1 474
Subscribers
No data24 hours
-37 days
-2130 days
Posts Archive
የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መልዕክት፡-
የኅብር ቀን
ብዝኃነት የኢትዮጵያ ጌጥ
ኢትዮጵያ በብዙ ጸጋዎች የተሞላች ሀገር ናት፡፡ እነዚህ ጸጋዎቿ የተለያዩ ሳይሆኑ ልዩ ልዩ ናቸው፡፡ የባህል፣ የቋንቋ፣ የታሪክ፣ የሥልጣኔ፣ የእምነት፣ የጾታ፣ የአመለካከት፣ ወዘተ. ብዝኃነት ያለንን የጸጋ ብዛት የሚያመለክት ነው፡፡ ብዝኃነት የኢትዮጵያ ታሪኳ እና መልኳ ነው፡፡
"ጳጉሜ 1 የጽናት ቀን" አከባበር " ጽኑ መሠረት ብርቱ ሃገር!"
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን … See more
የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ ቤት የነሐሴ ወር የስራ እንቅስቃሴን ያካተተውን የዜና መፅሄት በቀጣዩ ሊንክ በቴሌግራም ገፃችን ይከታተሉ።… See more
የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ ቤት የነሐሴ ወር የስራ እንቅስቃሴን ያካተተውን የዜና መፅሄት በቀጣዩ ሊንክ በቴሌግራም ገፃችን ይከታተሉ።… See more
የመንገድ መብራት ስራዎቻችን አንዳንዶች እንደሚተቹት ከተማን የማብለጭለጭ ሳይሆን በአዲስ አበባ የኮሪደር ልማት ትልቅ ለዉጥ ያመጣንበት (Breakthrough) የፈጠርንበት ስራችን ነዉ።በም/ከንቲባ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ… See more
"ጽኑ መሠረት ብርቱ ሀገር" በሚል መሪ ቃል የጳጉሜን የጽዳት ንቅናቄ መርሃ ግብር ተካሄደ።
የአዲስ አበባ ከተማ የፅዳት አስተዳደር ኤጀንሲ "ጽኑ መሠረት ብርቱ ሀገር" በሚል መሪ ቃል በኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከተማ ወረዳ 5 የፅዳት ንቅናቄ መርሀ ግብር በዛሬዉ እለት አካሂዷል።
በዚሁ የፅዳት የንቅናቄ መድረክ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ የፅዳት አስተዳደር ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ ገዛኸኝ ዴሲሳ በጽዳት ንቅናቄው ላይ እንደገለፁት አገራችን ዛሬ ላይ የደረሰችው ጽኑ መሠረት ስላላትና እኛ ደግሞ ዛሬ ላይ የህዳሴ ግድብን አጠናቀን ለማስመረቅ ዋዜማ ላይ በመገኘታችን በአለም አደባባይ ጎልተን እንድንታይ አስችሎናል ብለዋል።
አቶ ገዛኸኝ ዴሲሳ አክለውም እነዚህ ያከናወናቸው ተግባራት በቀጣይ አጠናክረን እንድንቀጥል የሚያደርገንና ከተማችንን ለመለወጥ ያለን ፅኑ ፍላጎት በተለይም በኮሊደር ልማትና የጽዳት ስራው ሁሉም ተሳታፊ በመሆን በአፍሪካ ብሎም በአለም ደረጃ ተወዳዳሪ ልንሆን ይገባል ሲሉም ተናግረዋል።
ከተማችን አዲስ አበባ በፅዳቷ እምርታዊ ውጤት ማስመዝገብ የቻለችዉ ሁላችንም ተቀራርበን እና ቅንጅታዊ ስራዎችን አጠናክረን በማስቀጠላችን ነው ሲሉ ጠቅሰዉ በቀጣይም ሁሉም የከተማዋ ነዋሪዎች በቀሪዎቹ የጳጉሜ ቀናት አካባቢያቸውን በማፅዳት ሁሉም ክፍለከተሞችን የማፅዳት ተግባር አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
በጽዳት ንቅናቄው ኘሮግራም ላይ የከተማ፣ የክ/ከተማ አመራሮች፣ የጽዳት አምባሳደሮች ፣የደንብ ማስከበር ባለሙያዎችና የአካባቢው ነዋሪዎች ተሳታፊ ሆነዋል።
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/aacitymanager
ጳጉሜ 1 - የጽናት ቀን
ጳጉሜ 1፣2017 "ጽኑ መሰረት ብርቱ ሀገር" በሚል አገራዊ መሪ ቃል የጽናት ቀን ይከበራል።
መሪ ቃሉ በጽናት ላይ የተገነባ ሀገር ጠንካራ እና ለየትኛውም ጊዜያዊ ፈተና የማይበገር ፣ እጅ የማይሰጥ በመጨረሻም ድል አድራጊ መሆኑን ያሳያል።
ፅናት ለእኛ ኢትዮዽያውያን እንደ ቡናችን ፣ እንደ አባይ ወንዛችን አንዱ መገለጫችን ነው። በጦርነት አዉድማ ቀደምቶቻችን በአድዋ ፣ በማይጨው፣ አትሌቶቻችን ደግም በስፓርት ሜዳ ፅናትን አሳይተውናል።
የቅርቡን እንኳን ብንመለከት በህዳሴ ግድባችን የባዳና ባንዳው ጥምረት እንዳለ ሆኖ ለ 13 ጊዜ ያህል በፀጥታው ምክር ቤት አጀንዳ ስንሆን ፣ ከዉስጥም ከዉጪም የተቀናጁ ፈተናዎችን በድል ተሻግረን ዛሬ ግድባችንን ጨርሰን የደረስንበት የታሪክ እጥፋት ከመሪ እስከ ህዝብ ያለንን ፅናት ለዓለም ህዝብ ያሳየንበት ነው።
በስንዴ አብዮት ፣ በአረንጓዴ አሻራ ጭምር የስኬታችን ዋነኛው ሚስጥር የመሪዎቻችንና መሪውን የተከተለዉ ህዝብ ፅናት ነው ።
በጽኑ መሰረት ላይ የተገነባ ከተማ ያለማቋረጥ ወደፊት ይገሰግሳል ፤ የትኛዉም ምድራዊ ሀይል ካለመበት አያስቀረውም፣ በአዲስ ሀይል አዳዲስ ስኬቶችን ይጨብጣል ።
በከተማችን በ2017 ዓ.ም የታየው ፣ ዓለምን ያስደነቀው ፣ አዲስ አበባን አዲስ እና አበባ ያደረገው ስር ነቀል መልሶ ማልማት ፣ የኮሪደርና የወንዝ ዳርቻዎች ልማት ፣ የገቢ አሰባሰብ ፣ የሰላምና ፀጥታ ወዘተ በርካታ ተግባራት ፣ እንዲሁ በቀላሉ የተገኘ ውጤት አይደለም፤ ይልቁኑ በፅናት በመጓዝ የተገኘ እንጂ። ፈተና ሳይኖር ቀርቶ አይደለም ፣ በሚሊዮን የሚቆጠር የከተማችን ነዋሪ ተሳትፎ ፣ በፅናት የተቀናጀ የአመራር ሰጪነት የታየበት ተጨባጭ ውጤት ፣ የጠንካራ ፅናታችን ውጤት በመሆኑ በአዲሱ የ2018 ዓመትም ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል።
በዛሬዉ እለት የጽናት ቀንን ስናከብርም ለሀገራችን እና ለከተማችን ሁለንተናዊ ብልጽግና እንደ ከዚህ ቀደሙ የትኛውንም መስዋዕትነት ለመክፈል ያለንን የማይናወጥ ጽናት ዳግም በማረጋገጥ መሆን ይኖርበታል።
አመሰግናለሁ
ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን ይባርክ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
ሚዲያ ህዝብ እና መንግስትን የሚያገናኝ ድልድይ እንደመሆኑ የአዲስ አበባ ከተማ ሥራ አስኪያጅ ጽህፈት ቤት ከአዲስ ሚዲያ ጋር የተፈራረመው የጋራ መግባቢያ ስምምነት ጽ/ቤቱ የሚያከናወናቸውን ስራዎች ወደ ህዝብ ለማድረስ ብሎም የህዝብን ሃሳብ ለማድመጥ የሚረዳ ነው-በምክ… See more
የ2017 ዓ.ም አምስቱን የጳጉሜ ቀናት ስያሜ በድጋሚ ለማስታወስ ያህል:-
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/aacitymanager
