cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

Ethiopia today ኢትዮጵያ ዛሬ

ፍቅርን አንድነትን እና ኢትዮጵያዊነትን ማወደስ:: ወቅታዊና አዳዲስ መረጃ ማድረስ። I proud to be an Ethiopian.

Show more
Advertising posts
509Subscribers
No data24 hours
No data7 days
-1030 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

እንዲህም ተጀምሯል❗❗🤔 ከትናንት በስተያ አመሻሽ ላይ ፌዴራል ፖሊስ ነን የሚሉ ሰዎች ከትራፊክ ፖሊስ ጋር በመተባበር ኡስታዝ አቡበከርን አስቆሙት በመኪና ስርቆት ወንጀል ተጠርጥረሃል የምትነዳው V8 መኪና የተሰረቀ ነው ፖሊስ ጣቢያ ሂድ አሉት ኡስታዝም የማጭበርበር ወንጀል መሆኑን ፈጥኖ በመረዳት ወደ ቤተሰብ ደውሎ አሳወቀ ቤተሰብም በፍጥነት መጡለት ። ከዚያም ቶታል 3 ቁጥር ማዞሪያ ወደ ሚገኘው ፖሊስ መምሪያ ይዘውት ሄዱ ፌደራል ፖሊስ ነን ያሉ ግለሰቦች ሀሰተኛ መታወቂያቸውን ለፖሊሶች በማሳየት ኡስታዝ አቡበከርን እና መኪናውን ለፖሊስ መምሪያው አስረክበው ሄዱ ። ከሌሊቱ 6 ሰዐት ሲሆን እነዚሁ አካላት ወደ ፖሊስ መምሪያው በመምጣት ተረኛ ፖሊሱን ወንጀለኛው ፌደራል ፖሊስ ጋር ይፈለጋል ስጡን አሏቸው ፖሊሱም ደብዳቤ ካላመጣችሁ አንሰጥም የሚል ምላሽ ሰጣቸው ። አሳልፎ ቢሰጣቸው ኖሮ ኡስታዝን ገድለው መኪናውን ዘርፈው ይሰወሩ ነበር ። ዛሬ ከሰዐት አከባቢ እነዚሁ አካላት ከለቡ ፖሊስ ጣቢያ ደብዳቤ በማምጣት ከሳሽ የሚገኘው ለቡ ፖሊስ ጣቢያ ነው በማለት ወደ ለቡ ፖሊስ ጣቢያ ወሰዱት ። ቤተሰብ የመኪናውን ሊብሬ ይዞ መንገድ ትራንስፖርት በመሄድ ሲያጣራ የመኪናው ሊብሬ በሌላ ሰው ስም ተቀይሮዋል ። ጉዳዩ አደገኛ የሆነ ሰንሰለት ያለበት ማጭበርበረ ወንጀል መሆኑን በመረዳት ጉዳዩ ወደ ፌደራል ፖሊስ ወደ ከፍተኛ የፖሊስ አመራሮች  እንዲደርስ ተደረገ ። መረጃው ወደ ሪፐብሊካን ጋርዶች  ሲደርስ የለቡ ፖሊስ ጉዳዩ እኔን አይመለከተኝም በማለት ወደ ፔፕሲ ፋብሪካ ጎተራ ወደ ሚገኘው ፖሊስ ጣቢያ እንዲሄድ ተደረገ ። የፌደራል ፖሊስ አባላት ጎተራ ፖሊስ መምሪያ መጥተው ጉዳዩን ሲመረምሩ ፌደራል ፖሊስ ነን ያሉ አካላት ፌደራል ፖሊስ አባል እንዳልሆኑ  እንዲሁም መኪናችንን ተሰርቀናል ብለው ሀሰተኛ ሊብሬ ያሰሩ አካላት  በቁጥጥር ስር ዋሉ ። ኡስታዝ አቡበክር ሁሴን እንዲፈታ ተደረገ አሁን ጥያቄው የመኪና ሊብሬውን ማን ስሙን ቀየረ የእነዚህ ወንጀለኞች ሰንሰለት እስከምን ድረስ ነው በቀጣይ ፖሊስ የሚያጣራው ይሆናል። ምንጭ:- አዱኛው ሙጬ ጊዜው ከፍቷል ጥንቃቄ ንቃት ያስፈልጋል
Show all...
አንድ አባት ከመሞቱ በፊት ለልጁ እንዲህ አለው ''ይህንን የእጅ ሰአት ሰአት እንካ አያትህ ለኔ ሰጡኝ እኔ ደግሞ አሁን ላንተ እሰጥሃለው። ይህ የእጅ ሰአት ወደ ሁለት መቶ አመታት ሆኖታል። መጀመሪያ ግን ላንተ ከመስጠቴ በፊት ይህንን ሰአት፤ ሰአት መሸጫ ሱቆች ወስደህ ልትሸጠው እንደምትፈልግና ስንት እንደሚገዙህ ጠይቀህ ና" አለው። ልጁም እንደተባለው ሰአት መሸጫ ሱቅ የአባቱን አሮጌ የእጅ ሰአት ይዞ ሄደ። ስንት እንደሚገዙት ጠይቋቸው ተመለሰ። ወደአባቱ ጋር ሄዱ ስላረጀ መቶ ብር እንደሚገዙት ነገረው። አባትየው አለ ... እስኪ የአሮጌ እቃ መሸጫ ቦታዎች ስንት እንደሚገዙህ ጠይቀህ ና አለው። ልጅም አባቱ እንዳዘዘው ወደ አሮጌ እቃ መሸጫ ሱቆች ሄዶ ስንት እንደሚገዙት ጠይቆ ተመለሰ። የሰአቱ መስታወት ስለተሰነጠቀ ሃያ ብር ብቻ እንደሚገዙት ነገረው። አባትየው ለሶስተኛ ጊዜ እስኪ አሁን ደግሞ ሙዚየም ሄደህ ስንት እንደሚገዙህ ጠይቀህ ና አለው። ልጁም እያቅማማ ሰአቱን ይዞ ወደ ሙዚየም ሄደ። ይህንን አሮጌ የእጅ ሰአት ስንት እንደሚገዙት ጠይቆ ተመለሰ። ልክ አባቱ ጋር ሲደርስ በአግራሞትና በደስታ አባዬ ሄጄ ስጠይቃቸው ይህ ሰአት የማይገኝና እጅግ ውድ ስለሆነ ሶስት መቶ ሺህ ብር እንደሚገዙን ነገሩኝ አለው። አባትየውም በተረጋጋ አንደበት እንዲህ አለው:- "ልጄ ላሳይህ የፈለኩት በትክክለኛው ቦታ ላይ ትክክለኛ ዋጋህን እንደምትገኝ ነው። ራስህን የማይሆን ቦታ አድርገህ ሰዎች ዋጋህን ዝቅ ቢያደርጉት እንዳትናደድ ጥፋቱ ያንተ ነውና። ያንተን የማንነት ዋጋ ከማያውቁ ሰዎች መሃል አትገኝ። የራስህን ዋጋ የማታውቅ ከሆነ ሁሌም ከሚገባህ በታች ለርካሽ ነገር ራስህን ትሰጣለህ" አለው።
Show all...
ከዕለታት ባንዱ ቀን አንድ ታዳጊ አባቱን እንዲህ በማለት ይጠይቃል። አባዬ! “#የህይወት_ዋጋው ስንት ነው?” ሲል ጠየቀ፡፡ አባትም መልስ በመስጠት ፈንታ ልጁን እንዲህ ሲል አዘዘው፡፡ “እንካ ይህንን #የድንጋይ_ቁራጭ ወደ ገበያ ውሰደው፡፡ ሰዎችም ዋጋውን ከጠየቁህ በጣቶችህ ሁለት ቁጥርን ብቻ አሳያቸው እንጂ ምንም አትናገር” አለው፡፡ . ልጁም ድንጋዩን ተቀበለ፡፡ ወጥቶም #በገበያ መሃል ቆመ፤ አንዲት ሴትም መጣች፡፡ “ይህ ድንጋይ ዋጋው ስንት ነው? ብትሸጥልኝ ወስጄ ግቢዬ ውስጥ አስቀምጠዋለሁ” አለችው፡፡ ልጁም እንደታዘዘው ምንም ሳይናገር ሁለት ጣቶቹን አሳያት፡፡ እሷም አለች “#ሁለት_ብር? በቃ እወስደዋለሁ!” ብላ ወሰደችው። ልጁም ወደ ቤቱ ተመለሰ፡፡በገበያ ያጋጠመውንም ለአባቱ ነገረው፡፡ . አባትየውም አለው “አሁን ደግሞ ድንጋዩን ይዘህ ወደ #ሙዚየም ሂድ፡፡ ዋጋውን ሲጠይቁህም ሁለት ጣቶችህን አሳይ”፡፡ ልጁም የአባቱን ትእዛዝ ተከትሎ ወደ ሙዚየም አቀና፡፡ ገዢም መጥቶ ዋጋ በጠየቀው ጊዜ ሁለት ጣቶቹን አሳየው፡፡ ገዢውም “#ሁለት_መቶ_ብር? እሺ እወስደዋለሁ!” አለው፡፡ ልጁም በድንጋጤ ወደ ቤቱ ተመለሰ፡፡ ያጋጠመውንም ለአባቱ ነገረው፡፡ . አሁንም አባትየው ለሶሥተኛ ጊዜ እንዲህ ሲል ተናገረ፡፡ “አሁን ደግሞ በመጨረሻ ድንጋዩን ይዘህ ወደ የከበሩ #ማዕድናት_መሸጫ ስፍራ ሂድ ለባለቤቱም አሳየው” አለው፡፡ ልጁም ያባቱን ሁኔታ እየገረመው ወደ ታዘዘው ስፍራ ሄደ፡፡ ቁራጭ ድንጋዩም ለሱቁ ባለቤት አሳየው፡፡ የሱቁ ባለቤት በመገረም “ይህ እኮ አለም ላይ እጅግ ውድ ከሆኑ የከበሩ ድንጋዮች አንዱ ነው” አለ፡፡ “ከየት አገኘኸው? ስንትስ ትሸጠዋለህ?” ሲል ጠየቀው፡፡ ልጁም ምንም ሳይናገር እንደተለመደው ሁለት ጣቶቹን አሳየ፡፡ የሱቁም ባለቤት አለ.... “ይህንን ድንጋይ #በሁለት_መቶ_ሺህ_ብር? ይገርማል! በቃ እወስደዋለሁ አለ።” ልጁም በመገረምና በመደነቅ እየሮጠ ወደ ቤቱ ተመልሶ ያጋጠመውን ሁሉ ለአባቱ ነገረው፡፡ . አባትየውም “ልጄ አሁን የህይወትህ ዋጋ ተገልጦልሃል” አለው፡፡ አየህ የመጣህበት ቦታ፣ ዘርህ፣ ኃይማኖትህ፣ የቤተሰቦችህ ሃብት፣ የተወለድክበት ቦታ ልዩነት አይፈጥርም፡፡ ዋናው ራስህን #የምታስቀምጥበት_ቦታ፣ ራስህን የምታገኝበት የሰዎች ስብስብ ነው፡፡ ልዩነቱ ያለው ራስህን ለመሸከም በምትመርጥበት መንገድ ነው። ህይወትህን ሙሉ የሁለት ብር ድንጋይ ዋጋ ስትሰጠው ኖረህ ይሆናል፡፡ ህይወትህን ሙሉ የኖርከው ዋጋህ ሁለት ብር ብቻ እንደሆነ በሚያስቡ ሰዎች ተከበህ ይሆናል፡፡ ነገር ግን እያንዳንዱ ሰው ውድ የሆነ የከበረ ድንጋይ በውስጡ ይዟል፡፡ . ልዩነቱም ያለው ውስጣችን ያለውን የከበረ ድንጋይ አይተው ዋጋ በሚሰጡን ሰዎች መሃል መገኘትን ስንመርጥ ነው፡፡ ራሳችንን በገበያ ወይም በከበሩ ማዕድናት ሱቅ የማስቀመጥ ምርጫው አለን፡፡ በሌሎች ሰዎች ውስጥ ያለውንም ውድ ዋጋ ለማየት ምርጫው የኛው ነው፡፡ ሌሎች ሰዎችም የከበረ ዋጋቸውን እንዲረዱ ማድረግ እንችላለን፡፡ #አብረህ_የምትውላቸውን_ሰዎች በጥንቃቄ ምረጥ፡፡ ይህ በህይወትህ ልዩነትን ይፈጥራልና፡፡ --------------- @ ምንጭ: ሻውን ቡንደናሂራን ከተረከው የተተረጎመ
Show all...
ኢትዮ ቴሌኮም የ2015 ዓ.ም በጀት ዓመት እቅድ በስኬት ስላጠናቀቀ ለአንድ ሳምንት የሚቆይ የ1 ጂቢ ዳታ 25 ደቂቃ ጥሪ እና 50 መዕክት እንዲሁም በቴሌብር ሱፐርአፕ ተጨማሪ ተመሳሳይ ስጦታ ማበርከቱን አስታውቋል።
Show all...
#ጥንቃቄ_አዎ_ጥንቃቄ እሰልሰዋለሁ ጥንቃቄ አድርጉ በዚህ በ21ኛው የዲጂታል አለም ከውጭም ከአገር ውስጥም እንዲሁም በተቀናጀ መልኩ እጅግ የረቀቀ የማታለል፣ የማጭበርበር ወንጀል ስራዎች እየተሰሩ በርካቶች ሳያውቁ ተታለው ጥረው ግረው የሰሩትን ገንዘብ ተጭበርብረዋል። ይሔን የደረሰባቸው የተጭበረበሩ እልፎች ያውቁታል። ወገን አንዳንዴ ቆም ብለን እናስተውል፤ ለምን ይሔን አድርግ አለኝ፣ ይሔን አዋጭ ቢዝነስ ነው ስራ አለኝ፣ ለምን ይሔን ያህል ዋስትና ለሌለው የቢዝነስ ሃሳብ ኢንቨስት (ብር ክፈል) አለኝ? ተሸላሚ ነህና ብር ክፈል አለኝ? Bla bla bla ወደ አዕምሯችሁ ሊመጡ ልታሰላስሉት የሚገባ በርካታ ጥያቄዎችን ደጋግሞ ማጤን ያስፈልጋል። የሚገርመው ኢትዮጵያ ውስጥ ኢንተርኔትን በመጠቀም የOnline business መስራት ይቻላል ይሔን ሊንክ Click አድርግና አካውንት ከፍተህ በየቀኑ Click click በማድረግ ገንዘብ መስራት ትችላለህ የሚሉ በርካቶች አሉ። ይሔ እኛ አገር ውስጥ የማይሰራ የፈለገ በነፃ Click ብታደርግ ገንዘብ Invest አድርገህ Click ብታደርግ ያለህን የሞባይል ካርድ አለፍ ሲል Invest ያደረገውን ገንዘብና ጊዜ ከማጥፋት ውጭ ኪሳራ እንጂ ገቢ በፍፁም አታገኙም። እንደሚታወቀው ዛሬ ላይ Mobile Banking, Tele birr, Internet Banking, ሌሎችንም የዲጂታል ፋይናንስ ብዙዎቻችን እንጠቀማለን። ታዲያ እነዚህ አጭበርባሪዎች ስልክ በመደወል ሽልማት ደርሷችኋል፣ አሁን በስልክህ የተላከ ኮድ አለ እሱን ላክልኝ ወይንም ንገረኝ/ሪኝ፣  በዚህ መሰረት ስልክህ ላይ በመጻፍ ሽልማት (Bonus) ይገባልሃል፣ ሌላም የማታለያ ዘዴዎችን በመጠቀም እያታለሉ በርካቶችን ዘርፈዋል። ወገን ኧረ እንንቃ። ማንም የማታውቀው ግለሰብ በዚህ ጊዜ አንተን ሊሸልም፣ ገቢ የሚያስገኝ ቢዝነስ ላይ ሊያሳትፍህ በቀጥታ በስልክ ደውሎ፣ በቴሌግራም ሊንክ (መልዕክት) በመላክ ሊያሰራህና ራስህን እንድትለውጥ አያደርግህም። በርካታ ባንኮች በተለይ ከዚህ ባንክ ነው ሽልማት ደርሷችኋል፣ የተላከ ኮድ አለ እሱን ይላኩልንና መሰል መልዕክት በመላክ እንዳትጭበረበሩ ተጠንቀቁ የሚል በተለያዬ ወቅት ሲያስጠነቅቁ ይታያል። ሽልማት እንኳን ቢሆን በአቅራቢያ ከሚገኝ የባንክ ቅርንጫፍ ሂዶ መጠየቅም ይቻላል። ከተባባሪ አካላት ጋር እጅግ በረቀቀ መልኩ ስለሚሰሩ ከመጠንቀቅ በስተቀር ከስሼ ብሬን አስመልሳለሁ አይሰራም። ወገን ከመሰል አጭበርባሪዎች እንጠንቀቅ። ቆም ብለን እናስብ፣ እናስተውል፣ ለሌሎችም ግንዛቤ እንፍጠር።
Show all...
አንድ ሚስኪን ለማኝ፥ የእለት ጉርሱን ሊለምን አንድ ገበሬ ቤት ይሄዳል። ቁራሽ እንጀራ በመጠበቅ እያለ የቤቱ አባወራ ከስራ ደክሞ ይመለሳል። ልጆቹ እየሮጡ መጥተው አቀፉት፤ ውድ ባለቤቱ ውሃ አዘጋጅታ እግሩን አጠበችው። ቀጥለውም ቤት ያፈራውን በመሳሳቅ መብላት ጀመሩ። በልተው እንደ ጨረሱ ገበሬው፦ “አንደኛው በሬ አርጅቷል። ከአሁን በኋላ ማረስ አይችልም። ስለዚህ ከአራጣ አበዳሪ ብር ተበድሬ፤ ሌላ በሬ መግዛት አለብኝ።” ብሎ ሚስቱ ያዋያታል። በገበሬው ቤት የሆነውን ሁሉ የታዘበው ይህ ሚስኪን ለማኝም የሰጡትን ተቀብሎ በመመለስ እያለ፦ “ቆይ የኔ ህይወት ምንድነው? እንደ ውሻ ሀገሩን ሁሉ ዞሬ ያገኘሁትን አጠረቃቅሜ እቤቴ ስመለስ፤ ስቀው የሚቀበሉኝ ልጆች የሉኝ። ድካሜን ተረድታ እግሬን የምታጥብ ሚስት የለኝ። እንዲሁ ልፋት! ገበሬው ምንኛ የታደለ ደስተኛ ነው?” ብሎ በገበሬው ህይወት ይቀናል። ገበሬውም ብር ለመበደር አራጣ አበዳሪው ጋር ሄደ። አራጣ አበዳሪውም ካዝናው ሲከፍተው፤ ብዙ የብር ኖቶች ታዩ። ከብሮቹ መሀከል ገበሬው የፈለገውን ሰጥቶ ካበደረው በኋላ ሸኘው። ገበሬውም በመንገድ እያለ፦ “አሁን የኔ ህይወት፥ ህይወት ነው? የልጆቼና የሚስቴ ልብስ መግዣ ብር የለኝ፤ ለችግሬ መሻገሪያ ስበደር ደግሞ ወለድ ያስጨንቀኛል፤ ህይወቴ በሁለት በሬ ትከሻ ዋስትና እስከመች ነው የሚቆየው? ካዝና ሙሉ ብር ያለው አራጣ አበዳሪው ግን ምንኛ የታደለ ደስተኛ ሰው ነው?” ብሎ ከራሱ ጋር ማውራት ይጀምራል። አራጣ አበዳሪውም ለልብስ መሸጫ ሱቁ እቃ ለማምጣት ወደ ተሻለ ከተማ ሄደ። ልብሶቹ ከሚገዛበት ደንበኛው ጋር ሳለ ብዙ እንደ እሱ ያሉ ነጋዴዎች ገዝተው ሲሄዱ አይቶ፦ “አሁን የኔ ህይወት፥ ህይወት ነው? ልብስ በፍሬ እየሸጥኩ መች ነው የሚያልፍልኝ? ብድርህ መልስ እያልኩ ከገበሬ ጋር የማልዳረቀው መቼ ነው? ይህ ደንበኛዬ ምንኛ የታደለ ደስተኛ ሰው ይሆን!?” ብሎ ይተክዛል። የአራጣ አበዳሪው ደንበኛም ደብዳቤ ይደርሰዋል። እርሱ ልብስ ከሚረከብበት አስመጪ ነበር። ደብዳቤውም 'እዳ አለብህ፤ እዳህን ክፈል' የሚል ነበር። እንደገና ሌላ ደብዳቤ ደረሰው። ከዋና ከተማው የአስመጪው ጓደኛ የሆነው አንዱ ሀብታም፥ ልጁን ሊድር፤ የሰርግ የጥሪ ወረቀት ነበር። ጥሪውን ተቀብሎ ወደ ሰርጉ ተሳፍሮ ሄደ። እንደ ደረሰም፤ ብዙ ልጥጥ ሀብታሞች፣ ብዙ ዝንጥንጥ ያሉ ዲታዎች፣ ተራራ የሚያካክሉ ወንዶችና ሴቶች እየተሳሳቁ 'ቺርስ' ይባላሉ። እርሱም ተቀላቀለ። “እነዚህ ሀብታሞች እዳህን ክፈል ብሎ የሚያስጨንቃቸው የለ፤ ኪሳራ አያጎብጣቸው፤ ከትንሽ ነጋዴ ጋር አይዳረቁ፤ ቤታቸው የሞላ፤ አምሮታቸው መወጣጫ አያጥራቸው፤ እነዚህ ምንኛ የታደሉ ደስተኞች ናቸው?” ብሎ አሰበ። ፕሮግራሙ እንዳለቀ የቤቱ አባወራ ራሱ ስቶ ይወድቃል። የግል ዶክተሩ ተጠርቶ መጣ። ከተወሰነ ክትትል በኋላ ነቃ። ተነስቶ ቆሞ። G+2 መኖሪያ ቤቱ ላይ ሆኖ፤ ወደ መስኮቱ ተጠጋ። ወደ ውጭ ሲያይ አንድ ሚስኪን ለማኝ ከረጢቱ አንከርፍፎ የግቢው አጥር ተደግፎ ቆሟል። በልቡም፦ “ይህ ለማኝ ኪሳራ አያውቅ፤ ፉክክር አይገባው፤ ልብ ድካም አያመው፣ እንቅልፉ አያጣ። ምንኛ የታደለ ደስተኛ ሰው ይሆን!?” ብሎ አጉተመተመ። 📝📝📝📝📝📝📝 አየህ......ባለህ ነገር ላይ መደሰት ካልቻልክ ህይወት ክብ ይሆንብሃል። ዞረህ አትጨርሰውም። እላይ ስትደርስ ታች መሆን ያምርሀል፤ እታች ስትሆን እላይ ያለው ያስቀናሃል። ሁሌ መጠማት ብቻ ትሆናለህ። ረካሁኝ ስትል መልሶ ይጠማሃል። ባለህ ስትደሰት ግን ይጨመርልሃል። ሰናይ ቀን!!
Show all...
Always stand up for what is right. Even ifit means standing alone.
Show all...