#ደም
#የቀላቀለ #ሰገራ
********
ውድ የዶክተር አለ ቤተሰቦች እንዴት አደራችሁ በየትኛው የጤና ጉዳዮች መረጃ መስጠት እንዳለብን አስተያየታችሁን ጠቁሙን። እኛ ለናንተ ይጠቅማን ያልናቸውን ወደናንተ ለማድረስ ዝግጁነን !!
ደም የቀላቀለ ሰግራ ማለት በየትኛውም የአንጀት ክፍል መድማት ሲያጋጥም በሰገራ መልኩ ደም ሲታይ ነው። ከተቀመጡ በኋላ ሰገራው ላይ እና የሽንት ቤት ወረቀት ላይ ደም ሲታይ ደም ሰገራ ላይ እንዳለ ይታወቃል ።
#ምክንያቶቹ
· የአንጀት ክፍል ላይ የወጣ ቀዳዳ መሰል ነገር(Diverticular Diseeas )
· የፊንጢጣ ኪንታሮት(Hemorrhoide)
· የፊንጢጣ መሰንጠቅ(Anal fissuer)
· የአንጀት መለብለብ(Colitis)
· የአንጀት አካባቢ ደም ስሮች ላይ ችግር ሲኖር(Angiodysplasia)
· የጨጓራ ቁስለት
· አንጀት ላይ ትርፍ ስጋ መሰል ነገር ሲያድግ(Polyps)
· አንጀት ካንሰር
· የምግብ ትቦ ላይ ችግር ካለ(Esophageal problem)
· የአንጀት ላይ ኢንፌክሽን
#ምልክቶቹ
አብዛኛው ሰው ምልክቶቹን ላያስተውል ይችላል ።በሌላ በኩል ደግሞ ከሚከሰቱ ምልክቶች ውስጥ
* የሆድ ህመም
*ማስመለስ
*ድካም
*ለመተንፈስ መቸገር
*ተቅማጥ
*ራስን መሳት
*የሰውነት ክብደት መቀነስ የማሳሰሉት ናቸው።
#ህክምናው
_ያመጣውን ነገር በምርመራ ከተረጋግጥ ወይም ከታወቀ በኋላ መንሰኤውን ማከም
_በህክምና ባለሙያዎች የሚሰጡ መድሀኒቶችን በአግባቡ መውሰድ
_በፋይብር የበለጸጉ ምግቦችን መመገብ፣ ሙቅ ውሀ ላይ መዘፍዘፍ(የፊንጢጣ ኪንታሮት፣የፊንጢጣ መሰንጠቅ ከሆነ ያመጣው)
እንደማጠቃለያ ደም የቀላቀለ ሰገራ በትንሽ (በቀላል) እንዲሆም ከበድ ባሉ ምክንያቶች በማንኛውም የእድሜ ክልል ላይ የሚከሰት እና ምልክቶቹ ቶሎ የማይስተዋሉ ሰለሆነ እንዳወቁ የጤና ባለሙያ ያማክሩ።
9102 ok ብለዉ በእጅ ስልክዎ በመላክ አጭር መልእክቶቻችንን በቀላሉ መከታተል ይችላሉ።
👉 በሚከተሉት የማህበረሰብ ትስስር ድህረ ገጾች ይከታተሉን:-
👉የዶክተር አለ የቴሌግራም ቻናል
https://t.me/Doctoralle8809
👉 የዶክተር አለ የዩቱብ ቻነል Subscribe ያድርጉ
https://www.youtube.com/channel/UCg8YTjuR_i3pUeQ0Jexa5yQ
👉 የዶክተር አለ የዶክተር አለ 8809 የቲክቶክ ገፅ Follow ያድርጉ
tiktok.com/@doctoralle8809
👉 የዶክተር አለ የአጭር መልእክት:-
👉👉👉 9102
Show more ...
Doctor Alle 8809/ዶክተር አለ 8809
ጤናዎን ያብዛሎ
8809 ዶክተር አለ
መተኪያ ስለሌለው ጤናዎ የሀኪም መፍትሄ የሚያገኙበት የጥሪ ማዕከል 8809 ዶክተር አለ
- አካላዎ ህመም -
- የውስጥ ደዌ
- የስነልቦና ችግር
- እንዲሁም የሚያስፈልግዎ ህክምና የት ሆስፒታል እንደሚሰጥ እንጠቁምዎታለን፡፡
- የውጪ ሀገር ህክምና ለሚያስፈልጋቸው ባለን ዓለምአቀፍ ኔትዎርክ ሁሉን ያሟላ