cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ዜና ቤተክርስቲያን

የተለያዩ በቅድስት በቤተክርስቲያን ዙሪያ መነሻ ያደረጉ ዜናዎችን ከቤተክርስቲያን ልሳናት ከሆኑ ምንጮች በማቅርብ መረጃ መለዋወጥ።

Show more
Advertising posts
1 608
Subscribers
No data24 hours
+37 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

"ያልታወቁ ስንባል የታወቅን ነን፤ የምንሞት ስንመስል እነሆ ሕያዋን ነን፤ የተቀጣን ስንሆን አንገደልም፤ ኀዘንተኞች ስንሆን ዘወትር ደስ ይለናል፤ ድሆች ስንሆን ብዙዎችን ባለ ጠጎች እናደርጋለን፤ አንዳች የሌለን ስንሆን ሁሉ የእኛ ነው።" ~ ፪ኛ ቆሮንቶስ ፮: ፱-፲
Show all...
👍 1
Photo unavailableShow in Telegram
አማላጃችን ሚካኤል ሆይ ፈጥኖ ደራሻችን ሚካኤል ሆይ የጌታን ዙፋን ከሚያጥኑ ሱራፌል ካህናት አንዱ ሰማያዊ ካህን አንተ ነህ ። የሰማያውያን ሊቃነ መላእክት ሁሉ አንተ አለቃቸው ነህ ። ይልቁንም የልዑላንም ልዑል አንተ ነህና በጠራሁህ ጊዜ ሁሉ በይቅርታና በቸርነት ድረስልኝ አትራቀኝ። (መልክአ ሚካኤል) ቅዱስ ሚካኤል ከክፉ ጠላት ይጠብቀን፤ ሀገራችንን ሰላም ያድርግልን።
Show all...
👍 3
Photo unavailableShow in Telegram
#13ቱ_ሕማማተ_መስቀል👇 1. አክሊለ ሦክ (ወደ 70 የሚደርስ ራስ ቅሉ ላይ የተተከለ የብረት እሾኽ የያዘ ዘውድ ወይም አክሊል) 2. ተኰርዖተ ርእስ (ራሱን በዘንግ ወይም በዱላ መመታቱ/መቀጥቀጡ) 3. ተጸፍኦ መልታሕት (ጉንጩን ወይም ፊቱን በጥፊና በቦክስ መመታቱ) 4. ሰትየ ሐሞት (ተጠማሁ ብሎ ስለ ውሃ ፋንታ መራራ ሐሞትን መጠጣቱ) 5. ወሪቀ ምራቅ (በፊቱ በአካሉ ላይ በንቀትና በጥላቻ በመሳለቅ በመዘባበት ፊቱ ላይ ምራቅ መትፋታቸው) 6. ተቀስፎ ዘባን (6,666 ጊዜ የሾለ አጥንትና ብረት በታሰረበት ጅራፍ መገረፉ) 7. ተአስሮ ድኅሪት (የፍጥኝ ወደኋላ መታሰሩ ...በአፍ ጢሙ መደፋቱ) 8. ፀዊረ ጒንደ ዕፀ መስቀል (የሚሰቀልበትን የእንጨት መስቀል መሸከሙ) 9. ሳዶር (ቀኝ እጁ ከመስቀሉ ጋር የተጣበቀበት ችንካር) 10. አላዶር (ግራ እጁ ከመስቀሉ ጋር የተጣበቀበት ችንካር) 11. ዳናት (ቀኝ እግሩ መስቀሉ ከቆመበት ፍልፍል ግንድ ጋር የተጣበቀበት ችንካር) 12. አዴራ (ግራ እግሩ መስቀሉ ከቆመበት ፍልፍል ግንድ ጋር የተጣበቀበት ችንካር) 13. ሮዳስ (ደረቱ ከመስቀሉ ጋር እንዲጣበቅ ከታሰረበት ሽቦ ጋር ልቡ ላይ የተቸነከረ...) አሥራ ሦስቱ ሕማማተ መስቀል የሚባሉት እሊህ ናቸው ብዙውን አንድ ብዙውን አንድ እያሉ በመቁጠር መናገር ነው እንጂ የመከራው ብዛት የስቃዩ ጽናት በቁጥር የሚገለጽ ሆኖ አይደለም!!! ጌታ ሆይ! ሕማምህ ይፈውሰን ዘንድ ቁስልህ እንዲሰማን ማስተዋልን ስጠን 🙏🙏🙏 እንበለ ደዌ ወሕማም እንበለ ፃማ ወድካም ዓመ ከመ ዮም ያብጽሐነ ያብጽሕክሙ እግዚአብሔር በፍሥሓ ወበሰላም አሜን! ምንጭ ፦ ቅዳሴ ማርያም አንድምታ ትርጓሜ
Show all...
👍 1
Photo unavailableShow in Telegram
❝ ወደ መሬት ወድቀን በሰገድን ጊዜ ኃጢአት እንዴት ወደ ታች ጎትታ እንደጣለችን እናስታውሳለን። ዳግመኛም ከወደቅንበት በተነሣን ጊዜ የእግዚአብሔር ጸጋ እና ምሕረት እንዴት ከመሬት እንዳነሣንና የሰማዩን ርስት እንደሰጠን እንመሰክራለን።❞ ቅዱስ ባስልዮስ ዘየዐቢ
Show all...
Photo unavailableShow in Telegram
« በፋሲካ ሰሞን የጽድቅ አምላክ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር የእግዚአብሔር ሀገር ወደምትሆን ወደ ደብረ ዘይት አቅራቢያ ቀረቡ ብዙ ሕዝብ ብዙ አዛውንትና ሕፃናት የዘንባባ ዝንጣፊ ይዘው ሆሳዕና በአርያም እያሉ ተቀበሉት ፣ ኀይልን ይሰጣቸው ዘንድ በአህያ ውርንጫ ተቀምጦ በፍጹም ደስታ ወደ ኢየሩሳሌም ገባ ። ›› « መድኀኒትሽ ቀረበ ደረሰ አደባባይሽን ተመልከቺ ፤ በሕዝብሽ ደስ ይበልሽ ፤ ከአብርሃም ጋራ የተወዳጀ ከእንድርያስ ጋር በባሕር ላይ የተጓዘ ፤ ከዮሐንስ ጋር ወደ ዮርዳኖስ የወረደ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ቃል ኪዳን ያደረገ ፤ በሰንበት ቀን የዞረ ሆሳዕና ተባለለት ለዳዊት ልጅ ሆሳዕና በአርያም ይሁን እያሉ በአህያ ውርንጫ ተቀምጦ ወደ ኢየሩሳሌም ሀገር በምስጋና ገባ ›› ሲል ሊቁ ቅዱስ ያሬድ ስለ በዓሉ ድባብ ጠቅለል ባለመልኩ ነግሮናል ። ይህንን ታላቅ የምስጋና በዓል እያሰብን በአንድ ልብ በአንድ ቃል ለማመስገን አምላከ ቅዱስ ሚካኤል ይርዳን።
Show all...
"ሁሉን የያዘውን ያዙት፤ ሁሉን የሚገዛውን አሠሩት፤ የህያውን አምላክ ልጅ አሠሩት፤ በቁጣ ጎተቱት፤ በፍቅር ተከተላቸው። በሚሸልተው ፊት እንደማይናገር እንደ የዋህ በግ በኋላቸው እየተከተለ ወሰዱት፤ ሊቃነ መላእክት በመፍራት እና በመንቀጥቀጥ ከፊቱ የሚቆሙለትን በአደባባይ አቆሙት፤ ኃጢአትን ይቅር የሚለውን ኃጥእ አሉት፥ በመኳንንት የሚፈርደውንም በእርሱ ፈረዱበት፤ ለሱራፌል ዘውድ የሚያቀዳጃቸውን የሾህ ዘውድ አቀዳጁት፤ ለኪሩቤል የገርማ ልብስ የሚያለብሳቸውን ለመዘበት ቀይ ግምጃ አለበሱት፤ ኪሩቤል በእሳት ክንፍ ተሸፍነው በፊቱ የሚሰወሩለትን እርሱን ክፉ ባሪያ አሥሮ ፊቱን ጸፋው፤ የመላእክት ሠራዊት በፍጹም መደንገጥ የሚሰግዱለት እየዘበቱበት በፊቱ ተንበረከኩ፡፡ ይህን ያህል ትህትና እንደምን ያለ ትህትና ነው? ይህን ያህል ትእግስት እንደምን ያለ ትእግስት ነው? ይህን ያህል ዝምታ እንደምን ያለ ዝምታ ነው? ይህን ያህል ቸርነት እንደምን ያለ ቸርነት ነው? ኃያል ወልድን ፍቅር ከዙፋኑ ሳበው እስከ ሞትም አደረሰው በደል የሌለበትን እንደበደለኛ ሰቀሉት፡፡ ህይወትን የሠራውን ከበደለኞች ጋር ቆጠሩት፤ አዳምን የሠሩ እጆች በመስቀል ቀኖዎት ተቸነከሩ፤  ወዮ በገነት የተመላለሱ እግሮች በመስቀል ተቸነከሩ፡፡ ወዮ በአዳም ፊት የህይወት እስትንፋስን እፍ ያለ አፍ ከሃሞት ጋር የተቀላቀለ የኮመጠጠ መፃፃን ጠጣ፤... ወዮ የወልድን መከራውን የሚናገር ምን አፍ ነው? ምን ከንፈር ነው? ምንስ አንደበት ነው? የፍቁሩ የጌታ ህማማት በተነገረ ጊዜ ልብ ይለያል፤ ህሊናም ይመታል፤ ነፍስም ትንቀጠቀጣለች፤ ሥጋም ይደክማል የማይሞተው ሞተ፤ ሞትን ይሽረው ዘንድ ሞተ፤ ሙታንን ያድናቸው ዘንድ ሞተ። የምትወዱት ሰዎች ፈጽሞ አልቅሱለት፡፡" https://t.me/zenaTewahedo16
Show all...
ዜና ቤተክርስቲያን

የተለያዩ በቅድስት በቤተክርስቲያን ዙሪያ መነሻ ያደረጉ ዜናዎችን ከቤተክርስቲያን ልሳናት ከሆኑ ምንጮች በማቅርብ መረጃ መለዋወጥ።

Photo unavailableShow in Telegram
+++ የማርያም መንገድ +++ ድሮ በልጅነት ከባልንጀሮች ጋር በየጎዳናው ላይ ስንበር ስንባረር አባራሪው ደርሶ መንገዱን ከዘጋ ከግራና ከቀኝ ማምለጫ ካሳጣ ተባራሪ ምስኪን መንገድ የጠበበው በጭንቁ 'ሚጠራት አንዲት ዋስ አለችው የእርሷን ስም ካነሣ የጠበበ ይሰፋል የተዘጋው ሁሉ መንገድ ይከፈታል ቀን በጎደለበት ባገኘው መከራ በጨነቀው ስዱድ ስሟ የሚጠራ ማርያም እርሷ ነች ሁሉን 'ምታራራ። ጸወን መጠጊያ ለሆነችን ለድንግል ማርያም ዓመታዊ በዓል እንኳን አደረሰን። ጭንቅ እና መከራ በተሞላ ዓለም ውስጥ ከክፋ ቀን ሁሉ የምንወጣበትን "የማርያም መንገድ" የሰጠን አምላካችን ስሙ የተመሰገነ ይሁን! ዲያቆን አቤል ካሳሁን ✅ቻናላችንን ለማግኘት👇👇         
Show all...
👍 2
Photo unavailableShow in Telegram
ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ ወደ አገር እንዳይገቡ ተከለከሉ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ እና የኒውዮርክና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በአሜሪካ የነበራቸውን ሐዋርያዊ አገልግሎት ጨርሰው ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርሱ እንዳይገቡ መከልከላቸው ተሰምቷል። ብፁዕነታቸው ከሳምንታት በፊት በቋሚ ሲኖዶስ እውቅና ወደ ሀገረ ስብከታቸው በመሄድ የአጋእዝተ ዓለም ሥላሴ ዓመታዊ በዓል፣ የከተራና የጥምቀት በዓላትን ከመንፈስ ልጆቻቸው ጋር ያከበሩ ሲሆን ለአዳጊ ሕጻናትም ማዕረገ ዲቁና መስጠታቸው ይታወቃል። ብፁዕነታቸው በአሁኑ ሰዓት ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያው እንደሚገኙ ታውቋል።
Show all...