cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

Grace Gospel

ትውልድ የእግዚአብሔርን ፍቅር በመማር በእግዚአብሔር ፍቅር ህይወቱ እንዲቀየር ለማድረግ የጸጋውን ወንጌል እናስተምራለን። Comment @EsseyShalom @Metu_boy

Show more
Advertising posts
485
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

ቀነአ / Rightly Dividing / orthotomeō ክፍል አንድ ሁሉም ክርስቲያን መጽሃፍ ቅዱስ ማንበብ እንዳለበት ሁል ጊዜ ይነገራል ሆኖም ግን አብዛኛው ክርስቲያን ጋር ያሉ ሁለት መሰረታዊ ችግሮች አሉ። የመጀመርያው መጽሃፍ ቅዱስ አለማንበብ ነው፤ ይህ በአብዛኛው አማኝ ዘንድ የሚስተዋል ችግር ነው(አማኙ መዝሙር እንጂ ቃል አያውቅም) ሁለተኛው ዋና ችግር ደግሞ እንዴት እንደሚነበብ አለማወቅ ነው (አሁን እያስተማርን ያለነው ማለት ነው) የእኛም አላማ እንደገለፅነው ሁሉም ይህ መልዕክት የሚደርሳየው በሙሉ በትክክል የእግዚአብሄርን ቃል ከፍለው እንዲመገቡ ማስቻል ነው። ሆኖም እንዴት መብላት እንዳለብን የሚወራው የመብላት ፍላጎት ላለው ነውና ልባችሁን ለእግዚአብሄር ቃል በመክፈት ዘወትር ቃሉን የምታነቡ እንድትሆኑ ያስፈልጋል ፤ለዚህም የቃል ረሃብ እንዲገቡባችሁ ጸሎታችን ነው። ወደቆምንበት ሃሳብ ስንመለስ የእግዚአብሄርን ቃል በምን በምን እንደምንከፍል ካወራንበት መንገዶች መካከል አንዱን ዛሬ ለማየት እንሞክራለን። ኪዳን ኪዳን ማለት ምን ማለት ነው? 📌ኪዳን በሁለት አካላት መካከል የሚደረግ ግንኙነትን የሚወስን ህጋዊ ስምምነት ነው። መጽሃፍ ቅዱሳችን ውስጥ እግዚአብሄር ከሰዎች ጋር ግንኙነት የሚመሰርተው በኪዳን አማካኝነት ሲሆን፤ ይህ ኪዳንም በእግዚአብሄር እና በሰው መካከል ያለውን ግንኙነት የሚወስን ድልድይ ነው። እግዚአብሄርን ለማብራራት ኪዳኑ ምን አይነት እንደሆነ ልናውቅ ይገባል ፤ ምክንያቱም እርሱ ኪዳኑን የማያፈርስ ስለሆነ በተገባው ኪዳን መሰረት እራሱን ይገልጣል። መጽሃፍ ቅዱሳዊ ኪዳን እነኚህን 3 ነገሮች ሊያሟላ ይገባል። ✍የተስፋ ቃል-የኪዳኑ እንብርት/መሰረት ሲሆን በቅድመ ሁኔታ ላይ የተመሰረተ ወይም ያልተመሰረተ ሊሆን ይችላል። ✍የቃልኪዳኑ ተጋቢዎች -ሁለት አካላት(እግዚአብሄር እና ሰው) ✍የቃል ኪዳኑ ማፅኛ - ደም በተጨማሪም ምልክት ሊኖር ይችላል። 📌በኪዳን ከፋፍለን ስናይ ወሳኝ የሆኑ 3 ኪዳኖች በመጽሃፍ ቅዱስ ውስጥ እናገኛለን። እነሱም፦                1, የአባቶች ኪዳን                2, የሙሴ/የብሉይ ኪዳን                3, አዲስ ኪዳን የአባቶች ኪዳን የአባቶች ኪዳን በውስጡ የአዳም ኪዳን, የኖህ ኪዳን እና የአብርሃም ኪዳን ይዟል። የአዳም ኪዳን እግዚአብሄር ከሰው ውድቀት በኋላ ለሰው ልጅ የደህንነት ተስፋን በመስጠት የገባው የመጀመርያ ኪዳን ነው። የተስፋ ቃል “በአንተና በሴቲቱ፣ በዘርህና በዘሯ መካከል፣ ጠላትነትን አደርጋለሁ፤ እርሱ ራስህን ይቀጠቅጣል፤ አንተም ተረከዙን ትቀጠቅጣለህ።””   — ዘፍጥረት 3፥15 (አዲሱ መ.ት) የሰው ልጃች ከወደቁበት የሚያነሳ አዳኝ እንደሚላክላቸው ለእነርሱ ደህንነት ዋጋ እንደሚከፍል(አንተም ተረከዙን ትቀጠቅጣለህ) ነገር ግን በድል የደህንነታችንን ስራ እንደሚሰራ የሚያሳይ ነው(እርሱ ራስህን ይቀጠቅጣል)። የኪዳኑ ማፅኛ “እግዚአብሔር አምላክ (ያህዌ ኤሎሂም) ከቈዳ ልብስ አዘጋጅቶ አዳምንና ሚስቱን አለበሳቸው።”   — ዘፍጥረት 3፥21 (አዲሱ መ.ት) እዚህ ጋር ቆዳ አለበሳቸው የሚል እናያለን በመጀመርያዎቹ የፍጥረት ምዕራፎች እግዚአብሄር ቆዳ እንዳልፈጠረ ግልፅ ነው። ይህ ቆዳ ከየት መጣ ለሚለው ጥያቄ ቆዳ የሚገኘው በሚሞት/በሚታረድ እንስሳ አማካኝነት ስለሆነ ለኪዳኑ ማፅኛነት ደም ፈሷል። ✍ይህ ኪዳን ቅድመ ሁኔታ ላይ የተመሰረተ ኪዳን አይደለም እግዚአብሄር ሰዎች ባደረጉት ሳይሆን እርሱ እራሱ ለዚህ ተስፋ ቃል ይሰራል። የኖህ ኪዳን በዘፍጥረት 9:8-11 እግዚአብሄር ከኖህ ጋር ያደረገው ኪዳን ሲሆን ሰው በምድር ላይ ሃጥያትን በጨመረ ጊዜ ኖህን እግዚአብሄር እንደመረጠው ለሚመጣው ጥፋት ውሃ እንዲዘጋጅ ከነገረው በኋላ ዳግመኛ ህያው ነፍስ ያላቸውን ፍጥረቶች ላለማጥፍት የገባው ኪዳን ነው። የተስፋ ቃል “እግዚአብሔርም (ያህዌ) ደስ የሚያሰኘውን መዐዛ አሸተተ፤ በልቡም እንዲህ አለ፤ “ምንም እንኳ ሰው ገና ከልጅነቱ ጀምሮ ሐሳቡ ወደ ክፋት ያዘነበለ ቢሆንም በእርሱ ምክንያት ሁለተኛ ምድርን አልረግማትም፤ አሁን እንዳደረግሁት ሕያዋን ፍጡራንን ዳግመኛ አላጠፋም።”   — ዘፍጥረት 8፥21 (አዲሱ መ.ት) የኪዳኑ ማፅኛ “ከዚያም ኖኅ ለእግዚአብሔር (ያህዌ) መሠዊያ ሠራ፤ መሠዊያው ላይ ንጹሕ ከሆኑት እንስሳት ሁሉ፣ እንዲሁም ንጹሕ ከሆኑት ወፎች የሚቃጠል መሥዋዕት አቀረበ፤”   — ዘፍጥረት 8፥20 (አዲሱ መ.ት) የኪዳኑ ምልክት -ቀስተ ዳመና (ዘፍጥረት 9:12-14) ✍ይህ ኪዳን ቅድመ ሁኔታ ላይ የተመሰረተ ኪዳን አይደለም። 📌ይህ ኪዳን አለምን ሁሉ በሀጥያት ምክንያት ዳግመኛ ላለመጥፋት ዋስትና ይሰጣል ።(ኢሳያስ 54:7-9) በቀጣይ የቀሩትን ኪዳኖች በጥልቀት የምናይ ይሆናልና ይህ መልዕክት ለሁሉም እንዲዳረስ መልዕክቱን በማጋራት ይተባበሩን። https://t.me/shalomgracegospel
Show all...
Grace Gospel

ትውልድ የእግዚአብሔርን ፍቅር በመማር በእግዚአብሔር ፍቅር ህይወቱ እንዲቀየር ለማድረግ የጸጋውን ወንጌል እናስተምራለን። Comment @EsseyShalom @Metu_boy

ቀነአ / Rightly Dividing / orthotomeō መግቢያ ከዚህ ቀደም ስለእግዚአብሄር ቃል ወሳኝ የሚባሉ ነገሮችን አንስተን በሰፊው አውርተናል የቀረውን ክፍሎች ከዚህ ትምህርት በኋላ እንደምንቀጥል ቃል እንገባለን። ከዚህ በመቀጠል ለእናንተ እንዴት የእግዚአብሄርን ቃል ማጥናት እንዲሁም ሃሳቡን መረዳት ይቻላል ስለሚለው ሃሳብ እናያለን። የዚህ ትምህርት ሃሳብ የሚነሳው ከመጽሃፍ ክፍል 2 ጢሞ 2:15 ይሆናል። “የእውነትን ቃል በቅንነት የሚናገር የማያሳፍርም ሠራተኛ ሆነህ፥ የተፈተነውን ራስህን ለእግዚአብሔር ልታቀርብ ትጋ።”   — 2ኛ ጢሞቴዎስ 2፥15 “Study to shew thyself approved unto God, a workman that needeth not to be ashamed, rightly dividing the word of truth."   — 2 Timothy 2፥15 (KJV) በዚህ ክፍል የማያሳፍር ሰራተኛ የተባለ ሰው ምን አይነት ነው የሚለውን ይመልስልናል እርሱም "የእውነትን ቃል በቅንነት የሚናገር" ይለዋል ። እዚህ ጋር ወደ ሌላ ትርጓሜ ከመሄዳችን በፊት "ቅንነት" የሚለው አማርኛ ቃል "ቀነአ" የሚል የግዕዝ ዋና ቃል ወይም ምኝጭ ያለው ሲሆን ትርጓሜውም ለሁለት እኩል መክፈል ወይም መሰንጠቅ ነው። በኢንግሊዘኛው KJV "rightly dividing the word of truth." በሚል ቀለል ባለ መልኩ ይናገራል። ስለዚህ የማያሳፍር ሰራተኛ ማለት ቀኑን ሙሉ ያስተማረ በጣም የተጋ ወይም እነዚህን የመሳሰሉትን ያደረገ ሳይሆን በትክክል የእግዚአብሄርን ቃል ከፋፍሎ የሚናገር ነው ፤ይህን ስንል ከላይ የጠቀስኩት አያስፈልጉም እያልን አይደለም ። የማያሳፍር ብለን ካነሳን የሚያሳፍር እንዳለ እንረዳለን የዚህ ትምህርትም አላማ ክርስቲያኖች በትክክል የእግዚአብሄርን ቃል ከፍለው እንዲመገቡ ለማስቻል ነው። ቀነአ / Rightly Dividing በምን? 📌በኪዳን ከፋፍለን 📌በህዝብ ከፋፍለን 📌በዘመን መግቦት/አስተዳደር ከፋፍለን 📌በመልዕክት ከፋፍለን 📌የተነገረበት መንገድ(እቅድ) ከፋፍለን በጥልቀት የምናይ ይሆናል። በእርግጠኝነት ይህ ትምህርት ህይወትን የሚለውጥ እንደሚሆን እርግጠኞች ነን! ለምትወዱት ለቤተሰብ ጓደኛ በማዳረስ የእርሶን አገልግሎት ያገልግሉ። https://t.me/shalomgracegospel
Show all...
Grace Gospel

#የእግዚአብሄር_ቃል ! #ክፍል_አንድ #ለምን_ስለ_እግዚአብሄር_ቃል_መማር_አስፈለገ ? 📌ለእግዚአብሄር ቃል ያለን እይታ ፣ስለ እግዚአብሄር ቃል ያለን ግንዛቤ እንዲሁም ለእግዚአብሄር ቃል የሰጠነው ዋጋ የእግዚአብሄር ቃል በህይወታችን ላይ ያለውን ተፅዕኖ ይወስናል ። የእግዚአብሄር ቃል በአማኝ ህይወት ውስጥ የሚሰራው አማኙ ስለ እግዚአብሄር ቃል መረዳት ልክ እንጂ ቃሉ ባለው ስልጣንና አቅም ልክ ወይም እግዚአብሄር እንዲሰራ በወደድነው ልክ አይደለም ፤ ይልቁንም ቃሉ የሚሰራው ስለቃሉ ባለን የተስተካከለ እውቀትና መረዳት ልክ ስለሆነ ስለ እግዚአብሄር ቃል መማር አስፈላጊ ነው። 📌ለእግዚአብሄር ቃል የምንሰጠው ትኩረት ለቃሉ ያለን አቀባበል እንዲቀየር ስለእግዚአብሄር ቃል እንማራለን፤ ምክንያቱም ቃሉ የእግዚአብሄርን ያክል ስልጣን ያለው መሆኑን መገንዘብ ያስፈልጋል። ለምሳሌ የቀበሌ አስተዳደር ቃል Operational የሆነበት ክልል የሚያስተዳድርበት ቀበሌ ላይ ብቻ ነው። በአንጻሩ የሃገሪቱ መሪ በሀገሪቱ ላይ የሚናገረው ሁሉ ተግባራዊ ይሆናል፣ ይገዛል የእርሱ ቃል የእርሱን ስልጣን ያህል ያዝዛል። ስለዚህ የእግዚአብሄር ቃል የስልጣኑ ልክ የእግዚአብሄርን ስልጣን ያህል ያክላል ።እግዚአብሄር ማዘዝ የሚችለውን መስራት የሚችለውን ያክል ማድረግ ይችላል። ቃል የሚሻረው በቃል ነው!! በቅድሙ ምሳሌ መሰረት የአንድ ቦታ አስተዳዳሪ ከእርሱ በተሻለ ስልጣን ባለው ሰው ቃሉ ወይንም ውሳኔው ሊሻር ይችላል። በህይወታችን ላይ ሰይጣን፣ ሰዎች ሁኔታወች ወዘተ ...የሚናገሩብንን ክፉ ቃላት ለመሻር የሚያስችለንና የሚያስፈልገን ከሁሉ ቃላት በላይ ከፍ ያለ ስልጣን ያለውን የእግዚአብሄርን ቃል በተነገረብን ላይ ከፍ በማድረግ ቃልን በቃል መሻር ነው። ብዙ ሰዎች ሟርትን በተለይም የአማኝን ሟርት ይፈራሉ ማለት አንዳች…

@whoweareinchrist ፋሽን ነው? “....... #ያንኑ_ደግሜ_ብጽፍላችሁ_እኔ #አይሰለቸኝም፤ #ለእናንተም #ይጠቅማችኋል።” — ፊልጵስዩስ 3፥1 (አዲሱ መ.ት) ብዙ ጊዜ ሰዎች በተደጋጋሚ በእምነት ስለመፅደቃችን ስናወራ ምንድነው #ፋሽን #ነው #እንዴ ሁሉም ሰው #ፀድቀናል የሚለው ሁሌ ፅድቅ ፅድቅ ብቻ #የሚባለው #ይላሉ። ቆም ብዬ አንድ ነገር አሰብኩ እንደዚህ ሀይማኖተኞች ቃሉን ሲሰሙ የተበሳጩበት ይህ ቃል እውነት ጊዜ አመጣሽ ነው? ቀላል ዋጋ ያለው ነው ብዬ አሰብኩ #ነገር_ግን_ይህ_የፅድቅ_ትምህርት_ሰው_ሰራሽ_እና_ጊዜ_አመጣሽ_ሳይሆን_እግዚአብሔር_አጥብቆ_የሚወደው_ልጁን_አጥብቆ_የሚጠላውን_ሀጢዓት_ያደረገበት_ኢየሱስ_ዋጋ_የከፈለበት_እውነት_ነው። እና ምን አሰብኩ....... ✍️ ፋሽን ነው ብለህ ጂንስ ሱሪ፣ጫማ ፈልገህ ትገዛ የለ?*** #ምን_አለበት_ኢየሱስ_ዋጋ_የከፈለበትን_ፅድቅ_ፋሽን_አድርጌ_ብሰብከው #አው #ለኔ #በክርስቶስ_መፅደቄ_ፋሽን_ነው ለዛውም ጊዜ #የማያልፍበት #በጊዜ #ሂደት #የማይቀዘቅዝ #ፋሽን። ስለዚህ ዛሬም መልዕክት አለኝ በክርስቶስ ያመነ ሁሉ የእግዚአብሔር ፅድቅ ነው። “እንግዲህ #በእምነት_ስለ_ጸደቅን፣ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ከእግዚአብሔር ጋር #ሰላም #አለን።” — ሮሜ 5፥1 (አዲሱ መ.ት) ፅድቅ በእምነት ብቻ የሚገኝ የእግዚአብሔር ስጦታ ነው። ሮሜ 10:4፤ የሚያምኑ ሁሉ ይጸድቁ ዘንድ ክርስቶስ የሕግ ፍጻሜ ነውና። #ስለዚህ_መፅደቄ_ለኔ_አው_የማያልፍበት_ፋሽን_ነውና_ሁሌ_እሱን_አወራለው። በክርስቶስ የእግዚአብሔር ፅድቅ ነኝ። @whoweareinchrist
Show all...
#እጅ_ነስተናል ፤ #ልባችን_ላይ_እንደደመቁ_ይኖራሉ" 2 ጢሞቴዎስ 4 7፤ #መልካሙን_ገድል_ተጋድዬአለሁ፥ #ሩጫውን_ጨርሼአለሁ፥ ሃይማኖትን ጠብቄአለሁ፤ 8፤ ወደ ፊት #የጽድቅ_አክሊል_ተዘጋጅቶልኛል፥ ይህንም ጻድቅ ፈራጅ የሆነው #ጌታ_ያን_ቀን_ለእኔ_ያስረክባል፥ ደግሞም #መገለጡን_ለሚወዱት_ሁሉ_እንጂ_ለእኔ_ብቻ_አይደለም። "ቄስ በሊና ሳርካ ወደጌታ ሄዱ" በማለዳ ይህን ዜና ስሰማ ማመን አልቻልኩም እናም የተለመደ የፌስቡክ ውሸት ነው በሚል አለፍኩት ከዚያ ግን በተደጋጋሚ ይህ ዜና ሲዘዋወር ሳየው ፍጹም የተመሰቃቀለ ስሜት ተሰማኝ። ቄስ በሊናን የማያውቅ ብዙ ሰው አለ ብዬ ባላስብም እንደው በሕይወት እያሉ በቤተክርስቲያን እውቅናና ምስጋና ከመቀበል ይልቅ በአንዳንድ ተችቶ አዳሪ የእግዚአብሔር ጠበቆች ነን ባዮች ያ ሁሉ ውረፋ ቢደርስባቸውም ከጌታ ለተቀበሉት ራዕይ፥ለሰሙት ድምጽና፥ለተረዱት እውነት በፍጹም ታማኝነት፥በፍጹም ታዛዥነት፥በፍጹም ትጋትና በፍጹም መሠጠት ስላገለገሉ የሚጠብቃቸውን ታላቅ ክብር በሰማይ ከአባታቸው የሚቀበሉትን አክሊል ሳስብ ልቤ በረታ ተጽናናሁ። በእርሳቸው ወደጌታ መሄድ ያዘንኩት ለራሴና ለቤተክርስቲያን ነው። ምክንያቱም ለእሳቸው ሞት ጥቅም ነውና ሩጫቸውን ጨርሰው ወደአባታቸው ሄደዋል። ለቤተክርስቲያን ግን እንዲህ ያሉ አባት ማጣት የሚያሳጣት ብዙ ጥቅም አለ። ፊልጵስዩስ 1 20፤ ይህ ናፍቆቴ ተስፋዬም ነውና፤ በአንድ ነገር እንኳ አላፍርም ነገር ግን በህይወት ብኖር ወይም ብሞት፥ ክርስቶስ በግልጥነት ሁሉ እንደ ወትሮው አሁን ደግሞ በስጋዬ ይከብራል። ቄስ ስለአገልግሎት፣ስለጸሎት፣ስለመጋቢነት፣ስለአባትነት፣ስለትውልድ የበራላቸውን ምስጢር እካፈል ዘንድ የዘወትር ናፍቆቴ ነበር፤አንድ ቀን እጆቻቸውን ጭነው እንዲጸልዩልኝ ተስፋ አደርግ ነበር። ይህ ሳይሆን ግን እርሳቸው የተሰጣቸውን ሩጫ ጨረሱ። በእርሳቸው አገልግሎት ብዙዎች ወንጌል ሰምተዋል፥የዘላለም ሕይወት አግኝተዋል፥ብዙ ቤተክርስቲያናት ተተክለዋል፥ ብዙዎች ከነፍስም ከስጋም ደዌ ፈውስ አግኝተዋል። ከደርግ ዘመን ጀምሮ ብዙ እስራትና እንግልት ደርሶባቸዋል፤ይሁን እንጂ የእርሳቸው ስራ ስላልተፈጸመ ነፍሳቸውን ከስጋቸው ማንም መለየት አልቻለም ነበር። በተለይም ብዙ ክፍሉ ሲፈጸም እርሳቸው በአይነስጋ ለማየት የታደሉት መጽሐፋቸው "#የከፍታ_ዘመን_ለኢትዮጵያ" በእርሳቸው በኩል ለትውልድ ደርሷል። ጥርት ያለ ትንቢታዊ መልዕክት ፈጽሞ ለማመን የሚከብድ መልዕክት ያውም በዚያን ጊዜ 😮😮😮 እምነት የማይታየውን ማየትና እርግጠኛ መሆን ስለሆነ የሰሙትን ቃል አምነው በመጽሐፍ መልክ አስቀርተውልናል። ወንጌል የቅብብሎሽ ነውና እንግዲህ በእርሳቸው የተገለገለው በእኛም ይቀጥላል። #ከመቀመጫችን_ተነስተን_ከወገባችን_ተጎንብሰን_ለቤተክርስቲያን_ላበረከቱት_ታላቅ_አስተዋጽኦ_በፍጹም_መደነቅና_አክብሮት_እጅ_ነስተናል ፤ #ልባችን_ላይ_እንደደመቁ_ይቀጥላሉ። እስከምንገናኝ . . . ድረስ ማለት የምችለው ይህንኑ ነው። 💔💔💔💔💔💔💔💔💔💔💔💔💔💔 #GraceGospelChannel
Show all...
Grace Gospel

ትውልድ የእግዚአብሔርን ፍቅር በመማር በእግዚአብሔር ፍቅር ህይወቱ እንዲቀየር ለማድረግ የጸጋውን ወንጌል እናስተምራለን። Comment @EsseyShalom @Metu_boy

Photo unavailableShow in Telegram
“መልካሙን ገድል #ተጋድዬአለሁ፥ #ሩጫውን_ጨርሼአለሁ፥ ሃይማኖትን #ጠብቄአለሁ፤” — 2ኛ ጢሞቴዎስ 4፥7 #Father_Of_Faith!! #Father_of_Nation!! #ቄስ_በሊና_ሳርካ #የከፍታ_ዘመን_ለኢትዮጵያ!!🙏 #GraceGospelChannel
Show all...
የእግዚአብሄር ቃል ክፍል አስራ ሁለት የእግዚአብሄርን ቃል እንዴት እናጥና? የሁሉ መሰረት የሆነውን ፣እግዚአብሄር ራሱን በክርስቶስ የገለጠበትን ፣ስለእኛ ትክክለኛ እውቀት የያዘውን ይህን የእውነት ቃል ማጥናት እንደሚገባን ብቻ ሳይሆን አጠናኑን(እንዴት ማጥናት እንዳለብን) ጭምር ቃሉ ይነግረናል። 2ጢሞ 2:15(kjv) study(አጥና) የሚለውን ቃል ይጠቀማል እንዴት ለሚለው "Rightly dividing" ብሎ ይገልፃል ። "በቅንነት እንደሚያስረዳ" ቅንነት ማለት (ግዕዙ ቀነአ)ሲሆን ቀጥ አድርጎ መቁረጥ ማለት ነው ። ይህ ክፍል በአጭሩ እያለን ያለው "በልታችሁ ብሉ"ወይም "መብላት አለባችሁ ነገር ግን ከመብላት መበለት ይቀድማል"ነው። ከፍፍሎ ማጥናት ለምን አስፈለገ ? ምክንያቱም መጽሃፍ ቅዱስ 1600 በላይ በሆነ የዘመን ርቀት ልዩነት የተፃፈ መፅሃፍ ነው። እንዲሁም 7 በሚደርሱ የእግዚአብሄር አስተዳደር ስልቶች (መገለጦችና አሰራሮች)የተከፍፈለ መፅሃፍ ስለሆነ ነው። ስለዚህ ይህ የሚሰራው ፤ ህያው የሆነ ቃል ራሱ ቃሉ አጥኑኝ ባለው መንገድ በማጥናት ፈጣሪነቱን፣ህያውነቱን በህይወታችን ልንገልጥ ያሰፈልጋል። ይቀጥላል ክፍል 11ን ለማግኘት ይህን ይጫኑ https://t.me/shalomgracegospel
Show all...
Grace Gospel

ትውልድ የእግዚአብሔርን ፍቅር በመማር በእግዚአብሔር ፍቅር ህይወቱ እንዲቀየር ለማድረግ የጸጋውን ወንጌል እናስተምራለን። Comment @EsseyShalom @Metu_boy

የእግዚአብሄር ቃል ክፍል አስራ አንድ ከዚህም በላይ መጽሐፍቅዱስ ስለ ሰይጣን ስለ ጨለማ ስለ ሞት ስለሃጥያት ... ወዘተ ለማስተማር አልተፃፈም። ይልቅ መፅሃፉ በክርስቶስ ስለተገለጠልን ስለ እግዚአብሄር ፣ ስለ ብርሃን ስለ ጽድቅ ስለ ህይወትና አለመጥፋት ይናገራል ። እነዚህም አምላክ የተገለጠበትና እኛም በእርሱ ሆነን በፀጋው የተቀበልነውን የህይወት ስርዓት እንዲሁም በክርስቶስ ያለን ተፈጥሮ(ባህሪያት) ናቸው። የእግዚአብሄር ቃል በአጠቃላይ የሚፈጥር በመሆኑ በእውነተኛ እምነት ከሰማነው በህይወታችን ላይ ይሰራል። የእግዚአብሄር ቃል ከሚያደርጋቸው ነገሮች በጥቂቱ ፦ 1,በሰው ልብ ውስጥ #እምነትን_ይፈጥራል ሮሜ 10 17፤ እንግዲያስ #እምነት ከመስማት ነው መስማትም #በእግዚአብሔር_ቃል ነው። 2,ሰዎች #ዳግም_እንዲወለዱ_ያደርጋል (ሰዎች ከህያው ዘር ዳግመኛ የሚወለዱት በእግዚአብሄር ቃል ነው ።) 1 ጴጥሮስ 1 23፤ #ዳግመኛ_የተወለዳችሁት ከሚጠፋ ዘር አይደለም፥ በሕያውና ለዘላለም በሚኖር #በእግዚአብሔር_ቃል_ከማይጠፋ_ዘር_ነው_እንጂ። 3, #የሚያሳድገን_መንፈሳዊ_ወተት ነው። 1 ጴጥሮስ 2 2-3፤ ጌታ ቸር መሆኑን ቀምሳችሁ እንደ ሆነ፥ ለመዳን #በእርሱ_እንድታድጉ አሁን እንደ ተወለዱ ሕፃናት ተንኰል የሌለበትን #የቃልን_ወተት_ተመኙ። 4, #በአዕምሮ_የምንታደስበት ከውስጥ ወደ ውጪ የእግዚአብሄርን ህይወት የምንገልጥበት መርህ ነው። ሮሜ 12 2፤ የእግዚአብሔር ፈቃድ እርሱም በጎና ደስ የሚያሰኝ ፍጹምም የሆነው ነገር ምን እንደ ሆነ ፈትናችሁ ታውቁ ዘንድ #በልባችሁ_መታደስ_ተለወጡ እንጂ ይህን ዓለም አትምሰሉ። 2 ጢሞቴዎስ 3 16-17፤ የእግዚአብሔር ሰው ፍጹምና ለበጎ ሥራ ሁሉ የተዘጋጀ ይሆን ዘንድ፥ #የእግዚአብሔር_መንፈስ_ያለበት_መጽሐፍ_ሁሉ_ለትምህርትና_ለተግሣጽ_ልብንም _ለማቅናት_በጽድቅም_ላለው_ምክር_ደግሞ_ይጠቅማል። ይቀጥላል ክፍል አስርን ለማግኘት ይሄን ይጫኑ 👇👇👇👇 https://t.me/shalomgracegospel
Show all...
Grace Gospel

የእግዚአብሄር ቃል ክፍል አስር ዛሬም ሁኔታ፣ሰዎች፣ሰይጣው፣አለም የራሳችን ህሊና ስለ እኛ ብዙ እውቀት(መረጃ) ሊሰጡን ይችላሉ። እነዚህ ሁሉ ግን ከእግዚአብሄር ቃል ውጪ ከሆኑ ልንቀበላቸው አይገባም። ስለእኛ የእውቀት ምንጭ ልናደርጋቸው ፈጽሞ አይገባም። ስለዚህ የእግዚአብሄር ቃል ስለእኛ የሚናገረውን ልንሰማ ልንቀበል ልናምንና በድፍረት ልንናገር ያስፈልጋል። ዮሐንስ 1 19፤ አይሁድም፡— አንተ ማን ነህ? ብለው ይጠይቁት ዘንድ ከኢየሩሳሌም ካህናትንና ሌዋውያንን በላኩበት ጊዜ፥ የዮሐንስ ምስክርነት ይህ ነው። 23፤ እርሱም፡— #ነቢዩ_ኢሳይያስ_እንዳለ፡— የጌታን መንገድ አቅኑ ብሎ #በምድረ_በዳ_የሚጮኽ_ሰው_ድምፅ_እኔ_ነኝ፡ አለ። ተጨማሪ ጥቅሶች:- ኢሳ 40:3-5 ማር 1:2-3 ሉቃ3:3-6  ማቴ3:3 መጽሃፍ ቅዱስ ስለእኛ የሚናገረው በእርግጥ ለአእምሮ አይመችም ፤ እስቲ ለመጥምቁ ዮሐንስ የተባለውን አስብ:- ድምፅ ነህ ማለት አሁን እንዴት ይሆናል?? ለአእምሮ ምን ትርጉም ይሰጣል?? እኛም ራሳችንን ስናውቅ መጽሃፍት ሁሉ በሚያወሩለት በክርስቶስ በኩል ፤የመጽሃፍ ትምህርት በሆነው የመዳን እውቀት በሆነው የፅድቅ መረዳት ሊሆን ያስፈልጋል። 2 ቆሮንቶስ 5 16፤ #ስለዚህ_እኛ_ከአሁን_ጀምሮ_ማንንም_በሥጋ_እንደሚሆን_አናውቅም፤ ክርስቶስንም በሥጋ እንደ ሆነ ያወቅነው ብንሆን እንኳ፥ አሁን ግን ከእንግዲህ ወዲህ እንደዚህ አናውቀውም። ኦ ስለዚህ እንዴት እንወቅ? 1ኛ ቆሮንቶስ 1 (አዲሱ መ.ት) ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ³⁰ #በክርስቶስ_ኢየሱስ ለመሆን የበቃችሁት ከእርሱ የተነሣ ነው፤ #እርሱ #ከእግዚአብሔር_ዘንድ_ጥበባችን፣ #ጽድቃችንና_ቅድስናችን፣ #ቤዛችንም_ሆኖአል። ተጨማሪ ጥቅሶች ሮሜ 6:11 2ቆሮ 5:17 1ቆሮ1:2 2ቆሮ 2:14 ሮሜ6:23,8:1 ማቴ 5:13-14 ሮሜ 8 16፤ #የእግዚአብሔ…

Photo unavailableShow in Telegram
Show all...
የእግዚአብሄር ቃል ክፍል አስር ዛሬም ሁኔታ፣ሰዎች፣ሰይጣው፣አለም የራሳችን ህሊና ስለ እኛ ብዙ እውቀት(መረጃ) ሊሰጡን ይችላሉ። እነዚህ ሁሉ ግን ከእግዚአብሄር ቃል ውጪ ከሆኑ ልንቀበላቸው አይገባም። ስለእኛ የእውቀት ምንጭ ልናደርጋቸው ፈጽሞ አይገባም። ስለዚህ የእግዚአብሄር ቃል ስለእኛ የሚናገረውን ልንሰማ ልንቀበል ልናምንና በድፍረት ልንናገር ያስፈልጋል። ዮሐንስ 1 19፤ አይሁድም፡— አንተ ማን ነህ? ብለው ይጠይቁት ዘንድ ከኢየሩሳሌም ካህናትንና ሌዋውያንን በላኩበት ጊዜ፥ የዮሐንስ ምስክርነት ይህ ነው። 23፤ እርሱም፡— #ነቢዩ_ኢሳይያስ_እንዳለ፡— የጌታን መንገድ አቅኑ ብሎ #በምድረ_በዳ_የሚጮኽ_ሰው_ድምፅ_እኔ_ነኝ፡ አለ። ተጨማሪ ጥቅሶች:- ኢሳ 40:3-5 ማር 1:2-3 ሉቃ3:3-6  ማቴ3:3 መጽሃፍ ቅዱስ ስለእኛ የሚናገረው በእርግጥ ለአእምሮ አይመችም ፤ እስቲ ለመጥምቁ ዮሐንስ የተባለውን አስብ:- ድምፅ ነህ ማለት አሁን እንዴት ይሆናል?? ለአእምሮ ምን ትርጉም ይሰጣል?? እኛም ራሳችንን ስናውቅ መጽሃፍት ሁሉ በሚያወሩለት በክርስቶስ በኩል ፤የመጽሃፍ ትምህርት በሆነው የመዳን እውቀት በሆነው የፅድቅ መረዳት ሊሆን ያስፈልጋል። 2 ቆሮንቶስ 5 16፤ #ስለዚህ_እኛ_ከአሁን_ጀምሮ_ማንንም_በሥጋ_እንደሚሆን_አናውቅም፤ ክርስቶስንም በሥጋ እንደ ሆነ ያወቅነው ብንሆን እንኳ፥ አሁን ግን ከእንግዲህ ወዲህ እንደዚህ አናውቀውም። ኦ ስለዚህ እንዴት እንወቅ? 1ኛ ቆሮንቶስ 1 (አዲሱ መ.ት) ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ³⁰ #በክርስቶስ_ኢየሱስ ለመሆን የበቃችሁት ከእርሱ የተነሣ ነው፤ #እርሱ #ከእግዚአብሔር_ዘንድ_ጥበባችን፣ #ጽድቃችንና_ቅድስናችን፣ #ቤዛችንም_ሆኖአል። ተጨማሪ ጥቅሶች ሮሜ 6:11 2ቆሮ 5:17 1ቆሮ1:2 2ቆሮ 2:14 ሮሜ6:23,8:1 ማቴ 5:13-14 ሮሜ 8 16፤ #የእግዚአብሔር_ልጆች_መሆናችንን_ያ_መንፈስ_ራሱ_ከመንፈሳችን_ጋር_ይመሰክራል። -መንፈስ ቅዱስ የሚመሰክረው ቃሉ የሚናገረውን እውነት ነው፤ይህ ስለእኛ ትክክለኛ እውቀት ነው። መጽሃፍ ቅዱስ ስለእኛ የሚናገረው ሁሉ እውነት ስለሆነ የመንፈስ ቅዱስ ምስክርነት አለን ። ስለዚህ መጽሃፍ ቅዱስ በዋናነት ስለማህበራዊ ህይወት ፣ ስለመላዕክት ፣ስለተፈጥሮ ወዘተ ለማስተማር አልተሰጠም። ይቀጥላል ክፍል ዘጠኝን ለማግኘት ይህን ይጫኑ https://t.me/shalomgracegospel
Show all...
Grace Gospel

የእግዚአብሄር ቃል ክፍል ዘጠኝ ስለዚህ እለት እለት ወደ ቃሉ  ስንቀብ ከቃሉ ለመማር፣ለመታረም፣ለመመከር ለመገሰፅ የለመድነው የኖርንበትም እንኳን ቢሆን ለመጣል ተዘጋጅተን ፈጽሞ በተከፈተ ልብ ሊሆን ይገባል። 3. ስለእኛ በትክክል ይናገራል መጽሃፍ ቅዱስ ትክክለኛ የእግዚአብሄር ሃሳብ በመሆኑ የእውቀታችንን ምንጭ ሊሆን የሚገባው እርሱ ብቻ ነው። እናም ስለእኛ ከራሳችን በላይ በትክክል የሚያውቀውና የሚናገረው እርሱ በመሆኑ ቃሉን ስናጠና ራሳችንን በትክክል በቃሉ መስተዋት ከቃሉ ላይ ማየት አለብን። ያዕ 1:23 ልክ መስተዋት የእኛን ትክክለኛ መልክ እንደሚያሳየው ሁሉ ቃሉ የመንፈሳዊ ማንነታችን ፣አቋማችን እንዲሁም መልካችን ትክክለኛ ማሳያ ነው ። ሰው የእግዚአብሄር አምሳል በመሆኑ የሳይንስ ግኝት ሳይሆን የእግዚአብሄር ቃል ነው ስለማንነቱ ትክክለኛው ትምህት፤ልክ እንደዚሁ በክርስቶስ አምነን ስለዳንን ሰዎች ደግሞ በይበልጥ ይናገራል። መጥምቁ ዮሐንስ ስለራሱ አይሁድ በጠየቁት ጊዜ ብዙ መናገር ይችል ነበር፦  የካህናት ዘር ፣ የካህኑ ዘካርያስ ልጅ ፣ የአገልግሎቱን አይነትና ቆይታ ወዘተ ... ነገር ግን እግዚአብሄር እርሱን በሚያይበት ቃሉ ስለእርሱ በተናገረው በዚያ እውቀት ራሱን አወቀ። ይቀጥላል ክፍል ስንምትን ለማግኘት ይህን ይጫኑ

https://t.me/shalomgracegospel

የእግዚአብሄር ቃል ክፍል ዘጠኝ ስለዚህ እለት እለት ወደ ቃሉ  ስንቀብ ከቃሉ ለመማር፣ለመታረም፣ለመመከር ለመገሰፅ የለመድነው የኖርንበትም እንኳን ቢሆን ለመጣል ተዘጋጅተን ፈጽሞ በተከፈተ ልብ ሊሆን ይገባል። 3. ስለእኛ በትክክል ይናገራል መጽሃፍ ቅዱስ ትክክለኛ የእግዚአብሄር ሃሳብ በመሆኑ የእውቀታችንን ምንጭ ሊሆን የሚገባው እርሱ ብቻ ነው። እናም ስለእኛ ከራሳችን በላይ በትክክል የሚያውቀውና የሚናገረው እርሱ በመሆኑ ቃሉን ስናጠና ራሳችንን በትክክል በቃሉ መስተዋት ከቃሉ ላይ ማየት አለብን። ያዕ 1:23 ልክ መስተዋት የእኛን ትክክለኛ መልክ እንደሚያሳየው ሁሉ ቃሉ የመንፈሳዊ ማንነታችን ፣አቋማችን እንዲሁም መልካችን ትክክለኛ ማሳያ ነው ። ሰው የእግዚአብሄር አምሳል በመሆኑ የሳይንስ ግኝት ሳይሆን የእግዚአብሄር ቃል ነው ስለማንነቱ ትክክለኛው ትምህት፤ልክ እንደዚሁ በክርስቶስ አምነን ስለዳንን ሰዎች ደግሞ በይበልጥ ይናገራል። መጥምቁ ዮሐንስ ስለራሱ አይሁድ በጠየቁት ጊዜ ብዙ መናገር ይችል ነበር፦  የካህናት ዘር ፣ የካህኑ ዘካርያስ ልጅ ፣ የአገልግሎቱን አይነትና ቆይታ ወዘተ ... ነገር ግን እግዚአብሄር እርሱን በሚያይበት ቃሉ ስለእርሱ በተናገረው በዚያ እውቀት ራሱን አወቀ። ይቀጥላል ክፍል ስንምትን ለማግኘት ይህን ይጫኑ https://t.me/shalomgracegospel
Show all...

Choose a Different Plan

Your current plan allows analytics for only 5 channels. To get more, please choose a different plan.