cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ኢትዮጵያ ታበጽዕ እደዊሃ ሐበ እግዚአብሔር

✝️✝️ ሰላም ውድ የቻናላችን ቤተሰቦች ÷ይህ ስለ ኦርቶዶክሳዊት ሀይማኖትና አስተምህሮ ሀሳብ የምንለዋወጥበት ቤት ነው። ✍️በዚህ ቻናል👉 ወረብ፣ሀይማኖታዊ መፃሀፍቶች÷ ዜማ÷ ቅዳሴ ÷ መዝሙሮች ÷ መንፈሳዊ ፎቶግራፍና ሌሎችም የተለያዩ የምትፈልጉትን መረጃ በጠየቁበት ፍጥነት እናደርሳለን። ሀሳብ፣አስተያየት እንዲሁም ጥያቄዎች ካሉበት ያናግሩን 👉👉👉 @Ethiopia_Orthodox_tewahdo_bot

Show more
Advertising posts
949
Subscribers
No data24 hours
+77 days
+1630 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

Photo unavailableShow in Telegram
አስቸኳይ ጥሪ ለመላው ኦርቶዶክሳውያን አቡ ገርቢ ቅዱስ እግዚአብሔር አብ ቤተክርስቲያን ይኸ በምስሉ ላይ የምትመለከቱት ቤተክርስቲያን የተመሰረተው የዛሬ 15 ዓመት ማለትም በ2001 ዓ.ም ነው። ከዛ በፊት ምዕመኑ ሰዎች የሞቱባቸው እና ለክርስትና የሁለት ሰዓት የእግዚአብሔር መንገድ በእግራቸው ሄደው ነው የቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን የሚያገኙት እና በዛ የተነሳ ቤተክርስቲያን ይቋቋምልን ብለው አቃቂ ወረዳ ላለው ቤተክህነት ጽ/ቤት ደብዳቤ ያስገባሉ እና 2001 ዓ.ም ተመሠረተላቸው። ወር በገባ በ13 እና መስቀል ጥምቀት ትንሳኤ በእነዚህ በዓላት ይቀደሳል ወርኃዊ ቅዳሴ ሲሆን ለአንድ ቅዳሴ 1000ብር ተከፍሎ ነው የሚቀደሰው በሦስቱ በዓላት ግን ይጨምራል ከ3000 እስከ 6000 ብር ይደርሳል ደብሩ አሁን አንድ ቄስ ነው ያለው በሰበካ ጉባኤ 4000 ብር ይከፈላቸዋል እንደዛም ሆኖ አራት ጊዜ ንግሥ አለ በአመት ውስጥ ህዳር 13 ጥር 13 ግንቦት 13 ነሐሴ 13 ንግሥ በዓል አለ። በተጨማሪ ለቅዳሴ የሚያስፈልጉ እንደ ጧፍ ፣እጣን፣ዘቢብ፣ሻማ፣ልብሰ ተክህኖ ፣ደወል ያንሳል የምትችሉትን ለዚህ ቤተክርስቲያን እየሰጣችሁ በረከትን አግኙ ። ለአሁን ደግሞ በአስቸኳይ የፊታችን ግንቦት 13 ቅዳሴ ቤቱ ንግሥ ስላለ በፍጥነት ለክብረ በዓሉ የሚሆን እጣን ጧፍ ዘቢብ በፍጥነት እንፈልጋለን። ሁላችሁም ኦርቶዶክሳውያን ብትረዱ እያልን በእግዚአብሔር ስም እንጠይቃለን ። ለማንኛውም ነገር አካውንት ለማግኘትም በእነዚህ ስልክ ቁጥር ይደውሉ 0911126270 ቀሲስ ሐረገወይን በየነ የደብሩ አስተዳዳሪ 0960029538 በረከት ከማኅበረ መዓዛ ሃይማኖት 0942133936 ማህሌት ከማኅበረ መዓዛ ሃይማኖት 0907610076 ማህደር ከማመሃ ሁላችሁም የምታደርጉትን ሁሉ እግዚአብሔር ይስጥልን።🙏🙏🙏 share ለ20ለ20 ሰው
Show all...
@ethiopia_orthodox_tewahdo @ethiopia_orthodox_tewahdo @ethiopia_orthodox_tewahdo #join and #share እንኳን ለዳግማይ ትንሳኤ በሰላም አደረሳችሁ
Show all...
Photo unavailableShow in Telegram
🌻🌻 💐 💐 💐 🌻🌻 🌻🌺 እንኳን ለጌታችን አምላካችን ፈጣርያችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በተዘጋ ቤት ለደቀመዛሙርቱና ከእነርሱ ጋር ለነበሩት ዳግመኛ ለተገለጠበት ዳግማዊ ትንሳኤ በዓል🌷🌻 💐🌷 🌼🌸🌹🌷🌸🌼 🌹🌺 🥀🌷 🌺🌼🌷🌷🌷 🌻🌻 🌾 🌾 🌾 🌻🌻 🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻 🌻🌺 መልካም 🌺🌻 🌻🌻 በዓል! 🌻🌻 🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻
Show all...
#ልደታ_ለማርያም ለእናንተ Profile ካዘጋጀናቸው ፎቶዎች @ethiopia_orthodox_tewahdo @ethiopia_orthodox_tewahdo @ethiopia_orthodox_tewahdo #join and #share
Show all...
ስርዓተ ማኅሌት ዘግንቦት ልደታ ለማርያም @ethiopia_orthodox_tewahdo @ethiopia_orthodox_tewahdo @ethiopia_orthodox_tewahdo #join and #share
Show all...
ሐዋ12:25 ቈላ4:10 1ጴጥ5:13 በሮም ተልእኮው ከቅዱስ ጴጥሮስ ጋር ሳለ ቅዱስ ጴጥሮስ ከፍጹምነት መድረሱን ዐውቆ ጵጵስና ሾሞ ከሀገረ ስብከቱ ግብጽን ከፍሎ አስተምር ብሎ ሰጠው:: እርሱም ሊያስተምር ሄዶ ወደከተማ ሊገባ ሲቃረብ የጫማው ጠፍር ተበጥሶበት አንያኖስ ወደሚባል ጫማ ሰፊ ሄደና ስፋልኝ ብሎ ሰጠው። አንያኖስ ጫማውን ተቀብሎ ሲሰፋ መስፊያው እጁን ወግቶት “ኢስ ታኦስ” ብሎ ጮኸ “አሐዱ እግዚአብሔር” ማለት ነው፤ የጠራኸውን ታውቀዋለህን? አለው፥ ሲሉ ሰምቼ እንጂ ያስተማረኝስ የለም አለው:: ቅዱስ ማርቆስም ፈቃደኛነቱን አይቶ አስተማረው አንያኖስም ከነቤተሰቦቹ አምኖ ተጠመቀ:: ከዚህ በኋላ አንያኖስን አስከትሎ በከተማ እየተዘዋወረ ያስተምር ጀመረ፤ ሕዝቡም ትምህርቱን ሰምተው ተአምራቱን አይተው አመኑ ተጠመቁ፤ አብያተ ጣዖታቱንም አፈራርሰው አብያተ ክርስቲያናትን ሠሩ። በዚህ ጊዜ የጣዖታቱ አገልጋዮች የለመዱት ቢቀርባቸው በጠላትነት ተነሡበት:: ምእመናኑ ተሰብስበው አባታችን እንድትለየን አንሻም ነገር ግን ገነውተ ጣዖታቱ በጠላትነት ተነሥተውብሀልና ቁጣቸው እስኪበርድ ጥቂት ጊዜ ወደ ሌላ ሥፍራ ሄደህ ቆይ አሉት:: አንያኖስን ኤጲስቆጶስ ልጆቹን ቄስና ዲያቆን አድርጎ ሾሞላቸው በባርቃና በሌሎች 5 አውራጃዎች እየሰበከ ቅዱስ ጴጥሮስን ለመጠየቅ ወደሮም ሄደ፥ በዚያ ሆኖ በስብከቱ ያመኑ የእስክንድርያ ምእመናን የተማሩትን እንዳይዘነጉ የማርቆስ ወንጌል ተብሎ የሚታወቀውን ወንጌል በሮማይስጥ ቋንቋ ጽፎ ልኮላቸዋል:: ዘመኑ ጌታ ካረገ 11ኛው ሲፈጸም 12 ኛው ሲጀመር ቀላውዴዎስ ቄሳር በነገሠ በ4ኛው ዓመት /45-46ዓ/ም/ ነው:: ከጥቂት ዓመታት ቆይታ በኋላ ወደ ግብጽ ተመለሰ፥ ምእመናኑ በቁጥር በዝተው በእምነት ጐልምሰው አግኝቷተቸው ደስ ብሎት እያስተማራቸው አብሯቸው ጥቂት ጊዜ ቆየ:: በዓለ ትንሣኤን በሚያከብሩበት ቀን አምልኮ ጣዖት ከስሞ አምልኮተ እግዚአብሔር በመስፋፋቱ ምቀኝነት ያደረባቸው ጣዖታውያን ሊጣሉት መጡ፥ ምእመናኑ አባታችን ሽሽ አሉት፥ እንግዲህስ በጌታዬና በአምላኬ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ስለ ወንጌል ክብር መከራ ልቀበል እንጂ ልሸሽ አይገባኝም አልሸሽም አለ:: እንደ ላም በአንገቱ ገመድ አስረው በረሀ ለበረሀ ሲጐትቱት ዋሉ ሥጋው በእሾህ በጋሬጣ ተቀረደደ:: ወደጌታ ቢያመለክት ስለተቀበልኸው መከራ ክብርህን ከ12ቱ ደቀመዛሙርቴ ክብር አንድ አድርጌልሀለሁ በስምህ የተማፀነኝንም እምርልሀለሁ ብሎ ቃልኪዳን ገብቶለት ነፍሱን በቃለ አቅርንት በይባቤ መላእክት አሳርጓታል:: በሞቱ ያልረኩት ጣዖታውያኑ ከሞተም በኋላ ሥጋውን ለማቃጠል ሽተው እንጨት ሰበሰቡ የሚያቀጣጥላቸውን ዝፍትም በከመሩት እንጨት ላይ አርከፈከፉ ጌታ ግን ይህን እንዲያደርጉ ዕድል አልሰጣቸውም ድንገት ታላቅ ነጐድጓድ ሆነ የተከማቹበት ሥፍራ ተናወጸ የፀሐይም ብርሃን ተሠውረባቸው በዚህ ጊዜ ምን መጣብን ብለው ማቃጠሉን ትተው ሸሽተዋል:: ኋላ ግን ምእመናን በመብረቅ ጸዳል ተከብቦ አግኝተው ቀብረውታል:: ቅዱስ ማርቆስ በሰማዕትነት ሲያርፍ የ70 ዓመት አረጋዊ ነበረ:: ከ30 ዓመታት በላይ በዘለቀ መዋዕለ ስብከቱ ለዓለም ሁሉ የምስራች የሚሆን የወንጌልን ቃል ከመጻፉ ባሻገር ከሐዋርያዊ ተልዕኳቸው የተነሣ ብርሃናተ ዓለም ከተባሉ ከቅዱስ ጴጥሮስና ከቅዱስ ጳውሎስ ጋር በብዙ አህጉረ ስብከት ተዘዋውሮ በማስተማሩና ይልቁንም የጥንት ግሪክ ሥልጣኔ ተስፋፍቶባትና የሮማ ሥርወመንግስት ቁልፍ የፓለቲካና የንግድ መዲና በነበረችው እስክንድርያ በሰማዕትነት እስካረፈባት ቅጽበት ድረስ በአንደበቱም በሕይወቱም በክብሩና በመከራው ሁሉ በማስተማር አይሁድን ከይሁዲነት ወደ ክርስቲያንነት አረማውያንን ከአምልኮ ጣዖት ወደ አምልኮተ እግዚአብሔር የመለሰ እንዲሁም በጸሎታቸው የሚጠብቁ በትሩፋታቸው የጽድቅን ዋጋ የሚያሰጡ የባሕታውያን አባት አባ ጳውሊን፣ የመነኮሳት አባት አባ እንጦንስን፣ አባ ጳኩሚስ እና አባ ሰራብዮንን፤ መናፍቃንን ተከራክረው የረቱ ሃይማኖትን ያቀኑ ቅዱስ እለእስክንድሮስን ቅዱስ አትናቴዎስ ሐዋርያዊን ቅዱስ ጢሞቴዎስ ዘአልቦ ጥሪትና ቅዱስ ዲዮስቆሮስን የመሳሰሉ ኦሮቶዶክሳውያን ሊቃውንትንና እስከ ዛሬም መከራ ሳይበግራቸው ሞትና ግርፋታቸውን እንደ ክብር ቈጥረው በሃይማኖታቸው ፀንተው የሚኖሩ የጸኑ ምእመናንን ያፈራች አንፀባራቂ ስም ያላት ኦርቶዶክሳዊትና ሐዋርያዊት ቤተክርስቲያንን ያቋቋመ ሐዋርያ በመሆኑ ዳግመኛም ከአባ ሰላማ ከሣቴ ብርሃን /4ኛ ክ/ዘ/ እስከ አቡነ ቄርሎስ /20ኛ ክ/ዘ/ ድረስ የኢትዮጵያን ቤተክርስቲያን በክህነት የመገቡ 111 ጳጳሳት ቅዱስ ማርቆስ ወንጌላዊ ያቋቋማት የዚህችው ቤተክርስቲያን ፍሬዎች በመሆናቸውና ትምህርታችን ከትምህርታቸው ሥርዓታችን ከሥርዓታ ቸው የተስማማ የተግባባ በመሆኑ “ማርቆስ አባታችን እስክንድርያ እናታችን” ማለት በኢትዮጵያውያን ምእመናን ዘንድ የተለመደ ነበር፥ ታሪክ ነውና ዛሬም ቢሆን ቤተክርስቲያናችን ሙሉ በሙሉ ከግብጽ ቤተክርስቲያን ጥገኝነት ተላቃ በኢትዮጵያውያን ጳጳሳት ብትመራም ይህ እውነታ የሚዘነጋ አይደለም:: ከዚህም በላይ ቤተክርስቲያናችን ቅዱስ ጳውሎስ “ተዘከሩ መኳንንቲክሙ ዘነገሩክሙ ቃለ እግዚአብሔር” ትርጉም “የእግዚአብሔርን ቃል የነገሩአችሁን ዋኖቻችሁን አስቡ” ዕብ13:7 እንዳለ ሐዋርያዊ ተልእኮውንና መንፈሳዊ ተጋድሎውን ለማስታወስ በስሙ ጽላት ቀርጻ ቤተክርስቲያን አንፃ ታዘክረዋለች ፥ የዕረፍቱንም መታሰቢያ በዓል በየዓመቱ ሚያዚያ 30 ቀን ታከብራለች:: @ethiopia_orthodox_tewahdo @ethiopia_orthodox_tewahdo @ethiopia_orthodox_tewahdo #join and #share
Show all...
Photo unavailableShow in Telegram
ማርቆስ የሚለው ስም ሦስት ፍቺዎች አሉት ንብ፣አንበሳ እና ካህን:: በወንጌልና በመጽሐፈ ቅዳሴ አንድምታ ትርጓሜ መጻሕፍት እንደታተተው ንብ የሚለው ፍቺ የተሰጠው ንብ አበባ ካለው ተክል ሁሉ ቀስማ ማር እንድትሠራ እርሱም ቀድሞ ከጌታ ኋላም ከጌታ የተማርኩት ይበቃኛል ሳይል ከሐዋርያት ተምሮ ደገኛይቱን ወንጌልን በማስተማሩና በመጻፉ ሲሆን አንበሳ መባሉ አንበሳ እንስሳት አራዊትን በክርኑ እንዲሰብር በግብጽ ይመለኩ የነበሩ በእንስሳ አምሳል የተሠሩ ጣዖታትን በወንጌል ቃል ኃይልነት በማጥፋቱ ነው:: ካህን የሚለው ትርጉም ደግሞ በሐዋ 14:13 “ወአምጽኡ ማሬ ዘድዮስ” ተብሎ ከተመዘገበው መጽሐፍቅዱሳዊ አሳብ የተወረሰ ነው:: ማርቆስ ከመባሉ በፊት ዮሐንስ ይባል የነበረ ሲሆን ቁጥሩ ከ72ቱ አርድዕት:: ሐዋ 12:12 አባቱ አርስጦቦሎስ እናቱ ማርያም ይባላሉ:: ማርያም በጌታ ትምህርት አምነው ሲከተሉትና ሲያገለግሉት ከነበሩት ደጋግ ሴቶች አንዷ ስትሆን ከጌታ ትንሣኤ በኋላ ቤቷን ለወንጌል አገልግሎት ሰጥታ ሐዋርያት በዚያ ተሰብስበው ለጸሎት ይተጉ ነበር፥ ጌታ ባረገ በ10 ኛው ቀን ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም ጋር በአንድነት ሳሉ መንፈስቅዱስን የተቀበሉትም በዚሁ በማርቆስ እናት በማርያም ቤት ውስጥ ነው:: ሐዋ 2:1 ፣12:12 የራሱን ሀገረ ስብከት ይዞ ማስተማር ከመጀመሩ በፊት ቅዱስ ማርቆስ ሐዋርያትን እየተከተለ ይማር በተልእኮም ይራዳቸው ነበር:: ከቅዱስ ጳውሎስ መጠራት በኋላ ጳውሎስንና አጎቱ በርናባስን ተከትሎ በአንጾኪያ ቅዱስ ጴጥሮስን ተከትሎ በሮም አስተምሯል፤ እነርሱም በመልእክቶቻቸው “ማርቆስ ሰላም ይላችኋል” እያሉ አንስተውታል::
Show all...