cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ርጢን ሚዲያ ( Ritin Media )

ርጢን ከሙጫ ተቀምሞ የሚዘጋጅ ልዩ ፈዋሽ እጣን ነው። #ተጨማሪ_አድራሻዎቻችን #YouTube https://youtube.com/channel/UC2rpoJAhNOxMgAiqgW5yqOw #Facebook https://www.facebook.com/ritintube/ #Tiktok https://vm.tiktok.com/ZMRc7Sg1N/ #For_Question_and_comments @Ritin_Media_bot

Show more
Advertising posts
1 510
Subscribers
+124 hours
-17 days
-530 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

እንኳን ለብርሃነ ትንሳኤ በሰላም አደረሰህ አደረሳችሁ
Show all...
🙏 1
✥✥✥ሦስት ሌሊት እና መዓልት✥✥✥ 👉 ጥያቄ:- ጌታችን ሦስት ቀንና ሌሊት በከርሠ መቃብር (በመቃብር ሆድ/ውስጥ/) ቆየ ስንል ኣቆጣጠሩ እንዴት ነው? 👉 መልስ:- በመጀመሪያ የጌታችን የመቃብር ውስጥ ቆይታ ሦስት ቀንና ሌሊት መሆኑን የገለጠልን ራሱ መድኅነ ዓለም ክርስትስ ነው ይኸውም :- " ዮናስ በዓሣ አንባሪ ሆድ ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት እንደ ነበረ ÷ እንዲሁም የሰው "ልጅ (ክርስቶስ) በምድር ልብ ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት ይኖራል። " (የማቴ ወን12÷40) በተጨማሪም " ጌታ ኢየሱስም መልሶ:-- ይህን ቤተ መቅደስ አፍርሱት በሦስት ዕለትም አነሣዋለሁ አላቸው " (የዮሓ ወን 2÷19) " ስለዚህ የጌታችን የመቃብር ውስጥ ቆይታ ሦስት ቀንና ሌሊት መሆኑን እርግጥ ነው። ➛ አቆጣጠሩ ፩— ጌታችን በዕለተ አርብ በእኩለ ቀን ስድስት ሰዓት ተሰቅሎ በዘጠኝ ሰዓት በራሱ ሥልጣን ነፍሱን ከሥጋው ለየ በአስራ አንድ ሰዓትም ወደ መቃብር ወረደ ከዚህ ጊዜ ጀምሮ ስንቆጥር አርብ ከ11—12 ሰዓት ያለው አንዱ ሰዓት እንደ አንድ ዕለት(ቀንና ሌሊት) እንቆጥረዋለን። ➛ (ማስታወሻ:– ዕለት ማለት በ24 ሰዓት ውስጥ ያለውን ቀንና ሌሊትን የሚገልጥ ሲሆን ቀን የምንለው ደግሞ 12 ሰዓት ብርሃንን ሲወክል ሌሊት ደግሞ የጨለማውን 12 ሰዓት ይወክላል። ከዚህ ላይ ልናስተው የሚገባው ለዕለት (ለ24 ሰዓት) ቀኑ ሳይሆን ሌሊቱ ነው የሚቀድመው ይህን የሚያስረዳ፦ ➛ ከኦሪ ዘፍ 1÷5 ጀምሮ በተከታታይ " ማታም ሆነ÷ ጠዋትም ሆነ " በማለት ለዕለት ጨለማው እንጂ ቀኑ እንደማይቀድም ገልጦልናል - ለምሳሌ በተለምዶ የሐሙስ ሌሊት የምንለው የአርብ እንጂ የሐሙስ አይደለም ስለዚህ በዚህ ትክክለኛ የመጽሓፍ ቅዱስ አቆጣጠርን መሠረት አድርገን ጌታችን አርብን ከቀኑ11 ወደ መቃብር ወረደ ስንል ዕለተ አርብ ልታልቅ የቀረው አንድ ሰዓት ብቻ ቢሆንም ይህች ከ11–12 ያለችው አንድ ሰዓት የዕለተ አርብን 24 ሰዓት ሁሉ ትወክላለች ለምሳሌ በዚህች ሰዓት ላይ ያለ ሰው ዛሬ አርብ ነው ይላል እንጂ አንድ ሰዓት ስለቀራት ዛሬ ቅዳሜ ነው አይልም ስለዚህ አርብ ከ11–12 ያለችው አንድ ሰዓት ዕለቱን (24 ሰዓቱን) ወክላ ጌታችን በመቃብር ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት ቆየ የተባለበትን አንዱን ቀንና ሌሊት ታስቆጥረናለች። — በመቀጠልም በተለምዶ አርብ ሌሊት ከሚባለው ከቅዳሜ12 ሰዓት ጀምሮ የምናድርበት 12 ሰዓት እና ነግቶም የምንውልበት 12 ሰዓት (በድምሩ 24 ሰዓት ሌሊት እና ቀን) ሁለተኛ የመቃብር ውስጥ ቆይታ ይሆናል። — በተለምዶ ቅዳሜ ሌሊት ከሚባለው ከእሁድ ከምሽቱ 12 ሰዓት ጀምሮ ጌታችን እስተነሳበት እኩለ ሌሊት 6 ሰዓት ያሉት ስድስት ሰዓታት የዕለተ እሁድን 24 ሰዓት ወክለው ሦስተኛውን የመቃብር ውስጥ ቆይታ ያስቆጥሩናል። ስለዚህ:– + አርብ ከ11—12 (ያለው አንድ ሰዓት አንድ ሌሊትና ቀን) + ቅዳሜ ከ12—12(ሌሊት)፣ ከ12—12 (ቀን) ሁለተኛ ሌሊትና ቀን + እሁድ ከ12—6 ያለው ስድስት ሰዓት ሦስተኛ ሌሊትና ቀን ይሆናል። ይህ የመጀመሪያው አቆጣጠር ነው። ፪— ጌታችን አርብ ጠዋት ሦስት ሰዓት ይሰቀል ይሙት ተብሎ ተፈርዶበታልና ሊቃውንትም ከዚህ ሰዓት ጀምሮ ያለውን እንደሞት እንደመቃብር ቆይታ በመቁጠር በወንጌል እንደተገለጠልን (የማር ወን 16÷24 ጀምሮ ይመልከቱ) ከ3—6 ሰዓት ብርሃን ነበር ከ6—9 ደግሞ ጨለማ ሆኗል ይህም ብርሃን እና ጨለማ እንደ አንድ ዕለት ይቆጠራል። — በዚያሁ በዕለተ አርብ ጌታችን ነፍሱን ከሥጋው በሥልጣኑ ከለየበት ከዘጠኝ ሰዓት ጀምሮ እስከ አስራ ሁለት ሰዓት ብርሃን ሆኗል÷ በተለምዶ አርብ ሌሊት ከሚባለው ከቅዳሜ አስራ ሁለት ሰዓት እስከ ጠዋቱ አስራ ሁለት ሰዓት ጨለማ ሆኗል ይህም ብርሃን እና ጨለማ ሁለተኛ ዕለት ይሆናል። — ቅዳሜ ከጠዋቱ 12 ሰዓት እስከ ምሽቱ 12 ሰዓት ያለው ብርሃን እና በተለምዶ ቅዳሜ ሌሊት ከሚባለው ከእሁድ 12 ሰዓት ጌታችን በሥልጣኑ እስከተነሣበት እኩለ ሌሊት 6 ሰዓት ያለው ጨለማ  
Show all...
👍 1
11ሰዓት
Show all...
3
Show all...
"በእርሱ ቁስል እኛ ተፈወስን!"

ተዋሕዶ ሚዲያ ማዕከል የኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እውነተኛ ድምፅ 🔗 Explore Our Channel: Tewahedo Media Center @TMC1 🎥 About TMC: Dive into the rich tapestry of Ethiopian Orthodox Tewahedo Church traditions and teachings with Tewahedo Media Center (TMC). We are dedicated to bringing you insightful, educational, and spiritually uplifting content that reflects the essence of our beloved Ethiopian Orthodox faith. 📺 Latest Videos: 🔍 Discover our latest videos covering a variety of topics, including religious ceremonies, sermons, cultural events, and more. Stay connected with the heart of our community through TMC's engaging content. 👥 Community Engagement: Join our growing community of viewers who share a passion for Ethiopian Orthodox Tewahedo Church. Your comments, likes, and shares contribute to the vibrant discussions and strengthen our online congregation. 🔔 Don't Miss Out: Hit the notification bell to stay updated on our newest releases. Be the first to experience the beauty of our cultural heritage and spiritual teachings. 🌐 Connect with Us: Follow Tewahedo Media Center on social media for behind-the-scenes glimpses, announcements, and community updates. Facebook:

https://www.facebook.com/tewahedomediacenter

Instagram: www.Instagram.com/tewahedo_media. Telegram:

https://t.me/tewahedomediacenter

Subscribe:

https://youtube.com/@TMC1

Tiktoke:

https://vm.tiktok.com/ZM8WVucY7/

🙏 Support TMC: If you appreciate our content, consider supporting Tewahedo Media Center. Your contributions help us continue sharing the wisdom and beauty of Ethiopian Orthodox Tewahedo Church with the world. 🔗 Explore More: #EthiopianOrthodox #TewahedoChurch #SpiritualJourney #CulturalHeritage #TMC 🎉 Thank you for being a part of Tewahedo Media Center! Subscribe, like, and share to spread the love and knowledge. #Tewahedo_Media_Center #EOTC #Ethiopian_Orthodox_Tewahdo_Church # #new_sibket_2023 #TMC

ዕለተ አርብ ሐዋርያው ቅዱስ ጳዉሎስ «አውቀውስ ቢሆን የክብርን ጌታ ባልሰቀሉት» /1ቆሮ.1-18/፡፡ እንዳለ ይህ ዕለት የአይሁድ ካህናት ያለበደል ያለጥፋት ንጹሕና ጻድቅ የሆነውን ጌታ የሰቀሉበት ዕለት ነው፡፡ ዕለቱም ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የዓለም ሁሉ መድኃኒት ለአዳምና ለልጆቹ ሲል በመልእልተ መስቀል በቀራንዮ አደባባይ ተሰቅሎ መዋሉን የምናስብበት ታላቅ ቀን ነው፡፡ /ማቴ.27-35-75/፡፡ በዚያን ጊዜ አሳልፎ የሰጠው ይሁዳ እንደተፈረደበት አይቶ ተጸጸተ ሠላሳውንም ብር ለካህናት አለቆችና ለሽማግሎች መልሶ ንጹሕ ደም አሳልፌ በመስጠቴ በድያለሁ አለ፡፡ እነርሱ ግን እኛስ ምን አግዶን? አንተው ተጠንቀቅ አሉ፡፡ ብሩንም በቤተ መቅደስ ጥሎ ሔደና ታንቆ ሞተ፡፡ የካህናት አለቆችም ብሩን አንሥተው የደም ዋጋ ነውና ወደ መባ ልንጨምረው አልተፈቀደም አሉ፡፡ ተማክረውም የሸክላ ሠሪ መሬት ለእንግዶች መቃብር ገዙበት፡፡ ስለዚህ ያ መሬት እስከ ዛሬ ድረስ የደም መሬት ተባለ፡፡ /ማቴ.27-3-9/ የሰው ልጆች በዘር ኃጢአት /ቁራኝነት/ ይኖሩበት የነበረው የጨለማ ሕይወት ያከተመበት ፍጹም ድኅነት ያገኙባት ታላቅ ዕለት ናት፡፡ ክርስቲያኖች ሁልጊዜም ዕለተ ዓርብ ሲመጣ ሕማሙን ስቅለቱን ሞቱን የሚያስቡበት ጊዜ ነው፡፡ በሮማውያን ሕግና ሥርዓት መስቀል የወንጀለኞች መቅጫ ምልክት የሕይወት መቅጫ አርማ ሆኖ ሳለ ለእኛ የዲያብሎስ ድል መንሻ ስላደረገው በስቅለቱና በሞቱም ሕይወትን ስለአገኘን በዚህም ምክንያት መልካሙ ዓርብ በመባል እንደሚታወቅ የቤተ ክርስቲያን አባቶች ያትታሉ፡፡ የስቅለት ዓርብ ይባላል ጌታችን የመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለአዳምና ለልጆቹ ሁሉ ቤዛ ሆኖ በመልዕልተ መስቀል ላይ ተሰቅሎ የዋለበት ዕለት ነውና ማቴ ፳፯፥፴፭ የስቅለት ዓርብ ይባላል። መልካሙ ዓርብ ይባላል ከጌታ ስቅለት በፊት በተለይም በሮማውያን ህግ የወንጀለኛ መቅጫ ምልክት የነበረውን መስቀል ጌታችን በደሙ ቀድሶ የምህረት፣ የሕይወት አርማ፣ የዲያቢሎስ ድል መንሻ ስላደረገው፤ በሞቱ መልካሙን ሕይወት ስላገኘን መልካሙ ዓርብ ይባላል።
Show all...
#ጌታችን_መድኃኒታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ_የተቸነከረባቸው_አምስቱ_ቅንዋተ_መስቀል_ችንካሮች፦ 1ኛ ሳዶር፣ በሚባል ችንካር ቀኝ እጁ የተቸነከረበት 2ኛ አላዶር፣ በሚባል ችንካር ግራ እጁ የተቸነከረበት 3ኛ ዳናት፣ በሚባል ችንካር ሁለት እግሮቹ የተቸነከረበት 4ኛ አዴራ፣ በሚባል ችንካር ደረቱን አጣብቆ እንዲይዘው የተቸነከረበት 5ኛ ሮዳስ፣ በሚባል ችንካር ከወገቡ (እምብርቱን) አጣብቆ እንዲይዘው የተቸነከረበት #ማስታወሻ አንዳንድ መጽሐፎች ይህ የአይሁድ ንጉስ ነው ብለው የጻፉበትንም እንደ ቅንዋት ይቆጥሩታል። ይህ ሁሉ ስለ እኔ ኃጥያት አንተ ዋጋ ከፈልክልኝ! ስለ ማይከፈለው ውለታህ ስማያልቀው ምህረትህ ስለ ማይሰስተው ፍቅርህና ስለ ቸርነትህ ስለ ማይነገረው ውለታህ ተመስገንልኝ ጌታዬ!!
Show all...
#ምሴተ_ሐሙስ ☞የተቀደሰውን ስዕል ልብ ብላችሁ ተመልከቱት! (ቅዱስ #ጴጥሮስ የጌታን እግር እያጠበ ነው) ✝በቤተክርስቲያን ትውፊት ጌታ ደቀመዛሙርቱን በትህትና ካጠባቸው በኋላ፦ ፩. ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ ጌታ ታጥቋት የነበረችውን "መክፌ" ተቀብሎ ታጥቋታል፤ በዚህ ከንጽሐ ጠባይእ ማዕረግ ደርሷል። ፪. አስቀድሞ "አልታጠብም" በሚል ተከራክሮ የነበረ ቅዱስ ጴጥሮስ (ፈጣሪነቱን ቢያስብ፥ ትህትናው ቢበዛበት) እሺ ብሎ ታጥቧል። ኋላም "ካልቀረስ እኔም ልጠብህ" ብሎ ጌታን ለምኖታል፡፡ ጌታም "እሺ" ብሎ ታጥቦለታል፡፡ ይህም ለቅዱስ ጴጥሮስ የክብር ክብር ሆኖለታል፡፡ (ለመኑ ተውህበ!) በዚህ አብነትም በአድባራቱ ፥ በገዳማቱ ትልልቆቹ (ሊቃነ ጳጳሳት፡ ጳጳሳት፡ ኤጲስ ቆጶሳት፥ ቆሞሳት፡ አበምኔቶች፡ ገበዛዝቱ) አስቀድመው ያጥባሉ! ኋላ በፈንታው ካህናት ያጥቧቸዋል! #አብነት የተቀደሰው ስዕል ደብረ መድኃኒት ዓቢየ እግዚእ (ጎንደር ውስጥ) ይገኛል፡፡ እንኳን አደረሳችሁ! ሐዋርያቱን በትህትና ያጠበ ቸሩ መድኃኔዓለም ፥ እኛንም ከከፋው ነገር ሁሉ ልቡናችንን ይጠብልን! አሜን!
Show all...