en
Feedback
Addis Ababa City Manager Office

Addis Ababa City Manager Office

Open in Telegram
1 474
Subscribers
No data24 hours
-37 days
-2130 days
Posts Archive
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ታላቁ የኢትዮጵያ ኅዳሴ ግድብን መረቁ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የኢትዮጵያውያን ሕብረ ብሔራዊነት መገለጫ የሆነውን ታላቁ የኢትዮጵያ ኅዳሴ ግድብ በዛሬው ዕለት መረቁ፡፡ የኢትዮጵያውያን የዘመናት ቁጭት የነበረው ታላቁ ኢትዮጵያ ኅዳሴ ግድብ ግንባታ ተጠናቅቆ የምረቃ ሥነ ሥርዓት በጉባ እየተካሄደ ነው፡፡ በምረቃ ሥነ ሥርዓቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፣ የፌደሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባዔ አገኘሁ ተሻገር፣ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባዔ ታገሰ ጫፎ እና ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ተገኝተዋል፡፡ በተጨማሪም በም/ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊ እና የብልጽግና ፓርቲ ም/ፕሬዚዳንት አደም ፋራህ፣ የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማሪያም ደሳለኝ፣ የቀድሞ ም/ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን፣ የክልል ርዕሳነ መስተዳድሮች:የከተማ አስተዳደር ከንቲቦች እና ሚኒስትሮች ታድመዋል፡፡

Ethiopia has ignored it!… See more · See original · Rate this translation

የታሪካችን እጥፋት ዋዜማ !…

የዘመናት ቁጭት ፣ ጥልቅ የአገር እና የሕዝብ ፍቅር ፣ የድል አድራጊነት ፣ የአሸናፊነት እና የደስታ እምባ ! የህዳሴው ግድብ ምርቃት ዋዜማ ላይ ከጉባ ሰማይ ስር! #Ethiopia #GERD #prosperity #victory #patriotis #Ethiopia #GERD #Prosperrity #Victory #Patriotism ከንቲባ አዳነች አቤቤ

የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ምረቃ የዋዜማ ዝግጅት #etv #PMOEthiopia #AbiyAhm… See more የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ምረቃ የዋዜማ ዝግጅት - ቀጥታ ከጉባ… See more

የረዳን ፈጣሪ አምላክ ይመስገን !! መላዉ ኢትዮዽያዊን በሙሉ እንኳን ደስ አለን!! የፅናታቻን ፣ የላባችን ፣ የደማችን ፣ የጥረታችን ዉጤት ፣ የዘመናት ቁጭታችን መደምደሚያ ፣ የብልፅግናችን መሰረት ፣ የአይበገሬነታችን ምልክት ለሆነዉ የታላቁ ህዳሴ ግድባችን ምረቃ እንኳን አደረሰን!! ባንድነት ስንቆምና ስንተባበር የማችለዉም የለም !! ፈጣሪ ኢትዮዽያና ህዝቦቿን ይባርክ ከንቲባ አዳነች አቤቤ

የሲቪል ምዝገባና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ በቴክኖሎጂ አገልግሎት አሰጣጥ እያመጣ ያለዉ እምርታዊ ለዉጥ የተሻለ መሆኑ ተገለፀ። “እምርታ ለዘላቂ ከፍታ” የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ “እምርታ ለዘላቂ ከፍታ” በሚል መሪ ቃል በሀገር አቀፍ ደረጃ እየተከበረ የሚገኘውን “የእምርታ ቀንን” ምክንያት በማድረግ የከተማ አምባሳደር የሆኑት የኪነ-ጥበብ ባለሙያዎች እና ታዋቂ ሰዎች የቴክኖሎጂ እምርታዊ ለዉጥ ጎበኙ፡፡ የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮሴፍ ንጉሴ የእምርታ ቀንን አስመልክቶ ኤጀንሲው ቀደምት የነበረውን ስም ሙሉ በሙሉ በመቀየር እና ተቋሙ ላለፉት አመታት ሪፎርም በማድረግ እና አገልግሎቱን ቀልጣፋ በማድረግ በቴክኖሎጂ የተደገፈ አገልግሎት እየሰጠ የሚገኝበትን መንገድ አስረድተዋል፡፡ ኤጀንሲው ከነበረበት ውስብስብ ችግር በመውጣት ከማዕከል እስከ ወረዳ ሙሉ በሙሉ በቴክኖሎጂዎች የታገዘ አገልግሎት እየሰጠ መሆኑን ያነሱ ዋና ዳይሬክተሩ ብልሹ አሰራር ከመከላከል እና ከመቀነስ አኳያ ትልቅ ስራ መስራቱን ገልፀዋል፡፡ በተያያዘም 2018 አመት እንደ ተቋም እና እንደ ሀገር ከፍ የምንልበት እንዲሁም በከተማችን ለሚገኙ ህብረተሰባችን ቀልጣፋ እና ተደራሽ የሆነ አገልግሎት ለመስጠት ቃል የምንገባበትና የከተማችንን ከፍታ የምናረጋግጥበት ዲጂታል ኢትዮጵያን እንገነባለን ሲሉ አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡ በመጨረሻም ጎብኚዎቹ ተቋሙ ያደረገውን ሪፎርም በማድነቅ ለሌሎች ተቋማት ሞዴል የሚሆንበት እና ሀገራችንን ለማንሰራራት የተነሳችበት ትልቅ እምርታ ነው በማለት መንግስት ለሀገራችን ከፍታ እየሰራ የሚገኘውን ተግባር ለህዝብ ተደራሽ በማድረግ የኢትዮጵያን ከፍታ እናረጋግጣለን ሲሉ ተናግረዋል፡፡ .ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች https://linktr.ee/aacitymanager

በአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ፅ/ቤት እና በተጠሪ ተቋማቱ የሚከናወኑ የሰው ተኮርና በጎ ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ በም/ከንቲባ ማእረግ የአዲስ አበ… See more

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ዛሬ ጠዋት በሁለተኛው የአፍሪካ የአየር ንብረት ጉባኤ መክፈቻ መርሃግብር አፍሪካ የአየር ንብረት ተጠቂ ብቻ ሳትሆን የመፍትሄውም አኅጉር መሆኗን አፅንኦት ሰጥተው በመግለፅ ከፍተዋል። እንደአረንጓዴ ዐሻራ የችግኝ ተከላ ሥራ፣ ለአየር ንብረት ጥበቃ የተመቸ ግብርና እና ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብን በማውሳትም የኢትዮጵያን ሥራዎች በምሳሌነት በማንሳት አውስተዋል። ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ከአየር ንብረት ርዳታ ወደ አየር ንብረት ኢንቨስትመንት ለውጥ ሊደረግ እንደሚገባ በመግለጽ Climate Innovation Compact የተሠኘ በ2030 1000 አፍሪካ መር መፍትሔዎች የሚገኙበትን ምክረ ሃሳብ አቅርበዋል። አፍሪካ በታዳሽ ኃይል፣ በምግብ ዋስትና እና የሥነ ምኅዳር ጥበቃ የመምራት አቅሟንም በማጽናት አንስተዋል። በተጨማሪም ኢትዮጵያ እኤአ በ2027 የCOP32 ጉባኤን ለማስተናገድ ያላትን ጥያቄም አቅርበዋል። ይኽም ሀገራችንን እና አኅጉራችንን በአየርንብረት ጥበቃ ተግባር የመሪነት ሚና የሚያጎናፅፍ ይሆናል። #PMOEthiopia

እንኳን ደህና መጣችሁ! እንኳን ደህና መጣችሁ! የማንሰራራታችን ሂደት ለአፍሪካውያን ወንድሞቻችን የሚተርፍ ፣ ለዓለም የሚነገር ምስክርነት ነው ! ዛሬ ለ2ኛው የአፍሪካ የአየር ንብረት ጉባኤ ወደ አዲስ አበባ የመጡ ከ25 ሺህ በላይ እንግዶችን ተቀብለን በጉባኤው ላይ እየተሳተፉ ይገኛሉ ። ጉባኤው “ዓለም አቀፍ የአየር ንብረት መፍትሄዎችን ማሳለጥ፣ የአፍሪካን አረንጓዴ ልማት በፋይናንስ መደገፍ” በሚል መሪ ሀሳብ ከጳጉሜን 3 እስከ 5፣ 2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ ይካሄዳል። በጉባዔው መሪ ሃሳብ መሠረት ኢትዮጵያ ለአየር ንብረት መዛባት መፍትሔ ይሆናሉ ያለቻቸውን ተግባራት ጥንቅቅ አድርጋ እየሰራች መሆኗን በኤግዚቢሽን ተሳትፎአችን ለአፍሪካውያን ወንድሞቻችን አስረድተናል። እጅ ለእጅ ተያይዞ ለማደግ፤ ለመጪው ትውልድ የሚተርፍ ስራ ለመስራት አዲስ አበባ ማሳያ ተሞክሮዎችን ይዛ ቀርባለች። ውድ የከተማችን አንግዶች አዲስ አበባ የእናንተ የምቾት ቤታችሁ ናት ። አዲስ አበባ የእናንተ የብልፅግና በር ናት። መምጣታችሁ፣ አብረን መምከራችን ለመጪው የአፍካዊያን መፃኢ ዕድል መሠረት ነው ። የከተማችን ነዋሪዎችም እስካሁን እያደረገችሁት ያለው አስተዋጽኦ ጉባኤው እስኪጠናቀቅና እንግዶች ወደየመጡበት አገር እስኪመለሱ ድረስ የተለመደ ትብብራችሁንና እንግዳ ተቀባይነታችሁን እንድታጠናክሩ ስል እጠይቃለሁ። ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና አፍሪካን ይባርክ ከንቲባ አዳነች አቤቤ