1 474
Subscribers
No data24 hours
-37 days
-2130 days
Posts Archive
+6
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በቦሌ የኮሪደር ልማት ስራ አፈፃፀም ክትትል እና ድጋፍ እያደረጉ ያሉ አካላትን አመሰገኑ።
ከንቲባ አዳነች አቤቤ እንደተናገሩት የኮሪደር ልማት ስራዎቻችን የእያንዳንዱ ቀን እና ምሽት ስራ እየተገመገመ የሚስራ ስራ መሆኑን ገልጸው ፤ ልማቱ ለመረጠን እና ቃል ለገባንለት የከተማችን ነዋሪ የኢኮኖሚ ፣ ማህበራዊ ትስስርን ማጠናከር የሚያስችሉ አገልግሎቶችን በማስፋፋት ፤ከዘመናዊነት ጋር የተቃኘ አሰራርን በመዘርጋት እና በማሳለጥ ለከተማችን የኢኮኖሚ እድገት ወሳኙን ሚና እንድንወጣ ያስቻለን ነዉ ብለዋል፡፡ በሂደቱም በምታደርጉት ተሳትፎ በአዲስ አበባ ፈጣን ለውጥ ውስጥ ታሪካዊ አሻራችሁን እያሳረፋችሁ መሆናችሁን ተረድታችሁ ስራውን በፍጥነት ብቻ ሳይሆን በጥራት እንድትሰሩ አበረታታችኋለሁ ብለዋል።
በታሪክ ሂደት የከተማዋን የሥራ ባህል በቀየርንበት ፤ ቀንና ለሊት በስራችሁበት ጎን ለሥራ ጥራት የምትሰጡት ትኩረት እንዲሁ ባህል ሆኖ መቀጠል እንዲችል መስራት አለብን ሲሉ አበክረው ተናግረዋል።
ከንቲባ አዳነች አቤቤ በቦሌ ሳይት በየምሽቱ በሥራ ላይ ለነበሩ ሰራተኞችን የእራት ግብዣ እያደረጉ ያሉትን የአካባቢውን ነዋሪዎች ምስጋናና ክብር ይገባቸዋል ብለዋል።
+7
ለ #ጽዱኢትዮጵያ ንቅናቄ ጥሪ ስናቀርብ ዜጎቻችን በከፍተኛ ተነሳሽነት በሥራው ተሳትፈዋል። ዋናው አላማችን አካባቢያችንን ሳቢ በማድረግ መፀዳጃ ቤት የመጠቀም ባህላችንን ከመሠረቱ ማዳበር ነበር። ዛሬ በዜጎቻችን በዋጋ የማይተመን የልብ መዋጮ እና እምነት የተገነቡትን ሥራዎች በቦታው በመገኘት ገምግመናል። ከፍተኛ ጥራት ባላቸው ጠንካራ እና ዘመን ተሻጋሪ በሆኑ ቁሶች በመጠቀም ደረጃቸውን የጠበቁ የህዝብ መፀዳጃ ቤቶች ለመገንባት ቁርጠኝነት ይዘናል። ይህ የሥራው መጀመሪያ ነው። በእናንተ ያላሰለሰ ድጋፍ የጀመርናቸውን ሥራዎች እናስፋፋለን።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ
የ#አረንጓዴዓሻራ የችግኝ ተከላ ወቅት ሥራችን ያስቀመጥነውን ግብ በሚያሳካ መልካም አጀማመር ላይ ይገኛል። የኅብረተሰባችንም የችግኝ ተከላ ተነሳሽነት ከፍተኛ ነው። ዛሬ በጫካ ፕሮጀክት ስፍራ የአፕል ችፍኞችን ተክለናል። በአካባቢው የተደረገውን የዘንድሮውን ችግኝ ተከላ ለየት የሚያደርገው ቀድሞ የነበረው የባህርዛፍ ሽፋን ተወግዶ በሀገር በቀል የእርከን ሥራ እና ተክል የተተካ መሆኑ ነው። ከሀረር አካባቢ እና ከኮንሶ የመጡ ህዝቦቻችን አፈር እንዳይሸረሸር የሚያደርገውን ጊዜ የማይሽረውን ክህሎታቸውን አካፍለውናል። በከተሞች የምንሠራውን የአረንጓዴ አሻራ ጥረቶቻችንን በጋራ በማስፋፋት የአዲስ አበባን አረንጓዴ ሽፋን መጨመር እንችላለን።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አቢይ አሕመድ
በከተማችን በበርካቶች የቀን ከሌሊት ልፋት ውብ ተደርገው በተገነቡ መሰረተ ልማቶች ላይ ቆሻሻ የሚጥሉ፣ ከተፈቀደላቸው መንገድ ውጪ የሚሄዱ እንዲሁም ከተማችንን አረንጏዴ ለማድረግ በመንገድ አካፋዮች ላይ የተተከሉ ዛፎችን በግዴለሽነት በተሽከርካሪ በመግጨት ጉዳት ያደረሱ አካላት ተቀጡ::
በዚህም 3 ተቋማት ከተፈቀደ ቦታ ውጪ ቆሻሻ በመጣል እንደየጥፋት ደረጃቸው 100 ሺሕ ፣ 50 ሺ እና 20 ሺሕ ብር የተቀጡ ሲሆን 5 አሽከርካሪዎች በመንገድ አካፋይ ላይ የተተከሉ ዘንባባ ዛፎችን ገጭተው በመጣላቸው እንደየጥፋት ደረጃቸው ከ150 እስከ 300 ሺሕ ብር እንዲሁም 11 ሰዎች ከተፈቀደው የእግረኞች መንገድ ውጪ በመሄዳቸው ከ150 እስከ 1000 ብር ተቀጥተዋል::
ነዋሪዎቻችን እነዚህ ደረጃቸውን ጠብቀው የተገነቡ መሰረተ ልማቶችን በተፈቀደው መንገድ ብቻ በመጠቀም እና በመንከባከብ እራሳቸውን እና ቤተሰቦቻቸውን ከቅጣት እና ከትራፊክ አደጋ እንዲከላከሉ ለማሳሰብ እንወዳለን::
ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ!
Facebook:-
👇👇👇👇
https://www.facebook.com/CITYMANAGER1
Telgram:-
👇👇👇👇
https://t.me/aacitymanager
Twitter:-
👇👇👇👇
https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r
YouTube:-
👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s
Tiktok
👇👇👇👇
https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager...
Website
👇👇👇👇
https://www.aacitymanger.gov.et
በተጠናቀቀዉ በ2016 ዓ.ም በጀት ዓመት በአዲስ አበባ ከተማ እና በአካባቢዉ ከደረሱ አደጋዎች ከ37 ቢሊየን ብር በላይ ከዉድመት ማዳን መቻሉ ተገለጸ።
በተጠናቀቀዉ የ2016 ዓ.ም በጀት ዓመት በአዲስ አበባ ከተማና በአካባቢዉ 523 አደጋዎች ያጋጠሙ ሲሆን ከደረሱት አደጋዎች መካከል 351 የእሳት አደጋ ሲሆኑ ቀሪ 172 አደጋዎች ደግሞ ከእሳት ዉጪ ያጋጠሙ ሌሎች ድንገተኛ አደጋዎች ናቸዉ።
በደረሱት አደጋዎች የሁለት ሰዎች ህይወት በእሳት አደጋ ሲያልፍ የአደጋ ገዜ ሠራተኞችን ጨምሮ 90 ሰዎች ላይ ቀላልና ከባድ ደርሷል።
ባጋጠሙት የእሳትና ሌሎች ድንገተኛ ምክንያት ህይወታቸዉ አደጋ ዉስጥ የነበሩ የ156 ሰዎችን ህይወት መታደግ የተቻለ ሲሆን በሌላ በኩል ከ 37 ቢሊየን ብር በላይ የሚገመት ንብረት ከዉድመት ማትረፍ ተችሏል።
ከደረሱት 523 አደጋዎች ዉስጥ 465 በአዲስ አበባ ከተማ ሲሆን ቀሪ 58 አደጋዎች በተለያዩ የሸገር ከተሞች ያጋጠሙ ናቸዉ።
ከአምና ተመሳሳይ ጊዜ ከደረሱ አደጋዎች ጋር ሲነጻጸር በተለይም በሰዉ ሞትና ከአካል ጉዳት ጋር ሲነጻጸር ሞት በሰባት ሲቀንስ
ጉዳት በ23 የቀነሰ ሲሆን ኮሚሽን መ/ቤቱ አደጋዎች ከደረሱ በኋላ በአደጋ ስፍራ ፈጥኖ በመድረስ የሰዉ ህይወትና ንብረት የማዳን አቅሙ እያደገ መምጣቱ ተገልጿል።
ለእሳትና ለሌሎች ድንገተኛ አደጋዎች እንዲሁም ለአንቡላንስ አገልግሎቶች በ939 ፈጥነዉ ያሳዉቁ !
ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ!
Facebook:-
👇👇👇👇
https://www.facebook.com/CITYMANAGER1
Telgram:-
👇👇👇👇
https://t.me/aacitymanager
Twitter:-
👇👇👇👇
https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r
YouTube:-
👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s
Tiktok
👇👇👇👇
https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager...
Website
👇👇👇👇
https://www.aacitymanger.gov.et
ከሰልን ሲጠቀሙ መወሰድ ያለባቸው ጥንቃቄዎች
በተለይም ቀዝቃዛ የአየር ሁኔታ ሲኖር ከሰልን በአማራጭ የኃይል ምንጭነት መጠቀም የተለመደ ተግባር ነው፡፡
በመሆኑም ከሰልን ሰዎች ለተለያየ አገልግሎት ሲጠቀሙ ተገቢውን ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለባቸው ባለሙያዎች ይመክራሉ፡፡
ምክንያቱም አስፈላጊው ጥንቃቄ ካልተደረገ የከሰሉ ጭስ ሞትን ጨምሮ የዕድሜ ልክ ህመም ለሆኑት የአዕምሮ ጉዳትና የልብ በሽታ ስለሚያጋልጥ ነው ይላሉ፡፡
በጉዳዩ ላይ የተካሄዱ ጥናቶች እንደሚያመላክቱትም÷ የከሰል ጭስ በዓይን የማይታይና ሽታ አልባ መርዛማ ጋዝ አለው፡፡
ይህ ጋዝ የሚፈጠረውም ጋዝ፣ ዘይት፣ ከሰል ወይም እንጨት ሙሉ በሙሉ ተቃጥለው ባለማለቃቸው መሆኑ ይጠቀሳል፡፡
የከሰል ጭስ ባለበት አካባቢ አየር ወደ ውስጥ በሚሳብበት ጊዜ÷ በደም ውስጥ በመግባት የቀይ የደም ኅዋስ አካል የሆነውና ኦክስጅን ተሸክሞ ለተያዩ የሰውነት ክፍሎች ከሚያደርሰው ሂሞግሎቢን ጋር በመቀላቀል ጉዳት ያስከትላል፡፡
ይህን ተከትሎም ደም ኦክስጅን መሸከሙን ያቆማል፤ በዚህ የተነሳ የኅዋሶቹ አነስተኛ ክፍሎች ይጎዳሉ፤ ብሎም ይሞታሉ፡፡
• በከሰል ጭስ (በካርበን ሞኖክሳይድ) የተጠቃ ሰው የሚያሳያቸው ምልክቶች
የራስ ምታት፣ ራስ ማዞርና መታመም፣ የድካም ስሜትና ግራ መጋባት፣ ሚዛንን ለመጠበቅ መቸገር፣ የዕይታና የትውስታ ማጣት፣ ራስን መሳት፣ በአንድ ነገር ላይ አትኩሮት ማጣት፣ የሆድ ህመም እንዲሁም ለመተንፈስ መቸገር ምልክቶች ሊታዩበት እንደሚችሉ ባለሙያዎች ያስረዳሉ፡፡
• የከሰል ጭስን እንዴት መከላከል ይቻላል?
በከሰል ምግብ ማብሰል ሲያስፈልግ በቂ አየር እንዲያገኝ ከተቻለ ከቤት ውጭ ማብሰል፤ ከቤት ውጭ ማብሰል ካልተቻለ ደግሞ ሙሉ በመሉ ከተቀጣጠለና ጭሱ መጥፋቱ ሲረጋገጥ ወደ ቤት ማስገባት ይመከራል፡፡
በተጨማሪም የከሰል ምድጃ እየተጠቀሙ በር እና መስኮት አለመዝጋት፣ በከሰል ምግብ አብስለው ሲጨርሱ በውኃ ማጥፋትና በርና መስኮት በመክፈት ቤቱን ማናፈስ እንዲሁም ከሰል ቤት ውስጥ አለማቀጣጠልን ባለሙያዎች ይመክራሉ፡፡
ከዚህ ባለፈም ከሰል ቤት ውስጥ አቀጣጥሎ ማሸለብ ወይም መተኛት አደጋው የከፋ በመሆኑ ከእነዚህ ድርጊቶች ይቆጠቡ።
FBC
ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ!
Facebook:-
👇👇👇👇
https://www.facebook.com/CITYMANAGER1
Telgram:-
👇👇👇👇
https://t.me/aacitymanager
Twitter:-
👇👇👇👇
https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r
YouTube:-
👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s
Tiktok
👇👇👇👇
https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager...
Website
👇👇👇👇
https://www.aacitymanger.gov.et
የምትተክል ሃገር የሚያጸና ትውልድ!
🌴 የ150 ሺህ ችግኝ ተከላ 🌱
በአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ፅ/ቤትና በተጠሪ ተቋማቱ በዘንድሮው የ6ኛ ዙር የአረንጓዴ አሻራ መርሐግብር ከ150 ሺህ በላይ ችግኞች ለመትከል የቅድመ ዝግጅት ስራዎች እየተከናወነ ይገኛል።
ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ!
Facebook:-
👇👇👇👇
https://www.facebook.com/CITYMANAGER1
Telgram:-
👇👇👇👇
https://t.me/aacitymanager
Twitter:-
👇👇👇👇
https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r
YouTube:-
👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s
Tiktok
👇👇👇👇
https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager...
Website
👇👇👇👇
https://www.aacitymanger.gov.et
ከሃገራችን የተለያዩ ከተሞች የመጡ ከንቲባዎች በአዲስ አበባ እየተከናወኑ የሚገኙ የኮሪደር ልማት ሥራዎችን በመጎብኘት ላይ ይገኛሉ፡፡
