1 474
Subscribers
No data24 hours
-37 days
-2130 days
Posts Archive
መዲናችን አዲስ አበባን መላው ነዋሪዎቿን በማስተባበር እንደ ስሟ ውብና ፅዱ በማድረግ ሂደት የከተማ አስተዳደሩ አመራሮች እያደረጉ ያለውን ንቁ ተሳትፎ አጠናክሮ ማስቀጠል ይገባናል ሲሉ በምክትል ከንቲባ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ወ/ ሮ ሂክማ ከይረዲን አስታወቁ::
በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ "ከተማዬን እያፀዳሁ የአመራርነት ሚናዬን እወጣለሁ" በሚል መሪ ቃል የከተማ :- የክፍለ ከተማው እና በአስሩም ወረዳዎች ላይ ያሉ 400 የሚጠጉ አመራሮች በወረዳ 5 ሰሚት ጊዮርጊስ ከተማ አካባቢ ከተማ አቀፍ የፅዳት ዘመቻ ንቅናቄ አካሂደዋል።
በዚህ የፅዳት ንቅናቄ ላይ ክብርት ሂክማ ከይረዲን ባስተላለፉት መልእክት በኦርቶዶክስ ክርስትናና በእስልምና እምነት ተከታዮች የፆም ወቅት መጀመሪያ ላይ የጾምና የፀሎት ጊዜያችንን ከተማችንን ውብና ፅዱ አድርገን ለመቀበል ማህበረሰቡን በማስተባበር በሁሉም ክ/ከተሞችና ወረዳዎች ፅዳት መካሄዱ የሚበረታታ ተግባር ነው ብለዋል::
አክለውም አካባቢያችንን ከቆሻሻ በማፅዳት አሉታዊ አስተሳሰቦችንና አመለካከቶችን በመግራት ሰላማችንና ፍቅራችንን እያጠናክርን ማህብረሰቡ ፅዳትን ባህል እስኪያደርግ ድረስ የፅዳት ስራዎችን በአብሮነትና በትብብር አጠናክረን ማስቀጠል ይገባናል ሲሉም አስገንዝበዋል::
የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ታረቀኝ ገመቹ በበኩላችው በከተማ ደረጃ የሚካሄደው የአመራሮች የፅዳት ዘመቻ እንደ ክፍለ ከተማችን በተጠናከረ ሁኔታ ህብረተሰቡን በማስተባበር በቀጣይ ሶስት ወራት የዘጠና ቀን እቅድ ጋራ አስተሳስረን አካባቢን በማፅዳት የከተማዋን ውብ ገፅታ ማስጠበቅ አለብን ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል።
ከተማዋን ፅዱና ውብ ለነዋሪዎቿ ምቹ ለማድረግ በየደረጃው የሚገኘው የአመራሩ ሚና ከፍተኛ ነው ያሉት የፅዳት አስተዳደር ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር እሸቱ ለማ በፅዳቱ ዘርፍ አመራሩ ከፊት ሆኖ የመምራትና የማስተባበር ስራውን አጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ገልፀዋል።
አክለውም ዋና ዳይሬክተሩ የፅዳት ስራ በመንግስት አቅም ብቻ የሚደረግ ተግባር ሳይሆን የሁሉንም አካላት ቅንጅታዊ ተሳትፎ የሚጠይቅ በመሆኑ ሁሉም የከተማዋ ነዋሪ ህብረተሰብ ያለ ማንም ቀስቃሽ ወጥቶ የአካባቢውን ፅዳት መጠበቅ እንደሚገባ አሳስበዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች ተወካዮች ጋር ያደረጉት ውይይት
ትክክለኛውንየአዲስሚዲያኔትዎርክዲጂታልሚዲያየትስስርአውታሮችንበመቀላቀልቤተሰብይሁኑን!
https://linktr.ee/AddisMediaNetwork
AMN - የካቲት 29/2016 ዓ.ም
በክፍለ ከተማው የሚስተዋሉ ችግሮችና የህዝብ ጥያቄዎዎችን በፍጥነት ለመፍታት ቅንጅታዊ አሰራር ወሳኝ ሚና እንደሚኖረው ተመለከተ
በቂርቆስ ክፍለ ከተማ የማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎቶችን አሳጣጥ ለማሻሻል የሚረዳ የተቋማት ቅንጅታዊ አሰራር ፎረም ምስረታ ተካሄደ፡፡
የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት የቅንጅታዊ አሰራር ያለፉት 8 ወራት አፈጻጸም ግምገማና የቀጣይ ስራዎችን ለማሳለጥ የሚረዳ የፎረም ምስረታ አካሂዷል፡፡
በምስረታ ፕሮግራሙም የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ምክትል ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ፍትሃለው ከፍያለው ባስተላለፉት መልዕክት ቅንጅታዊ አሰራር የሚያጋጥሙ ችግሮችን በመፍታት የህዝብ እርካታን ለማሻሻል አስፈላጊ በመሆኑ ትኩረት ሰጥተን ልንሰራበት የሚገባ ትልቅ ስራ መሆኑን አመላክተዋል ፡፡
በአፈጻፀም ግምገማው ወቅት የቅንጅት ስራው ውጤት የተመዘገበበት መሆኑ ከተሳታፊዎች የተገለፀ ሲሆን አሁንም ከአገልግሎቶች መቆራረጥና የቅንጅት ጉድለት ጋር ተያይዞ ከህብረተሰቡ የሚነሱ ቅሬታዎችን መፍታት አስፈላጊ መሆኑ ተገልጻል፡፡
በመድረኩም በጽ/ቤቱ አስተባባሪነት ተጠሪ ከሆኑና ባለድርሻ አካላት ጋር የሲቪል ምዝገባና ነዋሪነት አገልግሎት አሰጣጥ ማሻሻያ ፎረም፤የደረቅ ቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ ቅንጅት ፎረም እንዲሁም የእሳትና ድንገተኛ አደጋ መቆጣጠር ፎረም በከተማ ደረጃ የተደረገውን ሪፎርም መነሻ በማድረግ የተቋቋሙ ሲሆኑ የ3ቱም ፎረም አባላት ኃላፊዎች በተገኙበት የትስስር ሰነድ መፈራም ስነ ስርዓት ተካሂዷል፡፡
በመጨረሻም የቅንጅት ስራውን ከምንጊዜውም በላይ ማጠናከር፤የግንዛቤ ክፍተቶችን መሙላት፤የኮሪደር ልማት ስራው ላይ ተቀናጅቶ ውጤት ማምጣትና ሌሎች በክፍተት የተነሱ ችግሮችን በትብብር መፍታት አስፈላጊ መሆኑን የጽ/ቤቱ ኃላፊ አቶ አብድልሃዲ ረሺድ በመግለጽ መድረኩ ተጠናቋል፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ፅ/ቤት "ሴቶችን እናብቃ ሰላምና ልማትን እናረጋግጥ "በሚል መሪ ቃል በአለም ለ113ኛ በሀገራችን ለ48ኛ ጊዜ እየተከበረ ያለውን የሴቶቸ ቀን ከፅ/ቤቱ ሴት ሠራተኞች ጋር በድምቀት ተከበረ ::
እለቱን አሰመልክቶ በቢሮ ኃላፊ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ም/ዋ/ ስራ አስኪያጅ ወ/ሮ ቅድስት ወ/ ጊዮርጊስ እንደተናገሩት የከተማ አስተዳደሩ የሴት አመራሮችን የውሳኔ ሰጭነት ሚና በመገንዘብ ውጤታማ የአመራርነት ተሳትፎአቸውን እንዲያጎለብቱ እያደረገ ያለው ጥረት አበረታች ነው ሲሉ ገልፀዋል::
አክለውም እኛ በውሳኔ ሰጭነትና በሃላፊነት ላይ ያለን ሴት አመራሮች ይህንን መልካም እድል በመጠቀም የሴቶችን ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ተጠቃሚነታቸውን እንዲያሳድጉና ፖለቲካዊ ተሳትፏቸውን እንዲያጎለብቱ በማብቃት ለአገራችን ብልፅግና የበኩላችን ድርሻ መወጣት ይገባናል ብለዋል።
እንኳን ለዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን አደረሳችሁ!
“ሴቶችን እናብቃ ልማትና ሰላምን እናረጋግጥ!” በሚል መሪ ቃል ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀንን በዓድዋ ድል መታሰቢያ የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ክብርት ሳህለወርቅ ዘውዴ በተገኙበት በድምቀት አክብረናል።
የሴቶችን መብትና የፆታ እኩልነት በማረጋገጥ በሃገራችን ፖለቲካዊ፣ ማህበራዊ ፣ ኢኮኖሚያዊ እንዲሁም የልማት ተሳትፎዎች ላይ ያላቸውን ድርሻ ለማሳደግ በሁሉም ዘርፍ እየሰራን ነው።
እስከአሁን ብዙ ጥረት ሲደረግ ቢቆይም፣ የሴቶችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነትና እኩል ተሳታፊነት ማረጋገጥ ብዙ ክፍተት ስላለበት ተጨማሪ ጥረትና ስራ ይፈልጋል።
ይህን ክፍተት ማጥበብ ደግሞ ከማንም በላይ እድሉን አግኝተን ሀገር እየመራን ካለነው ሴት የፖለቲካ አመራሮች ይጠበቃል።
እኛ በየተሰማራንበት ውጤታማ ከመሆን አልፈን እድሉን ላላገኙ ሴቶች ምሣሌዎች፣ በር ከፋቾች፣ ማበረታቻዎችና እንደሚችሉ ማሳመኛ መረጃና ማስረጃዎች መሆን እንችላለን።
ከዚህም አልፎ የሴቶች ተጠቃሚነትንና ሁለንተናዊ ተሳትፎን ለማረጋገጥ የሚችሉ ተጨባጭ ስራዎችን የመስራት ኃላፊነት አለብን።
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ!
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
በሰውና በንብረት ላይ ሊደርስ የሚችለውን የኤሌክትሪክ አደጋ በጋራ እንከላከል!
=============
ኤሌክትሪክ ጠቀሜታው እጅግ ከፍተኛ የመሆኑን ያህል ተገቢው ጥንቃቄ ካልተደረገ በአጠቃቀም ወቅት በሰውና በንብረት ላይ አደጋ ሊያደርስ ይችላል፡፡ ባለማወቅም ሆነ በቸልተኝነት አስፈላጊው ቅድመ-ጥንቃቄ ካልተደረገ ኤሌክትሪክ በህይወት፣ በአካል እንዲሁም በንብረት ላይ በቅጽበት አደጋ ሊያደርስ እንደሚችል መረዳት ያስፈልጋል፡፡
ታዲያ የኤሌክትሪክ አደጋን መከላከል እንዴት እንችላለን? የማንስ ኃላፊነት ነው?
• የኤሌክትሪክ ሽቦዎች ከቆሮቆሮ አጥር፤ ከልብስ ማስጫ ሽቦዎች ወዘተ ጋር እንዳይገናኙ ማድረግ፣
• የኢንዱስትሪ ወይንም የቤት ውስጥ የኤሌክትሪክ መስመር ዝርጋታ በባለሙያ እንዲሰራ ማድረግ፣
• የግንባታ ሥራዎች በሚከናወንበት ወቅት መወጣጫዎች፣ የመሰሪያ ማሽነሪዎች ወዘተ ከኤሌትሪክ መስመሮች በቂ ርቀት ላይ መሆናቸውን ማረጋገጥ፣
• ማንኛውንም በኤሌክትሪክ የሚሰራ መሳሪያ ለማፅዳትና ለመጠገን ሲፈለግ ከሶኬት መላቀቁን ማረጋገጥ፣
• በአንድ ሶኬት ላይ ተደራራቢ ማከፋፈያዎችን በማገናኘት ኤሌትሪክ አለመጠቀም፣
• የኤሌክትሪክ መስመሮች በሚያልፉባቸው አካባቢዎች ዛፎች ሲቆረጡ መስመር ላይ እንዳይወድቁ ጥንቃቄ ማድረግ፣
የመሳሰሉ የጥንቃቄ መልዕክቶች ተግባራዊ በማድረግ በህይወት፣ በአካልና በንብረት ላይ የሚደርሰውን የኤሌክትርክ አደጋን በጋራ እንከላከል፡፡
ፈጣን እና ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት እነዚህን አድራሻዎች ይከተሉ፤ ቤተሰብ ይሁኑ!
Facebook:-
👇👇👇👇
https://www.facebook.com/CITYMANAGER1
Telgram:-
👇👇👇👇
https://t.me/aacitymanager
Twitter:-
👇👇👇👇
https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r
YouTube:-
👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s
በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ወ/ሮ ሂክማ ከይረዲን የሚመራው ልዑካን ቡድን በለሚኩራ ክ/ ከተማ በዘጠና ቀናት እየተሠሩ ያሉ የከተማ ግብርና ስራዎችን እንዲሁም የኮሪደር ልማት ስራዎች ያሉበትን ደረጃ በዛሬው እለት የካቲት 28/2016 ምልከታ አደረጉ።
የሪፎርም አስተግባሪ ኮሚቴ ሪፎርም ባካሄዱ በ16ቱ ተቋማት የተጀመረውን የሰራተኞች የስልጠና ሂደት ገመገመ፡፡
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
ፐብሊክ ሰርቨስ ቢሮ፤ የካቲት 28 ቀን 2016ዓ.ም
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የፐብሊክ ሰርቨስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ በአገልግሎት ሰጭ ተቋማት ያካሄደው ሪፎርም ሙያዊ ስነ ምግባርን የተላበሰ ብቃት ያለውና ለተገልጋዩ ህብረተሰብ በተገቢው የሚያገለግል ሲቪል ሰርቫንት መገንባት አላማ ያደረገ መሆኑ የሚታወስ ሲሆን ይህንንም ተከትሎ ሪፎርም ባካሄዱት 16ቱ ተቋማት በአዲስ መልክ ለተመደቡ ሰራተኞች የባህሪ ቀረፃና የአተገባበር ክህሎት የሚያዳብሩ ስልጠናዎች ለሰራተኛው በሁለት ዙር እየተሰጠ ይገኛል፡፡
ከዚህም ጋር ተያይዞ የሪፎርም አስተግባሪ ኮሚቴው የተጀመረውን የሰራተኞች የስልጠና ሂደት የገመገመ ሲሆን የሚሰጡት ስልጠናዎች ከስልጠና ስታንዳርድ አንፃር ወቅቱን እና የሰልጣኙን ክፍተት ያማከለ መሆኑን በግምገማው አንስቷል፡፡
በስልጠና ወቅት የሰልጣኞች የሰዓት አጠቃቀም ክፍት መኖሩን የጠቀሰው አስተግባሪ ኮሚቴው በሁለተኛው የስልጠና ዙር ሁሉም ምደባ ያገኙና በምደባ ያልተካተቱ ሰራተኞችን ተሳታፊ በማድረግ ስልጠናው ተደራሽ እንደሚደረግ የተጠቀሰ ሲሆን ከመጀመሪያው ዙር ከነበሩ የሰዓት አጠቃቀም በማሻሻል ሁሉም ሰራተኛ በትኩረት ስልጠናውን እንዲከታተል በማድረግ የስልጠናዎቹን ዓላማ ከግብ ማድረስ እንደሚገባ ተገልጿል፡፡
ዛሬ ከአዲስ አበባ ነዋሪዎች ጋር ውይይት አድርገናል። መዲናችን ከከተማ መስፋፋት ጋር የሚመጣ ፍላጎትን የሚያጎሉ ወሳኝ የሆኑ የእድገት እና የለውጥ ሂደት ውስጥ ትገኛለች። የዛሬው አይነት ስብሰባዎች በሚታዩ ክፍተቶች የጋራ ግንዛቤ ለመያዝ ብሎም መልካም አጋጣሚዎችን ለመለየት እጅግ አስፈላጊ ነው።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)
የጥንቃቄ መልእክት
በከተማችን አዲስ አበባ በአሁኑ ወቅት ያለው የአየር ፀባይ ቅዝቃዜን ለመከላከል በሚልና ለምግብ ማብሰያነትም ጭምር ሰዎች ከሰልን ሲጠቀሙ እንመለከታለን::
ይሁንና ከሰል በአግባቡና በጥንቃቄ ካልተያዘ ሕይወትን ከማሳጣት እስከ የዕድሜ ልክ ህመም እንደሚዳርግ ባለሙያዎች ይገልጻሉ።
ከሰልን ሲጠቀሙ አስፈላጊውን ጥንቃቄ ካላደረጉ÷ የከሰል ጭስ ሞትን ጨምሮ የዕድሜ ልክ ህመም ለሆኑት የአዕምሮ ጉዳትና የልብ በሽታ ያጋልጣል፡፡
ከዚህ ጋር ተያይዞ የተካሄዱ ጥናቶች እንደሚያመላክቱት÷ የከሰል ጭስ በዓይን የማይታይና ሽታ አልባ መርዛማ ጋዝ አለው፡፡
ይህ ጋዝ የሚፈጠረውም ጋዝ፣ ዘይት፣ ከሰል ወይም እንጨት ሙሉ በሙሉ ተቃጥለው ባለማለቃቸው ነው፡፡
የከሰል ጭስ በአካባቢያችን በሚኖርበት ጊዜ አየር ወደ ውስጡ በሚሳብበት ጊዜ÷ በደም ውስጥ በመግባት የቀይ የደም ህዋስ አካል የሆነውና ኦክስጅን ተሸክሞ ለተለያዩ የሰውነት ክፍሎች ከሚያደርሰው ሂሞግሎቢን ጋር በመቀላቀል ካርበ ኦክሲሄሞግሎቢን ይሆናል፡፡
ይህ ከሆነ በኋላ ደም ኦክስጅን መሸከሙን ያቆማል፤ በዚህ የተነሳ የህዋሶቹ አነስተኛ ክፍሎች ይጎዳሉ፤ ብሎም ይሞታሉ፡፡
በከሰል ጭስ ወይም በካርበን ሞኖክሳይድ የተጠቃ ሰው የሚያሳያቸው ምልክቶች፥
የራስ ምታት፣ ራስ ማዞርና መታመም፣ የድካም ስሜትና ግራ መጋባት፣ ሚዛንን ለመጠበቅ መቸገር፣ የዕይታና የትውስታ ማጣት፣ ራስን መሳት፣ በአንድ ነገር ላይ አትኩሮት ማጣት፣ የሆድ ሕመም እንዲሁም ለመተንፈስ መቸገር ምልክቶች ሊታዩበት እንደሚችሉ ባለሙያዎች ያስረዳሉ፡፡
የከሰል ጭስን እንዴት መከላከል ይቻላል፥
በከሰል ምግብ ማብሰል ሲያስፈልግ በቂ አየር እንዲያገኝ (ከተቻለ ከቤት ውጭ) ከቤት ውጭ ማብሰል ካልተቻለ ደግሞ ሙሉ በመሉ ከተቀጣጠለና ጭሱ መጥፋቱ ሲረጋገጥ ወደ ቤት ማስገባት ይመከራል፡፡
በተጨማሪም የከሰል ምድጃ እየተጠቀሙ በር እና መስኮት አለመዝጋት፣ በከሰል ምግብ አብስለው ሲጨርሱ በውኃ ማጥፋትና በርና መስኮት በመክፈት ቤቱን ማናፈስ እንዲሁም ከሰል ቤት ውስጥ አለማቀጣጠልን ባለሙያዎች ይመክራሉ፡፡
ከዚህ ባለፈም ከሰል ቤት ውስጥ አቀጣጥሎ ማሸለብ ወይም መተኛት አደጋው የከፋ በመሆኑ ከእነዚህ ድርጊቶች ይቆጠቡ።
የጥንቃቄ መልእክቱ ለሌሎችም እንዲደርስ ያጋሩ:;
ለጎርፍ አደጋ በተጋለጡ ቦታዎች ላይ አስቸኳይ መፍትሄ ለመስጠት እንዲቻል ያለመ መድረክ ከባለድርሻ አካላት ጋር ተካሄደ።
በአዲስ አበባ ከተማ ለጎርፍ አደጋ የተጋለጡና በጥናት በተለዩ ቦታዎች ላይ የጥናት ዉጤቱ ሰነድ ቀርቦ ዉይይት ተካሂዶበታል።
ዛሬ የካቲት 26 ቀን 2016 ዓ.ም በተካሄደዉ ዉይይት ላይ የጎርፍ አደጋን አስቀድሞ ለመከላከል የሚያስችል ሰነድ በኮሚሽኑ ም/ኮሚሽነርና የአደጋ ስጋት ቅነሳ ዘርፍ ሃላፊ በአቶ ይክፈለዉ ወ/መስቀል ቀርቦ ዉይይት ተካሄዶበታል።
የዉይይት መድረኩን የመሩት በቢሮ ኃላፊ ማዕረግ የአ/አ/ከተማ አስተዳደር ም/ዋና ስራ አስኪያጅ ወ/ሮ ቅድስት ወ/ጊዮርጊስ እንደተናገሩት በአዲስ አበባ ለጎርፍ አደጋ ተጋላጭ ተብለዉ በተለዩና አስቸኳይ መፍትሄ በሚሹ 135 ቦታዎች ላይ መፍትሄ ለመስጠት በትኩረት እየተሰራ መሆኑን አስታዉቀዋል።
ወ/ሮ ቅድስት አያይዘዉም ለጎርፍ አደጋ ከተጋለጡ የአካባቢ ነዋሪዎች ጋር ምክክር ተካሂዶ የንቅናቄ ስራ እንደሚሰራ አስታዉቀዋል።
አቶ ፍቅሬ ግዛዉ የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር በበኩላቸዉ እንደተናገሩት የክረምቱ ጊዜ ከመግባቱ በፊት አደጋን አስቀድሞ ለመከላከል እንዲቻል ከኮሚሽን መ/ቤቱ ጋር በቅንጅት በመስራት ኃላፊነታቸዉን እንዲወጡ በዉይይት መድረኩ ላይ ለተገኙት ባለድርሻ አካላት አሳስበዋል።
በዉይይት መድረኩ ላይ በአ/አ ከተማ አስተዳደር ስራ አስኪያጅ ፅ/ቤት አስተባባሪነት ፣የዲዛይንና ግንባታ ስራ ቢሮ ፣ ከፅዳት አስተዳደር ኤጀንሲ፣ ከህብረተሰብ ተሳትፎ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ፣ የሜጋ ፕሮጀክት ግንባታ ፅ/ ቤት ፣ የዉሃና ፍሳሽ ባለ ስልጣን፣ የአካባቢ ጥበቃ፣ የቦሌ፣የካ ፣የአራዳ እና የጉለሌ ክፍለ ከተሞች ስራ አስኪያጅ ፅ/ቤት የተወከሉ አመራርና ባለሞያዎች ተሳትፈዋል።
ፈጣን እና ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት እነዚህን አድራሻዎች ይከተሉ፤ ቤተሰብ ይሁኑ!
Facebook:-
👇👇👇👇
https://www.facebook.com/CITYMANAGER1
Telgram:-
👇👇👇👇
https://t.me/aacitymanager
Twitter:-
👇👇👇👇
https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r
YouTube:-
👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s
የጥንቃቄ መልዕክት
ለእሳት አደጋ መከሰት ምክንያት ከሆኑት መካከል ሻማ አንዱ ነዉ።
ሻማ ኤሌክትሪክ በሚቋረጥ ጊዜና ለተለያዩ ክብረ በዓሎች ሻማን በቤት ወይም በስራ ቦታ ልናበራ እንችላለን።
ይሁንና ሻማ በምናበራበት ጊዜ የሚከተሉትን ጥንቃቄዎች ማድረግ ይኖርብናል።
የምንለኩሰዉ ሻማ ከመጋረጃ፣ ከምንጣፍና ከሶፋ ከመሳሰሉት መራቅ ይኖርበታል።
ሻማ በምንለኩስበት አካባቢ ከተቀጣጣይ ነገሮችና ከኤሌክትሪክ መስመር መራቅ ይኖርበታል።
የተለኮሰ ሻማ በቤት እያለ በር ዘግተን መዉጣት ሻማዉ በተለያየ ምክንያት ወድቆና ተቀጣጣይ ነገር ላይ አርፎ ለእሳት መከሰት ምክንያት ስለሚሆን ከቤት ወጥተን የምንሄድ ከሆነ ሻማዉን ማጥፋታችንን ማረጋገጥ ያስፈልጋል።
የተለኮሰ ሻማ በቤት ዉስጥ እያለ መተኛች አደገኛ ነዉ ።
ስለሆነም ከመተኛታችን በፊት የተለኮሰዉ ሻማ መጥፋቱን ማረጋገጥ ይኖርብናል።
በቀላሉ ልንከላከላቸዉ በምንችላቸዉ አደጋዎች ህይወትና ንብረታችንን እንዳናጣ ጥንቃቄ የዘወትር ተግባራችን ይሁን።
ለእሳትና ለሌሎች ድንገተኛ አደጋዎች እንዲሁም ለአንቡላንስ አገልግሎት በ939 ወይም በ011-1-55-53-00 ፈጥነዉ ያሳዉቁ።
