1 474
Subscribers
No data24 hours
-37 days
-2130 days
Posts Archive
የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓልን ምክንያት በማድረግ የሁለተኛው ምዕራፍ የኮሪደር ልማት ሌት ከቀን በመስራት ላይ የሚገኙ ብርቱ ሰራተኛችን፣ ኮንትራክተሮችን፣ አማካሪዎችን እና የመንግስት ተቋማት አስተባባሪዎችን በማመስገን በጋራ አክብረናል።
በኮሪደር ልማት የስራ እድል አግኝታችሁ በታማኝነት እና በትጋት ሌት ከቀን በመስራት ላይ ለምትገኙ ብርቱ ሰራተኞቻችን ሁሉ ዛሬ እናንተ የጣላችሁት መሠረት ከትውልድ ትውልድ የሚተላለፍ ደማቅ ታሪክ በመሆኑ ላመሰግናችሁ እወዳለሁ::
መልካም በዓል!
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ አስተዳደር ለፀጥታ አካላትና ለተለያዩ ተቋማት የበዓል መዋያ የሚሆን የበግና የበሬ ስጦታ አበረከተ፡፡
የክፍለ ከተማ አስተዳደሩ የገና በዓልን አስመልክቶ ለበዓልመ መዋያ የሚሆን የበሬና የበግ እንዲሁም ሌሎች ተጨማሪ ስጦታዎችን አበርክቷል፡፡
የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ሃላፊ ወ/ሮ ሃቢባ ሲራጅ፣ የክፍለ ከተማው ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ አይዳ አወል፣ የብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ሙስጠፋ ትኩና ሌሎች አመራሮች በተገኙበት ለተስፋ ብርሃን የምገባ ማዕከል የተለያዩ ስጦታዎች ተበርክተዋል፡፡
በተጨማሪም ለፌደራልና አዲስ አበባ የፀጥታ አካላት፣ ለእሳት አደጋ ሰራተኞች፣ ለአማኑኤል ሆስፒታል ሰራተኞች፣ ለጤና ጣቢያ ሰራተኞች፣ ጥቃት ለደረሰባቸው ሴቶች እንዲሁም ለምገባ ማዕከላት በአጠቃላይ 17 የእርድ በሬዎችና ሌሎች ስጦታዎች ተበርክተዋል፡፡
በእለቱ መልዕክት ያስተላለፉት የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ሃላፊ ወ/ሮ ሃቢባ ሲራጅ የቆየውን የኢትዮጵያዊነት የመደጋገፍ ባህል በማጠናከር በዓሉን ሁሉም ደስተኛ ሆኖ እንዲያሳልፍ የተደረገ ድጋፍ ነው ብለዋል፡፡
የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ አይዳ አወል የህዝባችንን ሰላምና ደህንነት ለማስጠበቅ ሌት ከቀን እየተጉ ላሉ የፀጥታ መዋቅር ሰራተኞች በዓሉን ደስተኛ ሆነው እንዲያሳልፉ ስጦታ መበርከቱን ተናግረዋል፡፡
ባለሃብቶችን በማስተባበር የቁም እንስሳ ከብቶቹን በማሰባሰብ የክፍለ ከተማው ህብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት የአንበሳውን ድርሻ መወጣቱን የጽ/ቤቱ ሃላፊ ወ/ሪ ሃብታሟ ቡልቻ ተናግረዋል፡፡
Addis Ketema Communication-አዲስ ከተማ
ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ!
Facebook:-
👇👇👇👇
https://www.facebook.com/CITYMANAGER1
Telgram:-
👇👇👇👇
https://t.me/aacitymanager
Twitter:-
👇👇👇👇
https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r
YouTube:-
👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s
Tiktok
👇👇👇👇
https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager?is_from_webapp=1&sender_device=pc
Website
👇👇👇👇
https://www.aacitymanger.gov.et
የልደታ ከተማ ክ/ከተማ አስተዳደር ለተለያዩ ተቋማት የበዓል መዋያ የሚሆን የበሬ ስጦታ አበረከተ፡፡
የክፍለ ከተማ አስተዳደሩ የገና በዓልን አስመልክቶ ለበዓል መ መዋያ የሚሆን ለተስፋ ብርሀን ምገባ ማዕከል ፣ለፀጥታ አካላት ፣ለእሳትና ድንገተኛ አደጋ ልደታ ቅርንጫፍ ፣ለጥቃት ማዕከል በሬና ሌሎች ተጨማሪ ስጦታዎችን አበርክቷል፡፡
የልደታ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ አበባ፣ የክፍለ ከተማ አመራሮች በተገኙበት የተለያዩ ስጦታዎች ተበርክተዋል፡፡
የህዝባችንን ሰላምና ደህንነት ለማስጠበቅ ሌት ከቀን እየተጉ ላሉ የፀጥታ መዋቅር ሰራተኞች በዓሉን ደስተኛ ሆነው እንዲያሳልፉ ስጦታ መበርከቱን ተናግረዋል፡፡
ባለሃብቶችን በማስተባበር የቁም እንስሳ ከብቶቹን ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅንጅት በማሰባሰብ የክፍለ ከተማው ህብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ውጤታማ ስራዎችን መስራት በመቻሉ ምስጋና ይገባዋል
Lideta sub-city communication office
ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ!
Facebook:-
👇👇👇👇
https://www.facebook.com/CITYMANAGER1
Telgram:-
👇👇👇👇
https://t.me/aacitymanager
Twitter:-
👇👇👇👇
https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r
YouTube:-
👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s
Tiktok
👇👇👇👇
https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager?is_from_webapp=1&sender_device=pc
Website
👇👇👇👇
https://www.aacitymanger.gov.et
ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዬች እንኳን ለጌታችንና ለመድኃኒታችን ለእየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ!
የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ ቤት መዲናችን ማራኪ፣ ጽዱ፣ ውብ እና ከአደጋ ስጋት የተጠበቀች እንድትሆን ጽ/ ቤታችን ዘርፈ ብዙ ስራዎችን እያከናወነ ይገኛል።
ከተማችን በአፍሪካ ደረጃ በጽዳት፣በውበት እና በስማርት ከተማነት ሞዴል እንድትሆን ጥረት እያደረግን እንገኛለን።
መዲናችን በአለምአቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪና ለነዋሪዎቿ ምቹ የሆነች ከተማ እንድትሆን አብረን እንድንሰራ በዚሁ አጋጣሚ ጥሪዬን ለማቅረብ እወዳለሁ።
በአሉ የሰላም፣ የደስታና የጤና እንዲሆንልን በራሴና በአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ጽ/ ቤት ስም እመኛለሁ!
መልካም የገና በአል!
ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ
በምክትል ከንቲባ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ
እንኳን ለጌታችን ለመድሃኒታችን ለእየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን!
እየሱስ ክርስቶስ በሰው ልጆች እና በአምላክ መካከል የነበረውን የጥል ግድግዳ አፍርሶ በምህረት፣ በይቅርታ እና በታላቅ ፍቅር ወደ ምድር መምጣቱ ሰላምን እና ፍቅርን ለምድር እንዲሁም አብሮነት እንዲጎለብት ምሳሌ ለመሆን ነው::
ስለዚህ በዓሉን ስናከብር የእየሱስ ክርስቶስን ምሳሌነትን በመከተል የሰላም እሴቶችን እየገነባን፣ ፍቅራችንን ይበልጥ እያጎለበትን እንዲሁም አብሮነታችንን እያጠናከርን ሊሆን ይገባል::
በዓሉን ስናከብር ያላቸው ለሌላቸው ማዕድ በማጋራት ፍቅር፣ መተሳሰብና አብሮነት በሚገለጽበት መልክ እንዲሆን ጥሪ እያቀረብኩ፣ የሰላም እና የደስታ በዓል እንዲሆንላችሁ እመኛለሁ።
መልካም በዓል!
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
የገና በዓልን ምክንያት በማድረግ ከማዕከል እስከ ወረዳ ከ400 ሺሕ በላይ ለሚሆኑ በዝቅተኛ ገቢ ለሚተዳደሩ እና የኑሮ ጫና ላለባቸው የከተማችን ነዋሪዎች ማዕድ አጋርተናል።
እንዲህ ያሉ የህብረተሰቡን የኑሮ ጫና የሚያቀሉ ስራዎችን እንድንሰራ፣ “መስጠት አያጎድልም” ብለው ከጎናችን በመቆም ጉልበት የሆኑንን የከተማችን ባለሀብቶች በነዋሪዎቻችን ስም ላመሰግናቸው እወዳለሁ።
መልካም በዓል!
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
ለኢትዮጵያ ኢኮኖሚ እድገት እና ለዴሞክራሲ መጎልበት በትጋት በመስራት፣ ለህዝባቸው እና ለሀገራቸዉ ይጠቅማል ብለው ያመኑትን በድፍረት በመታገል በሚታወቁት አቶ ቡልቻ ደመቅሳ ህልፈተ ህይወት የተሰማኝን ጥልቅ ሃዘን እየገለጽኩ፣ ለቤተሰቦቻቸው እና ለወዳጆቻቸው መጽናናትን እመቻለሁ።
ፈጣሪ ነብሳቸውን በአጸደ ገነት ያኑርልን።
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
አቶ ቡልቻ ደመቅሳ በማረፋቸው የተሰማኝን ኀዘን እገልጻለሁ።
በሚችሉት ሁሉ ሀገራቸውንና አፍሪካን ያገለገሉ፣ በአቋማቸው ጽኑ፣ ሕዝቦችን ለማቀራረብ የተጉ፣ እውነት ነው ብለው ያመኑትን የትምና መቼም የሚናገሩ ነበሩ።
እንዲህ ዓይነት ብርቱ ሽማግሌዎችን ማጣት ጉዳቱ ለሀገር ነው። ፈጣሪ ነፍሳቸውን ይቀበላት።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
ሰሞኑን በተለያዩ የሃገራችን ክፍሎች ስለተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ እና ንዝረት እንዲሁም አጠቃላይ ስርጭቱን በተመለከተ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጂኦፊዚክስ፣ ስፔስ ሳይንስና አስትሮኖሚ ተቋም እንዲሁም ከጂኦሎጂካል ሰርቬይ ከመጡ ምሁራን ጋር ተወያይተናል::
በውይይታችንም ምሁራኑ ጥናቶችን ያቀረቡልን ሲሆን ጥናቶቹ እንደሚያሳዩት በአዲስ አበባ በአሁኑ ሰዓት በአፋር እና አካባቢው እያጋጠመን ካለዉ የመሬት መንቀጥቀጥ የተነሳ የመሬት ንዝረት እያጋጠመ መሆኑን ገልፀው ንዝረቱ ሲያጋጥም መደናገጥ እና መረበሽ ሳያፈልግ በባለሙያዎች የሚሰጡት ምክር በመከታተል መረጋጋት እንደሚገባ አስረድተዉናል ።
ቢሆንም ከተማችን አዲስ አበባ ወደፊት ተጋላጭነት ያላት በመሆኑ የምንችለዉን ተገቢውን ጥንቃቄ ከወዲሁ ለማድረግ እንዲያስችል ለአንዳንድ ቅድመ ጥንቃቄ የሚረዱ ጥናቶችን ለማድረግ የባለሙያዎች ግብረ ሃይል በማደራጀት በጋራ ለመስራት ተስማምተናል::
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ
ከንቲባ አዳንች አቤቤ
የአዲስ አበባ ከፍተኛ አመራሮች “ከቃል እስከ ባህል” በሚል መሪ ቃል ለሶስት ቀናት ስናካሄድ የነበረውን የብልጽግና ፓርቲ ሁለተኛ መደበኛ ጉባኤ የቅድመ ፓርቲ ጉባኤ ውይይታችንን አጠናቅቀናል።
ፓርቲያችን ብልጽግና ከምስረታው ጀምሮ ሀሳብን በማፍለቅ፣ ለህዝብ ቃል በመግባት እና በመተግበር አፈጻጸሙም ባህል ሆኖ እንዲዘልቅ በማድረግ ረገድ በርካታ ስኬቶችን አስመዝግቧል።
በአንደኛው መደበኛ ጉባኤያችን ለህዝብ በገባነው ቃል መሠረት የፓርቲያችንን ህብረ ብሔራዊ አንድነት ያጠናከርን፣ አካታችና አብሮነትን እንዲሁም አሳታፊ የፖለቲካ ስርዓትን በመዘርጋት ውጤት ያመጣን ሲሆን በአዲስ አበባ ወቅታዊ እና ዉዝፍ ፈተናዎችን በመሻገር፣ የአመራር አንድነትን እና ቅንጅትን በማረጋገጥ ከተማችንን የስበት ማዕከል ያደረጉ ታላላቅ ፕሮጀክቶችንና ፍትሃዊ ተጠቃሚነትን ያረጋገጡ ሰው ተኮር ስራዎችን ማከናወን ችለናል።
ከዚህ በመነሳት በግንባር ቀደምትነት ህዝብን ተጠቃሚ የሚያደርጉ በርካታ የልማት ተግባራትን ማከናወን የቻልን ሲሆን አመራሩ በተለወጠ የስራ ባህል የተግባር እና የአስተሳሰብ አንድነቱን አጠናክሮ እንደ ሀገርም እንደከተማም ለተመዘገቡ ውጤቶች ከፍተኛውን ሚና ተጫውቷል።
በቀጣይም በሁሉም መስኮች የተገኙ ውጤቶችን በማላቅ እንደ ድክመት የሚነሱ የአገልግሎት አሰጣጥ እና የአሰራር ችግሮችን ደግሞ በዘላቂነት በመቅረፍ የሀሳብ ልእልናን በብቃት እየተገበርን በስራ አዳዲስ ባህል እየገነባን ለኢትዮዽያን ብልፆግና ተግተን እንሰራለን።
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ!
Facebook:-
👇👇👇👇
https://www.facebook.com/CITYMANAGER1
Telgram:-
👇👇👇👇
https://t.me/aacitymanager
Twitter:-
👇👇👇👇
https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r
YouTube:-
👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s
Tiktok
👇👇👇👇
https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager...
Website
👇👇👇👇
https://www.aacitymanger.gov.et
