en
Feedback
Addis Ababa City Manager Office

Addis Ababa City Manager Office

Open in Telegram
1 474
Subscribers
No data24 hours
-37 days
-2130 days
Posts Archive
በመዲናችን እየተገነቡ የሚገኙት የመሰረተ ልማት ግንባታዎች የቀጣዩን ትውልድ ተጠቃሚነት ታሳቢ ያደረጉ መሆናቸው ተገለጸ AMN - ሚያዝያ 30/2017 የአዲስ አበባ ምክር ቤት የመሰረተ ልማትና ማዘጋጃ ቤታዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ለስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት እና ለተጠሪ ተቋማት የመስክ ምልከታ ግብረ መልስ ሰጥቷል። በመዲናዋ እየተገነቡ የሚገኙ የመሰረተ ልማት ግንባታዎች የቀጣዩን ትውልድ ተጠቃሚነት ታሳቢ ያደረጉ መሆናቸውን በመስክ ምልከታ ማረጋገጥ መቻሉን የመሰረተ ልማትና ማዘጋጃ ቤታዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ዶክተር ግዛቸው አይካ ገልጸዋል፡፡ በኮሪደር በለሙ የመንገድ ዳርቻዎች እና የውስጥ ለውስጥ የመንገድ ዳር መብራቶች ላይ በትኩረት መሰራት እንደሚገባም ሰብሳቢው ገልጸዋል። መጪው ጊዜ ክረምት እንደመሆኑ መጠን የጎርፍ አደጋ እንዳይከሰት ከተለያዩ አካላት ጋር በመቀናጀት የቅድመ መከላከል ስራ ላይ በትኩረት መስራት እንዳለበትም ተመላክቷል፡፡ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ በበኩላቸው፣ የቋሚ ኮሚቴው ግብረ መልስ ተጨማሪ አቅም የሚሰጥ እና የማህበረሰባችን ጥያቄዎች በአግባቡ ምላሽ ለመስጠት የሚያስችል መሆኑን ተናግረዋል። በቋሚ ኮሚቴው የመስክ ምልከታ የተደረገባቸው ተቋማትም የአዲስ አበባ የእሳት አደጋ ሥጋት ስራ አመራር ኮሚሽን እና ቅርንጫፍ ጣቢያዎች ፣ የሲቪል እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ እና በስሩ የሚገኙ የተወሰኑ ወረዳዎች፣ የፅዳት አስተዳደር ኤጀንሲ እና የመብራት አገልግሎት አስተዳደር ባለስልጣን መሆናቸውም ተመላክቷል፡፡ በዳንኤል መላኩ

በመዲናችን እየተገነቡ የሚገኙት የመሰረተ ልማት ግንባታዎች የቀጣዩን ትውልድ ተጠቃሚነት ታሳቢ ያደረጉ መሆናቸው ተገለጸ AMN - ሚያዝያ 30/2017 የአዲስ አበባ ምክር ቤት የመሰረተ ልማትና ማዘጋጃ ቤታዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ለስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት እና ለተጠሪ ተቋማት የመስክ ምልከታ ግብረ መልስ ሰጥቷል። በመዲናዋ እየተገነቡ የሚገኙ የመሰረተ ልማት ግንባታዎች የቀጣዩን ትውልድ ተጠቃሚነት ታሳቢ ያደረጉ መሆናቸውን በመስክ ምልከታ ማረጋገጥ መቻሉን የመሰረተ ልማትና ማዘጋጃ ቤታዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ዶክተር ግዛቸው አይካ ገልጸዋል፡፡ በኮሪደር በለሙ የመንገድ ዳርቻዎች እና የውስጥ ለውስጥ የመንገድ ዳር መብራቶች ላይ በትኩረት መሰራት እንደሚገባም ሰብሳቢው ገልጸዋል። መጪው ጊዜ ክረምት እንደመሆኑ መጠን የጎርፍ አደጋ እንዳይከሰት ከተለያዩ አካላት ጋር በመቀናጀት የቅድመ መከላከል ስራ ላይ በትኩረት መስራት እንዳለበትም ተመላክቷል፡፡ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ በበኩላቸው፣ የቋሚ ኮሚቴው ግብረ መልስ ተጨማሪ አቅም የሚሰጥ እና የማህበረሰባችን ጥያቄዎች በአግባቡ ምላሽ ለመስጠት የሚያስችል መሆኑን ተናግረዋል። በቋሚ ኮሚቴው የመስክ ምልከታ የተደረገባቸው ተቋማትም የአዲስ አበባ የእሳት አደጋ ሥጋት ስራ አመራር ኮሚሽን እና ቅርንጫፍ ጣቢያዎች ፣ የሲቪል እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ እና በስሩ የሚገኙ የተወሰኑ ወረዳዎች፣ የፅዳት አስተዳደር ኤጀንሲ እና የመብራት አገልግሎት አስተዳደር ባለስልጣን መሆናቸውም ተመላክቷል፡፡ በዳንኤል መላኩ

በመዲናዋ የአደጋ ስጋትን ለመቀነስ ተቋማት ቅንጅታቸውን አጠናክረው መቀጠል አለባቸው አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 30/2017(ኢዜአ)፦ በመዲናዋ የአደጋ ስጋትን ለመቀነስ ተቋማት ቅንጅታቸውን አጠናክረው መቀጠል እንደሚገባቸው በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ ገለጹ። ''ወቅታዊ የአደጋ መከላከል እና ዝግጁነት ለዘላቂ ደህንነታችንና ዋስትና'' በሚል መሪ ሀሳብ የባለድርሻ አካላት የምክክር መድረክ ተካሒዷል። ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ በዚሁ ወቅት እንደገለጹት፤ በመዲናዋ ከ378 በላይ ለአደጋ ተጋላጭ የሆኑ ቦታዎች በጥናት ተለይተዋል። ከእነዚህ መካከል ከፍተኛ አደጋ ያመጣሉ ተብሎ የተለዩ ከ170 በላይ ለሚሆኑት ምላሽ የተሰጠ ሲሆን በቀጣይም ቀሪዎችን የማጠናቀቅ ስራ ይከናወናል ነው ያሉት። በዋናነትም የተደፈኑ የፍሳሽ መሰረተ ልማቶችን የማጽዳትና የማስተካከል ስራዎችን ማከናወን ተጋላጭነትን እንደሚቀንስ አስረድተዋል። በሚቀጥሉት ሁለት ወራት ጎርፍና ሌሎች ተያያዥ አደጋዎችን ቀድሞ ለመከላከል በትኩረት በመስራት በዘላቂነት ችግሮችን ለመፍታት መረባረብ እንደሚገባም ጠቅሰዋል። በመዲናዋ የተካሔደው የኮሪደር ልማት የአደጋ ስጋት ተጋላጭነትን በእጅጉ የቀነሰ ነው ብለዋል። የመንገድ፣ የመብራት እና የቴሌኮም መሰረተ ልማት ግንባታዎች የጥራት ደረጃቸውን ጠብቀው መገንባታቸውን ለአብነት አንስተዋል። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እሳትና ድንገተኛ አደጋ ስራ አመራር ኮሚሽነር ኮማንደር አሕመድ መሀመድ በበኩላቸው፤ የምክክር መድረኩ ባለድርሻ አካላት በመዲናዋ የተለዩ የአደጋ ስጋት ቦታዎችን ለማሳወቅና በቅንጅት መፍትሔ እንዲያገኙ ለማድረግ ያለመ መሆኑን ተናግረዋል። ይሕም አስቀድሞ ለመከላከልና አደጋ ሲከሰት ፈጣን ምላሽ መስጠት የሚያስችሉ ተግባራትን በቅንጅት ማከናወን የሚቻልበትን አቅጣጫ ለማስቀመጥ ነው ብለዋል። ኮሚሽኑ በዘንድሮው የክረምት ወቅት ሊያጋጥሙ የሚችሉ አደጋዎችን በመለየት የቅድመ ጥንቃቄ ስራ እያከናወነ መሆኑን ገልጸዋል። በውይይቱ ከተሳተፉት መካከል የየካ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስኪጅ አቶ መርክነሕ ያእቆብ በበኩላቸው፤ የአደጋ ስጋትን ለመቀነስ እስካሁን በትብብር ሲሰሩ የቆዩ ተግባራትን አጠናክሮ መቀጠል ያስፈልጋል ብለዋል። የኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ዳኛቸው አበበ የተቋማት በትብብር መስራት ማህበረሰቡ ጉዳት ሳይደርስበት አደጋን መከላከል ያስችላል ነው ያሉት። በዚሁ ጎን ለጎንም ተቋማት አካባቢ የተጠያቂነት ስርዓትም ሊኖር እንደሚገባ ነው ያመለከቱት።

ከንቲባ አዳነች አቤቤ የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎችን ተጠቃሚ የሚያደርጉ የተለያዩ የሰው ተኮር ስራዎች መሰራታቸዉን እና እየተሰሩ መሆናቸዉን ከኢቲቪ ጋር በነበራቸዉ ቆይታ ገልፀዋል፡፡ ከንቲባዋ እንደገለፁት ምንም ገቢ የሌላቸዉ የከተማችን ነዋሪዎች በቀን 1 ጊዜ እንኳን መመገብ የሚቸገሩ የከተማችን ነዋሪዎች አሁን 36 ሺ የሚሆኑ ወገኖቻችን ትኩስ እና ንፁህ ምግብ በቀን 1 ጊዜ መመገብ የቻሉበት እና በዚህም ምግብ ብቻ ሳይሆን ክብርም፤ፍቅርም ያገኙበት ፕሮግራም መሆኑን ገልጸዋል:: በተጨማሪም ትዉልድ ላይ ትኩረት በማድረግ በተማሪዎች ምገባ በየትቤ/ቱ 1 ሚሊዮን የሚጠጉ ተማሪዎች በቀን 2 ጊዜ እንዲመገቡ ማድረግ የተቻለበትና የትምህርት ቁሳቁስ ግብዓት በሟሟላት የወላጆችን ጫናን ለማቃለል መንግስት ሃላፊነት ወስዶ እየሰራበት መሆኑንም አብራርተዋል፡፤ ከንቲባዋ አክለዉም በሰዉ ተኮር ስራወች ሰፋፊ እና በሚሊዮን የሚቆጠር የስራ እድል መፍጠር የተቻለበት እና በመሰረታዊነት የሰዉ ህይወት የተቀየረበት መሆኑን ገልፀዉ በሴፍቲኔት ብቻ ወደ 100ሺ የሚሆኑ የከተማችን ነዋሪዎች ባለፉት ዓመታት ወደ ተሻለ ህይወት በተጨባጭ ማሻገር የተቻለበት ነዉ ብለዋል፡፡

በመዲናችን እየተከናወኑ ያሉ አስደማሚና ፋና ወጊ የልማት ስራዎች አስተማማኝነት ለማረጋገጥ የቅድመ አደጋ መከላከል ሥርአታችንን የማጠናከር ጉዳይ በሁላችንም ዘንድ በልዩ ትኩረት ሊፈፀም ይገባል ሲሉ በም/ ከንቲባ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ አሳሰቡ። ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ በዛሬው እለት በከተማችን የአደጋ ስጋት ተጋላጭነትን ለመቀነስ በተከናወኑ ስራዎች ዙሪያ ከባለድርሻ አካላት ጋር ለመወያዬት በተጠራው የምክክር መድረክ ላይ እንደተናገሩት የምንሰራው ሰራ ወሳኝ መሆኑን ተገንዝበን በሚቀጥሉት 2 ወራት አደጋን የመከላከልን ስራ ቅድሚያ በመስጠት ልንረባረብበት ይገባል ሲሉ አመልክተዋል። የከተማችን የቅድመ አደጋ የመከላከል ስርአት የማጠናከር ጉዳይ በጊዜ የለኝም መንፈሰ በትጋት ከተጠያቂነት ጭምር በውሰን ሀብት መሰራት ይገባል ሲሉ ያስገነዘቡት ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ ይህን ተግባር ያለ እረፍት ሌት ተቀን በመስራት ካሳካነው እንደከተማ ለብልፅግና ጉዟችን መረጋገጥ ያለው ፋይዳ ከፍተኛ ነው ሲሉ አስገንዝበዋል። የመድረኩ ተሳታፊዎችም የከተማችንን የአደጋ ስጋት የመከላከል ሃላፊነት ያለባቸው ተቋማት የወሰዱትን ተልእኮ በአግባቡ እና በጊዜው ያጠናቀቁትን አድንቀው ያላጠናቀቁትም በብቃት ከፈፀሙት መልካም ተሞክሮ እና ትምህርት በመውሰድ የክረምቱ ጊዜ ሳይደርስ ቀሪ ስራዎችን በአፋጣኝ ሊያጠናቅቁ ይገባል ሲሉ አስተያዬታቸውን ሰጥተዋል። በተያያዘም የአደጋ ሰጋት ተጋለጭ ቦታዎች የማቅለያ እርምጃ በመውሰድ ችግሩን በዘላቂነት በመፍታት ረገድ ሁሉም የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ በመድረኩ በአፅንኦት ተነሰቷል።

በመዲናችን አደጋን ለመከላከል ተጋላጭ በሆኑ አካባቢዎች ላይ እየተከናወነ ያለው ፣ወቅታዊ ፣በተጨባጭ መረጃ የተመሠረተ እና ሰው ተኮር የሆነ ፈጣን የምላሽ ሰጭነት ተግባር በሁሉም ባለድርሻ አካላት ርብርብ ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ በም/ከንቲባ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ አስገነዘቡ። ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ ይህንን ያስገነዘቡት የአዲስ አበባ ከተማ ሥራ አስኪያጅ ጽ/ቤት "ወቅታዊ የአደጋ መከላከል ዝግጁነታችን ለዘላቂ ደህንነታችን እና ዋስትናችን" በሚል መሪ ቃል የመዲናችን የአደጋ ተጋላጭነትን ለመከላከል:እየተሰሩ ያሉ ስራዎች አፈፃፀምን ከባለድርሻ አካላት ጋር ለመገምገም ባዘጋጀው የምክክር መድረክ ላይ ነው። በመድረኩ በመዲናችን አዲስ አበባ በተለይም በመሬት መንሸራተት፣ በጎርፍ እና እሳት አደጋዎች ተጋላጭ ተብለው በበጀት አመቱ መጀመሪያ በተለዩ ቦታዎች ላይ ባለፉት 10 ወራት በከተማ አስተዳደሩ ተቋማት ቅንጅት እና በባለድርሻ አካላት ተሳትፎ የተሰሩ ስራዎች ያሉበትን ደረጃ የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር ኮማንደር አህመድ መሃመድ በሰነድ በተደገፈ መልኩ አቅርበዋል። ሰነዱ ከቀረበ በሁዋላ በተካሄደው የውይይት መድረክ ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ በመዲናችን ለአደጋ ስጋት ተጋላጭ ተብለው በተለዩ ቦታዎችና አጋላጭ የሆኑ ሁኔታዎችን መፍትሔ በመስጠት ረገድ እስካሁን የተሰረ ስራዎች አበረታች የሚባሉ እንደሆነ ገልፀው ይሁን እንጅ የዘንድሮው የክረምት ወራት ከመግባቱ በፊት ክባለድርሻ አካላት ጋር ቅንጅታዊ አሰራርን የበለጠ በማጠናከር ሁሉም የበኩሉን ሃላፊነት ሊወጣ እንደሚገባ አሳስበዋል። የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር አህመድ መሀመድ በበኩላቸው ኮሚሽኑ በዘንድሮው የክረምት ወቅት ሊያጋጥሙ የሚችሉ አደጋዎችን አስቀድሞ ለመከላከል አስፈላጊውን የቅድመ ዝግጅት ስራዎች ቅንጅታዊ አሰራርን ባጠናከረ መልኩ በተገቢው እየተሰራ መሆኑን አመልክተዋል። ኮማንደር አህመድ አክለውም በከተማችን አዲስ አበባ የአደጋ ስጋት የሆኑ 378 ቦታዎች ተለይተው ስራዎች ሲሰሩ መቆየታቸውን አመልክተው ዋና ዋና መንስኤዎችም የከተማችን ህዝብ አሰፋፈር፣ ያረጁ መሠረተ ልማቶች እና የትራፊክ አደጋ መሆናቸውን አብራርተው ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታት በከተማችን አሰደናቂ ለውጥ እየተየበት ያለው የኮሪደር ልማትአካል የሆኑ የወንዝ ዳርቻ ልማት ስራዎ መፍትሄ በመስጠት ረገድ ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንዳላቸው ገልፀዋል።