en
Feedback
Addis Ababa City Manager Office

Addis Ababa City Manager Office

Open in Telegram
1 474
Subscribers
No data24 hours
-37 days
-2130 days
Posts Archive
21 ፕሮጀክቶች ተጠናቀው ለአገልግሎት ክፍት ሆኑ ዛሬ በመዲናችን 31.5 ኪ.ሜትር ርዝመት ያላቸዉ 13 የመንገድ ፕሮጀክቶችን እና 8 ድልድዮችን በአጠቃላይ 21 ፕሮጄክቶችን መርቀን ለአገልግሎት ክፍት አድርገናል፡፡ ዛሬ የተመረቁት እነዚህ የመንገድ መሰረተ ልማቶች ፦ 👉ከአጉስታ- ወይራ መጋጠሚያ፣ቱሉዲምቱ ኮንዶሚኒያም መቃረቢያ 👉ከቃሊቲ ቀለበት መንገድ ዐደባባይ - በአቃቂ ድልድይ-ቱሉ ዲምቱ ዐደባባይ 👉ከቃሊቲ ቀለበት መንገድ አደባባይ ቡልቡላ-ቂሊንጦ 2ኛ ቀለበት መንገድ አደባባይ 👉የለቡ አደባባይ ማሻሻያ ፕሮጀክት 👉ከአፍሪካ ህንፃ- ጀሞ መስታዎት ፋብሪካ 👉ከቂርቆስ ማርገጃ - ቡልጋሪያ 👉ከቤላ -ፈረንሣይ ፓርክ - ፈረንሣይ አቦ ቤተክርስቲያን 👉ከናሰዉ ሪል ስቴት አርሴማ ቀለበት መንገድ እና ዮናስ ሆቴል ኬብሮን ፋርማሲ አስፋልት መንገዶች ናቸው።

21 ፕሮጀክቶች ተጠናቀው ለአገልግሎት ክፍት ሆኑ ዛሬ በመዲናችን 31.5 ኪ.ሜትር ርዝመት ያላቸዉ 13 የመንገድ ፕሮጀክቶችን እና 8 ድልድዮችን በአጠቃላይ 21 ፕሮጄክቶችን መርቀን ለአገልግሎት ክፍት አድርገናል፡፡ ዛሬ የተመረቁት እነዚህ የመንገድ መሰረተ ልማቶች ፦ 👉ከአጉስታ- ወይራ መጋጠሚያ፣ቱሉዲምቱ ኮንዶሚኒያም መቃረቢያ 👉ከቃሊቲ ቀለበት መንገድ ዐደባባይ - በአቃቂ ድልድይ-ቱሉ ዲምቱ ዐደባባይ 👉ከቃሊቲ ቀለበት መንገድ አደባባይ ቡልቡላ-ቂሊንጦ 2ኛ ቀለበት መንገድ አደባባይ 👉የለቡ አደባባይ ማሻሻያ ፕሮጀክት 👉ከአፍሪካ ህንፃ- ጀሞ መስታዎት ፋብሪካ 👉ከቂርቆስ ማርገጃ - ቡልጋሪያ 👉ከቤላ -ፈረንሣይ ፓርክ - ፈረንሣይ አቦ ቤተክርስቲያን 👉ከናሰዉ ሪል ስቴት አርሴማ ቀለበት መንገድ እና ዮናስ ሆቴል ኬብሮን ፋርማሲ አስፋልት መንገዶች ናቸው።

የረዳን ፈጣሪ ይመስገን !! እንኳን ደስ አላችሁ!! ዛሬ በመዲናችን 31.5 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያላቸዉ 13 የመንገድ ፕሮጀክቶችን እና 8 ድልድዮችን አጠቃላይ 21 ፕሮጄክቶችን መርቀን ለአገልግሎት ክፍት አድርገናል፡፡ ከተማችንን ለማዘመን ከኮሪደር ልማት ስራዎቻችን ባሻገር የመንገድ መሰረተ ልማት ተደራሽነትን ለማረጋገጥ ልዩ ትኩረት ሰጥተን እየሰራ እንገኛለን፡፡ ዛሬ የተመረቁት እነዚህ የመንገድ መሰረተ ልማቶች ፦ ከአጉስታ- ወይራ መጋጠሚያ፣ቱሉዲምቱ ኮንዶሚኒያም መቃረቢያ፣ ከቃሊቲ ቀለበት መንገድ ዐደባባይ - በአቃቂ ድልድይ-ቱሉ ዲምቱ ዐደባባይ፣ ከቃሊቲ ቀለበት መንገድ አደባባይ ቡልቡላ-ቂሊንጦ 2ኛ ቀለበት መንገድ አደባባይ፣ የለቡ አደባባይ ማሻሻያ ፕሮጀክት፣ ከአፍሪካ ህንፃ- ጀሞ መስታዎት ፋብሪካ፣ ከቂርቆስ ማርገጃ - ቡልጋሪያ፣ ከቤላ -ፈረንሣይ ፓርክ - ፈረንሣይ አቦ ቤተክርስቲያን፣ ከናሰዉ ሪል ስቴት አርሴማ ቀለበት መንገድ እና ዮናስ ሆቴል ኬብሮን ፋርማሲ አስፋልት መንገዶች ናቸው፡፡ ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቧቿን ይባርክ ከንቲባ አዳነች አቤቤ

"የአረንጓዴ አሻራ ማኖር ስራችን የመንግስት ብቻ ሳይሆን የህዝባችንም አጀንዳ ነው።" - በምክትል ከንቲባ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች https://linktr.ee/aacitymanager

መዲናችን አዲሰ አበባ ከተማ እያስመዘገበች ባለችው ፈጣን የከተሜነት እድገት የሚከናወኑ የግንባታ ስራዎች ላይ የዜጎችን ደህንነት የማስጠበቅ ጉዳይ በከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ ትኩረት እንደተሰጠው በምክትል ከንቲባ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ አስገነዘቡ። ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ ይህን ያስገነዘቡት በዛሬው እለት የአዲስ አበባ ከተማ የግንባታ ፈቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን 500 ለሚሆኑ ስራ ተቋራጮች፣ አማካሪዎች፣ ለሪል ስቴት አልሚዎች እና የምህንድስና ሙያ የሙያ ማህበራት ባዘጋጀው "የግንባታ ስራ ቦታ ደህንነት (safety)" የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ላይ ባደረጉት ንግግር ነው። ኢንጅነር ወንድሙ በዚሁ መድረክ ላይ ዘመናዊ የከተማ ግንባታን ለማሳካት በምናከናውናቸ ትላልቅ የህንፃና የመሰረተ ልማት ግንባታ ስራዎቻችን ጎን ለጎን ቅድሚያ የምንሰጠው የዜጎቻችንን ደህንነት የማስጠበቅ ጉዳይ ነው ሲሉ ገልፀው ይህ እንደመሆኑ ከዚህ በኋላ የከተማችን ነዋሪዎች ደህንነት (Public safety) አደጋ ላይ እንዳይወድቅ ከተለያዩ ተቋማት የተውጣጣ ግብረሐይል ተቋቁሞ በከፍተኛ ትኩረት ስራውን እንደሚያከናውን ተናግረዋል። ግብረሐይሉ በከተማው ሥራ አስኪያጅ አስተባባሪነት ከግንባታ ፈቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን፣ ከአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ ኮሚሽን፣ ከደንብ ማስከበር ባለስልጣን፣ ከእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የተውጣጣ ሆኖ እንደሚቋቋም ገልፀው የግብረሐይሉ ዋነኛ ተግባርም በከተማችን የግንባታ ስራ የሚያካሂዱ አልሚዎች የደህንነት ግምገማ (Safety Assesment) እንደሚያካሂድና በዚህ ላይ ተመሥርቶ በሚያዘጋጀው ሪፖርትም ላይ በመመስረትም ተገቢውን የስራ ቦታ የደህንነት መስፈርቶች በማያሟሉ አልሚዎች ላይ በቅድሚያ የግንዛቤ መስጠት፣ የእርምት እርምጃ የመውሰድ፣ በተደጋጋሚ ህግን በማያከብሩ አልሚዎችና ስራ ተቋራጮች ላይ የህግ የማስከበር ስራዎች እንደሚከናወኑ ገልፀዋል። ኮንትራክተሮች እና አልሚዎች ሀገራዊና አለምአቀፍ የደህንነት መስፈርቶች ማሟላት እና ትላልቅ ግንባታዎች በሚከናወኑባቸው ቦታዎች ላይ የስራ ላይ ደህንነት ጥበቃ ባለሙያዎች ( Safety Engineer) ሊኖራቸው እንደሚገባም አመልክተዋል። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የግንባታና ፈቃድ ቁጥጥር ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ኢንጅነር ህይወት ሳሙኤል በበኩላቸው የግንባታ ስራን የሚያካሂዱ አልሚዎች የደህንነት መስፈርት የማሟላት ጉዳይ ከዚህ በኋላ ለድርድር የማይቀርብ አስገዳጅ ሁኔታ መሆኑን አልሚዎች ተገንዝበው ትኩረት ሰጥተው ስራቸውን ሊያከናውኑ እንደሚገባ አሳስበዋል። ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች https://linktr.ee/aacitymanager

በመዲናዋ ተገንብተዉ የተጠናቀቁ ከ15,960 በላይ ፕሮጀክቶች ተመርቀዉ ከነገዉ እለት ጀምሮ ለአገልግሎት ክፍት እንደሚሆኑ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ እናትዓለም መለሰ ገለፁ፡፡ ከተማ አስተዳደሩ በ2017 በጀት ዓመት ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታቸው የጎላ ዘርፈ-ብዙ የልማት ስራዎችን በማቀድና ተግባራዊ በማድረግ ከ15 ,960 በላይ የተለያዩ ትልልቅ ፕሮጄክቶች ከነገ እሁድ ሰኔ 29/2017 ዓ.ም ጀምሮ ተመርቀዉ ለአገልግሎት ክፍት እንደሚደረጉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ እናትዓለም መለሰ ተናግረዋል፡፡ ለአገልግሎት ክፍት ከሚሆኑት እና ከሚመረቁትፕሮጀክቶች መካከል የመንገድ፣ የውሃ፣ የቤቶች ልማት ፣ የመስሪያ ቦታዎች፣ የወጣቶች ስፖርት ማዘወተሪያ ሜዳዎች፣ በአረንጓረዴ ልማት የተሰሩ እና ሌሎች ለህብረተሰቡ ፋዳቸው ጉልህ የሆኑ ፕሮጀክቶችን ያካተቱ ናቸው ተብሏል፡፡ ፕሮጀክቶቹ በ91 ቢሊዮን ብር ወጪ በመንግስት እና በ4 ቢሊየን ብር ወጪ በህብረተሰቡ ተሳትፎ የተገነቡ ሲሆን ፤ የተጠቀሰው በጀት ብቻ ሳይሆን ሌሎች በሂደት ላይ ያሉ ፕሮጀክቶችም በፈጣን ክትትል ሥራው ውስጥ እንዳሉ ወ/ሮ እናት ዓለም መለሰ በሰጡት ማብራሪያ ገልፀዋል፡፡ በተጨማሪም የከተማ አስተዳደሩ በበጀት ዓመቱ አጠቃላይ ከተያዘለት በጀት ውስጥ 71 በመቶ የሚሆነዉን ለካፒታል ፕሮጀክት ግንባታ እና ለድህነት ቅነሳ ፕሮግራም እንዲውል በቁርጠኝነት እየሰራ መሆኑን፣ ገልጸው፣ ለትራንስፖርት ለዳቦ ፍብሪካ ድጎማ፣ ለባሶች ግዥ፣ ለተማሪዎች ምገባ፣ ለጤና መድህን ፕሮግራሞች ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ እንደሚገኝም የቢሮው ኃላፊ አስረድተዋል፡፡ የከተማ አስተዳደሩ ለወጣቶች ስራ እድል በሰጠዉ ትኩረት ከ366ሺ በላይ ለሚሆኑ ወጣቶች የስራ ዕድል እንደተፈጠረላቸውም ተናግረዋል፡፡ ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች https://linktr.ee/aacitymanager

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ 4ኛ ዓመት 13ኛ መደበኛ ስብሰባዉን በሶስት ወሳኝ ከተማ አቀፍ አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ የሚከተሉትን ውሳኔዎች አሳልፏል፡፡ በዚህም መሰረት ፤ 1ኛ:- የከተማዋን ፈጣን ለዉጥ ታሳቢ በማድረግ፣ ወጪን ለመቀነስ ፣ አገልግሎት አሰጣጥን ለማሻሻል እና ወጤታማነትን ለማሳደግ እንዲረዳ ተጠንቶ የቀረበዉ የአስፈፃሚ አካላትን ስልጣንና ተግባር የማሻሽያ አዋጅ ላይ ተወያይቶ ለምክር ቤት እንዲቀርብ ዉሳኔ አሳልፏል፡፡ በዚህም መሠረት 1..ቱሪዝም ዘርፍ ራሱን ችሎ በኮሚሽን እንዲቋቋም፤ 2..የዲዛይን እና ግንባታ ሥራዎች ቢሮ እና የትላልቅ ፕሮጀክቶች ግንባታ ፅ/ቤት ጋር እንዲወUድ፤ 3.. ማህበራዊ ትረስት ፈንድ ፅ/ቤት ከህብረተሰብ ተሳትፎ እና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን ጋር እንዲወUድ 4..የከተማ ውበትና አረንጋዴ ልማት ቢሮ የህዝብ መፀዳጃ ቤቶችን የማልማት ተግባር ለውሃና ፍሳሽ ባለሥልጣን ማስተላለፍን ያከተተ ማሻሻያዎች ተደርገዉ ለምክቤት እንዲቀርብ ወስኖል። 2ኛ:-ለአስተዳደራዊ አመቺነት ፣ ለአገልግሎት ተደራሽነት እና ወጪን ለመቀነስ እንዲያግዝ በፕላን ልማት ቢሮ ተጠንቶ በቀረበዉ የሶስት የወረዳዎች አስተዳደር ወሰን ማሻሻል ጥናት ላይ ተወያይቶ አገልግሎት ተደራሽነትን እና ወደፊት በከተማዋ የሚመጣውን ልማት ታሳቢ ያደረገ በመሆኑ የቀረበውን ማሻሻያ ሀሳብ በሙሉ ድምፅ አፅድቋል፡፡ 3ኛ:-በጤና ቢሮ በኩል ተጠንቶ በቀረበዉ የማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን አባላት ክፍያ መጠን ላይ ተወያይቶ ዉሳኔ አሳልፏል፡፡ 4ኛ. አገራዊ ፋይዳ ያላቸውን ፕሮጀክቶች ላይ የቀረበ የመሬት ልማት ጥያቄ ላይ በመወያየት አፅድቋል ።

Repost from N/a
2017 ሰኔ ወር ዜና መጽሄት.pdf1.85 MB

ሰላምና ጸጥታን በተመለከተ ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው የሰላምና የጸጥታ ችግር ዋነኛው መንስኤ የተሳሳተ የፖለቲካ አመለካከት ነው። አንደኛው ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው የስንፍና ፖለቲካ የወለደው ችግር ነው። የስንፍና ፖለቲካ በሀገራችን ተንሰራፍቷል። በዚያ ምክንያት ግጭት ጠብ፣ ተቃርኖን ይወልዳል። ስራ አያውቁም ስራ አይወዱም ስራ አይሰሩም። አንድ ሰው ስራ ካልሰራ ደግሞ አልተማረም ማለት ነው። በስራ ተመንዝሮ የሚገኝ እውቀትና ልምድ ነው ሰውን አዋቂ የሚያሰኘው። በእኛ ሀገር አርሶ አደር፣ አርብቶ አደር ላብ አደር አለ፤ አሁን ደግሞ አውርቶ አደር ተጨምሯል። አውርቶ አደር ካላጋጩ ገቢ አያገኙም። እነዚህ ሰነፍ ፖለቲከኞች ስራ ሳይሰሩ፣ አገልግሎት ሳይሰጡ መብላት የሚፈልጉ ናቸው። ሁለተኛው መንስኤ የኃይል ፖለቲካ ነው። ክላሽ ካነገትኩ ፍላጎቴ ይሳካል ብለው የሚያምኑ በህዝብ የተመረጠን መንግስት በኃይልና በወሬ እናፈርሳለን ብለው የሚያምኑ፣ በመግደል መሸነፍ እንጂ ማሸነፍ እንደሌለ የማያምኑ ናቸው። በአንዳንድ አካባቢዎች ትምህርት አትማሩ፣ ማዳበሪያ አትውሰዱ ብለው ሰዎችን የሚገድሉ ሰዎች ካሉ ይህ እኩይ አላማ ነው። ግድያ ሽንፈት ብቻ ነው የሚያመጣው ብሎ ማመን ያስፈልጋል። መቆም አለበት። ሶስተኛው ገፊ ምክንያት ድህነት ነው፤ ድሀነትን ካልቀነስን ስራ ካልፈጠርን ችግሩን መቅረፍ ያስቸግራል። ኋላቀርነት እና ዘረኝነት አባባሽ ችግሮች ናቸው። ዘረኝነት ሌላው ስር የሰደደ ችግር ነው። ዘረኝነት ልኩን ሲስት ለሰው ልጅ ጠንቅ ይሆናል። እነዚህ እሳቤዎች የውጭ ጣልቃ ገብነት ታክሎበት የባንዳነት ስሪት ደግሞ በመስፋቱ ችግሩን አባብሶታል። ኢትዮጵያ ስትጋጭ ትርፍ እናገኛለን ብለው የሚያስቡ እሳት ጫሪ ጥልፊቶች አሉ። ኢትዮጵያውያንም እሳት ጫሪዎችን ማወቅና ማረም ያስፈልገናል። ያን ጊዜ ችግሩ ይፈታል። #የጠሚሩምላሾች #PMOEthiopia

በአማራ ክልል የማህበረሰቡን የሰላም ሚና በተመለከተ ማህበረሰቡ ሳይሸሽግ የታጠቁ አካላትን አትግደሉ፣ አትግደሉልኝ፣ እናንተም አትሙቱልኝ ማለት አለበት። ልጆቼን ፈተና እንዳይፈተኑ እንዳይማሩ አትከልክሉ፣ እንዳንሰራ አታድርጉ፣ ማዳበሪያ እንዳይመጣ አታድርጉ ማለት አለበት። ይህንን ሰሞኑን የአማራ ህዝብ በቅርቡ አሳይቷል፤ ሰላም ልማት እፈልጋለሁ ብሏል፤ በቃኝ ብሏል። ይህ ለሁሉም ግልፅ መልዕክት ነው። ለዚህ የህዝብ ጥያቄ የከበረ ምላሽ መስጠት ያስፈልጋል። ማንኛውም ሰው ወደ ስልጣን ሲመጣ ከዚህ ቀደም ምን ሰርተህ ታውቃለህ፣ ግብር ከፍለሃል ወይ፣ ማንን አገለገልክ፣ ታማኝ ነህ ወይ ብሎ መጠየቅ ያስፈልጋል። ህዝቡ ይህን እየጠየቀ ማጥራት አለበት። ማህበረሰቡ የሰላምና የብልሹ አሰራር ችግርን በዘለቂነት ለመፍታት ሚናውን መወጣት አለበት። ሰላም ሁልጊዜ የሚገነባ ጉዳይ ነው። ኢትዮጵያ ውስጥ ከዚህ ቀደም የተከሰቱ ግጭቶች ተፈትተው አንጻራዊ ሰላም ሰፍኗል። አንጻራዊ ሰላም ባይኖር ግብርናው፣ ማዕድኑ፣ ቱሪዝሙ አያድግም ነበር። አሁንም ቀሪ ችግሮችን በመፍታትና በጋራ በመስራት የሰላምን ዘላቂነት ማረጋገጥ ይገባል። #የጠሚሩምላሾች #PMOEthiopia

ትግራይ ክልልን በተመለከተ የፕሪቶሪያ ስምምንት ለትግራይ ህዝብ እፎይታ አምጥቷል። የትግራይ ህዝብ ልጆቹን በየቀኑ ከማጣት ታድጓል። ለኢትዮጵያ ህዝብና ለሌሎች ሀገራት ደግሞ መንግስት ሰላም ይሻላል ብሎ ለተዋጉት ኃይሎች እድል ይሰጣል የሚል አዲስ ባህል ፈጥሯል። በክልሉ አገልግሎትን በሚመለከት ቴሌኮም፣ ባንኮች፣ አየር መንገድና ሌሎችም አገልግሎቶች ሙሉ ለሙሉ ጀምረዋል። የተፈናቀሉ ሰዎችን በመሚመለከት ራያ መቶ በመቶ ጸለምትም ተመልሰዋል። ቀሪ ወልቃይት ያልተመለሱ አሉ፤ መንግስት ያልምተመለሱ ተፋናቃዮች ወደ ቀያቸው እንዲመለሱ የጸና አቋም ነው ያለው። የቀድሞ ታጣቂዎችን መልሶ ማቋቋምና ወደ ማህበረሰቡ መቀላቀልም በፍጥነት መፈጸም አለበት። ይህ ጥቅሙ ለክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ጭምር ነው። የፌደራል መንግስት ትግራይ ክልል ውስጥ ያሉ ጉዳዮችን በሰላም የመፍታት ፅኑ አቋሙን በተደጋጋሚ አሳይቷል። የትግራይ ህዝብ ጦርነት ፈጽሞ አይፈልግም። ሆኖም የዓለምን ሁኔታና የዘመኑን ውጊያ ባለመገንዘብ፣ መንግስት በተለለያዩ ችግሮች ተወሯል፤ የሚያገዙን ሀገራት አሉ በሚል የተሳሳተ ስሌት ጊዜው አሁን ነው በሚል ውጊያ ለመክፈት የሚፈልጉ አሉ። ይህ የተሳሳተ አካሄድ ነው ትግራይ የሚያስፈልገው ሰላም፣ ችገሮችን በውይይት በንግግር መፍታት ነው። የሃይማኖት አባቶችና የሀገር ሽማግሌዎች ትግራይ ክልል ያለው ሁኔታ ወደ ጦርነት እንዳይገባ አሁኑኑ የሰላም ሚናችሁን ተወጡ። መንግስት አንድም ጥይት የመተኮስ ፍላጎት የለውም። ማልመት ነው ፍላጎታችን። ሁሉም ህዝብ ማወቅ ያለበት ጦርነት አያስፈልግም። ትግራይ ክልልን ጨምሮ ለሀገራዊ ምክክሩ ስኬት ሁሉም የበኩሉን ሚና ማበርከት አስፈላጊ ነው። #የጠሚሩምላሾች #PMOEthiopia