cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

የግጥም ደብተሬ( ye getm debterae)

ለግጥም አፍቃሪዎችና ወዳጆች የግጥም ጥማቹን ለማርካት እንሆ ጀባ ብለናችሁል

Show more
The country is not specifiedThe language is not specifiedThe category is not specified
Advertising posts
423
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

​​#የአምላክ_እንባ (በላይ በቀለ ወያ) @Mgetem . . ከላይ ከሰማያት... በሰው ተበድሎ ፤ ፈጣሪ ያለቅሳል ከታች ያለ ፍጥረት... "ዝናብ ጣለ" ብሎ ፤ ምድሪቱን ያርሳል። ወራትን ጠብቆ፤ ርሀቡን አስታግሶ የሀገሬ ገበሬ... በፈጣሪ እንባ ነው ፤ የሚበላው አርሶ። እንዲያው በተለምዶ፤ ዝናብ የምንለው ትእግስት አጠራቅሞት... ለወራት የቆየ ፤ የአምላክ እንባ ነው። ።።። ከማንባቱ በፊት... ማዘኑን ሊያረዳ፤ ሰማይ ጠቁሮ ሳለ፤ ፈጣሪ ሲቆጣ... ትውልድ ያማትባል፤ "መብረቅ" ነው እያለ። የሀገሬ ገበሬ..... ሰማዩን እያየ፤ ምድሪቱን ያርሳል የገበሬው በሬ... ሳር ሳሩን እያየ፤ ከገደል ይደርሳል በፈጣሪ እንባ በሰው ልጆች ደባ የታረሰ መሬት... ስንዴና እንክርዳዱን፤ባንድ ላይ ያበቅላል ከላይ ከሰማያት... ስንዴን ከእንክርዳዱ ፤ሊለይ ይታገላል ከታች ያለ ፍጥረት ርሀቡን ሊያስታግስ ስንዴና እንክርዳድን፤ ደባልቆ ይበላል። ።።። ለእንደገና ክረምት ለእንደገና በደል ፣ ለእንደገና ለቅሶ የሀገሬ ገበሬ…… ሰማይ ሰማይ ያያል፤ ደረቅ መሬት አርሶ። ።፣ ከላይ ከሰማያት. የፈጣሪ እናት ልጇን ለማባበል ፤ ፈገግ ትላለች ከታች ያለች እናት... "ፀሐይ ወጣ"ብላ ፤ ብቅል ታሰጣለች። እንዲያው በተለምዶ፤ ፀሀይ የምንላት ልጇን ለማባበል…. ብርሀን የሰጠች፤ የአምላክ እናት ናት። @Mgetem @Mgetem @Mgetem_Bot
Show all...
2.51 KB
Some say this covid-19 is the 13th Apostle sent to Earth to bring us and our consciousness Back to GOD. are they right?
Show all...
Water can boil and freeze at the same time Seriously, it's called the 'triple point, and it occurs when the temperature and pressure is just right for the three phases (gas, liquid, and solid) of a substance to coexist in thermodynamic equilibrium. @Minutephysics
Show all...
እሱ :የህይወቴን ተስፋ ፍቅሬ አታዋት ብዙ ጊዜ አለፈኝ አይኑአን ... እሷ፦እንዴ አሁን አይድል እንዴ ከonline የወታሁት እሱ፦ዝም በይ ባክሽ አንቺን አይድለም 😜😜😜😜😁😁😂😝😋😀😱
Show all...
አችሬ ግጥም ቁመተ ዶሮ ምትንተራራ ወደ ሰው ጆሮ short man😳😍
Show all...
#ስንቴ_ገረዝኩት ✂️ : #ክፍል_አራት (የመጨረሻ ክፍል) : : ✍ደረሲ:-ሜሪ ፈለቀ : : ....“ባለቤትሽ? ኢሳያስ?…………” “ቢሮዬ ድረስ እየመጣህ ለምን ትረብሸኛለህ ኢሳ?” “ናፈቅሽኝ!! ከዚህ በላይ ሳላይሽ መቆየት አልችልም።” ከዩንቨርስቲ ጀምሮ የማውቀው ሰው ነው ኢሳያስ ። ለ6 ዓመት አብሮኝ የቆየ የትዳር አጋሬም ነው። አብረን በኖርንባቸው ጊዜያት መጀመሪያዎቹ አመታት በፍቅር ያጌጡ ነበሩ። እየሰነባበተ ግን ሳንጨቃጨቅ ያለፉ ቀናት ውስን ሆኑ። የሁለት ዓመት ልጃችን በሞት ስትለየን ሰላማችን ይብስ ደፈረሰ። ልጃችን የሞተችው በምግብ መመረዝ ነው። ታማ ስትሰቃይ ሁለታችንም ልንደርስላት አልቻልንም ነበር። ሰራተኛዋ ስትደውልልኝ ስራ ላይ ነበርኩ። ስልኬን እየሰማሁት ቆይቼ ለመደወል አስቤ ተውኩት። ግን ቆይቼም አልደወልኩም። ሌላ ስራ ያዝኩ። እናም ልጄን ሳልደርስላት ሞተች። እሱም በተመሳሳይ ምክንያት ስልክ ሳይመልስ ቀረ። ቆይቼ ስደርስ ዘግይቼ ነበር። ለዚህ በደሌ አንድ ሚሊየን ጊዜ ራሴን ብቀጣውም በቂ አይሆንም። ከኢሳያስ ጋር መወቃቀሱ አቁሳይ ስለነበር በሆነው ባልሆነው ሰበብ እየፈለጉ መነታረክ ሆነ ምሽታችን። ቤቱን ለቆ ከወጣ ሶስት ወር አለፈው። “ቁጭ ብለን እንድናወራ እፈልጋለሁ።” አለኝ አይን አይኔን በልመና እያየ። ምንድነው ልለው የነበረው? ‘ውጣልኝ‘ ነበር ሌላ ጊዜ ቢሆን የምለው። አሁን የምትሸሸዋን ሴት አይደለሁም። ምንም ቢሆን የምትጋፈጠዋን ማህደር እየተለማመድኳት ነው። “እደውልልሃለሁ።” ያልኩትን ያመነኝ አይመስልም። ተገርሞ እያየኝ ተሰናብቶኝ ወጣ። የገባኝ አንድ ነገር ሲሳይ በብዙ ፍጥነት ማንነቴን እያሾረው መሆኑ ነው። ወደ ቤቴ ገብቼ ሲሳይ ያለኝን አደረግኩ። «በህይወትሽ የምትሸሺው ነገር ምንድነው? መስታወት ፊት ቁሚና ለራስሽ ንገሪው። እመኚው!! መቀየር የማትችዪውን ነገር መቀበል ነው የሚፈውሰው።» ነበር ያለኝ የልጄን ፎቶዎች ከደበቅኩበት አወጣኋቸው። በመጀመሪያው ቀን ቀላል አይሆንም ነበር ያለኝ። ቀላል አልነበረም። ሁሉንም ፎቶዎች በፊት የተሰቀሉበት መለስኳቸው። መሸሽም መደበቅም መድሃኒት አይሆንም። ስሸሽ የተጠራቀመው እንባዬ ገደቡን ጥሶ አይኔን አደፈራረሰው። ስልኬ መጥራቱን እንኳን የሰማሁት ብዙ ከጠራ በኋላ ነበር። «ምን ሆነሻል? አልቅሰሽ አይደለምኣ?» ሲሳይ ነው። «ነው! አልቅሼ ነው።» እያልኩት ጭራሽ መንፈቅፈቅ ጀመርኩ። «እህህህ ምን ተፈጠረ ቆይ?» እቤቴ ደጅ ድረስ አድርሶኝ ነበር የተመለሰው። መልስ መመለስ እስኪያቅተኝ ሲቃዬ አነቀኝ። « በቃ በቃ እሺ መጣሁ። ስልኩን አትዝጊው እያወራሁሽ እደርስልሻለሁ። እኔ አጠገብሽ ሆኜ እንደፈለግሽ እንድታለቅሺ ፈቅድልሻለሁ። እስከዛ ግን ስወድሽ አታልቅሺ?» ብሎኝ ሊያስቀኝ እየሞከረ ከቤቱ ሲወጣ፤ «ብርድ እንዳይመታህ በደንብ ልበስ» ስለው «አትስጊ ካልሲ አጥልቄለታለሁ» ሲለኝ ታክሲ ሲያናግር «የኔ እመቤት ደሞ ስስ ፒጃማ ፍለጋ ቁምሳጥኑን ዘረጋግፊው አሉሽ!» ሲለኝ ሲከፍል «ስንቴ መስታወት አየሽ?» ሲለኝ ሲደርስ እውነትም ማልቀሴን ትቼ ልቤ ተሰቅሎ እየጠበቅኩት ነበር። በሩን ከፍቼ ተጠመጠምኩበት። ሙሽራውን በሰርጓ እለት ወደ መኝታ ቤታቸው እንደሚያስገባ ሙሽራ አቅፎኝ ወደሳሎኑ ገባ! ማልቀሴን እረሳሁት። ሳሎኑ ውስጥ የተሰቀለውን የእኔንና የኢሳያስን የሰርግ ፎቶ አይቶታል። ግን አልጠየቀኝም። ሌላ ነገር እያወራ ሲያስቀኝ ቆየ። «ሲስ?» «ወዬ እመቤቴ?» «ስለእኔ ማወቅ ያለብህ ነገር አለ።» «ምኑን ትነግሪኝ? በፎቶ አሳየሽኝኮ አስጎበኘሽኝ።» አለ ወደፎቶው እየጠቆመኝ። «እየቀለድኩ አይደለም ሲስ! ከምሬ ነው።» « እሺ እመቤቴ ንገሪኝ! ይኸው! Am all yours!» ስለኢሳያስ እና ስለልጄ ነገርኩት ብቻዬን ስለፈልፍ ሲያባብለኝ እና ሲደባብሰኝ ብቻ ቆየ። ብዙ ደቂቃ እቅፉ ውስጥ ካቆየኝ በኋላ « ባንቺ ደረጃ ካሉ ሴቶች ይልቅ አንዲት ምንም የማታውቅ የቤት እመቤት የሰመረ ትዳር ለምን የሚኖራት ይመስልሻል?» አለኝ « ጭራሽ እንደዛ ስለመሆኑም እንጃልህ! ምን ለማለት ፈልገህ ነው?» «ይሄ ሀቅ ነው ብዙ ጥናቶች እንደሚያመለክቱት በጋራ ስምምነት ባስቀመጥነው ደረጃ ብዙዎቹ ከፍተኛ ደረጃ ላይ ያሉ ሴቶች በትዳራቸው ስኬታማ አይደሉም።» «ምናልባት ከትዳራቸው ሌላ ትኩረታቸውን የሚሻ ሌላ ስራ ስላላቸው?» «እኔ አይመስለኝም። እነዛ በትዳር ውስጥ ለፍቅር ወይ ለልጃቸው አልያም በሌላ ምክንያት ዝቅ ማለትን ያውቁበታል። እስኪ አንድ ጥያቄ ልጠይቅሽ? ክርስቶስ ለባል የሰጠው ትእዛዛ ሚስትህን ክርስቶስ ቤተክርስትያንን በወደደበት ፍቅር ውደድ የሚል ነው። ያ ማለት ነፍሱን እስከመስጠት። ለሚስት ያላት ግን ሚስት ለባሏ ትገዛ ነው። የቱ የሚከብድ ይመስልሻል?» ሳልመልስለት ራሱ ቀጠለ። «ባትወጂም መገዛት ትችያለሽ። ወደሽ አለመገዛት ግን በፍፁም አትችዪም።» ዝም ነበር መልሴ። ከአንዱ ስሜት ወደሌላው መሻገር ምንም አይከብደውም። መከፋቴን አስረስቶኝ አመሸን። «ያው እንደምታውቂው ድንግል ነኝ። በዛ ላይ ቁስሉ ራሱ ሰበብ አይፈልግም።» ብሎኝ እኩለ ለሊት አልፎ ወደ ቤቱ ሄደ። ★ ★ ★ በሚቀጥለው ቀን በስራ የደከመ ሰውነቴን እየጎተትኩ መኪናዬጋ ደረስኩ። መሽቷል። እቤቴ ገብቼ ማረፍ ነው ያማረኝ። ስልኬ ጠራ። ሲሳይ ነው። “እራት በላሽ?” “አልበላሁም። ግን ደክሞኛል በጣም።” “እማ ቆንጆ እራት ነው የሰራችው። እየጠበቀችሽ ነው።” “ትቀልዳለህ እንዴ? ማን ነኝ ብዬ ነው እናትህ ቤት እራት ልበላ የምመጣው?” “ማንም መሆን አይጠበቅብሽም። ሰው መሆን የእማን እራት ለመብላት በቂ ነው።” ★ ★ ★ አመመኝ። የቤተሰቡ ፍቅር አሳመመኝ። “ደህና ነሽ ግን?” “ምነው ደስ አላለሽም?” “ምነው ልጄ ከፋሽሳ?” ይሉኛል እየተቀባበሉ ። አመመኝ። የሚታገለኝን እንባ እየዋጥኩ የደመቀ እራት በላሁ። የቤተሰብ ፍቅር ህመሜ፣ ንጭንጬ ፣ ሽንፈቴ፣ ድክመቴ……… መሆኑ አልገባቸውም። ይሄን ፍቅር በዘመኔ አይቼው አንጊንቼው እንደማላውቅ አያውቁም። የሲሳይ እናት ፊቴን እያገላበጡ፣ ፀጉሬን እየዳበሱ የሆንኩትን ሲጠይቁኝ እናት እንደማላውቅ አያውቁም። አባትየው እየደጋገሙ ‘ልጄ‘ ሲሉኝ። አይኑ ለማያይ ያአረጀ አያቴ እየተላላኩ እና ምርኩዝ ሆኜ እንዳደግኩ አልገባቸውም። እህቶቹ እግሬ ስር በርከክ እያሉ ‘ሲሳይ አስከፍቶሽ ነው? እሱ እኮ ክፍት አፍ ነው።” ሲሉኝ አያቴ ሞቶ የአክስቶቼ ልጆች እንደምናምንቴ እየቆጠሩኝ ተምሬ መጨረሴን አያውቁም። ብዙ አወሩኝ። እቤት ይዟት የመጣ ብቸኛ ሴት መሆኔን ነገሩኝ። ★ ★ ★ እንደምንም ያመቅኩትን እንባዬን መኪናዬ ውስጥ ሲሳይ እቅፍ ውስጥ ዘረገፍኩት። አላባበለኝም። እየደጋገመ እንባዬን እየጠረገ ፣ ፀጉሬን እያሻሸ ጠበቀኝ። “አውሪኝ። የተሰማሽን ሁሉ አውሪኝ።” አለኝ። ሲቃዬ አላስወራ አለኝ። ጣቶቹን ፀጉሬ ውስጥ ሰዶ ወደራሱ አስጠጋኝ። ይበልጥ ሲቀርበኝ ከመቃወም ይልቅ ልስመው ፈለግኩ። በሌላኛው እጁ እንባዬን ከጉንጬ ላይ ጠራረገው። ከንፈሩ ከንፈሬን የሚነካበት ሰዓት ረዘመብኝ። መጠበቅ አቃተኝ። ሳምኩት። ነፍስ በሚያሳርፍ መሳሙ ለደቂቃዎች ሳመኝ። “ምንም ይሁን ንገሪኝ፣ አንድም ሳታስቀሪ የተሰማሽን ንገሪኝ፣ አንቺ ራስሽን ከምትረጂው በላይ እረዳሻለሁ። እንባሽ ከመጣ አልቅሺ ብቻ ልስማሽ!” አለኝ መረጋጋቴን ሲያይ “አሁን እኮ መሽቷል። ሌላ ቀን ላውራህ?” “ማደር ካለብኝ እየሰማሁሽ አድራለሁ።” አውርቼ የማላውቃቸውን ብዙ ነገሮች ነገርኩት። ሳለቅስ አያባብለኝም። እጄን እየደባበሰ ይሰማኛል። ስለቤተሰቦቼ ሁሉንም ነገርኩት። አያቴ ሲሞት ከልጅነቴ ጀም
Show all...
#ስንቴ_ገረዝኩት ✂️ : #ክፍል_ሶስት : : ✍ደረሲ:-ሜሪ ፈለቀ : : ....እግሬና ሀሳቤ ሳይስማሙ እግሬ ቀድሞ ሬስቶራንቱ ውስጥ ተገኘ። ሲሳይ ቀድሞኝ ተገኝቷል። ልጨብጠው የዘረጋሁትን እጄን ሳብ አድርጎ አቀፈኝ። የምቀመጥበትን ወንበር ሳበልኝ። እራትና ወይን አዘዝን። ከእርሱ ጋር መጨቃጨቁ ትርፉ የሌላ ሰው ትኩረት ከመሳብ ያለፈ ስለማይሆን ዝም ብዬ የሚያደርገውን ከማየት ውጪ ተቃውሞም መስማማትም አልተነፈስኩም። አፉ ከማውራት እጁ ከማጉረስ ሳይቦዝን ነበር እራት ተመግበን የጨረስነው። “እኔ ከዚህ በላይ አልጠጣም። ስራ መመለስ አለብኝ።” ያልኩትን የሰማ አይመስልም። ቀዳልኝ። በአትኩሮት ሲመለከተኝ ከቆየ በኋላ “ሴክስ ካደረግሽ ስንት ጊዜሽ ነው? ወራት? አመታት?” አለ ቀለል አድርጎ “አንተ? ያምሃል እንዴ? ” አልኩት ደንግጬ ይሁን አፍሬ ሳይገባኝ “ምነው? አንቺ? ጭራሽ… ……ዜሮ ዞሮ ነሽ እንዴ?” በማብሸቅ ለዛ ነው ያወራው ። ደሞ አብሽቆኛልም። “አንተ እኔን ለማንጓጠጥ የሚያስችለህ ቦታ ላይ እንዳለህ ነው የሚሰማህ?” ሳልጨርስ መንፈቅፈቁን ያዘው ” ማሂ ከእኔ ጋር ስታወሪ ጨዋ ቃል አትፈልጊ…… ሃሃሃሃ ‘ትናንት እጄ ላይ ሸለፈትህን ተገርዘህ፣ ልጅህን በማስገረዣ እድሜህ አንዠርግገኸው…ምናምን ……‘ በይው ” “እንደሱ ለማለት እንኳን አልነበረም።” መለስኩለት “በጨዋኛ ስለብድ ምን ታውቅና? እንደማለት አይደል?” “በየሱስ ስም!» ከመደንገጤ የተነሳ ወንበሬ ላይ ዘልያለሁ። እሱ ምንም እንዳላለ ሁሉ በሁኔታዬ ይንፈቀፈቃል። “ያልተገረዘ ሴክስ አያደርግም ያለሽ ማነው?” አባባሉ ቀዝቃዛ ስሜት ስለነበረው ስሜቱን የጎዳሁት ስለመሰለኝ ወንዶች ስለማይገረዙባቸው ሀገራት፣ ገጥመውኝ ስለሚያውቁ አጋጣሚዎች ነገርኩት። “ኮንዶም የለ፣ ምን የለ… … ጫፉን ሸብ አድርጎ መሰማራት ነው። ተፈጥሯዊ ኮንዶም በይው ሃሃሃ” ብልግና ያወራ፣ በራሱ ያላገጠ አይመስልም። ደንግጬ ፈጥጬ አየዋለሁ። “ኸረ ስቀልድሽ ነው አንቺ!!” አለ መሳቁን ሳያቆም። በህይወቱ ውስጥ የሚያስከፋው፣ የሚያፍርበት፣ ሊያወራው የማይፈልገው ነገሩ ምን ይሆን? ብዬ አሰብኩ። ሲያወራ ፍፁም ጨዋ፣ ደግሞ ፍፁም ባለጌ፣ ደግሞ ፍፁም አዋቂ፣ ደግሞ ፍፁም ህፃን………ሁሉንም ይሆናል። ሲሳይን ማወቅ ከበደኝ። ያልተገረዘው ቤተሰባቸው ወንድ ልጅ እየሞተ ሲያስቸግራቸው የሄዱበት ጠንቋይ እንዳይገረዝ ስለነገራቸው መሆኑን እንደለመደው በራሱና በቤተሰቡ እየቀለደ ነገረኝ። “እያደግኩ ከመጣሁ በኋላ መገረዙ አሳፈረኝ እና አረጀሁ።” “በፍፁም አፍረህበት የምታውቅ ግን አትመስልም ነበር።” “አንቺጋ ስመጣማ ከማፈር አልፎ አስጠልቶኝ ነበር።” ሲያወራ በራስ መተማመኑ ለሰከንድ አይለየውም። ደጋግሞ ከሚያወራቸው ነገሮች በወላጆቹና በ6 እህቶቹ የተለየ ፍቅር ተሰጥቶት እንደኖረ ገባኝ። ከብዙ ሰው ጋር መግባባቱ፣ ብዙ ጓደኞች ማፍራቱ ምናልባትም ከተማረው የሳይኮሎጂ ትምህርቱጋ ግንኙነት ይኖረው ይሆናል ስል አሰብኩ። “ጓደኞች የሉሽም? የሆነ አብረሻቸው አንዳንዴ ዘና የምትዪበት ምናምን?” “የሉኝም!!” “እሺ ሲደብርሽ፣ ሲከፋሽ፣ ደስ ሲልሽ ወይ የተለየ ነገር ሲገጥምሽ ለማን ታወሪያለሽ?” አለኝ አይኖቹ የሚያነቡኝ ስለሚመስሉኝ እሸሻቸዋለሁ “ለራሴ አወራዋለሁ።” አልኩት አይኑን ሳይሰብር አየኝ። “አንተስ?” አልኩት “ያ ስሜት በተሰማኝ ሰዓት አጠገቤ ላገኘሁት ሰው። ለምሳሌ በኋላ ሸኝቼሽ ስመለስ ለሆስፒታላችሁ ዘበኛ ደስ እንዳለኝ ልነግረው እችላለሁ።” ቀለል አድርጎ ነው የሚያወራው “እየቀለድክ ነው?” “የምሬን ነው። ምነው?” “የምልህ ከእኩዮችህ፣ ቢያንስ ከቤተሰብህ……… ባንተ ደረጃ ካሉ ሰዎች ጋር……… ” አላስጨረሰኝም። “ደረጃ ምንድነው? ደረጃ መዳቢውስ ማነው? እኔን ከኒኛ ዘበኛ ወይ ከዚህ አስተናጋጅ በላይ ወይ በታች ደረጃ የሰጠን ማን ነው? የኔ መማር እና ቢሮ መቀመጥ? የሳቸው የእኔን እድል አለማግኘትና ዘበኛ መሆን? ንገሪኝ እስኪ እሳቸው የሚያውቁትን ወይ የሚችሉትን ደረጃ ብለን ባወጣንላቸው ዘበኝነት እንዴት እንመዝነዋለን?” አይቼበት የማላውቅበትን የለበጣ ፈገግታ ፈገግ ብሎ ቀጠለ “አፈር ምን ደረጃ አለው? ነፍስስ ብትሆን ያው ነፍስ አይደለች? በምትሰራው ስራ ካልዳኘናት በቀር? የሰው ደረጃው ‘ሰውነቱ‘ ነው።” አለኝ። ዝም አልኩት። ምንስ ልለው እችል ነበር? “ቤተሰቦችሽ? የት ናቸው?” አለኝ ወዲያው ከዛኛው ስሜት ወጥቶ “ቤተሰቦቼ………?…… ” “ምነው? ሞተዋል? ተጣልታችኋል? ወይስ…… እንደ እህል ዘርተውሽ ነው የበቀቀልሽው?…” ተናድጄ አቋረጥኩት ቁስሌን እያወራ እንደሆነ አልገባውም። “ምንም ስነስርዓት አታውቅም። ባለጌ ነህ እሺ!!” አልኩት “እሺ!” አለኝ ቁጣዬን ከምንም ሳይቆጥረው እጄን እየዳበሰ። “እሺ ግን ንገሪኝ። ማወቅ እፈልጋለሁ። ምኑን ልንገረው? አባቴ ከእህቱ ልጅ እንደወለደኝ እና ወንድ አያቴ እንዳሳደጉኝ? አድጌ ራሴን እስከማውቅ አባትና እናቴን እንደማላውቅ? ቤተሰቡ ውስጥ እንደ አንዳች መዓት ሲፀየፉኝ እንደኖርኩ? አያቴ ሲሞት ያየሁትን አስቀያሚ የህይወት ገፅታ? የቱን ልንገረው? ለማንም ለማውራት የሚቀል አልነበረም። እንባዬ መጣ። እያየኝ ማልቀስ አልፈለግኩም። ፈርጣጭ ይበለኝ። ተነስቼ መውጣት እንደጀመርኩ እንባዬን ማስቆም አቃተኝ። ሬስቶራንቱን መግቢያ እንዳለፍኩ እሮጦ ደረሰብኝ። አቀፈኝ። እንደህፃን ደረቱ ላይ አጥብቆ አቀፈኝ። አለቀስኩ። አላባበለኝም። ፀጉሬን እየደባበሰና እየሳመ ለቅሶዬን እስክተው ጠበቀኝ። ያስለቀሰኝ ምን እንደነበረም አልጠየቀኝም። እንደተለመደው እያሳቀኝ የሆስፒታሉ መግቢያ ድረስ ሸኘኝ። ሲሰናበተኝ መልሶ አቀፈኝ። እቅፉ ውስጥ ብዙ መኖር ፈለግኩ። ከሆነ ነገር የሸሸገኝ መሰለኝ። ሰላም ያለበት ዓይነት። እሱም የገባው ይመስል አቅፎኝ ለደቂቃዎች ቆየ። ግንባሬን ሳመኝ። “ዶክተር ሰላም አይደለሽም እንዴ?” ሲስተር ቀለም መግባቷንም አላስተዋልኩም። “ሰላም ነው ሲስተር” “ዶክተር ታዴ እየፈለገሽ ነው ኢመርጀንሲ ነው። ስልሽ እኮ አልሰማሽኝም።” እያወራችኝ የሻከረ መዳፏን ታፍተለትላለች። እስከዛሬ እጇን አይቼው አላውቅም። ከድምፅዋ በቀር ምኗንም አስተውዬ አላውቅም። ለምንድ ነበር አውርቻት የማላውቀው? ለምንድነው ግንባሬን እንደቋጠርኩ ገብቼ የምወጣው? እንዲያከብሩኝ? ሲሳይ እንዳለኝ በራሴ ስለማልተማመን? ወይስ ደረጃዬን ስጠብቅ? “ሲስተር ቤተሰብ አለሽ እንዴ?” አልኳት ለመሄድ እየተሰናዳሁ “አዎን ባለትዳር ነኝ። አንድ ልጅም አለኝ። ምነው? ምን አጠፋሁ?” ጉልበቴ ከዳኝ። ዞሬ አየኋት። በደቂቃ ብዙ ነገር አሰብኩ። ትፈራኛለች ምክኒያቱም ስራዋን ማጣት አትፈልግም። ከስራ ውጪ ስለምንም ነገር አውርቻት አላውቅም።ደሜ ቀዘቀዘ። እንዴት አይነት ጭራቅ አድርገው ነው የሚያስቡኝ? “እንዲሁ ማወቅ ፈልጌ ነው።ለምን ትፈሪኛለሽ? አንቺ በጣም ታታሪ ሰራተኛ ነሽ እኮ!!” ትከሻዋን ዳበስ አድርጌ ወጣሁ። ★ ★ ★ ፈገግ እያልኩ መሆኔ ለራሴ ይታወቀኛል። ታካሚዎቼን እየፈገግኩ እንደማዋራቸው ገብቶኛል እያፏጨሁም መሰለኝ።ሰሞኑን በተደጋጋሚ ከሲሳይ ጋር እራቴን መብላቴን ተከትሎ እንደዚያ እየሆንኩ ነው ዶክተር ሰይፈን ይቅርታ መጠየቄ የሆነ ጭነት ከላዬ ላይ እንደማራገፍ ነበር ወደ ስራ እንዲመለስ የሚያስፈልገውን ሁሉ እንደማደርግ ስነግረው ግን «ይቅርብኝ» ካለው ቃል በላይ ከቃሉ ጋር ከንፈሩን ነክሶ የፈገገው ፈገግታ ራሴን ደጋግሜ እንድረግም አድርጎኛል ሲስተር ቀለም በተረኛ ታካሚ ፈንታ ገባች “ዶክተር ሰው ይፈልግሻል?” “ሲሳይ ነው? ትንሽ ታገሰኝ በይውና ተረኛ ታካሚ
Show all...
ጠበኛ(ጠቢበኛ) እውነቶች ልብ ወለድ መፃህፍ በደራሲት ሜሪ ከበደ ቀርቦልናሌ ሁላችንም ገዝተን ብናነበው እላለው
Show all...
#ስንቴ_ገረዝኩት✂️ : #ክፍል_አንድ : : ✍ደራሲ:-ሜሪ ፈለቀ : : “አንቺማ አትገርዢኝም። በስመአብ! ” አለ እያማተበ ለመቀመጥም ለመነሳትም በቀረበ አኳኋን አየሩ ላይ ተንጠልጥሎ። “አየር ላይ ነህ፣ አረፍ ትል?” አልኩት አኳኋኑ ሳቄን እያመጣው “የታለ ዶክተሩ ከምር? ” አለኝ ወንበሩ ላይ ተስተካክሎ እየተቀመጠ “እኔ ነኝ!!” አልኩት ምን እንደሚያስብ ለመገመት እየሞከርኩ ካርዱ ላይ የተፃፈው እድሜ 33 ይላል። ወጣት ነው፣ ማንም ሴት አይታው የምትደነግጥለት ዓይነት ቁመናና መልክ፤ በራሱ የሚተማመን የሚመስል ገፅታ ፤ “አንቺማ አትገርዢኝም። ይዤው አረጃታለሁ እንጂ………” አለኝ ለኔ ሳይሆን ለራሱ የሚያወራ በሚመስል ድምፅ “ለምን? ሴት ስለሆንኩ?” “አወና ፣ ሴት ብቻ አይደለሽም። ህልም የመሰልሽ ቆንጆ ሴት ነሽ። ሆ!!” “እሱ ከስራዬ ጋር ምን አገናኘው?” “ላንቺ ነዋ ስራ…………” ቀጥሎ ያልሰማሁትን ነገር አጉተመተመ “ይቅርታ አቶ ሲሳይ ብዙ አገልግሎት ፈላጊዎች ውጪ ተሰልፈዋል። ስራችንን እንቀጥል?” “እህ ስለተቆጣሽ ይሰማሽ መሰለሽ እንዴ?” አለ ወደሱሪው ዚፕ አይኑን እየላከ። መሳቅ አምሮኛል ግን መሳቅ የለብኝም። “እንዴት ሳትገረዝ ……….?” ጥያቄዬን የምጨርስበት ቃል ስፈልግ “አረጀህ? አይባልም ግን እሺ! ……….. ባክሽ አንጀት ነው ታሪኩ። ………… ተረት ነገር ነው የሚመስለው።” “እየሰራሁ ታወራኛለሃ!!” ብድግ ብሎ ገላውን አራቆተው። “እንዴ እዚህ አይደለም የምሰራው።።።” አልኩት “ቆይ ግን ትልቅ ወንድ ገርዘሽ ታውቂያለሽ?” አለኝ ምንም የተጋለጠ ሳይመስለው ተረጋግቶ ልብሱን ወደሰውነቱ እየመለሰ። ” አዎ። አውቃለሁ። ” “እኔን የሚያህል?” ” ካንተም የሚበልጡ” “ይሄን ነገር መቼም እንዲህ እንደቆመ አትገዘግዢውም አይደል?” እፍረት አይታይበትም። ስለቆመው አክሱም እንጂ ስለቆመው ንብረቱ ያወራ አይመስልም። በድጋሚ መሳቅ አምሮኛል። ፊቴን አዙሬ ፈገግታዬን ደበቅኩበት። ጭንቅላቴ ውስጥ ብቅ ያለው ሀሳብ ግን ቆሞ ነበር እንዴ? የሚለው ነበር። በየሱስ ስም! “ማደንዘዣ እሰጥሃለሁ።” “እህ! አይደለም ማደንዘዣ ፀሀይ የመሰልሽ ሴት ነክተሽው ሞቼ እንኳን ቢሆን አይቆምም?” አሁን አለመሳቅ አልችልም ነበር። መጥሪያዬን ተጭኜ እጄን ከማንሳቴ ሲስተር ገባች። “ኸረ ፍጥነት? በሩ ላይ ነበረች እንዴ? ” በማያገባው የሚገባ ሰው በቸልታ ማለፍ አልችልም እኮ ግን እንዳልሰማ ወደ ሲስተር ዞርኩ ”OR 2 ይዘጋጅልኝ። ማረፊያውን ታሳይሃለች እዛ ቆየኝ።” ካርዱን ለሲስተር አቀበልኳት። እሷ ያልኳትን ሰምታ ወጥታለች። እሱ እንደተቀመጠ በትዝብት ያየኛል። “ምንድነው?” “ይሄን ፊትሽን ግን ስሞትልሽ ፀብ ሲኖረኝ ሲኖረኝ እዋስሻለሁ። እንቢ እንዳትዪኝ! ኸረ በኪዳነምህረት!! “ “አቶ ሲሳይ የሚመለከተን ነገር ላይ ትኩረት እናድርግ?“ “you see እያናደድኩሽ እንኳን ፈገግ ብለሽ ነው የምትቆጪኝ። ምክንያቱም ደሞዝሽን የምከፍልሽ እኔ ነኛ! ባትመቺኝ ሌላ አማራጭ እንደምጠቀም ታውቂያለሽ። ስለዚህ ምን ያህል ስድ የሆነ costumer እንኳን ቢገጥምሽ በትህትና ታስተናግጃለሽ። ረዳቶችሽ ወደውሽ እንጂ ደመወዝ ስለምትከፍያቸው ፈርተውሽ እንዲታዘዙሽ አታድርጊ! እንደዛ ሲሆን አብረውሽ ያሉት ምርጫ እስካጡ ድረስ ብቻ ነው ማለት ነው።” ልለው ያሰብኩት ብዙ ነበረ። ዋጋ ያለው ስላልመሰለኝ ተውኩትና እንዲወጣልኝ ብቻ በሩን አሳየሁት። ተነስቶ እየወጣ በሩን ተደግፎ ቆም አለና «ያንቺን ስራ ደመወዝ ከፍለሽ እንደምታሰሪያቸው ሳይሆን እነርሱም የስራው አካል እንደሆኑ እንዲሰማቸው አድርጊ ያኔ ላንቺ ወይ ለደሞዝ ብለው ሳይሆን የራሳቸው ስራ መሆኑን ስለሚያስቡ ማንም ስራው እንዲበላሽበት አይፈልግም።» «አቶ ሲሳይ ስድስት አመት ይሄን ሆስፒታል ቀጥ አድርጌ አስተዳርያለሁ። ሰራተኞቼን እንዴት መያዝ እንዳለብኝ አንተ አትነግረኝም!!» እንዴት ያለው ነው? እያናደደኝኮ ነው። ፈገግ ብሎ ከወጣ በኋላ መለስ ብሎ «አይባልም ግን እሺ! ቤት ውስጥ የተቀጠረ ሰው እንኳን አሁን ቀርቷል ሰራተኛ አይባልም። ሆስተስ፣ አቀናባሪ ምናምን ነው የሚባለው። በሙያቸው የሚረዱሽን ሰዎች ሰራተኞቼ? ኸረ አይባልም!» ብሎኝ በሩን ዘጋው!! ኡፍፍፍፍፍፍፍፍ ምን አይነቱን ነው ዛሬ ደግሞ የጣለብኝ? ★ ★ ★ በሶስት ቀናት ውስጥ የተኛሁባቸው ሰዓታት 7 መሙላታቸውን እንጃ። እቤቴ ሄጄ አላውቅም። ተረኛ ታካሚ እስኪገባ ስጠብቅ እያወራ ወደ ውስጥ ዘለቀ። “ስንቴ ነው የምትገርዢኝ?” “ማለት?” “ቁስሉ ተቦትርፎልሻል። ጨርሺኝ ብዬ ነው አንቺውጋ የመጣሁት።” “አልገባኝም። እስኪ እዛጋ ሁንልኝ። ምን ሆኖ ነው?” አልኩት “እኔ አንቺን ማሰብ ማቆም አቃተኝ። እሱም አለመቆም አቃተው። ተነፋፋሁ ሲል ቁስሉ ጣጣጣ…………” የሚያሾፍ ይመስላል። ቁስሉ ግን እንዳለው ቆስሎ ነበር። “ስነስርዓት ባለው መንገድ እንደአዋቂዎች እናውራ?” አልኩት።ማንም ደንበኛ በዚህ መጠን ነፃነት እንዳወራኝ አላስታውስም። “እኔ የምለው ማሂ?” አለ ኮስተር እንዳለ ” ዶክተር ማህደር” መለስኩለት “ኡፍ! ከክብርና ከፍቅር የቱ ይበልጥ ይመስልሻል?” “ሁለቱም ዋጋ ያላቸው የማይነፃፀሩ ነገሮች ናቸው።” ” ዶክተር ብልሽ ያከበርኩሽ ሊመስል ይችላል። ማሂ ስልሽ ግን ውዴታዬን እየነገርኩሽ ነው። ከክብር ሁሌም ፍቅር ይበልጣል። በክብር ውስጥ ፍቅር ላይኖር ይችላል። በፍቅር ውስጥ ግን ሁሌም ክብር አለ” የሆነ ነገሬን ያወቀ ስለመሰለኝ ተናደድኩ። ለተናገረው ትኩረት የሰጠሁ ባለመምሰል “ጨርሻለሁ። ተጨማሪ አንድ መድሀኒት አዝልሃለሁ። በትክክል መድሀኒቱን ከወሰድክ በድጋሚ እዚህ መመላለስ አያስፈልግህም።” አልኩት ” OK አልጋ ልትሰጪኝ ማለት ነው? እሱ ጥሩ ሀሳብ ነው። ” “አቶ ሲሳይ ለጨዋታ ጊዜ የለኝም።” ” ሊኖርሽ ግን ይገባል ማሂ!። ” መልስ ሳይጠብቅ የፃፍኩለትን ወረቀት ተቀብሎኝ ወጣ። ⚫️ይቀጥላል⚫️ ቶሎ ቶሎ እንዲደርሳችሁ Like 👍 እያደረጋቹህ ምርጦቼ😘 ማንኛዉንም አስተያየት በ @atronosebot አድርሱን
Show all...
Choose a Different Plan

Your current plan allows analytics for only 5 channels. To get more, please choose a different plan.