cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

Ewnet Media

Advertising posts
862
Subscribers
No data24 hours
-17 days
-530 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

Photo unavailableShow in Telegram
በ50ሺህ ብር ዋስትና ከእስር እንዲለቀቁ ተወሰነ‼️ አርቲስት አማኑኤል ሀብታሙ፣ የቴአትር አዘጋጅ ዳግማዊ ፈይሳ እና ፍላጎት አብርሃምን ጨምሮ 17 ግለሰቦች እያንዳንዳቸው በ50 ሺህ ብር ዋስትና ከእስር እንዲለቀቁ ፍርድ ቤት ፈቀደ።ግለሰቦቹ የታሰሩት ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓትን በትጥቅ ትግል ለመቀየር” በመንቀሳቀስ በሚል ነበር፡፡ ዛሬ በጉዳዩ ላይ ብያኔ ለመስጠት የተሰየመው የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ የጊዜ ቀጠሮ ችሎት፤ በመዝገቡ ከተካተቱት 20 ተጠርጣሪዎች ውስጥ አስራ ሰባቱ እያንዳንዳቸው የ50 ሺህ ብር የገንዘብ ዋስትና በማስያዝ ከእስር እንዲፈቱ ትዕዛዝ ሰጥቷል።ያሬድ ገብረፃዲቅ በማኅበራዊ ሚዲያ ስሙ ያያ ዘልደታ፣ ፍስሃ እያዩ እና ጌትነት ታከለ የተባሉት ተጠርጣሪዎች ግን 11 ተጨማሪ የምርመራ ቀናት እንደተፈቀደባቸው ጠበቃ አያሌው ገልጸዋል፡፡
Show all...
👍 1
በትግራይ ክልል ከ122 ሺህ በላይ ተማሪዎች የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና እየወሰዱ ነው‼️ በትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የትምህርት ጥራት ማረጋገጫ ኤጀንሲ ዳይሬክተር ዶክተር ታደሰ ካህሳይ እንደገለጹት፤ የስምንተኛ ክፍል ክልላዊ ፈተናው እየተሰጠ ያለው በ1ሺህ 129 ትምህርት ቤቶች ነው። ፈተናው ዛሬን ጨምሮ ለተከታታይ ሦስት ቀናት እንደሚሰጥም ተናግረዋል። እንደ ዳይሬክተሩ ገለጻ፣ ከተፈታኞች መካከል 62 ሺህ 732 የሚሆኑት ሴት ተማሪዎች ናቸው። ተማሪዎቹ ፈተናውን በተረጋጋ ሁኔታ እንዲወስዱ አስቀድሞ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራ መሰራቱን ተናግረዋል። የፈተና ኩረጃን ለመከላከል ተቆጣጣሪዎች በበቂ ሁኔታ መመደባቸውን ጠቁመው፣ ለፈተናው ሰላማዊነትም የጸጥታ አካላት የበኩላቸውን እየተወጡ መሆኑን መግለጻቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
Show all...
Photo unavailableShow in Telegram
መንግሥት ባለፈው ሳምንት ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያቀረበው "የንብረት ማስመለስ" አዋጅ፣ ከውጭ በተላከላቸው ገንዘብ ሃብት ያፈሩ ዜጎች ገንዘቡን የተረከቡበትን ደረሰኝ ለፍርድ ቤት አቅርበው ካላረጋገጡ መንግሥት ንብረታቸው እንዲወረስ ሥልጣን የሚሰጥ እንደኾነ ሪፖርተር ዘግቧል‼️ ማንኛውም ሰው ሊታወቅ ከሚችል ገቢው በላይ ሃብት አፍርቶ የምንጩን ሕጋዊነት ማረጋገጥ ካልቻለ፣ መንግሥት ንብረቱን የመውረስ ሥልጣን እንዳለው ረቂቅ አዋጁ እንደሚደነግግ ዘገባው አመልክቷል። ዓቃቤ ሕግ ምንጩ አይታወቅም ብሎ ለሚጠረጥረው 5 ሚሊዮን ብር ለሚገመት ንብረት 10 ዓመት ወደኋላ ሂዶ ክስ ማቅረብ እንደሚችልም ረቂቅ አዋጁ ይፈቅዳል ተብሏል።
Show all...
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ነቀምቴ በረራውን በይፋ ጀምሯል‼️ የነቀምቴ ጉዲና ቱምሳ አውሮፕላን ማረፊያ የበረራ ማስጀመሪያ ሥነ-ሥርዓት በዛሬ እለት ተከናውኗል።
Show all...
እንኳን ለ1445ኛው የኢድ አል አደሃ (አረፋ) በዓል በሰላም አደረሳቹ!!! ኢድ ሙባረክ!
Show all...
​​ነገ አዲስ አበባ ዝግ የሚሆኑ መንገዶች ይፋ ሆነዋል‼️ የ1445ኛው የኢድ አል አድሃ (አረፋ) በዓል ነገ ይከበራል። የኢድል አል አድሃ (አረፋ) በዓል ሶላት ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅም ለተሽከርካሪ ዝግ የሚሆኑ መንገዶችን የአዲስ አበባ ፖሊስ አሳውቋል። የሶላት ስነስርዓቱ የሚካሄደው በአዲስ አበባ ስታዲዮምና በዙሪያው በሚገኙ ዋና ዋና መንገዶች ላይ ነው። ይህ ተከትሎ ከለሊቱ 11:00 ሰዓት ጀምሮ የሶላት ፕሮግራሙ እስከሚጠናቀቅ ድረስ መንገዶች ለተሽከርካሪ ዝግ ይሆናሉ። በዚህም መሰረት ፦ - ከፒያሳ በቸርችል ጎዳና ወደ ለገሃር የሚወስደው መንገድ ቴዎድሮስ አደባባይ ላይ - ከጎተራ ማሳለጫ ወደ ስታዲዮም የሚወስደው አጎና ሲኒማ ላይ - ከሜክሲኮ ወደ ለገሃር የሚወስደው መንገድ ሜክሲኮ አደባባይ ላይ - ከብሔራዊ ቤ/መንግስት ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ፓርላማ መብራት ላይ - ከኦሎሚፒያ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ኦሎምፒያ አደባባይ ላይና ታች እንዲሁም ግራና ቀኝ - ከመገናኛ ወደ ኡራኤል ቤተ ክርስቲያን የሚወስደው መንገድ 22 መስቀለኛ መንገዱ አካባቢ - ከጥቁር አንበሳ ሼል ወደ ለገሀር የሚወስደው መንገድ ጥቁር አንበሳ ሼል አጠገብ - ከሲግናል እና ከአቧሬ ወደ ካዛንቺስ የሚመጣው መንገድ አቧሬ ሴቶች አደባባይ ላይ - ከመስቀል ፍላወር ወደ መስቀል አደባባይ የሚመጣው መንገድ ጋዜቦ አደባባይ ላይ - ከቄራ በአዲሱ መንገድ ወደ ቂርቆስ ቤ/ክርስቲያን የሚወስደው መንገድ ቂርቆስ ቤ/ክርስቲያን መገንጠያ ላይ - ከጌጃ ሰፈር በሰንጋተራ ወደ ለገሐር ለሚመጡ አሽከርካሪዎች ሰንጋ ተራ 40/60 የጋራ መኖሪያ ቤት አካባቢ - ከአብነት በጌጃ ሰፈር ወደ ብሔራዊ ቴአትር የሚወስደው መንገድ ጎማ ቁጠባ አጠገብ - ከተክለ ሐይማኖት አካባቢ በሜትሮሎጂ ወደ ብሔራዊ ቴአትር ሜትሮሎጂ መ/ቤት ላይ - ከተክለ ሐይማኖት አካባቢ በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል የኋላ በር ወደ ብሔራዊ ቴአትር ለሚሄዱ ጥቁር አንበሳ ሼል ድሬንስ አካባቢ - ከተክለ ሐይማኖት አካባቢ በጎላ ሚካኤል ውስጥ ለውስጥ ወደ ለገሐር ለሚሄዱ ጎላ ሚካኤል መስቀለኛው ላይ ይለፍ ለሌላቸው ተሽከርካሪዎች ከለሊቱ 11:00 ሰዓት ጀምሮ ዝግጅቱ እስከሚጠናቀቅ ድረስ ለተሽከርካሪ ዝግ ይሆናሉ። ህብረተሰቡ ይህን ተገንዝቦ የትራፊክ ፖሊስ አባላት በሚጠቁሙት አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀም ጥሪ ቀርቧል።
Show all...

Photo unavailableShow in Telegram
በምስራቅ ጎጃም ዞን ከ20 ሺህ ገደማ የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች በጦርነት ምክንያት 577 ተማሪዎች ብቻ ይፈተናሉ‼️ በአማራ ክልል አንድ ዓመት የሆነው የትጥቅ ውጊያ በትምህርት ላይ ከፍተኛ ቀውስ መፍጠሩ ተመላከተ። ከክልሉ የትምህርት ቢሮ የተገኘው መረጃ እንደሚያሳየው በአማራ ክልል ምስራቅ ጎጃም ዞን ብቻ ከ996 ትምህርት ቤቶች ውስጥ በስራ ላይ የሚገኙት 32ቱ ብቻ ናቸው። በ2016 የትምህርት ዘመን ከአንደኛ እስከ ሁለተኛ ደረጃ ድረስ ከ539 ሺህ 996 በላይ ተማሪዎች ወደ ትምህርት ገበታ ይገባሉ ተብሎ ቢጠበቅም ወደ ትምህርት ቤት የመጡት ከ13 ሺህ አይበልጡም ተብሏል። በብሔራዊ እና ክልላዊ ፈተናዎች ላይም ግጭቱ መስተጓጎል የፈጠረ ሲሆን የ6ተኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና 791 ትምህርት ቤቶች 42 ሺህ የሚጠጉ ተማሪዎች መፈተን ቢኖርባቸውም ለፈተና የሚቀመጡት ከ12 ትምህርት ቤቶች የመጡ 506 ተማሪዎች ብቻ ናቸው። 38 ሺህ 203 ተማሪዎች የ8ተኛ ክፍል ፈተና እንደሚፈተኑ ቢጠበቅም በዞኑ ባለው ከፍተኛ ጸጥታ ችግር ሳቢያ መፈተን የሚችሉት 431 ተማሪዎች ብቻ መሆናቸው ተገልጿል። ከ19 ሺህ 657 የ12ተኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ተፈታኞች መካከል ለፈተና ዝግጁ የሆኑት 577 ተማሪዎች ብቻ ናቸው።
Show all...
Photo unavailableShow in Telegram
ግንቦት 20 ከካላንደር ላይ ተሰረዘ‼️ ዛሬ በፓርላማ የፀደቀው የህዝብ በዓላት እና የበዓላት አከባበርን ለመወሰን የወጣው አዋጅ በልማድ ሲከበር የቆየውን ግንቦት 20 ብሔራዊ በአልነቱ አስቀርቷል፡፡  የሰማዕታትን ቀን (የካቲት 12) እና የብሔር ብሔረሰቦች ቀን (ህዳር 29 ) መስሪያ ቤቶች ክፍት ሆነው፤ ታስበው ይውላሉ ተብሏል። በሀገር አቀፍ ደረጃ የሰንደቀ ዓላማ ቀን፣ የመከላከያ ቀን፣ የሴቶች ቀንና ሌሎችም በዓላት ታስበው የሚውሉ ናቸው ተብሏል፡፡ አዋጁ ተከብረው በሚሉ ብሔራዊ እና ሃይማኖታዊ በዓላት ለሕዝብ አገልግሎት ክፍት መደረግ አለባቸው ያላቸውን ተቋማትን ዝርዝር አስቀምጧል፡፡ በዚህም የእለት ከእለት ኑሮ አስፈላጊ የሆኑ የውሃ፣ የመብራት፣ የስልክ እና መሰረታዊ አገልግሎቶች የጤና ተቋማትና መድሃኒት ቤቶች ለሕዝብ ደህንነት አስፈላጊ የሆኑ የደህንነት ተቋማት የእሳት አደጋ፣ መከላከል አገልግሎትና የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎቶች እንዲሁም ነዳጅ ማደያዎች ክፍት ሆነው እንዲውሉ በአዋጁ ተቀምጠዋል፡፡
Show all...
PRICK አዲስ ኤርድሮፕ ነው በቅርቡ ነው የጀመረው ቶሎ ጀምሩ በ SOLIANA የሚደገፍ ነው ካሁኑ ኢትዮጲያኖች ደረጃውን ተቆጣጥረውታል ለመጀመር ምትፈልጉ ሊንክ👇 Click Here
Show all...
👍 1
Photo unavailableShow in Telegram
PRICK አዲስ ኤርድሮፕ ነው በቅርቡ ነው የጀመረው ቶሎ ጀምሩ በ SOLIANA የሚደገፍ ነው ካሁኑ ኢትዮጲያኖች ደረጃውን ተቆጣጥረውታል ለመጀመር ምትፈልጉ ሊንክ👇 Click Here
Show all...
Choose a Different Plan

Your current plan allows analytics for only 5 channels. To get more, please choose a different plan.