en
Feedback
VGM Ethio

VGM Ethio

Open in Telegram

ስኬታማ ሰዎች አጋጣሚዎችን አይጠብቁም፣ አጋጣሚዎችን እራሳቸው ይፈጥራሉ እንጂ!

Show more
1 686
Subscribers
No data24 hours
-87 days
-5030 days
Posts Archive
sticker.webp0.03 KB

photo content
+1

sticker.webp0.03 KB

የኢስላም ጠላቶች ሳያውቁት ለኢስላም የሚያበረክቱት አስተዋፅኦ ቁረይሽ እስልምናን ለማጥፋት ያልሞከሩት ነገር አልነበረም። ሰዎች በነብይነታቸው እንዳያምኑና እስልምናን እንዳይቀበሉ ለማድረግ ረሱል ”ﷺ” ላይ መቅጠፍ፣ ስብዕናቸውን ማዋረድ እና ስማቸውን ማጉደፍ ዋነኛው መንገዳቸው ነበር በመሆኑም ስማቸውን ለማጥፋት ያላስወሩባቸው፣ ያልፈበረኩት ቅጥፈት አልነበረም። ባለቅኔ፣ አስማተኛ፣ ደጋሚ፣ ቀጣፊ፣ እብድ ብዙ ብዙ ቀጥፈውባቸዋል። "እብድ ናቸው" የሚለውን ወሬ የሰማው የባህል መድኃኒት ቀማሚው ዲማድ አል-ዐዝዲ (ረዐ) ታድያ የህክምና ሞያውን በመጠቀም ከእብደት ሊፈውሳቸው እንደሚችል በማሰብ ከሀገሩ ወደ መካ ይጓዝና ረሱልን ”ﷺ” ይገናኛቸዋል። ሲያገኛቸው ግን ያጋጠመው ፍፁም ተቃራኒ ሆነበት። የኢስላም ጠላቶች እንዳስወሩት፣ እሱም እንደሰማውና እንደጠበቀው አልሆነም። ረሱል ”ﷺ” ፍፁም ጤነኛ፣ ከተቀጠፈባቸው ስም ማጉደፊያዎች ሁሉ የራቁ፣ ግርማቸው የገዘፈ፣ መንፈሳቸውም እጅግ የረጋ፣ ንግግራቸው እንደ ጥዑም ዜማ በጆሮ አልፎ ወደ ልብ የሚዘልቅ፣ መልዕክታቸውም ከአለት የጠጠረ፣ እውነተኛነታቸው ቅንጣት የማያጠራጥር የሆኑ ታላቅ ሰው ሆነው አገኛቸው። በጣፋጭ አንደበታቸው የእስልምናን ጥሪ አቀረቡለት። እጅ ወደላይ ብሎ ያለአንዳች ማንገራገር እስልምናን በፍቅር ተቀበለ። "እብድ ናቸው" የሚል ወሬ ሰምቶ ሊፈውሳቸው የመጣው የነበረው ዲማድ አል-ዐዝዲ (ረዐ) ከኩፍር በሽታው በእስልምና ፈወሱት። ለመጣበት ህዝብም የሚተርፍ የኩፍር በሽታ መድኃኒት እስልምናን ይዞ ተመለሰ። በዚህ ዘመንም ምዕራባዊያን እስልምናን ለማጥፋት ሚዲያዎቻቸውን በመጠቀም እስልምና ላይ ብዙ ቀጣጠፉ፣ እስልምናን ጥላሸት ለመቀባት በርካታ እስልምናን የሚያንቋሽሹ መፅሐፍትን ፃፉ፣ ይህንን በማድረጋቸው በርካታ ምዕራባዊያን እስልምናን የማወቅ ጉጉታቸው ተቀሰቀሰ። መርምረው እና አውቀውም እውነቱን ካረጋገጡ ቡኃላ በርካታ ምዕራባዊያን እስልምናን እየተቀበሉ ነው። ታሪክ አይቶ በማያውቀው መልኩ ምዕራባዊያን ሀገሮች በሙስሊሞች እየተጥለቀለቁ ነው። ከጥቂት አስርተ ዓመታት ቡኃላም እነዚህ ሀገሮች በእስልምና እንደሚዋጡ የሚያሳዩ ጥናታዊ ስራዎች እየጦቀሙ ነው። የሀገራችንም ፅንፈኛ ዲያቆናት እና መምህራን ከሰሞኑ ለጆሮ የሚከብዱ፣ የተከታዮቻቸውን (የምዕመኑን) የማገናዘብ አቅም የናቀ ቅጥፈት በአደባባይ ሲቀጥፉ እየታዘብን ነው። ይህ ድርጊታቸው በርካታ ምዕመናኑን ስለእስልምና እውነታውን የማወቅ ፍላጎት ሰበብ ይሆናል። መርምረው እውነታው ላይ የደረሱ በርካቶች ኢንሻአላህ እስልምናን ይቀበላሉ። በመሆኑም ከጥቂት ጊዜያት ቡኃላ ሀገራችን ላይ እስልምናን የሚቀበሉ ሰዎች ቁጥር በብዙ እጥፍ እንደሚጨምር ከወዲሁ መገመት ቀላል ነው። https://t.me/Zelebet

photo content

sticker.webp0.03 KB

sticker.webp0.03 KB

photo content

sticker.webp0.03 KB

አሰላሙዓለይኩም ያ ጀምዓ! fb Page ለአንድ ወር ስለታገደ እስከዛው መልዕክቶቼን በዚሁ በቴሌግራም ቻናል ብቻ የማስተላልፍ ይሆናል።

ነባሩ እስልምና ስትሉ… ነባሩ እስልምና ስትሉን ረሱል ሰዐወ በሒራ ዋሻ በጅብሪል አማካኝነት ወህይ መቀበል የጀመሩበትን እስልምና ማለታችሁ ከሆነ እሰየው። ነባሩ እስልምና ስትሉን ቢላል (ረዐ) "ሁበል" በል ሲባል አሻፈረኝ ብሎ "አሀድ አሀድ" እያለ በግፍ ጅራፍ የተገረፈበትን እስልምና ማለታችሁ ከሆነ እንቀበላለን። ነባሩ እስልምና ስትሉን ረሱል ሰዐወ የተዋረዱለት፣ ክብራቸውን ዝቅ ያደረጉለት፣ ብዙ ስቃይና መከራ ያስተናገዱበትን፣ ስማቸው የጠለሸበትን እስልምና ማለታችሁ ከሆነ ልክ ናችሁ ነባር ነው። ነባሩ እስልምና ስትሉን ረሱል ሰዐወ ከሚወዷት እና ከተወለዱባትን ከተማ መካ ጥለው በጠላቶቻቸው ወደ መዲና የተሰደዱበትን እስልምና ማለታችሁ ከሆነ እንስማማለን። ነባሩ እስልምና ስትሉን እንጃፈርን (ረዐ) የመሳሰሉ ሰሐቦች ግፉ ሲያይልባቸው ወደ ሐበሻ ምድር የተሰደዱበትን እስልምና ማለታችሁ ከሆነ መልካም። ነባሩ እስልምና ስትሉን እነዑመር፣ እነዓሊይ፣ እነኻሊድን (ረዐ) የመሳሰሉ የጀግና ተምሳሌቶች የተዋደቁለት፣ የታገሉለት፣ የቆሰሉበት ብሎም የሞቱለት እስልምና ማለታችሁ ከሆነ ልዩነት የለንም። ነባሩ እስልምና ስትሉን አላህና መልዕክተኛው ያዘዙንን ብቻ የምንታዘዝበት ሶሐቦች በወጡበት የምንወጣው፣ ሰለፎች በተረዱበት የምንተረጉመው እስልምና ማለታችሁ ከሆነ እንቀበላለን። ነገር ግን ነባሩ እስልምና ስትሉን በአፄዎቹ ጭቆና ብዛት ወኔ እና ማንነቱን ያጣውን፣ ከኦርቶዶክሱ ማንነት ጋር ለመቀላቀል የሚዳዳውን፣ የኦርቶዶክስ ፅንፈኛ መምህራን እንዲሆን እንደሚፈልጉት አይነቱን በገብርኤልና በማርያም የሚምለውን፣ አልሃምዱሊላህ ታቦታችን ገባ የሚለውን፣ ጠበል ቅመሱ ሲባል ሄዶ ከጠላውም ከጠጁም ጭምር የሚቀምሰውን፣  ቤተክርስቲያን ማሰሪያ ገንዘብ አዋጥቶ የሚሰጠውን፣ ለኩፍር በዓላቸው በሬ ገዝቶ እጅ መንሻ የሚያቀርበውን፣ በሐይሓኖቱ ምክንያት ሲያንቋሽሹት እና መብቱን ሲገፉት አንገቱን ደፍቶ የሚኖረውን፣ ከዲኑ ይልቅ ለነሱ የሚያስቃብጠውን፣ ከአላህ ይልቅ ለነሱ የሚተናነሰውን፣ መሳጂዶችን ጫት መቃሚያ አድርጎ ያረከሳቸውን፣ ለዲኑ ደንታ ቢስ የሆነውን፣ ከስሙ በስተቀር በሁለ መናው ከኦርቶዶክሳዊያን የማይለየውን ማለታችሁ ከሆነ? እንዲህ ዓይነቱን ከሆነ ነባሩ እስልምና የምትሉን ይህንን ዝቅጠት የምንቀበል አይደለንም። https://t.me/Zelebet

sticker.webp0.03 KB

sticker.webp0.03 KB

የኢስላም ጠላቶች ከቁረይሽ እስከ አሁን የእስልምና እየተስፋፋ መምጣት እጅግ ያሳሰባቸው የነበሩ የቁረይሽ ሹማምንት ለሐጅ ከመላው አረቢያ ወደ መካ የሚመጡ ጎሳዎች እስልምናን በዚሁ አጋጣሚ እንዳይቀበሉና መላውን የአረቢያ ምድር እንዳያጥለቀልቀው ይበልጥ አሰጋቸው። ይህንን መስፋፋቱን ማስቆም እንዳለባቸው አሰቡ። አስበውም እንዴት ማስቆም እንደሚችሉም ለመምከርም ተሰባሰቡ። የረሱል ”ﷺ” ስብእናን የሚያጎድፍ የስም ማጥፋት ዘመቻ መክፈት ሁነኛ መንገድ መሆኑን ከስምምነት ደረሱ። የበኑ መኽዙም ጎሳ መሪ የሆነው የቁረይሽ ዋና መሪ አል-ወሊድ ኢብን አል-ሙጊራ ለተሰበሰቡት የቁረይሽ ሹማምንት እንዲህ አላቸው፦ "የቁረይሽ ሰዎች ሆይ! የሐጅ ወቅት እየደደረሰ ነው። በመሆኑም የዐረብ ነገዶች ወደዚህ መምጫቸው እየተቃረበ ነው። ሲመጡ ስለባልደረባቹ (ረሱልን ”ﷺ” ማለቱ ነው) መስማታቸው አይቀርም። በመሆኑም ስለርሱ የምንናገረው ተመሳሳይ መሆን ይኖርበታል አለዚያ ነገር ይበላሻል።" "አቡ ዐብድ ሸምስ ሆይ! ምን መናገር እንዳለብን አንተ ንገረን።" አሉት ተሰብሳቢዎቹ "የናንተን ሀሳብ መስማት ነው ምፈልገው።" አለ ወሊድ "ጠንቋይ ነው" ብንልስ አለ አንዱ አል-ወሊድም ይህንን ሀሳብ ተቃወመ። "ጠንቋዮች የማይጨበጡ ነገሮችን ይለፈልፋሉ። የድምፅ አወጣጣቸውም ይለያል። በመሆኑም ሙሐመድን ጠንቋይ ነው ማለት አሳማኝ አይሆንም።" አላቸው። "እብድ ነው" ብንልስ አለ ሌላኛው አል-ወሊድ ይህንንም ሀሳብ ተቃወመ። "ያበዱ ሰዎች በግልፅ ያስታውቃሉ። በመሆኑም ሙሐመድን እብድ ነው ማለት አያሳምንም።" አላቸው። "ባለቅኔ ነው" ብንልስ አለ ሌላኛው። "ይህም በፍፁም አሳማኝ አይሆንም።" አለ አል-ወሊድ እንግዲያውስ አስማተኛ እና ደጋሚ ነው" ብንልስ "አስማተኛ እና ደጋሚን በድግምቶቻቸው እና በቋጠሮዎቻቸው በሚገባ እናውቃቸዋለን። እርሱ ደጋሚም አስማተኛም አይደለም።" አለ አል-ወሊድ "ታድያ ምንድነው ብንል ይሻላል?" ሲሉ ተሰብሳቢዎቹ መልሰው አል-ወሊድን ጠየቁት። እርሱም እንዲህ አለ፦ "በአላህ ይሁንብኝ ንግግሩ ጣፋጭ ነው። የንግግሩ መልዕክት እንደዘምባባ ግንድ ጠንካራ ሲሆን ቅርንጫፎቹም ግሩም የሆኑ የበሰሉ ፍሬዎችን እንደሚያዥጎደጉድ ነው። ስለርሱ ንግግር አሉታዊ ሀሳብ ብትሰነዝሩ ወዲያው ይጋለጥባቹሀል። የሆነው ሆኖ ካቀረባችሁት ሀሳብ "አስማተኛ ነው" የሚለው የተሻለ ነው። ምክንያቱም ሰውን ከአባት እና ከወንድሙ፣ ባልን ከሚስቱ፣ ሰዎችን ከጎሳቸው የመለያየት ችሎታ ያላቸው አስማተኞች ናቸው።" አላህ ይህንን የቁረይሽን ሴራ አስመልክቶ የቁርዓን አንቀፅ አወረደ። የኢስላም ጠላቶች ያኔም ከተቻለ የእስልምናን ብርሃን ለማጥፋት ካልሆነም የእስልምናን መስፋፋት ለመግታት ያልሸረቡት ሴራ፣ ያልከፈቱት የዘመቻ፣ ያላወጁት የጦርነት ዓይነት አልነበረም። ግና የእስልምና ባለቤት ኃያሉ አምላክ አላህ ነውና እንኳን ሊያጠፉት እጅግ ተስፋፍቶ ዛሬ በቢሊዮን የሚቆጠሩ ሙስሊሞች በመላው ዓለም ይገኛሉ። ዛሬ በዚህ ዘመንም የኢስላም ጠላቶች እንደትላንቱ ሁሉ እስልምናን ለማጥፋት ተኝተው እያደሩ አይደለም። እንኳን ሊያጠፉት በነካኩት ቁጥር እጅግ ተስፋፍቶ ዛሬ በሚሊየን የሚቆጠሩ ሰዎች በመላው ዓለም እስልምናን እየተቀበሉ ነው። በፍጥነት እየተስፋፋ ያለ ብቸኛ ሐይማኖት መሆኑንም የገዛ ጠላቶቹ ጥንት አረጋግጧል።

sticker.webp0.03 KB

sticker.webp0.03 KB

የኦርቶ መምህራን የእስልምናን ፆም ሲተቹ ሳይ ጅህልናቸው ያሳቅቀኛል። የነሱም ፆም ተብሎ ማለት ነው😁 ሲበላ ሲጠጡ እየዋሉ ፆም አለ እንዴ? የሚፆሙት እኮ ከከብት ተዋፆ ብቻ ነው። ሌላውን እንዳሻቸው ሲበሉ ይውሉና ፆምን እያሉ የእስልምናን ፆም ለመተቸት ይሞክራሉ። ሲጀምር ከከብት ተዋፅኦ በላይ ከፍተኛ ጥቅም ያላቸው ምግቦች እንዳሉ ይታወቃል። ለምሳሌ ከስጋ የሚገኘውን ሰውነት ገምቢ እና ኃይል ሰጪ ፕሮቲንን የሚተኩ ከፍተኛ የፕሮቲን መጠን ያላቸው አትክልትና ጥሬጥሬ ዘሮች እንዳሉ የህክምና ባለሞያዎች አረጋግጠዋል። “አካዳሚ ኦፍ ኑትሪሽን ኤንድ ዲያቴቲክስ” የተባለ ተቋም እንዳጠናው፥ ባቄላ፣ ለውዝ የሱፍ አበባ፣ የለውዝ ቅቤ፣ ዱባ፣ ተልባ፣ አቮካዶን እና የመሳሰሉት ቢመገቡ ስጋን መተካት ይችላሉ። ሲል አረጋግጧል። ሲቀጥል ከዚህ የደኃ ደኃ ከሆነ ማህበረሰብ ምን ያህሉ ነው የከብት ተዋፅኦ የሆኑ ምግቦችን የሚመገበው? አብዛኛው ማህበረሰብ እነዚህን በገንዘብ ደረጃ ውድ የሆኑ ምግቦች እንዲመገብ ኪሱ አይፈቅድለትም። በመሆኑም እነዚህን የከብት ተዋፅኦ አለመመገብ ፆም ካስባለ ዳሀው ማህበረሰው ከዓመት ዓመት ፆመኛ ነው ማለት ነው። ሌላው እነዚህን የከብት ተዋፅኦ የማይመገቡ "ቬጅቴርያን" አትክልት ብቻ ተመጋቢ የሆኑ ሰዎች አሉ። የከብተ ተዋፅኦ አለመመገብ ፆመኛ ካስባለ እነሱስ ከአመት እስከ አመት ፆመኛ ናቸው ማለት ነው? በዚህ ስሌት ስንሄድ ከኦርቶዶክስ ማህበረሰብ ፆም ሲገባ አመጋገብ ስርዓቱ የሚቀየረው እጅግ በጣም ጥቂቱ ነው። አብዛሃኛው ፆም ገባም አልገባም ከዓመት እስከ ዓመት አመጋገብ ስርዓቱ ያው የተለመደችው ____ ናት። ሌላው ቢቀር በፆም ወቅት አስካሪ መጠጥ እንኳን መጠጣት አያቆሙም። ታድያ የኦርቶዶክስን ፆም ፆም ያስባለው ምኑ ነው? እንዲህ አይነት ፆም ነው እንግዲህ ፆም ተብሎ ዲያቆን ዮርዳኖስ የእስልምና ፆም ላይ ለማላገጥ የሚሞከረው😁 https://t.me/Zelebet