cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

Advertising posts
267
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

በጉራጌ ዞን ጉንችሬ ከተማ በግጭት ሳቢያ በሰውና በንብረት ላይ ጉዳት ደረሰ! ሁሌ አዲስ ሚዲያ የሙስሊም ሴት ተማሪዎች የተሟላ ሒጃብ (ኒቃብ) በሚማሩባቸዉ ትምህርት ቤቶች መልበስ አለብን በሚለው ጥያቄ ተነስቷል በተባለው ግጭት ከተማው ውጥረት ውስጥ ገብቶ ነበር። በደቡብ ክልል ጉራጌ ዞን ጉንችሬ ከተማ ላይ ያለፈው እሁድ ከምሽት ሁለትሁለት ሰዓት ጀምሮ እምነትን መሰረት አድርጓል በተባለዉ ጥቃት የግለሰብ መኖሪያ ቤቶችና የንግድ ተቋማት ሲወድሙ በሰዎች ላይ የአካል ጉዳት መድረሱን ሁሌ አዲስ ሚዲያ አረጋግጧል።  በከተማዋ በዋናነት ከ2014 ዓ.ም. ጀምሮ ይዘቱን እያሰፋ መጥቷል በተባለዉ ዉጥረት “በሙስሊም እና በኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች ዘንድ በሃይማኖታዊ ስርዓቱ ላይ የተፈጠረው አለመግባባት ሳቢያ ትላንት እሁድ ለተከሰተዉ ግጭት መነሻ” መሆኑን ምንጮች ገልፀዋል።   ዝርዝሩን ያንብቡ https://telegra.ph/%E1%89%A0%E1%8C%89%E1%88%AB%E1%8C%8C-%E1%8B%9E%E1%8A%95-%E1%8C%89%E1%8A%95%E1%89%BD%E1%88%AC-%E1%8A%A8%E1%89%B0%E1%88%9B-%E1%89%A0%E1%8C%8D%E1%8C%AD%E1%89%B5-%E1%88%B3%E1%89%A2%E1%8B%AB-%E1%89%A0%E1%88%B0%E1%8B%8D%E1%8A%93-%E1%89%A0%E1%8A%95%E1%89%A5%E1%88%A8%E1%89%B5-%E1%88%8B%E1%8B%AD-%E1%8C%89%E1%8B%B3%E1%89%B5-%E1%8B%B0%E1%88%A8%E1%88%B0-04-24
Show all...
በጉራጌ ዞን ጉንችሬ ከተማ በግጭት ሳቢያ በሰውና በንብረት ላይ ጉዳት ደረሰ

የሙስሊም ሴት ተማሪዎች የተሟላ ሒጃብ (ኒቃብ) በሚማሩባቸዉ ትምህርት ቤቶች መልበስ አለብን በሚለው ጥያቄ ተነስቷል በተባለው ግጭት ከተማው ውጥረት ውስጥ ገብቶ ነበር። በደቡብ ክልል ጉራጌ ዞን ጉንችሬ ከተማ ላይ ያለፈው እሁድ ከምሽት ሁለትሁለት ሰዓት ጀምሮ እምነትን መሰረት አድርጓል በተባለዉ ጥቃት የግለሰብ መኖሪያ ቤቶችና የንግድ ተቋማት ሲወድሙ በሰዎች ላይ የአካል ጉዳት መድረሱን ሁሌ አዲስ ሚዲያ አረጋግጧል።  በከተማዋ በዋናነት ከ2014 ዓ.ም. ጀምሮ ይዘቱን እያሰፋ መጥቷል በተባለዉ ዉጥረት “በሙስሊም እና በኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች ዘንድ በሃይማኖታዊ ስርዓቱ ላይ የተፈጠረው አለመግባባት ሳቢያ ትላንት እሁድ ለተከሰተዉ ግጭት መነሻ” መሆኑን ምንጮች ገልፀዋል።   ለሁሌ አዲስ ለደህንነታቸው ሲሉ ስማቸዉ እንንዳይጠቀስ የፈለጉና የጥቃቱ ሰለባ የሆኑ ምንጫችን ነዋሪነታቸዉን በጉንችሬ ካደረጉ ከ15…

"የሱዳን ወላፈን ለኢትዮጵያ ምኑ ነዉ"? (ተፃፈ በእያሱ ዘካሪያስ) ዛሬ 8ተኛ ቀኑን መያዙ በተነገረለት የሱዳን የእርስ በእርስ ጦርነት በመቶዎች ለሚቆጠሩ ንፁሃን ዜጎች ህልፈትና በእዛዉ ልክ ደግሞ ለግንባት ከሶስት ዓመት በላይና ከቢሊዮን ዶላር ፈሰስ የተደረጉባቸዉ መሰረተ ልማቶች በደቂቃዎች እንዲወድሙ ሆኗል። በርካቶች ጉዳት ደርሶባቸዋል ወደ ጎረቤት ሃገርም መሰደድ ጀምረዋል። የሁለቱ የጦር አበጋዞች የራሳቸዉን የስልጣን ጥም ለማርካት በማለት የዜጎች ሰላም ከመጠበቅ ይልቅ ምንም አይነት ደንታ እንደሌላቸዉ ያሳዩበት ክስተት መሆኑም እያነጋገረ ይገኛል። ይህ ብቻ አይደለም ሱዳን በተደጋጋሚ መፈንቅለ መንግስት በማድረግ በአፍሪካ ምን አልባትም በአለም አቀፍ ደረጃ ቀዳሚዋ ሳትሆን አትቀርም ። በመደበኛ ወታደሩና በፈጥኖ ደራሽ ኃይል መካከል የሚደረገዉ የስልጣን ሽኩቻ አንደኛዉ እጅ እስካልሰጠ ድረስ ማቆሚያዉ መች ይሁን ? የሚለዉ ጥያቄ አሳሳቢ ሆኗል። ኢትዮጵያ የቅርቤ ከምትላቸው ሀገራት ተርታ የምትመድባት ሱዳን በድንበር ብሎም በታላቁ ህዳሴ ግድብ ላይ በግብፅ ጋር በያዘችው አቋም ግንኙነታቸዉ ከጊዜ ወደ ጊዜ መሻከር ከጀመረ ሰነባብቷል። አልፋሽቃ ድንበርን ለመቀራመት የሚደረገዉ ትግል ሁለቱን ሀገራት ፍጥጫ ዉስጥ ከቷቸዋል። አሁን ኢትዮጵያ እና ሱዳን አለመተማመናቸዉ የሚጀምረዉ በድንበሮቻቸው ላይ በሺዎች የሚቆጠሩ ወታደሮቻቸዉን አስፍረዉ አሳቻ ሰዓት እየጠበቁ ጥቃት ማድረስ ነዉ። በተፈጥሮ ለም በሆነችዉና ለእርሻ ተስማሚ እንደሆነች በሚነገርላት የአልፋሽቃ ድንበር ይገባኛል በሚል ሁለቱ ሀገራት ፍጥጫ ዉስጥ መግባታቸው ይነገራል ምንም እንኳን ዲፕሎማሲያቸዉን ለማጠናከር ቢያስተባብሉም ። #ለዚህ ዉዝግብ መነሻ #የሆነዉ ምክንያቱ ምን ይሁን ? በፈረንጆቹ 1902 ተፈርሞ በነበረዉ አንግሎ-ኢትዮጵያ የካርታ ላይ ምልከታ ስምምነት አልፋሽቃ የእኔ መሆኑ ያሳያል ስትል ሱዳን ትከሳለች ። በቅኝ ግዛት ስምምነት ወቅት የአለም አቀፉ ድንበር ወደ ምስራቅ አምርቷል በዚህ ምክንያትም መሬቱ በሱዳን ተካቷል። ይሁን እንጂ ከ 1900 በፊት በስፍራዉ ቤተሰብ መስርተዉ የሚኖርበትና ግብር ደግሞ ለኢትዮጵያ ሲከፍሉም እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ቆይተዋል ። በተደረገው ስምምነትም ኢትዮጵያ ለዚህ እዉቅና ሰጥታለች ሱዳን በበኩላ ለዜጎቹ ነፃነታቸዉን እጠብቃለሁ በማለት በተለምዶ ድብቁ በተባለዉ መዝገብ ላይ ፊርማቸው አኑረዋል። በወቅቱ ሀገሪቷን ሲያስተዳድሩ የነበሩት ኦማር ሐሰን አል በሽር የኢትዮጵያ ሚሊሻዎች ወደ ድንበሩ ዘልቀዉ ሲገብና ጥቃት ሲፈፅሙ ዝምታን በመምረጣቸው የግጭቱ መንስኤ ነዉ ሲሉም ሱዳኖች ክሳቸዉን ጀምረዋል። በዚህ ሳቢያ ጦርነት የገጠሙት ሁለቱ አገራት አጨቃጫቂውን ድንበርን ለመቆጣጠር ሌትና ቀን ሲታትሩ ይዉላሉ ። እንደሁም በሰሜኑ ጦርነት እና በኦሮሚያና በአማራ ክልሎች ላይ ድጋፍ ለመስጠት በሚል ከድንበሩ ወደ መሃል ሀገር የገብትን ወታደሮች መሸሽ አጋጣሚዉን በመጠቅም ሱዳን ትግል ዉስጥ ገብታለች። ወደ ዋናዉ #ነጥቤ ልመሰለስ ... ኢትዮጵያ ሱዳንን የገጠመችዉ በአንድ ጉዳይ ብቻ ሳይሆን ሉዓላዊነቷን ላለማስደፈር የሚከፈለዉ መስዕዋትነት ተከፍሎ የበላይነቷን ማወጅ እንደሆነ መሸፋፈን አያስፈልግም ። በጦርነት ሰላም አይመጣም ነገር ግን ነፃነትን ለማወጅ የመጨረሻው መንገድ ነዉ የሚል አቋም ያላት ሱዳን 8ኛ ቀኑን በያዘዉ የተኩስ እሩምታ ትኩረታቸዉን ፈልገዉም ይሁን ተዘናግተዉ በአንድ አቅጣጫ ብቻ ላይ አድርገዋል። ከሱዳን የዜና ምንጮች ከሰሞኑ የተሰማዉ ኢትዮጵያ ጦሯን ወደ አልፋሽቃ ማስጠጋት ጀምራለች ተኩስ ተከፍቷል እስረኞች ተፈተዋል ..ብለዋል በኃላ ላይ ግን ዜናዉን አልተረጋገጠም ብሎ ማስተባበያ ቢሰጥም። የጠቅላዩ ፈጣን መግለጫ ደግሞ በአንድ በኩል የሚታየዉ የአዋሳኝ ድንበሩ ስጋት ምን ያህል እንደሆነ በግልፅ የታወቀበት ነዉ። ታዲያ ሆን ተብሎ ነዉ የሀሰት ዘገባ ነዉ በሚል መግለጫ ቢሰጥም ከዉስጥ የሚሰማዉ እና በእዉነታዉ ግን ኢትዮጵያ እድሉን መጠቀም ትፈልጋለች የሚለዉ ነዉ ። የጎረቤት ቤት ሲንኳኳ ይሰማል እኔ ጋር እንደሚለዉ ቢሂሉ የኢትዮጵያ የጦር ወታደሮች በዉስጥ ጉዳይ ላይ ትኩረታቸዉን በማድረግ ሰላም ማስከበሩ ዘመቻ ላይ በተሳተፉበት ወቅት ሱዳን ጦሯን ወደ አልፋሽቃ ድንበር አላስጠጋችም ? እሱ ብቻ አይደለም ተኩስ በመክፈት ለመቆጣጠር አልተቃረበችም? ታዲያ ኢትዮጵያን በዚህ ወቅት የአፀፋ ምላሽ አለመስጠቷ ምን ትርፍ አገኛለሁ ብላ ይሁን ? ( ተወያዩበት) ኢትዮጵያ በዲፕሎማሲያዊ ሂደት ላይ ያላትን አቋም የአለም ሀገራት ጠንቅቀው ያዉቁታል .. የሱዳኑ ግጭት ከተጀመረ ሳይዉል ሳያድር " ወደ ንግግር ተመለሱ ጦርነት አይበጅም" ስትል መግለጫ የሰጠች የመጀመሪያዋ ሀገር ነች። ግን ይሄም ቢሆን ቅድሚያ የሀገሪቷን ጥቅም ማስጠበቅ በመሆኑ ኢትዮጵያ የተደረገውን ስምምነት አክብራ ዜጎቿም በነፃነት እንዲኖሩ ማድረግ የመፈለግ አቅም እንዳላት እያሳየች ትገኛለች። ነገ ሌላ ቀን ነዉ አዲስ ነገር ይዞ ሊመጣ ይችላል ይህን አባባል የሁለቱም ባለስልጣናት በተደጋጋሚ ይጠቀሙታል።.... ይሄም ቢሆን በአልፋሽቃ የመጣ በአይኔ ብሌን ነዉ የሚመጣዉ ስትምል ሱዳን ተናግራለች ። በዚህ ሂደት የመጨረሻው መፍትሔ የሚሆነው ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚሄድበት ሂደት መሆኑ የማያከራክር ጉዳይ ነዉ። እያሱ ዘካሪያስ ( የግል እይታ ) @Hulaadiss
Show all...
ጣቢያውን ሆነ ፕሮግራሜን የሚከታተልልኝ አድማጭና ተመልካች በእጥፍ ተገኝቷል ተብሎ በተመልካች አይን እና ጆሮ ላይ እስከ መቼ ድረስ ይቀለዳል? በጋዜጠኝነት እና በአቅራቢነት መካከል ያለው ትልቅ ልዩነት የማይታይባት ኢትዮጵያ የኢትዮጵያ ሚዲያዎች አራተኛ መንግስት መሆን አይችሉም ለምን 1)ሚዲያው ላይ ያሉት ጥቂት ለሙያው መስዋዕትነት የሚከፍሉ ቢኖሩም አብዛኞቹ እንኳን ለጋዜጠኝነት ለእድር ጡሩምባ ነፊ አይመጥኑም 2)ሚዲያው ተቀበል ሚዲያ ነው 3)የግል ሚዲያ የሚባሉትም የጋዜጠኝነት ችሎታ ናፍላጎት ባላቸው ሰዎች ሳይሆን በዘመድ አዝማድ የተሞላ ነው 4)በተለይ ሴቶቹ በ host አድራጊ ስም ባ* ጭ* ቂ* ለማሳየት የተሰየሙ ይመስላሉ የቀረውን እመለስበታለሁ የሚዲያ ስነምግባርን (ethics) የሚጥሱ ያልተማረ ሆዳም ህሊናውን የሸጠ ማስተዋል የሚባል ነገር ያልፈጠረበት # ምስኪኑ ህዝብን ባህልና ወግን ረግጦ አፍኖ ምስኪኑን ዜጋን ያደናግራል ብቻ ሳይሆን የሙያውን ስነምግባር በቁሙ ገሎ ይቀብረዋል። ዘላባጁ ጋዜጠኝነት እንዴት አደብ ይግዛ? ሚዲያው በሌላ ሚዲያ፤ ጋዜጠኞችም በሌላ ጋዜጠኞች ስራቸው እየተመዘነ መተጋገዙና መተቻቸቱ ከዚያም አልፎ መወቃቀሱ ቢኖር አትራፊው ህዝብ ነው። የሚዲያ ስነምግባር ህጉስ ምን ይላል እስኪ እንወያይበት🙏
Show all...
ሳዑዲ የኢትዮጵያዊ የቤት ሰራተኞችን የቅጥር ክፍያ ይፋ አደረገች ለኢትዮጵያዊ የቤት ሰራተኞች ቅጥር መጀመሩን የሳዑዲ አረቢያ የሰው ሐብትና ማህበራዊ ልማት ሚኒስቴር በድረ ገፁ ይፋ ያደረገው ከሰአታት በፊት ሲሆን የክፍያውን(ጣሪያ) እደየሚመጡበት ሀገር የተለያየ መጠን አስቀምጧል። የክፍያው ምጣኔ ምን ላይ እንደተመሰረተ የማይጠቅሰው ይኸው የሳዑዲ የሰው ኃብትና ማህበራዊ ልማት ሚኒስቴር፣ የተገለፀው ክፍያ ቫትን ሳይጨምር እንደሆነም ይጠቁማል። ለኢትዮጵያዊ የቤት ሰራተኞች በሬን ከፍቻለሁ ያለው መስሪያ ቤቱ በቤት ሰራተኞቹ ቅጥር ላይ አገናኝ የሆኑ አካላትም ሆኑ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ካስቀመጠው የክፍያ ጣሪያ በላይ ዋጋ እንዳያቀርቡ የሚያስገድድ ሲሆን ለኢትዮጵያዊ ሰራተኞች 6,900 የሳዑዲ ሪያል እንዲሆን አስቀምጧል። የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ይህ ውሳኔ በቅጥር ገበያው የሚፈጠሩ የአሰራር ሂደቶችንና የዋጋ አስተዳደርን ለማደራጀት፣ እንዲሁም የቁጥጥር እና ክትትል ስራዎች አካል መሆኑን ይገልፃል። ህጋዊ ፍቃድ የተሰጣቸው ድርጅቶች እና መ/ቤቶችም የተቀመጠውን (ተጨማሪ እሴት ታክስ ሳያካትት) የክፍያ ጣሪያ መሰረት ብቻ ተግባራዊ የማድረግ ግዴታ መጣሉን ያሳስባል። የታወጀውን የክፍያ ጣሪያ በማክበርም ከቅጣት እንዲርቁ አስጠንቅቋል። የ 8 ሀገራት የቤት ሰራተኞች የተዘረዘሩበት ከላይ የተያያዘው ምስል ለፊሊፒንሳዊያን ከፍተኛው የክፍያ መጠን እንደተወሰነ ሲገልፅ፣ ዝቅተኛው ደግሞ ለኢትዮጵያዊያን የተተመነ ነው። =በሳዑዲ ሪያል= ▪️ኢትዮጵያ🇪🇹   6900 ▪️ቡሩንዲ🇧🇮    7500 ▪️ኡጋንዳ 🇺🇬    9500 ▪️ኬኒያ  🇰🇪     10,870 ▪️ ፊሊፒንስ 🇵🇭  17,288 የሳውዲ ሰው ኃብት ሚኒስቴር የቅጥር ገበያውን ለመቆጣጠር ደንበኞች ስለመብቶቻቸው እና ግዴታዎቻቸው እንዲሁም ስለ ቪዛ አሰጣጥ፣ የቅጥር ጥያቄ እና የውል ግንኙነትን ጨምሮ ተያያዥ አገልግሎቶችን እንዲያውቁ የሚረዳ ግልፅ አሰራር ለቤት ሰራተኞች አዘጋጅቻለሁ ብሏል። ለወቅታዊ እና ለፈጣን መረጃዎች የሁሌ አዲስ ሚዲያ የማህበራዊ ሚዲያዎችን ይቀላቀሉ። Facebook : https://www.facebook.com/Huleadissmedia/ Telegram : https://t.me/Hulaadiss YouTube Channel https://www.youtube.com/@huleaddismedia
Show all...
Log in or sign up to view

See posts, photos and more on Facebook.

እውቁ ጊኒያዊው ሙዚቀኛውና ባለሀብቱ ግራንድ ፒ እና ሮናልዲኒሆ ጎቹ በጊኒ ኮናክሬ የእርዳታ ማሰባሰቢያ ጨዋታ ላይ ተገናኝተው ለደሀው ማህበረሰብ አለኝታነታቸውን በተግባር አሳይተዋል። የኛስ ባለብቶችና ሙዚቀኞች ወዴት አላችሁ??? ለቦረና ፣ ለደቡብ ኦሞ ህዝብ ቀናነታችሁ የት አለ???
Show all...
መንግሥት በኢንተርኔት ግንኙነት ላይ የጣለውን ገደብ እንዲያነሳ ተጠየቀ መንግሥት በኢንተርኔት ግንኙት ላይ የጣለው ገደብ ሚዲያዎች ላይ ተጽእኖ እየፈጠረ በመሆኑ፣ ገደቡ እንዲያነሳ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ምክር ቤት ዛሬ ባወጣው መግለጫ ጠይቋል፡፡ ምክር ቤቱ በመግለጫው፣ መንግሥት በአንዳንድ የማኅራዊ ሚዲያ መተግበሪያዎች ላይ የጣለው ገደብ መገናኛ ብዙሃን መረጃ የማሰባሰብ፣ የማደራጀት እና ለሕዝብ ተደራሽ የማድረግ ሥራቸው ላይ ተግዳሮት ፈጥሯል ብሏል፡፡ በተለይ ኢንተርኔትን መሰረት ያደረገ የሚዲያ ሥራ በሚሰሩ ሚዲያዎች ላይ የፈጠረው ተጽእኖ ከፍተኛ መሆኑን ምክር ቤቱ ጠቁሟል፡፡ መገናኛ ብዙኃን ሥራቸው በማግባቡ ለሕዝብ ተደራሽ እንዳያደርጉ እንቅፋት የሆነው የኢንተርኔት ገደብ እንዲሳ ምክር ቤቱ ጠይቋል፡፡ አገልግሎቱ የተቋረጠባቸው የማኅበራዊ ሚዲያዎች ፌስቡክ፣ ቴሌግራም፣ ቲክቶክ እና ሜሴንጀር ሲሆኑ፣ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ችግር ጋር በተገናኘ መንግሥት በማኅበራዊ ሚዲያዎች ላይ የኢንተርኔት ገደብ ከጣለ 20 ቀናቶችን አስቆጥሯል፡፡
Show all...
አፄ ሚኒልክ የአፍሪካ የድል አድራጊ ዋነኛ ተምሳሌት ጀግና መሪ!💪 ለእናት ሀገራቸው በዱር በገደሉ አጥንታቸውን ከስክሰው ደማቸውን አፍስሰው በድል ወደፊት ላራመዷት ጀግኖች ሰማዕታት ክብር ይገባቸዋል🇪🇹🙏
Show all...
ውድ የሀገሬ ልጅ እህት ወንድሞቼ የቦረና ህዝብ የተረጂዎች ቁጥር ከ604 ሺህ በላይ ደርሷል። የቦረናን ህዝብ እንደግፋለን የምትሉት ሀሳብ አስተያየታቸውን አጋሩልን። እባካችሁ እንደግፍ። የማይነጥፍ የድጋፍ እጃችሁን አሳዩን!!!
Show all...
ዛሬ የአለም የሬዲዮ ቀን "ሬዲዮ እና ሰላም" በሚል መሪ ቃል በዓለምአቀፍ ደረጃ ለ12ኛ ጊዜ እየተከበረ ይገኛል ዛሬ የአለም የሬዲዮ ቀን "ሬዲዮ እና ሰላም" በሚል መሪ ቃል ለ12ኛ ጊዜ የሚከበር ሲሆን በኢትዮጵያም ለ6ኛ ጊዜ በመከበር ላይ ይገኛል፡፡ የአለም የሬዲዮ ቀን እ.ኤ.አ. በ2011 በዩኔስኮ አባል ሀገራት ለመጀመሪያ ጊዜ የተከበረ ሲሆን ፣ እ.ኤ.አ. በ2012 የተባበሩት መንግስታት ጠቅላላ ጉባኤ ይፋዊ የአለም አቀፍ ቀን እንዲሆን አድርጎታል። ሬድዮ የሰው ልጆችን የሃሳብ ልዩነት ለማክበር እና ለዲሞክራሲያዊ ንግግሮች መድረክ ሆኖ የሚያገለግል ሚዲያ ነው። እንደ ዓለም አቀፍ ዘገባዎች ፣ ሬዲዮ በዓለም አቀፍ ደረጃ በስፋት ጥቅም ላይ የሚውል እና ታማኝ ሚዲያ ሆኖ ቀጥሏል። ሬድዮ ከፍተኛውን ተመልካች የማድረስ ልዩ ችሎታ ስላለው የህብረተሰቡን የብዝሃነት ልምድ በመቅረፅ ሁሉም ድምጽ የሚናገርበት፣ የሚወከልበት እና የሚሰማበት መድረክ ሆኖ እያገለገለ እንደሚገኝ ከተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የትምህርት ፣ የሳይንስና የባህል ተቋም ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
Show all...
''አሽር ቤት'' ======= መጽሐፉ በአጠቃላይ 46 አጫጭር ክፍሎችን ይዟል። መጽሐፉ በዋናነት የሚያተኩረው ስለአብሮነት፣ ስለማይጠገበው ልጅነት፣ ስለአሽር ቤት ልጆች እና ስለቄስ ትምህርት ቤት ነው። የምረቃው ፕሮግራምም ልክ እንደ መጽሐፉ አብሮነታችንን የምናሳይበት ነው። ሁላችሁንም ተጋብዛችኋል። እንዳትቀሩ። የፕሮግራሙ መግቢያ መጽሐፉ ነው። የመጽሐፉን የሽፋን ዋጋ ብር 290 ቀድማችሁ ገቢ በማድረግ ስክሪንሾት አድርጋችሁ በኢንቦክስ ለ Hawlet Ahmed ኮድ ትልካላችሁ። በዚያ ኮድ መጽሐፉን የምረቃው ቀን መውሰድና ፕሮግራሙን መታደም ትችላላችሁ። የምረቃ ቀን: የፊታችን ቅዳሜ የካቲት 11 ቀን 2015 ሰዓት: ከጠዋቱ 2:30 - 6:00 ቦታ: ፒያሳ ሀገር ፍቅር ትልቁ አዳራሽ አካውንት ቁጥር: CBE 1000003155084 (Hawlet Ahmed Beshir)
Show all...