cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

™Ethiopian News Network

Promote Goods and Service

Show more
Advertising posts
1 334Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

የ12ኛ ክፍል ፈተና ውጤት ይፋ ሆነ የ12ኛ ክፍል ፈተና ውጤት ይፋ መሆኑን የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አስታወቀ፡፡
Show all...
ሰኞ ጥር 15/2015 ዓ.ም የማለዳ ዐበይት ዜናዎች 1፤ መንግሥት አዲስ የገጠር መሬት ግብይት ሥርዓት በመንደፍ የጋራ መሬት ባለቤትነትን በሕግ ለመደንገግ ማቀዱን ሪፖርተር ገና ይፋ ካልሆነው ሁለተኛው የአገር በቀል ኢኮኖሚ ማሻሻያ ረቂቅ ሰነድ ላይ ተመልክቻለሁ በማለት ዘግቧል። መንግሥት የገጠር መሬት አስተዳደርና የመሬት አጠቃቀም አዋጁን በማሻሻል፣ አርሶ አደሮች የገጠር መሬትን በዋስትና በማስያዝ ብድር እንዲያገኙ የሚያስችል አሠራር ጭምር እንደሚፈቅድ በሰነዱ ላይ እንደተገለጠ ዘገባው ጠቅሷል። ዜና ምንጩ ጨምሮም፣ መንግሥት በማሻሻያው "የረጅም ጊዜ የመሬት ንብረት ባለቤትነትን" እና መሬትን የመሸጥና የመለወጥ መብትን ሊፈቅድ እንደሚችል አንድ የመንግሥት ባለሥልጣን ነግረውኛል ብሏል። 2፤ የሕወሃት ከፍተኛ አመራርና ቃል አቀባይ ጌታቸው ረዳ ሕወሃት አዲስ የክልል ካቢኔ አላዋቀረም ሲሉ ትናንት ምሽት በትዊተር ገጻቸው ባሠፈሩት መልዕክት አስታውቀዋል። በክልሉ አመራር ላይ የተደረገ አዲስ ሽግሽግ እንደሌለ የገለጡት ጌታቸው፣ የትግራይን ሕዝብ ደኅንነትና ሕልውና መሠረት ያደረገ ለውጥ እንደሚያስፈልግ ግን ስምምነት አለ ብለዋል። ጌታቸው ይህን ያሉት፣ ሰሞኑን ሕወሃት የከፍተኛ አመራሮች ለውጥ አድርጓል የሚሉ መረጃዎች መሰራጨታቸውን ተከትሎ ነው። 3፤ የአሜሪካው ውጭ ጉዳይ ሚንስትር አንቶኒ ብሊንከን በኢትዮጵያ መንግሥት እና በሕወሃት ዘላቂ የግጭት ማቆም ስምምነት አፈጻጸም እና በኤርትራ ወታደሮች ከሰሜን ኢትዮጵያ መውጣት ዙሪያ ከጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ ጋር በስልክ እንደተነጋገሩ መስሪያ ቤታቸው ባወጣው መግለጫ አስታውቋል። ብሊንከን፣ የተመድ ሰብዓዊ መብቶች መርማሪ ኮሚሽን የጦርነት ቀጠና ወደነበሩ አካባቢዎች እንዲገባ የኢትዮጵያ መንግሥት እንዲፈቅድ ዐቢይን መጠየቃቸውን መግለጫው ጠቅሷል። ብሊንከን እና ዐቢይ፣ በኦሮሚያ ክልል ባለው የጸጥታ ችግር ዙሪያ ጭምር ተወያይተዋል ተብሏል። 4፤ በርካታ ቁጥር ያላቸው የኤርትራ ወታደሮች ከሽሬ ከተማ መውጣታቸውን ከረድዔት ድርጅቶች ሰምቻለሁ ሲል ሮይተርስ ዘግቧል። ሆኖም የኤርትራ ወታደሮች ከሽሬ የወጡት፣ የቦታ ሽግሽግ ለማድረግ ወይም ጠቅልለው ከትግራይ ለመውጣት ስለመሆኑ ማረጋገጥ እንዳልቻለ ዘገባው ጠቅሷል። የረድዔት ሠራተኞች፣ በመቶዎች የሚቆጠሩ ተሽከርካሪዎችም ከተማዋን ለቀው ሲወጡ መመልከታቸውን እንደተናገሩ አመልክቷል። ዜና ምንጩ፣ በጉዳዩ ዙሪያ ለኤርትራ መንግሥት፣ ለሕወሃት እና ለኢትዮጵያ መንግሥት ቃል አቀባዮች ላቀረብኩት ጥያቄ ምላሽ እላገኘሁም ብሏል። 5፤ የአልሸባብ ታጣቂዎች ትናንት የሞቃዲሾ ከተማን ከንቲባ ቢሮ ጥሰው በመግባት በፈጸሙት ጥቃት አምስት ሲቪሎች እንደተገደሉ የሱማሊያ ዜና ምንጮች ዘግበዋል። የመንግሥት ወታደሮች ጥቃቱን ለማክሸፍ በወሰዱት ርምጃ፣ ስድስት የአልሸባብ ታጣቂዎችን ስለመግደላቸው መንግሥት መናገሩን ዘገባዎቹ አመልክተዋል። የአልሸባብ ታጣቂዎች ጥቃቱን በፈጸሙበት ወቅት፣ ከንቲባው ቢሯቸው እንዳልነበሩ ተገልጧል። [ዋዜማ]
Show all...
ለቸኮለ ማለዳ! ቅዳሜ ጥር 13/2015 ዓ.ም የዋዜማ ዐበይት ዜናዎች 1፤ የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር የድሬዳዋ ከተማን ዕጣ ፋንታ ለመወሰን ሕዝበ ውሳኔ እንዲካሄድ ለመንግሥት ሃሳብ አቅርቧል ተብሎ ሰሞኑን በመገናኛ ብዙኀን የተሰራጨውን መረጃ በኮምንኬሽን ቢሮው በኩል ባወጣው መግለጫ አስተባብሏል። መግለጫው፣ ለድሬዳዋ ዕጣ ፋንታ ሕዝበ ውሳኔ እንዲካሄድ አንድ የሕዝብ ተወካይ በቅርቡ በተካሄደው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትና ፌደሬሽን ምክር ቤት የጋራ ስብሰባ ላይ ጠየቁ እንጅ፣ አስተዳደሩ ተወያይቶ ውሳኔ ላይ የደረሰበት ወይም የደገፈው ጉዳይ አይደለም ብሏል። የከተማዋ አስተዳደር አሁናዊ ተቀዳሚ ትኩረቱ፣ የከተማዋን መተዳደሪያ ቻርተር አሻሽሎ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ማጸደቅ እንደሆነ መግለጫው ጠቅሷል። 2፤ የተመድ ቃል አቀባይ ተመድ ትግራይ ውስጥ መሬት ላይ ባለው መረጃ የኤርትራ ወታደሮች ከክልሉ እየወጡ ስለመሆኑ ማረጋገጫ መስጠት እችላለሁ በማለት ትናንት ተናግረዋል። ቃል አቀባዩ፣ ሆኖም ጉዳዩን ይበልጥ በማጣራት ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ጥረት እንደሚያደርጉ እና ጉዳዩን መከታተል እንደሚቀጥሉ ገልጸዋል። የድርጅቱ ቃል አቀባይ ይህን ያሉት፣ የኤርትራ ወታደሮች ከትግራይ እየወጡ ናቸው ተብሎ ስለሚሰራጨው መረጃ ተመድ የተረጋገጠ መረጃ ይኖረው እንደሆነ ትናንት ኒውዮርክ ውስጥ ከጋዜጠኞች ለቀረበላቸው ጥያቄ በሰጡት ምላሽ ነው። 3፤ የፍልሰተኞች አስመላሽ ብሄራዊ ኮሚቴ ትናንት በሦስት የአውሮፕላን በረራዎች 1 ሺህ 173 ኢትዮጵያዊያን ፍልሰተኞችን ከሳዑዲ ዓረቢያ ወደ አገራቸው መመለሱን የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚንስቴር ባሰራጨው መረጃ አስታውቋል። ከትናንቶቹ ተመላሽ ፍልሰተኞች መካከል፣ 12ቱ ታዳጊዎች እንደሆኑ ሚንስቴሩ ገልጧል። ብሄራዊ ኮሚቴው ከኅዳር 12 ጀምሮ ባስተባበራቸው የሁለተኛ ዙር የአውሮፕላን በረራዎች እስከ ትናንት ድረስ ወደ አገራቸው የተመለሱ ፍልሰተኞች ብዛት፣ 31 ሺህ 919 ደርሷል ተብሏል። 4፤ የሱማሊያ ጦር ሠራዊት ትናንት ከአልሸባብ ታጣቂዎች ጋር ባደረገው ውጊያ ከ100 በላይ የቡድኑን ታጣቂዎች ገድያለሁ ማለቱን የአገሪቱ ዜና ምንጮች ዘግበዋል። በውጊያው "ደናብ" የተባለው በአሜሪካ የሰለጠነው የሱማሊያ ልዩ ኮማንዶ ብርጌድ ምክትል አዛዥን ጨምሮ ሰባት ወታደሮች እንደተገደሉ ጦር ሠራዊቱ መናገሩን ዘገባዎቹ ጠቅሰዋል። የትናንቱ ውጊያ የተካሄደደው፣ የቡድኑ ታጣቂዎች በአንድ የመንግሥት ወታደሮች ጦር ሠፈር ላይ ጥቃት ባደረሱበት ወቅት ነው። አልሸባብ በበኩሉ፣ በውጊያው 150 የመንግሥት ወታደሮችን ገድያለሁ ማለቱ ተዘግቧል። 5፤ የኬንያ መንግሥት እስከ ቀጣዩ ዓመት ታኅሳስ ወር ድረስ ለመንግሥታዊው የኬንያ አየር መንገድ የሚሰጠውን ድጎማ ሙሉ በሙሉ ለማቆም መወሰኑን ቢዝነስ ደይሊ ዘግቧል። በተያዘው የፈረንጆች ዓመት ብቻ፣ መንግሥት ኪሳራ ላይ ላለው አየር መንገድ 300 ሚሊዮን ዶላር መደጎሙን ዘገባው ጠቅሷል። ከወራት በፊት ወደ ሥልጣን የመጡት ፕሬዝዳንት ሩቶ፣ የአሜሪካው ዴልታ አየር መንገድ የኬንያ መንግሥት በአየር መንገዱ ውስጥ ያለውን የ50 በመቶ ድርሻ በሙሉ እንዲገዛ በቅርቡ ለዴልታ አየር መንገድ ሃሳብ ማቅረባቸው ተዘግቧል። የስልክ አየር መንገድ ዋና አማካሪ የሆኑት የቀድሞው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ተወልደ ገ/ማርያም በዴልታ ውሳኔ ላይ ጉልህ ሚና ይኖራቸዋል በማለት የኬንያ ጋዜጦች በቅርቡ መዘገባቸው ይታወሳል። [ዋዜማ]
Show all...
ጥር 12/2015 ዓ.ም የምሽት ዐበይት ዜናዎች 1፤ ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ በቅርቡ ከግብርና ሚንስትርነታቸው በተሰናበቱት ኡመር ሁሴን ምትክ የሾሟቸውን የኦሮሚያ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር የሆኑትን ግርማ አመንቴን ሹመት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲያጸድቅላቸው ማቅረባቸውን ጽሕፈት ቤታቸው አስታውቋል። ዓለሙ ስሜ ደሞ በዳግማዊት ሞገስ ምትክ የትራንስፖርት ሚንስትር እንዲሆኑ ጠቅላይ ሚንስትሩ በዕጩነት አቅርበዋቸዋል። በተመሳሳይ፣ ዐቢይ፣ የፌደራል መንገዶች ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ሐብታሙ ተገኝን በታከለ ኡማ ምትክ የማዕድን ሚንስትር እንዲሆኑ በዕጩነት አቅርበዋል። 2፤ ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ ይናገር ደሴን ከብሄራዊ ባንክ ገዢነት በማንሳት በምትካቸው ማሞ ምኅረቱን የባንኩ ኀዢ አድርገው መሾማቸውን ጽሕፈት ቤታቸው አስታውቋል። አዲሱ ተሿሚ ማሞ እስከ ሹመታቸው ቀን ድረስ፣ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ዋና ሥራ አስፈጻሚና የጠቅላይ ሚንስትሩ ዋና አማካሪ ነበሩ። በተመሳሳይ፣ ዓለምጸሃይ ጳውሎስ የካቢኔ ጉዳዮች ሚንስትርና የጠቅላይ ሚንስትር ጽሕፈት ቤት ሃላፊ፣ ዲያቆን ዳንዔል ክብረት የጠቅላይ ሚንስትሩ የማኅበራዊ ዘርፍ አማካሪ ሚንስትር እንዲሁም በተመድ የኢትዮጵያ ቋሚ መልዕክተኛ የነበሩት አምባሳደር ታዬ አጽቀ ሥላሴ የጠቅላይ ሚንስትሩ የውጭ ፖሊሲ አማካሪ ሚንስትር ሆነው ተሹመዋል። መለሰ ዓለሙ ደሞ፣ በሚንስትር ማዕረግ የዲሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤት ሃላፊ ሆነው እንደተሾሙ ተገልጧል። 3፤ የኤርትራ ወታደሮች ከአድዋ እና አክሱም ከተሞች እየወጡ መሆኑን የሁለቱ ከተሞች ነዋሪዎች ነግረውኛል ሲል ቢቢሲ አማርኛ ዘግቧል። ነዋሪዎቹ ዛሬ ጣት፣ የኤርትራ ወታደሮችንና ወታደራዊ መሳሪያዎችን የጫኑ በርካታ አውቶብሶችና አይሱዙዎች ከሁለቱ ከተሞች ሲወጡ ስለማየታቸው መናገራቸውን ዘገባው ጠቅሷል። የዓይን ምስክሮቹ፣ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት በአድዋ ከተማ ዳርቻ ሠፍሮ ማየታቸውንም እንደገለጹ ዜና ምንጩ አመልክቷል። ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ሰዓት ድረስ፣ ፌደራል መንግሥቱ፣ ሕወሃት ወይም የኤርትራ መንግሥት በጉዳዩ ላይ ያሉት ነገር የለም። 4፤ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትራንስፖርት ቢሮ በቅርቡ የተደረገውን የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ ዋጋ ጭማሪ መሠረት በማድረግ በትራንስፖርት ታሪፍ ላይ ማሻሻያ ማድረጉን አስታውቋል። በታሪፍ ማሻሻያው መሠረት፣ ለሕዝብ ማመላለሻ ሚኒባሶች በኪሎ ሜትር እስከ 2.5 ርቀት 3 ብር ከ50 ሳንቲም የነበረው ታሪፍ፣ አሁን 4 ብር እንዲሆን እንደተወሰነ ቢሮው ገልጧል። በተመሳሳይ ከ2.6 እስከ 5 ኩሎ ሜትር ርቀት፣ የታሪፍ ክፍያው ከ6 ብር ከ 50 ሳንቲም ወደ 7 ብር ከፍ የተደረገ ሲሆን፣ ከ5.1 እስከ 7 ኪሎ ሜትር ርቀት በላይ ግን የታሪፍ ክፍያው አሁን ባለበት 10 ብር ይቀጥላል ተብሏል። 5፤ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትራንስፖርት ቢሮ በሕዝብ ማመላለሻ አውቶብስ ታሪፍ ላይ ከ50 ሳንቲም እስከ ሁለት ብር የሚደርስ ጭማሪ ማድረጉን ዛሬ በሰጠው መግለጫ ማስታወቁን የአገር ውስጥ ዜና ምንጮች ዘግበዋል። ላለፉት 5 ዓመታት 1 ብር ከ50 ሳንቲም የነበረው ዝቅተኛው ታሪፍ፣ ወደ ሦስት ብር እንዲሁም 3 ብር ከ50 ሳንቲም የነበረው ታሪፍ፣ ወደ 4 ብር ከፍ እንደተደረገ የዜና ምንጮች ዘግበዋል። ቢሮው ታሪፉን ያሻሻለው፣ አስተዳደራዊና የሥራ ማስኬጃ ወጪዎች በመጨመራቸው እንደሆነ ገልጧል ተብሏል። የ20 ብሩ ታሪፍ ደሞ፣ ወደ 25 ብር አሻቅቧል። 6፤ ቴሌሞባይል-ደቡብ ሱዳን የተሰኘው የቴሌኮም ኩባንያ ኢትዮጵያዊውን አንዷለም አድማሴን ዋና ሥራ አስፈጻሚው አድርጎ መሾሙን ውጭ ጉዳይ ሚንስቴር በማኅበራዊ ትስስር ገጹ ባሰራጨው መረጃ አስታውቋል። በደቡብ ሱዳን በትልቅነቱ አራተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል የተባለው የቴሌ ሞባይል-ደቡብ ሱዳን ኩባንያ ባለቤት ኢትዮጵያዊ አይሸሹም ተካ እንደሆኑ ሚንስቴሩ ገልጧል። አንዷለም አድማሴ ቀደም ሲል በኢትዮጽያ ቴሌኮምንኬሽን ኩባንያ ውስጥ በከፍተኛ አመራርነት የበርካታ ዓመታት ልምድ ያላቸው ናቸው። ኢትዮ ቴሌኮም፣ በደቡብ ሱዳን በቴሌኮም መሠረተ ልማት ዝርጋታ ዘርፍ ወይም በቴሌኮም አገልግሎት ሰጪነት ለመሠማራት ጥናት እያደረገ መሆኑን በቅርቡ መግለጡ ይታወሳል። 7፤ ንግድ ባንክ ዛሬ የአንድ ዶላር መግዣ ዋጋ 53 ብር ከ4257 ሳንቲም እና መሸጫ ዋጋው 54 ብር ከ4942 ሳንቲም ሆኖ እንደዋለ በድረገጹ ገልጧል። የአንድ የእንግሊዝ ፓውንድ መግዣ ዋጋ ደሞ 62 ብር ከ9963 ሳንቲም፣ መሸጫው 64 ብር ከ2562 ሳንቲም ሆኗል። በተመሳሳይ አንድ ዩሮ በ58 ብር ከ0150 ሳንቲም ተገዝቶ፣ በ59 ብር ከ1753 ሳንቲም ሲሸጥ ውሏል። አንድ የቻይና ዩዋን ደሞ በ7 ብር ከ1572 ሳንቲም ተገዝቶ፣ በ7 ብር ከ3003 ሳንቲም እንደተሸጠ ባንኩ ገልጧል። [ዋዜማ]
Show all...
ዓርብ ጥር 12/2015 ዓ.ም የማለዳ ዐበይት ዜናዎች 1፤ የገንዘብ ሚንስትር ደዔታ እዮብ ተካልኝ መንግሥት የብር ምንዛሬን ዝቅ ለማድረግ አቅዷል ተብሎ የተሰራጨው መረጃ "መሠረተ ቢስ ነው" ሲሉ በትዊተር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት አስተባብለዋል። እዮብ መንግሥት መሠረታዊ የፋይናንስ ማሻሻያ የማድረግ ፍላጎቱ እንደተጠበቀ መሆኑን ገልጸው፣ ሆኖም የመንግሥት የፋይናንስ ማሻሻያ የብር ምንዛሬ ግሽበት ስጋት ሊፈጥር አይገባውም ብለዋል። የትናንቱ የአሜሪካ ዶላር ምንዛሬ 53 ብር ከ42 ሳንቲም እንደሆነና፣ በትይዩ ገበያ ግን ወደ 99 ብር ማሻቀቡን የሮይተርስ ዘገባ ያመለክታል። 2፤ ኢሰመኮ መንግሥት ለሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት ተጎጅዎች እተገብረዋለሁ የሚለው የሽግግር ፍትህ "እውነተኛ፣ ተዓማኒና ግልጽነት የተሞላበት" እንዲሆን የበኩሉን ድጋፍ እንደሚያደርግ ሊቀመንበሩ ዳንኤል በቀለ እንደነገሩት ጠቅሶ ቢቢሲ አማርኛ ዘግቧል። ዳንኤል መንግሥት የሽግግር ፍትህን አማራጭ አድርጎ መምረጡን "ትክክለኛ ርምጃ" በማለት እንዳወደሱትና ኮሚሽኑም እያጠናው ያለውን የሽግግር ፍትህ አስተዳደር ሥርዓት በምክረ ሃሳብ መልክ ለመንግሥት እንደሚያቀርብ መግለጻቸውን ዘገባው ጠቅሷል። ዳንዔል ኢሰመኮ መንግሥትና ሕወሃት የግጭት ማቆም ስምምነት ላይ ከደረሱ ወዲህ ያለውን የሰብዓዊ መብት ሁኔታ ለመመርመር እየተዘጋጀ መሆኑንን መናገራቸውንም ዜና ምንጩ አመልክቷል። 3፤ መከላከያ ሠራዊት በትግራይ ክልል አዲግራት ከተማ ወደሚገኘው የቀድሞ ጦር ሠፈሩ መግባቱን የከተማዋ ከንቲባ ለዓከ ተስፋ መስቀል ነግረውኛል ሲል ቪኦኤ ዘግቧል። የከተማዋ ነዋሪዎችም የሠራዊቱ አባላት ወደ ካምፑ በሰልፍ ሲገቡ ተመልክተናል ማለታቸውን ዘገባው ጠቅሷል። ከንቲባው የኤርትራ ሠራዊት ከከተማዋ በቅርቡ ርቀት ላይ እንደሚገኝና ሁኔታው በኅብረተሰቡ ላይ ስጋት መደቀኑን ገልጸዋል ተብሏል። የአካባቢው ፖሊስና ሚሊሽያ መደበኛ ተግባራቸውን እያከናወኑ እንደሆነ ከንቲባው መናገራቸውን ዘገባው ጨምሮ አመልክቷል። 4፤ በኢትዮጵያ በጦርነት፣ በአየር ንብረት ለውጥና በኢኮኖሚ ቀውስ ሳቢያ 22 ሚሊዮን ዜጎች የዕለት ደራሽ ዕርዳታ ፈላጊ መሆናቸውን የመንግሥታቱ ድርጅትና ዓለማቀፍ የረድዔት ድርጅቶች ካወጡት ሰነድ ዋዜማ ተመልክታለች። 11.6 ሚሊዮኑ እርዳታ ፈላጊዎች ጽኑ የጠኔ አደጋ የገጠማቸውና አጅግ አስቸኳይ ሰብዓዊ ድጋፍ የሚፈልጉ እንደሆኑ መረጃው ያሳያል። የርሃብ አደጋ ካንዣበበባቸው እርዳታ ፈላጊዎች መካከል፣ 3.9 ሚሊዮን ያህሉ ሕጻናት ናቸው። ለእርዳታ ፈላጊዎቹ በጠቅላላው ከሚያስፈልገው 3.3 ቢሊዮን ዶላር ውስጥ፣ እስካሁን ማሰባሰብ የተቻለው ግን 47 በመቶውን ብቻ ነው። 5. የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ከተጀመረበት ቀን እስከ ህዳር30/2015 ከ17 ቢሊዮን ብር በላይ ድጋፍ ከህዝብ መሰብሰቡን ከታላቁ ህዳሴ ግድብ ማስተባበሪያ ፅ/ቤት ሰምተናል። ከዚህም ጋር ተያይዞ የህብረተሰቡን ድጋፍ ለማጠናከርና ለማስተባበር ያግዛል የተባለለት በአባይ ወንዝ መነሻ ላይ ያተኮረ የስዕል ሲንፓዚየም እና ወርክሾፕ ከሰሞኑ ይካሄዳል። ከጥር 17 እስከ ጥር 26/2015 በአዲስአበባ በሚካሄደው ስንፓዚየም ከ23  ሀገራት የተወጣጡ ሰዓሊያን እንደሚሳተፉ ዋዜማ ሰምታለች። 6፤ መንግሥት የአገር ውስጥ ተፈናቃዮችን የፍትህ፣ የፖለቲካና ኢኮኖሚ መብቶች የሚያስጠብቅ አዋጅና ፖሊሲ እንዳረቀቀ የኢትዮጵያን ሰብዓዊ መብቶች ድርጅቶች ኅብረት መናገሩን ዶይቸቨለ ዘግቧል። ኢትዮጵያ የተፈናቃዮችን መብቶች የሚደነግገውን ዓለማቀፍ ስምምነት ከሁለት ዓመት በፊት መፈረሟን ያስታወሰው ድርጅቱ፣ የተፈናቃዮች ፖሊሲና አዋጅ የሚዘጋጀው ዓለማቀፉን ስምምነት ተግባራዊ ለማድረግ እንደሆነ ገልጧል ተብሏል። በቅርቡ ለሕዝብ ውይይት ይቀርባል ተብሎ የሚጠበቀው ረቂቅ አዋጅ፣ ለተፈናቃዮች ካሳ ለመክፈልና አፈናቃዮችን በሕግ ተጠያቂ ለማድረግ ያግዛል ተብሏል። ድርጅቱ ይህን የገለጸው፣ ሰሞኑን ሀዋሳ ላይ በተካሄደ ምክክር ላይ መሆኑን ዘገባው አመልክቷል። [ዋዜማ]
Show all...
🔆🔆 180 New vacancies at Melcon Construction PLC 💯 በሪፓርተር ጋዜጣ የሚወጡትን የሥራ ማስታወቂያዎች በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት (SMS) መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 7474 OK ብለው ይላኩ። ::•••••™ ✿::✿:: ✿::✿:: ✿™•••••:: 🔆🔆 Melcon Construction PLC ::•••••™ ✿::✿:: ✿::✿:: ✿™•••••:: ✅ Project Manager ✅ Equipment Maintenance & Administration Dept. Head ✅ Project Coordinator ✅ Secretary ✅ Supply Head ✅ Internal Auditor ✅ S/Accountant ✅ Accountant ✅ Cost Accountant ✅ Archive ✅ Purchaser ✅ S/ Personnel ✅ Lasion Officer ✅ Insurance Officer ✅ Maintenance Coordinator ✅ Construction engineer ✅ Site Engineer ✅ Office Engineer Head ✅ S/Quantity Surveyor ✅ S/Surveyor ✅ Surveyor ✅ Level Man ✅ Material Engineer ✅ S/Laboratory Technician ✅ Structure super Intendant ✅ Earth work super Intendant ✅ Structure Forman ✅ Earthwork Forman ✅ Bare bender Forman ✅ Plumber ✅ Store keeper ✅ Asphalt plant operator & Mechanic ✅ Project Administrator & Finance head ✅ Camp Administrator ✅ Cooker ✅ Project Accountant ✅ Project Casher ✅ Project Transport Coordinator ✅ Camp Administrator ✅ Project Equipment Maintenance & Administrator Head ✅ Project Equipment administrator ✅ Garage Forman ✅ Senior Machine Mechanic ✅ Senior light Vehicles Mechanic ✅ S/Welder ✅ J/Mechanic ✅ Auxiliary Machine Mechanic ✅ Senior Auto Electrician ✅ Senior Industrial Electrician ✅ Asphalt Plant Operator & Mechanic ✅ Crusher Forman ✅ Crusher Mechanic &Operator ✅ Dump Truck Driver ✅ Water Truck Driver ✅ Low Bed Driver ✅ High Bed Driver ✅ Light Vehicle Driver ✅ Grader operator ✅ Dozer Operator ✅ Excavator operator ✅ Loader operator ✅ Pneumatic roller / Roller operator 📌ብዛት: 180 + 📌 የሚፈለጉት የትምህርት ደረጃዎች: Accounting / Management / Business administration / secretarial & Office Management / Procurement &Supply management / civil engineering / Mechanical Engineering /Auto mechanic / surveying / Level 2/certificate or 10/12 grade / Transport & logistic / Industrial electricity / 10/12 grade &ደረቅ2/3 driving license / 10/12 grade &4ኛ/ፈሳሽ driving license / 🌟 ሰለ ሰራዎቹ ሙሉ መረጃ ለማየት እና ለማመልከት ይህንን ሊንክ ይጠቀሙ 👉 http://bit.ly/2M5RsqX ::•••••™ ✿::✿:: ✿::✿:: ✿™•••••:: ::•••••™ ✿::✿:: ✿::✿:: ✿™•••••:: ⚠️ከዚህ በፊት የተለቀቁ ስራዎችን ለማየት ከታች ይምረጡ ::•••••™ ✿::✿:: ✿::✿:: ✿™•••••:: 👉 360ground 👉 Melence Plc 👉 Gadaa Bank 👉 Commercial Bank of Ethiopia ::•••••™ ✿::✿:: ✿::✿:: ✿™•••••:: 💯 Don't forget to share/ወዳጅ ዘመድዎ እንዲደርሰው ሼር ያድርጉ ::•••••™ ✿::✿:: ✿::✿:: ✿™•••••:: ◢◤◢◤◢◤◢◤◢◤◢◤◢◤ 𝗝𝗼𝗶𝗻 𝗼𝘂𝗿 𝗖𝗵𝗮𝗻𝗻𝗲𝗹 ıllıllı @ethreporterjobs ıllıllı ıllıllı @ethreporterjobs ıllıllı ıllıllı @ethreporterjobs ıllıllı ◢◤◢◤◢◤◢◤◢◤◢◤◢◤
Show all...
Repost from N/a
ማክሰኞ ጥር 9/2015 ዓ.ም የማለዳ ዐበይት ዜናዎች 1፤ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ  በሚያካሂደው መደበኛ ስብሰባ ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ የሚያቀርቡለትን አዳዲስ የመንግሥት ተሿሚዎች ሹመት እንደሚያጸድቅ አስታውቋል። ጠቅላይ ሚንስትሩ ስንት ዕጩ ተሿሚዎችን እንደሚያቀርቡ ምክር ቤቱ አልገለጸም። የሚንስትሮች ምክር ቤት ባለፈው ሳምንት፣ የማዕድን ሚንስትር ታከለ ኡማ፣ የትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ሚንስትር ዳግማዊት ሞገስ፣ የግብርና ሚንስትር ኡመር ሁሴን እና በጠቅላይ ሚንስትር ጽሕፈት ቤት የካቢኔ ጉዳዮች ሚንስትር ተፈሪ ፍቅሬን ከሃላፊነት ማሰናበቱ ይታወሳል። 2፤ ከብሄራዊ ባንክና ማዕድን ሚንስቴር የተውጣጣ የባለሙያዎች ቡድን በወርቅ ግብይት ሥርዓቱ ላይ ጥናት አድርጎ የውሳኔ ሃሳቡን ለባንኩ ማቅረቡን ሪፖርተር ዘግቧል። የጥናት ቡድኑ ያቀረባቸው አማራጮች፣ ባንኩ በመደበኛና ጥቁር ገበያ የውጭ ምንዛሬዎች መካከል ያለውን የተመን ልዩነት ግምት ውስጥ በማስገባት የወርቅ መግዣ ዋጋ ማሻሻያ እንዲያደርግ የሚጠይቅ መሆኑን ዘገባው ጠቅሷል። የውጭ ምንዛሬ ተመን ልዩነት፣ የወርቅ አቅርቦቱን እንደጎዳው ጥናቱ ገልጧል ተብሏል። ቡድኑ የተሻለ አማራጭ ያደረገው፣ ባንኩ በዓለማቀፍ የወርቅ ግበያ ላይ በየ6 ወሩ የሚከለስ የ85 በመቶ ማበረታቻ ለወርቅ አቅራቢዎች ያቅርብ የሚል እንደሆነ ዘገባው አመልክቷል። 3፤ ኬንያ ለሱማሊያ የምትሸጥላትን የጫት ምርት ከእጥፍ በላይ እንድትጨምር ከሱማሊያ ፍቃድ ማግኘቷን ቢዝነስ ደይሊ ዘግቧል። ኬንያ ካለፈው ሐምሌ ጀምሮ ለሱማሊያ በቀን ስታቀርብ የቆየችው 19 ቶን ሲሆን፣ አሁን ግን 50 ቶን እንድታቀርብ እንደተፈቀደላት ዘገባው ጠቅሷል። ኬንያዊያን ጫት ላኪ ነጋዴዎች ለሱማሊያ ጫት የሚያቀርቡት ከኢትዮጵያ ጭምር በመግዛት ነው። ሱማሊያ ባሁኑ ወቅት አንድ ኪሎ ግራም ጫት የምትገዛው በ23 ዶላር እንደሆነ ዘገባው ጠቅሷል። 4፤ የሱማሊያ ጦር ሠራዊት በአልሸባብ ላይ ወታደራዊ ድሎችን መቀዳጀቱን ቀጥሏል። የመንግሥት ጦር ሰሞኑን ሂርሸበሌ እና ጋልሙዱግ በተባሉት የፌደራል ክልሎች ውስጥ፣ አደን ያባል እና ሐረርደር የተባሉ ስትራቴጂካዊ ከተሞችን ከአልሸባብ ነጻ ማውጣቱን ዘገባዎቹ ጠቅሰዋል። ጦሩ በተለይ ጋልሙዱግ ውስጥ ያለችውን ከተማ የተቆጣጠረው፣ በአሜሪካ የድሮን ጥቃት እገዛ ጭምር እንደሆነ ተገልጧል። ሁለቱ ከተሞች ላለፉት 10 ዓመታት በአልሸባብ ቁጥጥር ስር የቆዩ ናቸው ተብሏል። 5፤ የለንደን ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የብሪታኒያ መንግሥት ወደ ሩዋንዳ እልካቸዋለሁ ያላቸው "በሕገወጥ መንገድ" ብሪታኒያ የገቡ ጥገኝነት ጠያቂዎች ይግባኝ እንዲጠይቁ መፍቀዱን የአገሪቱ ጋዜጦች ዘግበዋል። የአገሪቱ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ከጥቂት ሳምንታት በፊት መንግሥት "በሕገወጥ መንገድ" የገቡ ያላቸውን ጥገኝነት ጠያቂዎች ወደ ሩዋንዳ ለመላክ ያሳለፈው ውሳኔ  "ሕጋዊ ነው" በማለት ብይን መስጠቱ ይታወሳል። የለንደን ፍርድ ቤት ለጥገኝነት ጠያቂዎቹ ይግባኝ የማለት መብት የፈቀደው፣ መንግሥት በርካታ ጥገኝነት ጠያቂዎችን ወደ ሩዋንዳ ለመላክ በሚዘጋጅበት ወቅት ላይ ነው። [ዋዜማ]
Show all...
ቅዳሜ ጥር 6/2015 ዓ.ም የምሽት ዐበይት ዜናዎች 1፤ የሚንስትሮች ምክር ቤት ከሥራ ለተሰናበቱ አራት ሚንስትሮች አሸኛኘት ማድረጉን የጠቅላይ ሚንስትር ጽሕፈት ቤት በማኅበራዊ ትስስር ገጹ ባሰራጨው መረጃ አስታውቋል። ዛሬ ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ በተገኙበት አሸኛኘት የተደረገላቸው፣ የማዕድን ሚንስትር ታከለ ኡማ፣ የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚንስትር ዳግማዊት ሞገስ፣ የግብርና ሚንስትር ኡመር ሁሴን እና የጠቅላይ ሚንስትር ጽሕፈት ቤት ኃላፊና የካቢኔ ጉዳዮች ሚንስትር ተፈሪ ፍቅሬ እንደሆኑ ተገልጧል። ሚንስትር ኡመር ሁሴን እና ተፈሪ ፍቅሬ በቅርቡ አምባሳደርነት እንደተሾሙ ይታወሳል። 2፤ ሚንስትሮች ምክር ቤት የተሻሻለውን የኤክሳይስ ታክስ አዋጅ አጽድቆ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መምራቱን የጠቅላይ ሚንስትር ጽሕፈት ቤት በማኅበራዊ ትስስር ገጹ ባሰራጨው መረጃ አስታውቋል። የኤክሳይስ ታክስ አዋጅ ተሻሽሎ የቀረበው፣ ባንዳንድ ምርቶች ላይ በተጣለው የማስከፈያ ምጣኔ ማስተካከያ የሚያስፈልገው ሆኖ በመገኘቱ እንደሆነ መረጃው አመልክቷል። የኤክሳይስ ታክስ በአገሪቱ ለመጀመሪያ ጊዜ በሥራ ላይ የዋለው፣ በ2012 ዓ፣ም ነበር። 3፤ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአሁኑ ወቅት በየዕለቱ ወደ መቀሌ ሦስት በረራዎችን እያደረገ መሆኑን ዛሬ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል። አየር መንገዱ ወደ መቀሌ የሚያደርገውን በረራ ቀንሷል ተብሎ የተሰራጨው መረጃ ስህተት ነው ያለው ኩባንያው፣ ወደፊት የመንገደኞችን ብዛት እያየሁ ወደ መቀሌ የሚደረጉ በረራዎችን ብዛት እጨምራለሁ ብሏል። አየር መንገዱ ላለፉት ስምንት ወራት ወዲህ በቅርቡ በተጀመረው የመቀሌ በረራም ሆነ በሌሎች የአገር ውስጥ በረራዎች ላይ የትኬት ዋጋ ጭማሪ አለማድረጉንም ገልጧል። 4፤ "ሆፕ ሉን" የተሰኘው የሆንግኮንግ የጨርቃ ጨርቅ ኩባንያ በደረሰበት ኪሳራ ሳቢያ ከባሕርዳር ኢንዱስትሪ ፓርክ መውጣቱን ሪፖርተር ዘግቧል። ኩባንያው ለኪሳራ የተዳረገው፣ አሜሪካ ኢትዮጵያን ከአፍሪካ የቀረጥ ነጻ ዕድል ተጠቃሚነት በማገዷ እንደሆነ ዘገባው ጠቅሷል። ኩባንያው ከፓርኩ ሲወጣ፣ ለ727 ሠራተኞቹ የሦስት ወር ደመወዝ ከፍሏል ተብሏል። ኩባንያው ምርት የጀመረው፣ በባሕርዳር ከተማ መንግሥት ያስገነባቸውን ስምንት የኢንዱስትሪ ፓርክ ሼዶች በመረከብ ነበር። 5፤ የፑንትላንድ ራስ ገዝ ፕሬዝዳንት አብዱላሂ ደኒ ከፌደራል መንግሥቱ ጋር የሚደራደር ኮሚቴ ማቋቋማቸውን የራስ ገዟ ዜና ምንጮች ዘግበዋል። ደኒ ተደራዳሪ ኮሚቴ ያቋቋሙት፣ ፑንትላንድ የፕሬዝዳንት ሐሰን ሞሐመድ መንግሥት "ፌደራላዊ ሥርዓቱን የተማከለ ለማድረግ ጥረት እያደረገ ነው" በማለት ከፌደራል መንግሥቱ ጋር ግንኙነቴን አቋርጩ ነጻ መንግሥት ሆኛለሁ ብላ ባወጀች ማግስት ነው። ፑንትላንድ ከፌደራል መንግሥቱ ጋር መነጋገር የምትፈልገው፣ የፌደሬሽኑ አባል መንግሥታት ከፌደራል መንግሥቱ ጋር በቅርቡ ከፈረሙት የሥልጣን ክፍፍል ሰነድ ውስጥ ለይታ ባለፈረመቻቸው ጉዳዮች ዙሪያ እንደሆነ ዘገባዎች ጠቅሰዋል። 6፤ በምሕጻረ ቃሉ "አፍሪኮም" የተሰኘው የአሜሪካው የአፍሪካ ወታደራዊ ዕዝ ትናንት በሱማላላንዷ ወደብ በርበራ ወታደራዊ ቅኝት ማድረጉን በሞቃዲሾ የአሜሪካ ኢምባሲ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል። አፍሪኮም በወደቧ ቅኝት ያደረገው፣ በወደቧ በየካቲት ወር ሌሎች አገራትን ጭምር ለሚያሳትፈው "ጀስቲፋይድ አኮርድ" ተብሎ ለተሰየመው ጥምር ወታደራዊ ልምምድ እንደሆነ ተገልጧል። በአፍሪኮም ወታደራዊ ልምምድ፣ ሱማሊያን ጨምሮ ከ28 አገሮች የተውጣጡ ወታደሮች የሚሳተፉ ሲሆን፣ አፍሪኮም በቀጣይነት በጅቡቲ፣ ኬንያ፣ ኡጋንዳ፣ ሩዋንዳ እና ቦትስዋና ጭምር ልምምድ ያደርጋል ተብሏል። የወታደራዊ ልምምዱ ዓላማ፣ የአፍሪካ አገራት ወታደሮችን ለጸረ-ሽብር ዘመቻዎችና ለሰላም ማስከበር ተልዕኮዎች ማብቃት ነው። 7፤ ኬንያ በሱማሌላንድ ኢምባሲ ለመክፈት አልወሰነችም ሲሉ የአገሪቱ ውጭ ጉዳይ ሚንስትር አልፈርድ ሙቱዋ በትዊተር ገጻቸው አስተባብለዋል። ሙቱዋ ማስተባበያ የሰጠት፣ አንዳንድ የዜና ምንጮች ኬንያ በሐርጌሳ ኢምባሲ ለመክፈት አቅዳለች የሚሉ መረጃዎችን ማሰራጨታቸውን ተከትሎ ነው። ኬንያ በሐርጌሳ ጉዳይ አስፈጻሚ ቢሮ ያላት ሲሆን፣ ካለፉት ጥቂት ዓመታት ወዲህ ከሱማሌላንድ ጋር ያላት ግንኙነትም እያደገ ሂዷል። በሌላ ዜና፣ ኬንያ ቁልፍ ተዋናይ የሆነችበት የምሥራቅ አፍሪካ ማኅበረሰብ፣ ማኅበረሰቡን ለመቀላቀል ጥያቄ ያቀረበችው ሱማሊያ የአባልነት መስፈርቱን ታሟላ እንደሆነ ለመገምገም የባለሙያ ቡድን ወደ ሞቃዲሾ መላኩን ገልጧል። [ዋዜማ]
Show all...
Repost from N/a
ቅዳሜ ጥር 6/2015 ዓ.ም የጠዋት ዐበይት ዜናዎች 1፤ የተመድ ዋና ጸሃፊ ቃል አቀባይ ስቲፈን ዱጃሪች ከኢትዮጵያ መንግሥት እና ሕወሃት ዘላቂ የግጭት ማቆም ስምምነት ወዲህ፣ በ3 ሺህ ካሚዮኖች ከ105 ሺህ ሜትሪክ ቶን በላይ የምግብና ሌሎች የዕርዳታ አቅርቦቶች ወደ ትግራይ መግባታቸውን ትናንት ማምሻውን በሰጡት መግለጫ ተናግረዋል። ከታኅሳስ የመጀመሪያ ሳምንት ጀምሮ፣ ከ3 ሚሊዮን በላይ ለሚሆን የክልሉ ሕዝብ የምግብ ዕርዳታ መሰራጨቱንና በሰሜናዊ ትግራይ ግን፣ አንዳንድ አካባቢዎች ዛሬም ለዕርዳታ ተደራሽ እንዳልሆኑ ቃል አቀባዩ ጠቅሰዋል። የተመድ የሰብዓዊ አውሮፕላን እና የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ክልሉ መደበኛ በረራ እያደረጉ መሆኑንም ዱጃሪች አውስተዋል። 2፤ በትግራይ ክልል ሽሬ ከተማ የአማራ ክልል ታጣቂዎች በብዛት እንደሚገኙ በአካባቢው የሚንቀሳቀሱ የረድዔት ድርጅት ምንጮች ነግረውኛል ሲል ሮይተርስ ዘግቧል። መከላከያ ሠራዊት በመንግሥትና ሕወሃት መካከል በተደረሰው የግጭት ማቆም ስምምነት መሠረት፣ የአማራ ክልል ልዩ ኃይሎች ከሽሬና አካባቢዋ ጠቅለው እንዲወጡ መደረጉን የገለጸው ትናንት ነበር። ሮይተርስ የመከላከያ ሠራዊት፣ የአማራ ክልል እና የሕወሃት ቃል አቀባዮች በጉዳዩ ላይ ማብራሪያ እንዲሰጡት ጠይቆ፣ ወዲያውኑ ምላሽ አለማግኘቱን ገልጧል። 3፤ የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ጉጂ ዞን ከቡሌ ሆራ ከተማ እስር ቤት ባለፈው ቅዳሜ ያስለቀቋቸው ታራሚዎች 480 እንደሚደርሱ ቢቢሲ ዓለማቀፍ ጣቢያ ዘግቧል። የከተማዋ ባለሥልጣናት ሁሉም የማረሚያ ቤቱ ታራሚዎች ማምለጣቸውን ማረጋገጣቸውን ዘገባው አመልክቷል። የአካባቢው ባለሥልጣናት ከእስር ያመለጡ ታራሚዎችን ለመያዝ አሰሳ እያደረጉ መሆኑን ተናግረዋል ተብሏል። ከእስር ቤቱ ካመለጡት መካከል፣ የኦነግ ሸኔ አባላት እንደሚገኙበት ዘገባው ጠቅሷል። ታጣቂዎቹ በጥቃቱ ወቅት 5 የፖሊስ አባላትን እንደገደኑ ተገልጧል። 4፤ የቱጃሩ ኤለን መስክ የኢንተርኔት ሳተላይት ስታርሊንክ በተያዘው ዓመት ሁለተኛ አጋማሽ በኬንያ የኢንተርኔት አገልግሎት እንድትሰጥ መታቀዱን ቢዝነስ ደይሊ ዘግቧል። የባለሃብቱ ኩባንያ ስታርሊንክ አገልግሎን ለማስጀመር፣ የመንግሥትን ፍቃድ እየተጠባበቀ መሆኑን መናገሩን ዘገባው ጠቅሷል። ስታርሊንክ በቅድሚያ ዒላማ የምታደርገው፣ ከፍተኛ ፍጥነት ያለው ኢንተርኔት የሚጠቀሙትን የቢዝነስ ኩባንያዎች ነው ተብሏል። የኬንያ ግዙፍ የኢንተርኔት አገልግሎት ሰጪ ኩባንያዎች ሳፋሪኮም እና ዙኩ ኢንተርኔት የሚያቀርቡት በፋይበር አማካኝነት ሲሆን፣ ስታርሊንክ ግን ከሳተላይት በቀጥታ ነው። 5፤ሱዳን እና ደቡብ ሱዳን በጋራ ድንበራቸው የሕገወጥ ጦር መሳሪያ ዝውውርን ለመግታት አንድ የጋራ የጸጥታ ግብረ ኃይል ለማቋቋም መስማማታቸውን የሱዳን ዜና ምንጮች ዘግበዋል። ሁለቱ መሪዎች እዚሁ ስምምነት ላይ የደረሱት፣ በደቡብ ሱዳን ይፋዊ ጉብኝት በማድረግ ላይ የሚገኙት የሱዳኑ ወታደራዊ መሪ ጀኔራል ቡርሃን እና ፕሬዝዳንት ኪር ጁባ ውስጥ ከተወያዩ በኋላ ነው። ሁለቱ መሪዎች፣ የአገሮቻቸውን የጸጥታ፣ ፖለቲካና ኢኮኖሚ ትብብር ለማጠናከር፣ የመረጃ ልውውጥ ለማድረግ፣ የአንዳቸው ዜጎች በሌላኛው አገር ሥራ መስራት፣ መኖር፣ ሃብት ማፍራትና በነጻነት መንቀሳቀስ እንዲችሉም መስማማታቸው ተገልጧል። [ዋዜማ]
Show all...