1 474
Subscribers
No data24 hours
-37 days
-2130 days
Posts Archive
የአዲስ አበባ ከተማ ሥራ አስኪያጅ ጽ/ቤት የሁለት ተጠሪ ተቋማቱን ያለፉት 6 ወራት የስራ አፈጻጸም ገመገመ።
በዛሬው እለት የበጀት አመቱ የመጀመሪያ 6 ወራት የስራ አፈፃፀማቸው ላይ ግምገማ የተካሄደው ሁለቱ ተጠሪ ተቋማት የአዲስ አበባ ከተማ የኤሌክትሪክ አገልግሎት ማስተባበሪያና የመብራት አገልግሎት አስተዳደር ባለስልጣን ናቸው።
የግምገማ መድረኩን የመሩት በምክትል ከንቲባ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ ሲሆኑ የጽ/ቤቱ ከፍተኛ አመራሮችም በተገኙበት ነው።
የሁለቱ ተጠሪ ተቋማት አመራሮች ባለፉት 6 ወራት በየተቋማቸው የተከናወኑ ዋና ዋና ስራዎችና ክንውኖች በሪፖርት ያቀረቡ ሲሆን የክፍለ ከተሞች ዋና ስራ አስኪያጆች በተገኙበት ግምገማው ተካሂዷል።
በዚሁ ወቅት በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የአዲስ አበባ አገልግሎት ማስተባበሪያ በኩል የዘመናዊ የክፍያ ስርዓትን ከማሳደግ ፣የበጀት አጠቃቀምን በተመለከተ፣ የደንበኞችን እርካታና ቁጥር ከማሳደግ፣ የኤነርጂ ሽያጭ ገቢን ከማሳደግ፣ የሀይል መቆራረጥን ከመቀነስ አንፃር የተከናወኑ ስራዎችን የሚያሳይ ሪፖርት ቀርቦ ውይይት ተካሂዶበታል።
በተያያዘም በአዲስ አበባ ከተማ የመብራት አገልግሎት አስተዳደር ባለስልጣን በኩል በግማሽ አመቱ የተከናወኑ ስራዎችን የሚያሳይ ሪፖርት የቀረበ ሲሆን በሪፖርቱም በተለይም የሪፎርም ስራዎችን በተመለከተ፣ ብልሹ አሰራርን ከመከላከል፣የቢሮ ግብአት ከማሟሟላት እና የኘሮጀክቶችን ርክክብን የተመለከቱ ስራዎች በሪፖርቱ ቀርቧል።
በተያያዘም የጥገና ስራዎችን ከማከናወን፣የስማርት ፖል አቅርቦት እና እንዲሁም ከኮሪደር ልማት ጋር የተያያዙ ስራዎችን የሚያሳይ ሪፖርት ቀርቦም ዉይይት ተካሂዶበታል።
በመድረኩ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ በበጀት አመቱ በሁለቱም ተቋማት የአገልግሎት አሰጣጥ የላቀ ለማድረግ እና ከመሠረተ ልማት ዝርጋታ አኳያ የተከናወኑ የማሻሻያ ስራዎች ከተማዋ በዚህ ረገድ የደረሰችበትን ደረጃ በይበልጥ የሚያሳይና አበረታች እንደሆነ ገልፀው የተገልጋይ እርካታን ከማሳደግ እና መልካም አስተዳደር ለማስፈን የተደረጉት ጥረቶችም መጠናከር እንዳለበት አስገንዝበዋል።
አክለዉም በሁለቱም ተቋማት በቀጣይ የበጀት አመቱ ቀሪ ጊዜያት በተለይም ስራዎች በቴክኖሎጂ እንዲታገዙ በማድረግ እና ዘላቂነት ያለዉ ስራ ከመስራት፣የነዋሪውን እርካታን ከማረጋገጥ፣የሚሰጡ አገልግሎቶችን በስታንዳርድ ከመማከናወን፣ፈጣን ምላሽ ሰጭነትን ከማጠናከር ፣ የአቅም ግንባታ ስልጠናን ከመስጠት፣የህዝብ ተሳትፎን ከማሳደግ፣ ቅንጅታዊ አሰራርን እና የሪፎርም ስራዎችን በአግባቡ ከመተግበር አንፃር ሰፊ ስራ መስራት እንደሚገባቸው አሳስበዋል።
በማጠቃለያም በመጀመሪያ 6 ወራት የመጡ ጠንካራ ዉጤቶችን በማስቀጠልና እንዲሁም እንዲስተካከሉ የተሰጡ አስተያየቶችን እንደ ግብአት በመውሰድ ለቀጣይ ቀሪ የበጀት አመቱ ወራት የተሻለ አፈፃፀም ለማስመዝገብ መላ አቅምን በማስተባበር የተጠናከረ ጥረት ማድረግ ይገባል ሲሉ ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ አቅጣጫ አስቀምጠዋል።
ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ!
Facebook:-
👇👇👇👇
https://www.facebook.com/CITYMANAGER1
Telgram:-
👇👇👇👇
https://t.me/aacitymanager
Twitter:-
👇👇👇👇
https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r
YouTube:-
👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s
Tiktok
👇👇👇👇
https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager...
Website
👇👇👇👇
https://www.aacitymanger.gov.et
በዛሬው እለት በደቡብ ምዕራብ ክልል ዳውሮ ዞን የተገነባውን የኢቲ ማዕድን ልማት አ.ማ የድንጋይ ከሰል ማጠቢያ ፋብሪካን መርቀን ስራ አስጀምረናል። ፋብሪካው በሀገር አቀፍ ደረጃ ያለውን የድንጋይ ከሰል ምርት ከማሻሻል ባሻገር ለበርካታ የአካባቢው ነዋሪዎች የስራ እድል የፈጠረ ነው።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)
ካዛንቺስ አያት የመኖሪያ መንደር በውስጥ:-
- 13,752 የመኖሪያ ቤቶች
- ደረጃውን የጠበቀ ሞል
- የንግድ ሱቆች
- አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት
- የጤና ማዕከል
- አራት መዋለ ሕፃናት
- ሁለት የመጫወቻ ቦታዎች
- የህዝብ ፕላዛ
- አረንጓዴ ቦታዎች
- 12,000 ተሽከርካሪ የሚያቆሙ ቤዝመንት ፓርኪንግ
- ለእግረኛ እና ለብስክሌት ተጠቃሚዎች ምቹ የሆኑ መንገዶች ያካተተ ነው::
ዛሬ በመንግስት እና ግል አጋርነት መርሀ ግብር ከአያት አክሲዮን ማህበር ጋር በመተባበር የ13,752 ቤቶች ግንባታን አስጀምረናል::
በካዛንቺስ አካባቢ ከኦቪድ ግሩፕ ጋር ካስጀመርነው ጋር ከ15 ሺሕ በላይ ቤቶችን የምናለማ ሲሆን ቅድሚያ የማልማት መብታቸውን በመጠቀም የሚገነቡ የግል አልሚዎችን ጨምሮ በጠቅላላው 20 ሺሕ ቤቶችን የሚገነቡ ይሆናል::
በከተማችን ያረጁ እና ለመኖር ምቹ ያልሆኑ እንደ ካዛንቺስ ያሉ አካባቢዎችን መልሰን ስናለማ በዋነኛነት የህዝቡን ዋንኛ አንገብጋቢ ጥያቄ የሆነውን የመኖሪያ ቤትን ለመመለስ ሲሆን የመኖሪያ ቤቶችን ስንሰራ ቤት ብቻ ሳይሆን ለኑሮ ምቹ የሆነ አካባቢዎችን እንገነባለን::
ካሳንችስ ከመልሶ ማልት በፊት ነባር 8000 መኖሪያና ንግድ ቤቶች በጥቅሉ ወደ 21ሺ ነዋሪዎችን የሚገለገሉበት አካባቢ የነበረ ሲሆን በመልሶ ማልማት ስራችን ሁለት ሺሕ የንግድ ሱቆች እና ሀያ ሺሕ መኖሪያ ቤቶችን በመገንባት ከ100 ሺሕ በላይ ነዋሪዎች የሚገለገሉበት አካባቢ ይሆናል።
ካዛንቺስ ላይ የምንገነባው ይህ የካዛንቺስ አያት መንደር በውስጡ ማህበራዊ ግልጋሎትን የሚሰጡ ተቋማት ጨምሮ የመማሪያ ቦታዎች፣ የጤና ተቋማት፣ የስፖርት ማዘውተሪያ ቦታዎች፣ አረንጏዴ ቦታዎች፣ ሞሎች፣ ሱቆች እንዲሁም ሰፋፊ የመኪና ማቆሚያዎችን ያካተተ ግዙፍ ፕሮጀክት ሲሆን ሰፊ የስራ እድል የሚፈጥር ነው::
በሚቀጥሉት 18 ወራት ጊዜ ውስጥ የ15 ሺህ ቤቶች ግንባታን ለማጠናቀቅ ያቀድን ሲሆን ሁላችንም ለፕሮጀክቱ ስኬት በጋራ እንድንሰራ አደራ እያልኩ ንጹህ፣ ፅዱ፣ ለነዋሪዎቿ ምቹ እና ተወዳዳሪ የሆነች አለም አቀፍ ከተማ መገንባታችንን አሁንም አጠናክረን ቀጥለናል::
ያስጀመረን ፈጣሪ በድል እንድናጠናቅቅ ይርዳን!
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት "የማህበራዊ ሚዲያ አጠቃቀምና የቀዉስ ጊዜ ተግባቦት" በሚል ርዕስ ስልጠና ሰጠ።
ለተጠሪ እና ባለድርሻ ተቋማት የኮሙኒኬሽን ሃላፊዎች፣ ለክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጆችና የኮሙኒኬሽን ሃላፊዎች፣ ለመንግስትና የግል የሚዲያ ባለሙያዎች በተሰጠ በዚህ የአቅም ግንባታ ስልጠና ላይ አቶ ወሰን መግራ፣ የከተማ ስራ አስኪያጅ የጽ/ቤት ኃላፊው ቀውስ በሚያጋጥም ወቅት የመረጃ አያያዝ፣ ልውውጥና መጋራት እንዴት መሆን እንዳለበት በሰፊው ያስረዱ ሲሆን በተለያዩ ምክንያቶች በየጊዜው ተቋማት በተለየ ሁኔታና ጥንቃቄ ሊያዩዋቸው የሚገቡ “ቀውሶች” ሲያጋጥሙ መደረግ ስልሚገባቸው ጥንቃቄዎችና መወሰድ ስለሚገባቸው እርምጃዎች ሳይንሳዊ ማብራሪያና አለማቀፍ፣ አገራዊና ከተማዊ ማሳያዎች ቀርበው ታዳሚዎች ተወያይተዋል። በዉይይቱም የቀዉስ ጊዜ ኮሚኒኬሽን በየተቋማቸው ምን አእንደሚመስል ታዳሚዎች ልምድና ተሞክሮዋቸውን የተጋሩ ሲሆን በቀጣይም በቅንጅትና ብትናበበ አግባብ መርህን የተከተለና ውጤት ተኮር መስተጋብርን ማጎልበት እንደሚገባ ተመላክቷል።
በስልጠናዉ ማጠቃለያ ላይ ተሳታፊዎች በሰጡት አስተያየት የአዲስ አበባ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት በተጠሪና ባለድርሻ ተቋማቱ የሚሰጡ የማዘጋጃቤታዊ አገልግሎት አሰጣጥ የመረጃ ተግባቦትን መሰረት እንዲያደርጉና ጊዜውን የዋጁ አንዲሆኑ በማሰብ ስልጠናዉ እንዲሰጥ ማድረጉ የሚደንቅና ለቀጣይም መበረታታት የሚገባው መሆኑን ተሳታፊዎች ተናግረው መሰል መድረኮች አቅምን ከመገንባት ባሻገር የሙያተኞችን መግባባትና በጋራ የመስራት ባህል ልማሻሻል ጉል ሚና እንዳላቸው ተናግረዋል።
የስራ አስኪያጅ ጽ/ቤቱ በትላንትናዉ ዕለትም "የማዘጋጃ ቤታዊ ኮሚኒኬሽን "፣"የተግባቦት ስራ ለማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት"፣ “የመልዕክት ቀረጻ እሳቤዎችና አሰራሮች” እንዲሁም “የአስተሳሰብ ለወጥ አስፈላጊነት” ዙሪያ ስልጠናዎችን መስጠቱ ታውቋል።
ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ!
Facebook:-
👇👇👇👇
https://www.facebook.com/CITYMANAGER1
Telgram:-
👇👇👇👇
https://t.me/aacitymanager
Twitter:-
👇👇👇👇
https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r
YouTube:-
👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s
Tiktok
👇👇👇👇
https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager...
Website
👇👇👇👇
https://www.aacitymanger.gov.et
የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጃንሲ 180 የአምስት ሚልዮን ኮደርስ ስልጠና የወሰዱ ሙያተኞቹን አስመረቀ
የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ያስጀመሩትና የ5 ሚሊዮን ኮደርስን ለማፍራት በታቀደው መሰረት የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ከዋና መስርያ ቤት እስከ ወረዳ የሚገኙ ባለሙያዎች የዝግጅት ስልጠና ኦሬንቴሽን በመስጠት ስልጠና እንዲወስዱ አድርጓል።
በዛሬው ዕለትም የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር በለጠ ሞላ ፣ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ-አስኪያጅ ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ ፣ የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሰለሞን አማረ እንዲሁም የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮናስ አለማየሁ በተገኙበት ከሁለት እስከ አራት ኮርስ የወሰዱ የመጀመርያ 180 ሰራተኞቹን አስመርቋል።
ማጠቃለያ ላይ የዕለቱ የክብር እንግዳ ዶ/ር በለጠ ሞላ የስልጠናው አስፈላጊነት እና ወሳኝነት ላይ አፅንኦት በመስጠት አሁን ያለንበት ዘመን የእውቀት ዘመን በመሆኑ መንግስት ያለማውን ሃገሪቱን ወደ ዲጂታል የማሸጋገር ውጥን ሰልጣኞች እራሳቸውን አብቅተው በዓለም ተወዳዳሪ ሃገር ለመገንባት በሚደረገው ጉዞ አስተዋፆዖ እንዲያደርጉ መልዕክትና የስራ መመርያ ለሰልጣኞች አስተላልፏል። ሚኒስትሩ የኤጀንሲው እርምጃ በኮደርስ ስልጠና ፕሮግራም እንደ ሃገር የሚወሰድ ተሞክሮ መሆኑን አክለዋል።
ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ!
Facebook:-
👇👇👇👇
https://www.facebook.com/CITYMANAGER1
Telgram:-
👇👇👇👇
https://t.me/aacitymanager
Twitter:-
👇👇👇👇
https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r
YouTube:-
👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s
Tiktok
👇👇👇👇
https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager...
Website
👇👇👇👇
https://www.aacitymanger.gov.et
የማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎቶችን ለህዝቡ በሚገባ በማስተዋወቅ የአገልግሎት እርካታ ለማሳደግ የሚያግዝ የተግባቦት ስራዎችን ማጠናከር እንደሚገባ የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ ቤት አስታወቀ።
ጽ/ ቤቱ ለተጠሪ ተቋማት፣ ለክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጆች፣ ለኮሙዩኒኬሽን አመራሮችና ባለሙያዎቾ እንዲሁም ለባለድርሻ አካላት " የተግባቦት ክህሎት ለማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት" በሚል መሪ ቃል የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና በመስጠት ላይ ይገኛል።
በስልጠናው ላይ በቢሮ ሃላፊ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ ም/ ዋ/ ስራ አስኪያጅ አቶ ተፈራ ሞላ ባስተላለፉት መልእክት የማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት ዘመኑን የዋጀ፣ በቴክኖሎጅ የተደገፈ አለምዓቀፋዊነትን የሚመጥን፣ አሰራሩን በማዘመን ላይ እንዳለ ገልፀው እነነዚህን ተግባራት በውጤታማነት ማከናወን የተቻለው ለህዝቡ ወቅታዊና ትክክለኛ መረጃ በማድረስ በሂደቱ ተሳታፊ እንዲሆን በመደረጉ ነው ብለዋል።
አቶ ተፈራ ሞላ አክለውም መዲናችን በአሁኑ ወቅት ጽዱ፣ውብ እና ለኑሮ ምቹ እየሆነች ከጊዜ ወደ ጊዜ መምጣቷን ገልፀው የዘረጋቻቸው መሠረተ ልማቶች እንዲጠበቁ እና የሚሰጡ ማዘጋጃ ቤታዋ አገልግሎቶችም የተሳለጡ በማድረግ ረገድ ለህብረተሰቡ መረጃን በፍጥነት፣ በጥራት ፣በእውቀትና በእምነት ላይ ተመሰርቶ ተደራሽ ማድረግ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ!
Facebook:-
👇👇👇👇
https://www.facebook.com/CITYMANAGER1
Telgram:-
👇👇👇👇
https://t.me/aacitymanager
Twitter:-
👇👇👇👇
https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r
YouTube:-
👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s
Tiktok
👇👇👇👇
https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager...
Website
👇👇👇👇
https://www.aacitymanger.gov.et
የሲቪል ምዝገባና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ በ2016ዓ.ም የተሰጡ የዲጂታል አገልግሎቶቹን ጤናማነት እንዲሁም የተሰራጩ ሰርተፍኬት እና ካርዶች በአግባቡ ስራ ላይ ስለመዋላቸው ኦዲት ማድረጉን አስታወቀ።
ዛሬ ጥር 13 የሲቪል ምዘገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮናስ ዓለማየሁ ተቋሙ በበጀት ዓመቱ ስድስት ወራት ካቀዳቸው የፈፀማቸውን ዋና ዋና ተግባራት አስመልክቶ ለሚድያ አካላት ማብራርያ ሰጥተዋል።
የሲቪል ምዝገባን በተመለከተ:
***
* በስድስት ወራት ውስጥ በከተማው ከተወለዱ ህፃናት ውስጥ 37,750 ለመመዝገብ የታቀደ ሲሆን 41,183 (109%) መመዝገብ ተችሏል። ይህም በከተማው ምዝገባ ታሪክ ትልቁ ቁጥር ሆኖ ተመዝግቧል። ከ2016ዓ.ም አፈፃፀም ጋር ሲነፃፀር 103% ብልጫ አሳይቷል። በዘገየ እና የግዜ ገደቡ ያለፈበት ወይም እስከ አንድ ዓመት ድረስ ያሉ ህፃናት ለመመዝገብ የታቀደው 201,761 ሲሆን 195,402 (96.85) መመዝገብ ተችሏል። ለዚህ አፈፃፀም መሻሻል በጤና ተቋማት የተዘርጋው የአንድ ማዕከል አገልግሎት ትልቁን ስፍራ ይይዛል።
* ከተከሰተው ጋብቻ 21,674 ለመመዝገብ ታቅዶ 15,574 (72.65%) ምዝገባ ማደረግ ተችሏል። ከ2016ዓ.ም ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር 7% የምዝገባ ቅናሽ አሳይቷል።
* ከተከሰተው ፍቺ 4,873 ለመመዝገብ ታቅዶ 3,769 (77.34%) ምዝገባ ማደረግ ተችሏል። ከ2016ዓ.ም ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር 33.99% የምዝገባ ጭማሪ አሳይቷል።
* ከተከሰተው ሞት 15,716 ለመመዝገብ ታቅዶ 11,376 (72.38%) ምዝገባ በማደረግ ተችሏል። ከ2016ዓ.ም ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር 29.83% የምዝገባ ጭማሪ አሳይቷል።
የነዋሪነት ምዘገባን በተመለከተ:
***
* ወደ ዲጂታል ምዝገባ ያልተቀላቀሉ 339,876 ነዋሪዎችን ለመመዝገብ ታቅዶ 340,45 (100%) መመዝገብ የተቻለ ሲሆን ከ2016ዓ.ም ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር የ9.17% ብልጫ አሳይቷል። ከዚህ ውስጥ የነዋሪነት መታወቂያ ለመስጠት የታቀደው 370,908 ሲሆን 268,470 ( 72.38%) ማሳካት ተችሏል። ከ2016ዓ.ም ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር 26.72% ቅናሽ አሳይቷል። ከተሰጡት የነዋሪነት መታወቂያ 99.84 % የሚሆነው ዲጂታል ሲሆን ቀሪው በቤት ለቤት የተሰጠ የማንዋል አገልግሎት ነው።
* ተቋሙ ታግደው የነበሩ አገልግሎቶችን ችግር የፈታ ሲሆን 25,581 የክልል መሸኛዎች ትክክለኛነት እንዲጣራ ለክልሎች መላኩን የገለፀ ሲሆን አገልግሎት ለማግኘት ሪፖርት ያደረጉ 9,504 አመልካቾችን መሸኛ መርምሮ የነዋሪነት ምዘገባ አድርገው አገልግሎት እንዲያገኙ ፈቃድ መስጠቱን አስታውቋል።
የፋይዳ ምዝገባን በተመለከተ:
***
* በአዲስ አበባ ከተማ ያለውን የፋይዳ ምዝገባን ከብሄራዊ መያወቂያ ጽ/ቤት ጋራ በጋራ ለመምራት በተደረገው ጥረት ላለፉት ሁለት ወራት 1.8ሚልዮን ነዋሪዎችን መመዝገብ ተችሏል።
* በቀጣይ በሚቀመጥ የግዜ ገደብ ቀሪ ያለተመዘገቡ ነዋሪዎችን ለመመዝገብ እቅድ የተዘጋጀ ሲሆን በከተማው ያሉ ትምህርት ቤቶች የተማሪ ምዝገባም ከልደት ምዝገባ ባሻገር የፋይዳ ምዝገባ አስገዳጅ እንዲሆን ተወስኗል።
ህገ-ወጥ ተግባራት ላይ የተወሰዱ እርምጃን በተመለከተ:
****
* በስድስት ወራቱ በቀላል 25 እና በከባድ 37 በድምሩ 71 ሰራተኞች ላይ የዲሲፕሊን እርምጃ የተወሰደ ሲሆን ከእነዚህ ውስጥ 8 ሰራተኞች አገልግሎት በገንዘብ በመሸጥ 1 ሰራተኛ ሃሰተኛ ሰነድ በማዘጋጀት በጠቅላላ 9 ሰራተኞች በወንጀል ተጠርጥረው ከስራ ታግደው በምርመራ ሂደት ላይ ይገኛሉ።
* 28 ባለጉዳዮች በወረዳ እና በዋና መስርያ ቤት ሃሰተኛ ሰነድ ይዘው በመቅረብ ለህግ እንዲቀርቡ የተደረገ ሲሆን በድምሩ 110 ሰራተኞች እና ተገልጋዮች በአስተዳደራዊ እና በወንጀል በህግ እንዲጠየቁ ተደርጓል።
የኦዲት እርምጃን በተመለከተ:
***
* በበጀት ዓመቱ ስድስት ወራት ዋና መስርያ ቤትን ጨምሮ 11 ክ/ከተማ እና 27 የወረዳ ጽ/ቤቶች በ2016ዓ.ም የተሰጡ አገልግሎቶች እና ለአገልግሎት መስጫ ስራ ላይ የዋሉ ህትመቶች ኦዲት ተደርጓል።
* በዚሁ መሰረት በተሰጠው አገልግሎት ላይ የተሰራጩ የካርድ ፣ የሰርተፍኬት እና የዲጂታል መታወቂያ አሰራርን ባለ መከተል፣ አሰራርን በመጣስ ፣ ጉድለት በመፍጠር፣ ስራን በአግባቡ ባለመምራት እና ጉድለት በመፍጠር በስድስቱ ክ/ከተሞች ጉድለት የተገኘ ሲሆን በዚህም 33 ሰራተኞች ተጠያቂነት ያረፈባቸው ሲሆን 19 በወንጀል ፣ 24 በአስተዳደራዊ እንዲሁም አንድ አመራር ስራን በአግባቡ ባለማምራት በሃላፊነት እንዲጠየቁ መወሰኑን ዋና ዳይሬክተሩ በማብራርያቸው ገልፀዋል።
አቶ ዮናስ በሚሰጡ አገልግሎቶች ውስጥ በቅንነት እና በታማኝነት የሚያገልግሉ ህብረተሰቡም እውቅና የሚሰጣቸውና ጤናማ ያልሆነ ነገር ሲያዩ ለተቋም በመወገን ሌብነትን የሚያጋልጡ ሰራተኞችን እውቅና የሚሰጥበት 2ኛው የሰራተኛ እውቅና መርሃ ግብር ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ጠቁመዋል።
ሃላፊው በተቋም ግንባታ ሂደት የመጡ ለውጦችን በማስቀጠል የተሻለ ተቋም ለመፍጠር ስራዎች መቀጠላቸውን የገለፁ ሲሆን የቅሬታ አፈታት እና የስታንዳርድ ጉዳዮች ላይ ትኩረት ሰጥተው እንደሚሰሩና በከፋ ሁኔታ የገጠመውንም የሲስተም ችግር ለመፍታት በቤት ስራነት እንደተያዘ ጠቁመዋል።
ለበለጠ መረጃ፣ በነፃ መስመርጠ7533 ይደውሉ
ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ!
Facebook:-
👇👇👇👇
https://www.facebook.com/CITYMANAGER1
Telgram:-
👇👇👇👇
https://t.me/aacitymanager
Twitter:-
👇👇👇👇
https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r
YouTube:-
👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s
Tiktok
👇👇👇👇
https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager...
Website
👇👇👇👇
https://www.aacitymanger.gov.et
ጥምቀትና ቃና ዘገሊላ በዓላት በሰላም ተከብረው መጠናቀቃቸውን የፀጥታና ደኅንነት ጥምር ኃይል አስታወቀ
የፀጥታና ደኅንነት ጥምር ኃይል ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ደረጃ በዩኒስኮ ካስመዘገበቻቸው ከማይዳሰሱ ቅርሶች ውስጥ አንዱ የሆነው የጥምቀት በዓል አዲስ አበባን ጨምሮ በመላው ሀገራችን በሰላም መጠናቀቁን ለመገናኛ ብዙሃን በላከዉ ጋዜጣዊ መግለጫ አስታውቋል።
በተመሳሳይ በዛሬው ዕለት የተከበረው የቃና ዘገሊላ በዓልም በሰላም መከበሩን ጨምሮ ገልጿል።
በመሆኑንም በዓሉ ያለምንም የፀጥታ ችግር እንዲከበር የበኩላቸውን ድርሻ ላበረከቱት ለመላው የሀገራችን ሕዝብ፣ ለሃይማኖት አባቶች፣ ለምዕመናን፣ ለሰላም ሠራዊት አባላት እና ለበዓሉ አስተባባሪዎች እንዲሁም የተሰጣቸውን ኃላፊነት በብቃት ለተወጡት የፀጥታ ተቋማት አመራርና አባላት የፀጥታና ደኅንነት ጥምር ኃይል በመግለጫው ላቅ ያለ ምስጋና ማቅረቡን የፌደራል ፖሊስ መረጃ ያመለክታል።
ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ!
Facebook:-
👇👇👇👇
https://www.facebook.com/CITYMANAGER1
Telgram:-
👇👇👇👇
https://t.me/aacitymanager
Twitter:-
👇👇👇👇
https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r
YouTube:-
👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s
Tiktok
👇👇👇👇
https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager...
Website
👇👇👇👇
https://www.aacitymanger.gov.et
