymanager Twitter:- 👇👇👇👇 https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r YouTube:- 👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s Tiktok 👇👇👇👇 https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager... Website 👇👇👇👇 https://www.aacitymanger.gov.et

በክፍለ ከተማው እየተሰራ ያለው ኮሪደር ልማት ስራ የከተማ ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት የመስክ ቅኝትና ጉብኝት ተካሄደ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ የሚሰራው የሁለተኛ ዙር ሰባተኛው ኮሪደር ልማት ስራ ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት በዛሬው እለት የመስክ ቅኝትና ጉብኝት ተካሂዷል። በእለቱም በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ ፣ የክፍለ ከተማው ዋና ስራ አስፈፃሚ ወይዘሮ ካባ መብራቱ ጨምሮ ሌሎች የከተማና የክፍለ ከተማ የኮሪደር ልማት አስተባባሪዎች እንዲሁም የወረዳ አመራሮች ተገኝተዋል። በመስክ ጉብኝቱም ከሳር ቤት - መካኒሳ - ፉሪ አደባባይ የሚሸፍነው ሁለተኛው ዙር 7ኛው የኮሪደር ልማት ስራው የደረሰበት ደረጃ አበረታች መሆኑ የተገለፀ ሲሆን በቀጣይ ስራው በተያዘለት ጊዜ ተሰርቶ ለማጠናቀቅ መስተካከል ያለባቸውን በመለየት ለተሻለ አፈፃፀም ዝግጁ መሆን እንደሚገባ የትኩረት አቅጣጫ ተቀምጧል። በ2ኛ ዙር የአዲስ አበባ ከተማ የኮሪደር ልማት 7ኛ ኮሪደር ወይም ሳርቤት - መካኒሳ - ፉሪ አደባባይ ኮሪደር በንፋስ ስልክ ላፍቶና በልደታ ክፍለ ከተሞች እየተሰራ መሆኑ ይታወቃል:: ከዚህ ውስጥ ከመካኒሳ እስከ ፉሪ አደባባይ ያለው የኮሪደር ልማት በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወሰን ውስጥ እየተሰራ ያለ ሲሆን ስራውም በመገባደድ ላይ ይገኛል። የሳርቤት- መካኒሳ - ፉሪ አደባባይ ኮሪደር (የሁለተኛ ዙር ኮሪደር ልማት አካል የሆነው "7ኛ ኮሪደር" ) በንፋስ ስልክና ልደታ ክ/ከተሞች አስተዳደር ውስጥ እየተሰራ የሚገኝ ሲሆን ከ16 ኪሎሜትር በላይ ርዝመት ያለው ፕሮጀክት ነው:: የካቲት 17/ 2017 Lafto Communication- ላፍቶ ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ! Facebook:- 👇👇👇👇 https://www.facebook.com/CITYMANAGER1 Telgram:- 👇👇👇👇 https://t.me/aacitymanager Twitter:- 👇👇👇👇 https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r YouTube:- 👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s Tiktok 👇👇👇👇 https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager... Website 👇👇👇👇 https://www.aacitymanger.gov.et

የሲቪል ምዝገባና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ አንድ የወረዳ ጽ/ቤት አመራር እና አንድ ሰራተኛውን በፖሊስ ቁጥጥር ስር እንዲውሉ አደረገ ኤጀንሲው በደረሰው የተገልጋይ ጥቆማ የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ወረዳ 9 ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ተስፋዬ አያለው እንዲሁም የነዋሪ መረጃ፣ ህትመት ስርጭት እና ቁጥጥር ቡድን መሪ አቶ መንግስቱ እጅጉ በጋራ በመመሳጠር ላልተገባ ሰው አገልግሎትን በገንዘብ ለመሸጥ በ10 ሺህ ብር ተደራድረው የዲጂታል ምዝገባ በማከናወን ላይ ሳሉ በተደረገው ክትትል እጅ ከፍንጅ ተይዘዋል። የተቋሙ የስነ-ምግባር እና ፀረ-ሙስና ክፍል ከፖሊስ ጋር በመተባበር ላለፉት ሶስት የስራ ቀናት ክትትል ሲያደርግ በመቆየት ተጠርጣሪዎቹ ዛሬ የካቲት 17 በጽ/ቤቱ ውስጥ በቁጥጥር ስር እንዲውሉ ተደርጓል። ተቋሙ በክትትሉ የተደራጁ የድምፅ ቅጂ እና ተጨማሪ ማስረጃዎችን ለፖሊስ አስረክቧል። ውድ ነዋሪዎቻችን ተቋማችን እራሱን ከህገ-ወጥነት ለመከላከል የስነ-ምግባር እና ፀረ-ሙስና የስራ ክፍል የመረጃ አቅምን እያጠናከረ ያለና የዲጂታል አገልግሎቱም ኦዲት የሚደረግበት ስርዓት የዘረጋ በመሆኑ ይህንን ተቋማዊ ቆራጥ አቋም በመረዳት ከህገ-ወጥ ደላሎች እና አገልግሎትን በገንዘብ ከሚሸጡ እራሳችሁን እንድትጠብቁ እንዲሁም እራሳችሁም ተባባሪ ከመሆን እንድትቆጠቡ ኤጀንሲው እያሳሰበ መሰል ሁኔታዎች በአገልግሎታችን ላይ ሲገጥማችሁ በ7533 የነፃ የስልክ መስመር ወይም ከታች ባለው የፌስቡክ ገፅ በቀጥታ ሊያገኙን ይችላሉ። Addis Ababa CRRSA - Civil Registration and Residency Service Agency ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ! Facebook:- 👇👇👇👇 https://www.facebook.com/CITYMANAGER1 Telgram:- 👇👇👇👇 https://t.me/aacitymanager Twitter:- 👇👇👇👇 https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r YouTube:- 👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s Tiktok 👇👇👇👇 https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager... Website 👇👇👇👇 https://www.aacitymanger.gov.et

ለተለያዩ ተቋማት የአደጋ መከላከል መስፈርቶች ምን ምን ናቸው? አንድ ህንፃ ሊያሟላቸው የሚገቡ የአደጋ መከላከል መስፈርቶች እንደሚከተለው ቀርበዋል። # የእሳት ማጥፊያ፣ #አውቶማቲክ የእሳት አደጋ መከላከያ ማስገጠም፣ #የአደጋ መከላከል ምልክቶችን በሚታይ ቦታ ማስቀመጥ፣ #አመቺ የአደጋ ጊዜ መውጫ የግድ ሊኖረው ይገባል፡፡ በመዲናችን ህንጻዎች ሲገነቡ አስገዳጅ የደህንነት መስፈርቶችን ማሟላት እንደሚገባቸው የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ባለሙያዎች ይገልጻሉ ። በከተማችን የተገነቡ ቤቶችና ህንጻዎች በአብዛኛው የሚገነቡበትን አከባቢ ሁኔታ ታሳቢ ያደረገ የዲዛይን ስታንዳርድ፣ ዲዛይንና ግንባታ በሚፈለገው ደረጃ ያለማድረግ፤ ግንባታዎቹ የተፈጥሮና ሰው ሰራሽ አደጋዎችን መቋቋም እንዲችሉ የአደጋ ደህንነትን አሟልተው በሚፈለገው መጠንና ጥራት አለመገንባት፤ ከግንባታ በፊት፣ በግንባታ ወቅትና በመጠቀም ሂደት የአደጋ ደህንነታቸውን በሚመለከተው ተቋማት አለማረጋገጥ የሚስተዋሉባቸው ችግሮች እንደሆኑ የዘርፉ ባለሙያዎች ይገልጻሉ። ተቋማት ማሟላት ያለባቸውን የአደጋ ደህንነት ማሟላት፤ ከግንባታ በፊት፣ በግንባታ ወቅትና በመጠቀም ሂደት የአደጋ ደህንነትን ታሳቢ ያደረጉ ስራዎችን በመስራት ደህንነታቸውን በየጊዜው ማረጋገጥ ወሳኝ መሆኑንም የዘርፉ ባለሙያዎች ያመለክታሉ። ህንጻዎች ለተገነቡበት ዓላማ ብቻ ማዋል፤ የአደጋ ደህንነት ስታንዳርዶችን የሚያሟሉ ግብዓቶችን መጠቀም፤ እሳትንና ጎርፍ የሚቋቋሙ ግብዓቶችን መጠቀም፤ የመሬት መንቀጥቀጥ፣ መስመጥንና መሬት መናድን ታሳቢ ያደረጉ ግንባታዎችን መገንባት፣ አደጋ ቢከሰት እንኳን ሊደርስ የሚችለውን ጉዳት ለመቀነስ ጠቃሚ እርምጃዎች መሆናቸውን ባለሙያዎች ይጠቅሳሉ! በማንኛውም ሁኔታ ቅድሚያ ለደህንነታችን እንስጥ! Safety First! ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ! Facebook:- 👇👇👇👇 https://www.facebook.com/CITYMANAGER1 Telgram:- 👇👇👇👇 https://t.me/aacitymanager Twitter:- 👇👇👇👇 https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r YouTube:- 👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s Tiktok 👇👇👇👇 https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager... Website 👇👇👇👇 https://www.aacitymanger.gov.et