en
Feedback
Addis Ababa City Manager Office

Addis Ababa City Manager Office

Open in Telegram
1 474
Subscribers
No data24 hours
-37 days
-2130 days
Posts Archive
ሰላምና ፀጥታን በተመለከተ 👉በሠላምና ፀጥታ ጉዳዮች የኅብረተሰቡን ተሳትፎ ለማጎልበት በአካባቢ ሠላም፣ በአብሮነትና ትብብር የሰላም እሴት ግንባታ ዙሪያ በድግግሞሽ ከ7.9 ሚሊዮን በላይ የኅብረተሰብ ክፍሎችን በግንዛቤ በብሎክ የማኅበረሰብ አቀፍ ምክክር መድረኮች ላይ ማሳተፍ ተችሏል፡ 👉በማኅበረሰብ አቀፍ ፀጥታ አጠባበቅ ላይም አካባቢን በመጠበቅ፣ ለወንጀለኞች መደበቂያ ሊሆኑ የሚችሉ ሁኔታዎች በማጽዳትና የሥጋት ቦታዎችን ለይቶ መከላከል እንዲቻል የሠላም ሠራዊት አደረጃጀቶችን እና የማኅበረሰብ ክፍሎችን በማሳተፍ ሕዝቡን የሰላም ባለቤት ማድረግ ተችሏል። 👉የወንጀል ድርጊቶችን በመቀነስ ረገድ ከ3,628 በላይ የፀጥታ መረጃዎችና ጥቆማዎች በመሰብሰብና በማደራጀት ህገ ወጥ የገንዘብ ዝውውር እና ሃሰተኛ ሰነድ፣ከከባድና ቀላል ወንጀል፣ ከትምህርት ተቋማት ደህንነት፣ ለፀጥታና ደህንነት አስጊ ከሆኑ ሁኔታዎችና ግጭቶች እንዲሁም ከተለያዩ አዋኪ ድርጊቶች፤ ከኢኮኖሚ አሻጥርና ህገ ወጥ የንግድ ቁጥጥር ጋር በተያያዘ ከሌሎች ሕግ አስከባሪ አካላት ጋር በመቀናጀት 11,517 የወንጀል ድርጊቶችና የፀጥታ ስጋቶችን የመለየት፣ የመከላከል እና እርምጃ እንዲወሰድ የማድረግ ሥራ ተሰርቷል።

3ኛዉ የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ጉበዔዉን ማካሄድ ጀመረ የጉባኤው አጀንዳዎች፦ 1. የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ2017 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርትና የ2018 በጀት ዓመት እቅድ የትኩረት አቅጣጫዎች 2. የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት የ2017 በጀት ዓመት የኦዲት ሪፖርትን ማድመጥ 3.የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍርድ ቤቶች የ2017 በጀት አመት ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ላይ ተወያይቶ ማጽደቅ 4. የአዲስ አበባ ከተማ አስፈጻሚ አካላትን ስልጣንና ተግባር እንደገና ለመወሰን የወጣውን አዋጅ ቁጥር 84/2016 ለማሻሻል የቀረበው ረቂቅ አዋጅ ላይ ተወያይቶ ማጽደቅ 5. የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ2018 በጀት ረቂቅ አዋጅ ላይ በመወያየት ማጽደቅ 6. ልዩ ልዩ ሹመቶችን ማጽደቅ

3ኛው የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ጉባኤ

ይህ በፎቶ ላይ የሚታየው ኮንክሪት ቡኬት፤ ከማሠልጠኛ ወደ ጋርመንት በሚወስደው የቀለበት መንገድ ክፍል ላይ ኃላፊነት በጎደለው ሁኔታ የተደፋ ነው። ይህ ህገ-ወጥ ድርጊት እንዴትና በየትኛው አካል ሊፈፀም እንደሚችል መረዳት አያዳግትም። በተደጋጋሚ እንደምንለው፤ ጥቂት አጥፊዎች በግዴለሽነት በነዋሪዎቿ ተሳትፎ ፅዱ እና ውብ የሆነችው መዲናችን አዲስ አበባን ገፅታ የሚያቆሽሽ የመሠረተ ልማቶቻችን የመጠቀም መብት የሚጋፋና የትራፊክ እንቅስቃሴንም የሚያስተጓጉል ነው። ህገ-ወጦች እንዲታረሙ በማድረግ የከተማችን ፅዳት እና ውበት በጋራ እንጠብቅ! በከተማችን ፅዳት ላይ የሚስተዋሉ ጥፋቶችንና ህገወጥነትን በምስል የተደገፉ መረጃዎችን እና ጥቆማዎችን በነፃ የስልክ መስመር 6199 ወይም ደግሞ በማህበራዊ ሚዲያ ገፆች የውስጥ መስመሮችን በመጠቀምና በማጋራት ኃላፊነታችንን እንወጣ! የመዲናችንን ፅዳት በዘላቂነት የመጠበቅ የሁላችንም ሃላፊነት ነው! ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች https://linktr.ee/aacitymanager

ይህ በፎቶ ላይ የሚታየው ኮንክሪት ቡኬት፤ ከማሠልጠኛ ወደ ጋርመንት በሚወስደው የቀለበት መንገድ ክፍል ላይ ኃላፊነት በጎደለው ሁኔታ የተደፋ ነው። ይህ ህገ-ወጥ ድርጊት እንዴትና በየትኛው አካል ሊፈፀም እንደሚችል መረዳት አያዳግትም። በተደጋጋሚ እንደምንለው፤ ጥቂት አጥፊዎች በግዴለሽነት በነዋሪዎቿ ተሳትፎ ፅዱ እና ውብ የሆነችው መዲናችን አዲስ አበባን ገፅታ የሚያቆሽሽ የመሠረተ ልማቶቻችን የመጠቀም መብት የሚጋፋና የትራፊክ እንቅስቃሴንም የሚያስተጓጉል ነው። ህገ-ወጦች እንዲታረሙ በማድረግ የከተማችን ፅዳት እና ውበት በጋራ እንጠብቅ! በከተማችን ፅዳት ላይ የሚስተዋሉ ጥፋቶችንና ህገወጥነትን በምስል የተደገፉ መረጃዎችን እና ጥቆማዎችን በነፃ የስልክ መስመር 6199 ወይም ደግሞ በማህበራዊ ሚዲያ ገፆች የውስጥ መስመሮችን በመጠቀምና በማጋራት ኃላፊነታችንን እንወጣ! የመዲናችንን ፅዳት በዘላቂነት የመጠበቅ የሁላችንም ሃላፊነት ነው! ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች https://linktr.ee/aacitymanager

የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት 4ኛ መደበኛ ጉባኤን ዛሬ ማካሄድ ይጀምራል የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 4ኛ መደበኛ እና የበጀት አመቱን ማጠቃለያ ጉባኤ ሃምሌ 4 እና 5 ቀን 2017 ዓ.ም በአድዋ ድል መታሰቢያ ያካሄዳል። በጉበኤዉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ2017 በጀት ዓመት የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት እና የ2018 በጀት ዓመት ዋና ዋና አቅጣጫዎች ይቀርባሉ ተብሎ ይጠበቃል።

የአዲስ አበባ ከተማ ሥራ አስኪያጅ ጽ/ቤት የመዲናችንን ስማርት ከተማነት የሚያረጋግጡ ከነዋሪዎቻችን የእለት ከእለት ህይወት ጋር ቀጥተኛ ግኑኝነት ያላቸውን አገልግሎቶችን ሰትራቴጅካዊ በሆነ መንገድ እንደሚመራ ተቋም በ2017 በጀት አመት ያከናወናቸው ስራዎች አበረታች ውጤት የተመዘገበባቸው መሆናቸውን በም/ከንቲባ ማእረግ የአዲስአበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ አስታወቁ። ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ ይህን ያስታወቁት በዛሬው እለት ፅ/ቤቱ በ2017 እቅድ አፈጻፀም እና በ2018 በጀት አመት አቅድ እንዲሁም በ90 ቀናት የማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት የ1ወር እቅድ አፈፃፀም ላይ ከፅ/ ቤቱ ሠራተኞች ጋር ባካሄዱት ውይይት ላይ ነው። ኢንጅነር ወንድሙ አክለውም በተለይም የአዲስ አበባ ከተማ ማዘጋጃቤታዊ አገልግሎት ዘርፍ ለከተማዋ የስማርት ሲቲ ጉዞ አይነተኛ ሚና ባለቸው የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪዎች አገልግሎት፣ለከተማዋ ነዋሪዎች ደህንነት ጉልህ አስዋጽኦ ባለው የፋይዳ ምዝገባን ተግባር በመምራት 5 ነጥብ 7 ሚሊዮን በላይ የከተማችን ነዋሪዎችን መመዘገብ የተቻለበት እና ከሌሎች የሚመለከታቸው ተቋማት ጋር በቅንጅት በመሰራት የሁነት ምዝገባዎቸን ውጤታማ በሆነ መንገድ እንዲፈፀሙ ስትራቲጅካዊ አመራር መሰጠት መቻሉን ጠቁመዋል። ጽዳትን በተመለከተም አዲስ አበባ ከተማ ጽዱ እና ውብ ለነዋሪዎቿ የተመቸች እንድትሆን ጽዳትን ባህሉ ያደረገ ማህበረሰብ ለመፍጠር በርካታ የንቅናቄ ተግባራትን በአጀንዳ በመምራት ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት በመሰራት በከተማችን ከፍተኛ ችግር የነበረውን የግንባታ ተረፈ ምርት ቆሻሻ በቅንጅት ማሰወገድ መቻሉ ተግባሩም ባህል ሆኖ እንዲቀጥል መደረጉን ማሳያ ነው ሲሉ ተናግረዋል። የበጀት አመቱ እንደ ከተማ ማሳያ የሚሆኑ ሞዴል የጽዳት ወረዳዎችን ብሎኮችን የመፍጠር ቆሻሻን ወደ ሀብትነት የመቀየር ሰራዎች በሰፋት እንዲሰሩ አመራር የተሰጠበት እንደነበር የጠቀሱት ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ የእሳትና አደጋ ሰጋት ሰራ አመራር ተግባርን በተመለከተ በበጀት አመቱ ለአብነት 170 ያህል የአደጋ ሰጋት ተጋላጭ ቦታዎችን ችግር መፍታት መቻሉ ተቋሙ አደጋ የመከላከል ሰራዎችን በብቃት እንዲወጣ በቴክኖሎጅ እንዲዘምን እና ራሱም ከአደጋ ሰጋት የተጠበቀ እንዲሆን አመራረ የተሰጠበት መሆኑንም አብራርተዋል። የመንገድ መብራተ አገልግሎትን በተመለከተም የአዲስ አበባ ከተማ ሰራ አስኪያጅ ጽ/ቤት ባለቤት ያልነበረውን ተግባር በጥናት ተመስርቶ በማደራጀት ወደ ሰራ ያስገባው መሆኑን እና በዘላቂነት የከተማዋን ለውጥ የሚያፋጥን የስልጣኔ የሰለም እና የደህንነት ማሳያ አንዲሆን ሰትራቲጅካዊ አመራር የተሰጠበት እና ለወደፊቱም ይኸው ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን ገልፀዋል ። በቢሮ ሀላፊ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ ም/ዋ/ሥራ አስኪያጅ አቶ ተፈራ ሞላ በበኩላቸው የ2017 በጀት አመት የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት አፈጻፀም ስኬታማ ነበር ማለት የሚያስችል ግምገማ እንዳለቸው ጠቅሰው ማስረጃዎቹም በሪፖርት፣ በድጋፍ እና ክትትል፣በግምገማ እና በኤንስፔክሸን የተረጋገጡ ማሳያዎች ያሉት ከመዋቅራችን እና በተጠሪ ተቋማትም ጭምር ተናባቢ እንደሆነ ገልፀዋል። በመድረኩ የ90 ቀናት የማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎትን እና የበጎ ፈቃድ ስራዎች የጽ/ቤቱ የአንድ ወር አፈፃፀም ቀርቦ ተገምግሟል። ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች https://linktr.ee/aacitymanager

ተቋማዊ የመፈፀም አቅሙን በአጭር ጊዜ ውስጥ ያደራጀና ለቀጣይ ኃላፊነት የተዘጋጀ ተቋም ተፈጥሯል- በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ የመብራት አገልግሎት አስተዳደር ባለስልጣንን የስራ እንቅስቃሴ ጎበኙ፡፡ በጉብኝታቸው ወቅት ባለስልጣኑ ከተሰጠው ስልጣንና ተግባራት ውስጥ ወደ ስራ የገባበትን የስማርት ፖል ዝርጋታና ተከላ እንዲሁም በነባር የመንገድ መብራት መሰረተ-ልማቶች ላይ የተከናወኑ ሰፊ የጥገና ስራዎች የከተማ አስተዳደሩ የጣለበትን ኃላፊነት መወጣት የቻለ፣ ተቋማዊ የመፈፀም አቅሙን በአጭር ጊዜ ውስጥ ያደራጀና ለቀጣይ ኃላፊነት የተዘጋጀ ተቋም መፍጠር ተችሏል ሲሉ አንስተዋል፡፡ በም/ ከንቲባ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ ባለስልጣኑ በአዋጅ ከተቋቋመበት ጊዜ ጀምሮ ባለስልጣኑን በማደረጃት ሂደት ላይ ጠንካራ ክትትልና ድጋፍ በማድረግ፣ ከአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን ይፋዊ የስራ ርክክብን በመምራትና በማስፈፀም፤ ባለስልጣኑን በቅርበት በመከታተል ረገድ ከፍተኛ አስተዋፅዖ በማድረግ ላይ እንደሚገኙ ይታወቃል፡፡ ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ በባለስልጣኑ ዋና መ/ቤት በመገኘት ከባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሰብስብ ሁሴን ጋር በተቋሙ አጠቃላይ የስራ እንቅስቃሴና በቀጣይ አቅጣጫዎች ዙሪያ የጋራ ውይይት አድርገዋል፡፡ በዋና ዳይሬክተሩ ቢሮ ካደረጉት ሰፊ ውይይት በተጨማሪ አጠቃላይ የስራ እንቅስቃሴውን በየስራ ዘርፎቹ በአካል የጎበኙ ሲሆን ተቋሙ በአጭር ጊዜ ውስጥ ተቋማዊ አቅምና ቁመና በመፍጠርና ውጤት በማምጣት ረገድ በተጨባጭ በከተማው ልማት ላይ እያበረከተ ያለው ድረሻ ሰፊ መሆኑን አንስተዋል፡፡ በመጨረሻም ለቀጣይ ድርብ ተልዕኮ በቴክኖሎጂ እና ብቃት ባለው በሰው ሀይል የተደራጀ ያለ ተቋም መሆኑንም ገልጸዋል፡፡ ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች https://linktr.ee/aacitymanager

ችግኞችን መትከል ብቻ ሳይሆን ተንከባክቦ ማሳደግና ለውጤት ማብቃት ይገባል" በምክትል ከንቲባ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ ችግኞችን መትከል ብቻ ሳይሆን ተንከባክቦ ማሳደግና ለውጤት ማብቃት ይገባል ሲሉ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ ገለፁ። በዛሬው ዕለት "በመትከል ማንሰራራት" በሚል መሪ ቃል የአዲስ አበባ ከተማ ፅዳት አስተዳደር ኤጀንሲ በረጲ ላንድፊል የችግኝ ተከላ ማስጀመሪያ መርሃ ግብር በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ወንድሙ ሴታን ጨምሮ የከተማና የክ/ከተማ የመንግስትና የፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች ፣ የወረዳ አመራሮች ፣ የፀጥታ አካላት፣ የፅዳት አምባሳደሮች ፣ አርቲስቶች፣ ከማዕከል እስከ ወረዳ ድረስ ያሉ የመዋቅሩ አመራሮችና ሰራተኞች እንዲሁም የአካባቢው ነዋሪ ህብረተሰብን ጨምሮ ከ5ሺህ በላይ የህብረሰብ ክፍሎች በተሳተፉበት የችግኝ ተከላ መርሀግብር በድምቀት አካሂዷል። በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ በዚሁ ወቅት ባስተላለፉት መልዕክት ሀገሪቱ የጀመረችውን ልማትና ብልፅግና ዘላቂነት እንዲኖረው አንዱና ዋነኛው አረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር መሆኑን ጠቅሰው ለፅዳት አስተዳደር ተቋም ደግሞ ትልቅ ትርጉም ያለው መሆኑን ተናግረዋል። በሚጣሉ ቆሻሻዎች ከተማዋ እንዳትቆሽሽና እንዳትበከል የከተማውን ገፅታ በዘላቂነት መፍታት እንደሚገባ ገልፀው ችግኝ በዘመቻ መትከል ብቻ ሳይሆን ተንከባክቦ ማሳደግና ለውጤት ማብቃት ትኩረት የሚሻ ጉዳይ መሆኑን ተናግረዋል። የአዲስ አበባ ከተማ ፅዳት አስተዳደር ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ ገዛኸኝ ደሲሳ በበኩላቸው የረጲ ላንድፊል ስፍራ የከተማዋን ደረቅ ቆሻሻ የሚቀበል በመሆኑ እዚህ አከባቢ ችግኝ መትከል ከቆሻሻው የሚወጣውን የተለያዩ ጋዞችና መርዛማ ፍሳሽ ከመከላከሉም በተጨማሪ ቦታውን አረንጓዴ በማድረግ የአከባቢውን ስነ ምህዳር መቀየር ረገድ የሚጫወተው ሚና ከፍተኛ መሆኑን ተናግረዋል። በዛሬው ዕለት ብቻ ከ20 ሺህ በላይ ችግኞች የሚተከሉ መሆኑን የጠቀሱት ዋና ዳይሬክተሩ ይህ ተግባር ቀጣይነት እንደሚኖረውም አመላክተዋል። አቶ ገዛኸኝ አክለውም ሁላችንም ችግኞችን በመትከል ብቻ ሳይሆን በመንከባከቡም የድርሻችንን እንወጣ ሲሉም መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡ በችግኝ ተከላው መርሀግብር ላይ የተሳተፉ አካላት በበኩላቸው ከተማዋ እንዳትቆሽሽ እለት ከዕለት ከምናደርገው የጽዳት ስራ ባሻገር በዘላቂነት ውጤት ሊያመጣ የሚችለው የአካባቢውን ገጽታ በአረንጓዴ አሻራ መለወጥ ሲቻል በመሆኑ በዚሁ ዕለት አረንጓዴ አሻራችንን ለማስቀመጥ በመሳተፋችን ደስተኞች ነን ብለዋል፡፡

ኤጀንሲው የደንብ ጥሰት የፈፀሙትን የመንገድ ጥርጊያ ፈፃሚዎች በህግ እንዲጠየቁ አደረገ። የአዲስ አበባ ከተማ ፅዳት አስተዳደር ኤጀንሲ ከከተማው ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ጋር በመቀናጀት በከተማ ፅዳት ዙሪያ ለህብረተሰቡ ግንዛቤ ከመፍጠር ጎን ለጎን የደንብ ጥሰት በሚፈፅሙ ግለሰቦችና ተቋማት ላይ አስተዳደራዊ እርምጃ ተግባራዊ እየተደረገ ይገኛል ሰኔ 24 ቀን 2017 ዓ.ም በለሚኩራ ክ/ከተማ ወረዳ 08 በተለምዶ ሳፋሪ አካባቢ የተመደቡ የመንገድ ጥርጊያ ፈፃሚዎች የአካባቢውን መንገድ አፅድተው የሰበሰቡትን አሸዋ ቱቦ ውስጥ ሲደፉ በመታየታቸው በደንቡ መሠረት 2ሺህ ብር እንዲቀጡ ማድረግ ተችሏል። ይሄ ተግባር ብርዱና ፀሀዩ ሳይበግራቸው የከተማችንን መንገዶች ፅዳት ዘውትር የሚጠብቁ አይበገሬ የመንገድ ጥርጊያ ፈፃሚዎቻችንን በጎ ገፅታ የሚያጠለሽ ተግባር በመሆኑ ኤጀንሲው በፅኑ የሚወገዝ ተግባር ነው ብሏል። ለከተማዋ ፅዳት ተቆርቋሪ የሆኑ የከተማዋን ነዋሪዎች ኤጀንሲው እያመሰገነ በግዴለሽ መንገድ ቆሻሻ የሚጥሉትን ግለሰቦች እና ተቋማትን ደግሞ በደንብ ቁጥር 167/2016 መሠረት ተጠያቂ የማድረጉ ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲልም አስታውቋል:: ሐምሌ 2/2017 ዓ.ም ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች https://linktr.ee/aacitymanager