en
Feedback
Addis Ababa City Manager Office

Addis Ababa City Manager Office

Open in Telegram
1 474
Subscribers
No data24 hours
-37 days
-2130 days
Posts Archive
በአዲስ አበባ ከተማ ሥራ አስኪያጅ ጽ/ቤት የማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት የቅዳሜ እለት የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪዎች የወረዳ አገልግሎት አሰጣጥ፣ የፍሳሽ መወረደ መስመሮች ፣የሞዴል ፅዳት ብሎኮች፣ ወረዳዎች የመስክ ጉብኝት በምስል;-

ዛሬ "የወጣቶች ሚና ለሁለንተናዊ ብልጽግና" በሚል መሪ ሀሳብ በተዘጋጀው መድረክ ከአስራ አንዱም የአዲስ አበበባ ክፍለ ከተሞች ከተወጣጡ የወጣቶች ተወካዮች ጋር በሀገራዊ እና ከተማ አቀፍ ጉዳዮች ዙሪያ ተወያይተናል። ከለውጡ ወዲህ በአዲስ አበባ ከተማ ልዩ ትኩረት ከተሰጣቸው አጀንዳዎች መካከል ወጣቶች በአካል እና በስነልቦና ተገንብተዉ አስተማማኝ የስራ ዕድል እንዲያገኙ ለማስቻል በተሰራው ስራ አመርቂ ውጤቶች መመዝገባቸውን እና በውጤቱም ተጠቃሚ መሆናቸውን ገልፀውልናል ። ለአብነትም ከ1400 በላይ የስፖርት ማዘውተሪያ ሜዳዎች መገንባታቸውን እና ባለፉት 5 ዓመታት ብቻ 1.1 ሚለየን ወጣቶች ቋሚ የስራ ዕድሎችን እንዲያገኙ ለማስቻል ባከናወንነው ስራ የበርካታዎችን ህይወት በተጨባጭ መለወጥ መቻሉን አረጋግጠውልናል። የከተማችን ወጣቶች የነገዋን ኢትዮጵያ ለመዋጀት ይቻላችሁ ዘንድ ዛሬ ላይ በስነልቦና፣ በአካል ብቃት፣ በእውቀት እና በክህሎት ራሳችሁን በማዘጋጀት እያበረከታችሁ ያላችሁን አስተዋጽኦዎችን ጨምሮ በበጐ ፍቃድ አገልግሎት ለሰራችሁት የተቀደሰ ተግባር በሰላም ሰራዊት ተደራጅታችሁ የከተማችሁን ሰላም በማስጠበቅ ረገድ እየሰራችሁ ላላችሁት አኩሪ ስራዎች የከተማ አስተዳደራችን በጣም ያመሰግናችኋል። ለወደፊትም የወጣቶችን ኢኮኖሚያዊ ፣ማህበራዊ እና ፖለቲካዊ ተሳትፎ እና ተጠቃሚነትን ይበልጥ በሚያረጋግጡ አጀንዳዎች ዙሪያ ትኩረት ሰጥተን እንድንሰራ ላነሰችሁልን ሀሳቦችና ጥያቄዎች የከተማ አስተዳደራችን አቅዶ የሚሰራ መሆኑን አረጋግጥላችኋለሁ ። ለቸራችሁን እውቅናም እናመሰግናለን፤ ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን ይባርክ ከንቲባ አዳነች አቤቤ

እንኳን ደስ አለን!! ዛሬ 5ተኛዉን ግዙፍ እና ዘመናዊ የገበያ ማእከል አጠናቀን ለአገልግሎት ክፍት አድርገናል። ለህዝባችን ጥያቄዎች እና ቅሬታዎች የምንሰጣቸው ምላሾች ተጨባጭና መሰረታዊ ለዉጥ የሚያመጡ ናቸው!! የኢፌዴሪ ንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስትር ከክቡር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) ጋር በመሆን አምራቹንና ሸማቹ ህዝባችንን እንደ ድልድይ ሆኖ በቀጥታ በማገነኘት የኑሮ ውድነቱን እና የዋጋ ንረትን በመቀነስ የነዋሪዎቻችንን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ የሚያስችል የላፍቶ ቁጥር 2 የገበያ ማዕከልን መርቀን ለአገልግሎት ክፍት አድርገናል። እስካሁን ካከናወናቸው በርካታ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ፋይዳ ካላቸው ፕሮጀክቶች መካከል የኑሮ ውድነት እና የዋጋ ንረትን በመቀነስ ረገድ ጉልህ አስተዋጽዎ እያበረከቱ የሚገኙ በከተማችን አምስቱም በሮች ማለትም በላፍቶ፣ አቃቂ ቃሊቲ፣ ለሚ ኩራ እና ኮልፌ ክፍለ ከተሞች ዉስጥ ተገንብተው አገልግሎት በመስጠት ላይ የሚገኙት የግብርና ምርቶች መሸጫ ማዕከላት ተጠቃሾች ናቸው፡፡ እነዚህ የገበያ ማዕከላትን በመገንባት የአሰራር ስርዓት ዘርግተን ስራ ዉስጥ ማስገባት በመቻላችን በርካታ ዉጤቶች የተመዘገቡ ሲሆን፣ በተለይም ከዚህ ቀደም በአምራች እና በሸማቹ ህዝባችን መካከል ጋሬጣ ሆኖ የነበረዉ የደላላ ሰንሰለትን መቆራረጥ በመቻላችን በዉድድር ላይ የተመሰረተ የግብይት ስርዓት በመፈጠሩ ህዝባችን እፎይታን አግኝቷል። ዛሬ የተከፈቱትን 159 ሱቆች ጨምሮ እስካሁን በተገነቡት ማዕከላት ዉስጥ 1037 ሱቆችና ግዙፍ መጋዘኖች አገልግሎት በመስጠት ላይ ያሉ ስሆን፤ በዛሬዉ ዕለት መርቀን ለአገልግሎት ክፍት ያደረግነዉ የላፍቶ ቁጥር 2 የምርት ግብይት ማዕከልም 8.8 ሄክታር ላይ የተገነባ፣ 159 ሰፋፊና ምቹ ሱቆችን፣ 9 የጅምላ ማከፋፊያዎች እና 2 ሞሎችን የያዘ በመሆኑ በዚህ ዘርፍ ለጀመርነው ሁለንተናዊ ለውጥ ትልቅ አቅምን የሚፈጥር ነዉ። እነዚህ የገበያ ማዕከላት አገልግሎት መስጠት ከጀመሩ ወዲህ ከዚህ ቀደም የምርት መደበቅ ሴራ እና ምክንያታዊ ያልሆነ የዋጋ ጭማሪ በማስወገድ ለህዝባችን አለኝታ መሆን ስለቻላችሁ በነዋሪው ህዝባችንና በከተማ አስተዳደራችን ስም ያለንን አድናቆት እየገለጽን፣ ለገበያ ማዕከሉ ግንባታ ቦታቸውን የለቀቁ በግብርና ስራ የሚተዳደሩ የከተማችን ነዋሪዎች፣ ለዲዛይንን እና ግንባታ በሮ፣ ለኮንትራክተሩ የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ስራዎች ድርጅት እና ለአማካሪው ኢንጂነሪንግ ምስጋናዬን ማቅረብ እወዳለሁ። ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን ይባርክ ከንቲባ አዳነች አቤቤ

በምክትል ከንቲባ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ሥራ አስኪያጅ ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ ከፋና ኤፍ ኤም 98. 1 ሬድዮ. ጋር ከመዲናዋ የመሠረተ ልማት ቅንጅት ስራዎች ዙሪያ ያደረጉትን ቃለ ምልልስ ይከታተሉ

ብቃት ያለው እና ከሌብነት የፀዳ አገልግሎት ለኢትዮጵያ ብልፅግና!! "ብቃት ያለው ሲቪል ሰርቪስ ለኢትዮጵያ ብልጽግና " በሚል መሪ ሀሳብ በዛሬው እለት ከወረዳ እስከ ከተማ ማዕከል ካሉ ተቋማት ከተውጣጡ የመንግሥት ሰራተኞች ተወካዮች ጋር በከተማዊና ሀገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ ተመካክረናል። አዲስ አበባ ለነዋሪዎቿ ምቹ፣ ለጎብኚዎቿ አስተማማኝ የቱሪስት መዳረሻ እንድትሆን በየደረጃው ካለው የመንግሥት ሰራተኛ ጋር በጋራ በመሆን ከከተማዋ ገቢ 71 በመቶውን ለዘላቂ ልማት ስራዎች በማዋል ውጤቶችን ማስመዝገብ ችለናል። ለህዝባችን የምንሰጣቸው መንግሥታዊ አገልግሎቶች ፍትሃዊ እና ጥራት ያላቸው እንዲሆኑ ጽኑ አቋም ይዘው ተጨባጭ ውጤቶችን ያስመዘገቡ እና በተግባር ውጤታማ የሆኑ የመንግሥት ስራተኞቻችን ሚና ከፍተኛ ነው። ሆኖም ተገልጋዩን ህዝብ የሚያማርሩ ሙሠኛ የሆኑ ሰራተኞችም እንዳሉ በየደረጃው በምናደርጋቸው ግምገማዎች ብሎም ህዝባችን በሚሰጠን ጥቆማዎችና ክትትሎች እየለየን የእርምት እርምጃዎችን ስንወስድ ቆይተናል። አሁንም የመንግስት ሰራተኞቻችንን በጀምላ ከመዉቀስ ወጥተን ችግር ያለባቸዉን እያረምን፤ ጥፋተኞቹን እያጋለጥንና ተጠያቂ እያደረግን ህዝባችንን በላቀ ትጋትና ታማኝነት ማገልገላችንን አጠናረን እንቀጥላለን። ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ ከንቲባ አዳነች አቤቤ

"ዛሬ ከመላው ኢትዮጵያ ከተወጣጡ የንግዱ ማኅበረሰብ ተወካዮች ጋር በዞን፣ በክልል እና ከተሞች ደረጃ ከተካሄዱ ውይይቶች የቀጠለ ውይይት ዛሬ በፌዴራል ደረጃ አካሂደናል። ይኽ መድረክ በየደረጃው የተሰበሰቡ የንግዱ ዘርፍ ጉዳዮች እና ሃሳቦች በሀገር አቀፍ እቅዶች እና የልማት ግቦች ዝግጅት ግብዓት ይሆኑ ዘንድ ለማካተት የተዘጋጀም ነው"። ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አሕመድ

የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ቅዳሜ ሙሉቀን የሚሰጡ አገልግሎቶች ፈጣን እና ተደራሽ እየሆኑ መምጣታቸውን በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢ/ር ወንድሙ ሴታ ገለጹ ፡፡ AMN-Addis Media Network

የግንቦት ወር ዜና መፅሔት ለንባብ በቅቷል።