cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

DBCTUBE ETHIOPIA

🇩 🇧 🇨 🇹 🇺 🇧 🇪 - 🇪 🇹 🇭 🇮 🇴 🇵 🇮 🇦☑ 𖣘 እንኳን ደህና መጡ ! እያልን በዚህ ቻናል ሲቆዩ ያተለያዩ የስነፅሁፍ ስራዎችን ያሚገኙ ሲሆንኑ፣ እነሱም፦ ግጥም፣ልብወለድ፣ወግ እንዲሁም አዝናኝና አስታማሪ ዝግጅቶች ያሚገኝ ሲሆን በተጨማሪም ከራስ ወጣ ያሉ ወቅታዊ ፣ የስፖርት ፣ እንዲሁም የቴክኖሎጂ መርጃዎች የምናቀርብላቹ ይሆናል። አብራቹሁን ስላላችሁ እናመሰግናለን!

Show more
Advertising posts
17 135
Subscribers
-1924 hours
-1747 days
-80030 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

Photo unavailable
የሰው ልጅ የማድረግ አቅም የሚፈተንበት የዓለማችን አዲስ ከተማ…..😱 በረሃን ወደ ከተማነት የመቀየር ጥበብ ልንለው እንችላለን፡፡ ከ1 ትሪሊየን ዶላር በላይ የሚፈጅ ውድ ሥራም ነው፡፡ ከገንዘቡ ባሻገር ብዙ እውቀቶች ፈሰውበታል፤ አዳዲስ ነገሮች ተዋውቀውበታል፡፡ ዓለምን እጅ በአፍ አስጭኗል…. “ኒዮም ሲቲ” (Neom City) በሳውዲው ልዑል መሀመድ ቢን ሳልማን ይፋ የሆነው ይህ ፕሮጀክት እ.ኤ.አ በ2017 የተጀመረ ሲሆን በውስጡ አራት ሥራዎች ይገኙበታል፡፡ እነሱም ዘ ላየን፣ ኦክሳገን፣ ትሮጄና እና ሲንዳላህ ይሰኛሉ፡፡ የፕሮጀክቱ የመጀመሪያ ምዕራፍም እ.ኤ.አ በ2030 ይጠናቀቃል ተብሏል፡፡ እስቲ ለዛሬ የዚህ ፕሮጀክት አንድ አካል የሆነውና ከቀናቶች በፊት ግንባታው የደረሰበትን ደረጃ ስለሚያሳየው ቪዲዮ የተለቀቀውን ዘ ላይን (The Line) ፕሮጀክት እንመልከት፡፡ እንደ ቀጭን መስመር ቀጥ ያለ ከተማ ነው፡፡ 170 ኪ.ሜ ይረዝማል፡፡ በጎን እና ጎን ታጥሮ 170 ኪ.ሜትር ቀጥ ብሎ የተሰመረ የከተማ መስመር፡፡ ወደ ጎን 200 ሜትር ስፋት ያለው ሲሆን እስከ 9 ሚሊየን የሚደርሱ ነዋሪዎችን መያዝ ይችላል ተብሏል፡፡  ከተማው በጎን እና ጎን ወደ ላይ በ500 ሜትር ከፍታ ታጥሯል፡፡ አጥር ሲባል ግን በግንብ ወይ በቆርቆሮ የተሰራ አይደለም፡፡ በመስታወት ነው፡፡ ከኒዮርኩ ኢምፓየር ስቴት ጋር የሚስተካከል፤ የፓሪሱን ኤፍል ታወር በ170 ሜትር የሚበልጥ ሰማይ ጠቀስ የመስታወት አጥር፡፡ ይህ አዲስ የከተማ ሞዴል ተፈጥሯዊ ለሆኑ ነገሮች ቅድሚያ የሚሰጥ ሲሆን መቶ በመቶ ታዳሽ ሀይልን ይጠቀማል፡፡ በመሆኑም ምንም አይነት የካርበን ልቀት አይኖርም፡፡ 170 ኪሎ ሜትሩን በ20 ደቂቃ ብቻ ከጫፍ ጫፍ መመላለስ የሚችል ፈጣን የሆነ ትራንስፖርት ተሰርቶለታል፡፡ ከዚህ ትራንስፖርት ውጪ ሌላ የግል መኪናም ሆነ መጓጓዣ መጠቀም አይፈቀድም፡፡ የምን አየር መበከል ነው? ሲጀመርም ነዋሪዎች ከቤት እንደወጡ ከሆስፒታል እስከ ትምህርት ቤት፣ ከሱፐር ማርኬት እስከ መዝናኛ ስፍራ የፈለጉትን አገልግሎት በ5 ደቂቃ ብቻ ለማግኘት እንዲያስችላቸው ይደረጋል፡፡ በ5 ደቂቃ የእግር መንገድ ብቻ ሁሉንም አገልግሎት ማግኘት ይቻላል፡፡ በዚህ ስፍራ አገልግሎት የሚሰጠው በሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) በበለፀጉ አሰራሮች ነው፡፡ ላዩ ክፍት የሆነ ሲሆን የቀኑን አየር ንብረት እየለካ ሞቃቱን ወደ ቅዝቃዜ ቅዝቃዜውን ወደ ሙቀት የሚቀይር ማሽን ተገጥሞለታል፡፡ ብቻ ይህ በአለም የዘመናዊነት ታሪክ ውስጥ የራሱን ቀለም አስቀምጦ ያልፋል የተባለለት ፕሮጀክት እውን ሳውዲ ጨርሳ ታስመርቀዋለች ወይ? የብዙዎች ጥያቄ ነው! #NEOM city #the_line_project ᴅʙᴄ ᴛᴜʙᴇ ᴇᴛʜɪᴏᴘɪᴀ✅ 📸ʟɪᴋᴇ         ✍️ᴄᴏᴍᴍᴇɴᴛ      ⬅️sʜᴀʀᴇ
Show all...
👍 13 1🥰 1
ዋ! ያቺ ዓድዋ ቅጽ አንድ ዋ! .... ዓድዋ ሩቅዋ የዓለት ምሰሶ አድማስ ጥግዋ ሰማይ ጠቀስ ጭጋግ ዳስዋ ዓድዋ .... ባንቺ ብቻ ሕልውና በትዝታሽ ብፅዕና በመስዋዕት ክንድሽ ዜና አበው ታደሙ እንደገና…. ዋ! ዓድዋ የዘር ዐፅመ ርስትዋ የደም ትቢያ መቀነትዋ በሞት ከባርነት ሥርየት በደም ለነፃነት ስለት አበው የተሰውብሽ ለት፤ ዓድዋ የኩሩ ትውልድ ቅርስዋ የኢትዮጵያነት ምስክርዋ ዓድዋ የኩሩ ደም ባንቺ ጽዋ ታድማ በመዘንበልዋ ዐፅምሽ በትንሣኤ ነፋስ ደምሽ በነፃነት ሕዋስ ሲቀሰቀስ ትንሣኤዋ ተግ ሲል ሲንር ትቢያዋ ብር ትር ሲል ጥሪዋ ድው-እልም ሲል ጋሻዋ ሲያስተጋባ ከበሮዋ ሲያስገመግም ዳኘው መድፍዋ ያባ መቻል ያባ ዳኘው ያባ ነፍሶ ያባ ቃኘው ያባ በለው በለው ሲለው በለው-በለው-በለው-በለው! ዋ! .... ዓድዋ .... ያንቺን ጽዋ ያንቺን አይጣል ማስቻል ያለው አባ መቻል በዳኘው ልብ በአባ መላው በገበየሁ በአባ ጐራው በአባ ነፍሶ በአባ ቃኘው በለው ብሎ፥ በለው-በለው! ዋ! .... ዓድዋ .... ዓድዋ የትላንትናዋ ይኸው ባንቺ ሕልውና በትዝታሽ ብፅዕና በመስዋዕት ክንድሽ ዝና በነፃነት ቅርስሽ ዜና አበው ተነሡ እንደገና። ᴅʙᴄ ᴛᴜʙᴇ ᴇᴛʜɪᴏᴘɪᴀ✅ 📸ʟɪᴋᴇ         ✍️ᴄᴏᴍᴍᴇɴᴛ      ⬅️sʜᴀʀᴇ .... ዋ! .... ያቺ ዓድዋ ዓድዋ ሩቅዋ የአለት ምሰሶ አድማስ ጥግዋ ሰማይ ጠቀስ ጭጋግ ዳስዋ ዓድዋ.... ከጸጋዬ ገብረመድህን የኢትዮጵያ ባለቅኔ ሎሬት የካቲት - (፲፱፻፷፬ - ዓድዋ) ምንጭ፦ እሳት ወይ አበባ የሥነ ግጥም መድብል
Show all...
DBCTUBE ETHIOPIA

🇩 🇧 🇨 🇹 🇺 🇧 🇪 - 🇪 🇹 🇭 🇮 🇴 🇵 🇮 🇦☑ 𖣘 እንኳን ደህና መጡ ! እያልን በዚህ ቻናል ሲቆዩ ያተለያዩ የስነፅሁፍ ስራዎችን ያሚገኙ ሲሆንኑ፣ እነሱም፦ ግጥም፣ልብወለድ፣ወግ እንዲሁም አዝናኝና አስታማሪ ዝግጅቶች ያሚገኝ ሲሆን በተጨማሪም ከራስ ወጣ ያሉ ወቅታዊ ፣ የስፖርት ፣ እንዲሁም የቴክኖሎጂ መርጃዎች የምናቀርብላቹ ይሆናል። አብራቹሁን ስላላችሁ እናመሰግናለን!

👍 2🥰 2 1🔥 1
  • Photo unavailable
  • Photo unavailable
  • Photo unavailable
እንኳን አደረሳችሁ❗️❗️❗️      ዕለቱ በፈረንጆቹ ህዳር 15 ቀን 1884 ነበር፣የአውሮፓ ሀገራት መሪዎች በአሁኗ ጀርመን ዋና ከተማ በርሊን "Congo conference" በሚል ስያሜ አፍሪካን የመቀራመት እና የመከፋፈል ድስኩራቸውን ያደረጉት። በዚህ ኮንፈረንስ ላይ ማንም የአፍሪካ ሀገራት መሪዎች አልተሳተፉም። ከላይ በካርታ ለማሳየት እንደሞከርኩት ሙሉ ምዕራብ አፍሪካ፣ መካከለኛው አፍሪካን ለፈረንሳይ፣ኢትዮጵያ፣ሊቢያ እንዲሁም ኤርትራን ለጣሊያን፣በወቅቱ መጠሪያዋ Eritrean Sudan(የዚሬዋ ሱዳን) እንዲሁም ግብፅን ለእንግሊዝ በሚል ተከፋፍለው ጨረሱ፣ብዙ የአፍሪካ ሀገራት በቅኝ ግዛት ስር ወደቁ። ታሪካቸው ጠፋ፣ባህላቸው፣ቋንቋቸው ተበረዘ፣የፈረንጅ ባሪያ ሆኑ.....ብዙ ብዙ ማለት ይቻላል። ከእነዚህ ሀገራት ውስጥ ግን የምስራቅ አፍሪካዋ ፈርጥ ኢትዮጵያ ለቅኝ ግዛት እጄን አልሰጥም በማለት የወቅቱ የኢትዮጵያ ጀግኖች ጣሊያንን ሲዋጉ ቆይተው የዛሬ 128 ዓመት በአፄ ሚኒልክ የክተት አዋጅ ጥሪ አደዋ ላይ ጣሊያንን ድል ነሱ፣ምዕራባዊያንን አንገት አስደፉ፣ለሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ነፃነት በር ከፈቱ፣አርንጓዴ ቢጫ ቀዩ ሰንደንቅ የድል ማንዲራ ተብሎ ተየመ፣አብዛኛው የአፍሪካ ሀገራት ከቅኝ ግዛት ነፃ ሲወጡ አረንጓዴ ቢጫ ቀዩን ማንዲራ የሀገራቸው መለያ አደረጉ። አድዋ የአፍሪካዊያን የነፃነት ቀንዲል ችቦ ሆኖ፣ለምዕራባውያን ደግሞ የእግር እሳት ሆኖ ይኖራል፣ አድዋ ህያው ነው። ታሪክ የሌለው ህዝብ ታሪካዊ ስራ ለመስራት አይጓጓም። በታሪኩ እና በባህሉ የማይኮራ ህዝብ ደግሞ በሌሎች ዘንድ እንዲናቅ ያደረግዋል ነፃነትም የማያውቅ ህዝብ ነፃነቱን ለማግኘት አይደክምም። ኢትዮጵያ የረጅም ዘመን ታሪክ ያላት ነፃ ሀገር ስለሆነች ልጆቿ ታሪኳን ዐውቀው የነፃነቷን ጉልላት ጠብቀው/ ከተፈፀሙ ስህተቶች ተምረው እንዲኖሩ ግዴታቸው ነው። ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር፣ሰላም ለሀገራችን🕊🕊 ᴅʙᴄ ᴛᴜʙᴇ ᴇᴛʜɪᴏᴘɪᴀ✅ 📸ʟɪᴋᴇ         ✍️ᴄᴏᴍᴍᴇɴᴛ      ⬅️sʜᴀʀᴇ
Show all...
👍 1

ቅዱስ ሲኖዶስ ጥሪ አቀረበ‼️ ጥቁር ልብስ!!! ጾመ ነነዌን ምክንያት በማድረግ ጥቁር ልብስ ብቻ በመልበስ በጾምና በጸሎት ምሕላ በመያዝ ከቤተ ክርስቲያን ዓውደ ምህረት በመገኘት ወደ እግዚአብሔር ጾም፣ ጸሎትና ምሕላ እንድታቀርቡ ሲል ቅዱስ ሲኖዶስ ጥሪ አስተላለፈ። ᴅʙᴄ ᴛᴜʙᴇ ᴇᴛʜɪᴏᴘɪᴀ✅ 📸ʟɪᴋᴇ         ✍️ᴄᴏᴍᴍᴇɴᴛ      ⬅️sʜᴀʀᴇ
Show all...
👍 14🤔 3
🤔 ዓለም ላይ ችግር የሌለበት አንድም ሰው የለም ይነስም ይብዛም ሁሉም የራሱ ችግር አለበት። ነገር ግን አንዳንድ ሰዎች ላይ ችግር አብሯቸው እንደሆነ በግልፅ ይታያል አንዳንድ ሰዎች ጋር ደሞ በፍፁም የችግር ወይም የድክመት ምልክት አይታይባቸውም። ለዚህም ትልቁ ምክንያት ችግራቸውን የተቆጣጠሩበት መንገድ ነው። ዛሬ ያልመራኸው ችግር ነገ ወደ ፈለገው መንገድ ይመራሃል ወደ መጥፎ ወደ ማፈልገው ህይወት ይወስድሃል ወደ ገደል ወደ ጨለማ ያስገባካል። እናም እልሃለው ችግርክ ላይ ድክመትክ ላይ ስልጣን ያዝበት የዛኔ ድራሽዓባቱ ይጠፋል እሱ ሳይሆን አንተ ተቆጣጠረው ወደ ፈለገው ሳይሆን ወደ ፈለከው መንገድ ምራው ቀስ በቀስም ቢሆን ለችግርህ መፍትሄ ያለው ከሆን መፍትሄ ስጠው መፍትሔ የማይኖረው ከሆነ ደሞ አምነህ ተቀበለው እና ጣፋጭ ህይወትህን አጣፍጠህ ኑረው። ....🙏መልካም ቀን ይሁንልን!!🙏 ᴅʙᴄ ᴛᴜʙᴇ ᴇᴛʜɪᴏᴘɪᴀ✅ 📸ʟɪᴋᴇ         ✍️ᴄᴏᴍᴍᴇɴᴛ      ⬅️sʜᴀʀᴇ
Show all...
👍 26 5🔥 3
🎦#መልስ_የምታገኝበት_ድብቁ_ኃይል! 🔹ሁሌም ጠዋት ከእንቅልፍህ ስትነቃ ለመኖር ሌላ እድል እንደተሰጠህ አስብና ደስ ይበልህ እና ለፈጣሪህ ይሄን በለው.... 🇧🇦እንደምን ጠበቅከኝ ፈጣሪዬ? 🇧🇦ዛሬ ምን እንዳደርግ ትፈልጋለህ? 🇧🇦ለምን አላማ አቆየኸኝ? ህይወቴ የእኔ ሳይሆን ያንተ ነውና...እኔ ያገኘሁት ሳይሆን አንተ የሰጠኸኝ ነው...ራሴን ላንተ ሰጥቼሃለሁ። 🙏ዛሬን በመንገዴ ሁሉ እንድትመራኝ እለምንሃለሁ! 🙏አንተ ይገባሃል የምትለኝን ለማድረግ እወዳለሁ። 🙏እኔ ያንተ ፍቃድ ነኝና ለስህተቴ አሳልፈህ አትስጠኝ። 🙏ያለፈ ውድቀቴን እማርበት ዘንድ ብልሃቱን ስጠኝ። 🙏አላማዬን እንዳሳካ የፍርሃት ስንፍናን ከእኔ አርቅ እንድበረታ አማኝ ልብ ስጠኝ። 🙏ስለወደድከኝና ዛሬን ስላሳየኸኝ ምስጋናዬ ከፊትህ ያማረ ይሁን....ሃይሌ አንተ እንድትሆን እለምንሃለሁ። “ 🙏 ጸሎት ለሁሉም የሰው ልጅ የተሰጠ የተፈጥሮ ጸጋ ነው ምስጋና የነፍስ ምግብ ስለሆነ ስናመሰግን ውስጣችን በሀሴት ይሞላል ጸሎት የዚህ ወይም የዚያ ኃይማኖት አይደለም ..ጸሎት ለሰው ልጅ ሁሉ እኩል የተሰጠ ጸጋ ነው። ስለ ራስህ ጸልይ፣ ስለ ቤተሰብህ ጸልይ፣ ስለ አካባቢህ እንዲሁም ስለ ሀገር፣ ስለ አለም ጸልይ። ጸሎት ለውስጥህ ሰላም የሚሰጥ የጥያቄህን ሁሉ መልስ የምታገኝበት ኃይልህ ነው። ᴅʙᴄ ᴛᴜʙᴇ ᴇᴛʜɪᴏᴘɪᴀ✅ 📸ʟɪᴋᴇ         ✍️ᴄᴏᴍᴍᴇɴᴛ      ⬅️sʜᴀʀᴇ
Show all...
22👍 6💔 2👏 1
🧠brain :-ለምን እራስህን አጥፍተህ ከዚ ስቃይ አትገላገልም . . . . . 🫀heart :-ግን እናትህ ብቻዋን ትቀራለች 😔 ᴅʙᴄ ᴛᴜʙᴇ ᴇᴛʜɪᴏᴘɪᴀ✅ 📸ʟɪᴋᴇ         ✍️ᴄᴏᴍᴍᴇɴᴛ      ⬅️sʜᴀʀᴇ
Show all...
😐 21🥰 5🔥 4😇 3 2👏 2😁 2😱 2👎 1
የቻይና ሳይንቲስቶች ህጻን አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ሰሩ በቤጂንግ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት የተሰራችው ይህች አዲ ፈጠራ ለመጀመሪያ ጊዜ በአውደርዕይ ላይ ለጎብኚዎች ቀርባለች የቻይና ሳይንቲስቶች ህጻን አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ሰሩ፡፡ የወቅቱ የቴክኖሎጂ ፉክክር የሆነው አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ወይም ሰው ሰራሽ አስተውሎት በየሀገሩ አዳዲስ ፈጠራዎች ይፋ እየሆኑ ሲሆን ቻይናም የመጀመሪያውን ህጻን አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ይፋ አድርጋለች፡፡ የቤጂንግ ጠቅላላ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት የተሰራችው ይህች ህጻን ሰው ሰራሽ አስተውሎት በአውደርዕይ ላይ ለተመልካቾች ቀርባለች፡፡ ህች ህጻን ከሶስት እስከ አራት ዓመት እድሜ ካላት እውነተኛ የሰው ልጅ ጋር ተቀራራቢ አስተሳሰብ ይኖራታልም ተብሏል፡፡ አዲሱ ፈጠራ የህጻናትን ባህሪ ለማጥናት አይን ገላጭ ይሆናል የተባለ ሲሆን ህች ህጻን የራሷ የሆነ ደስታ፣ ሀዘን እና ንዴት አይነት ስሜቶች እንዳላትም ተገልጿል፡፡ የምንሞትበትን ቀን የሚተነብየው አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ከዚህ በተጨማሪም ይህች አዲስ ፈጠራ ከሰዎች ጋር መግባባት እንድትችል ተደርጋ ተሰርታለች የተባለ ሲሆን የሰዎችን አካላዊ እንቅስቃሴ እና ቃላት ልውውጥ መሰረት አድርጋ ምላሽ ትሰጣለችም ተብሏል፡፡ የቤጂንግ ጠቅላላ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት በቀጣይ ተጨማሪ ማሻሻያዎችን በማድረግ ቀስ በቀስ ሌሎች ፈጠራዎችን ይፋ እንደሚያደርግም አስታውቋል፡፡ ለዓለማችን ስጋት ሆናል የተባለው አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ጥብቅ ቁጥጥር ካልተደረገበት ለሰው ልጆች መጥፋት ምክንት ሊሆን እንደሚችል ተመራማሪዎች በተደጋጋሚ ማስጠንቀቃቸው ይታወሳል፡፡ በፈረንጆቹ 2050 ላይም 40 በመቶ የዓለማችን ስራዎች በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ እንደሚያዙ ከአንድ ወር በፊት የተካሄደው የዓለም ኢኮኖሚ ጉባኤ አስታውቆ ነበር፡፡ ᴅʙᴄ ᴛᴜʙᴇ ᴇᴛʜɪᴏᴘɪᴀ✅ 📸ʟɪᴋᴇ         ✍️ᴄᴏᴍᴍᴇɴᴛ      ⬅️sʜᴀʀᴇ
Show all...
👍 3🤯 3🤬 2👏 1
❤️ይቅጥል የምትሉ?  like 👍
Show all...
👎 7💯 6👏 5🥰 3