1 474
Subscribers
No data24 hours
-37 days
-2130 days
Posts Archive
"እናገልግለዎ" በሚል የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት ከኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ኤፍ ኤም 97 .1 ጋር በመተባበር በየሳምንቱ በሚተላለፈው ፕሮግራሙ በትናንትናው እለት መጋቢት 17 ቀን 2016 አ.ም የተላለፈውን የፕሮግራሙ ሁለተኛ ክፍል ይከታተሉ::
በከተማዋ መንገዶች ላይ የተሰሩ የመንገድ ዳር መብራቶች ወንጀልን ለመከላከልና ለሰላማዊ የስራ እንቅስቃሴ እገዛ እያደረጉ መሆኑን ነዋሪዎች ተናገሩ::
በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 በተለምዶ ጨርቆስ አደባባይ በሚባል የቦሌ አራብሳ አካባቢ ነዋሪ የሆኑትና በጉሊት የንግድ ስራ የተሰማሩት ወይዘሮ ዘይቱና ከዚህ ቀደም ስራ የሚሰሩት ቀን ላይ ብቻ እንደነበርና ይህም በገቢያቸው ላይ ተፅዕኖ እንዳሳደረ ይናገራሉ ፡፡
እንደ ወይዘሮ ዘይቱና ማብራሪያ፣ የጉሊት ስራ በባህሪው እስከ ምሽት መስራትን ይፈልጋል። አትክልት እና ፍራፍሬ በየቀኑ ሽጦ መጨረስ ያስፈልጋል፡፡
ይህም በቦታው ላይ ማምሸትን ይጠይቃል፡፡ የመንገድ ዳር መብራት ባልነበረበት ጊዜ የቀማኛ ሲሳይ የመሆን ችግር ይፈጠራል፡፡
ወ/ሮ ዘይቱናም ሆነ በጉሊት የሚሰሩ ሌሎች ነጋዴዎች የእጅ ስልካቸውን፣ ንብረትና ገንዘብ ተዘርፈው እንደሚያውቁ ጠቁመው፣ የመንገድ ዳር መብራት ከተዘረጋ ወዲህ ስራቸውን ያለስጋት አምሽተው መስራት መቻላቸውን ተናግረዋል፡፡
በዚሁ ጉሊት የተለያዩ የአትክልትና ፍራፍሬ ምርቶችን በመሸጥ ኑሮአቸውን የሚመሩት ወይዘሮ ሰሚራ ሙላቱ የመንገድ ዳር መብራት ባልነበረበት ጊዜ እንደልብ አምሽተው መስራት ተስኗቸው እንደ ነበረና በዚህም በአካባቢው የተቀዛቀዘ የስራ እንቅስቃሴ እንደ ነበር አስታውሰዋል፡፡
አሁን ግን አምሽተው ለሚገቡ የአካባቢው ነዋሪዎች አትክልትና ፍራፍሬዎችን በመሸጥ የተሻለ ገቢ እያገኙ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሰላምና ጸጥታ ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ጌታሁን አበራ፣ የመንገድ ዳር መብራቶችን በመዘርጋት ህብረተሰቡን ከወንጀል እና ከአደጋ በመጠበቅ ያለ ስጋት እንዲንቀሳቀስ እየተደረገ መሆኑን ገልጸዋል።
እንደ አቶ ጌታሁን ገለጻ፣ ጨለማን ተገን በማድረግ ህብረተሰቡ ላይ የስርቆትና ሌሎች የወንጀል ድርጊቶች እንዳይፈጸሙ የመንገድ ዳር መብራት የሌላቸው መንገዶች መብራት እንዲያገኙ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መንገዶች ባለስልጣን ጋር ሲሰራ በመቆየቱ በርካታ የከተማዋ ክፍሎች ከዚህ ችግር መውጣታቸውን ተናግረዋል፡፡
በከተማዋ 833 ብሎኮችና 4 ሺህ 952 መንደሮች እንዳሉ ጠቁመው፣ በእነዚህ መንደሮች ላይ ከነዋሪዎች የተውጣጡ የሰላም ሰራዊቶች ከማህበረሰብ አቀፍ የፖሊስ አካላት ጋር ተቀናጅተው እየሰሩ መሆኑንም አስታውቀዋል፡፡
የመንገድ ዳር መብራት በምሽት የሚኖረውን የትራፊክ እንቅስቃሴ ሰላማዊና ደህንነቱ የተጠበቀ እንዲሆን ከማስቻሉም ባሻገር የከተማዋን ገፅታ ከመለወጥ አኳያም ያለው ሚና ጉልህ ነው፡፡
የአዲስ አበባ መንገዶች ባለስልጣን ባለፉት ስድስት ወራት 4 ሺህ 810 የመንገድ ዳር የመብራት ምሶሶዎችን ለመጠገን አቅዶ 7 ሺህ 97 ማከናወን መቻሉን ያገኘነው መረጃ ያመላNetwork
የአዲስ አበባ ከተማ ሰራ አሰኪያጅ ፅ/ ቤት ከአዲስ አበባ ከተማ ቲያትር እና ባህል ማእከል ጋር በጋራ ለመሰራት የሚያስችል የመግባቢያ ሰነድ ስምምነት ተፈራረመ::
የከተማ ሰራ አስኪያጅ ፅ/ ቤት በማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት ዙሪያ መረጃዎችን ለህብረተሰቡ ተደራሽ ለማድረግና ይህንኑ በላቀ ደረጃ ለማሳካት እንዲሁም ከነዋሪው ጋር ያለውን መስተጋብር ለማጠናከር የኪነ ጥበብ ዘርፉን መጠቀም አስፈላጊ በመሆኑ ከማእከሉ ጋር በዛሬው እለት የመግባቢያ ስምምነት ሰነድ ፊርማ ስነ ስርአት ማካሄዱ በዚሁ ወቅት ተጠቁሟል::
የመግባቢያ ሰነድ ስምምነቱን በምክትል ከንቲባ ማአረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ሰራ አስኪያጅ ወ/ሮ ሂክማ ከይረዲን እና በማእከሉ በኩል አቶ ካሳሁን ገበየሁ ፈርመዋል::
በዚሁ ወቅት ክብርት ወ/ ሮ ሂክማ ከይረዲን የከተማ ማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎቶች በተለይም የከተማችን ፅዳትና ውበት:የአደጋ ሰጋት መከላከልና የቅድመ ጥንቃቄ ስራዎችና የኤሌክትሪክ መሠረተ ልማት ጥበቃ ስራዎች ሰፊ የሆነ የህብረተሰብ ተሳትፎ የሚጠይቁ እንደመሆናቸው ለከተማው ህዝብ መረጃ የሚሰጥበት የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎችም የኪነ- ጥበብ ዘርፉን በመጠቀም ሳቢና አስተማሪ በሆነ መንገድ በስፋት መድረስ እንዳለበት አስምረውበታል::
አክለውም በሲቪል ምዝገባና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲም ረገድ ህብረተሰቡ አገልግሎት ፈልጎ ወደ የፅ/ቤቶች ሲሄድ የሚጠበቅበትን ቅድመ ሁኔታዎች በማሟላት በተቀመጠው ስታንደርድ መሠረት አገልግሎት የማግኘት መብት እንዳለው በመገንዘብ ለዚሁና መሰል ስራዎች ተግባራዊነት የኪነጥበብ ዘርፉ አጋዥ መሆኑን ገልፀው በተገባው ስምምነት መሰረትም ስራዎችን በጊዜ የለኝም ሰሜት መተግበር እንደሚገባ አሳሰበዋል::
ፈጣን እና ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት እነዚህን አድራሻዎች ይከተሉ፤ ቤተሰብ ይሁኑ!
Facebook:-
👇👇👇👇
https://www.facebook.com/CITYMANAGER1
Telgram:-
👇👇👇👇
https://t.me/aacitymanager
Twitter:-
👇👇👇👇
https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r
YouTube:-
👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s
Tiktok
👇👇👇👇
https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager...
Website
👇👇👇👇
https://www.aacitymanger.gov.et
ነዋሪዎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ አዲስ የኤሌክትሪክ መስመር ዝርጋታ እየተከናወነ ነው
በአዲስ አበባ ከተማ ቦሌ ቡልቡላና አካባቢው ያሉ ደንበኞችን የኤሌክትሪክ ኃይል ተጠቃሚ የሚያደርግ የ14 ኪሎ ሜትር የመካከለኛ መስመር ዝርጋታ ስራ እየተከናወነ ነው፡፡
በዚህ ፕሮጀክት ከኮየ-አቦ የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ ወጪ በማድረግ እስከ ቦሌ ቡልቡላ የሚደርስ የኃይል መስመር ዝርጋታ እየተከናወነ ይገኛል፡፡
ከአቅም በላይ በሆነ የኃይል ጭነት ምክንያት ቀድም ሲል በአካባቢው ተደጋጋሚ የኃይል መቆራረጥ የነበረ ሲሆን፤ የተጀመረው ሥራ ሲጠናቀቅ ግን በቦሌ ቡልቡላና አካባቢው የነበረውን ችግር በከፍተኛ ደረጃ መቅረፍ የሚያስችል ይሆናል፡፡
በተጨማሪ ዝርጋታው ከኮየ እስከ ቡልቡላ አጠቃላይ መስመሩ የሚያልፍባቸው አካባቢዎችን በሙሉ የኤሌክትሪክ ኃይል ተጠቃሚ ማድረግ የሚያስችል ዓቅም ያለውም ነው፡፡
እንዲሁም አሁን ላይ ያሉ ደንበኞችን በቂ የኃይል እንዲያገኙ ከማስቻሉም በላይ፤ በአካባቢው በርካታ የቤቶች ግንባታ የሚከናወንበት በመሆኑ በቀጣይ የሚኖረውን የኃይል ፍላጎት ለማስተናገድም ያስችላል፡፡
ይህ ሥራ ጥር 1 ቀን 2016 ዓ.ም ተጀምሮ አሁን ላይ 14 ኪሎ ሜትር የሚሸፍን 320 የኮንክሪት ምሰሶ ተከላ ስራ ተከናውኖበታል፡፡
በተጨማሪም ከኃይል ማከፋፈያ ጣቢያው 800 ሜትር ርቀት ያለው እንዲሁም ቡልቡላ ወንዝ ድልድይ ስር የሚያልፍ የ300 ሜትር የመሬት ውስጥ መስመር ዝርጋታ ስራ ለማከናወን የቁፋሮ ስራ እየተሰራ ይገኛል፡፡
አጠቃላይ የግንባታ ወጪው 172 ሚሊየን ብር የሚፈጅው ፕሮጀክቱ፤ ግንባታው ለሀገር በቀል ኩባንያዎች የሥራ ዕድል የፈጠረ መሆኑም ተመላክቷል፡፡
አሁን ላይ አጠቃላይ የሲቪል ስራዉ አፈፃፀም 80 ፐርሰንት የደረሰው ይህ ፕሮጀክት፤ ቀሪ ስራዎችን በአጭር ጊዜ ውስጥ አጠናቆ መስመሩን ወደ ስራ ለማስገባት በልዩ ትኩረት እየተሰራ ይገኛል፡፡
#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት
ፈጣን እና ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት እነዚህን አድራሻዎች ይከተሉ፤ ቤተሰብ ይሁኑ!
Facebook:-
👇👇👇👇
https://www.facebook.com/CITYMANAGER1
Telgram:-
👇👇👇👇
https://t.me/aacitymanager
Twitter:-
👇👇👇👇
https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r
YouTube:-
👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s
Tiktok
👇👇👇👇
https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager...
Website
👇👇👇👇
https://www.aacitymanger.gov.et
የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት ከአዲስ ሚዲያ ኔትወርክ ኤፍ ኤም 96 .3 ሬድዮ ጋር በየሳምንቱ ዘወትር ሰኞ ማለዳ ከ2 ሰዓት 30 እስከ 3 ሰዓት የሚተላለፈውን ፕሮግራም ይከታተሉ: https://www.facebook.com/CITYMANAGER1/videos/1543151809861561
የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ፅ/ ቤት ወቅቱ የበልግ ወራት እንደመሆኑ ከሚጥለው ዝናብ ጋር ተያይዞ አደጋ እንዳይከሰት የሚመለከታቸው አካላትና የከተማዋ ነዋሪዎች የቅድመ ጥንቃቄ ስራዎችን ማጠናከር እንደሚገባ አሳስቧል፡፡
ፅ/ቤቱ በተለያዩ ምክንያቶች ተቆፍረው ክፍት በተተው ጉድጓዶች፣ በውሃ መውረጃ ቱቦዎች፣ ፍሳሽ ማስወገጃ መስመሮችና ቦዮች ደረቅ ቆሻሻዎችን መጣል ለጎርፍ አደጋ መከሰትና መባባስ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ስለሚያደርግ ህብረተሰቡ ከዚህ ድርጊት በመቆጠብና በማፅዳት በዚህ ምክንያት ሊደርሱ የሚችሉ አደጋዎችን መከላከል እንደሚገባ ያስገነዝባል ፡፡
የኤሌክትሪክ መሰመሮችን ተጠግተው የሚገኙ ዛፎች፣ የረገቡ የኤሌክትሪክ መስመሮችና የዘመሙ ምሶሶዎች ዝናብ በሚጥልበት ወቅት በሰውና በንብረት ላይ ጉዳት ሊያደርሱ ስለሚችሉ የሚመለከታቸው አካላት ተከታታይ የመፍትሄ እርምጃዎችን እንዲወስዱም ፅ/ ቤቱ በአፅንኦት ያሳስባል፡፡
እንዲሁም ከኤሌክትሪክ ችግር ጋር ተያይዞ የሚከሰትን የእሳት ቃጠሎ አደጋ ለመከላከል በቤት ውስጥ ወይም በስራ ቦታ የኤሌክትሪክ መገልገያ መሳሪያዎች ከሀይል ማከፋፈያ መቋረጣቸውን ሳያረጋግጡ ትተው እንዳይወጡ ያስገነዝባል፡፡
በቅዝቃዜ ወቅት ከሰልን ሲጠቀሙ በርና መስኮት በመክፈት በቂ የአየር ዝውውር እንዲኖር በማድረግና በመጨረሻም ከሰሉን በውሃ በማጥፋት ሊደርስ የሚችልን ሰብአዊ አደጋን መከላከል እንደሚገባ ተመልክቷል፡፡
ፈጣን እና ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት እነዚህን አድራሻዎች ይከተሉ፤ ቤተሰብ ይሁኑ!
Facebook:-
👇👇👇👇
https://www.facebook.com/CITYMANAGER1
Telgram:-
👇👇👇👇
https://t.me/aacitymanager
Twitter:-
👇👇👇👇
https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r
YouTube:-
👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s
በፓርቲያችን መተዳደሪያ ደንብ መሰረት “ቃልን በተግባር ለኢትዮጵያ ብልፅግና” በሚል መሪ ሃሳብ ከተማ አቀፍ ማጠቃለያ ኮንፈረንስ እያከሄድን ነው።
ፓርቲያችን፣ በባለፉት ሁለት ተኩል የምርጫ ዘመን አጋማሽ ዓመታት አባላቱን እና አመራሩን አቀናጅቶ በመምራቱና ሕዝቡን በቀጥታ በማሳተፉ አበራታች ዉጤቶች አስመስግቧል ።
የበለጠ ውጤት ለማስመዝገብ በምርጫ ዘመን አጋማሽ በአፈፃፀሞቻችን የተገኙ ስኬቶችንና ያጋጠሙ ተግዳሮቶችን ቆም ብሎ መመዘንና መፈተሸ አስፈላጊ ነው።
በባለፉ ሁለት ተኩል ዓመታት አንፀባራቂ ድሎችን ስናስመዘግበ ሁሉም ነገር አልጋ በአልጋ አልነበረም።
በርካታ ፈታኝ ሁኔታዎችም ገጥመውናል። መሻገር የቻልነዉ በያዝነዉ የፖለቲካ ዓላማ ጽናት በመርህ ላይ ቆመን በመታገላችን ነው። ፈተናዉን መቋቋም ያልቻሉ ከረጅሙ የትግል ጉዞ ገና በማለዳዉ ተለይተዉናል።
ሀሳባችን የጠራ፣ ዓላማችን ሁለተናዊ ብልፅግናን ማረጋገጥ፣ ለመጪዉ ትዉልድ ዕዳን ሳይሆን ምንዳን ማስተላለፍ በመሆኑ በየምዕራፉ የሚገጥሙን መሰናከሎች ለጊዜዉ ሊፈትኑን ይችሉ ይሆናል ከመዳረሻ ግባችን አያደናቅፉንም።
ቃላችንን ጠብቀን ህዝባችንን በታማኝነት ማገልገላችንን እንቀጥላለን !
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
በሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ኤጀንሲ እየተካሄደ ባለው ተቋማዊ ሪፎርም ስልጡን፣ ዘመናዊ እና ስነ-ምግባር የተላበሰ ሲቪል ሰራተኛ የመፍጠር አካል የሆነ ሁለት ሺህ ለሚጠጉ ሰራተኞች አዲስ የደንብ ልብስ በዛሬው እለት ይፋ ሆኗል።
በአድዋ ድል መታሰቢያ በተካሄደው የኤጀንሲው ሰራተኞች የደንብ ልብስ ይፋ ማድረጊያ ስነስርአት ላይ የፌዴራል መንግስት የስራ ሃላፊዎች: የከተማ አስተዳደሩ የካቢኔ አባላትና በየደረጃው የሚገኙ የከተማ አስተዳደሩ አመራሮች ተገኝተዋል::
በምክትል ከንቲባ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ወ/ሮ ሂክማ ከይረዲን በስነ ስርአቱ ላይ ባስተላለፉት መልእክት ኤጀንሲው በተቋም ግንባታና ሪፎርሙ ያስመዘገበውን ስኬት ያህል አሁንም የትኩረት ማእከላችን የአገልግሎት አሰጣጡን ወደ ላቀ ደረጃ ማድረስና የህብረተሰቡን እርካታ ማረጋገጥ መሆን ይኖርበታል ሲሉ ተናግረዋል::
አክለውም በዚህ ረገድ በኤጀንሲው የሚሰጡ ማንኛውንም አይነት የኩነት አገልግሎቶች ስታንዳርዶችን መሰረት ያደረጉ፣ የብልሹ አሰራርን መከላከልና የመልካም አስተዳደር ችግሮችን መፍታትን ልዩ ትኩረትን የሚሰጡ ሊሆን እንደሚገባም በአፅንኦት ገልፀዋል::
የሲቪል ምዝገባና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮናስ አለሙ እንደገለፁት ኤጀንሲው መላው ሠራተኞች ከለበሱት የደንብ ልብስ ስርዓት ጎን ሊተላለፏቸው የማይችሏቸውን የስነ-ምግባር መመርያ ህግጋት በጋራ ውይይትና በመተማመን አፅድቀናል ብለዋል:: ነዋሪውንም በቁርጠኝነት ለማግልገል በአመራሩና በከተማው ነዋሪዎች ፊትም ለመጀመርያ ግዜ ቃለ-መሃላ መፈፀማቸውን አስታውቀዋል።
በስነ-ስርዓቱ ላይ በስራ አፈፃፀማቸው የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ የኤጀንሲው መዋቅር ሰራተኞች የእውቅና መርሐግብርም ተካሂዷል::
ከቃሊቲ ማሰልጠኛ - ቱሉ ዲምቱ የመንገድ ዳር መብራት የኤሌክትሪክ መሠረተ ልማት ዝርጋታ እየተፋጠነ ይገኛል።
በአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ፅ/ቤት አስተባባሪነት ልዩ ክትትልና ድጋፍ እየተደረገለት በከተማው የኤሌክትሪክ አገልግሎት እና በመንገዶች ባለስልጣን በቅንጅት እየተከናወነ የሚገኘው ከቃሊቲ ማሰልጠኛ - ቱሉ ዱምቲ የመንገድ ዳር መብራት ስራው የትራንስፎርመር ማስቀመጥና ሌሎች አስፈላጊ የመሠረተ ልማት ዝርጋታ እየተፋጠነ ሲሆን በአጭር ጊዜ ውስጥ ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት እንዲጀምር በፅ/ ቤቱ አመራሮች ማሳሰቢያ ተሰጥቷል::
በቢሮ ኃላፊ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ስራ አስኪያጅ አቶ ተፈራ ሞላ፤ በም/ቢሮ ኃላፊ ደረጃ የጽቤቱ የኮሙኒኬሽን ዘርፍ ኃላፊ ወ/ሮ ኃይማኖት ዘለቀ እና የአቃቂ ቃሊቲ ከ/ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ማናዬ ጫኔ የመንገድ ዳር መብራት ዝርጋታ የደረሰበትን ደረጃ በመዘዋወር ምልከታ በዛሬው እለት ባደረጉበት ወቅት ኃላፊዎቹ የመሠረተ ልማት ዝርጋታ ስራው በጥሩ ሁኔታ እየተሳለጠ እንደሆነ ጠቁመዋል::
የአዲስ አበባ ከተማ ም/ ዋ/ ስራ አስኪያጅ አቶ ተፈራ ሞላ የኤሌክትሪክም ሆነ የመንገድ መሰረተ ልማቶች እንዳይሰረቁ የከተማችን ነዋሪ ንብረቱን እንደራሱ ንብረቶች ቆጥሮ ሊጠብቅ እንደሚገባና የከተማው የኤሌክትሪክ አገልግሎትና የመንገዶች ባለስልጣንም ቅንጅታዊ ስራቸውን በማጠናከር የመንገድ ዳር መብራቱ በፍጥነት አገልግሎት እንዲጀምር ማድረግ ይገባቸዋል ሲሉ በአፅንኦት አስገንዝበዋል።
ፈጣን እና ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት እነዚህን አድራሻዎች ይከተሉ፤ ቤተሰብ ይሁኑ!
Facebook:-
👇👇👇👇
https://www.facebook.com/CITYMANAGER1
Telgram:-
👇👇👇👇
https://t.me/aacitymanager
Twitter:-
👇👇👇👇
https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r
YouTube:-
👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s
Tiktok
👇👇👇👇
https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager...
Website
👇👇👇👇
https://www.aacitymanger.gov.et
በመዲናዋ የደረቅ ቆሻሻ አስተዳደር ስርዓቱን ለማዘመን እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ።
የአዲስ አበባ ከተማ ፅዳት አስተዳደር ኤጀንሲ ከጃይካ አማካሪ ቡድን /JIca Advisory Group/ ጋር በመተባበር በከተማዋ የተቀናጀ ደረቅ ቆሻሻ አስተዳደር ስርዓቱን ለማዘመን እየተሰራ አንደሆነ በኢሊሊ ሆቴል በተደረገ ውይይት ተገልፅዋል።
አማካሪ ቡድኑ የከተማዋን ደረቅ ቆሻሻ አስተዳደር ስርዓት ነባራዊ ዳሰሳ ጥናት በመስራት ለውይይት አቅርበዋል።
የውይይቱ ዓላማም ደረቅ ቆሻሻን ከምንጩ መቀነስ እንደ ፓይለት ፕሮጀክት በመያዝ የመልሶ መጠቀምና ዑደት ማድረግ ተግባርን በማሳደግ ረጲ የሚወገደውን የደረቅ ቆሻሻ መጠን በመቀነስ የአገልግሎት እድሜውን ለማራዘም እንደሆነ ተገልፅዋል።
አማካሪ ቡድኑም ከጃፓን መንግስት ጋር በመተባበር የከተማዋን ፅዳት ለመጠበቅ እየተደረገ ያለውን ጥረት በሙያና በገንዘብ ድጋፍ እንደሚያደርጉም ተናግረዋል።
ፕሮጀክቱ ለቀጣይ 2035/36 ዓ.ም ድረስ በከተማዋ የሚመነጨውን ደረቅ ቆሻሻ ሳይንሳዊ በመሆነ መንገድ ለማስተዳደር እንደሚያገለግል አማካሪ ቡድኑ አብራርተዋል።
ፈጣን እና ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት እነዚህን አድራሻዎች ይከተሉ፤ ቤተሰብ ይሁኑ!
Facebook:-
👇👇👇👇
https://www.facebook.com/CITYMANAGER1
Telgram:-
👇👇👇👇
https://t.me/aacitymanager
Twitter:-
👇👇👇👇
https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r
YouTube:-
👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s
Tiktok
https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager...
