en
Feedback

Don't get caught by a cheater! Telemetrio finds and tags such channels 👉 If you want to see the tag, subscribe 👈

Addis Ababa City Manager Office

Addis Ababa City Manager Office

Open in Telegram
1 474
Subscribers
No data24 hours
-37 days
-2130 days
Posts Archive
የብሔራዊ ቤተመንግሥት እድሳት የታሪክ እና የባሕል ቅርሳችንን ጠብቆ ለማቆየት የምናደርገው ጥረት ከፍ ያለ ርምጃ ነው። በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የተጀመረው የእድሳት ተግባር አሁን አንድነት ፓርክ ከሆነው ከታላቁ ብሔራዊ ቤተመንግሥት ጀምሮ ይኽን ትእምርታዊ ስፍራ እንደገና ለታላቅ አገልግሎት እንዲሰናዳ በማድረግ ቀጥሏል። ብሔራዊ ቤተመንግሥት አሁን የሕዝባችንን ጽናት፣ ጥበባዊ አቅምና ርዕይ ግዘፍ ነስቶ የሚታይበት የሀገራዊ ጉዟችን ዋቢ ሆኖ ይታያል። የቀደመ ግዝፈቱን እና ውበቱን በመመለስ ያለፈ ታሪካችንን እናከብራለን። ለትውልዶችም የኩራትና የተነሳሽነት ዘላቂ ተምሳሌት አኑረናል። እንሆ የቤተመንግሥት ሙዝየም ለሁሉም ሆኗል። The restoration of the National Palace is a significant step in preserving our history and cultural legacy. The restoration efforts initiated by Prime Minister Abiy Ahmed, beginning with the Grand National Palace—now Unity Park—have continued with the revitalization of this iconic landmark. The National Palace now stands as a testament to our nation’s journey, embodying the resilience, artistry, and vision of our people. By restoring it to its former glory, we honor our past and create a lasting symbol of pride and inspiration for future generations. The Palace Museum has now become a site for everyone. #PMOEthiopia

የብልጽግና ፓርቲ የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት በአዲስ አበባ ከተማ ጉብኝት የብልጽግና ፓርቲ የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት በአዲስ አበባ ከተማ ጉብኝት… See more

የስራ ባህላችን እየተለወጠ ነው፣ በምሽት የሻይ ችግኝ ዝግጅት ስራ ይበል የሚያስብል ነው። ከትጋት ውጭ የሚበለፅግ ሀገር የለም። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

ዛሬ ጠዋት እየተከናዋኑ ባሉ ጥረቶች ላይ ለመወያየት የብልጽግና ፓርቲ ማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ ጀምረናል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አቢይ አህመድ

አዲስ አበባ ከተማ ሰራ አሰኪያጅ ጽ/ቤት ለሴት ሠራተኞች በውጤታማ የሰራና የህይወት ሚዛን ክህሎት ላይ ሰልጠና ተሰጠ። የሰራ ላይ ሰልጠናው አላማም ሴት ሠራተኞች ያለባቸውን ማህበራዊ ሀላፊነት በብቃት በመወጣት በሰራ ገበታቸው ውጤታማ እንዲሆኑ ለማሰቻል ሴቶችን ማብቃት አሰፈላጊ በመሆኑ የተሰጠ መሆኑን የጽ/ቤቱ የሰው ሃብት ዳይሬክተር ወ/ሮ ሰናይት መርከቡ ገልፀዋል። ሰልጠናው ሴት ሠራተኞች ውጤታማ የሰራና የህይወት ሚዛን እንዲኖራቸው ጊዜን በአግባቡ በመጠቀም በየጊዜው የስራና የህይወት ሚዛንን በመገምገም ድንበር በማበጀት ሴቶች የሚጠቀሟቸውን የሚዲያ አማራጮች መርጦ የማሰተዳደር እና ተግባራትን በእቅድ መምራትን ያካትታል። የጽ/ ቤቱ ሴት ሰልጣኝ ሠራተኞችም ሰልጠናው በሰራ ገበታቸውም ሆነ በግል ህይወታቸውም በተግባር የሚተረጎም ሆኖ እንዳገኙትና መነቃቃትን እንደፈጠረላቸው ገልፀዋል። ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ! Facebook:- 👇👇👇👇 https://www.facebook.com/CITYMANAGER1 Telgram:- 👇👇👇👇 https://t.me/aacitymanager Twitter:- 👇👇👇👇 https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r YouTube:- 👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s Tiktok 👇👇👇👇 https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager... Website 👇👇👇👇 https://www.aacitymanger.gov.et

ከአዲስ አበባ ከተማ ውጪ ደረቅ ቆሻሻ በመኪና ጭኖ ወደ ከተማዋ ግለሰቦች 425 ሺህ ብር ተቀጡ ታህሳስ 18 ቀን 2017 ዓ.ም ****አዲስ አበባ****… See more

የነገዋ አዲስ አበባ ለማየትና ለመኖር የምታጓጓ ናት - ም/ጠ/ሚ ተመስገን ጥሩነህ የነገዋ አዲስ አበባ ለማየትና ለመኖር የምታጓጓ ናት ሲሉ የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንትና ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ፡፡ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ፥ የብልጽግና ፓርቲ የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ስብሰባ መጠናቀቁን ተከትሎ በአዲስ አበባ የተገነቡና በመገንባት ላይ ያሉ የልማት ስራዎችን መጎብኘታቸውን ገልጸዋል፡፡ በጉብኝቱ የኮሪደር፣ የአካባቢ ስነ ምህዳር ጥበቃ፣ የወንዝ ዳርቻ ልማት፣ ማህበራዊ ተቋማት፣ የፒያሳና ካዛንቺስ መልሶ ማልማትና የተነሺዎች ሁሉን አሟልተው የተገነቡ መንደሮችን መመልከታቸውን ጠቁመዋል፡፡ እነዚህ በከተማዋ የተጠናቀቁና እየተፋጠኑ የሚገኙ የልማት ስራዎች ፈጠራና ፍጥነትን አስተሳስረው እየተከናወኑ መሆኑን ማየታቸውን ገልጸዋል፡፡ በከተማዋ ለልማት ተነሺዎች የተገነቡ ቤቶች፣ የተቀናጁ የማህበራዊ ተቋማትና የመሰረተ ልማት ስራዎችም የነዋሪዎችን የቀድሞ ህይወት ከመለወጥ ባለፈ የፓርቲውን ሰው ተኮርነት በተጨባጭ ያረጋገጡ ተግባራት መሆናቸውንም ነው ያነሱት፡፡ የኮሪደር ልማት ከተሞችን የማብቃት ሥራ ነው ያሉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ "ከተሞቻችን ሲቆረቆሩ በታሪክ አጋጣሚ እንጂ በዕቅድ አልነበረም ፤ ይሄም ለኑሮ፣ ለቢዝነስና ለአገልግሎት ምቹ እንዳይሆኑ አድርጓቸዋል" ብለዋል። የአዲስ አበባ የኮሪደር ልማት የዘመናትን የከተማነት ፈተና የሚፈታ መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡ የኮሪደር ልማቱ መኖሪያን፣ የሥራ ቦታን፣ ቢዝነስን፣ ቅርስን፣ ማኅበራዊ ትሥሥርን፣ እንቅስቃሴን፣ ጤናን፣ ጽዳትንና መዝናኛን በጥቅሉ የአኗኗር ዘይቤ ማሻሻልን አማክሎ እየተገነባ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ የነገዋ አዲስ አበባ ለማየትና ለመኖር የምታጓጓ ናት ያሉት አቶ ተመስገን ፥ ተመሳሳይ ስራ ለጀመሩ የክልል ከተሞች ምሳሌና ሞዴልም ሆናለች ብለዋል፡፡ ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ! Facebook:- 👇👇👇👇 https://www.facebook.com/CITYMANAGER1 Telgram:- 👇👇👇👇 https://t.me/aacitymanager Twitter:- 👇👇👇👇 https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r YouTube:- 👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s Tiktok 👇👇👇👇 https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager... Website 👇👇👇👇 https://www.aacitymanger.gov.et

ቃልን በተግባር...! የፓርቲያችን ምክትል ፕሬዝዳንት እና ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ተመስገን ጥሩነህ የተመራው የብልፅግና ፓርቲ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት በአዲስ አበባ ከተማ እየተከናወኑ ያሉ ዘርፈ ብዙና መጠነሰፊ የተቀናጁ የልማት ተግባራትን ተመልክተናል። የአኗኗር ዘይቤን ያሻሻሉ፣ ፍትሐዊነትን የሚያረጋግጡ፣ አዳዲስ የዕውቀትና የቴክኖሎጂ ሽግግር ለማካሄድ ያስቻሉ፣ መነሻና መድረሻቸው ሰው ተኮር የሆኑ፣ ሰፋፊ የሥራ ዕድል የፈጠሩ፣ በከፍተኛ ፍጥነትና ጥራት የተከናወኑ፣ ማህበረ ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ ያላቸው ድንቅና ስኬታማ ተግባራትን ተመልክተናል። ከተማዋን ፅዱ፣ አረንጓዴና ለኑሮ ተስማሚ ለማድረግ የተጀመረው ጥረት የብልፅግና ዕሳቤዎች ወደ ተግባር የተቀየሩበት፣ የአመራር ትጋት፣ ቁርጠኝነትና ፅናት የታየበት የህዝብ የመልማት ፍላጎት የተረጋገጠበት ሲሆን ክብርት ከንቲባና የሥራ ባልደረቦቻቸው ያሳዩትን ትጋት ላደንቅ እወዳለሁ። የሰሩ እጆች ሁሉ ብሩክ ይሁኑ! የስራ እና ክህሎት ሚንስትር ሙፈሪያት ካሚል

ሁለተኛውን ዙር የኮሪደር ልማት እስካሁን ድጋፍና ፍቅሩን እያሳየን ላለው ህዝባችን 24/7 ሰርተን ልንክሰው እየተረባረብን ነው"!! ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ የሁለተኛውን ዙር የኮሪደር ልማትን በልደታና ንፋስ ስልክ ከተማ አስተባባሪ የሆኑት በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር ወንድሙ ሴታን ጨምሮ የከተማ ደጋፊ ከፍተኛ አመራሮች፣ የልደታ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ አበባ እሸቴና የኮሪደር ልማት ተግባሪዎችና፥ አማካሪዎች በተገኙበት ከሳር ቤት እስከ አረቄ ፋብሪካ እንዲሁም ከካርል እስከ አቦ ማዞሪያ ያለው ምልከታ ተካሂዶበታል። በዚህም የኮሪደር ልማት ስራው በፍጥነትና በጥራት እየተሰራ እንዳለ ከፍተኛ አመራሮቹ ተዘዋውረው ምልከታ ያደረጉ ሲሆን በቀጣይ በሚሰሩ ተግባራት ዙሪያም በመወያየት ኢንጅነር ወንድሙ የቀጣይ አቅጠጫ አስቀምጠዋል። የሁለተኛው ዙር ሰባተኛ የኮሪደር ከሳር ቤት አረቄ ፋብሪካ እንዲሁም ከካርል እስከ አቦ ማዞሪያ ያለውን የኮሪደር ልማትን በፍጥነትና በጥራት በማጠናቀቅ የከተማችንን መልካም ገፅታ ከመለወጥ ባለፈ የህዝባችን ተጠቃሚነት ባረጋገጠ መልኩ ለመፈፀም ሁሉም ባለ ድርሻ አካል የድርሻውን ሊወጣ እንደሚገባ ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ አሳስበዋል። Lideta sub-city communication office ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ! Facebook:- 👇👇👇👇 https://www.facebook.com/CITYMANAGER1 Telgram:- 👇👇👇👇 https://t.me/aacitymanager Twitter:- 👇👇👇👇 https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r YouTube:- 👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s Tiktok 👇👇👇👇 https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager... Website 👇👇👇👇 https://www.aacitymanger.gov.et

ዛሬ በፓርቲያችን ምክትል ፕሬዚዳንት እና በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ክቡር አቶ ተመስገን ጥሩነህ የተመራ የብልፅግና የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት በአዲስ አበባ የተገነቡትን አጠቃላይ የልማት ሥራዎችን ተዘዋውረን ጎብኝተናል ። ከእንጦጦ እስከ ፒኮክ የሚዘልቀውን 21. 5 ኪ.ሜ የወንዞች ዳርቻ ልማት፤ የግንፍሌ አካባቢ 19.5 ኪሜ የሚሸፍን ወንዝ ዳርቻ ልማት ፣የካዛንቺስን መልሶ ማልማት ፤ የመኖሪያ ቤቶች ግንባታ እና 40.4 ኪ ሜ የሚሸፍን ኮሪደር ልማት እንዲሁም የካዛንቺስ የልማት ተነሺዎች የገቡበትን የአቃቂ ገላን ጉራ የተቀናጀ የልማት መንደር እና የአካበባቢ ልማት ፤ የፒያሳ ልማት ተነሺዎች የገቡበትን የአቃቂ ዘመናዊ ተገጣጣሚ ቤቶች መኖሪያ መንደር ፤ የቦሌ ቡልቡላ ካርጎ ተርሚናል እና የአቃቂ አዲሱ መንገድ የ37 ኪ.ሜ የአረንጓዴ ልማት ሥራ ፤ “የብርሃን አዳሪ ት/ቤት" እና የ "ለነገዋ" የሴቶች ተሃድሶ እና ክህሎት ማበልፀጊያ ማዕከል ጎብኝተናል። በጉብኝታችን ከተማችን መሠረተ ልማት አቅርቦትእና ቅንጅት በፍጥነት እያደገ ያለ መሆኑን፤ የከተማዋን ፅዱና ዉብ በማድረግ ገፅታዋን እየቀየረ ያለ ልማት ፣ የማህበረሰቡን ተጠቃሚነት በፍትሀዊነትን እያረጋገጡ ያሉ ሰዉ ተኮር ሥራዎች የተጎበኙ ሲሆን እነዚህ ሥራዎች ብልፅግና ከባለፈው ጉባኤ ወዲህ በቃሉ መሰረት አዲስ አበባን ዉብ አበባ ለማድረግ የተገበራቸው ሥራዎች አካል ናቸዉ። ፈጣሪ ኢትዮጵያ እና ህዝቦቿን ይባርክ ! ጉብኝት በምስል : _ ከንቲባ አዳነች አቤቤ