en
Feedback
Addis Ababa City Manager Office

Addis Ababa City Manager Office

Open in Telegram
1 474
Subscribers
No data24 hours
-37 days
-2130 days
Posts Archive
የጎርፍ አደጋን ለመከላከል የቅድመ ዝግጅት ስራዎች እየተሰሩ ነው ++++++++++++++++++++ በአዲስ አበባ ከተማ የጎርፍና አደጋ ተጋላጭ በሆኑ የወንዝ ዳርቻዎች የጎርፍ አደጋን ለመከላከል የቅድመ ዝግጅት ስራዎች እየተሰሩ መሆኑ ተገለጸ። በአዲስ አበባ ከተማ የጎርፍና አደጋ ተጋላጭ በሆኑ የወንዝ ዳርቻዎች የተሰሩ የአደጋ መከላከል ተግባራትና የስራ እንቅስቃሴ የመስክ ምልከታ ተካሂዷል። በምልከታው ላይ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ እንደገለፁት፤ በመጪው ክረምት የሚደርስ የጎርፍ አደጋን ለመከላከል የቅድመ ዝግጅት ስራዎች እየተሰሩ ነው። በከተማው 278 ለተለያዩ አደጋ ተጋላጭ የሆኑ ቦታዋች ያሉ ሲሆን፤ ከነዚህም ቅድሚያ 170 የሚሆኑ ቦታዎችን በመለየት የቅድመ ጥንቃቄ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን አንስተዋል። በተለይም የክረምት ወራት መቃረብን ተከትሎ የሚደርሱ የጎርፍ፣የመሬት መንሸራተት እና በፍሳሽ ምክንያት የመንገዶች መዘጋትን ለመከላከል ሰፊ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች እየተሰሩ ነው ብለዋል። በዚህም በከተማዋ የሚገኙ ወንዞች ድጋፍ ግንብ እየተሰራ መሆኑን ገልፀው፤ የሚሰራው ግንብም ጎርፍ እንዳይከሰት ብሎም ጎርፍ ሰብሮ በመኖሪያ አካባቢዎች እንዳይገባ የሚከላከል መሆኑን ጠቅሰዋል። በተጨማሪም የጎርፍ ስጋት ካለባቸው አካባቢዋች ነዋሪዋችን የማንሳት እና አካባቢን የማልማት ስራ እየተሰራ መሆኑን አስታውቀዋል። የቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ ስርአትን በመከተልም የፍሳሽ ማስወገጃ ቱቦዋችን የማፅዳትና ወደወንዝ የሚገቡ ገባሮችንም መንገድ መክፈት ያስፈልጋል ብለዋል። የአደጋ ተጋላጭ በሆኑ አካባቢዋች የሚገኙ ነዋሪዋች ህይወትና ንብረትን ለአደጋ ከማጋለጥ በተዘጋጀ ምቹ ማረፊያ እንዲያልፉ ቢደረግም ከአካባቢው ለመነሳት ፍቃደኛ የማይሆኑ እንዳሉ አመላክተው፤ የህብረተሰብ ተሳትፎ ወሳኝ በመሆኑ ሁሉም ተባባሪ ሊሆን እንደሚገባ አሳስበዋል። በማህሌት ብዙነህ +++++++++++++++++++++++ Gazette plus #ጋዜጣ_ፕላስ #Ethiopia #ኢትዮጵያ #Gazette_Plus

በጋና ከጆስፖንግ ግሩፕ የመጡ ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች በከተማችን የሚገኘውን ከደረቅ ቆሻሻ ኤሌክትሪክ ሀይል ማመንጫ /Waste to energy/ ጣቢያ ውስጥ እየተከናወኑ የሚገኙ ስራዎችን ጎበኙ። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከጋና የመጡ የጆስፖንግ ግሩፕ ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎችን ተቀብሎ በረጲ ላንድፊል ከደረቅ ቆሻሻ ኤሌክትሪክ ሀይል ማመንጫ /Waste to energy/ ጣቢያ ውስጥ እየተከናወኑ ያሉ የስራ እንቅስቃሴዎችን አስጎብኝቷል። በጉብኝቱ ላይም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ም/ስራ አስኪያጅ ወ/ሮ ይመኙሻል ታደሰን ጨምሮ የኤጀንሲው ኃላፊዎች ፣ በጋና የጆስፖንግ ግሩፕ ልዑካን ቡድን እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተሳትፈዋል። ጎብኝዎቹም ከረጲ ላንድፊል ከደረቅ ቆሻሻ ኤሌክትሪክ ሀይል ማመንጫ ጣቢያ በተጨማሪ በአራዳ ክ/ከተማ ወረዳ 01 የሚገኘውን ጊዚያዊ የደረቅ ቆሻሻ ቅብብሎሽ ጣቢያን ጎብኝተዋል። የጆስፖንግ ግሩፕ በአፍሪካ በመልማት ላይ ላሉ ሀገራት በተቀናጀ የደረቅ ቆሻሻ አስተዳደር ስርአት ዙሪያ ለሚስተዋሉ ችግሮች የመፍትሄ ሀሳቦችንና አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን በማልማት ረገድ እየሰራ የሚገኝ ድርጅት እንደሆነ ተገልፅዋል። ልዑካን ቡድኑ ከተማችን አዲስ አበባ ደረቅ ቆሻሻን ወደ ሀብትነት እየቀየረች ያለውን የስራ እንቅስቃሴ የሚበረታታ መሆኑን ጠቅሰው በተለይ በረጲ ላንድፊል ከደረቅ ቆሻሻ ኤሌክትሪክ ሀይል ማመንጫ /Waste to energy/ ጣቢያ ውስጥ እየተከናወኑ ያሉ ተግባራት እንደተሞክሮ ሊወሰድ የሚገባ ተግባር መሆኑን ተናግረዋል። ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች https://linktr.ee/aacitymanager

የምሽት የደረቅ ቆሻሻ መሰብሰብ አገልግሎት ማስጀመሪያ መርሀ ግብር ተካሄደ የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ የፅዳት አስተዳደር ጽ/ቤት ከዚህ በፊት በማለዳው መርሀ ግብር ሲሰራ የነበረውን የማለዳ የደረቅ የቆሻሻ መሠብሠብ አገልግሎት ፕሮግራምን በመቀየር በምሽት የደረቅ ቆሻሻ መሠብሠብ አገልግሎት ፕሮግራም በአስሩም ወረዳዎች በዛሬው እለት ማስጀመሩ ገልጿል። መርሀ ግብሩን በይፋ ያስጀመሩት የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ የስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ወንድማገኝ ታደሠ የከተማችን ገፅታን ለመቀየርና የስራ ባህላችንን የቀየረ የኮሪደር ልማት ስራን ከደረቅ ቆሻሻ አወጋገድ ስርዓት ጋር በማቀናጀት መተግበር በማስፈለጉ ከዛሬ ግንቦት 18/2017 ዓ.ም ጀምሮ በክፍለ ከተማችን ባሉ በአስሩም ወረዳዎች ተግባሩ መጀመሩን ተናግረው ይህ የምሽት የደረቅ ቆሻሻ መሠብሠብ አገልግሎት ሰኞ፣ሐሙስና ቅዳሜ ከምሽቱ 12 ሰዓት ጀምሮ እስከ ምሽት 3 ሰዓት ድረስ አገልግሎቱ እንደሚሠጥም በንግግራቸው ገልፀዋል። ግንቦት 18/2017 ዓ.ም Lemi Kura Communication ለሚ ኩራ ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች https://linktr.ee/aacitymanager

በአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ፅ/ቤት በጋና ከጆስፖንግ ግሩፕ የመጡ ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች ጋር በዛሬዉ እለት በጽዳት መስክ የልምድ እና የተሞክሮ ልውውጥ መድረክ ተካሄደ። በመድረኩም በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ እንደተናገሩት በመዲናችን ከለዉጡ በኋላ በተለያዩ መስኮች አስደናቂ ለዉጦች መመዝገቡን ጠቅሰዉ በተለይም ከተማዋን ዉብ፣ፅዱና ለነዋሪዎቿ ምቹ ከማድረግ አንፃር እምርታዊ ለዉጥ መመዝገቡን ገልፀዉላቸዋል። አክለውም በአዲስ አበባ ከተማ በተለይም ቆሻሻን ከመሰብሰብ እንዲሁም በማጓጓዝ ብሎም ለማስወገድ የመጣው ለዉጥ የመልሶ መጠቀም ስራችንን በማሳደግ የሰርኩላር ኢኮኖሚን ለማሳደግ ሰፋፊ ስራዎች በጥናት በተደገፈ መልኩ ለመተግበር እየተሰራ እንደሆነሞ በአጽንኦት ተናግረዋል። በጋና ከጆስፖንግ ግሩፕ የመጡት ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች የልኡካን ቡድን ተወካዮች እንደገለፁት አዲስ አበባ ከቅርቡ ጊዜ ወዲህ እያመጣች ያለዉ የፅዳት ለዉጥ ትምህርት የሚቀሰምበት እንደሆነ ገልፀው በተለይም በጋና ቆሻሻን መልሶ በመጠቀም ወደ ሀብት በመለወጥ በዘርፉ ለበርካታ ዜጎቿ የስራ እድል ለመፍጠርና የተለያዩ ሀገር አቀፍ ካምፓኒዎች በስራዉ ላይ እንዲሰማሩ በማድረግና የመልሶ መጠቀም ካምፓኒዎች በመገንባት ከ50% በላይ የሚመረተዉን ቆሻሻ ወደ መልሶ መጠቀም ስርዓት ዉስጥ ማስገባት መቻሉን ጠቅሰዋል። ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች https://linktr.ee/aacitymanager

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከልዑክ ቡድናቸው ጋር ጣልያን ሮም ገብተዋል። በቆይታቸውም ከጠቅላይ ሚኒስትር ጂዮርጂያ ሜሎኒ ጋር ውይይት ያደርጋሉ።

እንኳን ለዓለም አቀፉ የእሳት አደጋ ሰራተኞች ቀን አደረሳችሁ! እሳት ውስጥ ገብተዉ እሳት ለሚያታጠፉ የሌሎችን ህይወት እና ንብረት ለመታደግ እስከ ህይወት መስጠት ድረስ ዋጋ ለሚከፍሉ ጀግኖቻችን ከዚህ በላይ ክብርና እውቅና ይገባቸዋል ። ከንቲባ አዳነች አቤቤ

የእሳትና አደጋ ስጋት መከላከል ሠራተኞች ደህንነታችን የምትጠብቁ፣ በመስዋእትነት ህዝባችንን የማገልገል ተምሳሌቶች ናችሁ ሲሉ በምክትል ከንቲባ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ አስታወቁ። ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ በዛሬው እለት በዓለምዓቀፍ ደረጃ ለ26ኛ ጊዜ በመዲናችን አዲስ አበባ ለ3ኛ ጊዜ በተከበረው ዓለምዓቀፍ የእሳት አደጋ ተከላካዮች ቀን ላይ ባስተላለፉት መልእክት የአደጋ ጊዜ መከላከል ሠራተኞቻችን በታማኝነት፣ በዲስፕሊን፣ በቁርጠኝነት፣ ፍፁም በሆነ ሰብአዊነትና ሙያዊ መሰጠት ስላገለገላችሁን ክብር እና ምስጋና ይገባችኋል ሲሉ ተናግረዋል። አክለውም መዲናችን አዲስ አበባ እያስመዘገበች ያለው ፈጣን የከተሜነት እድገት እና የኮሪደር ልማታችን የፈጠረው ምቹ የመሠረተ ልማት ዝርጋታ ባስገኛቸው ተጨማሪ መልካም እድሎች ሳቢያ የአደጋ ተጋላጭነት ስጋቱ በእጅጉ መቀነስ መቻሉን አመልክተዋል። ኢንጅነር ወንድሙ አያይዘውም በአሁኑ ወቅት የአደጋ ጊዜ መከላከል ባለሙያዎቻችንን አቅም በማሳደግ፣ ዘመናዊ ቴክኖሎጅን በመጠቀም፣ ለአደጋ ስጋት አጋላጭ የሆኑ ጉዳዮችን በመለየት ተግተን በመስራት እና የህዝባችንን ግንዛቤ በማሳደጋችን በመዲናችን ከጊዜ ወደ ጊዜ የአደጋ ተጋላጭነታችን እየቀነሰ ለመምጣቱ ተጠቃሽ ምክንያቶች እንደሆኑም አስገንዝበዋል። ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ በመልእክታቸው ማጠቃለያም የአለምዓቀፍ የእሳት አደጋ ተከላካዮች ቀንን በመዲናችን ያከብርንበት ዋና አላማም የአደጋ መከላከል እና ህዝባችንን ከአደጋ የመጠበቅ አቅማችን ከማጎልበት ጎን ለጎን የአደጋ ተከላካዮቻችን የትኛውንሞ አይነት አደጋ አስቀድሞ የመከላከልም ሆነ የመመከት አቅምና ብቃታችሁን ከጊዜ ወደ ጊዜ በማሳደግ ካለፈው በበለጠ ተነሳሽነትና ቁርጠኝነት ህዝባችሁን ለማገልገል በድጋሚ ቃላችሁን የምታድሱበት እንደሚሆን ባለን ሙሉ ተስፋና እምነት ነው ሲሉም ተናግረዋል።

እንኳን ለዓለም አቀፉ የእሳት አደጋ ሰራተኞች ቀን አደረሳችሁ! ዛሬ ማለዳ በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ26ኛ በሀገራችን ደግሞ ለ3ኛ ጊዜ እየተከበረ ያለውን የእሳት እና ድንገተኛ አደጋ ሰራተኞች ቀንን በድምቀት አክብረናል። እለቱ በእሳት እና ድንገተኛ አደጋን መቆጣጠር ስራ ወቅት መስዋዕት የሆኑ የአደጋ ጊዜ ሰራተኞቻችንን የምንዘክርበት እና በስራ ላይ ያሉ እሳት ውስጥ ገብተው እሳት የሚያጠፉ ጀግኖቻችንን ደግሞ ክብርና እውቅና የምንሰጥበት ነው። ተቋሙን በሰው ሃይልና በሎጂስቲክ በማደራጀት ዘመናዊ የእሳት አደጋ መከላከል ተቋምን ለመገንባት የጀመርነው ስራ ፍሬ እያፈራ የሚገኝ ሲሆን፣ በኮሪደር ልማት ዘመናዊ መሰረተ ልማት በመዘርጋት አደጋውን ይበልጥ ለመቀነስ በመስራት ላይ እንገኛለን። የእሳት አደጋ መከላከል ሰብአዊነት የተሞላበት እና እሳት ውስጥ በመግባት እሳት በማጥፋት ህይወት የሚታደግበት እንዲሁም ንብረት ለማትረፍ የሚሰራ በጎ ስራ ነው። በከተማችን በጀመርነው የኮሪደር ልማት ስራ እሳትን የምንከላከለው በልማት በመሆኑ 129 የፋየር ሃይድራንቶችን በመዲናችን የተለያዩ አካባቢዎች በመገንባት አደጋውን ለመከላከል ከተማችን ዝግጁ መሆኗን ማረጋገጥ ችለናል። የከተማችን አደጋን የመቋቋም አቅም እንዲጎለብት ጠንክረን እንሰራለን! ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ ከንቲባ አዳነች አቤቤ

መምህራንን ጨምሮ በከተማ አስተዳደሩ የሚገኙ የመንግስት ሰራተኞችን በ25/75 ፕሮግራም የቤት ባለቤት ለማድረግ የሚያስችል የውል ስምምነት ፊርማ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዘዳንት አቶ አቤ ሳኖ እና በአዲስ አበባ ከተማ ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ በወይዘሮ ቅድስት ወልደ ጊዮርጊስ አማካይነት ተካሄደ። በስምምነት ፊርማ መርሀ ግብሩ የአዲስ አበባ ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ ፣ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ እንዲሁም የአዲስ አበባ መምህራን ማህበር አመራሮችና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው አካላት የተገኙ ሲሆን በጉዳዩ ዙሪያ ለተለያዩ ሚዲያዎች ጋዜጣዊ መግለጫ ሰተዋል። የአዲስ አበባ ከተማ ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ ቅድስት ወልደ ጊዮርጊስ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በከተማ አስተዳደሩ ለሚገኙ ቤት ፈላጊ ሰራተኞች በዝቅተኛ የወለድ መጠን በ20 አመት የሚከፈል ብድር በማመቻቸቱ በከተማ አስተዳደሩ ስም ምስጋና አቅርበው ቀደም ሲል ተደራጅተው በመጠባበቅ ላይ የነበሩ ቤት ፈላጊ መምህራን በፕሮግራሙ ቅድሚያ የሚሰጣቸው መሆኑንም አመላክተዋል። የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዘዳንት አቶ አቤ ሳኖ በበኩላቸው ባንኩ በከተማ አስተዳደሩ ለሚገኙ እና ቤት ፈላጊ ለሆኑ የመንግስት ሰራተኞች 25% የሚሆነውን ገንዘብ መቆጠብ ለሚችሉ ሰራተኞች ብድር ለማቅረብ ዝግጅት ማድረጉን ገልጸው ከተማ አስተዳደሩም በፍጥነት መሬት ማቅረብ ከቻለ እና ሰራተኛውም የሚጠበቅበትን ገንዘብ በአግባቡ በመቆጠብ ዝግጁ ከሆነ ባንኩ ብድሩን ለመልቀቅ ዝግጁ መሆኑን በጋዜጣዊ መግለጫው አረጋግጠዋል። ከተማ አስተዳደሩ ቤት ፈላጊ መምህራንን የቤት ባለቤት ለማድረግ ያላሰለሰ ጥረት ሲያደርግ መቆየቱን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ ገልጸው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በ25/75 መርሀ ግብር ለመምህራን ቅድሚያ በመስጠት በዝቅተኛ የወለድ መጠን ብድር በማመቻቸቱ ምስጋና አቅርበው ከተማ አስተዳደሩም ከሊዝ ነጻ የሆነ መሬት ለማቅረብ ዝግጅት ማጠናቀቁን አስታውቀዋል። የዛሬው የስምምነት ፊርማ ከተማ አስተዳደሩ የመምህራንን ጥያቄ ለመመለስ ቁርጠኛ መሆኑን ያረጋገጠበትና ለአመታት በመምህራን ሲጠየቅ የቆየ ጥያቄ ምላሽ ያገኘበት መርሀግብር መሆኑን የአዲስ አበባ መምህራን ማህበር ፕሬዘዳንት አቶ ድንቃለም ቶሎ ሳ ጠቁመው ንግድ ባንክን ጨምሮ የመምህራንን ጥያቄ ምላሽ ለሰጡ አካላት ምስጋና አቅርበዋል።