en
Feedback

Don't get caught by a cheater! Telemetrio finds and tags such channels 👉 If you want to see the tag, subscribe

Addis Ababa City Manager Office

Addis Ababa City Manager Office

Open in Telegram
1 474
Subscribers
No data24 hours
-37 days
-2130 days
Posts Archive
በመዲናዋ የትንሳኤ በዓል ምንም ዓይነት የጎላ አደጋ ሳይከሰት ተከብሯል በአዲስ አበባ የትንሳኤ በዓል ምንም ዓይነት አደጋ ሳይከሰት በሰላም ተከብሮ ማለፉን የአዲስ አበባ እሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አስታወቀ። ሕብረተሰቡ የቅድመ ጥንቃቄ መልዕክቶችን ተግባራዊ በማድረግ ላሳየው ትብብርም ኮሚሽኑ ምስጋናውን አቅርቧል። ኮማሽኑ ያወጣው መግለጫ እንዳመለከተው በበአሉ ዋዜማ በተከሰተ የእሳት አደጋ ሕይወቱ ካለፈ አንድ ግለሰብ ውጪ ሌላ የእሳትና ድንገተኛ አደጋ አልደረሰም። ቅዳሜ ምሽት በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 12 ማርያም ማዞሪያ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ ጄነሬተር ለማስነሳት ነዳጅ በመጨመር ላይ የነበረ የ26 ዓመት የሆቴል ሰራተኛ በጄነሬተሩ ላይ በተነሳ እሳት ወዲያው ሕይወቱ ማለፉሞ ተመልክቷል። ይሁን እንጅ በበዓል ወቅት ሊኖር ከሚችለው የአደጋ ተጋላጭነትና ስፋት አኳያ አደጋዎች አለመከሰታቸውን በመግለጫው ተጠቅሷል። ኮሚሽኑ ከበዓሉ አስቀድሞ ሕዝብ በብዛት በሚሰበሰብባቸው ስፍራዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች በስፋት መከናወኑም መግለጫው አስታውሷል። ኮሚሽኑ ማህበረሰቡ የቅድመ አደጋ የጥንቃቄ መልዕክቶችን በአግባቡ መተግበሩ በዓሉ በሰላም እንዲያልፍ አስተዋጽኦ ማድረጉን ጠቅሶ ለዚህም በመግለጫው ምስጋና አቅርቧል። ፈጣን እና ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት እነዚህን አድራሻዎች ይከተሉ፤ ቤተሰብ ይሁኑ! Facebook:- 👇👇👇👇 https://www.facebook.com/CITYMANAGER1 Telgram:- 👇👇👇👇 https://t.me/aacitymanager Twitter:- 👇👇👇👇 https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r YouTube:- 👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s Tiktok 👇👇👇👇 https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager... Website 👇👇👇👇 https://www.aacitymanger.gov.et

ዛሬ ማልደን በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ከሚገኙ አቅመ ደካሞች እና የሃገር ባለውለታ የከተማችን ነዋሪዎችን በአብረሆት ቤተ መጽሃፍትፆም አስፈትተናል:: ትንሳኤ የፍቅር እና የርህራሄ ተምሳሌት በመሆኑ
+9
ዛሬ ማልደን በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ከሚገኙ አቅመ ደካሞች እና የሃገር ባለውለታ የከተማችን ነዋሪዎችን በአብረሆት ቤተ መጽሃፍትፆም አስፈትተናል:: ትንሳኤ የፍቅር እና የርህራሄ ተምሳሌት በመሆኑ እኛም ጎብኚ እና ጠያቂ ከሌላቸው ነዋሪዎቻችን ጋር ምግብን ብቻ ሳይሆን ፍቅርን ተጋርተናል:: ሁላችንም በያለንበት አቅመ ደካሞችን እና ጠያቂ የሌላቸውን እያሰብን በዓሉን በፍቅርና በአብሮነት እናሳልፍ:: ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ! ከንቲባ አዳነች አቤቤ

የአዲስ አበባ ከተማ ሥራ አስኪያጅ ጽ/ቤት ከከተማው ትያትርና ባህል አዳራሽ ጋር በመተባበር ተዘጋጅቶ በብስራት ኤፍኤም 101.1 ሬድዮ በዛሬው እለት ቅዳሜ ሚያዝያ 26 / 2016 አ.ም የቀረበ ትምህርታዊ ድራማ በፌስ ቡክ ገጻችን እንዲከታተሉ በአክብሮት ተጋብዘዋል::

የጥንቃቄ መልዕክቶች እየተላለፉ ነዉ። የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የትንሳዔ በዓል ያለምንም የአደጋ ክስተት በሰላም እንዲከበር ህብረተሰቡ ለአደጋ የሚያጋልጡ አሰራሮችን ተረድቶ እራሱን እንዲጠብቅ በሁሉም የከተማችን ስፍራዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች እያከናወነ ይገኛል። ህብረተሰቡ በዓሉን በሰላም ያልፍ ዘንድ እየተላለፉ ያሉ የጥንቃቄ መልዕክቶች የሚከተሉት ናቸው:: ኤሌክትሪክ በሚጠቀሙ ጊዜ ማድረግ የሚገባዎት ጥንቃቄ! ምግብ ለማብሰልና መሰል ስራዎችን በሚያከናዉኑበት ጊዜ በአንድ ኤሌክትሪክ ማከፋፈያ ላይ ደራርቦ አለመጠቀም። በኤሌክትሪክ ምድጃ ከተጠቀሙ በኋላ ሶኬት መንቀልዎን አይርሱ! በኤሌክትሪክ እየተጠቀሙ ባለበት ጊዜ የኤሌክትሪክ ኃይል ቢቋረጥ ሶኬት መንቀል አይዘንጉ! ከሰል በምንጠቀምበት ጊዜ መደረግ ያለበት ጥንቃቄ! ከሰል በሚጠቀሙበት ጊዜ ጢሱን ያልጨረሰ ከሰል ወደቤት ከማስገባት ይቆጠቡ! ጢሱን የጨረሰውንም ከሰል ቢሆን ወደቤት ካስገባን በኋላም በርና መስኮት በመክፈት በቂ የአየር ምልልስ እንዲኖር ያድርጉ! በከሰሉ ተጠቅመዉ ከጨረሱ በኃላ ምድጃዉን ከቤት አዉጥተዉ በዉሀ በማጥፋት ቤቱን ያናፍሱ! ሻማ በሚለኮስበት ወቅት መደረግ ያለበት ጥንቃቄ የሚለኩሱት ሻማ ከመጋረጃ ፣ከሶፋ ፣ ከምንጣፍና ከተቀጣጣይ ነገር መራቅ ይኖርበታል። በቤት ዉስጥ የተለኮሰዉን ሻማ ሳያጠፉ ከቤት መዉጣት እንዲሁም መተኛት ለአደጋ ያጋልጣል። ጋዝ ሲሊንደር በሚጠቀሙበት ጊዜ ሊደረግ የሚገባው ጥንቃቄ:- ሲሊንደሩን ከመለኮስዎ በፊት የጋዝ ማስተላለፊያ መስመር መጥበቁን ያረጋግጡ! በቤት ዉስጥ የጋዝ ሽታ ካለ ጋዝ ሲሊንደሩን ከመለኮስ ይቆጠቡ ! ሁሉንም የበዓል ስራዎች በተመሳሳይ ጊዜ ከማከናወን በመቆጠብ ስራዎችን በቅደም ተከተል ያድርጉ። በሌላ በኩልም እንደቤተሰብ አባል ብዛትና ችሎታ ስራን መከፋፈል አደጋን ይቀንሳል። ምሽቱንና ሌሊቱን የሚዘልቁ ስራዎች በድካምና በመሰላቸት መዘናጋቶች ሊፈጠሩ ስለሚችሉ አብዛኛዉን ስራዎች በቀኑ ክፍለ-ጊዜ ያጠናቅቁ! በዓል የደስታ ከመሆኑ አንጻር ደስታዎን ሊያደበዝዙ ከሚችሉ አደጋዎች እራስዎንና ቤተሰብዎን ከአደጋ ይጠብቁ! ከዚህ አልፎ ለሚያጋጥሙ አደጋዎች በአቅራቢያዎ ላለ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ፈጥነዉ ያሳዉቁ! ማዕከል 939 ወይም 0111555300 አራዳ ቅርንጫፍ 0111-56-02-49 ቂርቆስ ቅርንጫፍ 0114663420/21 አዲስ ከተማ ቅርንጫፍ 0112-76-91-45 ንፋስ ስልክ ቅርንጫፍ 0114-42-55-63 አቃቂ ቃሊቲ ቅርንጫፍ 0114-34-00-96 ቦሌ ቅርንጫፍ 0116-63-03-73 ኮልፌ ቀራንዮ ቅርንጫፍ 0113-69-60-85 ጉለሌ ቅርንጫፍ 0112-73-06-53 ለሚኩራ ቅርንጫፍ 0116-68-08-46 ልደታ ቅርንጫፍ 0115-58-95-33 መልካም በዓል!

ለክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለብርሃነ ትንሳኤ በዐል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። የትንሳኤ በዓል ኢየሱስ ክርስቶስ ለሰው ልጆች ሁሉ በመስቀል ላይ እስከሞት ድረስ ራሱን አሳልፎ በመሰጠት ወደር የለሽ ፅኑ ፍቅር ያሳየበት እና እንዲሁም ለበደሉት ሳይቀር ይቅርታና ምህረትን የሰጠበት፣ ሞትንም ድል ያደረገበት መታሰቢያ በዓል በመሆኑ እኛም፣ እርስ በርሳችን ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ሁሉንም ሰው በመውደድ፣ በይቅርታ፣ በምህረትና በመርዳዳት እንድንኖር ፈጣሪ ይርዳን። በዚህ በኩል ለተዳከሙ እሴቶቻችንም ትንሳኤ ይሁን። በዓሉ የፍቅር፣ የሰላም፣ የይቅርታ፣ የምህረት፣ የመርዳዳት፣ የደስታ እና አብሮነታችን የሚጠናከርበት ይሁን። በድጋሚ እንኳን አደረሳችሁ፣ መልካም በዓል ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ ከንቲባ አዳነች አቤቤ

የፋሲካ በዓልን ምክንያት በማድረግ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ አስተዳደር በወረዳ 01 ኦሎምፕያ አከባቢ የፅዳት ንቅናቄ ተካሄደ። መርሃ ግብሩን ያስጀመሩት የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት
+9
የፋሲካ በዓልን ምክንያት በማድረግ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ አስተዳደር በወረዳ 01 ኦሎምፕያ አከባቢ የፅዳት ንቅናቄ ተካሄደ። መርሃ ግብሩን ያስጀመሩት የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አብድልሃዲ ረሺድ ሲሆኑ ንቅናቄው "ፅዱ ኢትዮጵያ፤ ውብ አዲስ አበባ" በሚል መሪ ሀሳብ መካሄዱን ጠቅሰው ዓላማው በዓላትን በፅዱና ውብ አካባቢ ለማክበርና ህገወጥ ቆሻሻ መጣልንና ብክለትን ለመከላከል መሆኑን ገልፀዋል። በመልዕክታቸውም ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክታቸውን አስተላልፈው በዓሉ በፅዱ አከባቢ እንዲከበር እንዲሁም ከበዓል በኃላም የቆሻሻ መጠንና የእርድ ተረፈ ምርቶች ስለሚጨምሩ ሁሉም ነዋሪ የአካባቢውን ፅዳት በባለቤትነት መጠበቅ አለበት ሲሉ አሳስበዋል። … See more

የአዲስ አበባ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለትንሳኤ በአል በሰላም አደረሳችሁ እያለ መልካም ምኞቱን ይገልጻል:: ለቅድመ ክፍያ አገልግሎት ተጠቃሚ ደንበኞቹም በት
የአዲስ አበባ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለትንሳኤ በአል በሰላም አደረሳችሁ እያለ መልካም ምኞቱን ይገልጻል:: ለቅድመ ክፍያ አገልግሎት ተጠቃሚ ደንበኞቹም በትንሳኤ በአል ዋዜማ ዛሬ ቅዳሜ ሚያዚያ 26 ቀን 2016 እና ነገ እሁድ የበአሉ እለት ሚያዚያ 27/ 2016 አ.ም አገልግሎት በተመረጡ ማዕከላት ካርድ የመሙላት አገልግሎት እንደሚሰጥ እየገለጸ ከታች ከተዘረዘሩት ማዕከላት በአቅርቢያችሁ ወደሚገኘው ማእከል በመሄድ ካርድ መሙላት እንደምትችሉ አስታውቋል:: -ምስራቅ አዲስ አበባ ዲስትሪክት ቁጥር 9 (ሃያት) -ምስራቅ አዲስ አበባ ዲስትሪክት ቁጥር 6 (ወሰን) -ምስራቅ አዲስ አበባ ዲስትሪክት ቁጥር 7 (ካሳንቺስ) -ሰሜን አዲስ አበባ ዲስትሪክት ቁጥር 2 (አራት ኪሎ) -ደቡብ አዲስ አበባ ዲስትሪክት ቁጥር 9 (አቃቂ) -ደቡብ አዲስ አበባ ዲስትሪክት ቁጥር 10 (ለቡ) -ምዕራብ አዲስ አበባ ዲስትሪክት ቁጥር 1 (ልደታ) -ምዕራብ አዲስ አበባ ዲስትሪክት ቁጥር 2 (አየርጤና)

የአዲስ አበባ ከተማ ሥራ አስኪያጅ ጽ/ ቤት ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለትንሳኤ በአል በሰላም አደረሳችሁ እያለ በአሉ የደስታና የጤና እንዲሆንላችሁ መልካም ምኞቱን ይገልጻል!

እንኳን ለ2016 ዓ.ም የትንሣኤ በዓል በሰላም አደረሳችሁ! ኢየሱስ ክርስቶስ መከራና ሞት፤ ግፍና ሙስናን፤ ሲዖልና መቃብርን አሸንፎ የተነሣበትን የትንሣኤ በዓል በየዓመቱ እናከብራለን። ከበዓሉ በፊት የሕማማትን ሰሞን እናሳልፋለን። ሰሞነ ሕማማቱ ፈተናን፣ ስቃይን፣ ክህደትን፣ አሳልፎ መስጠትን፣ የክፉዎችን ኅብረት፣ የምናስብበት ነው። ሐሰት ያሸነፈች፣ እውነት የተሸነፈች መስላ የታየችበት ነው። ብዙዎች መሥዋዕትነትን ፈርተው የሸሹበት ነው። አንዳንዶችን የሚያልፍ ጎርፍ ወሰዳቸው፤ አንዳንዶችን የሚሰክን ማዕበል ነጠቃቸው። ጥቂቶች ከሕማማቱ አልፈው ትንሣኤውን ለመመልከት ቻሉ። የከተማው ጩኸት እና የሐሰቱ ወሬ እንኳን በሩቅ የነበሩትን፣ ቅርብ የነበሩትንም አሸንፏቸዋል። የሆሳዕና ዕለት ደግፈው የወጡት ከሦስት ቀን በኋላ ሊቃወሙ ሲወጡ ምንም አልመሰላቸውም። ድጋፋቸውም ተቃውሟቸውም ሁለቱም የጥቅም እንጂ የመርሕ አልነበረም። ሁለቱም ከእውነታው የተጣሉ ነበሩ። ሕማማት የውስጥና የውጭ ጠላቶች ተባብረውበታል። በሌላ ጊዜ ለሞት የሚፈላለጉ አካላት እውነትን ለመስቀል ሲሉ ግን ተባብረው ቆመዋል። ሰዎቹ ያልተረዱት አንድ እውነታ ነበር። ከሕማማቱ ይልቅ ትንሣኤው ይበልጣል፤ ይረዝማልም። ሕማማቱ አምስት ቀን ሲሆን ትንሣኤው ግን አስር እጥፍ ይሆናል። የአምስት ቀን ፈተና የሃምሳ ቀን ዋጋ አለው። በርግጥ የሕማማቱን ሽብርና ዋይታ፣ መከራና እንግልት ለተመለከተ ትንሣኤ የሚመጣ አይመስለውም። ትንሣኤው ግን የታመነና የተረጋገጠ ነው። የበለጠ ማረጋገጥ የሚቻለውም ጸንቶ እንደ ዮሐንስ በመቆም ብቻ ነው። ኢትዮጵያ በፈተና ውስጥ እያለፈች ነው። በፈተና ውስጥ የቆመች ሀገር ግን አይደለችም። በፈተና ውስጥ እያለፈች ያለች እንጂ። ወቅቱ ለኢትዮጵያ የሕማማት ሰሞን ይሆን ይሆናል። አራት ነገሮች ግን እውነት ናቸው። የመጀመሪያው የኢትዮጵያ ሕማማት አጭር መሆኑ፤ ሁለተኛው አጭር ቢሆንም ከባድ መሆኑ፤ ሦስተኛው ኢትዮጵያ ሕማማቱን ለማለፍ የሚያስችል ኃይል ያላት መሆኑ፤ አራተኛው ከአጭሩ ሕማማት በኋላ ረዥሙ የኢትዮጵያ ትንሣኤ የሚመጣ መሆኑ ነው። የተነሣነው ኢትዮጵያ እንደምትፈተን ዐውቀንም፤ አምነንም ነው። ለዘመናት የኖሩ ስብራቶችንና ብልሽቶችን ልናክም ስንነሣ መንገዱ አልጋ በአልጋ አይሆንም። ከችግሩ ማትረፍ የለመዱ አካላት ዝም አይሉም፤ ኢትዮጵያ በማሽን እንደሚረዳ ሕመምተኛ ሆና በሞትና በሕይወት መካከል እንድትኖር የሚፈልጉ ኃይሎች ዐርፈው አይቀመጡም። ግን ሕማማቱን እኛ ካልተቀበልንላት ለኢትዮጵያ ማን ይቀበልላታል የመከራውን ቀንበር ካልተሸከምንላት የሀገር ልጅነቱ የቱ ጋ ነው “ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ” እያሉ በስሟ ሲምሉ የነበሩ ብዙዎች ነበሩ፤ ከልባቸው ለቃላቸው ታምነው ልጅ የሆኗት ግን ጥቂቶች ብቻ ናቸው። አንዳንዶች በስሟ የሚገዘቱት እንጀራዋን ለመብላት እንጂ መከራዋን ለመካፈል አይደለም፤ በተቃራኒው እንጀራዋን በልተው ተረከዛቸውን አነሡባት። የሕማማቱ ወቅት አጭር ቢሆንም ከባድ መሆኑን እናውቃለን። የኮሶ መድኃኒት እንዲያሽር ከተፈለገ በአንድ ጊዜ በከባዱ መወሰድ አለበት። በትንሽ በትንሹ ከተወሰደ አያሽርም። የኢትዮጵያም ሕማማት እንደዚሁ ነው። በፊስካል ፖሊሲ፣ በግብርና፣ በማኑፋክቸሪንግ፣ በውጭ ጉዳይ ፖሊሲ፣ በኅብረ ብሔራዊ አንድነት፣ ነጻነትን በማስተዳደር፣ በክልል አደረጃጀት፣ በሲቪል ሰርቪስ፣ በጋራ ትርክት ግንባታ፣ ወዘተ. የተረከብናቸው ውዝፍ ዕዳዎች ብዙ ናቸው። ወገባችንን አሥረን፣ እጅጌያችንን ሰብስበን መራራውን የኮሶ መድኃኒት ውጠን፣ እነዚህን ችግሮች ካልፈታናቸው ቆመው አይጠብቁንም። በፈጣኑ ዓለም ውስጥ ቀስ ብለን ልንሄድ አንችልም። ተጠንቅቀን ግን ፈጥነን፤ አስበን ግን ዋጋ ከፍለን መጓዝ አለብን። ይሄ ነው ሕማማቱን የሚያሳጥረው። ኢትዮጵያ ሕማማቱን ለማለፍ የሚያስችል ኃይል አላት። ከዚህ በፊትም ብዙ አልፋለች፣ አሳልፋለች። የማይተዋት አምላክ አላት። የሚወዳት፣ የሚያስብላት ብቻ ሳይሆን የሚሞትላትም አመራር አላት። ዓላማ አይቶ ዋጋ የሚከፍል ሕዝብ አላት። አንጡራ ሀብት አላት። ይሄ የፈጣሪ፣ የአመራሩ፣ የሕዝቡ እና የአንጡራ ሀብቷ አራት ማዕዘናዊ ዐቅም፣ ሕማማቱን ማሳጠርና ማስቻል ብቻ ሳይሆን ቀጥሎ የሚመጣውን ፋሲካ ረዥም እንዲሆን ያደርገዋል። ብርቱውን ይዘናል - እንበረታለን፤ ኃይል በሚሰጠው እንታመናለን። ንጽሕናንና ለሀገር ያለንን በጎ ራእይ መሠረት አድገን ቆርጠን እንሠራለን። የጥብርያዶስ ሞቅታም ሆነ የፕራይቶሪዮን ግቢ ጩኸት ከመንገዳችን አያቆሙንም። የሆሳዕና ድጋፍም ሆነ የዕለተ ዓርብ ተቃውሞ መንገዳችንን አያስቀይሩንም። የኢትዮጵያን እውነት ብቻ ተከትለን እንገሠግሣለን። በዚህም ሕማማቱን አሳጥረን የኢትዮጵያን የትንሣኤ ጊዜ እናረዝመዋለን። በድጋሜ መልካም የትንሣኤ በዓል! ኢትዮጵያ በልጆቿ ጥረት ታፍራና ተከብራ ለዘላለም ትኑር!! ፈጣሪ ኢትዮጵያና ሕዝቦቿን ይባርክ! ሚያዚያ፣ 2016 ዓ.ም ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አቢይ አህመድ

የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ ቤት ከኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን (ኢቢሲ) ኤፍኤም 97.1 ጋር በመተባበር ዘወትር በየሳምንቱ ማክሰኞ ከጠዋቱ 2 ሰአት 30 - 3 ሰአት ድረስ ለ30 ደቂቃ ያህል በማዘጋጃ ቤታዊ ጉዳዮች ላይ አተኩሮ የሚተላለፈው ትምህርታዊ ውይይትና ፕሮግራሞች እነሆ 7ኛ ክፍል ላይ ደርሷል:: የዚህ ሳምንት ፕሮግራም ትኩረቱ ያደረገው ቅዝቃዜን ለመከላከልና በተለይም በበአላት ወቅት ደግሞ ቡና ከማፍላት ጀምሮ ለተለያዩ አይነት ምግቦች ማብሰያነት በስፋት ጥቅም ላይ የሚውለውን ከሰልና መርዛማ ጋዙን እንዴት መከላከል ይቻላል? በሚለው ላይ ያተኮረ ፕሮግራም በፌስቡክ ትከታተሉት ዘንድ እነሆ ብለናል::

የጋራ ግብረ-ኃይሉ በዓሉ ያለምንም የፀጥታ ችግር በሰላም እንዲከበር ዝግጅት ማጠናቀቁን ገለጸ የፀጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረ-ኃይል ሕዝበ ክርስቲያኑ ትንሣኤን በዓል ያለምንም የፀጥታ ችግር በሰላም እ
የጋራ ግብረ-ኃይሉ በዓሉ ያለምንም የፀጥታ ችግር በሰላም እንዲከበር ዝግጅት ማጠናቀቁን ገለጸ የፀጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረ-ኃይል ሕዝበ ክርስቲያኑ ትንሣኤን በዓል ያለምንም የፀጥታ ችግር በሰላም እንዲያከብር በሁሉም ክልሎች እና በሁለቱም ከተማ አስተዳደሮች ዝግጅቱን አጠናቆ ወደ ተግባር መግባቱን አስታወቀ፡፡ ሕዝቡም ሰላምና ደኅንነትን ለማረጋገጥ በሚካሄደው የፀጥታ ማስከበር ሥራ ውስጥ በባለቤትነት እያደረገ ያለውን ተሳትፎ የበለጠ አጠናክሮ በመቀጠል የአካባቢውን ሰላምና ደኅንነት የሚያውኩ አጠራጣሪ ነገሮችን ሲመለከት ለፀጥታ አካላት ጥቆማ በመስጠትና አስፈላጊውን ትብብር በማድረግ ከጋራ ግብረ-ኃይሉ ጎን በመሆን የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ ጥሪውን አቅርቧል። ግብረ-ኃይሉ ለመላው የክርስትና ሃይማኖት ተከታዮች የእንኳን አደረሳችሁ መልካም ምኞቱንም አስተላልፏል። ፈጣን እና ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት እነዚህን አድራሻዎች ይከተሉ፤ ቤተሰብ ይሁኑ! Facebook:- 👇👇👇👇 https://www.facebook.com/CITYMANAGER1 Telgram:- 👇👇👇👇 https://t.me/aacitymanager Twitter:- 👇👇👇👇 https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r YouTube:- 👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s Tiktok 👇👇👇👇 https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager... Website 👇👇👇👇 https://www.aacitymanger.gov.et

ሚያዚያ 24 ቀን2016 ዓ.ም ምሽት 3:10 ሰዓት ላይ በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ወረዳ 03 አቃቂ የገበያ መዕከል በተነሳ የእሳት አደጋ 16 ንግድ ሱቆች ሙሉ በሙሉና በከፊል ተቃጥለዋል። የእሳት አደጋዉን ለመቆጣጠር አምስት የአደጋ መቆጣጠር ተሽከርካሪ ሁለት የዉሀ ቦቴ ከ44 የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች ጋር የተሰማራ ሲሆን እሳቱ ወደገበያ ማዕከሉ ተስፋፎቶ በሰዉና በንብረት ላይ የከፋ ጉዳት ሳይደርስ መቆጣጠር መቻሉን የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አሰታውቆ አደጋዉን ለመቆጣጠር ሁለት ሰዓት ያህል መውሰዱንም ገልጿል። በአደጋ መቆጣጠሩ ሂደት የፌደራልና የአዲስ አበባ ፖሊስ አባላት ከፍተኛ ድጋፍ ያደረጉ ሲሆን በሰው ላይ የደረሰ ጉዳት እንደሌለም አመልክቷል ። ኮሚሽኑ አያይዞም አቃቂ የገበያ ማዕከል ትንሹ መርካቶ እየተባለ የሚጠራ የገበያ ማዕከል ሲሆን ገበያ ማዕከሉ በከተማ ደረጃ ለእሳት አደጋ ተጋላጭ ተብለዉ ከተለዩት አንዱ መሆኑን ጠቅሶ በገበያ ማዕከሉ በተደጋጋሚ የእሳት አደጋ እያጋጠመ በንብረት ላይ ጉዳት ሲደርስ መቆይቱንም አብራርቷል። ኮሚሽን መ/ቤቱ ገበያ ማዕከሉ ለአደጋ የተጋለጠባቸዉን ዝርዝር ጉዳዮችን የመፍትሄ ሀሳቦችን አካቶ ለገበያ ማዕከሉ ማህበራትና ለሚመለከታቸዉ አካላት ያቀረበ ቢሆንም የማስተካከያ ዕርምጃዎች አልተወሰዱም ብሏል። በመሆኑም በቀጣይ መሰል አደጋዎች እንዳያጋጥሙ መፍትሄ እንዲሰጥ ኮሚሽኑ አሳስቧል። ለእሳትና ለሌሎች ድንገተኛ አደጋዎች እንዲሁም ለአንቡላንስ አገልግሎት በ939 ፈጥነዉ ያሳዉቁ! ፈጣን እና ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት እነዚህን አድራሻዎች ይከተሉ፤ ቤተሰብ ይሁኑ! Facebook:- 👇👇👇👇 https://www.facebook.com/CITYMANAGER1 Telgram:- 👇👇👇👇 https://t.me/aacitymanager Twitter:- 👇👇👇👇 https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r YouTube:- 👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s Tiktok 👇👇👇👇 https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager... Website 👇👇👇👇 https://www.aacitymanger.gov.et

ሚያዚያ 24 ቀን2016 ዓ.ም ምሽት 3:10 ሰዓት ላይ በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ወረዳ 03 አቃቂ የገበያ መዕከል በተነሳ የእሳት አደጋ 16 ንግድ ሱቆች ሙሉ በሙሉና በከፊል ተቃጥለዋል። የእሳት አደጋዉን ለመቆጣጠር አምስት የአደጋ መቆጣጠር ተሽከርካሪ ሁለት የዉሀ ቦቴ ከ44 የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች ጋር የተሰማራ ሲሆን እሳቱ ወደገበያ ማዕከሉ ተስፋፎቶ በሰዉና በንብረት ላይ የከፋ ጉዳት ሳይደርስ መቆጣጠር መቻሉን የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አሰታውቆ አደጋዉን ለመቆጣጠር ሁለት ሰዓት ያህል መውሰዱንም ገልጿል። በአደጋ መቆጣጠሩ ሂደት የፌደራልና የአዲስ አበባ ፖሊስ አባላት ከፍተኛ ድጋፍ ያደረጉ ሲሆን በሰው ላይ የደረሰ ጉዳት እንደሌለም አመልክቷል ። ኮሚሽኑ አያይዞም አቃቂ የገበያ ማዕከል ትንሹ መርካቶ እየተባለ የሚጠራ የገበያ ማዕከል ሲሆን ገበያ ማዕከሉ በከተማ ደረጃ ለእሳት አደጋ ተጋላጭ ተብለዉ ከተለዩት አንዱ መሆኑን ጠቅሶ በገበያ ማዕከሉ በተደጋጋሚ የእሳት አደጋ እያጋጠመ በንብረት ላይ ጉዳት ሲደርስ መቆይቱንም አብራርቷል። ኮሚሽን መ/ቤቱ ገበያ ማዕከሉ ለአደጋ የተጋለጠባቸዉን ዝርዝር ጉዳዮችን የመፍትሄ ሀሳቦችን አካቶ ለገበያ ማዕከሉ ማህበራትና ለሚመለከታቸዉ አካላት ያቀረበ ቢሆንም የማስተካከያ ዕርምጃዎች አልተወሰዱም ብሏል። በመሆኑም በቀጣይ መሰል አደጋዎች እንዳያጋጥሙ መፍትሄ እንዲሰጥ ኮሚሽኑ አሳስቧል። ለእሳትና ለሌሎች ድንገተኛ አደጋዎች እንዲሁም ለአንቡላንስ አገልግሎት በ939 ፈጥነዉ ያሳዉቁ! ፈጣን እና ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት እነዚህን አድራሻዎች ይከተሉ፤ ቤተሰብ ይሁኑ! Facebook:- 👇👇👇👇 https://www.facebook.com/CITYMANAGER1 Telgram:- 👇👇👇👇 https://t.me/aacitymanager Twitter:- 👇👇👇👇 https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r YouTube:- 👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s Tiktok 👇👇👇👇 https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager... Website 👇👇👇👇 https://www.aacitymanger.gov.et

የየካ ክፍለ ከተማ ጽዳት አስተዳደር ጽህፈት ቤት በ4ኛ ዙር የ90 ቀናት ዕቅድ ትግበራ ወረዳ 01 እና 04ን በፅዳትና ውበት ሙሉ በሙሉ ሞዴል በማድረግ አስመረቀ ፅህፈት ቤቱ በ4ተኛ ዙር የ90 ቀናት እቅድ ትግበራ ወረዳ አንድ እና አራትን በፅዳትና ውበት ሙሉ በሙሉ ሞዴል በማድረግ በዛሬው እለት አስመርቆ ለነዋሪዎች አስረክቧል። በምረቃ መርሀ ግብሩ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አማካሪ አቶ በላይ ታደሰ ፣ የአዲስ አበባ ከተማ ፅዳት አስተዳደር ኤጀንሲ ምክትል ዋና ዳሪክተር አቶ ሳዲቅ ሽኩሪ፣የአዲስ አበባ ከተማ ፅዳት አስተዳደር ኤጀንሲ ምክትል ዋና ዳሬክተር አቶ ሙላት ተገኝ፣የየካ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ስራ አስኪያጅ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ጫሊ ቤኛ፣የየካ ክፍለ ከተማ ፅዳት አስተዳደር ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ከፋያለው ተሾመ፣የሁለቱም ወረዳ የስራ ሀላፊዎች፣የሀገር መከላከያ አባላት፣የፅዳት አንባሳደሮች እና የአከባቢው ነዋሪዎች ተገኝተዋል። በመርሀ ግብሩ ላይ ንግግር ያደረጉት የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አማካሪ አቶ በላይ ታደሰ አዲስ አበባን እንደ ስሟ ውብ ለማድረግ ከተማ አስተዳደሩ በልዩ ትኩረት እየሰራ እንደሚገኝ በመግለፅ የካ ክፍለ ከተማ ለነዋሪዎች ምቹ እና ፅዱ አከባቢ በመፍጠር ሒደት ውስጥ ቀዳሚውን ቦታ እንደሚይዝ አንስተው ይህ እንዲሳካ ላደረጉ አካላት ምስጋና አቅርበዋል። የየካ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ስራ አስኪያጅ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ጫሊ ቤኛ በበኩላቸው በ3ኛ እና 4ኛ ዙር 90 ቀናት እቅድ ትግበራ ካሉት 12 ወረዳዎች 6 ወረዳዎችን በክፍለ ከተማው ስር ካሉ 407 ብሎኮት 334ቱን ሙሉ ለሙሉ ሞዴል ማድረግ መቻሉን በማንሳት በቀጣይም የቀሩ ብሎኮችን ሞዴል ለማድረግ ከፍተኛ ርብርብ እና ጥረት እየተደረገ እንደሚገኝ ገልፀው የአከባቢው ነዋሪዎች ፅዳቱን በማስቀጠል የበኩላቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል። በ2016 በጀት አመት በ4ኛ ዙር የ90 ቀናት እቅድ ትግበራ በወረዳ አንድ 38 ብሎኮች እና 18 የመንግስት እና የግል ተቋማት እንዲሁም በወረዳ አራት 31 ብሎኮች በፅዳት እና ውበት ሙሉ ለሙሉ ሞዴል በማድረግ ተመርቀው ለነዋሪዎች የማስረከብ ስነ ስርአት ተካሂዷል። በመርሀ ግብሩ ላይ የመልሶ መጠቀም አውደ ርዕይ የተካሄደ ሲሆን ወረዳዎችን ሞዴል በማድረግ ሒደት ውስጥ አስተዋጽኦ ላደረጉ አካላትም እውቅና ተሰጥቷል። ፈጣን እና ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት እነዚህን አድራሻዎች ይከተሉ፤ ቤተሰብ ይሁኑ! Facebook:- 👇👇👇👇 https://www.facebook.com/CITYMANAGER1 Telgram:- 👇👇👇👇 https://t.me/aacitymanager Twitter:- 👇👇👇👇 https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r YouTube:- 👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s Tiktok 👇👇👇👇 https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager... Website 👇👇👇👇 https://www.aacitymanger.gov.et