Medan tube/መዳን ቲዩብ
Open in Telegram
በባህላዊ ህክምና በቁርአን ህክምና በጤና ነክ ጉዳይ አቶክሮ የሚሰራ ተቋም ነወ(የማማከር አገልግሎት አንሰጣለን)መድሀኒቶችን ያላችሁበት ድረስ እንልካለን 093 603 8353 ይደውሉ
Show more824
Subscribers
No data24 hours
-37 days
+1630 days
Posts Archive
በጫማ ላይ የሚሰሩ ሲህሮች ሲጋለጡ
ሲህሮች ከዚህም በላይ በየቀኑ ይፈበረካሉ፡፡ ከነኛም ውስጥ ፍፁም አይደለንም እና በጥናቶቻችን ስለደረስንባቸው ብቻ እናወራለን፡፡ ያ ማለት ግን ሌላ አይነት ምልክቶች የሏቸውም ማለትን አያስይዝም፡፡
ምልክቶቻቸው!!
1.የውስጥ እግር ማሳከክ፡፡ በአንድ ወይም በሁለቱም ለይቶ የውስጥ እግር መብላት፡፡ ግዜን ጠብቆ አልያም በተከታታይ፡፡
2.የውስጥ እግር ማቃጠል፡፡ ይህም ሁለት ወይም አንዱን ብቻ እግር መርጦ በተለይ ምሽት ለሊት እና ጥዋት ላይ ማቃጠል፡፡ ህመም ባይኖረውም መለብለቡ እረፍት ይነሰል፡፡
3.የእግር መውጋት፡፡ ይህ የእግር ውጋት ከመሃል አንስቶ ጭንቅላት ድረስ የሚሰማ ቢሆንም አንዳንዴ እዚያው ስመሙ ሊያልቅ ይችላል፡፡
4.የጉልበት መታመም፡፡ ይህ ህመም ከየት እንደመጣ አናውቀውም አንዳንድ ግዜ ብቻ ነው የሚመን፡፡ ጉልበታችንን ብንራመድበትም ችግር የለውም ግና ህመሙ ክፉ ነው፡፡
5.የእግር ማበጥ፡፡ ይህ የእግር ማበጥ ታድያ ብዙ አይነት ምልክቶችን ሊያዝ ይችላል፡፡ ይህም አንድ የ ጉበት የ ኩላሊት እና የልብ ህመም ምልክቶችን፡፡ ይህን በቀላሉ ይለዩ ዘንድ፡፡ እብጠቱ ከእግር ጀምሮ ወደላይ የሚመጣና አይን ሳይቀር የሚያብጥ ከሆነ፡፡ ይህ ከሲህር አደለም ይህ የኩላሊት በሽታ ምልክት ነው፡፡ እግር ብቻ አብጦ እስከ ጉልበት ያለምንም ህመም ብሎም ቶሎቶሎ መተንፈስ ድካም ካለ ይህ የልብ በሽታ ነውና ባፋጣኝ ወደ ህክምና ያምሩ፡፡ የጉበት በሽታም የሰውነት ከለር መለወጥን ያመጣል፡፡ ሆድ ያብጣል እግርም ያብጣል፡፡ ይህም ከዚህ የሲህር በሽታ ጋር የሚገናኘው ነገር የለም፡፡ እነሆ የዚህ ሲህር በሽታ እግር ሲያሳብጥ እስከ ጉልበት ብቻ ሁኖ መለብለብ አለው፡፡ ሲነኩት ወደ ውስጥ ስምጥ ይላል እግር፡፡ መራመድ አይችሉም በጣም ህመም አለው፡፡ ግዜን ጠብቆም ነው የሚመጣው፡፡
6.የቆዳ ቅርፊቶች መነሳት፡፡ ይህ ከመሆኑ በፊት ሰውነት በጣም ያሳክከናል፡ ይህ ሰውነት ሲያሳክከን ከግድግዳ ጋር እንኳ መፋተግ ልምዳችን ይሆናል፡፡ ከዚያም ልክ እንደ እባብ በአመት አንዴ ቅርፊታችንን እንለውጣለን፡፡
7.የጸባይ መለዋወጥ ብቻ ማውራት መለፍለፍ፡፡ ብሎም መቀባጀር ይኖራል፡፡ ይህም በታማሚ ቤተቦች ላይ ላይ ችግር ይፈጥራል፡፡
8.በህልም መቃዠት ቅዠቱ ልክ የለውም ድንገተኛ ትኩሳት ብሎም ለሊት ላይ መንቀጥቀጥ መጮህ የዚህ ምልክቶች ናቸው፡፡
9.በእንቅልፍ ልብ መራመድ በእንቅልፍ ልብ መደባደብ መሳደብ፡፡
10.ተኝተው ሲነሱ ሰውነታቸው በልዞ ማግኘት አይናቸው አብጦና ቀልቶ ማግኘት፡፡
11.ለሊት የመታነቅ አይነት ምልክቶች አየር ቀጥ የማለት አይነት አዝማሚያዎች ይኖራሉ፡፡
ይህን ምልክት ከ 2 በላይ የሚያስተውሉ ከሆነ ፈጥነው ያናግሩን ፡፡
ቻናላችንን ለኡማው ያስተዋውቁ 👇
https://t.me/medantube36
ህክምና ለማግኘት👇
@Medantube1
ህክምና ለማግኘት👇
0936038353
👆
የፀባይ መቀያየርና ሲህር !
ከምልክቶቹ ውስጥ አንደ በአንድ እንይ
1.አንድ ሰው ከመቅስፈት ሴጣን ይሆንብናል ሲስቅ ሲጫወት የነበረ ሰው እሳ ይጎሳ ፡፡ ይናደዳል ይናገራል ይበሽቃል፡፡ እናንተን ያደናግራል፡፡ ይህ ፀባይ እወቁ የሲህር መለያ ፀባይ ነው፡፡ እንዴት እንደሆነ እናስረዳ፡፡ አሁን ከባለቤትሽ ጋር ሰላም ሆነሽ እየተሳሳቅሽ እያለሽ ድንገት ዞር ብለሽ መለስ ስትይ መነጫነጭ እንዲህ ሆነ እንዲህ አደረግሽኝ እያለ ማበድ ይጀምራል፡፡ ብዙ ግዜ እንደ ሲህሩ መጠን የንዴት ወይም የመናደጃ ሰአቱ ይለያያል አንዳንዴ ቀኑን ሙሉ ሊዘጋሽ ይችላል አንዳንዴ ደግሞ ወድያው ይመለሳል፡፡ ይህ በርሱ ላይ ሸይጧኑ ተቆጣጣሪ ሲሆን ነውና አደራ በዚህ ሰአት አንቺ ብሶትሽን አታሰሚ ወይም አታሰማ፡፡
2. በየመሃሉ ቁና ቁና መተንፈስ፡፡ ይህ መተንፈስ የህመም አልያም የድካም ስሜት ሁኖ አይደለም፡፡ ይህ እስትንፋስ ተበሳጭቻለው ተናድጃለው የሚል አይነት ነው፡፡ በዚህ ሰአት ባልሽ አልያም ሚስትህ አኩርፋለች፡፡ በምን እንዳኮረፉ ጀሊሉ ብቻ ይወቀው፡፡ ግራ ያጋቡሃል፡፡ ምንም ሳትገናኙ አኩርፈው ውለው ያድራጉ፡፡
3. ባንተ አልያም ባንቺ ላይ ንዴትን ማልቀስ መበሳጨትን ሲያዩ ውስጣቸው ይረካል፡፡ ይህ አሸሚ ሁኖ እናገኘዋለን ከሲህሩ ጋር ለመለየት፡፡ ምክንያቱም የናንተን መበሳጨት ከመፈለጋቸው ሰአትና ደቂቃ በፊት ምን ስታደርጉ ነበር የሚለውን መገምገም ያስፈልጋል፡፡ ግና ከመሬት ተነስቶ የሚያኮርፍ የሚናደድ ከሆነ ይህም የሲህር መገለጫ ነው፡፡
4.ድንገት ኮምፕሌን ማቅረብ ወይም ሂስ ማቅረብ፡፡ ይህን አላደረግሽልኝም ይህን አላደረግክልኝም ሲሉ ነጋ ጠባ መጨቃጨቅ ፡፡ እዚህ ላይ ነው ብዙሃን የሚሸወዱት ይህ በፍፁም የሲህር ምልክት ሊሆን አይገባም፡፡ አንቺ ወይም አንተ የፈለገ ነገር ቢሆን ሙሉ አትሆኑም አንድም ሰው ይህ አልተደረገልኝም ሲል ቅሬታ የሚያቀርብ ከሆነ በዚያ ረገድ ላይ የሚነሱ ሂሶችን አስታኮ ሌሎች ቅሬታዎች እንዳሉት መረዳትና ያን ነገር መፍታት እንጂ ሲህር ሊሆን አይቻለውም፡፡
5. በፊት ባለቤቴ ገላዋን በየግዜው ትታጠብ ነበር አሁን መሽተት ጀምራለች፡፡ ይህ በፍፁም የሲህር ጥቃትን አያካትትም፡፡ አዎን ሷሂሮች ቆሻሾች ናቸው፡፡ ግና የሚስትህ ወይም የባልሽ መለወጥ የሚያመላክተው አንተን ወይም አንቺን ባገኙ ሰአት የነበራቸው ማንነትን ማጣት ይሆናል ፡፡ ይህም ከአንዛይቲ ወይም ጭንቀት ጋር የሚመጣ አልያም የስራ መደራረብ እና ስንፍና ሲፈጠር ይሆናል፡፡ በዚህ ግዜ ታድያ ሌሎች የሲህር ባህሪዎች የሚታዩበት ከሆነ ይህ ገባሪ ምልክት እንጂ እራሱን ችሎ የሲህር ምልክት ሁኖ መቆም አይቻለውም ፡፡ አልሃምዱሊላህ ለዘመናት ስናጠናቸው የምንቆያቸውን ትምህርቶች እናንተ በቀላሉ በቀልብ ዶክተር ላይ በማግኘታችሁ፡፡
6.ሱሶች ላይ ጥገኛ መሆን፡፡ ይህ የሩቅያህ ሊቃውንቶች እንደነ ዶክተር አቡ ፈርሃንን ጨምሮ በዚህ ላይ ብዙ ፋላሲዎችን አካተዋል፡፡ ሊገናኝም ወይም ላይገናኝም ይችላል የሚሉ እንድምታዎችን ይዘው በሰፊው ጥናቶችን አቅርበዋል፡፡ ሱሶች ከሲህር በፊት አልያም ከሲህር ኋላ ወይ ደግሞ በራሱ የጠነከረ ሱስ አልያም ድንገት የመጣ ሱስ በሚል ከፋፍለውታል፡፡ ብሎም ብዙ አይነት መከፋፈሎችን አድርገው ትንታኔ ሰጥተዋል፡፡ ግና ላንተና ላንቺ በቀላሉ ትረዱት ዘንድ ሱስ ወጣትነትን ውትድርናን ወንደላጤነትን ተከትሎ የሚመጣ ከሆነ ከሲህር አይደለም፡፡ ግና ሱስ ድንገት የሚመጣ አልያም ከአእምሮ መላሸቅ ጋር የሚከተል ከሆነ ብቸኛ የሲህር ገላጭ ምልክት ነው፡፡
7.ግዜውን በእንቶ ፍንቶ ሶሻል ሚድያ ላይ ማሳለፍ፡፡ ይህ ከሲህር ነው ወይ፡፡ ይህ ከሲህር ሊሆን ይችላል ላይሆንም ይችላል፡፡ ልክ ከላይ እንደገለፅነው ነው፡፡ ብዙ ትንታኔዎች ያስፈልጋቸዋል፡፡ በዚህም ላይ እንደነ ኡስታዝ አልዘንዳኒ እና ሌሎችም በርካታ ኡስታዞች በጥናታቸው ላይ ባካተቱዋቸው ፅሁፎች ስር ብዙዎችን የማያስማሙ ሃሳቦች እንዳሉም ጭምር እንዲህ ሲሉ ጠቅሰውታል ‹‹ብዙ ሩቅያህ ሊቃውንቶች ሶሻል ሚድያ በራሱ እራሱን የቻለ ሲህር ነው! ሲሉ ያምናሉ፡፡ ያም በአይናችን ልናየው በማንችለው አንዳች መተት አንድን ነገር ሲሰራ ማየት በራሱ ሲህር ነው አስማተኞች ሲጠቀሙበት የነበረ ስልት ነው ብለው ሲደመድሙ አንዳንዶች ደግሞ የሚሰራትን አኳኋን ካወቅን እና እንዴት እንደሚሰራ ከተረዳን ሲህር ሊሆን አይችልም ባይ ናቸው፡፡ በመካከል ያለውን የሃሳብ አለመስማማት ማስፋት ወይም ማጉላት አንሻም፡፡ ይሁንና የኛንም እይታ መግለፅ አንፈልግም፡፡ ግና አንባቢ በራሱ እንዲፈርደው ትተናል፡፡
8.ሽንትቤትን ረጅም ሰአት መቀመጥ፡፡ ይህ መቀመጥ ሲባል ለሰገራ መቀመጥ ብቻ አይደለም በሲህር አልያም በጅን የተለከፉ ሰዎች ሽንትቤት ረጅም ሰአት ሞባይላቸውን ይዘው ይቆማሉ፡፡ አልያም በባዶ ሃሳብ እያወረዱ እያወጡ ይቆማሉ ወይም ረጅም ሰአት ያለምንም ስራ ወይ የሚነበቡ ነበሮችን ይዘው ይቀመጣሉ፡፡ ይህ ከሲህር ብቻ ሳይሆን ከጅን ጥቃት መሆኑን ያመላክታልና፡፡ ይህ አይነት ጸባዮች ሲኖሩ እነርሱን ማረም የተሸለ ነው፡፡ አሏህም ሁሉን ያውቃል፡፡ ወሰላሙ አለይኩም ወራህመቱሏህ
‹‹ ወሰን ገላ፤ ጨንገሬ ፤አባ መላ ››
መጥፎ ጅኖችን አዛዦችና የሸይጧን ሰረገላን ተቆጣጣሪ ጠንቋዮች ሴራ!
ቻናላችንን ለኡማው ያስተዋውቁ 👇
https://t.me/medantube36
ህክምና ለማግኘት👇
@Medantube1
👆
ህክምና ለማግኘት👇
0936038353
👆
ብጉር ( ACNE)
ብጉር እጅግ የተለመደ እና አብዛኞቻችንን የሚያጠቃ የቆዳ ችግር ነው።
በአብዛኛው በጉርምስና ጊዜ የሚመጣው ብጉር የሆርሞን መለወጥን ተከትሎ ነው።
የብጉር ምልክቶች እንደ አይነቶቻችው ይለያያሉ።
1, ቀዳዳዎቻቸው የተደፈኑ ( ነጭ የሚሆኑ ብጉሮች)
2,ቀዳዳዎቻቸው የተከፋቱ (ጥቁር ብጉሮች)
3,ቁስለት ያለው ብጉር ( የተቆጣ ብጉሮች)
4,መግል የያዙ ብጉሮች ( የባክቴርያ ኢንፌክሽን ያለው ብጉሮች)
5,ጠጣር ብጉር ( ትልቅና የህመም ስሜት ያላቸው ብጉሮች) ናቸው።
ብጉርን የሚያስከትሉ ሁኔታዎች ምንድን ናቸው?
* የሆርሞኖች በሰውነታችን መለዋወጥ
*መድሃኒቶች በተለይም ሆርሞኖችን የያዙ ከሆኑ
*ቅባትነት ያላቸውን መዋቢያዎችን መጠቀም
*ጭንቀት
*የወር አበባ መምጣት ናቸው።
ለብጉር ተጋላጭነትን የሚጨምሩ ሁኔታዎች ምንድን ናቸው?
*እድሜ
ሁሉም የእድሜ ክልል ላይ የሚገኙ ሰዎች የሚጠቁ ቢሆንም የጉርምስና እድሜ ላይ ገን በብዛት ይስተዋላል።
*በዘር የመተላለፍ እድሉ ከፍተኛ ነው።
*ቅባቶች
ቅባቶችን መጠቀም ይህን ሊያስከትል ይችላል።
*ጭንቀት
ጭንቀት ብጉር እንዲባባስ ስለሚያደርግ ማስወገድ ተገቢ ነው።
ብጉር እንዳይባባስ ለመቆጣጠር ምን ማድረግ እንችላለን
*ብጉር የወጣበትን ቦታ በሰሱ ማጽዳት በውሃና በሳሙና መታጠብ (በቀን ሁለት ጊዜ)።
*ቅባታማ የሆኑ የመዋቢያ ውጤቶችን መጠቀምን ያስውግዱ።
*በብጉር የተጎዳ ቆዳዎን በእጅዎ አይነካኩ።
*ከባድ የጉልበት ስራ ከሰሩ በሗላ ገላዎን እና ፊትዎን ይታጠቡ።
ብጉር ቆዳዎን እያጠቃ የሚያስቸግርዎ ከሆነ ህክምናውን ለማግኘት
0936038353
@Medantube1
ቻናላችንን ለሌሎች ሼር ያድርጉ
https://t.me/medantube36
የመንደድ ሲህር፡፡
ይህ ሲህር ቀላል የሚባሉ አይነት ሲሆን ቀላል ያደረገውም የህመሙ ቀላል መስሎ ህይወትን የማመሰቃቀሉ ሁኔታ እንጂ ለህክምናው ከባድ ናቸው፡፡
1.የውስጥ እግር መቃጠል፡፡ ይህም ብዙውን ግዜ ማታ ላይ ይጨምራል፡፡
2..የሆድ መቃጠል፡፡ ይህም ሆድ ከምንግዜውም በላይ ሞቅታ ይኖረዋል፡፡ በቀዝቃዛ ነገር ሲነካም እጅግ ያማል፡፡
3.ከሚባለው በላይ የጨጓራ ተጠቂ መሆን፡፡ በምንም መልኩ በህክምና አልድን ማለት ወተት ቢጠጡ መድሀኒት ቢቅሙ ሲነዱ መዋል፡፡
4.የመላ ሰውነት መንደድ፡፡ ይህ ብዙውን ግዜ ከመግሪብ ቡሃላ የሚፈጠር ሲሆን በቀዝቃዛ ውሃ እንኳን ታጥበው ሙቀቱ አይወጣላቸውም፡፡
5.የአፍ መሽተት ይህን በምንም መደበቅ አይችሉም ማስክ እንኳ ቢያደርጉ በራሳቸው የአፍ ሽታ እራሳቸው ይደነግጣሉ፡፡
6.የራስ ሙቀት ይህ ሙቀት ከራስ ምታት ጋር አይገናኝም ነገር ግን ብዙ ላቦት አለው፡፡ እራሳቸውም በቀዝቃዛ ቦታ ላይ ቢያገኙት ከሌላው በተለየ ሁኔታ መጨስ ይጀምራል፡፡
7.በትንሽ ነገሮች መበሳጨት ሰውን ለመደብደብ መሞከር፡፡ ያናደዳቸው ሰው ተጎድቶ ካላዩ አይወጣላቸውም፡፡
8.እነኚህ ሰዎች እራሳቸውን ሊስቱ ይችላሉ ነገር ግን ከ ሶስት ቀን ወይም ከዛ በታች መንቃት አይችሉም፡፡
9.ሰዎችን መቅረብ በጣም ይጠላሉ ትንሽ ሲርቁ ደግሞ ሰዎችን በጣም ይናፍቃሉ፡፡
10. ሁሌም ተበዳዮች ናቸው ተበደልኩ ብለው ማውራት ደስ ይላቸዋል፡፡
ቻናላችንን ለኡማው ያስተዋውቁ 👇
https://t.me/medantube36
ህክምና ለማግኘት👇
@Medantube1
👆
ህክምና ለማግኘት
0936038353
https://t.me/medantube36
የሳምባ ሲህር፡፡
ይህ ሳምባ ላይ የሚደገም ሲህር ብዙ ግዜ አጠገቦ ጭሳጭስ በማጨስ የሚሰራ ሲሆን ልብም ላይሉት ይችላሉ፡፡ ጎረቤት እንኳ በሚያጨሰው ጭስ ለርሶ ከተባለ በጭስ ይደርሶታል፡፡ ምልክቶቹ፡፡
1.ብን ብን የምትል ስሜት ጉሮሮ ስል መከርከር፡፡
2.ደም ማሳል፡፡ ንፍጥ ቢምጉ እንኳ ደም መሆን፡፡
3.ድድ መድማት ያልተነካ ድድ ሲደማ ይታወቆታል፡፡
4.ጥቁር አክታ መኖር አክታዎ ከነ አካቴው ይጠቁራል፡፡
5.ሲተነፍሱ ሲጥ ሲጥ የሚል ድምፅ ይሰማዎታል ፡፡ ሀኪም ቤት የሽሮፕ መአት ቢደረድሩ ይህሽ ሲጥ ሲጥ የምትል ድምፅ አትጠፋም፡፡
6.መተንፈስ የሚያቅቶት አጋጣሚ አለ በተለይም ከሽንትቤት በሚወጡበት እና በሚገቡበት ሰአት ይታፈናሉ፡፡
7.ሳሎ ከቀን ወደ ቀን አንዴ ደረቅ አንዴ እርጥብ እየሆነ መቸገር እየጨመረ እየቀነሰ መቸገር፡፡
8.በተደጋጋሚ የሳንባ ምች ተብለው መታከም ይሑንና ህመሙ የለቀቀ ይመስላል ተመልሶም ይመጣል
ይህ ምልክት ካለቦት አፋጣኝ ያናግሩን፡፡ ቁርአን ይቅሩ የትኛውንም አያት በቀን ቢያንስ በተደጋጋሚ ይቅሩ፡ ከ 4 በላይ ምልክት ካለቦት ግን ባፋጣኝ ወደ ሩቅያህ ህክምና ያምሩ፡፡
ቻናላችንን ለኡማው ያስተዋውቁ 👇
https://t.me/Medan122
ህክምና ለማግኘት👇
0936038353
ህክምና ለማግኘት
@Medantube1
የሳምባ ሲህር፡፡
ይህ ሳምባ ላይ የሚደገም ሲህር ብዙ ግዜ አጠገቦ ጭሳጭስ በማጨስ የሚሰራ ሲሆን ልብም ላይሉት ይችላሉ፡፡ ጎረቤት እንኳ በሚያጨሰው ጭስ ለርሶ ከተባለ በጭስ ይደርሶታል፡፡ ምልክቶቹ፡፡
1.ብን ብን የምትል ስሜት ጉሮሮ ስል መከርከር፡፡
2.ደም ማሳል፡፡ ንፍጥ ቢምጉ እንኳ ደም መሆን፡፡
3.ድድ መድማት ያልተነካ ድድ ሲደማ ይታወቆታል፡፡
4.ጥቁር አክታ መኖር አክታዎ ከነ አካቴው ይጠቁራል፡፡
5.ሲተነፍሱ ሲጥ ሲጥ የሚል ድምፅ ይሰማዎታል ፡፡ ሀኪም ቤት የሽሮፕ መአት ቢደረድሩ ይህሽ ሲጥ ሲጥ የምትል ድምፅ አትጠፋም፡፡
6.መተንፈስ የሚያቅቶት አጋጣሚ አለ በተለይም ከሽንትቤት በሚወጡበት እና በሚገቡበት ሰአት ይታፈናሉ፡፡
7.ሳሎ ከቀን ወደ ቀን አንዴ ደረቅ አንዴ እርጥብ እየሆነ መቸገር እየጨመረ እየቀነሰ መቸገር፡፡
8.በተደጋጋሚ የሳንባ ምች ተብለው መታከም ይሑንና ህመሙ የለቀቀ ይመስላል ተመልሶም ይመጣል
ይህ ምልክት ካለቦት አፋጣኝ ያናግሩን፡፡ ቁርአን ይቅሩ የትኛውንም አያት በቀን ቢያንስ በተደጋጋሚ ይቅሩ፡ ከ 4 በላይ ምልክት ካለቦት ግን ባፋጣኝ ወደ ሩቅያህ ህክምና ያምሩ፡፡
ቻናላችንን ለኡማው ያስተዋውቁ 👇
https://t.me/medantube36
ህክምና ለማግኘት👇
0936038353
ህክምና ለማግኘት
@Medantube1
https://t.me/medantube36
የፊንጢጣ መድማት vs ሲህር
ምልክቶቹ፡፡
1.በመቀመጫ ላይ ማሳከክ!! ይህም በግራ አልያም በቀኝ ጎን አልያም ፊንጢጣ ላይ ይሆናል፡፡ እስካልደማ ድረስ እርካታን አይሰጥም፡፡
2.ወንዶችን የሚያደናግጥ ምልክት ይሆናል፡፡ ቦታውን በሚያኩ ግዜ ስሜት መቀስቀስ፡፡
3.በስብሰባ ወቅት ሰዎች በተቀማመጡበት ወቅት ድንገት መጥቶ ማሳከክ ፡፡
4.ዙርያው መመርቀዝ ልክ እንደ ቡጉንጅ ! ግና በጣም ይጠዘጥዛል፡፡
5.ልክ የሌለው እራስ ምታት! እራስ ምታት መጣም ይፈጠራል፡፡
6.ሽንትቤት ከተጠቀሙ ኋላ ጡሃራ ሲያደርጉ የፊንጢጣ መቃጠል መንገብገብ፡፡ ውሃ እንዳይነካን መፈለግ፡፡
7.የሆድ ድርቀት ውስጣችን የሚወጣው ነገር ቆርጦን የሚወጣ ያህል መሰማት፡፡
8.የሽንትቤት ብዙ ግዜ መቀመጥ! ሽንት ቤት ውስጥ ማልቀስ፡፡ ሽንትቤት ውስጥ ብቻን ማውራት ረጅም ግዜ ኤሌክትሮኒክስ መጠቀም!!
9.ከሰው ጋር አለመስማማት፡፡ በትንሽ ነገር ቁጡ መሆንና ሰውን መበደል፡፡ ያም ታካሚውን የሚስደስት ይሆናል፡፡
10.የጥፍር መንጣት ፡፡ ይህ ሲባል ጥፍሮች ስር እጅግ በጣም ንፁህ ወይም ነጭ ምልክት መፍጠር፡፡
11.ጥዋት ላይ እጅግ በጣም አርፍዶ መነሳት፡፡ አላርም ቢጮህ አለመስማት፡፡ ሱብሂን ማምለጥ ለሌላው የሚሰማ አዛን ለኛ አይሰማንም፡፡
12.የብልት መሽተት፡፡ ሴት ላይ ከማሳከክ ጋር የሚሸት ሲሆን ወንድ ላይ ከስር ያሉ የዘር እንቁላሎች ይሸታሉ፡፡ ሽታው ገና ሱሪ ሲፈታ ያስታውቃል፡፡
13.የቡጉር መብዛት ፡፡ ይህ ድንገት ከነኚህ አይነት ምልክቶች ጋር ይመጣል፡፡
14.የወገብ ህመም፡፡ ይህ ከስር ወደላይ የሚመጣ አይነት ህመም ሲሆን ታካሚው ብቻ ያውቀዋል፡፡ ወንድ ከሆነ ከ ዘርፍሬዎቹ በመነሳት ወደላይ እንደ ቀስት የሚሄድ ህመም ሲሆን፡፡ ሴቶች ደግሞ ከጎንና ጎን ብሎም ከጎድን አጥንታቸው በመነሳት የሚሄድ ነው!!
እነኚህ ምልክቶች የሚታዩባችሁ ከሆነ ይደውሉ
ህክምና ለማግኘት👇
0936038353
https://t.me/Medan122
https://t.me/Medan122
እረፍት እንዳይሰማዎት የሚሰሩ ሲህሮች ሲጋለጡ!
አጋልጥ! የሸይጧንን ጭፍሮች ራቆታቸውን እስኪቀሩ ድረስ ጉድ አድርጋቸው፡፡ የአሏህ ባርያ ነህና ይህን ለአለም አድርስ በወንድም እህቶችህ ላይ የሚሰራውን ሸር አስቁም፡፡ ሷሂሮች ሲህሮች በሙሉ በአላህ ሃይል ወዳቂዎች ናቸው፡፡ ይህ ምልክት ከላይ ርእሱ እንደሚለው አይነት ናቸው አላህ ይጠብቀን የተያዙ ያቁታል፡፡ ይምጡ በአሏህ ቃል ይታከሙ፡፡ ይዳኑ!!
ሲህር የተደረጉበት ሰው ምልክቶች!
1.ቶሎ ቶሎ እንቅልፍ መውደቅ
3.ድክም ማለትና ስራ መስራት መጥላት
3.ስራ አለመሳካትና ወደ ስራ ቦታ መሄድን መጥላት
4.ጉሮሮ ቶሎ ቶሎ መቁሰል፡፡ እንደ ቶንሲል ቢሆንም ታማሚዎች ከውስጣቸው አንዳች ነገር ያለች እስክትመስላቸው ድረስ ይስላሉ፡፡
5.ሆዳቸው ስር የሚገላበጥ ነገር አለ፡፡ ያም ምን እንደሆነ አያውቁትም ብዙ ምርመራዎችን ቢያደርጉ እንኳ!
6.በህልማቸው ጥቁር ሰው ሲገናኛቸው አልያም ጥቁር ሰው ሲጎዳቸው ያያሉ!
7.እራሳቸውን ማጥፋት ይመኛሉ፡፡
8.ልጆች አይሳካላቸውም ግዜያዊ መካን ይሆናሉ፡፡
9.በሴቶች ላይ የወር አበባ በእጅጉ ይዛባል፡፡
10.በወንዶች ላይ ፍርሃት ቁጭት ፀጸት ይኖራቸዋል፡፡ በጥቃቅን ነገሮች፡፡
ከዚህ አይነት ሲህሮች በአሏህ ሃይል እንጠበቃለን፡፡
ህክምና ለማግኘት👇
0936038353
https://t.me/Medan122
የቀልብ መረጋጋትን የሚነፍገው ሲህር!!
ቢስሚሏህ አለማትን ላስገኘልን በውስጧም ምስጢራትን ላካተተው በዚያም የበላይነትን ለተቆናጠጠው ለሚፈልገውም ሂዳያን ላሻውም አፈያን በሚሰጠው በርሱ በአዛኙ ጌታ ስም ይሁን ሲህር በሰው ላይ ጉዳት አድራሽ አይደለም አሏህ በዚያ ሰው ላይ ኸይርን ውዴታን ቢሻለት እንጂ፡፡ አንድ ሰው ሲህርን አይሰራም ከሚነሏህ የተረገመ ከአሏህ ራህመት የተባረረ ቢሆን እንጂ፡፡ ስንቶቻችሁ ናችሁ ውስጣችሁ በሲህር ሰላም ያጣችው፡፡ ስንቶቻችሁስ ናችሁ ሃብት ስኬት ኑሯችሁ ውስጣችሁ ዛሬም የምትሸበረው የማትረጋጋው፡፡ ቀልበን ሰሊም ያቺ እርግት ያለችው ቀልብ ለሙእሚኖች ቃል ተገባች፡፡ ያን የሚያጠፉ ደግሞ ሷሂሮች የአሏህም ቅጣት አለላቸው፡፡ በዚህ ስራ ላይ ለረጅም አመታት ባደረግነው ትግል ሰው ልጅ ልብ የማይለውና ግና ብዙሃኑን ጨርቅ የሚያስጥለው ከሚወዱት ቤተሰባቸው የሚለየው ይህ የቀልብ መረጋገትን የሚያሳጣ ሲህር ነው፡፡ አሏህ ይጠብቀንና ይህን ወዲያው እልባት ካላስገኘ አንድ ሰው በህይወቱ ደስተኛ ሳይሆን ቀርቶ ያለፈውን ህይወት ኑሮውን ሲረግም ይውላል፡፡ ታድያ ይህ የሲህር ምልክት ምንድነው!!
ምልክቶቹ፡፡
ክፍል 2
9.ጥዋት ላይ ከእንቅልፋቸው ሲነቁ ጭንቀት መጀመር፡፡ ነጋ አልሃምዱሊላህ ሳይሆን ደሞ ነጋ አይነት ሙድ ውስጥ መግባት የልብ ምት ቀስ እያለ መጨመር የሚሆኑትን ማጣት፡፡ መፍራት ፡፡
10. ሽንትቤት ሲቀመጡ በተደጋጋሚ ማዛጋት፡፡ ይህ የማይካድ ሃቅ ነው፡፡ ከእንቅልፋቸው ተነስተው ሽንትቤት መቀመጥ ይሻሉ በመቀጠልም እዚያው ሳሉ ያዛጋሉ፡፡ አንዳንዴም ብቻቸውን ያወራሉ፡፡ ከሽንትቤት መውጣት ይቀፋቸዋል፡፡ ብሎም የሚጠቀሙት ሽንትቤት በጣም ሽታው ለሁሉም የሚያውክ ይሆናል፡፡
11.ቀን ቀን አይኖቻቸው ላይ የሚመጡባቸው ነገሮች ጆሮዎቻቸው ላይ ውልብ የሚሉ ድምፆች አሉሉ፡ ይህ ከታካሚ ታካሚ የሚለይ ሲሆን አንዳንዱ የሞተ ሰውን በቀን ያያል፡፡ በጆሮዋቸው ትእዛዝ አልያም ድምፅን ወይ ደግሞ እንዲህ አድርገው ግደለው አይነት ስሜቶችን ያስተናግዳሉ፡፡
12.የወሲብ ህይወታቸው እጅግ ቀዝቃዛ ይሆንና መልሰው ደግሞ የወሲብ አርበኛ ይሆናሉ፡፡ ይህን ፀባያቸውን መቆጣጠር አይቹል፡፡ ሴቶች ሲሆኑ ላልተፈለገ እርግዝና እና ለተላላፊ በሽታዎች የሚጠቁ ሲሆን ወንዶች ሲሆኑ ደግሞ ለኤች አይቪና ለአባላዘር በሽታዎች የሚጠቁ ይሆናሉ፡፡ አሏህ ይጠብቀን፡፡
13.ልጆች ካሏቸው ልጆቻቸው ላይ ቁጣፈቸውን መግለፅ አልያም ልጆቻቸው ላይ አጉል ልፍስፍስ መሆን መቆጣት ማቆም ወይ ደግሞ ሲቆጡ እስከ ማነቅ ድረስ ይደርሳሉ፡፡ ይህ ፀባያቸው ለራሳቸው የሚያስደነግጣቸው ናቸው፡፡
14.ሰው ሁሉ ይበድላቸዋል፡፡ ማንም ሰው ህመማቸውን የሚረዳ የለም ጥሩ የሆነ ቀረቤታ ስለሚኖራቸውና ከራሳቸው ጋር ችግርን ለማምለጥ እየተጋፈጡ ስለሆነ ሰው ደግሞ ይህን እንደ ድክመት ስለሚያይ ስራ ያበዛባቸዋል እነርሱ ላይ ሁሉም ጉልበቱን ያሳያል፡፡ እነርሱም የማይወጡት አዘቅት ውስጥ ይገባሉ፡፡
15.ሱሰኛ ከሆኑ ይህ ለነርሱ እጅግ በጣም አስቸጋሪ ነው፡፡ በተለይ የጫት ሱሰኛ ከሆኑ ለሊት ላይ ሲቃዡ ያድራሉ፡፡ ብቻቸውን ማውራት ጸጉራቸውን መላጨት መጡብኝ ሊገድሉኝ ነው አይነት መቃዠቶችን ይቃዣሉ፡፡
16.አፎቻቸው ብልቶቻቸው ብብቶቻቸው በሙሉ ከሰውነት ቀዳዳ ማስተንፈሻ ያላቸው ነገሮች በሙሉ በጣም የሚሸቱ ይሆናሉ፡፡ ይህ የሲህሩን እጅግ መባስና መክፋት አመላካች ሲሆን ይሄኔ ሰውየው አፋጣኝ ወደ ሩቅያህ ካላመራ ከሰው ህይወት ኑሮ ተገፍቶ የመውጣቱ አዝማምያ መቶ በመቶ ነው፡፡ ጓደኛ ይርቃቸዋል፡፡ ሰላም ይርቃቸዋል፡፡ ወዳጆቻቸው ይርቋቸዋል፡፡
ውድ የመዳን ቤተሰቦች እንዲሁም መላው የኢስላም ወንድም እህቶቻችን ብሎም የሌላ እምነት ተከታይ ማህበረሰቦች እንዲህ አይነት የሲህር ወረርሽኝ ሲያጠቃችሁ
ይደውሉ
ቻናላችንን ለኡማው ያስተዋውቁ 👇
https://t.me/Medan122
ህክምና ለማግኘት👇
0936038353
https://t.me/Medan122
