cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

SINA THE GLORY OF GOD

ነገር ግን መንፈስ ቅዱስ በእናንተ ላይ በወረደ ጊዜ ኃይልን ትቀበላላችሁ፥ በኢየሩሳሌምም በይሁዳም ሁሉ በሰማርያም እስከ ምድር ዳርም ድረስ ምስክሮቼ ትሆናላችሁ አለ። የሐዋርያት ሥራ 1 : 8

Show more
The country is not specifiedThe language is not specifiedThe category is not specified
Advertising posts
202
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

Photo unavailableShow in Telegram
ቢል ብራይት ይባላሉ ታላቅ የወንጌል አገልጋይ ናቸው በአንድ ምሽት በኮሪያ ሲዎል በሚባል ከተማ በነበራቸው ክሩሴድ አንድ ሚሊዮን ሶስት መቶ ሺ ሰው ታድሞ ነበር በስብከታቸውም ተነክተው 1 000 000ኑ ጌታን ተቀብለዋል #የሰበኩትም #ኤፌሶን #2-(8-9) https://t.me/Tamerat9 https://t.me/Tamerat9
Show all...
በልምድና በንግግር ችሎታ ለሰዓታት ከምትደረድሩት ያማሩና የተሽቀረቀሩ ቃላቶች ይልቅ በረሀብና ከልብ በሚመነጭ ጥማት ያነባቹት አንዲት የእንባ ጠብታ #መንፈስ #ቅዱስን ወደ እናንተ የመጋበዝ ሀይል አላት #ከተራብክ #ከተጠማህ #እመነኝ #መንፈስ #ቅዱስ #ያገኝሀል https://t.me/Tamerat9
Show all...
SINA THE GLORY OF GOD

ነገር ግን መንፈስ ቅዱስ በእናንተ ላይ በወረደ ጊዜ ኃይልን ትቀበላላችሁ፥ በኢየሩሳሌምም በይሁዳም ሁሉ በሰማርያም እስከ ምድር ዳርም ድረስ ምስክሮቼ ትሆናላችሁ አለ። የሐዋርያት ሥራ 1 : 8

ብዙ ንግግሮች እንደ ጥናታዊ ጽሑፍ የሚቀርቡ ብቻ ናቸው #እግዚያብሔርን #ቀርበው #የሚያውቁት #ሰዎች #የሚናገሯቸው #ቃላት #ብቻ #ናቸው #ዘር #የሚሆኑት https://t.me/Tamerat9
Show all...
SINA THE GLORY OF GOD

ነገር ግን መንፈስ ቅዱስ በእናንተ ላይ በወረደ ጊዜ ኃይልን ትቀበላላችሁ፥ በኢየሩሳሌምም በይሁዳም ሁሉ በሰማርያም እስከ ምድር ዳርም ድረስ ምስክሮቼ ትሆናላችሁ አለ። የሐዋርያት ሥራ 1 : 8

የአለማችን ብዙ ገቢ ያስገባ የክርስቲያን ፊልም -------------------------------------------------- ክርስቲያኖች ዳግም በክርስቶስ ፍቅር እንዲወድቁ ያደረገ ፊልም! በዝነኛው የሆሊውድ ተዋናይ፥ ደራሲና ዳይሬክተር ሜል ጊብሰን ተፅፎ የተዘጋጀና ፕሮዲዩስ የተደረገ ፊልም ነው። በጌታችን፥ በመድሃኒታችን እየሱስ ክርስቶስ የመጨረሻዎቹ አስራ ሁለት የስቃይና የስቅላት ሰዓታት ላይ አተኩሮ የተሰራው ይህ The Passion Of The Christ ፊልም ሊታይ የሚገባበት ወቅት እንደመሆኑ፤ በፊልሙ ዙሪያ የተከሰቱ አንዳንድ ተአምራትና እውነታዎችን እንዲሁም ፊልሙ በክርስትና እምነትና በሲኒማው ኢንዱስትሪ ያሳደረውን ተፅዕኖ ላስታውሳችሁ… 1. የጌታችን የእየሱስ ክርስቶስ ህይወት መሰረት አድርገው ከተሰሩት ቀደምት የሆሊውድ ፊልሞች በተለየ ሁኔታ The Passion Of The Christ የክርስቶስን እውነተኛ ስቃይ በተሻለ ሁኔታ አቀራርቦ ለማሳየት በመሞከሩና የፊልሙ ቋንቋንም በወቅቱ የነበረውን፥ ጥንታዊውን “አርማይክ” ቋንቋን በመጠቀሙ ምክንያት የሆሊውድ ስቱዲዮዎች በስራው ለመሳተፍ ፍቃደኛ አልነበሩም። በፍፁም ተመልካች ያገኛል ብለው አልገመቱም። ይልቁንም ብዙዎቹ ሜል ጊብሰን ገንዘቡንና ጉልበቱን እንዳያባክን መከሩት። + ነገር ግን ሜል ጊብሰን በአቋሙ ፀንቶ፥ 30 ሚልዮን ዶላር የግል ገንዘቡን አፍስሶ ሰራው። 2. ሜል ጊብሰን የእየሱስ ክርስቶን ገፀ ባህሪ ወክሎ ለመተወን ዕድለኛ የሆነውን ተዋናይ ማፈላለግ ሲጀምር አንድ መመዘኛ አስቀምጦ ነበር። እሱም ስሙ JC መሆን አለበት የሚል ነበር። ልክ እንደ Jesus Christ ስሞቹ በJ እና በC የሚጀምር መሆን አለበት ማለት ነው። በዛ መሰረትም ቀደም ሲል The Thin Red Line, Frequency እና The Count of Monte Cristo በሚባሉት ፊልሞቹ የሚታወቀውን JC, Jim Caviezelን መረጠ። + በእርግጥ ጂም ካቪትዜል ከስሙ ባሻጋር መልካም ስነ ምግባር ያለው አማኝ ክርስቲያንም ነው። ለምሳሌ ከ The Passion Of The Christ በፊት በሰራቸው Angel Eye እና High Crime ፊልሞች ላይ ከጄኒፈር ሎፔዝ እና ከአሽሊ ጁድ ጋር በነበሩት የፍቅር ትዕይንቶች “ልብሴን አውልቄ፥ እርቃኔን አልቀረፅም፥ ሃጢያት ነው” ብሎ ከወገብ በላይም እርቃኑ ሳይወጣ፥ ልብሱን እንዳደረገ ሰርቷል። የካንሰር ህመምተኛ የሆኑ ሶስት ቻይናዊያን ልጆችን በጉዲፈቻ በመውሰድም አሳድጓል። 3. በፊልሙ ቀረፃ ወቅት ላይ የፊልሙ ረዳት ዳይሬክተር Jon Mikalini ሁለት ጊዜ በመብረቅ ተመቷል። የእየሱስ ክርስቶስን ገፀ ባህሪ ተላብሶ የሰራው Jim Caviezelም የስቅለቱን ትዕይንት በሚሰራበት ጊዜ፥ በተሰቀለበት በመብረቅ ተመቷል። የመብረቅ ክስተት አጥኚዎች በዛ በተወሰነ ሰዓትና ቦታ ላይ ብቻ ሶስት ጊዜ መብረቅ መከሰቱ ያልተለመደ ነው ያሉ ሲሆን ረዳት ' ዳይሬክተሩና ተዋናዩ በእንደዛ ሁኔታ በመብረቅ ተመተው አለመሞታቸው ደግሞ ተአምር ነው ብለውታል። 4. ፊልሙ ላይ የይሁዳን ገፀ ባህሪ ተላብሶ የሰራው ተዋናይ Luca Lionelloን ጨምሮ በርካታ ፊልሙ ላይ የተሳተፉ ሰዎች የክርስትና እምነትን ተቀብለዋል። ክርስትና ተጠምቀዋል። 5. በአጠቃላይ የፊልሙ ስራ ሂደት ላይ በርካታ ተአምራት እንደነበሩ ሜል ጊብሰን ተናግሯል። ልዩ ልዩ ህመም እንዲሁም የእይታና የመስማት ችግር የነበረባቸው፥ በፊልሙ ስራ ላይ የተሳተፉ ሰዎች ተፈውሰዋል። + ከፊልሙ ስራ ጋር በተያያዘ ሌላው አስገራሚ ተአምር ደግሞ የፊልሙ የቀረፃ ስራ አባል የነበረ አንድ ባለሙያ የስድስት ዓመት ልጁ በሚጥል በሽታ ትሰቃይ ነበር። በሚያሳዝን ሁኔታ ህፃኗ በቀን እስከ ሃምሳ ጊዜ ትወደቅ የነበረ ሲሆን አባቷ የፊልሙ ስራ ላይ ተሳትፎ ወደ ቤቱ ከተመለሰ በኋላ ከስቃይዋ ድናለች። 6. ፊልሙ እንዲሰራ ገንዘብ ለመመደብ ያፈገፈጉት የሆሊውድ ስቱዲዮዎች፤ የፊልሙ ስራ ሲጠናቀቅም ፊልሙን ለማከፋፈል ፈቃደኛ አልሆኑም። “ፊልሙ ጁዎች ላይ ጥላቻን የሚያነሳሳ ነው” በሚልም ዘመቻ ተከፈተበት። ሆኖም ፊልሙ የተከፈቱበትን ዘመቻዎች ሰባብሮ፥ በግለሰቦች አቅም ለእይታ በቃ። ውጤቱም ሌላ ተአምር ሆነ። + ፊልሙ በመላው ዓለም ለዕይታ ሲቀርብ፥ መድሃኒታችን እየሱስ ክርስቶስ የእኛን ሃጢያት ለማሰረይ፥ በተቀበለው ስቃይና በከፈለው መስዋእትነት መላው የዓለም ክርስቲያን በእንባ ተራጨ። + The Passion Of The Christ ህዝበ ክርስቲያን የክርስቶስ ፍቅሩን ዳግም እንዲያድስ ያደረገና በክርስትና እምነት ከፍተኛ ተፅዕኖ ያሳደረ ፊልም እንደሆነ የሃይማኖት አባቶች፥ የፊልም ሃያሲያንና ሚዲያዎች መሰከሩለት። 7. The Passion Of The Christ በፊልም ታሪክ ውስጥ በተመልካቾች ዘንድ "A+" ደረጃ ከተሰጣቸው ጥቂት ፊልሞች አንዱ ሆኗል። + ከ622 ሚልዮን ዶላር በላይ ገቢ በማግኘትም በኢንዲፐንደንት ፊልሞች እና በክርስቲያን ፊልሞች ታሪክ ባለ ከፍተኛ ገቢ ፊልም ሆኖ ቁጥር 1 ደረጃውን ያዘ። [ለዛውም R-Rated ፊልም ሆኖ ማለትም ዕድሜያቸው ከ18 በታች የሆኑ ሁሉ እንዳያዩት ተከልክሎ] + ሜል ጊብሰን አልሞቀውም አልበረደውም እንጂ ለሶስት የኦስካር ሽልማቶችም ታጭቶ ነበር። 8. ፊልሙ ላይ ያለው የክርስቶስ ስቃይ እጅግ በጣም አስጨናቂ ከመሆኑ የተነሳ ብዙ ተመልካቾች ሳይጨርሱት አቋርጠው ለመውጣት ተገደዋል። + ዊቺታ በምትባል የካንሳስ ግዛት ከተማ፥ ፔጊ ሎው የተባሉ አሜሪካዊት ሴት ፊልሙን እየተመለከቱ እያለ፥ በፊልሙ መጨረሻ አካባቢ ባለው አስጨናቂ ትዕይንት እዛው ሲኒማ ቤት ውስጥ ህይወታቸው አልፏል። + ሜል ጊብሰን በበኩሉ “በጥናት ከደረስንበት የጌታችን የእየሱስ ክርስቶስ እውነተኛ ስቃይ ውስጥ 40 በመቶውን ብቻ ነው የሰራነው። 60 በመቶው እውነተኛውን ስቃይ አላሳየናችሁም” ብሏል። 9. በበርካታ ስኬታማ ፊልሞቹ በሆሊውድ የዝና ጣሪያ ላይ ደርሶ፥ የኦስካር ሽልማትን ጨምሮ ሁሉም ዓይነት የዚህ ዓለም ፀጋ ያጣጣመው ሜል ጊብሰን፥ ከሰራቸው ፊልሞች ሁሉ የሚኮራበት The Passion Of The Christ ብቻ መሆኑንና ሰዎች ሌላውን ረስተው በዚህ ስራው ብቻ እንዲያስቡት እንደሚፈልግ ተናግሯል። + ከስቅለት እስከ ትንሳኤ ያለውን የክርስቶስን ታሪክ የሚያሳይ The Resurrection of the Christ በሚል ቀጣይ ክፍል መስራት እንደሚፈልግም አበስሯል። + ጂም ካዝቪቴል የእየሱስ ክርስቶስን ገፀ ባህሪ ተላብሶ ከሰራ በኋላ ከዴንዘል ዋሺንግተን ጋር የሰራውን Déjà Vuን ጨምሮ በበርካታ ፊልሞች ላይ የተሳተፈ ቢሆንም ክርስቲያንነቱን ይበልጥ አጥብቆ በብዙ መድረኮች ላይ ክርስትናን መስበኩን ቀጥሏል። + ጂም ከሁለት ዓመት በፊት ለዕይታ በበቃው Paul, Apostle of Christ በተባለው ፊልም ላይም የቅዱስ ሉቃስን ገፀ ባህሪ በመወከል ተውኗል። ሜል ጊብሰን በሚሰራው The Resurrection of the Christ ላይም ተመልሶ ይመጣል ተብሎ ይጠበቃል። አስደናቂ የእግዚያብሔር ፀጋ https://t.me/Tamerat9 https://t.me/Tamerat9 https://t.me/Tamerat9
Show all...
SINA THE GLORY OF GOD

ነገር ግን መንፈስ ቅዱስ በእናንተ ላይ በወረደ ጊዜ ኃይልን ትቀበላላችሁ፥ በኢየሩሳሌምም በይሁዳም ሁሉ በሰማርያም እስከ ምድር ዳርም ድረስ ምስክሮቼ ትሆናላችሁ አለ። የሐዋርያት ሥራ 1 : 8

#ኢየሱስ #ተወልዶልናል ሉቃስ 2 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ⁸ በዚያም ምድር መንጋቸውን በሌሊት ሲጠብቁ በሜዳ ያደሩ እረኞች ነበሩ። ⁹ እነሆም፥ የጌታ መልአክ ወደ እነርሱ ቀረበ የጌታ ክብርም በዙሪያቸው አበራ፥ ታላቅ ፍርሃትም ፈሩ። ¹⁰ መልአኩም እንዲህ አላቸው፦ እነሆ፥ ለሕዝቡ ሁሉ የሚሆን ታላቅ ደስታ የምሥራች እነግራችኋለሁና አትፍሩ፤ #ኢየሱስ #ታሪኩ #የጀመረው #ከ2000 #ዓመት #በፊት #አይደለም #እርሱ #ለፍጥረቱ #ጅማሬ #የሌለው #አልፋና #ኦሜጋ #ፊተኛና #ኋለኛ #መጀመሪያና #መጨረሻ #ነው #ነገር #ግን #ስለኔና #ስለናንተ #የእግሩ #መረገጫ #ወደሆነችዉ #ምድር #ራሱ #በፈጠራት #ሴት #ተወለደ #ኢየሱስ #ተወልዶልናል #መልካም #ገና https://t.me/Tamerat9 https://t.me/Tamerat9
Show all...
SINA THE GLORY OF GOD

ነገር ግን መንፈስ ቅዱስ በእናንተ ላይ በወረደ ጊዜ ኃይልን ትቀበላላችሁ፥ በኢየሩሳሌምም በይሁዳም ሁሉ በሰማርያም እስከ ምድር ዳርም ድረስ ምስክሮቼ ትሆናላችሁ አለ። የሐዋርያት ሥራ 1 : 8

Watch "Best protestant tik tok video collection watch share like comment and subscribe" on YouTube https://youtu.be/1Rc8ZaZvlXk
Show all...
Best protestant tik tok video collection watch share like comment and subscribe

https://youtube.com/channel/UCO5TZATx9M7XCSdhHdguIUw

Show all...
July 3, 2021

“በሕይወት ትኖሩ ዘንድ መልካሙን እንጂ ክፉውን አትፈልጉ፤ እንዲህም እናንተ እንደ ተናገራችሁ የሠራዊት አምላክ እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ይሆናል።” — አሞጽ 5፥14 @Tamerat9
Show all...
🖐🖐🖐 ሰላም የአባቴ ልጆች🖐🖐🖐 #ወዳጆቼ #በኢትዬጲያ ውስጥ #ከአባቶችና ከብዙ #የእግዚአብሄር ሰዎች #እንደሰማሁት #በኢትዮጲያ ዉስጥ #ጥቂትም #ቢሆን #የሪቫይቫል #ንፋስ ታይቶ #ነበር፡፡ በእዛ #የሪቫይቫል ንፋስ #አማካኝነት #ወንጌል እየተሰራጨ #ይገኛል፡፡ከእምነት #አባቶቻችን እንደሰማሁት #በአንድ ወቅት #የሪቫይቫል ዘመን #ነበረ፡፡ 🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥 #በእነ #ሐዋርያው ዳንኤል መኮንን #ዘመን ለምሣሌ #እግዚአብሄር #በኢትዮጲያ ውስጥ #በአካል #እየተንቀሳቀሰ ነው የተባለበት #ዘመን ነበረ፡፡ #በጊዜዉ ከተነሳው #የመንፈስ #ቅዱስ #ክብር የተነሳ ታላቅ #የወንጌል አገልግሎት በየስፍራው #ሊሠራጭ ችሏል፡፡#እግዚአብሄር ቃሉን #በድንቅና #በምልክት #እያፀና የመገኘቱን #ሚስጥር ገሀዳዊ #አድርጎት ነበር፡፡ 🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥 #ብዙነፍሳት ከልብ #መነካት፣#ከመፀፀትና #ከእዉነተኛ መረዳት ጋር ወደ ጌታ #መንግስት ፈልሰዋል፡፡ #እግዚአብሄር አምላክ #ኢትዮጲያን ልዩ #የመንፈስ ቅዱስ #ክብር ወይም #ሪቫይቫል እንደሚያገኛት #በብዙ #የግዚአብሄር ሰዎች #በተደጋጋሚ ሲናገር #ቆይቷል፡፡ 🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥 #ስለዚህ የእስካሁኑ #በምድራችን #ኢትዮጲያ #የታየው ሁሉ #አሁን ሊመጣ ላለው #ሪቫይቫል #ጥላ #እንጂ #አካሉ አይደለም አሁን #የመጨረሻው ዘመን #ሪቫይቫል በጣም #በደጅ ነው ይሄ #ሪቫይቫል #ከኢትዮጲያ ተነስቶ ምድርን #ሚሸፍን ነው ታድያ #እራሳቹን ምን ያክል ለዚ #ክብር እያዘጋጃቹ #ነው? #በቅርቡ በከባድ #ክብር #እንገናኛለን❤️❤️❤️ #Share with your #friends #Join this #channel 👉@metshafe5👈 👉@metshafe5👈 👉@metshafe5👈 👆 👆👆👆👆👆👆
Show all...
የማይሞተው ሞተ ንፁህ ሆነህ ሳለ አዛኝ ሆኖ ልብህ ሞትህን ፈልገው አይሁድ መከሩብህ አወቀህ እንዳላወቅህ ምክራቸው ሲፀና የሞትህን ፅዋ ተጎነጨህና በጠላቶችክ ፊት ቆምክ በትህትና በአንደበትህ ሀሰት ባይገኝም ቅሉ የልባቸው ክፋት ለከቱን አጣና ሁሉም ፈረዱብህ ይሰቀል እያሉ ጲላጦስም ገፋህ ሄሮድስም አልራራ አሰለፈው ሰጡህ አንተን ለመከራ አንገላቱህ በግፍ ገረፋህ አብዝተው አዳኝነትህን ክብርህን ዘንግተው ተዘባበቱብህ አፋቸውን ከፍተው ልባቸውን ዘግተው አጥንትህ ሲቆጠር ስጋህ ተበጣጥሶ መላ ሰውነትህ ደም አቯራ ለብሶ ንጉስ ሆይ እያሉ ይሳለቁበሀል አንተ የኔ ቤዛ መስቀል ተሸክመህ ስቃይ በዝቶብሀል ምድረ ጎለጎታ መከራህ በረታ በሾህ አክሊል ስለት እራስህ ተመታ እጅህን በሚስማር እግርህን በሚስማር ልብህ ደረትህም በሚስማር ተወጋ ሰጋህ ተቆረሰ አጥንትህ ደቀቀ የአለሙ ጌታ አልፋና ኦሜጋ ከወንበዴዎች ጋር አቆሙህ በመስቀል ቀኑ ደረሰና የአዳም እርግማኑ በሞትህ ሊነቀል ተጠማሁ ብትልም የጭካኔን ፅዋ ቀድመው ስለዋጡት ሀሞት ሰጡህና ጥምህን ቆረጡት አለቀሰች ድንግል አዘነች አብዝታ ተሰቅለህ በመስቀል በግፈኞች በትር መከራህን አይታ እሚያደርጉትን ሁሉ እያቁትምና አባት ሆይ ማራቸው በማለትም ፀለይክ የምህረትህ ነገር ጥግ የለውምና ላደረገው ሁሉ በአይሁዶች እይታ መሞት ሆነ ዋጋህ ትንቢት ይፈፀም ዘንድ በፈቃድህ ለየህ ነፍስህን ከስጋህ ምድር ተናወጠች ጨርቃም ደም ለብሳ ከዋክብት ረገፉ መቃብር ተከፍቶ ሙታኑም ተነሳ ቃሉም ተፈፀም አዳም ነፃ ወጣ እንጦረጦስ ገባ ሰይጣን ሀይሉን አጣ የሚሆነው ሆኖ የማይሞተው ሞተ የሂወት በራችን በደሙ ማሀተም ዳግም ተከፈተ ይሄን የአምላክ ፍቅር የማዳኑን መንገድ መግለፅ ይከብደኛል ምትን በምት ሽሮ ሂወትን የሚሰጥ ከ ወዴት ይገኛል የማይሞተው ሞተ @Tamerat9 @Tamerat9 @Tamerat9
Show all...
Choose a Different Plan

Your current plan allows analytics for only 5 channels. To get more, please choose a different plan.