cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

በክርስቶስ ( in christ)

Who is ownership of kingdom በዚህ ቻናል መንፈሳዊ አገልግሎት እና ጉዳዬች ላይ ይተኮራል @ownkin

Show more
Advertising posts
684Subscribers
+124 hours
+57 days
+2430 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

(አኗሪ ) ክርስቶስ በልባችን ማኖር የእኛ ስራ አይደለም በልባችን የሚያኖር አካል አለ እርሱ መንፈስ ቅዱስ ይባላል ። መንፈስ ቅዱስ ክርስቶስን በልባችን ላይ ለማኖር ብዙ ኢንቨስትመንቶችን ያረጋል ። እኛን በህልውናው ያውደናል ፣ የእግዚአብሔር ፍቅር እንድንለማመድ የቀመስነውን ፍቅር መልሶ መላልሶ ያስታውሰናል ፣ በልባችን ሊኖር የተገባውን ክርስቶስ ማን እንደሆነ ይነግረናል ፣ እኛ የተረጨንበትን ክቡር ደም ያሳስበናል ። ክርስቶስን በልባችን ማኖር የመንፈስ ቅዱስ ድርሻ መሆን ካወቅንበት አንዱ ምክኒያት መካከል ክርስቶስን በልብ ማኖር የሚቻለው በውስጥ ሰውነት በመንፈሱ በኩል በመጠንከር ስለሆነ ነው ።   በውስጥ ሰውነት መጠንከር በውስጠኛው ማንነታችን ከመንፈስ ቅዱስ ጋር በሚኖር ጣፋጭ ህብረት በሀሳብ ፣ በዕውቀት ፣ በስሜት ፣ በፈቃዳችን መንፈስ ቅዱስ ላይ ጥገኛ መሆን ነው ። በመንፈስ ቅዱስ ውስጠኛው ሰውነታችን ሲበረታ ልባችን ክርስቶስ ለማኖር ዝግጁ ይሆናል ። ሀሳባችን ፣ ስሜታችን ፣ ፈቃዳችን ክርስቶስ ለማኖር ይጓጓሉ ።በመንፈሱ በውስጥ ሰውነት መጠንከር ክርስቶስ በልባችን እንዲኖር ልባችንን ብቁ ያደርገዋል ። @cgfsd @ownkin
Show all...
14👍 3
(ቤተኝነት ለቤተኛው ) ክርስቶስ በልባችሁ እንዲኖር ብሎ ሲፀልይ ሐዋሪያው ጳውሎስ በመንፈስ ቅዱስ አማካኝነት ወደ እናንተ ማንነት የገባው ክርስቶስ እናንተ ለቤትነት ይፈልጋችኋል እያለ ነው ። የክርስቶስ ቤተመቅደስ ናችሁ ማለት የክርስቶስ መኖሪያ ቤት ናችሁ ማለት ሲሆን ክርስቶስ በልባችሁ ይኑር ማለት ግን እናንተ ቤት ያደረጋችሁ ክርስቶስ ቤተኝነት ይሰማው ፣ በራሱ ቤት ነፃነት ያግኝ፣ የደም ዋጋ ያወጣበት የቤቱን ባለቤትነት ማንም አይጋራው። ክርስቶስን በልባችን ማኖር በነፍሳን ላይ ቤተኛ እና ባለቤት ማድረግ ነው ። @cgfsd @ownkin
Show all...
14👍 1
(እየኖረ የሚኖር) ክርስቶስ በመስቀል ላይ በከፈለው ድንቅ መስዋትነት የተነሳ እኛን ቤተ መቅደስ አድርጎ በእኛ ውስጥ ይኖራል ። ክርስቶስ ኗሪ ነው ። በደሙ በሰራው ፣ በደሙ ባጠበው በመስቀል ላይ ሙቶ ባቆመው መቅደስ ሊኖር አለ ፤ በመንፈሳችን ውስጥ ይኖራል ። ነገር ግን በመንፈሳችን ውስጥ እየኖረ እንዳለ ሁሉ በዕለት ተዕለት ኑሮ በልባችን ሊኖር ይፈልጋል ። ልብ ማለት ሀሳብ፣ እውቀት ፣ ፈቃድ ፣ስሜት ሁሉ ጠቅልሎ የያዘ ነው ። ክርስቶስ በልብ ይኑር ሲባል በዕውቀታችንም፣ በሀሳባችን፣ በፈቃዳችንም ፣ በስሜታችን ውስጥ በሙሉ እሱ እየኖረ በስሜታችን እሱ ሊሰማው ፣ በፈቃዳችን ላይ እሱ ሊፈቅድ፣ በዕውቀታችን ውስጥ እሱ ሊያውቅ፣ በአስተሳሰባችን ውስጥ እሱ ሊያስብ ክርስቶስ በልባችን ሊኖር በእኛ ውስጥ አለ ። ክርስቶስ እየኖር የሚኖር ነው ። @cgfsd @ownkin
Show all...
14🥰 7
ኢየሱስ የራሱን መንግስት ያስተዋወቀው  እሱ ራሱ በመንግስቱ ውስጥ ንጉስም ወታደርም በመሆን ነው ። @cgfsd @ownkin
Show all...
16👍 2
(67ተኛ መፀሀፍ)   በመልካም ምግባሩ ፣በሰባአዊነቱ ተጠቃሽ ከሆኑት ሰዎች መካከል አንዱ ማህተመ ጋንዲ አንዱ ነው ። ጋንዲ በኖረበት ዘመን ዝናው በአለም ላይ ናኝቶ ነበር ።  ለተወሰኑ አመታት  በተሰማራበት የህግ ሙያው ተቀጥሮ ወደ ደቡብ አፍሪካ እንዲመጣ ሆነ ። በደቡብ አፍሪካ ቆይታው በዘሩ ምክኒያት ነጮች ያሰቃዩት ፣ያገሉት ሲያሻቸው ያወግዙት እንደነበር እራሱ ይናገራል ። እዛው ደቡብ አፍሪካ በነበረበት አመታት ከክርስቲያኖች ጋር ይገናኝ ፣ ይነጋገር አልፎ አልፎ በመፀሀፍ ቅዱስ ጥናታቸው ይሳተፋል ። በተለይ ከእሱ ጋር ቅርብ የነበረው ሰው በተደጋጋሚ የመዳን ብቸኛ መንገድ ክርስቶስ በማመን እንደሆነ ያበስረዋል ። ጋንዲም በግሉ መፀሀፍ ቅዱስ ሲያነብ፣ ሲሰበክም ከሚሰማው በጠቅላላ የክርስቶስ ህይወት እንደሚማርከው ይናገራል ። ጌታን እንደግል አዳኙ አርጎ ግን  አልተቀበለም!!!!! ጋንዲ እንዲህ  አለ " ክርስቶስን እወደዋለሁ ክርስቲያኖች ግን እንደእሱ አይደሉም "።     ለጋንዲ ካነበበው መፀሀፍ ቅዱስ እና ከሰበኩለት ክርስቶስ የክርስቲያኖች ህይወት ርቆበታል ።       መፀሀፍ ቅዱስ 66 መፀሀፍት ጠቅልሎ ይዟል  እነርሱም ፤ የብሉይ 39፣  አዲስ ኪዳን 27 ናቸው።  አንበብን ይሆናል ወይም ደግሞ ከጥግ እሰከ ጥግ ሸምደደውም ሊሆን ይችላል  ነገር ግን መፀሀፍ ቅዱሳችን 67 እንደሆነ እናውቃለን ወይ ??? ወይስ አናውቅም ??? እውነት ነው ግራ ሊገባን ይችላል በመፀሀፍ ቅዱሳችን ያሉት መፀሀፍት 66 ነው ነገር ግን አንድ ክፍት አለ 67ተኛው መፀሀፍ እርሱም የክርስቲያን ህይወት ነው ። ጋንዲ ምናልባት ስልሳ ስድስቱን አንብቦ 67ተኛውን ከአማኞች አቶት ይሆን ??? ወንጌል የምንሰራ በአለማዊያን ፊት ለምንመላለስ 67ተኛው ሁኖ ሊናገር ክርስቶስ ሊያሳይ የሚችለው ህይወታችን ነው ። 67ተኛው መፀሀፍ የክርስቲያን ህይወት ነው !!     መፀሀፍ ቅዱሳችን  መነበብ እንደሚገባን መክሮናል ። ልንነበብ ይገባል !!!" 67ተኛው መፀሀፍ ያልተፃፈ ግን የሚታይ የዕለት ተዕለት ኑሮአችን ነው ። ✍  ፊሊሞን ነጋ @ownkin @cgfsd
Show all...
16👍 1
ዓለምን ያነጋገረው የይቅርታ ልብ! ሰሞኑን መነጋገሪያ የሆኑት በምስሉ ላይ የምትመለከቷቸው በአሦርያውያን ቤተ ክርስቲያን የአውስትራሊያ ጳጳስ የሆኑትና በተለያዩ የማኅበራዊ ትስስር ገጾች በሚዘዋወሩ ክርስቶስ ተኮር ስብከታቸው የሚታወቁት አቡነ ማር ማርያም ኢማኑኤል በአገልግሎት ላይ ሳሉ የተፈፀመባቸውን ጥ*ቃት ብዙዎቻችሁ እንደሰማችሁት ጥርጥር የለኝም፤ እጅግ በጣም የገረመኝ ነገር ግን አክራሪ ሙ'ስሊም የሆነው ወጣት በቪዲዮ ላይ ሲዘወወር እንዳያችሁት ደጋግሞ ጥ*ቃት ቢያደርስባቸው የመጀመሪያ ያደረጉት ነገር እንደምንም አቁሙኝ ብለው በአጥቂው ራስ ላይ እጃቸውን አድርገው መጸለይ መጀመራቸው ነው። እንዴት ያለ አስደናቂ የይቅርታ ልብ ነው ወዳጆቼ? እንደ እርሳቸው እየ*ወጉት የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅር በላቸው ያለውን የክርስቶስን ፈለግ በሕይወት መከተል የምንችልበት፤ በመወጋታችንም ቢሆን ለሚሊዮኖች ክርስቶስ እንዲሰበክ ምክንያት የምንሆንበት ፀጋ ይብዛልን። ✍️አክሊሉ ተስፋዬ @cgfsd
Show all...
🥰 7👍 3🔥 1
በልባችን ውስጥ ሊኖር እኛን ቤተ መቅደስ አደርጎ ይሔው አዲስ መኖሪያ ብሎ በደሙ መረቀ ። ወደ አባቱ እንድንገባ ወደ ዙፋኑ የሚንገባበትን መንገድ ይሔው ብሎ በደሙ መርቆ መንገዱን ከፈተው ።   ኢየሱስ ስጋው እየቆረሰ ደሙን እያፈሰሰ ይሔው አዲሱ መኖሪያ ይሔው አዲሱ መንገድ በማለት መርቆታል ። @cgfsd @ownkin
Show all...
19🔥 3👍 1
ክርስቶስ በየትኛው ልብ ውስጥ ይኖራል ? #በክርስቶስ ደም በተረጨ ልብ ውስጥ #በመንፈስ ቅዱስ በኩል የእግዚአብሔር ፍቅር በፈሰሰበት ልብ ውስጥ #የእግዚአብሔር ታላቅ ምህረት ያረፈበት ልብ ውስጥ #ክርስቶስ ኢየሱስ ይመጣል በሚል ግሩም ተስፋ በተሞላ ልብ ውስጥ #በእግዚአብሔር የህልውና መአዛ በታወደ ፤ በታጠነ ልብ ውስጥ #ኢየሱስ የሚለውን ስም ሁልጊዜ እንዲጠራ ፈቃድ በሰጠው ልብ ውስጥ #ክርስቶስ ኢየሱስ  በራሱ ለራሱ በዋጀው ልብ ውስጥ         ክርስቶስ ኢየሱስ የሚኖርበት ልብ ራሱ ክርስቶስ ባፈሰሰው ደም የደመቀ፣ በቅዱስ መንፈሱ የተዋበ፣ በጥልቅ ፍቅሩ ያሸበረቀ ፣ በድንቅ ስሙ ያበራ፣ በአስደናቂው ፀጋ የተጥለቀለቀ፣ በተባረከው ተስፋ ኢየሱስ በኩል የታወደ፣ በውድ ምህረት የሚያብረቀርቅ ልብ ውስጥ ክርስቶስ ይኖረናል ።      " ኢየሱስ ሌላ ምንም አላለንም በደም ባፈሰስኩበት ልብ ውስጥ ልኑር " @cgfsd @ownkin
Show all...
16👍 1😢 1
ክርስቶስ በየትኛው ልብ ውስጥ ይኖራል ? #በክርስቶስ ደም በተረጨ ልብ ውስጥ #በመንፈስ ቅዱስ በኩል የእግዚአብሔር ፍቅር በፈሰሰበት ልብ ውስጥ #የእግዚአብሔር ታላቅ ምህረት ያረፈበት ልብ ውስጥ #ክርስቶስ ኢየሱስ ይመጣል በሚል ግሩም ተስፋ በተሞላ ልብ ውስጥ #በእግዚአብሔር የህልውና መአዛ በታወደ ፤ በታጠነ ልብ ውስጥ #ኢየሱስ የሚለውን ስም ሁልጊዜ እንዲጠራ ፈቃድ በሰጠው ልብ ውስጥ #ክርስቶስ ኢየሱስ  በራሱ ለራሱ በዋጀው ልብ ውስጥ         ክርስቶስ ኢየሱስ የሚኖርበት ልብ ራሱ ክርስቶስ ባፈሰሰው ደም የደመቀ፣ በቅዱስ መንፈሱ የተዋበ፣ በጥልቅ ፍቅሩ ያሸበረቀ ፣ በድንቅ ስሙ ያበራ፣ በአስደናቂው ፀጋ የተጥለቀለቀ፣ በተባረከው ተስፋ ኢየሱስ በኩል የታወደ፣ በውድ ምህረት የሚያብረቀርቅ ልብ ውስጥ ክርስቶስ ይኖረናል ።      " ኢየሱስ ሌላ ምንም አላለንም በደም ባፈሰስኩበት ልብ ውስጥ ልኑር " @cgfsd @ownkin
Show all...