cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ከመጽሐፍት መንደር💠

አንብብ አዕምሮህ ልክ አንደባህር ይሰፋል። ወንዞችም ለአንተ መገበር ይጀምራሉ። አንተ ወደ ሰዎች ሳይሆን ሰዎችም ወደአንተ ይመጣሉ። ማንብብ ሙሉ ሰው ያደርጋል!! አንብብ ብታነብ የሚቀርብህ ድንቁርና 🟩🟩🟩🟩🟩🟩🟩🟩🟩🟩 🟨🟨🟨🟨🟨🟨🟨🟨🟨🟨 🟥🟥🟥🟥🟥🟥🟥🟥🟥🟥 ለማንኛውም አስተያየት @manbabemuluyadergal_bot

Show more
Advertising posts
3 640Subscribers
+224 hours
+147 days
+6530 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

♥️የከንቲባው ልጅ♥️ 🥀ክፍል 19🥀 . . Notice :- እውነተኛ ታሪክ ነው! . . ━━━━━━━✦✗✦━━━━━━━ አዘጋጅ እና አቅራቢ=-ከደራሲያን አለም የቴሌግራም ቻናል . . ከከንቲባው ልጅ ጋር ቲቪ ከፍተን እያየን እያለ ስልኬ ላይ Msg ገባና አውጥቼ ሳየው Cost ገብቶልኝ ነው ። Non cafe ስለሆንኩኝ እንደ ተለመደው መንግስት #450 የኢትዮጵያ Dollar ባንክ account ላይ አስገብቶልኛል ። እኔ የምለው ግን ፡ መንግስት ለካ እንዲህ ቋጣሪ ነው ። cost መግባት የነበረበት በየወሩ በ #28 ነበር ። የዚህኛው ወር ግን በ #36ኛው ቀን ነው የገባው ። ቆይ ግን #450 ብር ለ #1 ወር በዚህ ኑሮ ፡ ብር ሆና ነው የምትበላው .? ያውም ከተማሪ ። እኛኮ ለምሳ እና እራት ብቻ #1200 ብር ነው የምንከፍለው ። እነሱ ግን የ #5 ሚሊዮን ብር እራት በልተው ፤ በ #450 ብር መፋቅያ ጥርሳቸውን ይፍቃሉ ። Bisrat tv እያየን ነው ። ፕሮግራሙም ስለ ሶሪያ ህፃናት ነው ። አንድ የ #7 ዓመት ህፃን እንዲህ እያለ ነው "በሽር አል አሳድ'ን (የሶርያ president) ምን አደረግነው ...? ዝምብለን እየኖርን ነበር ። ምንም ሳናደርገው ቤታችንን አፈራረሰብን ፣ ቤተሰቦቻችንን እንዳለ ገደላቸው ። ቆይ ግን ምን አድርገነው ነው ...?" ። ይሄንን ሲናገር ፊቱ እንደ ጎርፍ ዝናብ በዕምባ ተሞልቶ ነበር ። ሶሪያ ውስጥ የሞቱት ህፃናት ብቻ ከ #50,000 በላይ ናቸው ። አብዛኛዎቹ ሀገር ሰላም ብለው የትምህርት ገበታ ላይ የነበሩ ታዳጊዎች ናቸው ። በራሳቸው ጥፋት ሳይሆን በአባቶቻቸው የእርስ በእርስ ጦርነት ምክንያት ነገን ሳያዩ ዛሬን ሳይኖሩ በአጭር የተቀጩ ህፃናት ። ዛሬም ድረስ ጦርነቱ ቀጥሏል ፣ ሀገሪቷ ምድረ በዳ ሆናለች ፣ የሶሪያ ህፃናትና ህዝቦችም ስደት ላይ ናቸው ። አሸናፊ የሌለው የእርስ በእርስ ጦርነት መጨረሻው እንግዲህ ይህ ነው ። ከወር በፊት ሳቢያን ፡ ድሬዳዋ ብር ለማውጣት ባንክ ቤት ስሄድ መንገድ ላይ የሶሪያ ስደተኞች ተቀምጠው ሲለምኑ አይቼ ነበር ። ባልና ሚስት መሀላቸውን ልጃቸውን አስቀምጠው ፊትለፊት ደግሞ በአማርኛ ፊደል የተፃፈ "የሶሪያ ስደተኞች ነን ፡ እባካችሁን እርዱን" የሚል Copy ወረቀት ተቀምጦ ፣ በዚያ በኩል የሚያልፍ ሰው ደግሞ ከንፈሩን እየመጠጠላቸው ያለውን #1 ፣ #5 ፣ #10 ብር እየሰጣቸው ያልፍ ነበር ። እኔም ሳያቸው አንጀቴን ነበር የበሉኝ ። በተለይ ደግሞ መሀላቸው የተቀመጠው ፣ ምንም የማያውቀው ፣ #4 ዓመት እንኳን ያልሞላው ህፃን ልጅ እንዴት እንደ ሚያሳዝን ። anyways አያድርገውና ኢትዮጵያን ሳስባት እንደ ሶሪያ ካልሆንኩኝ ሞቼ እገኛለሁ ያለች ትመስላለች ። ሰላም ስልችት ብሏት ደም ደም ከሸተታች ሰነባብታለች ። ሰላም ሲሆን ጀርባዋን ይበላታል መሰለኝ ግደል ግደል ፣ ሰልፍ ውጣ ሰልፍ ውጣ ፣ ኮብል ኮብል ፣ አፍርስ አፍርስ ፣ ረብሽ ረብሽ ፣ ወዘተ ወዘተ ይላታል ። (ወዘተ ወዘተ እንኳን አይላትም ...😜) ። ከሶሪያ እንኳን መማር አልቻለችም ፤ የሰላም ዋጋ ምኑም አልገባትም ። ዛሬ ሁላችንም በየቤታችን ሆነን የምናየው የሶሪያ መጨረሻ የሌለው ዕልቂት ፣ መድረሻው የማይታወቅ ስደት ፣ መልስ የማያገኝ ጥያቄ ፣ ቀስ በቀስ የኛው ታሪክ ሆኖ ዓለም በየቤቱ ቁጭ ብሎ ይታዘበናል ። ልክ ዛሬ ለነዚህ ስደተኞች ከንፈር እየመጠጥን ሳንቲም እንደ ወረወርን ፤ አንድ ቀን ደግሞ ለኛም በባዕድ ሀገር ይወረወርልን ይሆናል ። ይሄ እንዳይሆን ከፈለግን ሁሉን ነገር የመንግስት ስራ ነው ማለቱን ትተን ለሰላማችን ስንል እራሳችን ፣ ቤተሰባችን ፣ ጓደኛችን ፣ ጎረቤታችን ፣ ሰፈራችን ፣ ቀበሌያችን ፣ ወረዳችን ፣ ዞናችን ፣ ክልላችን ፣ ምናምን ሳንል ለአንዲት ሀገራችን በጋራ ብንሰራ የተሻለ ብቻ ሳይሆን ተመራጭም ይሆናል ።.... የከንቲባው ልጅ በጣም ተጨንቃለች ። የአባቷ ስልክ አለመስራት ፣ ደብረ ዘይት ያየነው ሰውዬ ፣ ወደ ቤት ስንመለስ መብራቶቹ በርተው ማግኘታችን ፣ በቃ ሁሉም ነገር መጥፎ መጥፎውን እንድናስብ አርጎናል ። ከዚህም በላይ ደግሞ ያሳሰባት ነገር እኔን የሷ ችግር ውስጥ ማስገባቷ ነው ። አዚህ ቤት ውስጥ መሆን ይበልጥ ስለ ችግሩ እንድናስብ እንደሚያደርገን አውቃለሁ ። ይዣት ወጥቼ እንዳላስረሳት ፤ አባቷ እንዳሉትም ዛሬ የሚመጡ ከሆነ ከቤት እንዳያጧት ስለሰጋሁ ነው ። ለፖሊስ እንዳናመለክት ስለጉዳዩ ትተው ወደኛ እንደ ሚዞሮ ግልፅ ነው ። የሚከታተለንን ሰውዬ ትተው እኛን "እናንተ ማናችሁ ፣ ይሄ ቤት የማነው ፣ ይሄን ሁሉ ንብረትስ ከየት አመጣችሁ ...?" ከማለት አያልፉም ። ለጊዜው እንደ መፍትሔ ያየሁት ፊልም ማየቱን ነውና After የሚል ምርጥ የፍቅር ፊልም ሶፋ ላይ ሆነን እያየን ነው ። በመሀል በመሀል ሲሳሳሙ እየተሳሳምን ፣ ሲተቃቀፉ እየተቃቀፍን ፣ ሲጣሉ ደግሞ በመሃላችን ክፍተት እየፈጠርን በስተመጨረሻ ተቃቅፈን ፊልሙ አለቀ ። በፊልሙ ላይ ቅር ያለን ነገር ቢኖር ሲያልቅ ተዋንያን ሲፅፍ የኛን ስም አለመጥቀሳቸው ነበር ። እሱን እንደ ጨረስን ቁርስም ስላልበላን በጣም እርቦን ስለነበር ተያይዘን ወደ ኩሽና ገባን ። የጊቢ ተማሪ ሞያ + የቤት ልጅ ሞያ = ሞያሽ ሞያሽ ይዘርዘርልሽ ። ቁርስን መቀነስ ፣ ምሳን መሰረዝ ፣ እራትን ማሳነስ ብዙ ዕድሜ ለመኖር ዋስትና ነው ይላሉ ከቤተሰብ የተላከላቸውን ብር በአንድ ሳምንት የሚጨርሱ የጊቢ Non cafe ተማሪዎች ። በአለማችን ላይ በረሃብ የሞቱ ሰዎች ጥቂቶች ናቸው ። በተቃራኒው ግን በጥጋብ የሞቱት በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ናቸው ። ስንቶቻችን ነን በምላሳችንና በጥርሳችን መቃብራችንን ስንቆፍር የምንውለው ...! ሆድ እንዳሳዩት ነው ፣ ወስፋታችንን መግታት ከብዶን ሁሉንም እችላለሁ ብለን አግበስብሰን ቁንጣን እስኪይዘን ድረስ የምንበላ ከሆነ መጨረሻችን እስኪሻለን ድረስ መፆም መሆኑን ማወቅ ይኖርብናል ። አንዳንድ ሰዎች "ስትበላ እንደልብ ፣ ስትጠጣ እንደልክህ" ይላሉ ። እኔ ግን እላችኋለሁ 'ሲርብህ ብላ ፣ ሲጠማህ ጠጣ' ። ፈላስፋው ሶቅራጥስም በዘመኑ "እኔ ለመኖር ስበላ ፣ ሌሎች ግን ለመብላት ይኖራሉ" ብሎ ነበር ። በዚህ ዘመን ግን ሀብታም ከሆነ በፈለገ ጊዜ ፣ ደሀ ከሆነ ደግሞ በአገኘ ጊዜ ሆኗል ነገሩ ። anyways ቤት ውስጥ ስጋ ነክ ነገሮችና እንጀራ ለጊዜው ስለሌሉ ቆንጆ ፓስታ ከከንቲባው ልጅ ጋር ተባብረን ሰርተን ተባብረን በልተናል ። ከሰዓታችንን ደግሞ መፅሐፍ በማንበብና ሙዚቃ በመስማት ልናሳልፈው አቅደናል ። ከአጫጭር የልቦለድ መፅሐፍት ውስጥ የአሌክስ አብርሃም "ዶክተር አሸብር" የሚለውን በጣም ስለምወደው እሱን ተራ በተራ የምንወደውን ርዕስ እየመረጥን አንዳችን ላንዳችን እያነበብን ከልባችን እየሳቅን ሳናስበው ቀኑ ለምሽት መንበርከክ ጀመረ ። በስተመጨረሻም ካሏት የግጥም መፅሐፍት ውስጥ አንዱን መርጬ በጣም የምወደውን አንድ ግጥም እንዳነብላት ጋበዘችኝ ። እኔ ግን Control ብፌው ውስጥ የሚታየኝን ወይን ከሁለት ብርጭቆ ጋር አውጥቼ ፣ እጇን ይዤ ከሳሎን ወደ ጊቢ ውስጥ ወጣን ። በረንዳ ላይ ተቀመጥንና ወይን እየጠጣን ፣ ጨረቃዋን እያየን የምወደውንና በቃሌ የማውቀውን አንድ ግጥም በዜማ እልላት ጀመር ። እንዲህ ብዬ ...🔈 ከ 100 ላይክ ቡኋላ ክፍል 20 ይለቀቃል🌹   ኢትዮጵያን ይጠብቅልን 🫶🇪🇹🇪🇹♥️❥❥__⚘_
Show all...
♥️የከንቲባው ልጅ♥️ 🥀ክፍል 18🥀 . . Notice :- እውነተኛ ታሪክ ነው! . . ━━━━━━━✦✗✦━━━━━━━ አዘጋጅ እና አቅራቢ=-ከደራሲያን አለም የቴሌግራም ቻናል . . ትዝ ይለኛል ስንወጣ አጥፍተን ነበር። ህይወት ዞር ብላ በፍርሃት ታየኝ ጀመር..።    "አጥፍተን ነበር አ የሄድነው ...?" አለችኝ ። እራሴን በአዎንታ ወደላይ ወደታች ነቀነኩኝና 'አባትሽ የዚህን ቤት ቁልፍ አላቸው እንዴ ...?' አልኳት ባለፈው ሲመጡ በር ላይ ነኝ ብለው ስለደወሉላት ። "አዋ አለው ፣ ባለፈው ሲመጣ ረስቼ ነው ብሎኛል" አለችኝ ። ከእሷና ከአባቷ ውጪ ቁልፉን ማንም ከሌለው ፣ በዛላይ አባቷ እንዳሉትም ሀገር ውስጥ ከሌሉ ፣ በተጨማሪም ቢሾፍቱ እያለን ካየነው ሰውዬ ጋር ሲደማመር የሆነ ችግር እንዳለ በግልጽ ተሰማኝ ። "ይሄኔ ነው መሸሽ" አለ ያገሬ ሰው ፤ አሁን ገና ፍርሀት የሚባለው ስሜት አካሌን ወረረው ። "ሞት ላይቀር ፍርሀት ፤ አመል ላይቀር ቅጣት" ። "ፈሪ ውሃ ውስጥ ሆኖ ያልበዋል" ፤ እኛ ግን የጦርነት ቀጠና ውስጥ ሆነን ደርቀናል ። "ፈሪ ከአልጋ ላይ ወድቆ ይሞታል" ፤ እኛ ግን አልጋ ላይ የመውጣት አቅምም የለንም ። "ፈሪ የሚያባርረው ሳይኖር ይሸሻል" ፤ እኛ ግን የሚያባረን እያለ ካለንበት መንቀሳቀስ ከብዶናል ። ሞት በየሁሉም ሰው በራፍ ላይ የሚቆም ጥቁር መላክ ነው ። እኛም ቤቱን ፈትሸነው ባዶ መሆኑን ስናረጋግጥ ይህ በራፋችን ላይ የቆመው የሞት መላክ እንዳይወስደን በሩን ሁለት ጊዜ ቆለፍነው ። ተስፋና ፍርሀት ሁሌም አይነጣጠሉም ። ፍርሃት ያለ ተስፋ ፣ ተስፋም ያለ ፍርሃት አይኖርም ። ፍርሃትን የሰጠ አምላክ ፡ ተስፋንም አይነፍግም ። "ተስፋ ያልቆረጠ መነኩሴ ምናኔ ሲሄድ ሴቲቱን ይሰናበታል" አሉ አበው ። እኛም ምንም እንኳን ወደሞት እየሄደን ቢመስለን በምድር ተስፋ አልቆረጥንም ። አባቷ መጥቶ ከሆነ ብለን በሀገር ውስጥ ስልኩ ላይ ስትደውልለት "የደወሉላቸውን ደምበኛ አሁን ማግኘት አይችሉም..." አለች የቴሌ ሰራተኛ ። በጣም ተጨንቀናል ። ጭንቀታችን በከንቱ ይሁን አይሁን ግን አናውቅም ። ከመተኛታችን በፊት ከጊቢ የዶርም ጓደኛዬ ደውሎልኝ ነገ ትምህርት እንደሚጀምር እና class ባልገቡት ተማሪዎች ላይ እርምጃ እንደ ሚወሰድ ነገረኝ ። ስልኩ speaker ላይ ስለነበር ያለኝን ነገር የከንቲባው ልጅም ሰምታለች ። አንድ ሶፋ ላይ ሆነን የመረቀነ የድሬ ልጅ መስለን አይናችንን አፍጥጠን እየተያየን የዕሮቡ ለሊት ለሀሙሱ ጀምበር እጁን ሰጠ ። ስንት ሰዓት እንደ ተኛን አላውቅም ። እራሳችንን እዛው ሶፋ ላይ ተቃቅፈን አገኘን ። አዲስ ነገር ካለ ብለን ቤቱንና ጊቢውን ፊትሽነው ። ሁሉንም ነገር ግን ትተነው እንደ ተኛን አገኘን ። ትንሽም ቢሆን ተረጋግተን "በቃ አንተ ወደ ጊቢ ተመለስ ፡ በኔ ምክንያት ትምህርትህን እንድታጣ አልፈልግም ። እስካሁን ድረስ ለኔ ያደረከው እራሱ ከበቂም በላይ ነው" አለችኝና ልትሸኘኝ ወደ ጊቢው ወጣን ። እኔም እቅፍ አረኳትና 'አይዞሽ እሺ ምንም አይፈጠርም ። ደግሞ ብዙም አልቆይም ፡ ፍቃድ ብቻ ጠይቄ ነው የምመልሰው እሺ' አልኳትና ስታለቅስ ላለማየት ብዬ በፍጥነት ወደ ውጪኛው በር አመራሁ ። ልክ በሩን ስከፍት "ትተኸኝ በዛው እንዳትቀርብኝ እሺ የኔ ጌታ ፣ ብቻዬን እፈራለሁ ፣ ደግሞም ማንም እንደሌለኝ ታውቃለህ አይደል...?" አለችኝ ልክ የመጀመሪያው ቀን ስንገናኝ "ትተኸኝ አትሂድ ፡ ማንም ሰው የለኝም" ባለችኝ ዜማ ። ዞር ብዬ ሳያት ፊቷ በዕምቧ እየታጠበ ነው።... በሩን አልፌ የመሄድ አቅም አልነበረኝም ። ዘጋሁትና ወደሷ ተመልሼ እቅፌ ውስጥ አስገባዋት ። ስቅስቅ ብላ አለቀሰች ፤ ሁለመናዋም ይንቀጠቀጣል ። 'እሽሽሽ ፡ በቃ አታልቅሺ ፣ በየትኛውም ጊዜና ቦታ ካንቺ ጋር ነኝ ። ትቼሽ የትም አልሄድም ። ሁሉንም ችግሮችሽን ላላስወግድልሽ እችላለሁ ፤ ነገር ግን ብቻሽን እንድትጋፈጪው በፍፁም አላደርግም' አልኳትና ዕምባዋን ጠራርጌ ፡ ግንባሯን ፣ አይኗን ፣ ጉንጯንና አንገቷ ስር ስሜያት ተያይዘን ወደ ቤት ተመለስን ። ድሬዳዋ ዩኒቨርስቲ ዘንድሮ ባወጣው ህግ መሠረት የ #3 ቀን ቀሪ ከጊቢው ያሰናብታል ። የኔ ቀሪ ደግሞ ከዚያ እያለፈ ስለሆነ ትንሽ አሳስቦኝ እንጂ መጀመሪያውኑ የትምህርት ፍቅር ኖሮኝ አይደለም ወደ ጊቢ ለመመለስ የተነሳሁት ። ይሄው አሁን ትምህርቱ ላይ ፈርጄ የከንቲባው ልጅ ቤት ቀርቻለሁ ። ትውልድ ይዳን ፤ ትምህርት በኔ ይብቃ ። ሳስበው ግን ህይወት በዚሁ ሁኔታ ከቀጠለች ወደፊት ልጄን ትምህርት ቤት ወስጄ የማስተምረው አይመስለኝም ። ለነገሩ ልጄ እንደኔ ደደብ ፣ ደነዝ እና ሰነፍ የሚሆን አይመስለኝም ። በኔ ከወጣ ግን ውሃ በላው ። Campus ባይገባ ነው የሚሻለው ። ልግባ ቢል እራሱ ማን ሲያስገባው ...? ከኔጋር እየኖረ ትምህርቴን ማቄን ምናምን የሚል ከሆነ #18 ዓመት እስኪሞላው ደረስ አልጠብቅም ። ልክ ይቺን ጥያቄ ስያነሳ በሬን ከፍቼ ካለኝ ንብረት ላይ የድርሻውን ሰጥቼው አሰናብተዋለው ። (ንብረት ግን የሚኖረኝ አይመስለኝም ...🙆) ። የኔ ነገር ፡ ለራሴም ሳልሆን የልጄን ፈተፈትኩ አይደል ። (አንተ ልጅ ግን ልጅ አለህ እንዴ ...?😬) ። ምን ላርግ ፡ ከ #3 ወር በፊት የተፈተነው Applied Maths final ፈተና ትዝ ብሎኝ እኮ ነው ። On time #02:00 ሰዓት ሻርፕ (flat ...😜) ላይ class ተገኘሁና አሰላለፍ አሳምሬ አስተማሪውን ጠበቅነው ። ዛሬማ ካልደፈንኩት ከዚህ ክፍል ውስጥ ንቅንቅ አልልም ብዬ ቆረጥኩ ። በስተ ሰሜን ጎበዙ የዶርሜ ልጅ ፣ በስተ ደቡብ ከዋላዬ ስለሆነ አይመቸኝም ፣ በስተ ምስራቅ ከክፍል #1ኛ ውጤት ያለው ልጅ ፣ በስተ ምዕራብ ደግሞ ከዲፓርትመንታችን ከፍተኛ ውጤት ያመጣው ልጅ ተቀምጠዋል ። Morino እራሱ አሰላለፍ እንዲህ አይችልበትም ። የተከተልኩት የጨዋታ ስልትም ፡ ትንሽ ማንበብ + ብዙ መኮረጅ = #50/50 የሚለው ነው ። ኩረጃ ላይ ብዙም ልምድ የለኝም ። እንግዲህ የኔ ጉድ ዛሬ ይታያል ። (ጉድ = Good ...😬) ፈታኙም ፈተናውን ይዞ ከተፍ አለ ። (ምናለበት አሁን ቢቀር ይሞታል ...?🙆) ። ፈተናውን ጠረጼዛ ላይ አስቀመጠና እንዲህ አለን "Continous ከ #50 ሁላችሁም ከ #40 በላይ ስላመጣችሁ አይያዝም ። ስለዚህ የዛሬው ፈተና የሚያዘው ከ #100% ነው ። #90 ጥያቄ ተዘጋጅቷል ፣ ለእያንዳንዱ ጥያቄ #3 pharagraph ትፅፋላችሁ ። ሁሉም ጥያቄ የወጣው ከተማራችሁት ውጪ ሲሆን ፤ ጥያቄዎቹ እንኳን ለእናንተ ለኛም አዲስ ናቸው ። የቀረው #10% ነጥብ ደግሞ ስማችሁን በቻይንኛ መፃፍ ይሆናል ። አሁን ፈተናውን እንጀምራለን ልክ ጀምሩ እንዳልኳችሁ pencil down እላቹዋለው ታቆማላችሁ ። ፈተናው ላይ #1 ኤክስ (❌) የገባበት ተማሪ ከጊቢው ይሰናበታል ። መልካም ፈተና ። ነጮች "ስለ ሰው ይበልጥ ባወክ ቁጥር ውሻህን ትወደዋለህ" ይላሉ ። እኔ ግን እላቹዋለው 'ስለ Maths ይበልጥ ባወክ ቁጥር አለመማርን ትወዳለህ' ።... ከከንቲባው ልጅ ጋር ቲቪ ከፍተን እያየን እያለ ስልኬ ላይ Msg ገባና አውጥቼ ሳየው... ከ 100 ላይክ ቡኋላ ክፍል 19 ይለቀቃል🌹             𝗝𝗼𝗶𝗻 𝘂𝘀 ╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗   ♥️♥️ተቀላቀሉን ♥️♥️ https://t.me/ethio_author https://t.me/ethio_author ╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝ ፈጣሪ ኢትዮጵያን ይጠብቅልን 🫶🇪🇹🇪🇹♥️❥❥__⚘_
Show all...
😘የከንቲባው ልጅ😘 🔥ክፍል 20 . . አዘጋጅ እና አቅራቢ=- ከደራሲያን አለም የቴሌግራም ቻናል ✍ . . ..ቤተሰብ ሼር ላይክ በደንብ አርጉ በፍጥነት እዲለቀቅ ♥️♥️♥️♥️ የማውቀውን አንድ ግጥም በዜማ እልላት ጀመር ። እንዲህ ብዬ ...🎤 አመሻሽ ላይ ሆኜ ፡ ሳስብሽ ሳስብሽ        በረንዳ ላይ ሆኜ ፡ አንቺኑ ስስልሽ        ስላንቺ የሚያወሳ ፡ ግጥም ስፅፍልሽ        ዕምባ ከአይኖቼ ፡ ዱብ ዱብ እያሉ        አይኔና ጉንጮቼ ፡ በዕንባ ሲሞሉ        ከሰማይ ላይ ሆና ፡ ትታዘበኛለች        እጇን በአፏ ጭና ፡ ታፈጥብኛለች        ደንገጥ አልኩኝና ፡ ዕምባዬን ጠረኩኝ        እሷም ቀስ በቀስ ፡ እኔን ቀረበችኝ       ብርሃኗ ልዩ ነው ፡ ሁሉን የሚያስረሳ       ፈዝዤ ቀረሁኝ ፡ ፎቶ እንደሚነሳ       እኔጋር ደረሰች ፡ ከዋክብት አጅቧት       መንቀጥቀጥ ጀመርኩኝ ፡ እኔም በፍርሃት       ጠጋ አለችና ፡ አይዞህ ጨረቃ ነኝ አለችኝ        አትፍራ አትሽሽ ፡ ብላ አቀፈችኝ        ኮከብ እንዳጀባት እየነገረችኝ        እንባዬን ጠራርጋ ፡ አይኖቼን እያየች         በሹክሹክታ መንፈስ ፡ ማውራት ጀመረች         አይዞህ ጠንከር በል ፡ ምንም አትሆንም         እውነት ካፈቀርቃት ፡ የትም አትሄድም        ለፍቅርክ ምስክር ፡ እሆንልሀለው        ካለችበት ሄጄ ፡ እነግርልሃለው        ያቺ ውብ ጨረቃ ፡ ቀርባ አፅናናችኝ        ለተከፋው ልቤ ደስታን ሰጠችኝ፣    "ጤዛ ሞቷን ሞታ ፡ ኮከብ ባናት ስትወጣ ፣      ድምፅ ወደኔ መጣ ፡ አለኝም ጠጣ   አንተ ድንቅ ፍጡር ጠጣ ፡ ወደኔ እስክትመጣ" ። የሚለውን ግጥም መረኩላትና ወይናችንን እየጠጣን የጨረቃን ውበት ማድነቅ ጀመርን ። አይኖቻችን ግን እሷ ላይ ለመቆየት ብዙም የፈለጉ አይመስለኝም ። ከኛ በብዙ ሺህ እጥፍ የምትርቅ ፣ ያውም የማናገኛት ጨረቃ ላይ ከማፍጠጥ ይልቅ የቅርባችን ይሻላል ብለን አይኖቻችን ውስጥ ያለውን ጨረቃ ለመፈለግ ይመስል እርስ በእርስ መፋጠጥ ጀመርን ። ብዙም ሳንቆይ ህይወት ወለላዋ ፣ ነክታኝ በስምያዋ ፣ ኑር ለዘላለም ስትል ፣ ከንፈሮቿ ነፍሴን ከአፋፍ ላይ አወጧት ፣ ባይኔ እያየሁ ወደ ጨረቃዋ አከነፏት ። መቼም የማልደርስባት ፣ ማገኛት ማይመስለኝ ፣ ያቺን እሩቅ ያለች ጨረቃ አፌን በአፏ ጎርሳ አሳየችኝ ። ከንፈሬ ከንፈሯን ፈልቅቆ ሲነካው ፣ ነፍሴ ከነፍሷ ጋር ጋብቻ የፈፀሙ ነው የሚመስለኝ ። ከንፈሯ ደግሞ ለስላሳ ነው ፤ ለዘለዓለም እንድትስመው ይገፋፋል ። መሞት ካለብኝ ልሙት ፤ ሞቴ ግን ከንፈርሽ ላይ ይሁን የሚያስብል ፣ ምሽቱ ነግቶ ፣ ወፎች እስኪንጫጩ ፣ ምድርም እስክትነቃ ድረስ ልቀቁኝ የማይል ከንፈር ። (ኧረ በህግ አምላክ ልቀቃት ...🙆) ። በስንት መከራ ከንፈራችን ተላቆ አይኖቻችን ማውራት ጀመሩ ። የከንቲባው ልጅ ከብዙ ዝምታ በዋላ "በህይወቴ አንድ የማይሰለቸኝን ነገር ልንገርህ...?" አለችኝና ቀጠለች "ካንተ ጋር #24 ሰዓት ማሳለፍ ፣ እንደውም ሰዓቱ በጣም አንሶኛል ፣ ሰዓቱም ልክ ቀናቱ #365 በሆነልኝ ። ቀናቱን ሁሉ ፣ ሳምንቱን ሙሉ ፣ ወራቱን እንዳለ ፣ ዓመታቱንም እንደዛው ካንተ ጋር በሆንኩ ። ካንተ ጋር ከሆንኩኝ ሁሉም ቀን ለኔ የፍቅር ቀናት ናቸው ። አንተኮ መውደድን የማነብብህ ደብተሬ ፣ ፍቅርን የማይብህ መስታወቴ ፣ ያለ ስጋት የምኖርብህ ሀገሬ ፣ በእስትንፋስህ የምተነፍስ ንፁህ አየሬ ነክ ። ባንተ ፍቅር እንደ ጤፍ ሺህ ቦታ ብትንትን ብልም ባንተው ፍቅር ደግሞ ይኸው እየኖርኩ ነው ። በህይወቴ ውስጥ አንተን ስላገኘሁ በጣም ደስተኛ ነኝ ። በምታደርገውና በምትለኝ ነገሮች የተለየሁ እንደሆንኩ ያክል እንዲሰማኝ ታደርጋለህ ። እናም በጣም ነው የምወድህ ፤ ሁሌም ደግሞ አደርገዋለው" ብላኝ አይኖቿን ጨፍና ከንፈሬን ድጋሜ ስትስመኝ ከውጪ በሩ ተንኳኳ ። ደንግጠን ከንፈራችን ተላቆ አይኖቻችን በሩ ላይ አረፈ ። የልብ ምታችንም ከሚንኳኳው በር በላይ ይሰማናል ። እኔ ምናልባት አቧቷ ከሆኑ ብዬ ለጥንቃቄ ወይኑንና ብርጭቆዎቹን ይዤ ወደ ቤት ውስጥ ገባሁና ኩሽና አስቀምጬ ወደ ሳሎን ተመልሼ በመስኮት የሚሆነው ነገር መከታተል ጀመርኩኝ ። የከንቲባው ልጅ ደግሞ ፈራ ተባ እያለች "ማነው ...?" ብላ ወደ በሩ አቀናች ። ከዚህ በፊት አባቷ ሲመጡ ለምልክት አስቀድመው ይደውሉ እንደ ነበር ነግራኛለች ። ታድያ ከውጪ በር ላይ ቆሞ እያንኳኳ ያለው ሰው ማነው ...? ። ህይወት ላይ ጥቃት ሊፈፅም የመጣ ሰው ከሆነ ግን እንዴት እንደሆነ ባላውቅም ሰውዬው በእጄ ሰበብ መሆኑ ነው ። (ኡ ኡ ቴ ፡ አልቀረብህም...🙆) ። አቧቷ ከሆኑ እሰየው ፡ ግን የት ነው የምደብቀው ...? ። ከውጪ ምን እንደሚል ባይሰማኝም የሷ ድምፅ ግን ይሰማል ። ብዙም ሳይቆይ በሩ ተከፈተ ። አይኔ ፣ ልቤ ፣ መላ ሰውነቴ በሩ ላይ ፈዘዋል.. ወደ ውስጥ አንድ ሰው ገባና በሩን ዘግቶ ከህይወት ጋር ጥምጥም ብለው ተቃቀፉ ። አባቷ ናቸው አልኩኝ በልቤ ። ደንግጬ ወዴት እንደ ምሄድ ግራ ገብቶኝ ወደዚያ ወደዚህ ስል አንዴ ከግድግዳ ጋር ተላተምኩና ግንባሬን እያሻሸው ወደ ከንቲባው ልጅ ክፍል ገባሁ ። ለማየትና ለመስማት እንዲያመቸኝ የክፍሉን በር ሙሉ በሙሉ አልዘጋሁም ። መብራት ግን አጥፍቻለሁ ። አባትና ልጅ ተያይዘው ወደ ውስጥ ገቡ ። ደስ የሚለው አባቷ ላለሁበት ክፍል ጀርባቸውን ሰጥተው ነው የተቀመጡት ። ህይወት ደግሞ በኔ ፊትለፊት ሶፋው ላይ ቁጭ ብላ ከፀሀይ በላይ ፈክታ በናፍቆት ወደ አባቷ እያየች ታወራለች ። "አባቢ ደና ነህ አይደል ፡ እኔኮ ተጨንቄ ስልክህ ላይ ከጠዋት ጀምሮ ስሞክር ነበር ፤ ግን አይሰራም" አለቻቸው ። አባቷም "የኔ ህይወት አመሻሹ ላይ ነው እኮ አዲስ አበባ የገባሁት ፤ እረፍት ሳልወስድ ነው በዛው በድሬ plane ወደዚህ የመጣሁት" አሏት ። "ደክሞሀል አይደል በሙቅ ውሃ እግርህን ልጠብልክ ...?" ስትላቸው "አይ ፡ ባይሆን ሻዎር ልውሰድና ብዙ የማወራሽ ነገር አለኝ" ብሏት ተነስቶ ግንባሯን ሳሟትና እኔ ወዳለሁበት ቦታ አመሩ ደንግጬ ከበሩ ጀርባ ተደበኩኝ ። ካለሁበት አጠገብ በቀኝ በኩል ያለው ክፍል ሲከፈት ይሰማኛል ። ባለፈው ለመጀመሪያ ጊዜ እዚህ ቤት ስመጣ የከንቲባው ልጅ "አባቴ ሲመጣ እዚህ ነው የሚያድረው" ያለችኝ ክፍል ነበር ። ከትንሽ ደቂቃ በዋላ ተመልሶ ተዘጋና ወደኔ እየቀረበ የሚመጣ የእግር ኮቴ እየሰማው አልፎኝ ሄደና በግራዬ በኩል ያለው ክፍል ተከፍቶ ወዲያው ተዘጋ ። በሆዴ 'አባቷ ሻዎር ገቡ ማለት ነው' ብዬ ሳልጨርስ በድጋሜ ወደኔ የሚመጣ የሰው ኮቴ ሰማሁ ። በቅስፈት ያለሁበት ክፍል መብራት ሲበራብኝ ባለሁበት ደርቄ ቀረሁ... ከ 100 ላይክ ቡኋላ ክፍል 21 ይለቀቃል ♥️♥️♥️♥️👍👍👍👍 ቶሎ ቶሎ እንዲለቀቅ አንብባችሁ ስጨርሱ ላይክ ለወዳጆ ሼር ያርጉ ♥️🫶 #ከደራሲያን አለም #የቴሌግራም_ቻናል Join በማለት ራሶን በጣፋጭ ትረካዎች ዘና ያርጉ ..♥️
Show all...
♥️የከንቲባው ልጅ♥️ 🥀ክፍል 17🥀 . . ሞትን ባልፈራም ፡ በዚህ ሰዓት ግን መሞት አልፈልግም ። ቁጥሩ ይብዛም ይነስም ወደፊት መኖር እፈልጋለሁ ፤ ግን ዛሬ መሞት አልፈልግም ፡ ነገም እንደዛው ። ከዚህ በፊት ብዙ ጊዜ ከሞት አምልጫለሁ ። (ደግሞ በሩጫ አይደለም.😜) ። እናቴ እንደ ነገረችኝ ከሆነ ለመጀመሪያ ጊዜ ሞትን የተጋፈጥኩት ልጅ እያለሁ ነፍስ ሳላውቅ በሁለት ዓመቴ ነበር ። ታሪኩም እንዲህ ነው "የጠዋት ፀሀይ ለልጆች ጥሩ እንደሆነ የትኛውም ዶክተር ሳይነግራቸዉ እናቶች በራሳቸው ጥበብ ስለሚያውቁት ፡ እናቴም ጠዋት ከአልጋ ላይ አንስታኝ ግቢ ውስጥ ወደሚበራው የማለዳ ብርሃን አውጥታኝ እሷ ደግሞ እቤት ውስጥ ምሳ እየሰራች ነበር ። ቆሜም ፣ በዳዴም መሄድ አልጀመርኩም ። እንደዛ ለመሄድ ብዙ ዓመት እንደ ፈጀብኝ እናቴ ነግራኛለች ። እናቴ ምሳ እየሰራች ፡ በመሀል ደግሞ ደህንነቴን ለማረጋገጥ እየወጣች ታየኛለች ። አይኔ ተከድኗል ፣ ተኝቼ እንደሆነ ለማረጋገጥ ጠጋ ብላ በጆሮዋ ትንፋሼን ለመስማት ስትሞክር ምንም አይነት የመተንፈስ ነገር አልነበረም ። ልብ ምቴንም ስታዳምጠው ቆሟል ። ይሄኔ ነበር እናቴ ብቻዋን ማንም በሌለበት ሰፈር እምቧዋን ወደላይ መርጨት የጀመረችው ። የደም እምባ አለቀሰች ። እንዴት አሳይተኸኝ ትነሳኛለህ ብላ የፈጣሪ ልብስ ይመስል የመሬቱን ሳር ጭምድድ አርጋ ይዛ አነባች ። ምነው እመቤቴ ፡ የልጅን ፍቅር ካንቺ በላይ የሚያውቅ የለ ፤ ልጄን እኮ ባንቺ ቤት ክርስትና ማስነሳቴ በፍቅርሽ እንድታኖሪልኝ ነበር ፤ ምነው ታድያ ሳልጠግበው ነጠቅሽኝ እያለች አምርራ አለቀሰች ። በዚህ መሀል ግን እናቴ ከሷ ለቅሶ በተጨማሪ የሌላ ሰው የለቅሶ ድምፅ ሰምታ ዝም አለች ። ወደኔ ስታይ እኔ ነበርኩ የማለቅሰዉ ። ያቺ ቀን ለኔ ለደቂቃዎች ምድርን ለቅቄ ሰማይን ነክቼ ፡ ፈጣሪ ከእናቱ ጋር የእናቴን እምባ አይቶላት ድጋሜ ወደ ምድር የመለሰኝ እለት ነበረች" ። ተወልጄ ለሁለት ተከታታይ ዓመታት በጣም እታመም ነበር ። እንደውም ሀኪም ቤት በየቀኑ ከመመላለሴ የተነሳ ቂጤ በመርፌ ብዛት ወንፊት ይመስል ነበር አሉ ። በሽታው በግልፅ ባይታወቅም ፡ ለማስታገሻ ተብሎ ሁሌም መርፌ እወጋ ነበር ። በዚያ ምክንያት እንደውም ነጭ ልብስ የለበሰ ሰው ካየሁ ዶክተር ስለሚመስለኝ ኡ ኡ ታውን እንደ ምለቅ እናቴ ነግራኛለች ። ያን ቀን ግን ሞቼ ከተነሳሁ በዋላ እስካሁኗ ሰዓት ድረስ አሞኝ ሀኪም ቤት ስሄድ ትዝ አይለኝም ። ያቺ እለት ለኔ ከሞት ወደ ህይወት ብቻ ሳይሆን ከህመም ወደ ሙሉ ጤንነት የተመለስኩባትም ናት ። ለ #2ኛ ጊዜ ደግሞ ከሞት አፋፍ ላይ የተመለስኩት ከ #5 ዓመት በፊት የጥምቀት በዓል ላይ ነበር ። በዓሉን ለማክበር ከጎረቤት ልጅ ቤቲ ጋር ተያይዘን ወደ ጥምቀተ ባህሩ ወረድን ። ቤቲ ለትምህርት እንዲያመቻት ወላጆቿ ጋር ሳይሆን ለት/ቤቱ ቅርብ በነበሩ ዘመዶቿ (ጎረቤታችን) ጋር ነው የምትኖረው ። በወቅቱ ደግሞ እሷ ኢዶ የሚባል ፍቅረኛ ነበራት ። ምክንያቱን ባላውቅም ወላጅ አባቷ ደግሞ ይሄን ነገር ሰምቶ ልጁን ሊገድለው ይፈልግ ነበር ። ሆኖም ግን የልጁን መልክ ለይቶ ስለማያውቅ የጥምቀት ቀን እኔንና ቤቲን አንድላይ አይቶን ኢዶ መስዬው ሽጉጡን አወጣና ሊገድለኝ ወደኛ አመራ ። ይሄኔ ነበር የቤቲ አሳዳጊ ጎረቤታችን ኡኡኡ እያለች እግሩ ስር ወድቃ "እሱ አይደለም ፣ ይሄ የአበቡ ልጅ ነው ፣ ይሄ የጎረቤት ልጅ ነው" ብላው ከሞት ያስጣለችኝ ። "ሰዎች መሞት አይፈልጉም ነገር ግን ፣ መንግሥተ ሰማይ መግባት ይፈልጋሉ ። ንሰሐ አይገቡም ግን ሁሉንም የሰፈር ዕድር ገብተዋል"። ሲመስለኝ አሁን ሞት ለ #3ተኛ ጊዜ ነገር እየፈለገኝ ነው ። የከንቲባው ልጅ ከመፍራቷ የተነሳ ጥቅልል ብላ ደረቴ ውስጥ ሽጉጥ ብላለች ። ("ሞት ርስት ነው ፤ መፈራቱስ ለምንድነው.?") ። የጠረጠርነው ሰውዬ ይመጣ ይሆን እያልን በጉጉት (ይቅርታ በፍርሃት 😬) እየጠበቅን ነው ። እስካሁን ግን ምንም ነገር ሳናይና ሳንሰማ ቀኑ ወደ ምሽት ተለወጠ ። ሁሉም ነገር ፀጥ ረጭ ብሏል ። እኛም ድምፃችንን ብቻ ሳይሆን ትንፋሻችንን ጭምር አጥፍተን ኩርምት ብለን ተቀምጠናል ። በድንገት ሳናስበው በራችን ሲንኳኳ ሁለታችንም ከአልጋው ላይ ተስፈንጥረን ተነሳን ። ቀስ ብዬ ወደ በሩ አመራሁና 'ማ ማ ማነው?' አልኩኝ በተንቀጠቀጠ ድምፅ ። "እኔ ነኝ" አለ ድምፁ አዲስ ያልሆነብኝ ሰው ። 'አንተ ማነህ ፡ ስም የለህም' አልኩት ፈራ ተባ እያልኩ ። "እኔ ነኝ የናንተን የዕንግድነት ቆይታና መስተንግዶ የምከታተል" አለን በትህትና ። ሁለታችንም በሀይል ኡፍፍፍ አለንና በሩን ከፈትኩለት ። "ዛሬ ምነው ድምፃቹ ጠፋ ፡ ምሳ ላይም አልነበራቹም ፡ እራቱንም ልትዘልቁበት አስባቿል እንዴ ?" አለን በተለመደው ትህትናና ፈገግታ ። የእጅ ሰዓቴን ሳይ #01:33 ይላል ። እራት እዚው እንዲያ መጣልን ነግሬው እጅ ነስቶ ተመለሰ ። ብዙም ሳይቆይ ምግብ ከወይን ጋር ይዞ መጣ ። የምግብ ፍላጎት ባይኖረንም ነገ መንገደኛ በመሆናችን እንደ ነገሩ አድርገን ከላይ ትንሽ ወይን ከለስንበት ። በስተ መጨረሻም የእስካሁኑን ሙሉ ወጪ አስደምረን ከፍለንና አመስግነን ከአስተናጋጁ ጋር ተለያየን ። ለነገ ጠዋት #12:00 ሰዓት Alarm ሞልተን አንሶላ ውስጥ ገባን ። "ሞት ወደ ትጉህ ነፍስ ፣ እርጅናም ደግሞ ወደ አፍቃሪ ልብ አትመጣም" በሚለው ቃል እራሳችንን አሳምነን ተኛን ። ጠዋት ነግቶ Alarm እኛን ሳይሆን እኛ አላርሙን ቀስቅሰነው ከውቢቷ ደብረ ዘይት ከተማ ወደ በረሃዋ ንግስት ድሬዳዋ ጉዞ ጀመርን ። አዲስ አበባ ፣ አዳማ ፣ አዋሽ ፣ መታሃራ እያለን ሂርና ደረስን ። ወርደን ምሳችንን ዕሮብ በመሆኑ ቆንጆ በየ አይነት በልተን ጉዞ ቀጠልን ። ከዋላችን ከተለመዱት የጭነትና የህዝብ ማመላለሻ አውቶብሶችና ሚኒባሶች ውጪ የተለየ አይነት መኪና ስላላየን ውስጣችን ለጊዜው ሰላም ተሰምቶታል ። ሙቀቱንና የመንገዱን አሰልቺነት ተቋቁመን ፣ የደንገጎን አስፈሪ ተራራማ zigzag ቁልቁለት መንገድ ወርደን #11:00 ሰዓት አካባቢ ድሬዳዋ ገባን ። ለጥንቃቄ ብለን ቀስ ስላለች እንጂ የሸገር ድሬ መንገድ ለትክክለኛው ሾፌር ከ #9 ሰዓት አያልፍም ። Tata የሚባሉት አውቶብሶች ግን በጣም ደካማ ስለሆኑ ጠዋት #12:00 ሰዓት ከሸገር ተነስተው ምሽት #03:00 ሰዓት ድሬ የሚገቡበት ሰዓት ይበዛል ። ለጊዜው ድሬዳዋ ራስ ሆቴል አርፈን እራት እዛው በልተን ትንሽ አምሽተን ወደ ከንቲባው ልጅ ቤት በከዚራ በኩል አድርገን አቀናን ። የቀድሞ ቤቷና የአባቷ መኖርያ ቤት አካባቢ ስንደርስ መኪናውን አቆመችና ለትንሽ ደቂቃ ትኩር ብላ በቁጭት አየችው ። እምባዋ ጉንጮቿ ላይ ሳይራመዱ ታፋዋ ላይ ዱብ ዱብ ማለት ሲጀምሩ ፤ አይኗን ከቤቱ ላይ ነቀለችና እምባዋን ዋጥ አድርጋ መኪናውን አስነስታ ወደ ራሷ ፣ ከአባቷ ውጪ አንድም ሰው ወደ ማያውቀውና ዝር ወደማይልበት ቤት አመራን ከምሽቱ #02:00 ሰዓት አልፏል ። የከንቲባው ልጅ ቤት ደርሰን የውጪኛውን በር ከፍተን ገብተን ፣ መኪናዋንም ጊቢ ውስጥ አቁማ ወደ ውስጥ ገባን ። የሳሎንና መኝታ ክፍሏ መብራቶች በርተው ነበር የጠበቁን ። ትዝ ይለኛል ስንወጣ አጥፍተን ነበር ። ህይወት ዞር ብላ በፍርሃት ታየኝ ጀመር.. ከ 100 ላይክ ቡኋላ ክፍል 18 ይለቀቃል🌹            𝗝𝗼𝗶𝗻 𝘂𝘀 ╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗ ♥️♥️ተቀላቀሉን ♥️♥️ @ethio_author ╚═❖•🌺🌸•❖═╝ ፈጣሪ ኢትዮጵያን ይጠብቅልን 🫶🇪🇹🇪🇹♥️❥❥__⚘_
Show all...
♥️የከንቲባው ልጅ♥️ 🥀ክፍል 15🥀 . . Notice :- እውነተኛ ታሪክ ነው! . . ━━━━━━━✦✗✦━━━━━━━ አዘጋጅ እና አቅራቢ=-ከደራሲያን አለም የቴሌግራም ቻናል . . ቀጥላም "ቆይ ግን አንተ ሴት ልጅን መተህ አታውቅም ...?" አለችኝና ብዙ ዓመት ወደዋላ እንድመለስ አረገችኝ ። 'ትዝ ይለኛል እንደ ትናንት ፡ ከ #10 ዓመት በፊት በ #2001 ዓ.ም #4ኛ ክፍል እያለሁ ነበር ። #6ኛውን period ተምረን ተደወለ ። ምሳ ሰዓት በመሆኑ ፣ እቤታችንም ለት/ቤቱ ቅርብ ስለነበረ ወደ ቤት ለመግባት ቦርሳዬን ይዤ ከ desk ላይ ተነሳሁ ። ነገር ግን አጠገቤ ትቀመጥ የነበረችው አቢጊያ የምትባል የክፍላችን ቆንጅዬዋና ጎበዟ ልጅ ለምን እንደሆነ ዛሬም ድረስ መልስ ባላገኝም ፤ መሄድ እስኪሳነኝ ድረስ ቦርሳዬን ይዛ ትጎትታለች ። በሰዓቱ በጣም እርቦኝ ስለነበር ፣ በዛላይም ልጅነትም ስላለብኝ ለምን እንደ ምትጎትት ከመጠየቅ ይልቅ ቦርሳዬን በግድ ለማስለቀቅ ከፊቷ ጋር አላትሜው ወደ ቤት ገሰገስኩኝ ። ምሳዬን በልቼ ለከሰዓቱ ትምህርት ወደ ት/ቤት ተመልሼ ወደ ክፍሌ ስገባ የገጠመኝ ግን ያልጠበኩት ነገር ነበር ። የምቀመጥበት desk አጠገብ መሬት ላይ ፈሶ የደረቀ ደም ይታያል ። desk ላይ ደግሞ አልቅሳ ጉንጮቿ ላይ የደረቀ እምባ ውበቷን የሸፈነና የአፍንጫዋ ቀዳዳ ውስጥ ሶፍት የሰገሰገች ሴት ተቀምጣለች ። አቢጊያ ነበረች ። ለካስ እኔ እንደ ቀልድ ቦርሳዬን ለማስለቀቅ ያደረኩት ነገር ከባድ ነበር ። እኔ ስመታት ዞር ብዬ እንኳን ለአፍታ ሳላያት ነው የሮጥኩት ። ያን ቀን ነበር እራሴን የጠላሁት ፣ ያን ቀን ነበር እጄን የሰበሰብኩት ። ከዛን ቀን ጀምሮ ሴት ልጅን እንኳን ልመታት ይቅርና የሚመታት ሰው ባገኝ ባልመታላትም እንኳ ብያንስ አብሬያት አለቅሳለሁ ። ለነገሩ ከዛን ቀን በፊትም ሴት ልጅን መትቻት አላውቅም ። የዛን ቀንም ሳላውቅ እንጂ አቅጄበት አልነበረም' አልኳትና አይኔ የሆነ ሰውዬ ላይ አረፈ ። ሰላሜን የነሳ ሰው ነው ። በሄድንበት ቦታ ሁሉ አንድ ጥቁር ሙሉ ልብስ እስከነ ኮፍያ የሚለብሰው ይህ ሰውዬ ከአቅራብያችን አይጠፋም ነበር ። ሁሌም ደግሞ በኔ ፊትለፊት ከልጅቷ ደግሞ በስተጀርባ ነው የሚቀመጠው ። ለመጀመሪያ ጊዜ ያየሁት ኩሪፍቱ ሪዞርት መጀመሪያ ቀን የመጣን ጊዜ እራት ስንበላ ነበር ። ከዛን በዋላም በሄድንበት ሁሉ አብሮን ነው ። ከኛ በትንሽ ርቀት ላይ ሆኖ ይቀመጣል ። መጀመሪያ ዝምብሎ ለመዝናናት የመጣ ሰው መስሎኝ ነበር ። አሁን ግን ሲደጋገም ሀሳብ ውስጥ ገባሁ ። ደግሞ እንዳትጨነቅ ብዬ እስካሁን ለሷ አልነገርኳትም ። ጭንቅላቴ ውስጥ የሚመላለሰው ብቸኛው ጥያቄ 'ይሄ ሰው ማንም ይሁን ማን ፡ እኛን ከሆነ የሚከታተለው ፡ ከኛ ምንድነው የሚፈልገው ...?' የሚለው ነው ። ሳላስበው ለካ ሰውየው ላይ እያፈጠጥኩ ነበር ። ይሄን ያወኩት የከንቲባው ልጅ አይኔ ወደ ሚያይበት አቅጣጫ ዙራ ያየሁትን ሰውዬ አይታ ስትደነግጥ ነበር ። እንደዚህ ስትደነግጥ አይቻት አላውቅም ። ድንጋጤዋ ይበልጥ ፍርሀቴን ጨመረው ። ሴኮንድ ሳታባክን ነበር እጄን ይዛኝ ወደ መኪናችን በፍጥነት እያጣደፈችኝ የወሰደችኝ ። ሁለመናዋ ይንቀጠቀጣል ፤ በጣም እንደ ፈራች ያስታውቅባታል ። እንደ ምንም አረጋጋዋትና የምታውቀው ነገር ካለ ጠየኳት ። "እየውልህ የኔ ጌታ ፡ እኔኮ ምንም ነገር ልደብቅህ ፈልጌ አይደለም ። ግን በቃ ያቺን ቀንና ያን እለት የተፈጠረውን ነገር ማስታወስ ስለማልፈልግ ነው" አለችኝ ዕምባ እየቀደማት.... "ከአራት ዓመት በፊት #9ኛ ክፍል እንደጀመርኩ ነበር ። የከዚራ ልጅ ብሆንም Elementery እያለን በጣም የምወደውና የምቀርበው ብቸኛው ልጅ አቤል የሳቢያን ሰፈር ልጅ ስለነበር አንድላይ ለመሆን ሳብያን high school ተመዘገብኩኝ ። ከእለታት በአንዱ ቀን በትምህርት ቤታችን ጊቢ ውስጥ crazy day የሚባለውን የፈረንጆች የዕብደት ቀን ለማክበርና ለየት ብሎ የሚመጣ ሰውም እንደ ሚሸለም ጭምር ከተማሪዎች ጋር ወስነን የሚከበርበት ቀን ደረሰ ። አብዛኛው ተማሪ የተቀዳደደ ልብስ ለብሰው እንደ ሚመጡ ግልፅ ነውና እኛ ግን ከነሱ ለየት ብለን ለመቅረብ የግድ አዲስ ፈጠራ መጠቀም ነበረብን ። በደምብ አስበንበትና ተዘጋጅተንበት ሁለታችንም የዕብደቱን ቀን ለማክበር ተያይዘን ወደ ሳቢያን ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት አቀናን ። እንዳሰብነውም አብዛኞቹ የተቀዳደደና የቆሸሸ ልብስ ለብሰው ፣ ፊታቸውን ደግሞ ከሰል ተቀብተው ነበር የመጡት ። ትኩረት መሳብ የቻልነው ግን እኛ ነበርን ። ያን ዕለት እኔን አይቶ ይቺማ ሴት ናት የሚል ፤ ልክ እንደኔው አቤልንም አይተው ወንድ መሆኑን የሚያውቅ ከሁለታችን በስተቀር አንድም አልነበረም ። ከፆታችን ውጪ ሁሉንም ነገር ተቀያይረናል ። እሱ የኔን ቀሚስ ፣ ጡት ማስያዣ ፣ ሹራብ ፣ ሂል/ታኮ ጫማ ፣ human hair ጭምር ገዝተን አድርጎ ፣ ሁሌም ከኔላይ የማጠፋዋን pink ሻርፕ በአንገቱ ዙሪያ ጠምጥሞ ፣ ቦርሳዬንም በጀርባው ተሸክሞ ፣ ከንፈሩንም Lip stick ተቀብቶ ምን የመሰለች ቆንጆ ኮረዳ መስሏል ። እኔ ደግሞ የሱን ሰፊ ጂንስ ሱሪ ፣ ሸሚዝ ፣ Adidas ጫማ ፣ ፀጉሬ እንዳይታይ ደግሞ ከላይ በሱ ኮፊያ ሸፍኜ ፣ እሱ ፂም ባይኖረውም ጉንጮቼ ላይ ፀጉር ለጣጥፌ ምን የመሠለ ሸበላ ወንድ ሆኛለሁ ። ለኛ ዕብደት ልብስ መቅደድ ፣ የቆሸሸ መልበስ ፣ ፊትን በቀለም ማጥቆር ሳይሆን ፈጣሪ ወንድ አድርጎ ፈጥሮት እንደ ሴት የሚሆን ፤ ሄዋን አድርጎ ፈጥሯት እንደ ወንድ የሚያረጋት ፣ ባጠቃላይ ወንድና ሴት ቦታቸውን ተቀያይረው ተፈጥሮን ሲቃወሙ ማየት ነው ዕብደት ። ይህ ነገር ደግሞ ከነጮቹ ከነ ሰልባጃቸው ወደ ሀገራችን እየገባና እየተስፋፋ ያለው ጉዳይ ነው ። ወንዱ ሴት ይመስል ከንፈሩን ደም የጠጣች ድመት አስመስሎ ፣ ፀጉሩን አሳድጎ እንደ ጭላዳ ዝንጀሮ ነስንሶ ፣ ከሰውነቱ ጋር የተጣበቀ ሱሪ ለብሶ ፣ ጆሮውን ተበስቶ ፤ ሴቷም ፀጉሯን ተቆርጣ ፣ ሱሪ ለብሳ ፣ ጡንቻ እያሳየች የወንድ አካሄድ እየሄደች ማየት ቀስ በቀስ በሀገራችን እየተለመደ መቷል ። አላማችንም ይህን ነገር መፀየፍና መከላከል ስለነበር ይህ አይነቱ ድርጊት ዕብደት መሆኑን ማሳወቅ እንጂ ፆታ ተቀያየሩ የሚል አልነበረም ። በዚህም ሁሉም ተስማምተውበት ሽልማቱን ወስደን ዝግጅቱም አለቀ ። ከት/ቤት ጊቢ ወተን አቤል ሊሸኘኝ ወደኛ ሰፈር አቀናን ። በሰዓቱ በጣም ጠምቶኝ ስለነበር እዚው ጠብቀኝ መጣው ብዬው በቀኝ በኩል ወደሚታየው ሱቅ ሄድኩኝ ። ባለሱቁን #2 ጁስ ስጠኝ ብዬው መቶ ብር ሰጠውት ። ወንድ መስዬው ስለነበር ድምፄን ሲሰማ ደንግጦ ነበር ። መልሱን እስኪፈልግ ድረሰ ዞር ብዬ አቤልን እያየሁት ፤ እሱም ወደኔ ዞሮ በአይኑ እየቃየኝ ነበር ። እውነት ለመናገር ከራስ ፀጉሩ እስከ እግር ጥፍሩ ድረስ እንዳለ የኔን ልብሶች ስለተጠቀመ ላየው ሰው እሱ አቤል ሳይሆን ህይወት ናት ። ባለሱቁ 'ይኸው የኔ ወንድም ይቅርታ እህት ለማለት ነው' ብሎኝ መልሱን ሲሰጠኝ ከዋላዬ የተኩስ ድምፅ ሰማሁ" ። "ስዞር ፡ አቤል እዚው ጠብቀኝ ባልኩበት ቦታ ላይ ተዘርሮ ወድቆ አየሁት ። ከ 100 ላይክ ቡኋላ ክፍል 16 ይለቀቃል🌹             𝗝𝗼𝗶𝗻 𝘂𝘀 ╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗   ♥️♥️ተቀላቀሉን ♥️♥️ https://t.me/ethio_author https://t.me/ethio_author ╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝ ፈጣሪ ኢትዮጵያን ይጠብቅልን 🫶🇪🇹🇪🇹♥️❥❥__⚘_❥
Show all...
♥️የከንቲባው ልጅ♥️ 🥀ክፍል 13🥀 . . Notice :- እውነተኛ ታሪክ ነው! . . ━━━━━━━✦✗✦━━━━━━━ አዘጋጅ እና አቅራቢ=-ከደራሲያን አለም የቴሌግራም ቻናል . . ከጠዋት እስከ ማታ ቀኑን ሙሉ በልቤ የልደቷን ቀን እያከበርኩ ፡ ድምፄን አጠፋሁ ። ሳልደውልላትና መልዕክት ሳልክላት ምሽቱ ወደ መገባደድ ደረሰ ።..ከምሽቱ #05 ሰአት አከባቢ ከማራኪዬ እንዲህ የሚል txt ግባልኝ ። "የልደቴን ቀን ብዙ የምወዳቸው ሰዎች አክብረውልኝ ደስ ብሎኝ ዋልኩኝ ። ነገር ግን ከሁሉም በላይ አስበልጬ ቦታ የሰጠሁት ልጅ ዝም ብሎ ዋለ ፤ ዝምም" ። እንዲህ ስትለኝ ምን ያክል ልቤን እንደ በላችው ፈጣሪ ያውቃል ። በጣም ነበር ያሳዘነችኝ ። ቢሆንም ግን ምንም አይነት መልስ ሳልሰጣት ያ ቀን አለፈ ። ከወር በዋላ ሁለተኛው የፈተና ቀን ደረሰ ፤ የልደቴ ቀን ። የሚገርምሽ ነገር ጠዋት #12:00 ላይ ነበር "እንኳን ተወለድክልኝ" የሚል መልዕክት መላክ የጀመረችው ። እስከ ማታ ድረስ እኔ ምንም ሳልመልስላት #14 txt ተስፋ ሳትቆርጥ ላከችልኝ ። መጨረሻ ላይ እንዲህ የሚል message ግባልኝ ። "ማራኪዬ ፡ ይኸው #15ኛ txt ላኩልህ ፡ አንተ ግን አንዱንም አልመለስክልኝም ፤ አላሳዝንህም ...?" አለችኝ ። በዚህ txt ልቤ ቢደማም እንደ ምንም ላለመመለስ እራሴን አስጨክኜ ያቺ ቀንም አለፈች ። ከዛም በዋላ በፈተናው ምክንያት txt ብዙም አላወራትም ነበር ። በዚህም ምክንያት ትምህርት እንደ ጨረሰች ክረምት ላይ ወደ ሙገር መጣች ። #3ኛው የፈተና ቀን ። ምን እንደ ተፈጠረ ጠየቀችኝ ። እኔ ግን እንኳን እሱን ልመልስላት ይቅርና በፈተናው መሠረት ጭራሽ ፊት ነሳዋት ። አይኗን እያየሁ መዋሸት ስለ ከበደኝ አንገቴን አቀርቅሬ እንደ ማልፈልጋት act አደረኩ ። ችላ አልኳት ፣ እንደ ድሮው አልስማትም ፣ አላጫውታትም ። ባጠቃላይ የቀደመውን ፍቅሬን ተውኩት ። ይሄን ሁሉ ሳደርግ ግን በውስጤ የደም እምባ እያነባሁ ነበር ። እሷንም ሳያት እንደዛው ነበረች ። ቃል አውጥታ ባትነግረኝም በኔ ልቧ ተሰብሯል ። ትንፋሿን ዋጥ አድርጋ ፡ ለኔ ስሜት ተጨንቃ ምንም እንዳልተጎዳች ታስመስል ነበር ። አብረን ባሳለፍናቸው ቀናት ምንም አይነት የፍቅር ስሜት አላሳየዋትም ነበር ። የመሄጃዋ ቀን ሲደርስ "ማራኪዬ ፡ አንተ ሁሉ ነገሬ ነህ ፤ እኔስ ላንተ ምንድነኝ ...?" የሚል ያላሰብኩትን ድንገተኛ ጥያቄ አቀረበችልኝ ። ሁለት ሀሳብ ውስጥ ገብቼ ነበር ። #1ኛው በፈተናው ህግ መሠረት 'ምኔም እንዳልሆነች act ማድረግ' ሲሆን #2ኛው ደግሞ እውነታውን 'ሁሉ ነገሬ እንደሆነች መናገር' የሚሉት ናቸው ። ፈተናውን ጀምሬ በስተ መጨረሻ ተስፋ መቁረጥ አልፈለኩም ። ከዛን ነበር አይኔን በጨው አጥቤ #3ኛውን ፈተና የተገበርኩት ። አፍ አውጥቼ ምኔም አይደለሽም አላልኳትም ። በዝምታ ብቻ ነበር የመለስኩላት ። ዝምታም መልስ ነው በሚለው ተረዳችኝና ምንም ሳትለኝ ከዱከም ይዛልኝ የመጣችውን ስጦታ ሰጥታኝ ወደ ሀገሯ ተመለሰች ። ስጦታውን እቤት እስክገባ አለማየት ስላላስቻለኝ መንገድ ላይ ነበር የከፈትኩት ። እንዲህ አይነት ስጦታ ከማንም ተሰቶኝ አያውቅም ነበር ። የኔን ስዕል በእንጨት ፍሬም ላይ በሰዓሊ አስላ ሰጠችኝ ። ስለኔ ወቅታዊ ፀባይ መቀየርም በደብዳቤ ፅፋልኝ ነበር ። anyways ከዛን ቀን በዋላ ማራኪዬን አይቻት አላውቅም ፣ ስልኬን አታነሳም ፣ txt አትመልስም ። ስልኳ እንደውም አብዛኛውን ጊዜ አይሰራም ነበር ። በጓደኞቼም ስልክ ስደውል አታነሳም ። 'በቅርብ ጊዜም ላወራት ፈልጌ ነበር ፤ እሷ ግን እኔ መሆኔን ስታውቅ መልስ አትሰጠኝም ። ባጠቃላይ ከኔጋር ስለምንም ነገር ለማውራት ፍቃደኛ አይደለችም ። ሲመስለኝ ረስታኛለች ፤ ወይም ደግሞ እኔን ለመርሳት እየሞከረች ይሆናል ። ለዚህ ሁሉ ምክንያት የሆነው ደግሞ ፈተናው ነበር ። እሷ ደግሞ እኔን ለማናገር ፍቃደኛ ባለመሆኗ ምክንያት ስለ ፈተናው እስካሁን ድረስ ምንም የምታውቀው ነገር የለም ። እንኳን ጊዜ ሰጥታኝ ሁሉንም ነገር ልትሰማኝ ይቅርና ከሰላምታ ውጪ ከኔጋር ምንም ነገር ማውራት አትፈልግም ። ባጠቃላይ ስለኔ ጉዳይ ከኔጋርም ይሁን ከሰዎች ጋር ማውራት እንደ ማትፈልግ ከሷም ከጓደኞቿም ሰምቻለሁ ። ከጓደኞቿ ጋርም ለማውራት ፈልጌ ነበር ፤ ግን ሁሉም እኔን ከመውቀስና ወንዶች ስትባሉ ግን ከማለት ውጪ የኔን እውነታ የሚሰማኝ አላገኘሁም ። በቃ ፈተናውን እንደ ቀላል ነገር አይቼው ፍቅሬን ተነጠኩኝ ። አጠገቧ ሆኜ እውነታውን ባላውቅም ይመስለኛል በኔ ተስፋ ቆርጣለች ወይንም ደግሞ ተስፋ መቁረጥ ትፈልጋለች ። በዚህ ሁሉ መሀል ግን ለአንድም ቀን ማራኪዬን ወቅሻት አላውቅም ። ምክንያቱም ጥፋቱ ሁሉ የኔ ስለነበር ። እሷ ከደሙ ንፁህ ናት ። ባይሆን ግን ትንሽም ቢሆን ቅር ያለኝ ነገር በቀላሉ በኔ ተስፋ መቁረጧ ነበር ። ለአንድም ቀን አስቤም ስለማላውቅ ይሄ ነገሩ አስከፍቶኛል ። እንዲህም ሆኖ ግን በጣም እንደ ጎዳዋት ይሰማኛል ። በኔ ክህደት የተፈፀመባት ስለሚመስላት አይኗ እስኪጠፋ ድረስ እንደ ምታለቅስ አውቃለሁ ። ልቧ ተሰብሮ ከሰዎች ተለይታ ለብዙ ቀናት ብቸኛ እንደ ምትሆን ይታየኛል ። እውነታውን ስታውቅ ግን ምን እንደ ምትለኝ አላውቅም ። "ይቅር" ብላኝ እንደ በፊቱ አብረን መሆን እንጀምር ይሁን ፤ ወይንም ደግሞ "ሁሉም አልፏል ፡ አንዴ ከልቤ አስወጥቼሀለው ፡ ከአሁን በዋላ እኛ የሚባል ነገር የለም" ትለኝ ይሁን አላውቅም ። እኔ እስካሁን ስለሷ ሳወራ በስሟ እንኳን ጠርቻት አላውቅም ። የእሷን ግን እንጃ ፤ እንኳን ማራኪዬ ብላ እኔን መጣራቷ ይቅርና ስለኔ ማሰቧም ጥያቄ ምልክት ውስጥ ነው' ። ከዚህ በላይ ለከንቲባው ልጅ ስለ ማራኪዬ የመተረክ አቅም አልነበረኝም ። 'በጣም ደክሞኛል' አልኳትና ወደ መኝታዬ አመራሁ ። በጣም ከፍቶኛል ፤ በዛላይ ሳልፈልግ እምባዬ እየፈሰሰ አስቸገረኝ ። ብዙም ሳልቆይ እንደ ተገረፈ ህፃን ድምፅ አውጥቼ ማልቀስ ጀመርኩኝ ። ይሄኔ ነበር የከንቲባው ልጅ በፍጥነት ከመኝታዋ ተነስታ አልጋዬ ላይ ወጥታ እቅፍ አድርጋኝ እያባበለችኝ ፣ ግንባሬን እየሳመችኝ ፣ ፀጉሬን ልጅ እያለሁ እናቴ እንደ ምታደርገው በጣቶቿ እየዳበሰችኝ ፣ "እሽሽሽ ..." የሚል ለስላሳ ድምጿን በጆሮዬ ተጠግታ እያሰማችኝ ዝም ያስባለችኝ ። ግን ዝምታዬ በዛው አልፀናም ነበር ። ተነስቼ ምንም የማታውቀው ልጅ ላይ ጮህኩኝ ፣ አለቃቀስኩባት ፣ ማራኪዬ እሷ የሆነች ይመስል 'ለምንድነው የማታዳምጠኝ ፣ ለምንስ ነው እውነታዬን የማትሰማው ...? ፡ እኔኮ ማንም ሰው እንዲያምነኝ አይደለም ፍላጎቴ ። በቃ እውነቱን ብቻ እንዲሰሙ ነው' እያልኳት በሀይል ተናገርኳት ። በሁኔታዬ ብትደናገጥም ለብቻዬ አልተወችኝም ፤ በተቃራኒው ተጠምጥማብኝ በማባበል "እኔ እሰማሀለው ፡ እኔ አምንሀለው የኔ ጌታ" እያለችኝ ከኔጋር ማልቀስ ጀመረች ። ከ 100 ላይክ ቡኋላ ክፍል 14 ይለቀቃል🌹             𝗝𝗼𝗶𝗻 𝘂𝘀 ╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗   ♥️♥️ተቀላቀሉን ♥️♥️ https://t.me/ethio_author https://t.me/ethio_author ╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝ ፈጣሪ ኢትዮጵያን ይጠብቅልን 🫶🇪🇹🇪🇹♥️❥❥__⚘_❥
Show all...
♥️የከንቲባው ልጅ♥️ 🥀ክፍል 10🥀 . . Notice :- እውነተኛ ታሪክ ነው! . . ━━━━━━━✦✗✦━━━━━━━ አዘጋጅ እና አቅራቢ=-ከደራሲያን አለም የቴሌግራም ቻናል . . . የሆነ ነገር ወዳልሆነ ነገር ሊመራክ ከሆነ ፡ ማድረግ ያለብህ ከሆነ ነገር መራቅ ነው ። አልጋ ልብሱን አልብሻት ወደ አልጋዬ ተመልሼ ተኛሁ ። ጠዋት ነግቶ ከእንቅልፋችን ስንነቃ ፡ #03 ሰዓት አልፎ ነበር ። እዛው ካለንበት ሆቴል ቆንጆ ቁርስ በልተን ፡ ያለብንን የ #1 ለሊት የቤት ኪራይ ከፍለን ወደ ቡቲክ አመራን ። ውቢቷ ቢሾፍቱ ላይ ፈክተን የምናበራበትን ልብስ ገዝተን #05:30 ላይ ጉዞአችንን ወደዛው አደረግን ። ለሸገር ቅርብ ስለሆነች ብዙም ደቂቃ አልፈጀብንም ። ኩሪፍቱ ሪዞርት ከበር ላይ በክብር ተቀበሉን ። የምንቆይበት ክፍል ይዘን ፈታ ለማለት ትጥቃችንን አሟልተን ወደ መዋኛ ገንዳ አመራን ። ዋና እንደማትችል ጠጋ ብላ በጆሮዬ ነገረችኝ ። እኔም ልክ እሷ እንደነገረችኝ ፈራ ተባ እያልኩ በጆሮዋ እንደማልችል ነገርኳት ። በድንጋጤ አየችኝና "እና ምን ልናደርግ ነው የመጣነው ...? ፡ እኔ ደግሞ ምትችል መስሎኝ አንተን ተስፋ ማድረጌ" አለችኝ አኩርፋ ። ከዛን ሳኩባትና 'ስቀልድ ነው ባክሽ ፡ ዶልፊን እራሱ ጉልበቴ ስር ቁጭ ብሎ ነው የተማረው' አልኳት ። (ዶልፊን ግን ቁጭ ማለት ይችላል እንዴ ...😝) ። "ሂድ ፡ ጉረኛ" አለችኝና ትከሻዬን በፍቅር መታችኝ ። እኔ ለክባድ ብዬ ተከርብቼ ውሃው ውስጥ ገባሁ ። እሷ ግን ውሃ ነክታ አታውቅም መሠለኝ በስንት ልመና በዳዴ ገባች ። ለመዋኘት ገብቼ አሰልጣኝ ሆኜ አረፍኩ ። ያን ያክል እንኳን አላስቸገረችኝም ። ነገሮችን በቀላሉ የመያዝ ልዩ ችሎታ አላት ። ዋና የለመድኩት እንዲህ ባማረ ገንዳ ሳይሆን እንደ አብዛኛው ኢትዮጵያዊ ወንዝ ውስጥ ነበር ። እየዋኘሁ ፣ እያለማመድኳት ፣ እያረፍን ፣ በድጋሜ ያሁኑን step እየደገምን ከአንድ ሰዓት በላይ ቆየን ። አይን አይኔን እያየች "አስቸገርኩህ አይደል ...? ፡ በቃ የመጨረሻ አንድ ዙር አለማምደኝና ይብቃን" አለችኝ ። ሁለቱ እጆቼን ውሃው ውስጥ እንደ ምንጣፍ ዘረጋሁላት ። በሆዷና ታፋዋ እጆቼ ላይ ተኝታ በእጆቿ ደግሞ ውሃውን ወደ ዋላዋ እየገፋች ወደ ፊት ትመነጠቃለች ። እኔም ከጎኗ ሆኜ እከተላታለሁ ። እንደዛ እያደረገን የገንዳው ጫፍ ላይ ደረስን ። ከእጆቼ ላይ ወርዳ እዛው ውሃው ውስጥ በኔ ፊትለፊት ቆመችና አይን ለአይን ተጋጨን ። ውበቷ እንዴት እንደ ሚያስደነግጥ ideaw የላቹም ። አላወቁም እንጂ ሴቶቻችን የሚያምሩት በሜካፕ ሳይሆን በተፈጥሮአቸው ነው ። በዋናው ውሃ ታጥባ ኩልል ብላ ቆማ ስታየኝ ፈዘዝኩኝ ። በጣም ተቀራርበናል ። እንደውም ንፋስ በመሃላችን ለማለፍ ፈልጎ ሲታገለን ይሰማኛል ። አይኖቼ ከንፈሯ ላይ ደርቀው ቀሩ ። እሷም እንደኔው በአይኖቿ ከንፈሬ አካባቢ እየሾፈችኝ ነው ። ወደ ከንፈሬ በጣም ቀረበች ። ከንፈሯ እንኳን እሁድ ተገኝቶ ፡ እሮብንና አርብን እራሱ ያስገድፋሉ ። የሁለታችንም ስሜት እናታችን ላይ ሲወጣ ተጎራረስን ። ከንፈሯ ከከንፈሬ ፣ ትንፋሿ ከትንፋሼ ተዳመረ ። የኔን ትንፋሽ ወስዳ የሷን ለገሰችኝ ። ትንፋሿ ይሞቃል ፤ ከንፈሯ ይጣፍጣል ። ለብዙ ሴኮንዶች ከንፈር ለከንፈር ተገጣጥመን ፡ የአለምን አየር ንቀን ውስጣችን ያለውን ተለጋግሰን ዋና ገንዳው ውስጥ ከቆየን በዋላ ከንፈራችን ተላቀቀ ፡ አይናችንም ተከፈተ ። ትንሽ እንደ መተፋፈር ሆነን ከውሃው ውስጥ ወጣን ። በርዷት ነው መሠለኝ መንሰፍሰፍ ጀመረች ። አሳዘነችኝና ፎጣ አልብሻት ተሸከምኳትና ወደ ክፍላችን ጉዞ ጀመርኩኝ ። እሷን መሸከም ለኔ ብርቄም ድንቄም አይደለም ። ሶፋ ላይ በተኛችና በሰከረች ቁጥር እስከ መኝታ ክፍሏ የማድረስ የሁለት ቀን ስራ ልምድ አለኝ ። የዛሬው ግን ለየት ይላል ። አልሰከረችም ፣ አልተኛችም ፣ እራሷን አልሳተችም ፣ አይኖቿ አልተከደኑም ፣ ወዘተ ። ክፍላችንን እንደምንም በአንድ እጄ ከፍቼ ገባንና መልሼ በእግሬ ዘግቼው አልጋው ላይ ቀስ ብዬ አስተኛዋት ። አይኗን ቁልጭ ቁልጭ እያደረገች ወደላይ በስስት ታየኛለች ። እኔም ወደታች እንደዛው ። አንዲት ቃል ሳናወጣ በአይኖቻችን ብቻ እናወራለን ። ከዛን እጆቿን አንገቴ ላይ ጠምጥማ ወደራሷ ጎተተችኝና ድጋሜ ከንፈሮቻችን ህብረት ፈጠሩ ። ፎጣውን ከላዩዋ ላይ ወርውራ አልጋው ላይ ጣለችኝ ። ሁለታችንም ከዋና ገንዳው እንደ ወጣን ፡ እኔ ከላይ ራቁቴን ፡ ከስር ደግሞ በዋናው ቁምጣ ፤ እሷ ደግሞ ከላይ ጡት ማስያዣና ከስር በዋናው ፓንት ነው ያለነው ። ቅድም ከውሃው ስንወጣ በርዷት እንደዛ እንዳል ተንዘፈዘፈች ፡ አሁን ላይ ግን ገላዋ በሙሉ እንደ እሳት እየፈጀኝ ይገኛል ። አንገቷ ስር ገብቼ ስስማት ፡ አይኖቿን ጨፍና ፣ ትንፋሿን ዋጥ አድርጋ ፣ መልሳ ደግሞ በሀይል ትተነፍሳለች ። (አንገቷ ስር ከገባህ ፡ አይኗን ስትጨፍን እንዴት አየህ ...😝) ። ዛሬም እንደ በፊቱ 'ሴትና ወንድ ብቻቸውን ይሆኑ ዘንድ መልካም አይደለም' አልኩ ለራሴ ። ምን እያደረግን ነው ...? ፡ እዚህ ድረስ ለምን መጣን ...? ፡ ፈታ ማለት ምን ማለት ነው ...? ፡ አልኩኝ ለራሴ ። ከሀሳቤ ነቃሁ ፡ ከአንገቷ ምሽግ ወጣሁ ፡ ከአልጋዋ ላይ ተነሳሁ ፡ ወደ ራሴ አልጋ ሄድኩ ፡ ወደ ራሴም ተመለስኩ ። እሷም ግራ በመጋባትና በመናደድ አይነት ስሜት ከተኛችበት ቀና ብላ ታየኛለች ። የሆነ ነገር ልትለኝ ስትል በራችን ተንኳኳ ። እኔ እከፍታለሁ አልኳትና ከላይ ሸሚዝ ለብሼ ከፈትኩኝ ። አስተናጋጅ ነበር እና "የምትፈልጉት ነገር ካለ ማዘዝ ይቻላል" አለኝ በክብር እጅ እየነሳኝ ። እኔም 'ትንሽ ርቦናልና ምግብ ብናገኝ ደስ ይለናል' አልኩት ። እሱም "ከፈለጋችሁ እዚህ ፡ ፍቃዳችሁ ከሆነም ደስ የሚል ቦታ እወስዳችሁና እዛ ትበላላችሁ" አለኝ ። 'አይ ፡ ላሁኑ እዚህ እንበላለን ፤ ባይሆን ደስ የሚለውን ቦታ ማታ ትወስደናለህ' አልኩትና ሄደ ። #08 ሰዓት አልፏል ። አኩርፋኝ ቢሆንም አስተናጋጁ ያመጣልንን ምግብ እንደ ተለመደው ለራሷ ሳትበላ መጀመሪያ አጎረሰችኝ ። እኔም አጎረስኳትና ትንሽ በልተን ተውነው ። ከበላን በዋላም ሁለታችንም በአንድ ቤት ውስጥ ሆነን ሳናወራ ጀምበር እየታዘበችን ወደ ቤቷ ገባች ። ላወራት ብዬ ስነሳ በራችን ድጋሜ ተንኳኳ ። ስከፍት የቅድሙ አስተናጋጅ ነበርና ቅድም ወዳለኝ ቦታ ሊወስደን እንደ መጣ ነገረኝ ። #10 ደቂቃ ስጠን ብዬው ፡ ተመልሼ ፈራ ተባ እያልኩ ልጅቷን ቀሰቀስኳት ። 'ተነሽና ልብስሽን ቀይሪ ፡ ወደ ሆነ ቦታ እንሄዳለን' አልኳት ። አልተቃወመችኝም ፡ ልትቀይር ወደ ውስጥ ገባች ። ከሸገር የገዛነውን ልብስ አውጥቼ ለበስኩትና እሷ እስክትጨርስ መጠበቅ ጀመርኩኝ ። በዛ ውበቷ ላይ ቅድም የገዛነውን ልብስ እሷ ላይ ስስለው ፡ በቃ ጨረቃ እራሷ በአካል መጥታ የምታገኘኝ መሠለኝ ። ልጅቷ ከገባችበት ቀይራ ወጣች ።      "ደምቀሽ ስትወጪ ፡ ደምቀሽ ስትወጪ ፣       ደምቀሽ ስትወጪ ፡ ጨረቃ አፈረች"። ከ 100 ላይክ ቡኋላ ክፍል 11 ይለቀቃል🌹 ━━━━━━✦✗✦━━━━━━ አዘጋጅ እና አቅራቢ=-ከደራሲያን አለም የቴሌግራም ቻናል             𝗝𝗼𝗶𝗻 𝘂𝘀 ╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗   ♥️♥️ተቀላቀሉን ♥️♥️ https://t.me/ethio_author https://t.me/ethio_author ╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝ ፈጣሪ ኢትዮጵያን ይጠብቅልን 🫶🇪🇹🇪🇹♥️❥❥__⚘_❥
Show all...
♥️የከንቲባው ልጅ♥️ 🥀ክፍል 12🥀 . . Notice :- እውነተኛ ታሪክ ነው! . . ━━━━━━━✦✗✦━━━━━━━ አዘጋጅ እና አቅራቢ=-ከደራሲያን አለም የቴሌግራም ቻናል . . ,በኛ ካምፕ ውስጥ ደግሞ አንድ ታሪኩ ብቻ ነበር ያለው ፤ እሱም ምርጥ ጓደኛዬ ነበር ። ከዛን ልጆች እሱን ጠቁመዋት አገኘችው ። ስታየው እኔ እንዳልሆንኩ አወቀች ። ታሪኩ ደግሞ ከኔጋር ሲገናኝ ስሟንና ከየት እንደመጣች እየጠቆመ የተፈጠረውን ነገረኝ ። ያኔ ነበር እኔን እየፈለገች እንደሆነ የተረዳሁት ። ቀኑን አላውቅም እንጂ እንደ ማገኛት አውቅ ነበር ። ከሁለት ዓመት በዋላ ያቺን ልጅ ድጋሜ አየዋት ። ቆንጅናዋ እንዳለ ነው ፤ ኧረ እንደውም ይበልጥ ተውባ ነበር ። ተገናኘን ፣ ተቃቀፍን ፣ ለብዙ ሰዓት ቁጭ ብለን አወራን ። ሲመሽብን ስልክ ቁጥር ተለዋውጠን ተለያየን ። ከዛን ቀን አንስቶ ወደ ዱከም እስክትመለስ ድረስ በየቀኑ እንገናኝ ነበር ። ሁለታችንም እንደ በፊቱ ዝምተኛ አልነበርንም ። ስለ ብዙ ነገር አወራን ፣ ተጫወትን ፣ ብዙ ቦታ አብረን ዞርን ። በቃ ባጠቃላይ ፊልም ላይ ወይንም ልቦለድ ላይ የምታውቂውን የፍቅር ህይወት አብረን አሳለፍን ። በህይወቴ ለመጀመሪያ ጊዜ የሷን ከንፈር ነበር የሳምኩት ። ወክቱ ክረምት ነበር ፤ የቴዲ አፍሮ "ኢትዮጵያ" አልበም ደግሞ በብዛት ይደመጥ ነበር ። ከሱ አልበም ውስጥ ሁለታችንም "ማራኪዬ" የሚለውን ዘፈን ከቴዲ አፍሮ በላይ ወደድነው ። ልምድ ሆኖብን ሁለታችንም ከዛን በዋላ #ማራኪዬ እያልን መጠራራት ጀመርን ። ማንም ወንድ ቢቀርባት በፍቅር የሚወድቅላት ልጅ ነበረች ። እኔም ወደኩላት ። በጣም ነበር የምንዋደደው ፤ ከምነግርሽ በላይ ። የሚገርምሽ ቀኑን ሙሉ አብረን ውለን ሰለ ማንጠጋገብ ማታ ማታ ደግሞ በስልክ txt እንፃፃፍ ነበር ። እንደውም የሆነ ቀን የተፃፃፍነውን የመልዕክት ብዛት ሳይ #5000 አልፎ ነበር ። እና ማራኪዬ ለኔ ሁሉ ነገሬ ነበረች ። የኔ አሳቢ ፣ የኔ እናት ፣ የኔ ፍቅር ፣ የኔ ረቡኒ ፣ በቃ ምን ልበልሽ ፡ እሷን ምድር ላይ ያሉ ቃላት አይገልጿትም ። በዚች ምድር ላይ እንደሷ የሚወደኝ ፤ እኔም እንደሷ የምወደው አልነበረኝም ። ፍቅርን ምድር ላይ ባሉት ነገሮች ግለፅልኝ ቢሉኝ #ማራኪዬን ነበር የምጠቁመው ። ያን ጊዜ እሷ የ #10ኛ ክፍል matric ፡ እኔ ደግሞ የ #12ኛ ክፍል entrance ፈተና ወስደን ውጤት የምንጠብቅበት ነበር ። ክረምቱን አብረን በፍቅር ዘመትን ። የመጣችሁ ክረምቱን ዘመድ ጋር ለማሳለፍ ነበርና ክረምቱ ሲገባደድ መሄጃዋ ደርሶ በእምባ ተለያየን ። ውጤት ተለቀቀ ፡ ሁለታችንም አለፍን ፡ ድሬዳዋ ዩኒቨርስቲ ደረሰኝ ። በስልክ ብቻ በየቀኑ txt እየተፃፃፍን ፡ በሳምንት እየተደዋወልን #8 ወር አለፈ ። ናፍቆታችን ገደቡን ሲያልፍ ቢሾፍቱ መጥቼ እንደማገኛት ቃል ገባሁላት ። በቃሌ መሠረትም ለፋሲካ በዓል ወደ ቤት ስመለስ አንድ ቀን ቀደም ብዬ ከድሬዳዋ ፡ ሸገር ፡ ከዛም ደብረ ዘይት እሷን ላገኛት ሄድኩኝ ። ለሶስተኛ ጊዜ ቢሾፍቱ የሄድኩት ያኔ ነበር ። #27-08-2010 ዓ.ም ። ተገናኘን ፣ በፍቅር ተቃቀፍን ። ስንተያይ እንዴት ደስ እንዳለን ideaw የለሽም ። የሆሳዕና ሳምንት ነበርና የሰራሁላትን የዘንባባ ቀለበት አደረኩላት ። ደብረ ዘይት ላይ አብረን ለ #3 ሰዓታት በፍቅር ሰከርን ። የመጀመሪያው ምሳችንን አብረን በላን ፣ ቢሾፍቱ ሀይቅ ሄደን juice እየጠጣን ተዝናናን ፣ photo ተነሳን ፣ ስለኛ ብዙ ነገር አወራን ፣ ተሳሳምን ፣ ተቃቀፍን ፣ ብቻ ያቺን ቀን በህይወቴ መቼም አልረሳትም ። ስጦታ የአንገት መስቀል አስራልኝ ልባችን እያለቀሰ ተለያየን ። እና አሁን አንገቴ ላይ የምታዪው ይህ መስቀል ማራኪዬ ያን ቀን ያደረገችልኝ ነው' አልኳትና በረጅሙ ተነፈስኩ ምንም ሳትለኝ አልጋው ውስጥ ገብታ ተኛች ። እኔም ከዛን በዋላ አልተናገርኳትም ። እንደ መሸ አልቀረም ፡ ነጋና በጠዋት ተነሳን ። ቁርስ ከበላን በዋላ "እና ደብረ ዘይትን አታስጎበኘኝም ?" አለችኝ ። 'እሺ' አልኳትና ባቦጋያ ፣ ምሳ ሰዓት ሆራ አርሰዴ ፣ ምሽት ላይ ደግሞ ቢሾፍቱ ሀይቅ ወስጃት ደስ የሚል ቀን አሳለፍን ። ትናንት ማታ በነገርኳት ታሪክ ምክንያት እንደ ከዚህ በፊቱ አትስመኝም ፣ አታቅፈኝም ፣ ሌላው ቢቀር ድንገት አይን ለአይን ስንጋጭ እራሱ አንገቷን ትደፋለች ። ወደ ኩሪፍቱ ተመልሰን እራት ከበላን በዋላ "ማታ ምንም ሳልልህ በመተኛቴ ይቅርታ ። ግን ታሪኩን እንድትጨርስልኝ እፈልጋለሁ" አለችኝ ። እኔም ካቆምኩበት ቀጠልኩላት ። 'እንዳልኩሽ ማራኪዬ ለኔ ሁሉ ነገሬ ነበረች ። ይሄን ደግሞ የፍቅር ታሪኬን ለሚጠይቀኝ ሁሉ አወራ ነበር ። የሆነ ቀን ግን ታሪኬን ከነገርኳቸው ሰዎች መሀል አንዱ "ስለሷ ስታወራ ከልክ በላይ እርግጠኛ የሆንክ ይመስለኛል ። ግን ተስፍሽ አንድ ነገር ልንገርህ ። ከራስህ ውጪ በማንም እርግጠኛ አትሁን ። ሁሉም ሰው አንተ እንደ ምታስባቸው ላይሆኑ ይችላሉ ። እንደዚህ የምልህ ክፉ ነገር አስቤ አይደለም ። ስለ ልጅቷ ከልክ በላይ የተማመንክባት ስለመሰለኝና አንድ ቀን እንዳትጎዳ ስለፈለኩኝ ነው" አለኝ ። በሱ አስተያየት ምንም አልተሸበርኩም ነበር ። እንደውም 'አንተ ማራኪዬን ስለማታውቃት ነው' አልኩት ። ከዛ በዋላ ነው እንግዲህ ጨዋታው የተጀመረው ። "ስማ ተስፍሽ ፡ እንደ ነገርከኝ ከሆነ ማራኪዬ የምትላት ልጅ ፡ አንተ ምንም ብትሆን ፣ የትም ብትሄድ ፣ ሌላው ይቅርና አንተ ብትተዋት እንኳን የማትተውክ ፣ እስከ እለተ ሞቷ ድረስ የምታፈቅርክ የተለየች ሴት ናት ። ይሄን ያክል ደግሞ በሷ እርግጠኛ ከሆንክ ለምን እኔ የምነግርህን ፈተና አታቀርብላትም ...?" አለኝና ፈተናው ምን እንደሆነ ጠየኩት ። ቀጠለና "ምን መሰለህ ፡ #3 ነገሮችን እንድታደርግ እፈልጋለሁ ። #1ኛው ፡ የልደት ቀኗ ሲደርስ ምንም አይነት txt እንዳትልክላት ፣ እንዳት ደውልላትም ። በዚህም ከሁሉ በላይ አንተን ስለ ምትጠብቅህ በጣም ታዝንብሀለች ። #2ኛው ፡ ያንተ የልደት ቀንም ሲደርስ ፡ ከሷ ለሚመጡልህ የመልካም ምኞት መግለጫ መልስ አትስጥ ። ይሄ ነገርም የንዴት መጠኗን ከፍ ያደርጋል ። #3ኛውና ወሳኙ ደግሞ ፡ ክረምት ክረምት እናንተ ጋር ሙገር እንደ ምትመጣ ነግረኸኛል ። እናም ባሁኑም ክረምት መምጣቷ ስለማይቀር ፡ ያኔ ስትገናኙ ፊት ንሳት ፣ እንደ ማትወዳት act አርግ ፣ ከሷ ጋር በመሆንህም ደስተኛ እንዳልሆንክ አስመስል ። አንተን ብላ መጥታ እንደዛ ስትሆንባት መቼም ምን እንደሚሰማት መገመት አይከብድም ። እውነት እልሀለሁ ተስፍሽ እነዚህን ሶስቱን ነገሮች ተግብረህ ፡ ማራኪክ 'እኔ አልተውህም ፣ እንደዚህ ብትሆንብኝም እወድሃለሁ' የምትልህ ከሆነ she is the best girl in the world" አለኝ ። ሶስቱን ፈተና ብሎ የነገረኝን ስሰማ መጀመሪያ ስቄበት ነበር ። እንደ ቀላል አይቼው ፣ እንደ ምታልፈውም በሙሉ ልቤ ስለተማመንኩኝ ልፈትናት ወሰንኩኝ ። ስለዚህ ጉዳይ ከኔና ከልጁ ውጪ ማንም ሰው አያውቀውም ። ደስ የሚለው ነገር የልደቷ ቀን ያኔ የነበርንበት ወር ውስጥ ነበር ። የመጀመሪያው የፈተና ቀን ደረሰ ፡ የልደቷ ቀን.. ከ 100 ላይክ ቡኋላ ክፍል 13 ይለቀቃል🌹             𝗝𝗼𝗶𝗻 𝘂𝘀 ╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗   ♥️♥️ተቀላቀሉን ♥️♥️ https://t.me/ethio_author https://t.me/ethio_author ╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝ ፈጣሪ ኢትዮጵያን ይጠብቅልን 🫶🇪🇹🇪🇹♥️❥❥__⚘_❥
Show all...
♥️የከንቲባው ልጅ♥️ 🥀ክፍል 16🥀 . . Notice :- እውነተኛ ታሪክ ነው! . . ━━━━━━━✦✗✦━━━━━━━ አዘጋጅ እና አቅራቢ=-ከደራሲያን አለም የቴሌግራም ቻናል . . መኪና ውስጥ ሆነው ነበር የተኮሱትና መኪናዋ ሳትቆም በዛው ሄዳ ተሰወረች ። በቃ በዛች ሰዓት የማስታውሰው ነገር ቢኖር ለአባቴ ደውዬ ያለንበትን ቦታ ነግሬው ፤ እስኪመጣ ድረስ ሰው ተሰብቦ እንዳይበዛ ባለሱቁን ለምኜው አቤልን ተሸክመን ወደ ቤቱ ውስጥ እንዳስገባን ነው ። አቤል በጣም ተዳክሞ ነበር ፤ ብዙ ደምም ከተተኮሰበት የዋላው ጭንቅላት ፈሶታል ። ሆስፒታል መውሰዱ አማራጭ አልነበረም ፤ መጀመሪያውኑ ወደሱ ሮጬ ስደርስ ህይወቱ አልፏል ። አባዬም በፍጥነት መጥቶ ሁለታችንንም ወሰደን ። ቦታው በከዚራ እና በሳቢያን መካከል ስለነበር ባለሱቁ ሁለታችንንም አያውቀንም ነበር ። ሳስበው አባቴ መጥቶ እስኪወስደን ድረስ ተጠምጥሜበት እያለቀስኩ ስለነበር ከአለባበሱ አንፃር አቤል ሴት እንደሆነ ነው የሚያምነው ። ከዛን አባቴ ምን እንዳደረገ ታውቃለህ ...? ገዳዮቹ ማንም ይሁኑ ማንም እኔን እንደገደሉ አድርገው ስለሚያምኑ በአቤል መቃብር ላይ የኔን ስም አፃፈበት ። ከኔና ከአባቴ ውጪ ስለዚህ ጉዳይ የሚያውቅ ሶስተኛ ሰው አንተ ብቻ ነህ ። አቤል ዘመድና ቤተሰብ አልነበረውም ። በቃ ብቻውን በራሱ ለራሱ ሰርቶ የሚማር ልጅ ነበር ። እኔ እሱን እሱም እኔን ብቻ ነው የሚቀርበው ። የዋህ ፣ ለሰው አሳቢ ፣ መልከ መልካም እና ጠንካራ ልጅ ነበር ። ልባቸውን አቆሽሸው ልብሳቸውን ከሚያሳምሩት ወገን አልነበረም ። ባለው አቅም ያለውን ፅድት ያለች ዩኒፎርም ከንፁህ ልቡ ጋር ያዋሀደ ምርጥ ልጅ እንጂ ። ለዛም ነበር እሱ የሚማርበት ት/ቤት የተመዘገብኩት ። አባቴ የኔን ምርጫ ስለሚያከብር ብቻ ሳያቅማማ ነበር እዛ ያስመዘገበኝ ። ምን ዋጋ አለው ፡ አሁን ላይ ስሙ እንጂ እሱ የለ ። ለኔ የታሰበውን አፈር እሱ ቀመሰልኝ ። እሱንና እናቴን ለይቼ እላያቸውም ። እናቴ ህይወት ልትሰጠኝ ህይወቷን አጣች ። አቤል ደግሞ ህይወቴን ሊያስቀጥል ህይወቱ ተቋረጠ ። ሁለቱም አስበውበትና አቅደውበት ባያድኑኝም ለዛሬው ህይወቴ ምክንያቶች ናቸው ። ከአቤል ቀብር በዋላ አባቴ እንኖርበት ከነበረው ከዚራ ከሚገኘው ቤት ሌላ አዲስ ቤት ገዛና በድብቅ እዛ አስቀመጠኝ ። ቤቱ ላይም ከላይ 'የሚከራይ' ብሎ ለጠፈበት ። ሰዎች ሊከራዩ ሲደውሉ ብዙ ብር ስለሚጠራባቸው ማንም አይከራየውም ። ከኔና ከአባቴ ውጪ እዛ ቤት ውስጥ እኔ እንዳለሁ የሚያውቅም አልነበረም ። በዛ ቤት ውስጥ ለ #4 ተከታታይ ዓመታት አብዛኛውን ጊዜ ብቻዬን ፤ ጥቂቱን ደግሞ ከአባቴ ጋር አሳለፍኩኝ ። አንተን እስካወኩበት እለት ድረስ ከቤት መውጣት ፣ መልበስ ፣ መብላት ፣ መጫወት ፣ ምንም ነገር አያምረኝም ነበር ። የሁሉም ቀናት ውሎዬ ተመሳሳይ ናቸው ። መተኛት ፣ ማንበብ ፣ ፊልም ማየት ፣ ትንሽ መብላት ፣ በጊታሬ መዝፈን ፣ ቅዳሜና እሁድ ደግሞ ከአባቴ ጋር መሆን ነው ። ይሄንንም ለማድረግ አንድ ዓመት ፈጅቶብኛል ። ከአቤል ሞት በዋላ ለአንድ ዓመት በአንድ መኝታ ቤት ውስጥ የሱ ደም የለበሰ አካል በህሊናዬ ውስጥ እየተመላለሰ እየወቀሰኝ ደንዝዤ አሳለፍኩኝ ። ከዛን በዋላ ነው ቀስ በቀስ ወደ ቀልቤ የተመለስኩት ። ከነዚህ ሁሉ ጊዜያት በዋላ አንተን ሳገኝ ለምን በአንዴ እንደ ተለወጥኩ ታውቃለህ ...?" አለችኝና ከቦርሳዋ ውስጥ የሆነ ፎቶ አውጥታ ሰጠችኝ ። ፎቶው ላይ ያለውን ልጅ ሳይ ለማመን ነበር የከበደኝ ። "አንተን የሚመስል ሰው አውቃለሁ ፣ አንተን የሚመስል ዘመድ አለኝ ፣ እኛ ሰፈር አንተን የሚመስል ልጅ አለ ፣ ወዘተ" ነገሮችን ብዙ ሰዎች ሲሉኝ 'ይሆናል እንግዲህ የፈጣሪ ጥበቡ ብዙ ነው' ከሚል መልስ ውጪ ብዙም ትኩረት አልሰጠዋቸውም ነበር ። science እንደ ሚለው በአለማችን ላይ ከ #4 በላይ በመልክ የሚመሳሰሉ ሰዎች አሉ ። እኔን የሚመስል ሰው እስካሁን ባካል ባይገጥመኝም ፡ ከብዙ ሰዎች ግን እሰማ ነበር ። በዚህ ዓመት ብቻ #4 ሰዎች በቁምነገር እንደዛ ብለውኛል ። አንዱ ልጅ እንደውም መንገድ ላይ አስቁሞኝ "ባህር ዳር አውቅሀለሁ እኮ እንዴት ነህ ...?" ብሎኛል ። እኔ ግን ባህርዳርን በስም እንጂ በአካል አላውቃትም ። ከሁሉ ነገር ግን ያስገረመኝ ፡ እኔን የሚመስሉ #4ቱ ሰዎች የተገኙት ኢትዮጵያ ውስጥ ነው ። ቆይ ግን እንዴት እኔን የሚመስል ሰው ህንድ ወይንም ደግሞ Spain ውስጥ አልተገኘም ...? ሌላው ቢቀር ቢጠፋ ቢጠፋ እኔን የሚመስል ሰው ቱርክና brazil ውስጥ ይጠፋል ...? science እኮ ያለው በአለማችን ላይ እንጂ በአንድ ሀገር ውስጥ ብቻ አላለም ። anyways ምናልባት የኔ ሌላ የቀረ high copy ሰው ካለ ግን ባልኳቸው ሀገራት ውስጥ ባይገኙም ፤ ኢትዮጵያ ውስጥ ስለበዛሁ ቻይና ወይ Nigeria ውስጥ ቢገኙ አይከፋኝም ። (ደግሞ ስቀልድ ነው ...😜) ። ሳሉት እስኪ እኔን የሚመስል ቻይናዊ ። (በናታችሁ አትሳሉት ...🙆) ። ከከንቲባው ልጅ ጋር ያንን ሰውዬ አይተን አጣድፋኝ መኪና ውስጥ ገብተን ወደ ኩሪፍቱ ማረፊያ ክፍላችን ገብተን አረጋግቻት ሁሉን ነገር ከነገረችኝ በዋላ በሰጠችኝ ፎቶግራፍ ላይ ፈዝዤ ቀርቻለሁ ። እኔን የሚመስል ልጅ በአካል አይቼ ባላውቅም ዛሬ ግን በፎቶ አየሁኝ ። ሰው እንዴት በተለያየ ቦታና ከተለያየ ሰው ተወልዶ እንዲህ ሊመሳሰል ይችላል ...? አልኩኝ ለራሴ ። እውነትም የፈጣሪ ጥበቡ ብዙ ነው ። የከንቲባው ልጅ አንዴ ፎቶውን ፡ አንዴ ደግሞ እኔን እያየች ማውራቷን ቀጠለች ። "ለመጀመሪያ ጊዜ በመኪናዬ ውስጥ ሆኜ ሳይክ አቤልን ያገኘሁ ፤ በቃ ፈጣሪ የኔን ዕምባ አይቶልኝ ወደ ምድር የመለሰው ነበር የመሠለኝ ። ወርጄ ተጠመጠምኩብህ ፣ ሳምኩህ ፣ እጅህን ያዝኩህ ፣ አይኖችህን ጎበኘሁ ፣ አለቀስኩብህ ፣ አስጨነኩህ ፣ አዝነህልኝ እቤት ድረስ ይዘኸኝ መጣህ ፣ አወራሁክ ፣ አብረን ተመገብን ፣ ሳታውቀኝ ሳላውቅህ እቤት አሳደርኩህ ፣ ሀሳቤን ጭንቀቴን ነገርኩክ ፣ ሰማኸኝ ፣ ትምህርቴን ብለክ ብቻዬን አልተውከኝም ፣ ከአባቴም በላይ ቀርበኸኝ ለኔ ደስታ ስትል እዚህ ድረስ አብረኸኝ መጣህ ። አየህ ካየውክ ሰዓት ጀምሮ እንደ አቤል ስለማይክ መጥፎ ነገሮችን ማሰብ አልፈለኩም ። አላውቀውም ፣ ይጎዳኛል ፣ እንዴት ልመነው የሚሉ ነገሮች ውስጥ አልገባውም ። በቃ እንዳየውክ አመንኩህ ። የሚፈጠረው ነገር ሁሉ ይፈጠር ብዬ እራሴን አሳመንኩኝ ። እምነቴ ገደል አልገባም ፤ ካሰብኩህና ከጠበኩህ በላይ ሆነኽልኛል ። ይሄን ሁሉ ደግሞ የደበኩህ ማስታወስ የማልፈልገው ታሪኬ ስለሆነ ነው ። አሁንም የነገርኩህ ልክ እኔን ለመግደል አስበው አቤልን እንደ ገደሉት አንተንም እንዳይ ነጥቁኝ ስለፈራሁ ነው እሺ የኔ ጌታ" አለችኝና አሁኑኑ መተው የሚገድሉን ይመስል ተጠምጥማብኝ "ከዚህ ቤት ውስጥ አኖጣም እሺ ...?" ትለኛለች ። ነገሩ ትንሽም ቢሆን ቢያስፈራም ለማፅናናት ብዬ 'አንቺን እንደገደሉ ነው የሚያውቁት ፣ በዛላይ ከቤት ወተሽም ስለማታውቂና እዚህም በለሊት ስለሆነ ከድሬ የመጣነው በምንም ተዐምር ስላንቺ ሊያውቁ አይችሉም አይዞሽ' አልኳትና ተረጋጋች ። ከ 100 ላይክ ቡኋላ ክፍል 17 ይለቀቃል🌹             𝗝𝗼𝗶𝗻 𝘂𝘀 ╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗   ♥️♥️ተቀላቀሉን ♥️♥️ https://t.me/ethio_author https://t.me/ethio_author ╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝ ፈጣሪ ኢትዮጵያን ይጠብቅልን 🫶🇪🇹🇪🇹♥️❥❥__⚘_
Show all...
♥️የከንቲባው ልጅ♥️ 🥀ክፍል 11🥀 . . Notice :- እውነተኛ ታሪክ ነው! . . ━━━━━━━✦✗✦━━━━━━━ አዘጋጅ እና አቅራቢ=-ከደራሲያን አለም የቴሌግራም ቻናል . . ይሄን የመሠለ ውበትማ ለትውልድ እንደ ቅርስ መተላለፍ አለበት ብዬ ስላሰብኩኝ አስተናጋጁን ፎቶ አንሳን ብዬው ተነሳን ። እኔ በሱፍ ነኝ ፤ እሷ ቬሎ ነገር ጣል ብታደርግ ኖሮ የሰርግ ፎቶ ነው የሚመስለው ። እጅ ለእጅ ተያይዘን አስተናጋጁ ወደ ሚወስደን ቦታ ደረስን ። በአበባ የተሽቆጠቆጠ መሬት ፣ እጅግ ውብ በሆኑ ምግብና ወይን የተሞላ ጠረጴዛ ፣ ለስለስ ብሎ ከተለቀቀ ሙዚቃ ጋር ተፋጠጥን ። የከንቲባው ልጅ ቅድም ተኮራርፈን ስትተኛ ከአስተናጋጁ ጋር በመተባበር ‍ ነበር እንዲህ ያስዋብነው ። ለቦታው ደግሞ ይበልጥ ውበት የሰጠው ፡ አጠገቡ ሀይቅ መኖሩ ነው ። አስተናጋጁ "መልካም ጊዜ ይሁንላችሁ ፡ የምትፈልጉት ነገር ካለ ይችን ደወል መጫን ብቻ ነው" ብሎን ጠረጴዛ ላይ ወዳለው ነገር ጠቁሞን ሄደ ። ጨረቃዋ ቁልቁል በቅናት እያየችን ደስ የሚል እራት በልተን ወይን እየጠጣን ነው ። "ጨረቃዋ አታምርም የኔ ጌታ ...?" አለችኝ ። ትኩር ብዬ አይኖቿን እያየሁ 'ካንቺ ባትበልጥም ቆንጅዬ ናት' አልኳት ። እንደተለመደው በፍቅር ትከሻዬን እየመታች "ሙት እሺ" ትለኛለች ። ለጨዋታው ድምቀት 'አንቺ እንዳታለቅሺ አስቤ እንጂ እኔኮ መሞት አላቃተኝም' ስላት ፡ ባንዴ ፊቷ ተቀያይሮ ብርሃን ይመስሉ የነበሩ አይኖቿ ወደ ደመናነት ተቀይረው በእንባ ተሞሉ ። 'አንቺ አመረርሽው እንዴ ፡ እኔኮ እየቀለድኩ ነው' ስላት ፡ "ካሁን በዋላ ግን ለቀልድም ይሁን አይሁን ፡ እሞታለሁ እንዳትለኝ እሺ ...?" አለችኝ እንባ እየተናነቃት ። አንጀቴን ስትበላኝ ቁጭ ብዬ ማየት ከበደኝ ። ከወንበሬ ላይ ተነሳሁና ተንበርክኬ 'እሺ በቃ አይለምደኝም' አልኳትና እንባዋን ጠራርጌ ከተቀመጠችበት እጇን ይዤ ተነሳን ። ወደ ጆሮዋ በአፌ ተጠግቼ በለሆሳስ 'ከኔጋር መደነስ አትፈልጊም...?' አልኳት ። "አሎድህም እሺ ...!" አለችኝና በፈገግታ ለዳንሱ እጇን ዘረጋችልኝ ። ያው የተከፈተው ሙዚቃ ለስለስ ያለ ስለሆነ የኛም ውዝዋዜ ጠንከር ያለ አይደለም ። ግራ እጄን እንደ እናቶቻችን መቀነት ወገቧ ላይ ጠምጥሜ ፣ የቀኝ እጄን ጣቶች የግራ እጇን ጣቶች ክፍተት ሞልቼበት ፣ እሷም ቀኝ እጇን ትከሻዬ ላይ አሳርፋ ፣ በእግሮቻችን አንዴ ወደፊት ፡ አንዴ ወደዋላ ፡ ሌላ ጊዜ ደግሞ ወደ ጎን እያልን በመሀል በመሀል ደግሞ እያወራን ደቂቃዎች ተቆጠሩ ። ከደሬቴ ላይ ተነስታ ቀና ብላ አይን አይኔን ታያለች ። እንዲህ ስታየኝ ደግሞ ልቤን ታቆመዋለች ፤ ምድር ላይ መኖሬን ታስረሳኛለች ። አይኖቿ ውስጥ እስከ ዳግም ምፅአት ድረስ የሚበቃ የብርሃን ሀይል ይታየኛል ። ወረድ ብዬ ከንፈሯን ሳይ ደግሞ የቴዲ አፍሮ ሙዚቃ ትዝ ይለኛል ።    "ሳማት ሳማት አለኝና ፡    ቀልቤን ገዛው እንደገና ፣    ሳሙኝ ፡ ሳሙኝ የሚል ከንፈር ፡    ድንገት አጉል አርጎኝ ነበር" ። ከዛ በዋላ ነው እንግዲህ ሳሙኝ ሳሙኝ የሚል ከንፈር ድንገት አጉል የሚያደርገኝ ። እነዚያ የህይወትን ነዳጅ የሚያመነጩ ከንፈሮቿን ስጎርስ እስከ እለተ ሞቴ ድረስ ምግብ ባልበላ እንኳ የሚያኖሩኝ ይመስሉኛል ። ስስማት አይኖቿን ጭፍን አርጋ ትቀልጥብኝ ነበር ። ከብዙ ደቂቃ ዝምታ በዋላ "ውጪው ይበርዳል አይደል የኔ ጌታ ፡ ወደ ውስጥ እንግባ ...?" አለችኝ ። እንዳለችውም ውጪው ያን ያክል ባይበርድም ፡ ሃሳቧን ላለመቃወም ብዬ እጅ ለእጅ ተያይዘን ወደ ክፍላችን አመራን ። ወደ ክፍላችን የሚወስደን ደረጃ ጋ ስንደርስ "እንደ ቅድሙ ተሸክመኸኝ አትገባም የኔ ጌታ" አለችኝ ። ልክ ሙሽሮች የሰርጋቸው ለት ማታ እንግዳውን "በሉ እናንተ ብሉ ፣ ጠጡ ፣ ጨፍሩ ፡ እኛ ልንተኛ ነው" ብለው ወደ መኝታቸው እንደ ሚሄዱ ፤ እኔም ልጅቷን እንደ ሙሽራ ተሸክሜያት ፡ እሷ ደግሞ በተዘረጉላት እጆቼ ላይ ፍልስስ ብላ ወደላይ እያየችኝ አልጋው ጋር ደረስን ። ዛሬ ፈርቻለሁ ፤ የፈሩት ደግሞ ይደርሳል ተብሎ ተፅፏል ። ከጠጣነው ወይን ይልቅ ትንፋሿ አሰከረኝ ። ከተቀባነው ሽቶ ይበልጥ የገላዋ መዐዛ ማረከኝ ። ልብሶቻችንን ማወላለቅ ጀመርን ። ኮቴ ፣ ሸሚዜ ፣ የሷም ልብስ እንደዛው ። እኔ ከላይ ፤ እሷ ከታች ። በዚህ መሀል ነበር የአንገት መስቀሌ ከአንገቴ ላይ በመሀላችን ሲንጠለጠል በድንጋጤ የተነሳሁት ። እንደ ቅድሙ ዝም አላለችኝም ። "የሆንከው ነገር ካለ ለምን አትነግረኝም ፡ እእእ ...?" አለችኝ በልመና አይነት ድምፅ ። አልጋዬ ላይ ቁጭ ብዬ ልነግራት ተዘጋጀሁ ። 'እየውልሽ ህይወት ፡ የፍቅር ታሪኬን አንድ ቀን እነግርሻለሁ ብዬሽ ነበር ። እና እሱን ዛሬ ብነግርሽ ነው የሚሻለው ብዬ ታሪኩን ጀመርኩላት ። #2007 ዓ.ም ክረምት ላይ አንዲት ቆንጅዬ ልጅ ከዱከም / ደብረ ዘይት ከተማ ዘመድ ጥየቃ ወደ ሙገር ትመጣለች ። ለመጀመሪያ ጊዜ ያየዋት በካምፓችን ውስጥ በሚገኘው ሆቴል ቁጭ ብላ መፅሐፍ ስታነብ ነበር ። ብዙ የሰፈራችን ልጆችም በስፍራው ላይ ነበሩ ። አዲስ ሴት በሰፈራችን ከታየች ደግሞ አብዛኛው ወንድ ይጋደልባታል ። እዛ የነበሩት ወንዶች ተራ በተራ ወደሷ እየሄዱ አፍረው ተመለሱ ። ልጅቷ መስሚያዋ ጥጥ ነበር ። እኔ ደግሞ በዚያን ጊዜ ሴት ልጅን እንኳን ቀርቤ ላናግራት ይቅርና አይኔን ብቻ ካዩኝ በፍርሃት እምባዬ ይመጣል ። ያቺን ቀን ያቺን ልጅ በቅርብ ርቀት ላይ ሆኜ በማየት ብቻ ቀኑ አለፈ ። ከዛን ቀን በዋላ ቤተ ክርስቲያን ሰንበት ተማሪ ነበርኩና ፕሮግራም አዘጋጅተን ነበር ። እና ያቺን ልጅ ድጋሜ እዛ አየዋት ። ያን ምሽት ተዋውቀን ከቤተ ክርስቲያን አብረን ወደ ቤት እየተመለስን እያለ መንገድ ላይ ዝናብ መጣብን ። ፀጉሯ ቱክስ ስለነበር እንዳይበላሽባት እንሩጥ አልኳት ። እሷ ግን "ዝናብ በጣም ስለምወድ እንደውም ቀስ ብለን እንሂድ" አለችኝ ። ሁሉም ሰው ከዝናቡ ሸሽቶ ወደቤት ገብቷል ። እኔና እሷ ብቻ በእግዚአብሔር ፀበል እየተጠመቅን በኩራት ዝናብ ውስጥ እየሄድን ፡ እሷ ስለምትወድ ብቻ ብርዱን እየጠጣሁ እስከ ዘመዷ ቤት አደረስኳት ። ብዙም አልተግባባንም ፤ ልጅቷ ብዙም አታወራም ነበር ። ግን በጣም ሳቂታ እንደ ነበረች አሁንም ድረስ ትዝ ይለኛል ። ብዙም ሳላውቃት መሄጃዋ እንደ ደረሰ ነገረችኝ ። የተገናኘነው ከሶስት ቀን አያልፍም ፤ እሱንም ለትንሽ ደቂቃ ፡ ያውም ብዙም ሳናወራ ። ስልክ ቁጥሬን የ #2008 የእንቁጣጣሽ ፖስት ካርድ ላይ ፅፌ ሰጥቻት ተሰነባበትን ። ከዛን ቀን በዋላ ያቺን ልጅ ሳላያት አንዱ ክረምት አልቆ ሌላኛው ተተካ ። ከሁለት ዓመት በዋላ #2009 ዓ.ም ክረምት ላይ ድጋሜ ወደ ሙገር መጣች ። ስለሷ ከስሟና ከመጣችበት ዘመድ ቤት ውጪ ምንም ነገር አላውቅም ነበር ። እሷ ደግሞ ከመጣች በዋላ ስሜ ጠፍቶባት ታሪኩ በሚል ስም እኔን ፍለጋ ጀመረች ።... ከ 100 ላይክ ቡኋላ ክፍል 12 ይለቀቃል🌹 ━━━━━━✦✗✦━━━━━━ አዘጋጅ እና አቅራቢ=-ከደራሲያን አለም የቴሌግራም ቻናል             𝗝𝗼𝗶𝗻 𝘂𝘀 ╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗   ♥️♥️ተቀላቀሉን ♥️♥️ https://t.me/ethio_author https://t.me/ethio_author ╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝ ፈጣሪ ኢትዮጵያን ይጠብቅልን 🫶🇪🇹🇪🇹♥️❥❥__⚘_❥
Show all...