cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking ÂŤAccept allÂť, you agree to the use of cookies.

avatar

Ye hareruwa ebd lej😜😝🙃

Best pp Old music Capl pic New music Funny Tik tok video Ulum ale enant beca share join and for ward bmarg tebablun Endkrb ymflgut ngr kale @yabatlej beze teykug

Show more
The country is not specifiedThe language is not specifiedThe category is not specified
Advertising posts
354
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

ማታ መሽቶብኝ ወደ ቤት ስገባ አባቴ ፥ የት ነበርክ? እኔ ፥ ጓደኛዬ ጋር በፊት ለፊቴ 10 ጓደኞቼ ጋር ደወለና 4ቱ ስልክ አንስተው አዎ እዚህ ነበር 2ቱ አሁን ወጣ 3ቱ አለ እያጠና ነው ስልኩን ልስጠው? 1ዱ ከሁሉም ይባስ ብሎ በእኔ ድምፅ "ሄሎ አባዬ ፈለከኝ?"😳😕👏👍
Show all...
ሰው ምንም ቢበድልህ ፣ ቢያስከፋህ ፣ ቢጠላህ በአፈጣጠሩ ብቻ ውደደው! ምክንያቱም ሰውን የአምላኩ አምሳል እና እንዳ'ንተ ድንቅ ፍጡር ስለሆነ ብቻ ልትወደው እንጂ ከተፈጠረ በኋላ ያደረገውን መጥፎ ተግባር እያነሳህ ልትጠላው የተገባ አይደለምና! ፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨ ሰውን ስትወድ አምላክህ ይቀርብሀል ፤ ሰውን ስትጠላ ከአምላክህ ትርቃለህ!
Show all...
በደረቴ ልተኛ እልና . . . አንቺ ልቤ ውስጥ ስላለሽ ያፍንሻል ብዬ እተዋለው♥️😂
Show all...
@boznwa ✌️✌️✌️
Show all...
😘ሰሜናዊት ሙሽራ😘 💞ክፍል 11 ✍ዮሴፍ ተሾመ . . . ቀኑ ጷጉሜ 5 ነው።የአዲስ አመት ዋዜማ።በጠዋት ፀሐይ እዩኝ እዩኝ ማለት ጀምራለች።ከአሁኑ መስከረም ወር መጣሁ እያለ በሚመስል መልኩ እለተ ዋዜማው እንቁጣጣሽን መስሏል።የዮርዳኖስ ቤተሰቦች አዲስ አመትን ለመቀበል ሽር ጉድ እያሉ ነው።ዮርዳኖስ ጥሩ ውጤት በማምጣት ቤተሰቡን አስደስቷል ።የዩኒቨርስቲ መግቢያ ነጥብ 491 ነው ያስመዘገበው። ዮርዳኖስ ሔዋንን ከተሰናበተ በኋላ ጨዋታ እና ሳቅ ከእሱ ኮብልለው ሔደዋል።ጭምት ሆኗል።ዝምተኛ ሆኗል።ቤት ውስጥ ገፍተው ካላወሩት እሱ እንደበፊቱ ቤተሰቦቹን በወሬ መጥመዱን እርግፍ አድርጎ ከተወ ውሎ አደረ።ቤተሰቡም ምክንያቱን ስለሚያውቁ እሱን ለማስደሰት መከራቸውን ሲያዩ ነው የሚውሉት። "ዮርዲ ስልክህ አየጠራ ነው"አለች ወይዘሮ አለም ዮርዳኖስ ስልኩን ከቻርጀሩ ላይ ነቅሎ ሲመለከት ቃለአብ ነው የደወለው ። ዮርዳኖስ ስልኩን አነጋግሮ ከቃል ጋር ተቆጣጥረው ስልኩን ዘጋው። ቃለአብ እና ዮርዳኖስ ከብስክሌቱ ቀን በኋላ በደንብ ተዋውቀዋል ።የሁለቱ የደሳለኝ እና የዮርዳኖስ ፍቅር ላይ ቃለአብ ተጨምሮበት ደምቀዋል።ነገር ግን ዮርዲ ውስጡን የሆነ የሚረብሸው ነገር አለ።ቃለአብን ሲያይ ልቡ ይሸበራል።ምክንያት አልባ ፍርሀት ያስጨንቀዋል። ቃለአብ ዮርዳኖስን እና ደሳለኝን ለመተዋወቅ ቀናት አልፈጀበትም በአንዴ ነበር በሁለቱም ልብ ውስጥ መግባት የቻለው ።በአዲስ አመት ደሴ ወደ ዋቻሞ ዮርዲ ደግሞ ወደፊት ወደ ሚደርሰው ዮኒቨርስቲ ሲበታተኑ ቃለአብ ብቸኝነት እንደሚገድለው እያሰበ ነው።እዚህ ግቡ የማይባሉ ጓደኞች ያሉት ቃለአብ ጓደኝነትን ከዮርዲ እና ከደሴ በዚች አጭር ጊዜ ውስጥ ተምሯል።ፍቅርን በደንብ ከትበውታል። ፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨ ደሳለኝ ሲመጠ ቤት ቤት ውስጥ ወይዘሮ አለም እና ዮርዳኖስ ብቻ ናቸው ያሉት።ወይዘሮ አለም የዳቦ ቡኮ እያዘጋጀች ሲሆን ዮርዲ ደግሞ የአዲስ አመት ዋዜማን አስመልክቶ ለተዘጋጀው የግጥም ምሽት ግጥሙን እየተለማመደ ነው።አቶ ተሾመ በግ ለመግዛት ደብረ ማርቆስ ሔዷል።ቤዛ ደግሞ ሱቅ የአባቷን ቦታ ተክታ እየሰራች ነው።እልፍነሽም የሚገዛዛውን ለመግዛት ገበያ ወጥታለች። ፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨ "እኔ እምልህ ግጥማችን የሚያሸንፍ ይመስልሀል?"አለ ዮርዲ ደሳለኝን በፍቅር እያየው ። "እንዴታ ከዚህ በፊት ተሸንፈህ አታውቅም።አሁን ደግሞ ከቃለአብ ጋር ነው በጥምረት የሰራችሁት።ሁለቱን ትጉህ ወንድሞቼንማ ማንም አይበልጣቸውም "አለ ደሴ ኩራት እየተሰማው። "እሺ አሁን ለቃል ደውልለት እና እንውጣ አብረን መለማመድ አለብን።ቅድም እኮ ደውሎ ደሴ ይምጣና እደውልልሀለሁ ብዬው ነበር።"አለ ዮርዲ "እሺ እደውልለታለሁ።ግን አንተ ስላየኸው ህልም ለምን አትነግረውም መንታ ወንድሜ እንደሆንክ ነው የሚሰማኝ ብሎ ለመናገር እንደዚህ መፍራት ምንድን ነው?አለ ደሴ "ባክህ ባልነግረውም እኮ አሁን የወንድማማች ያህል ነው የቀረበን"አለ ዮርዲ "አየህ አንተ እሱን በአጋጣሚ ሳይሆን በምክንያት ነው ያገኘኸው።ደግሞ አልገባህ አለኝ እንጂ የሆነ ነገር እየሸተተኝ ነዉ" አለ ደሴ ። "እስኪ ማታ ከፕሮግራሙ በኋላ እምናየው ይሆናል።"አለ ዮርዲ ፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨ ምሽቱ በግጥም ተወዳዳሪዎች ደምቋል።በእየ እረፍቱ የባህል ቡድኑ ሞቅ ያለ ውዝዋዜ እያቀረቡ ግዙፋን የትንሣኤ አዳራሽ በዓል በዓል አሽትተውታል ።ሶስተኛ እና ሁለተኛ የወጡት ልጆች ግጥማቸውን አቅርበው አሁን አንደኛ ማን እንደወጣ ሁሉም በጉጉት እየጠበቀ ነው። "አንድ ሞቅ ያለ የባህል ሙዚቃ ጋብዘናችሁ ተመልሰን እንገናኛለን መልካም አዲስ አመት"ብሎ መድረክ መሪው ለተወዛዋዦች መድረኩን ለቀቀ። ዮርዳኖስ ቃለአብ እና ደሳለኝ ሁሉም የበዓል ልብሳቸውን ለብሰው አሸብርቀው በረድፍ ተቀምጠዋል።ከአንድ ማህፀን የወጡ ወንድማማቾች ነው የሚመስሉት። ፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨ "የዚህ የግጥም ምሽት አሸናፊ ከዚህ በፊት ከአንዴም ሁለት ሶስት ጊዜ በተደጋጋሚ የግጥም ምሽትን ሽልማት የወሰደው እንዲሁም የወረዳችን ታዳጊ ገጣሚ በሚል ከወረዳ ባህልና ቱሪዝም ሜዳሊያ የተበረከተለት ዮርዳኖስ ተሾመ እንዲሁም ለግጥም ምሽት እንግዳ የሆነው ቃለአብ ተሾመ በጥምረት "ትንሳኤሽ" በሚል ርዕስ አሸናፊ ሆነዋል።ወደ መድረክ" አለ መድረክ መሪው ። ዮርዲ እና ቃል ወደ መድረክ ሲወጡ ወንድማማቾች ናቸው እንዴ የሚል ሹክሹክታ ጭብጨባውን አልፎ እየተሰማቸው ነበር።ደሳለኝ ዮርዲ እና ቃል መድረክ ላይ ወጥተው ማይክ እስኪቀበሉ ድረስ ቆሞ በፌሽታ ጮቤ እየረገጠ ነበር። ግጥሙን አቀረቡ ።ታዳሚ በሙሉ ቆሞ አጨበጨበላቸው።የግጥም ምሽት ታዳሚ በሙሉ በፊት ዮርዲ አሸንፎ ካጨበጨበለት በላይ ዛሬ ከቃል ጋር ጥምረታቸውን አድንቆ ጥበብ ውለታችሁን ትክፈላችሁ ብሎ መረቃቸው።ዘለዓለም አንድ ላይ ተጣምረው መድረክ ላይ ደምቀው እንዲታዩ ደሳለኝ በልቡ ፀለየ። ቃለአብ ደስታውን መቆጣጠር አቅቶት እዛው መድረክ ላይ"የአንተ ወጤት ነው"እያለ ዮርዲን ደጋግሞ ያቅፈዋል።ዮርዲ ቃለአብ ሲያቅፈው ልቡ ሰትንሸራት ይሰማዋል ። ፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨ ፕሮግራሙ ከተጠናቀቀ በኋላ ሶስቱም የሻነው ባር ውሰጥ መጠጥ አዝዘው ደስታቸውን እያከበሩ ነው። "ዮርዲዬ የሆነ ነገር ልነግርህ እያሰብኩ ነገር ግን እየፈራሁ እተወዋለሁ ።"አለ ቃል ደሳለኝ ጣልቃ ገባና "ከዛ በፊት ዮርዲ የሚነግርህ ነገር አለ እሱን አድምጠው"አለ ዮርዳኖስን ተናገር በሚል አስተያየት እያየው "እሺ ልስማህ ወንድሜ ቀጥል "አለ ቃል ወንድሜ ብሎ ሲጠራው ዮርዲን የሆነ ነገር ነዘረው "ግዴለም አንተ ቀጥል እኔ ቀስ ብዬ እነግርሃለሁ "አለ ዮርዲ ቃለአብ ከብርጭቆው ተጎነጨና"ዮርዲዬ እንደ እውነቱ ከሆነ አንተን ያወቅኩህ ያው እንደነገርኩህ የግጥም ምሸት ፕሮግራም ላይ ግጥም ስታቀርብ ነው።በፕሮግራሙ ላይ ለውድድር ስቀርብ የመጀመሪያ ቢሆንም ለመታደም ግን አልፎ አልፎ እመጣ ነበር ።የመጀመሪያ ቀን እንዳየውህ እንዴት እንደደነገጥኩ አትጠይቁኝ።" "ለምን"አሉ ደሴ እና ዮርዲ በአንድ ድምፅ ቃል ዮርዲን ትክ ብሎ ሲመለከት ከቆየ በኋላ ብርጭቆው ላይ የቀረውን መጠጥ በአንድ ትንፋሽ ጭልጥ አደረገና መናገር ጀመረ። "ገና እንዳየውህ ልቤ በፍጥነት መምታት ጀመረች።ወንድሜ ወንድሜ መስለህ ታየኸኝ" አለና ቀና ብሎ ዮርዲን ሲመለከት ዮርዲ በጉንጮቹ እንባ ሞልቶ እየፈሰሰ ነበር። "እኔም እኮ የመጀመሪያ ቀን ያገኘውህ በአጋጣሚ ሳይሆን በምክንያት ነው"አለ ዮርዲ ደሳለኝ ድራፍቱን ፋት እያለ የሚፈጠረውን በጉጉት እየጠበቀ ነው ። ቃለአብ ዮርዲ ለምን እንዳለቀሰ ባይገባውም ያገኘውህ በምክንያት ነው የሚለው የዮርዲ ንግግር ልቡ ላይ ቀርቷል ። "በምን ምክንያት ነው ያገኘኸኝ"አለ ቃል " ደሳለኝ የዚያን ቀን ብስክሌቱን የተበደረህ እውነት ፈልጎት ሳይሆን እኔ እና አንተ ተቀራርበን እንድናወራ ነበር ።አየህ ከወራት በፊት ህልም አየሁ..........ብሎ ያየውን ህልም ነገረው።"ዮርዲ ተናግሮ እንደጨረሰ ቃለአብ እያነባ ተነሳና ወንድሜ ብሎ አቀፈው። ፨ ፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨ "ለእናቴ ብቸኛ ልጅ ነኝ አባቴን አላውቀውም እሱ ግን ያውቀኛል።በእየ ጊዜው ልብስ ይልክልኛል።እናቴን አባቴን አስተዋውቂኝ ስላት ትቆጣለች ትናደዳለች።ወንድም እህት የሚባል ነገር የለኝም።"አለ ቃል እንባ እየቀደመው ። "ቃል እኔም እኮ ወንድም የለኝም ግን
Show all...
​​አለኝ አየህ መወለድ ቋንቋ ነው ይባል አይደል?ደሴ ከእናቴ ማህፀን ባይወለድም ለእኔ ግን ወንድሜ ነው።ደግሞ ከዚህ በኋላ እንደዚህ ስትል እንዳልሰማ እኔም ደሴም ወንድሞችህ ነን"አለ ዮርዲ። ቃል በደስታ ማበድ ነበር የቀረው ።ምንም ማለት አልቻለም ደሴን እና ዮርዲን እየተካካ ያቅፋቸዋል። "እስከ አሁን ሳዳምጥ ነበር አሁን ደግሞ አድምጡኝ ልናገር"ብሎ ደሴ መናገር ጀመረ።"እውነት ሔዋን ከሔደች ጀምሮ ዮርዲ እንደዚህ ሲደሰት አይቼው አላውቅም።ቃለአብ አንተ ዮርዲን ህይወት ዘርተህበታል።ዮርዲ ፈገግ ሲል ወጥሮ ይዞኝ የነበረው ጭንቀት ለቀቀኝ።አንድ ነገር ግን አሁንም እየከነከነኝ ነው።በሁለታችሁ መካከል የሆነ ነገር እንዳለ እየተሰማኝ ነው።በጣም እኮ ነው የምትመሳሰሉት "አለ ደሴ ቃል እና ዮርዲ በደሴ እየሳቁ ነበር እየቀለደ መስሏቸው ።ነገር ግን ደሴ እየቀለደ አልነበረም ። ይቀጥላል
Show all...

Ena hulam yanhi merha endalhonku awkalew gen yene merha gen ahnhi beha neshi💔💔 @boznwa @boznwa
Show all...
Yaw hulam anhin mewdedan alakomem hulam💔💔 @KiyaD1994 @king_tin
Show all...
🤣🤣🤣🤣🤣🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰 @boznwa
Show all...
Ebdt 🥰😜😝❣❣❣❣❣❣❣❣ @boznwa
Show all...