cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ትምህርት ቤታችን ሳቅና ቁምነገር

ይሳቁ 😅😆😁 ቁምነገር ይሸምቱ

Show more
The country is not specifiedThe language is not specifiedThe category is not specified
Advertising posts
147Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

Show all...
አዲስአበባ መገናኛ አካባቢ

ልዩ መረጃ™: ለአየር ኃይል አብራሪነት እና ቴክኒሽያንነት የቅጥር ማስታወቂያ በኢትዮጵያ አየር ኃይል መቀጠር ለምትፈልጉ:_ ሀ/ አጠቃላይ የምልመላ መስፈርት 1) ከፖለቲካ ወገንተኝነት ነፃ የሆኑ 2) ከአሁን በፊት የመከላከያ ሰራዊትና የፖሊስ አባል ያልነበሩ 3) በወንጀል ይሁን በፍትሕብሔር ተከሰው ክርክር የሌለባቸው 4) ኢትዮጵያዊ የሆኑ 5) ለአየር ኃይል አብራሪነት ቢያንስ ለ10 አመት፣ ለቴክኒሻንነት ቢያንስ ለ7 አመት ለመፈረም ፈቃደኛ የሆኑ 6) ትዳር ያልመሰረቱና ልጅ ያልወለዱ 7) የጤና ምርመራ የሚያልፉ 8) በአካባቢያቸው ሕብረተሰብ ተቀባይነት ያላቸውና ከአጉል ሱሶች የራቁ 9) በሚመለመሉበት ቦታ ቢያስ በ2 አመት በነዋሪነት የታወቁ 10) ከላይ ለተጠቀሱት መመዘኛዎች ከቀበሌ መስተዳድርና ከፖሊስ የፅሁፍ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ ለ) ለአየር ኃይል ተመልማዮች አካላዊ ሁኔታ 1) ቁመት 1 ነጥብ 68 ሳ/ሜና ከዛ በላይ የሆኑ 2) ክብደት ከ55 እስከ 60 ኪ/ግ የሆኑ 3) እድሜ ከ18 እስከ 22 አመት የሆኑ ለ) የትምህርት ሁኔታ 1) በ2009 ዓ/ም የ10 ክፍል መልቀቂያ ፈተና ወስደው በሶስት የትምህርት አይነቶች ማለትም በእንግለዘኛ፣ በሂሳብና በፊዚክስ ውጤታቸው B እና ከዛ በላይ ውጤት ያላቸው 2) ዩኒቨርሲቲ ተማሪ ለሆኑ በ2011 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ወስደው የዩኒቨርሲቲ መግቢያ 300ና ከዛ በላይ ያመጡ 3) በዩኒቨርሲቲ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪ አጠቃላይ ውጤት 2 ነጥብ 6 ያላቸው 4)በአየር ኃይል አካዳሚ የሚሰጠውን Aptitude ፈተና ከ65 በላይ ማምጣት የሚችሉ 5) በአብራሪዎች ስልጠና የተዘጋጀ ቃለ መጠይቅ አጥጋቢ ውጤት ያመጡ 6) የ8ኛ እና 10 ክፍል ብሔራዊ ፈተና የወሰዱበትን ሰርተፊኬት ኦርጅናል ማቅረብ የሚችሉ 7) የትምህርት ውጤታቸውን በሀገር አቀፍ የፈተናዎች ድርጅት ለማረጋገጥ ፈቃደኛ የሆኑ ሐ/ ለአውሮፕላን ጥገና ተመልማዮች 1) ቁመት ከ1 ነጥብ 65 ሴ/ሜ በላይ 2) ክብደት ከ50 እስከ 60 ኪ/ግ 3) ከ18 እስከ 22 አመት መ) የትምህርት ሁኔታ 1) በ2010 እና በ2011 ዓ/ም የትምህርት ዘመን የ10 ክፍል ብሔራዊ ፈተና ወስደው በእንግሊዘኛ፣ ሂሳብና ፊዚክስ ውጤታቸው C እና ከዛ በላይ የሆኑ፣ አጠቃላይ ውጤት 2 ነጥብ 4 እና ከዛ በላይ ያላቸው 2) በ2011 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል የመሰናዶ ፈተና ወስደው አጠቃላይ ውጤት 270ና ከዛ በላይ ያላቸው 3)በአየር ኃይል አካዳሚ የወታደራዊና አካል ብቃት ትምህርት ቤት የሚሰጠውን የሳይኮሜትሪክ ፈተና ማለፍ የሚችሉ 4) የ8፣10 እና 12 ብሔራዊ ፈተና ያለፉበትን ኦርጅናል ማቅረብ የሚችሉ፣ በሀገር አቀፍ ፈተናዎች ድርጅት ለማረጋገጥ ፈቃደኛ የሆኑ የምዝገባ ቦታና ጊዜ:_ ለአዲስ አበባ:_ጦር ኃይሎች ፊት ለፊት ከሚገኘው ምድር ኃይል ግቢ ማደ/ማስ/ ቢሮ አማራ ክልል:_ ባሕርዳር፣ ጎንደርና ደሴ ለኦሮሚያ ክልል:_ ባሌ ሮቤ፣ ጅማ፣ ነቀምቴ፣ ደብረዘይት የሌሎች ክልሎች:_በየ ክልሎቹ ዋና ከተሞች የምዝገባ ጊዜ ከታህሳስ 15/2013 እስከ ታህሳስ 30/2013 ዓ/ም ለበለጠ መረጃ 0114330636 መደወል ትችላላችሁ!! https://t.me/joinchat/AAAAAEyYjxSHWM66afKljA @LiyuMereja
Show all...
ልዩ መረጃ ™

#ልዩ_መረጃ | #ቀዳሚ_ምርጫዎ ➠ ፈጣን እና ተዐማኒ መረጃ ➠ወቅታዊ መረጃዎች ➠ልዩ ልዩ ዘገባዎች ➠ የስፓርት እና መዝናኛ ዜናዎች ➠ጠቃሚ ጥቆማዎች ይደርሶታል። አብራችሁን ስላላችሁ እናመሰግናለን። ለማንኛውም መረጃ ➥ @LiyuMerejaBot PROMOTION ➥ @Liyu_adsBot 🎬 "ተመራጭ የዜና ምንጭ" News & Media Channel®

'ጩኸቱ በጠበጠኝ" በሚል አውራ ዶሮ ተኩሶ የገደለው በእስር ተቀጣ‼️ ↘️ ፈረንሳይ ውስጥ አንድ ግለሰብ 'ጩኸቱ በጠበጠኝ' በሚል ሰበብ የጎረቤቱን ዶሮ ተኩሶ በመግደሉ በአምስት ወራት እስራት ተቀጥቷል። ↘️ ሰውዬው አውራ ዶሮውን ተኩሶ መግደሉ አልበቃ ብሎት በፌሮ በሳስቶታል ተብሏል። ↘️ ማርሴል የሚል መጠሪያ የነበረው አውራ ዶሮ የተገደለው ባለፈው ግንቦት ወር ላይ ነበር።ገዳዩ ግለሰብ አውራው ዶሮ ከአቅሙ በላይ እየጮኸ ሰላሜን ነስቶኛል በሚል ምክንያት ነው ድርጊቱን የፈፀመው ተብሏል። ↘️ የማርሴል ባለቤት የሆነው ሴባስቲያን ቨርኒ 'ፍትህ ለአውራ ዶሮዬ' በሚል በበይነ መረብ ፊርማ ማሰባሰብ ጀምሯል።እሳካሁን ድረስ ከ100 ሺህ በላይ ሰዎች 'ፍትህ ለማርሴል' ሲሉ ፊርማቸውን አሳርፈዋል። ↘️ ገዳዩ የጎረቤት እንስሳ ላይ ግፍ በመፈፀምና በሌሎች ወንጀሎች ጥፋተኛ ሆኖ ተገኝቷል። ከተፈረደበት የአምስት ወራት እስር በተጨማሪ 300 ዩሮ እንዲቀጣ ዳኛው ፈርደውበታል። ↘️አውራ ዶሮ በጭካኔ ገድሏል የተባለው ግለሰብ ለሚቀጥሉት ሶስት ዓመታት ማንኛውንም ዓይነት የጦር መሣሪያ እንዳይዝም ታግዷል። ↘️ ለአውራ ዶሮው ፍትህ ፊርማ እያሰባሰበ ያለው ሴባስቲያን ግን "ምንም ቢሆን አውራ ዶሮዬ ላይ የተፈፀመውን ግፍ አይመልስልኝም" ኤኤፍፒ ለተሰኘው የዜና ወኪል ድምፁን አሰምቷል። አውራ ዶሮው በመገደሉ ምክንያት እሱና ቤተሰብ ከፍተኛ ሃዘን ላይ እንዳሉም ተናግሯል ሴባስቲያን።
Show all...
Fana News (FBC): የጥሪ ማስታወቂያ‼️ ለዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ የ2012 ዓ.ም ተመራቂ ለነበራችሁ ተማሪዎች በሙሉ:- ↘️ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒሰቴር በቅርቡ ባደረገው ግምገማ፣ በኦሮና ቫይረስ ወረርሺኝ ምክንያት በ2012 ዓ.ም ተቋርጦ የነበረው የዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ መማር ማስተማር ፣ ተማሪዎች በተለያዩ ሁሮች ወደ ትምህርት ገበታቸው እየተመለሰ መማር ማስተማሩ እንዲቀጥል አቅጣጫ ተቀምጧል፡፡ ↘️በዚህ መሰረት የዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ የመጀመሪያ ድግሪ መደበኛ የ2012 ዓ.ም ተመራቂ የነበራችሁ ተማሪዎች ብቻ የመግቢያ ግዜ ጥቅምት 23 እና 24፣ 2013 ዓ/ም እንዲሁም፣ ትምህርት የሚጀምርበት ቀን ጥቅምት 25 ፣ 2013 ዓ/ም መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
Show all...
Fana News (FBC): ወልዲያ ዩኒቨርሲቲ ተመራቂ ተማሪዎቹን ጠርቷል‼️ ↘️በ2012 ዓ.ም በወልድያ ዩኒቨርሲቲ ተመራቂ ለነበሩ መደበኛ ተማሪዎች ብቻ ዩኒቨርሲቲው የምዝገባ ቀን ከጥቅምት 25- 26/2013 ዓ.ም መሆኑን አስታውቋል፡፡ ↘️ ከተጠቀሱት ቀናት ቀድሞም ሆነ ዘግይቶ የሚመጣ ተማሪ የማያስተናግድ መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አስታውቋል፡፡ ↘️በተጨማሪም የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር በሚሰጠው አቅጣጫ መሰረት የሚሻሻል ወይም የሚቀየር ነገር ካለ ዩኒቨርሲቲው በማህበራዊ ትስስር ገጾቹ የሚያሳውቅ መሆኑን ገልጿል፡፡
Show all...
D/R LIA TADDESE ✪: ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገው 8,024 የላብራቶሪ ምርመራ 865 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ የ9 ሰዎች ህይወት አልፏል። በተጨማሪ በትላንትናው ዕለት 668 ሰዎች አገግመዋል። በአጠቃላይ በሀገራችን በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች 82,662 የደረሱ ሲሆን የሟቾች ቁጥር 1,271 ደርሷል ፤ ከበሽታው ያገገሙ አጠቃላይ ሰዎች ቁጥር ደግሞ 37,102 ደርሷል።
Show all...
Fana News (FBC): ሰበር ዜና‼️ የአሜሪካው ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ እና ቀዳማዊት እመቤት ሜላኒያ ትራምፕ በኮሮናቫይረስ መያዛቸው ተረጋገጠ። ዶናልድ ትራምፕ የቅርብ አማካሪያቸው በኮሮናቫይረስ መያዟን ተከትሎ እርሳቸው እና ቀዳማዊት እመቤት ሜላኒያ ትራምፕ የኮሮናቫይረስ ምርመራ አድርገው ውጤቱን በመጠባበቅ ላይ እንገኛለን ብለው ነበር። የምርመራውን ውጤቱን ተከትሎ እርሳቸው እና ባለቤታቸው በቫይረሱ መያዛቸውን ዶናልድ ትራምፕ በትዊተር ገጻቸው ላይ ይፋ አድርገዋል።
Show all...
D/R LIA TADDESE ✪: #COVID19Ethiopia በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገው 6,475 የላብራቶሪ ምርመራ 730 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ የ7 ሰዎች ህይወት አልፏል። በተጨማሪ በትላንትናው ዕለት 226 ሰዎች አገግመዋል። በአጠቃላይ በሀገራችን በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች 76,098 የደረሱ ሲሆን የሟቾች ቁጥር 1,205 ደርሷል ፤ ከበሽታው ያገገሙ አጠቃላይ ሰዎች ቁጥር ደግሞ 31,430 ደርሷል።
Show all...
D/R LIA TADDESE ✪: #COVID19Ethiopia በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገው 6,139 የላብራቶሪ ምርመራ 784 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ የ7 ሰዎች ህይወት አልፏል። በተጨማሪ በትላንትናው ዕለት 199 ሰዎች አገግመዋል። በአጠቃላይ በሀገራችን በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች 75,368 የደረሱ ሲሆን የሟቾች ቁጥር 1,198 ደርሷል ፤ ከበሽታው ያገገሙ አጠቃላይ ሰዎች ቁጥር ደግሞ 31,204 ደርሷል።
Show all...