cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

Wanaw Media - ዋናው ሚዲያ

Media - ሚዲያ

Show more
Advertising posts
4 643
Subscribers
+124 hours
-107 days
-8130 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የዲጀታል ሚዲያ እና ማኅበራዊ ሚዲያ አጠቃቀምን በተመለከተ የራሷን ሕግና መመሪያ እንደምታዘጋጅ አሳወቀች። "እውቀቱ ሳይኖራቸው ቤተክርስቲያንን ወክሎ ሃይማኖታዊ አስተምህሮ ማስተላለፍ አይገባም " ሲሉ ብፁዕ አቡነ አብርሃም የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ ፣ የባህር ዳርና የሰሜን ጎጃም አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ መናገራቸው ተሰምቷል።ይህንን የተናገሩት"ኦርቶዶክሳውያን ብዙኃን መገናኛ ለኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን " በሚል በቤተክርስቲያኗ የሕዝብ ግንኙነት መመሪያ በተዘጋጀ ሥልጠና ላይ ነው። በተጨማሪም:— ✔" ቤተክርስቲያንን ሳያውቁ ተገቢው ሙያና እውቀት ሳይኖራቸው የሃይማኖት አስተምህሮ ለማስተላለፍ እና በየማኅበራዊ ሚዲያው እና ዲጂታል ሚዲያው ለመንቀሳቀስ የሚሞክሩ አሉ።እውቀቱ ሳይኖራቸው ቤተክርስቲያንን ወክሎ ሃይማኖታዊ አስተምህሮ ማስተላለፍ አይገባም " ✔" ማኅበራዊ ሚዲያውና ዲጀታል ሚዲያው  ከቤተክርስቲያን ይልቅ ለግለሰቦች እና ለቡድን ፍላጎቶች የመቆም ዝንባሌ በሰፊው ይታያል።ቅድሚያ ለቤተክርስቲያን መስጠት ይገባል ፤ ገንዘብ መስብሰብን ዓላማ ያደረገ የዲጂታል ሚዲያ እና ማኅበራዊ ሚዲያ ሥራ በመንፈሳዊ ቅኝት ያልተቃኘ በመሆኑ እርምት የሚሻ ነው " ✔" በቀጣይ የዲጀታል ሚዲያና ማኅበራዊ ሚዲያ አጠቃቀምን በተመለከተ የቤተክርስቲያኗ የራሷን ሕግና መመሪያ እንዲዘጋጅ ይደረጋል " ብለዋል።
Show all...
👍 3🤣 1
«ሌላ ትርጉም እንዳይሰጠዉ ብለን በሆደ ሰፊነት ብንታገስም ሙስሊሙን ማህበረሰብ መከራ ዉስጥ ጨምሮታል» የአማራ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት በአማራ ክልል ባለፉት 8 ወራትና መጋቢት 29/2016 በባህር ዳር ከተማ ሙስሊም ወንድሞች ላይ በተፈጠሩ ግድያ ላይ የተሰጠ መግለጫ፡- እንደሚታወቀዉ ሀገራችን ኢትዮጵያ የብዝህ ብሄር እና እምነት መገኛ ነች፡፡ በረጅሙ የሀገር ግንባታ ሂደት የተለያዩ ብሄሮችና እምነቶች በመደጋገፍ የጋራ ጠላት በገጠማቸዉ ጊዜ አብረዉ በመቆምና መስዋት በመክፈል በጋራ ደማቸዉን አፍሰዋል፣ አጥንታቸዉን ክስክሰዉ ሀገራችንን አስረክበዉናል፡፡ የተለያዩ እምነቶች በሰላምና በችግር ጊዜ አብረዉ በመቶም ለሀገር መጽናት ዉድ ዋጋ ከፍለዉ የጋራ የሆነችን ሀገራችንን አስረክበዉናል፡፡ የዚህ ታሪክ ወራሽ የሆን ልጆቻቸዉ አባቶቻችን በከፈሉት ዋጋ ኩራት ይሰማናል፡፡ ነገር ግን ባለፋት ስምንት ወራት በአማራ ክልል መንግስትና በታጣቂ ቡድኖች መካከል የተፈጠረዉ ግጭት ህዝባችንን የከፋ ዋጋ እያስከፈለዉ ስለሆነ በዋናነት በሙስሊሞች ላይ እየደረሰ ያለዉ ግፍ፣ መፈናቀል፣ ዘረፋ፣ መታገትና መገደል ከጊዜ ጊዜ እየተባባሰ በመሄድ ላይ ነዉ፡፡ ሌላ ትርጉም እንዳይሰጠዉ ብለን በሆደ ሰፊነት ብንታገስም ጉዳዩ ሀይል ከቀን ወደ ቀን ንጹሀን ዜጎችን በማገትና በመሰወር እንዲሁም በመግደል የክልሉን ህዝብ በተለይ ሙስሊሙን ማህበረሰብ መከራ ዉስጥ ጨምሮታል፡፡ ለማሳያ ያህል- 1. በቀን በ29/07/16 በባህር ዳር ከተማ ቀበሌ 14 የመቅሪብ ሶላት ሰግደዉ ወደ ቤታቸዉ በሚሄዱ አማኞች ላይ ማንነታቸዉ ያልታወቁ የታጠቁ ኃይሎች 4 (አራት) የአንድ ቤተሰብ አባላትንና 1 (አንድ) ጎረቤታቸዉን በመግደል ተሰዉረዋል፡፡ 2. 28/07/16 በጎንደር ከተማ ማክሰኝት አካባቢ 4 (አራት) ሙስሊሞች ተገድለዋል፡፡ 3. 29/07/16 በሞጣ ከተማ አንድን ወጣት ካገቱ በኋላ ቤተሰቦቹን በማስፈራራት ሶስት መቶ ሺ ተቀብለዉ ታጋቹን በአሰቃቂ ሁኔታ ገድለዉ ጥለዉታል፡፡ 4. በቢቸና ከተማ በቀን 26/07/16 ንጹሀን ባልና ሚስት ለምን ለመንግስት ግብር ከፈላችሁ ተብለዉ በግፍ ተገድለዋል፡፡ በአጠቃላይ በክልሉ በተለያዩ ቦታዎች ባለፉት ስምንት ወራት ከ80 (ሰማኒያ) በላይ ሙስሊሞች ሲገደሉ፤ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ሙስሊሞች ተፈናቅለዋል፤ 47 ሰዎች ታግተዋል፣ ከ260 በላይ ዘረፋ ተፈጽሟል፡፡ ስለሆነም የአማራ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ይህን ዘረፋ! ብዙ ስቃይ እና እንግልት፤ መገደልና መፈናቀል በጽኑ እናወግዛለን፡፡ ከዚህም በላይ ይህን እኩይ ተግባር ለማስቆም መንግስት፣ ሰላማዊዉ የክልሉ ህዝባችን፤ የሌላ እምነት ተከታይ ወገኖቻችን የኃይማኖት አባቶች እንዲሁም ጉዳዩ የሚመለከታችሁ አካላት በሙሉ የበኩላችሁን እንድትወጡ ወገናዊ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡ ይህ ሰላማዊ ዜጎች ላይ ያነጣጠረ ግፍና ግድያ ለዘመናት አብሮና ህብረት ፈጥሮ የኖረዉን ህዝባችንን አብሮነት ለማናጋት የታሰበ ስለሆነ በጋራ እንድንታገለዉ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡ በእኛ እምነት ይህን የሚያደርገዉ ገዳይ ዘራፊ ቡድን የማንንም እምነትና ብሄር የማይወክል መሆኑን እናምናለን፡፡ አሏህ አክብር! የአማራ ክልል እስ/ጉ/ከ/ም/ቤት መጋቢት 30/2016 ባህር ዳር
Show all...
👍 5
Repost from N/a
Update ባህርዳር ከተማ ትናንት ምሽት ከመስጅድ ሲወጡ የተገደሉት 5 ሰዎች ስርዓተ ቀብር ከመፈፀሙ በፊት በነበረው የጎዳና ላይ ተቃውሞ ሁለት የባጃጅ አሽከርካሪዎች ሰልፍ በሚያካሂዱት ላይ F1 ቦምብ ለመወርወር በዝግጅት ላይ እንዳሉ  ወዲያው ከፀጥታ አባላት በተተጎሰ ጥይት ተመተው ህይወታቸው ማለፉን የሊንክ ኢትዮጵያ የመረጃ ምንጮች ከስፍራው ገልፀዋል።ለትናንቱም ግድያ ሆነ ለዛሬው አደገኛ የእልቂት ሙከራ ሃላፊነቱን የወሰደ አካል የለም።ግድያ ፈፃሚዎች ስለመያዛቸው ከመንግስት አካል አልተገለፀም። @linkethiopia99
Show all...
የ10 ዓመት  ታዳጊ ልጁን በቢላዋ አርዶ የተሰወረ ተጠርጣሪ ወላጅ አባት በቁጥጥር ስር መዋሉን ፖሊስ አስታወቀ። በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ስልጤ ዞን በምዕራብ አዘርነት በርበሬ  ወረደ የ10 ዓመት ታዳጊ ልጁን በቢላዋ አርዶ የተሰወረዉ ተጠርጣሪ ወላጅ  አባት በቁጥጥር ስር መዋሉ የስልጤ ዞን ፖሊስን ጠቅሶ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል። እንደ ኮሚሽኑ ገለፃ በዞኑ ምዕራብ አዘርነት በርበሬ ወረደ በሙጎ ከተማ ልዩ ስሙ ሀሊቾ ተብሎ በሚጠራዉ መንደር ነዋሪ የሆነዉ ተጠርጣሪ መጋቢት 28 ቀን 2016 ዓ.ም በግምት ከረፋዱ 4:30 ግድም ለጊዜው ምክንያቱ በግልፅ ባይታወቅም ከራሱ አብራክ የተገኘን  የ10 ዓመት ታዳጊ ሕፃን ከመኖሪያ ቤቱ ጓሮ በመውሰድ መሬት ላይ አጋድሞ በቢላዋ አርዶት  ለጊዜው ከአካባቢው ተሰዉሮ እንደነበር ሸገር ታይምስ ሚዲያ ከኮሚሽኑ ማብራሪያ ላይ ለመመልከት ችሏል። በወንጀል መፈፀሙ መረጃ ደረሰዉ  የወረዳው ፖሊስ ከአካባቢዉ ህብረተሰብ ጋር በመሆን ድርጊቱ ከተፈፀመ ከደቂቃዎች በኋላ በፍጥነት  በተደረገ  ብርቱ ክትትል ተጠርጣሪውን በቁጥጥር ስር ማዋል እንደተቻለና የሟቹን  ታዳጊ አስክሬን በማንሳት ወደ ወራቤ ኮምፕርሄኔሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በመላክ አስክሬኑን በማስመርመር የሟች በድን ገላ በክብር እንዲያርፍ ለቤተሰቦቹ  ተመላሽ  መደረጉም ተገልጿል። ተጠርጣሪው ከተደበቀበት ጫካ ተደርሶበት በቁጥጥር ስር የማዋሉ ሂደት የአካባቢው ነዋሪዎች በተለይም ወጣቱ ያበረከተዉ አስተዋፅኦ ከፍተኛ ነበር ያለዉ ፖሊስ ህብረተሰቡ ላደረገዉ እገዛ አመስግኗል። የተፈፀመው ድርጊት አፀያፊና አሳፋሪ  መሆኑና ድርጊቱ የአካባቢዉን ማሀበረሰብ በጣም ያሳዘነ መሆኑን የገለፀዉ ፖሊስ ምርመራዉ  በተደራጀና በተቀናጀ መልኩ ተጣርቶ መዝገቡን  በአጭር ግዜ ዉስጥ ለሚመለከተው የህግ አካል የሚላክ መሆኑ የዞኑ ፖሊስ የወረዳዉን ፖሊስ ዋቢ አድርጎ ያደረሰው መረጃ መጠቆሙን ሸገር ታይምስ ሚዲያ ከኮሚሽኑ የተመለከተው መረጃ ያስረዳል።
Show all...
ይህ ዘገባ ስሜት የሚረብሽ መሆኑን እንገልፃለን።ዝርዝሩ ከታች አለ።
Show all...
👍 1

የሰላም ጥሪ የተቀበሉ የቀድሞው የአማራ ልዩ ኃይል አባላት ሁለተኛ ዙር ሠልጣኞች በብርሸለቆ የውትድርና ማሠልጠኛ ትምህርት ቤት የተሐድሶ ሥልጠናቸው ዛሬ መመረቃቸው አሚኮ ዘግቧል።
Show all...
😁 7
ይህ ፓስታ ሳይሆን ሐዋሳ ከተማ ከ8 ዓት ህፃን ጉሮሮ በቀዶ ህክምና የወጣ ትል/ፓራሳይት/ ነው። ትሉ የልጁን ጉሮሮ በመዝጋት ከተበከለ በኋላ በቀዶ ጥገና ተወግዷል። እነዚህ ትሎች/ፓራሳይቶች/ ወደ አንጀታችን የሚገቡት የእጃችንን ንፅህና ባለመጠበቅ ነው። በተጨማሪም ንፁህ ያልሆኑ/የተበከሉ ፍራፍሬዎችን እና አትክልቶችን በመመገብ ወደ እኛ ይተላለፋል። ስለዚህ የምግብ ንፅህናን በመጠበቅ እራሳችንን እና ሌሎችን ከበሽታው እንጠብቅ! (ዶክተር ናፊያ)
Show all...
👍 3🥰 2
መንግስት ጀማሪ ስራ ፈጣሪዎች/startups እንዲያብቡ በርካታ የፖሊሲ ለውጦችን ለማድረግ መወሰኑን " ካፒታል ጋዜጣ " ዘግቧል። ከነዚህም መካከል ፦ - ከስራ ፈቃድ፣ - ከግብር፣ - ከቢሮ ኪራይ፣ - ከፋይናንስ አቅርቦት፣ - ከጉምሩክ አሰራር ጋር በተያያዘ ወሳኝ ለውጥ የሚደረግባቸው ይሆናሉ ተብሏል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ አህመድ በተገኙበት ዛሬ ይፋ የተደረጉ ለውጦች በተለይ ስራ ፈጣሪዎች ከውጭ ለሚኖራቸው ግዥ የቀጥታ ክፍያ መፈፀም እንዲችሉ እንዲሁም ያገኙትን የውጭ ምንዛሪ ሙሉ ለሙሉ መጠቀም እንዲችሉ የሚፈቅድ መሆኑን ካፒታል ጋዜጣ አስነብቧል።
Show all...
👍 2