cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

Doctor Alle 8809/ዶክተር አለ 8809

ጤናዎን ያብዛሎ 8809 ዶክተር አለ መተኪያ ስለሌለው ጤናዎ የሀኪም መፍትሄ የሚያገኙበት የጥሪ ማዕከል 8809 ዶክተር አለ - አካላዎ ህመም - - የውስጥ ደዌ - የስነልቦና ችግር - እንዲሁም የሚያስፈልግዎ ህክምና የት ሆስፒታል እንደሚሰጥ እንጠቁምዎታለን፡፡ - የውጪ ሀገር ህክምና ለሚያስፈልጋቸው ባለን ዓለምአቀፍ ኔትዎርክ ሁሉን ያሟላ

Show more
Advertising posts
66 528
Subscribers
-1624 hours
-1447 days
-41430 days
Posts Archive
✍️ #የስንፈተ #ወሲብ #መድሐኒት #የጎንዬሽ #ጉዳት 🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹 ♥♥#በቅንነት #ሼር #ያድርጉልን♥♥ 👉👉 #የስንፈተ ወሲብ ችግር በዋናነት ወደ ብልት የሚደርሰዉ የደም ዝዉዉር እና የነርቭ ስርአት ላይ ተፅእኖ ሲፈጠር ፤በሆርሞን መዛባት እንዲሁም የጡንቻ መዛል ሲኖር ሊከሰት ይችላል፡፡ ከዚህም ጋር ተያይዞ ያለ ባለሙያ ምክር እና ትዛዝ የተለያዩ መድሃኒቶችን ሲያዘወትሩ ይስተዋላል የነዚህን መድሃኒቶች የጎንዮሽ ጉዳት 👉👉 በሚዋጥ በሚቀቡ ወይም በሌሎች መንገድ የተቀመሙ መዳኒቶች የጎንዮሽ ጉዳት 🔵 የራስ ምታት 🔵 የደም ግፈት መቀነስ 🔵 የጡንቻ ህመም 🔵 የጀርባ ህመም 🔵 ማዞር እስከ ራስ መሳት የሚያስከትል ሊሆን ይችላል 🔵 የአይን ብዥታ 🔵 የሰውነት መቅላት (መቆጣት) 🔵 የአፍንጫ ማፈን 🔵 ብልት አካባቢ ጤናማ ያልሆነ እብጠት 🔵ብልት አካባቢ ኢንፌክሽን 👉👉 #በጣም #ያልተለመዱ #ወጣ #ያሉ #የጎንዮሽ #ጉዳቶች 🔵 የብልት ከ 4 ሰአት በላይ መነሳት ይህም በብልት አካባቢ ያሉ የደም ስሮች እስከ መበጠስ ሊያደርስ ይችላል 🔵 የእይታ መጣት (አይነ ስውርነት) 🔵 የመስማት ችግር 🔵 ድንገተኛ ሞት 👉👉 ውድ የዶክተር አለ ተከታታዮች የስንፈተ ወሲብ መዳኒቶች ሙሉ ለሙሉ ከስሩ ችግሩን የማፈታ አይደለም በተጨማሪም ሌሎች ህመሞች ያለባቸው ሰዎች ይህን መዳኒት መውሰድ ፈፅሞ አይችሉም እስከ ሞት የሚያደርስ ውስብስብ ችግሮችን ይዞ ይመጣል፡፡
Show all...
✍️ #ስለ #ማር #ማወቅ #ያለብዎ #ነገሮች 🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹 ♥️♥️#በቅንነት #ሼር #ያድርጉልን♥️♥️ ⏩ ንቦች እንዴት ነው ማር የሚሰሩት? 🔺 አጀማመሩ ንብ ከአበባ ኔክታር ስትመጥ ነው። ኔክታሩን ሃኒኮምብ ወደሚባል ክፍል ወስዳ ታጠራቅማለች። እዛው በተቀመጠበት ዙሪያ ሌሎች ንቦች ሲበሩ የሚፈጥሩት የመርገብገብ ነፋስ ኔክታሩን በማድረቅ ወደ ማር ይቀይረዋል። ኔክታሩ ወደ ማር እንደተቀየረ የተቀመጠበት ሴል በሰም ይደፈናል። ንቦች አንድ ፓውንድ ማር ለማምረት 2ሚልየን አበባ መቅሰም አለባቸው። ⏩ ማር ወይስ ስኳር? 🔺 ማር ይሻላል ወይስ ስኳር አከራካሪ ርእስ ነው። ነገር ግን ማር ከስኳር የሚሻልባቸው ገጽታዎች አሉት። ማር በውስጡ ጸረኦክሲዳንቶች፣ አሚኖ አሲዶች እና ቫይታሚኖችን ይይዛል። አንድ የሻይ ማንኪያ ማር 21 ካሎሪ ሲኖረው አንድ ሻይ ማንኪያ ስኳር 16 ካሎሪ ይይዛል። ⏩ማር ሳይበላሽ ምን ያህል ግዜ ይቆያል? 🔺 ማር ረጅም ህይወት አለው። ሳይንቲስቶች ቢበላ ችግር የማያመጣ ለሺህ አመታት የተቀመጠ ማር ማግኘት ችለዋል። ማር በተዘጋ እቃ ውስጥ ከተቀመጠ በቀላሉ አይበላሽም። ማር በተፈጥሮ እርጥበቱ ዝቅተኛ ነው፣ ጠንካራ አሲዳማ ይዘት አለው፣ እንዲሁም ጸረ ባክቴሪያ ንጥረነገሮችን የያዘ ነው። በተዘጋ እቃ ደረቅ ቦታ ውስጥ በማስቀመጥ ከመበላሸት መከላከል ይቻላል። ⏩ ማር ምን ምን የጤና ጥቅሞች አሉት? 🔺 የብርድ ስሜትን ያጠፋል፡- የተለያዩ ጥናቶች እንደሚናገሩት ማር የብርድ ስሜትን ለመከላከል እንደሚጠቅም ነው። በልጆች ላይ ሳል ለመቀነስ እንዲሁም የተሻለ እንቅልፍ እንዲያገኙ ይረዳል። 🔺 ቁስልን ያድናል:- ማርን ቁስል እና ቃጠሎ ላይ መቀባት የተለያዩ ቦታዎች እንደ ባህላዊ መድሃኒት ይቆጠራል። ጥንትዊ ግብጽ ውስጥ እንደ መድሃኒት ይውል ነበር። ማር ውስጡ ባክቴሪያ የሚዋጉ፣ ቁስል የሚያድኑ፣ ኢንፌክሽን የሚከላከሉ እና እብጠትን የሚቀንሱ ንጥረነገሮችን የያዘ ነው። ነገር ግን ለጥንቃቄ ሲባል በመድሃኒት መልክ የተዘጋጀ ማርን ገዝቶ መጠቀም ይመከራል። ቁስሉ ከባድ ከሆነ ዶክተርን ማማከር ይመከራል። 🔺 የንብ መነደፍ ሲያጋጥም፡- ህመሙን ለመቀነስ እና እብጠቱን ለመቀነስ ይረዳል፡፡ 🔺 የልብን ጤንነት ይጠብቃል፡- አንዳንድ ጥናቶች እንደሚያሳዩት ማር የደም ግፊትን እና የደም ቅባትን መጠንን ይቀንሳል፤ የልብ ምትን ይቆጣጠራል፤ የጤነኛ ሴሎችን ሞት ይከላከላል፡፡ 🔺 በህፃናት ላይ የሚከሰት ሳልን ይቀንሳል፡- ከ 1 አመት በላይ ለሆኑ ህጻናት ማር እንደ ተፈጥሯዊ እና ደህንነቱ የተጠበቀ የሳል ህክምና ሊያገለግል ይችላል፡፡ 🔺 በቀላሉ በአመጋገብ ስርአታችን ውስጥ መጨመር ይቻላል፡- ማርን በመጠቀም እርጎን ወይም መጠጦችን ለማጣፈጫነት በመጠቀም፣ በብዙ የምግብ አዘገጃጀት ውስጥ እንደ አንድ ንጥረ ነገር በመጨመር፣ ከሻይ ጋር በመጠጣት እና እንዲሁም ብቻውን በመዋጥ መጠቀም ይቻላል፡፡ ⏩ አንድ አመት ያልሞላቸው ልጆች ማር መመገብ የለባቸውም። ማር በውስጡ ህጻናትን የሚያሳምም ቦቱሊዝም የተባለ ንጥረነገር ሊይዝ ይችላል፡፡ ⏩ ማር ዘርፈ ብዙ የጤና ጥቅሞች ቢኖሩትም የስኳር አይነት መሆኑን ግን አስታውሱ፤ ስለዚህ እሱን መጠቀም የደምዎን የስኳር መጠን እንዲጨምር ያደርጋል፡፡ ⏩ በተጨማሪም ከፍተኛ መጠን ያለው ማር ለረጅም ጊዜ ያለማቋረጥ መመገብ ለክብደት መጨመር አስተዋጽኦ ያደርጋል፡፡ እንደ ዓይነት 2 የስኳር በሽታ ወይም የልብ ሕመም ያሉ በሽታዎችን ይጨምራል። ስለዚህ, ከዝቅተኛ እስከ መካከለኛ አወሳሰድ ይጠቀሙ፡፡
Show all...
✍️ #ለጸጉሮት #ቀለም #ይጠቀማሉ? #እንግዲውስ #እነዚህን #ልብ #ይበሉ! 🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹 ♥♥#በቅንነት #ሼር #ያድርጉልን♥♥ የተከበራችሁ የገጻቸን ቤተሰቦች በአሁን ጊዜ ጸጉርን ለማሳመር ሲባል ብዙዎች ቀለም ይቀባሉ ወንድም ይሁን ሴት ሆኖም ግን ያለውን የጎንዮሽ ጉዳ ያተዋሉት አይመስልም እኛም እንደጤና ባለሙያ ግዴታችን ነውና እስኪ አውቃችሁ ትጠነቀቀቁ ዘንድ እነሆ አልን፡፡ 📌 ሽበት፡- የጸጉር ቀለሞች በብዛት አሞኒያ እና ፐርኦክሰሳይድ ንጥረ ነገሮች ይይዛሉ፡፡ እነዚህ ኬሚካሎች ደግሞ የጸጉር ተፈጥሯዊ ቀለምን በማሳጣት ሽበት እንዲከሰት እንዲሁም ጸጉር ሳስቶ እንዲሰባበር ያደርጋል፡ 📌 የቆዳ አለርጂ፡- የጸጉር ቀለሞች ፓራፌናይልዲአሚን የሚባል አለርጂ አምጪ ንጥረ ነገር ይይዛሉ ይህ ደግሞ ቆዳን እንዲቆጣ፣ እንዲያሳክክ እንዲሁም ቀልቶ እንዲያብጥ ያደርጋል፡፡ 📌 በእርግዝና ወቅት፡ ነብሰጡር ሴት በፍጹም የጸጉር ቀለም መጠቀም የለበትም ምክንያቱም ጽንሱን ከማስወረድ ጀምሮ እስከ ካንሰር መከሰት ስለሚዳርግ 📌 አስም፡- ልክ እንደአስም አይነት የመተንፈሻ አለርጂ ችግር ያለባቸው ሰዎች የጸጉር ቀለምን ማሶገድ የግድ ይላቸዋል ምክንያቱም በውስጣቸው የሚይዙት ኬሚካሎች ሳንባን በከባድ ሁኔታ ስለሚጎዳ ነው፡ 📌 እርግዝናን ማዘግየት፡- በእርግጥ በዚህ ዙሪያ ብዙ የተደረጉ ጥናቶች ባይኖሩም ነገር ግን እንዳንዶች እንደሚያሳዩት የጸጉር ቀለም እርግዝና ለሚጠብቁ ጥንዶች የማዘግየት ሁኔታ እንዳለው ጠቁመዋል፡፡ 📌 የአይን ደም ስሮች መቆጣት፡- አይናችን በብዙ ነገር የተከለከለ ቢሆንም ግን አሁንም ቢሆን ከሰደጋ የጸዳ አይደለም በመሆኑም የአይናችን ደም ስሮች ከሚጎዱበት ዋነኛም ምክንያቶች መሀከል የጸጉር ቀለም ዋነኛው ነው፡፡ 📌 ካንሰር፡- አንዳንድ የጸጉር ቀለም የቆዳ ካንሰር አምጪ የሆኑ ኬሚካሎችን በውስጣቸው ስለሚይዙ ጥንቃቄ ማድረግ አስፈላጊ ነው፡፡ 👉👉 በማንኛውም የጤና ጉዳይ ባለሙያ ማማከር ከፈለጉ የዶክተር አለ 8809 ሀኪሞችን ላይ እየደወሉ የየዕለቱን የጤና ላይ ለውጦችዎን በማማከር ነገ ከሚከሰት የጤና ችግር አስቀድመው ራስዎንና ቤተሰብዎን ይጠብቁ ይንከባከቡ:: 👉👉 ከጧት 2 ሰዓት እስከ ማታ 1 ሰዓት ከሰኞ እስከ ሰኞ ቢደዉሉ የዶክተር አለ ሀኪሞች ሊያማክሩዎ በመስመር ላይ ይገኛሉ!!!
Show all...
✍️ እውቁ ፀሐፊ ፓውሎ ኪሊዮ እዲህ ይላል፤ ✍️ ሰዎች እንዲረዱህ ከመጠን በላይ አትድከም ሰዎች እንደሆኑ የሚሰሙት መስማት የሚፈልጉትን ብቻ ነውና። ✍️ አንድቀን ከእንቅልፍህ ስትነቃ ጊዜህ አልቆ ልታገኘው ትችላለህ፤ ስለዚህ ልታደርገው የምትፈልገውን ነገር አሁኑኑ አድርገው። ✍️ ስኬታማ ለመሆን ከፈለክ አንድ ሕግ አክብር ፈጽሞ ራስህን አትዋሽ። ✍️ የህይወት ምስጢሩ ሰባት ጊዜ ወድቆ ስምንት ጊዜ መነሳት ነው። ✍️ ሕልምህ እንዳይሳካ የሚያደርግ አንድ መጥፎ ነገር አለ "አይሳካልኝም" የሚል ፍርሃት። ✍️ በዓለም ላይ ያለ ማንኛውም ሰው ሊገባው የሚችለው ቋንቋ አለ "ፍቅር "! ✍️ ስትሸነፍ አይደለም የተሸነፍከው በቃኝ ብለህ ስታቆም እንጂ! ✍️ ምንም ምክንያት ከማያሻቸው ነገሮች አንዱ ማፍቀር ነው። ✍️ አንድ ነገር አስታውስ ልብህ ያለበት ቦታ ሀብትህም ተቀምጧል። 🙌መልካም ቀን፤ ቸር ያሰማን፤
Show all...
✍ #በተደጋጋሚ #በሆድ #ጥገኛ #ትላትል #እጠቃለሁ #ምን #ይሻላል? 🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹 ♥♥#በቅንነት #ሼር #ያድርጉልን♥♥ ⏩ #የሆድ ጥገኛ ትላትሎች በየትኛዉም የእድሜ ክልል የሚከሰቱ ሲሆኑ በዋናነት ክብ እና ጠፍጣፋ በመባል በሁለት ይከፈላሉ፡፡የሆድ ጥገኛ ትላትሎች ወደ ሰዉነት የሚገቡት በቆዳ፣ በአፍንጫ እና በአፍ በኩል በእንቁላል መልኩ ሲሆን ወደ ሰዉነታችን ከገቡ በኃላ በአንጀታችን ላይ ይራባሉ፡፡ ⏩ #ለሆድ #ጥገኛ #ትላትል #መንስኤዎች 🔹 በንፅህና ያልተዘጋጁ ምግቦችን መመገብ 🔹 የተበከለ ዉሃ 🔹 በደንብ ያልበሰለ ምግብ መመገብ 🔹 በባዶ እግር መሄድ 🔹 የግል ንፅህና አለመጠበቅ 🔹 የበሽታ መከላከል አቅም መቀነስ 🔹 በጥገኛ ትላትሎች ከተያዙ የቤት እንስሳ ጋር መኖር ⏩ #ምልክቶች 🔹 የሆድ ድርቀት ወይም ተቅማጥ 🔹 የምግብ ፍላጎት መቀነስ/መጨመር 🔹 ማቅለሽለሽና ማስመለስ 🔹 የሆድ ህመም/ቁርጠት 🔹 በሰገራ ላይ የሆድ ጥገኛ ትላትሎችን መታየት 🔹 የሆድ መነፋት እና ጋዝ መብዛት 🔹 በፊንጢጣ ወይም ብልት ዙሪያ ማሳከክ ⏩ #የሆድ #ጥገኛ #ትላትሎችን #መከላከል #መንገዶች 🔹 ፍራፍሬዎች ከመመገብ በፊት በደንብ ማጠብ 🔹 ከመመገብ በፊት ምግብን በደንብ ማብሰል 🔹 ፈልቶ የቀዘቀዘ ወይም የተጣራ ዉሃ መጠቀም 🔹 ንፅህና መጠበቅ 🔹 ከመመገብ በፊት፣ ምግብ በሚያበስሉበት ወቅትና ከመፀዳጃ ቤት መልስ እጅን በዉሃና ሳሙና መታጠብ፤ እንዲሁም የቤት እንስሳዎችን ከነኩ በኋላ እጅን በደንብ መታጠብ፡፡ 🔹 በባዶ እግር አለመሔድ እና ንጽህናዉ በተጠበቀ/በታከመ ገንዳ ዉስጥ መዋኘት ⏩ #ህክምና 🔹ለሆድ ጥገኛ ትላትሎች መኖራቸዉ በሰገራ ምርመራ ከተረጋጋጠ በኋላ ለተገኘዉ የትላትል አይነት መድሐኒት እንዲወስዱ ይደረጋል፡፡ 👉 👉 የሆድ ጥገኛ ትላትሎች በአግባቡ ካልታከመ እና አመጋገብ ካላስተካከልን ከፍተኛ የአንጀት ጉዳት ያስከትላል፡፡
Show all...
Follow my tic toc page
Show all...
01:30
Video unavailableShow in Telegram
✍️ #ጭንቀት እና #ችግሮቹ 🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹 ♥️♥️#በቅንነት #ሼር #ያድርጉልን♥️♥️ ♥️♥️ውድ የዶክተር አለ ተከታታዮች ዛሬ ይዘን የቀረብነው ፁሁፍ ስለ ጭንቀት ሲሆን ማንም ሰው በህይወት ዘመኑ ሳይጨነቅ ሙሉ ህይወቱን ሊቀጥል አይችልም ፡፡ ጭንቀት የኑሮ አካል ነው፤ ነገር ግን ጭንቀት የበዛና ተደጋጋሚ ሲሆን ጤናን ወደሚያሰጋ ደረጃ ሊቀይር ይችላል። ከጭንቀት ጋር በተያያዘ ከስነ-ልቦና ባለሙያ ጋር ማማከር ከፈለጉ ዶክተር አለ 8809 ላይ እየደወሉ መፍትኤውን እንመካከር፡፡ 🔵 በጭንቀት ምክንያት ስለችግሩ ማሰላሰል መፍትሄ ላይ እንድንደርስ ምክንያት ሊሆን ይችላል። ነገር ግን በጭንቀት ምክንያት ማከናወን የምንፈልጋቸውን ነገሮች መፈጸም እንኳ ስንቸገር ለጤና ችግር እንጋለጣለን። 🔵 #ጭንቀት #እና #ፍርሃት #የሚከተሉትን #ባህሪዎች #ሊያስስትሉ #ይችላል 🔹 በቂ እንቅልፍ አለማግኘት 🔹 ነጭናጫ መሆን (የባህሪ ለውጥ) 🔹 ስራን በአግባቡ አለመስራት 🔹 መጠጣት እና ማጨስ 🔹 የአመጋገብ ስርአት መዛባት 🔵 #በጭንቀት ግዜ የሰውነት ሲምፓታቲክ ነርቭ ስርአት ስራት ይጀምራል። ይህም የሚከተሉት የሰውነት ለውጦች ያስከትትል ፡- 🔹 የልብ ምት መጨመር 🔹 በፍጥነት መተንፈስ 🔹 የትንፋሽ እጥረት 🔹 ማዞር 🔹 ራስ ምታት 🔹 ማቅለሽለሽ 🔹 የጡንቻ ውጥረት
Show all...
0911233656/0911799754
Show all...
03:32
Video unavailableShow in Telegram
✍✍#የጭንቀት #ምንጮች #ምንድን #ናቸው? 👉👉የጭንቀት ምክኒያቶች በርካታ ናቸው፡፡ ሆኖም በሁለት ዋና ዋና ክፍሎች ለይቶ ማየት ይቻላል፡- 1. ስነ ልቦናዊ መንስሄዎች 2. አካላዊ 1.#ከስነ #ልቦናዊ #ምንጮች፦ በስራ ቦታ በሚፈጠር የሥራ ጫና፣ የሥራ አሰራር ግልፅነት ማጣት፣ ከሚወዱት ሰው ጋር የሚፈጠር ችግር፣ መሰረታዊ የኢኮኖሚ ግዴታዎችን መወጣት አለመቻል፡- ለምሳሌ የቤት ኪራይ፣ አስቤዛ፣ ወርሃዊ የመብራት ክፍያ ወዘተ…፣ ለአዳዲስ ነገሮች መዘጋጀት፡- ለምሳሌ ልጅ መወለድ፣ አዲስን ስራ መያዝ፣ የትራፊክ መጨናነቅ፣ ከፍተኛ ድምፅ… 2. #አካላዊ #መንስሄዎች፦ ህመም፣ ከፍተኛ የአየር ሁኔታ፡- ለምሳሌ ከባድ ሙቀት ወይም ከባድ ቅዝቃዜአካላዊ ህመም፣ እንቅልፍ ማጣት፣ ከመጠን ያለፈ አልኮል መጠጣትና ሲጋራ ማጨስ በሰውነት ላይየሚፈጥሩት ጫና ወዘተ ናቸው። 👉👉የጭንቀት ውጤቶች ምንድን ናቸው? የሰውነት ድካም ከፍተኛ የራስ ምታት ብስጭት የምግብ ፍላጎት መዛባት የማስታወስ ችሎታ መቀነስ ለራስ የሚሰጥ ዋጋ ወይም ክብር መቀነስ(low self-esteem) ከማህበራዊ ህይወት መገለል የ ደም ግፊት መጨመር ትንፋሽ ማጠር የወሲብ ፍላጎት መቀነስ የእንቅልፍ መዛባት የጨጓራና አንጀት ስርዓት መዛባት የልብ ህመም የቆዳ ችግር (skin disorders) 👉👉ጭንቀት ለስነልቦናዊ ቀውሶች ለምሳሌ፡- ለፍርሃትና ለድብርት ይዳርጋል፡፡ 👉👉 ጭንቀትን ለመቆጣጠር የሚከተሉትን መፍትሄዎች ይጠቀሙ። በውስጣችን የሚያቆጠቁጠውን የተስፋ ቢስነት ስሜት ማወቅ የቁጣ ስሜቶቻችንን መለየት የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ ማኅበራዊ ሕይወት ውስጥ ንቁ ተሳትፎ ማድረግ የሚወዱትን ሥራ መሥራት አስቂኝ ፊልሞችንን መመልከት ራስን አለማማረር ባለሙያ ማማከር
Show all...
#ደም #የቀላቀለ #ሰገራ ******** ውድ የዶክተር አለ ቤተሰቦች እንዴት አደራችሁ በየትኛው የጤና ጉዳዮች መረጃ መስጠት እንዳለብን አስተያየታችሁን ጠቁሙን። እኛ ለናንተ ይጠቅማን ያልናቸውን ወደናንተ ለማድረስ ዝግጁነን !! ደም የቀላቀለ ሰግራ ማለት በየትኛውም የአንጀት ክፍል መድማት ሲያጋጥም በሰገራ መልኩ ደም ሲታይ ነው። ከተቀመጡ በኋላ ሰገራው ላይ እና የሽንት ቤት ወረቀት ላይ ደም ሲታይ ደም ሰገራ ላይ እንዳለ ይታወቃል ። #ምክንያቶቹ · የአንጀት ክፍል ላይ የወጣ ቀዳዳ መሰል ነገር(Diverticular Diseeas ) · የፊንጢጣ ኪንታሮት(Hemorrhoide) · የፊንጢጣ መሰንጠቅ(Anal fissuer) · የአንጀት መለብለብ(Colitis) · የአንጀት አካባቢ ደም ስሮች ላይ ችግር ሲኖር(Angiodysplasia) · የጨጓራ ቁስለት · አንጀት ላይ ትርፍ ስጋ መሰል ነገር ሲያድግ(Polyps) · አንጀት ካንሰር · የምግብ ትቦ ላይ ችግር ካለ(Esophageal problem) · የአንጀት ላይ ኢንፌክሽን #ምልክቶቹ አብዛኛው ሰው ምልክቶቹን ላያስተውል ይችላል ።በሌላ በኩል ደግሞ ከሚከሰቱ ምልክቶች ውስጥ * የሆድ ህመም *ማስመለስ *ድካም *ለመተንፈስ መቸገር *ተቅማጥ *ራስን መሳት *የሰውነት ክብደት መቀነስ የማሳሰሉት ናቸው። #ህክምናው _ያመጣውን ነገር በምርመራ ከተረጋግጥ ወይም ከታወቀ በኋላ መንሰኤውን ማከም _በህክምና ባለሙያዎች የሚሰጡ መድሀኒቶችን በአግባቡ መውሰድ _በፋይብር የበለጸጉ ምግቦችን መመገብ፣ ሙቅ ውሀ ላይ መዘፍዘፍ(የፊንጢጣ ኪንታሮት፣የፊንጢጣ መሰንጠቅ ከሆነ ያመጣው) እንደማጠቃለያ ደም የቀላቀለ ሰገራ በትንሽ (በቀላል) እንዲሆም ከበድ ባሉ ምክንያቶች በማንኛውም የእድሜ ክልል ላይ የሚከሰት እና ምልክቶቹ ቶሎ የማይስተዋሉ ሰለሆነ እንዳወቁ የጤና ባለሙያ ያማክሩ። 9102 ok ብለዉ በእጅ ስልክዎ በመላክ አጭር መልእክቶቻችንን በቀላሉ መከታተል ይችላሉ።
Show all...
✍️ #የአረንጓዴ #ሻይ #የጤና #ጥቅሞች ⏩ # #አረንጓዴ ሻይ ለመድሀኒትነት ለሺህ አመታት ሲጠቀሙበት ኑረዋል፣ መነሻው ከቻይና ቢሆንም በመላው ኤስያ በስፋት ጥቅም ላይ ውሏል፣ የአረንጓዴ ሻይ ከጥቁር ሻይ አንጻር ይበልጥ የጤና ጥቅሞች ያሉት በምርት ሂደቱ ምክንያት ነው:: የጥቁር ሻይ አመራረት በማብላላት መልኩ ሲሆን የአረንጓዴ ሻይ አመራረት ደግሞ የማብላላት ሂደትን በማስወገድ ነው:: በዚህም ምክንያት፣ አረንጓዴ ሻይ ከፍተኛ የሆነ የአንቲ ኦክሲዳንት እና ፖሊ_ፌኖልስ መጠን አሉት እነዚህም ነገሮች አረንጓዴ ሻይ ብዙ ጥቅሞች እንዲኖሩት ምክንያት ናቸው:: 🔺 #ክብደት #ለመቀነስ: - አረንጓዴ ሻይ ሜታቦሊዝምን ይጨምራል:: በአረንጓዴ ሻይ የሚገኘው ፖሊፌኖል የስብ ኦክሲዴሽንን የሚያጧጡፍ ስራ የሚሰራና ሰውነታችን ምግብን ወደ ካሎሪ የመቀየሩን ተግባር የሚያለሳልስ ነው:: 🔺 #ለስኳር ምግብ ከተመገብን በኋላ በደማችን ውስጥ የሚጨምረውን የግልኮስ መጠን፤ አረንጓዴ ሻይ ፍጥነቱ እንዲገታ ለማድረግ ይረዳል:: ይህም የከፍተኛ ኢንሱሊን ጡዘትንና የስብ ክምችት ማስከተሉን የሚከላከል ነው:: 🔺 #ለልብ #በሽታ ሳይንቲስቶች እንደሚያስቡት፣ አረንጓዴ ሻይ በደም ቧንቧ የላይኛው ገጻቸው ላይ ስራውን የሚሰራና፣ የደም ቧንቧወች ፋታ እንዲያገኙና ለደም ግፊት ለውጦች የተሻለ መቋቋም እንዲኖራቸው ይረዳል:: እንዲሁም ደግሞ የደም መርጋትን ይከላከላል፣ የደም መርጋት የልብ ችግር ግንባር ቀደም ምክንያት ነው:: 🔺 #የጉሮሮ #ካንሰር በጉሮሮ ካንሰር የመያዝ አደጋን የሚቀንስ ነው፣ ግን በስፋት እንደሚታወቀው የካንሰር ሴሎችን መግደል የሚችል እና በዙሪያው በሚገኙት ጤነኛ የሆኑ ቲሹዎች ላይ ጉዳት የማያደርስ ነው:: 🔺 #ኮሌስትሮል አረንጓዴ ሻይ በደም ውስጥ ያለን መጥፎ ኮሌስትሮል የሚቀንስና የጥሩውን ኮሌስትሮል ከመጥፎው ኮሌስትሮል የተሻለ የሚያመዛዝን ነው:: 🔺 #አልዛይር #እና #ፓርኪንሰን በአልዛይመር እና በፓርኪንሰን የሚመጡትን ችግሮች የሚያዘገይ እንደሆነ ይነገራል:: ጥናት እንደሚያሳየው አረንጓዴ ሻይ የአዕምሮ ሴሎችን ከመሞት የሚያድንና የተጎዱ የአዕምሮ ሴሎችን የሚጠግን ነው:: 🔺 #የጥርስ #መበስበስ ጥናቶች እንደሚያመልክቱት በሻይ የሚገኘው “ካቴቺን” የተባለው አንቲኦክሲደንት ኬሚካል የጉሮሮ መመርቀዝ፣ የጥርስ መበስበስ እና ሌሎች የጥርስ ችግሮችን የሚያስከትሉትን ባክቴሪያና ቫይረሶች የሚያወድም ነው፡፡ 🔺 #የደም #ግፊት አረንጓዴ ሻይን አዘውትሮ መጠቀም የደም ግፊት አደጋን እንደሚቀንስ ይታመናል:: 🔺 #ድብርት ቲያኒን በሻይ ቅጠሎች በተፈጥሮ የሚገኝ አሚኖ አሲድ ነው:: ይህ ንጥረ ነገር የሚያዝናና እንዲሁም የሚያረጋጋ ተጽዕኖ ያለው ሲሆን ለሻይ ጠጪወችም ላቅ ያለ ጥቅም ይሰጣል:: 🔺 #ፀረ-ቫይረስ #እና #ፀረ-ባክቴሪያል ጠንካራ ፀረባክቴሪያል እና ፀረቫይረስ ባህርይ ያለው ሲሆን ከኢንፍሉየንዛ እስከ ካንሰር ያሉ በሽታወችን በማከም ውጤታማ ናቸው:: በአንዳንድ ጥናቶችም አረንጓዴ ሻይ የአብዛኞቹን የበሽታወች ስርጭት መግታት እንደሚችል ያመላክታል:: 🔺 #ለቆዳ #ውበት አረንጓዴ ሻይ የቆዳ መጨማደድንና የማርጀት ምልክትን ለመቀነስ የሚረዳ ነው፣ ለዚህ ምክንያትም ያላቸው ፀረ-ኦክሲደንት እና ፀረ-መመረዝ ተግባር ነው:: በእንስሳት ሆነ በሰው ላይ የተደረጉት ጥናቶች እንደሚያሳዩት አረንጓዴ ሻይ በጸሀይ የሚመጣ ጉዳትን የሚቀንስ ነው:: ⏩ #ምን #ያህል #እንጠቀም? 🔺 #በቀን ውስጥ ከአንድ እስከ ሁለት የአረንጓዴ ሻይ ስኒ መውሰድ ይመከራል፡፡ 🔺 #ሌላው መጠቀስ ያለበት ጉዳይ በአረንጓዴ ሻይ ውስጥ ካፊን እንደሚገኝ ነው፡፡ ስለዚህም ለካፊን ስሜታችሁ ስስ ከሆነ አንድ ስኒ በቂያችሁ ነው:: 🔺 #አረንጓዴ ሻይ ታኒስ(የብረትን እና የፎሊክ አሲድን ውህደት የሚቀንስ) ይገኝበታል፣ ስለዚህም ነፍሰጡር ከሆንሽ ወይም ደግሞ ለማርገዝ እቅዱ ካለሽ አረንጓዴ ሻይ ለአንቺ አይሆንም:: 🔺 #አረንጓዴ ሻይን እንደ ዝንጅብልና ሌሎች ጤናማ ንጥረ ነገሮች ላይ ማዋሀድ ይቻላል ።
Show all...
✍#ስኪለስ #አዲስ #ለልጅዎ #ጥያቄ #ዘመናዊ #መልስ ! * ከራስዎ አስበልጠው #ለሚወዷቸው ልጆችዎም ሆነ ለራስዎ ፤ከዘመኑ ጋር አብሮ የዘመነ የጆሮ መብሻና የጆሮ ጉትቻዎችን እነሆ በረከት የሚልዎት ስኪለስ አዲስ ነው! *ስኪለስ አዲስ ግዙፉ #የስቴዴክስ ካምፓኒ የንግድ አጋር በመሆኑ በሀያ አራት ካራት ወርቅ የተለበጡ የጆሮ መብሻን ከጆሮ ጌጦቻቸው ጋር በልዩነት #ድንቅ በሆነ ሁኔታ በሀገራችን #ብቸኛ #ወኪል በመሆን እያስመጣ ከበቂ ልምድ ጋር በመስራት ላይ ይገኛል፡፡ *በመሆኑም #የልጆችዎን #ጆሮ ለማስበሳትም ሆነ ጉትቻዎችን ለመግዛት ወደ ስኪለስ አዲስ መጡ ማለት ሙሉ በሙሉ #ከአለርጂና በጆሮ ላይ ከሚደርሱ ማንኛውም ህመሞች ነጻ እንደሚሆኑ ዋስትና ገቡላቸው ማለት ነው፡፡ *ምን ይሄ ብቻ #ሲጫወቱም ሆነ #ሲተኙ አልያም ሲታጠቡ ወድቆ ቢጠፋባቸውስ ከሚል ስጋትም በስኪለስ አዲስ ግሩም አቅርቦትና አገልግሎት ተገለገሉም እንጂ! *ሌላስ ካሉ ፤ የስኪለስ አዲስ የአመብሻ ጌጦች የተሰሩት ከኒኬል ነፃ ስለሆነ #ማሳከክ ፣መቁሰል ማበጥ #መቆርቆርና #እንዲሁም አለርጂ የሚባል ነገር የለም። በተጨማሪም በብዙ #ወላጆች #ጥያቄ መሠረት ከአራት ወር በታች ላሉ ልጆቾ በአይነቱ ለየት ያለ #ድምፅ አልባ የጆሮ መብሻ ለአንድ ልጅ ብቻ ተጠቅመዉ የሚጥሉት መብሻ መሳሪያ አስመጥተን አገልግሎት መስጠት ጀምረናል። *ታዲያ ይሄን የመሰለ #መልካም #ዜና ስንነግርዎት ምን አሉ? ጉዞ ወደ ስኪለስ አዲስ አላሉም? ለልጆቾ በማሰብ እንዲሁም ካለዉ የስራ መደራረብ #ጨቅላ ልጆቾን ይዘዉ ወረፋ በመጠበቅ እንዳይጉላሉ እንዲሁም ከኮሮና ቫይረስ እራስዎትንም ሆነ ጨቅላ ልጆቾን ለመጠበቅ በቀጠሮ ይስተናገዱ። *ካሉበት ወደእኛ ለመምጣት ሲወስኑ ቀጠሮ እንዲያዝልዎት 0911799754 እነዚህን ቁጥሮች ይጠቀሙ። አድራሻችን ኤድና ሞል ፊት ለፊት የሚገኘዉ ቦሌ መድሀኒያለም ሞል አንደኛ ፎቅ ቁጥር 107 እንዲሁም ጋራድ ሲቲ ሴንተር ወሎ ሰፈር ምድር ላይ ቁጥር G 13። #ስኪለስ #አዲስ #የብልህ #ወላጆች #ምርጫ። ***በተጨማሪም አዳዲስ ጌጣጌጦችን በየጊዜው ስናስገባ ለምርጫ እንዲረዳዎት 👉👉 የቴሌግራም ቻናላችንን አሁኑኑ ይቀላቀሉ https://t.me/skillusjewelery
Show all...