en
Feedback
ዶ/ር ሶፎንያስ ኤርምያስ_Dr Sofonias Ermias

ዶ/ር ሶፎንያስ ኤርምያስ_Dr Sofonias Ermias

Open in Telegram

ጤና ነክ ጥያቄ ካለዎት፣ በጽሑፍ በቴሌግራም ብቻ ይሄንን➡️  t.me/Dr_Sofonias በመጫን ያስቀምጡልኝ ሙያዊ ምላሽ ለመስጠት ጊዜ ሊወስድብኝ ስለሚችል፣ በትዕግስት ይጠብቁኝ ​📢 ለማስታወቂያ/ስፖንሰርሺፕ: ​ለስፖንሰርሺፕና ምርትዎ በሙያዊ ምክር እንዲተዋወቅ ከፈለጉ፣ ይሄንን ➡️ t.me/MASTAWKIYA በመጫን ያናግሩን

Show more

📈 Analytical overview of Telegram channel ዶ/ር ሶፎንያስ ኤርምያስ_Dr Sofonias Ermias

Channel ዶ/ር ሶፎንያስ ኤርምያስ_Dr Sofonias Ermias (@drsofonias) in the Amharic language segment is an active participant. Currently, the community unites 19 989 subscribers, ranking 1 154 in the Medicine category and 1 680 in the Ethiopia region.

📊 Audience metrics and dynamics

Since its creation on невідомо, the project has demonstrated rapid growth, gathering an audience of 19 989 subscribers.

According to the latest data from 25 June, 2026, the channel demonstrates stable activity. Although there has been a change in the number of participants by -558 over the last 30 days and by -23 over the last 24 hours, overall reach remains high.

  • Verification status: Not verified
  • Engagement rate (ER): The average audience engagement rate is 22.78%. Within the first 24 hours after publication, content typically collects 5.94% reactions from the total number of subscribers.
  • Post reach: On average, each post receives 4 556 views. Within the first day, a publication typically gains 1 188 views.
  • Reactions and interaction: The audience actively supports content: the average number of reactions per post is 11.

📝 Description and content policy

The author describes the resource as a platform for expressing subjective opinions:
ጤና ነክ ጥያቄ ካለዎት፣ በጽሑፍ በቴሌግራም ብቻ ይሄንን➡️  t.me/Dr_Sofonias በመጫን ያስቀምጡልኝ ሙያዊ ምላሽ ለመስጠት ጊዜ ሊወስድብኝ ስለሚችል፣ በትዕግስት ይጠብቁኝ ​📢 ለማስታወቂያ/ስፖንሰርሺፕ: ​ለስፖንሰርሺፕና ምርትዎ በሙያዊ ምክር እንዲተዋወቅ ከፈለጉ፣ ይሄንን ➡️ t.me/MASTAWKIYA በመጫን ያናግሩን

Thanks to the high frequency of updates (latest data received on 26 June, 2026), the channel maintains relevance and a high level of publication reach. Analytics show that the audience actively interacts with content, making it an important point of influence in the Medicine category.

19 989
Subscribers
-2324 hours
-1207 days
-55830 days
Posts Archive
የቆዳ ቀለም ለምን በከፊል መልኩን ይቀይራል? ቆዳዎት ላይ በከፊል እየጠቆረ ተቸግረዋል? ይህ ምን አልባት በህክምናው ሀይፐርፒግመንቴሽን (Hyperpigmentation) እየተባለ የሚጠራው ችግር ሊሆን ይችላል። ሀይፐርፒግመንቴሽን (Hyperpigmentation) የቆዳ በከፊል (ከሌላው የሰውነት የተፈጥሮ ቆዳችን በተለየ) መልኩን የመቀየር ችግር ነው። ☑️ ችግሩ ለምን ይከሰታል? ይህ አይነቱ የቆዳ ችግር የሚከሰተው ለቆዳ እና ለጸጉራችን የተፈጥሮ ቀለማቸውን እንዲይዙ የሚያደርገው ሜላኒን (melanin) በተወሰነ የቆዳችን ክፍል ላይ ከመጠን በላይ ሲበዛ ነው። ይህ በእንዲህ እንዳለ የቆዳ ቀለም በከፊል መቀየር በተለያዩ ምክንያቶች ሊፈጠር ይችላል። ከነዚህም መካከል:- 🔹 አዲሰንስ በሽታ (Addison’s Disease):- ይህ ህመም ሲከሰት የአድሬናል እጢ ላይ ጉዳት ያስከትላል፣ ይህም በተራው ሜላኒን በብዛት እንዲመረት ተጽዕኖ ስለሚያደርግ ቆዳችን ላይ የተለያዩ ጥቋቁር ምልክቶች ይከሰታሉ። 🔸 ሜላስማ (Melasma (Mask of Pregnancy)):- ይህ በእርግዝና ጊዜ በሚኖር የሆርሞን መለዋወጥ የሚከሰት የቆዳ ቀለም ለውጥ ነው። 🔹 የጸሀይ ብርሃን የሚያስከትለው ጉዳት (Sun Damage):- ቆዳችን ለረጅም ጊዜ ለጸሀይ ብርሃን ሲጋለጥ የቆዳችን የተፈጥሮ ቀለም በከፊል የመቀየር ችግር (Hyperpigmentation) ሊያጋጥመን ይችላል። ☑️ እንዴት እንከላከል? 🍀 የጸሀይ ብርሃን በተቻለ መጠን በቀጥታ ቆዳችንን እንዳያገኝ እንጠንቀቅ 🍀 ችግሩ በተደጋጋሚ የሚያጋጥማቸው ሰዎች በጸሀይ ኮፊያ እንዲጠቀሙ ይመከራል 🍀 እንደ SPF (Sun Protection Factor) ያሉ የፊት የጸሀይ ጨረር መከላከያ ቅባቶችን (Sun Screen) መጠቀም ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ የጤና መረጃ ለማግኘት፤ በፌስቡክ 👇 https://www.facebook.com/DrSoffonias በቴሌግራም 👇 @DrSofonias

በርግጥ እነዚህ በ40ዎች የእድሜ ክልል ውስጥ ለሚገኙ ሴቶች ከባድ መርዶ ናቸው፡፡ ምክንያቱም በዚህ እድሜ ላይ ልጆች አድገው ትልልቅ የሚሆኑበትና ራሳቸውን የሚችሉበት ስለሚሆን ሴቶች ተንፈስ የሚሉበት የወሲብ ነፃነት የሚያገኙበት፡፡ ሰውነተቻውን እንዴት ለወሲብ ዝግጁ እንደሚያደርጉበት የሚያቁበት ጊዜ ነው፡፡ ሌላው በዚህ ጊዜ እድሜአቸውም ወደ 51 ስለሚጠጋ ያርጣሉ፡፡ ያኔ ደግሞ የወሊድ ስጋት ስለማይኖርባቸው የወሊድ መቆጣጠሪያ መውሰድ አለብኝ ብለው አይጨነቁም፡፡ በወሊድ መቆጣጠሪያ ምክንያት የሚመጣ የወሲብ ፍላጎት አለመነሳሳት ችግር አያሰጋቸውም፡፡ ☑️ ምክር በ40ዎቹ የእድሜ ክልል ለሚደረጉ ወሲቦች “ሰውነትዎ በዝግመተ ለውጥ ፍላጎት እና ምላሽ እንደሚሰጥ ተስፋ በማድረግ፡፡ ከሰውነትዎ ጋር ድጋሚ ለመተዋወቅና ግንኙነት ለመፍጠር መሞከርና የማይቻለውን መቀበል በዚያ ደስታን ለማግኘት ያስችልዎታል፡፡ በብልት መድረቅና ማረጥ የሚፈጥሩት የጎንዮሽ ጉዳት ከረበሽዎ የስነተዋልዶ ጤና ዶክተር ያናግሩ፡፡ “ፕሮጄስትሮን ወይም ቴስቶስትሮን ወይም አልያም ሁለቱንም የሚደረግ ሕክምና በአንዳንድ ሴቶች ላይ የጾታ ስሜትን ለማሻሻል ይረዳል። ሆኖም ግን ልብ ይበሉ እያጋጠምዎት ያለው ነገር በቀላሉ የእርጅና ተፈጥሯዊ አካል ሊሆን እንደሚችል፣ ስለዚህ ጤናማ በመሆን እና ከአጋርዎ ጋር የመሆን ፍላጎትን በማምጣት የወሲብ ፍላጎት አነቃቂቅ ቅመምዎን ከፍ ማድረግ ይችላሉ፡፡” ትላለች ፍራንሲስ። መልካም ጤንነት!! ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ የጤና መረጃ ለማግኘት፤ በፌስቡክ 👇 https://www.facebook.com/DrSoffonias በቴሌግራም 👇 @DrSofonias

የወሲብ ፍላጎትዎ በእድሜዎ መለዋወጥ ውስጥ ምናልባት ረዥም ጊዜዎን በስራ በማሳለፍዎ አልያም ከጓደኛዎ ጋር በመሰላቸትዎ በወሲብ ፍላጎትዎ ላይ ለውጥ ሳያስተውሉ አይቀሩም፡፡ ነገር ግን በቀላሉ ሊያስተውሉት የማይችሉት አንድ ጉዳይ ግን እድሜዎ እየገፋ በሄደ ቁጥር የወሲብ ፍላጎትዎን የሚያነቃቃውም ቅመምም በዚያው መጠን እየቀነሰ እንደሚሄድ ነው፡፡ “የወሲብ ፍላጎት መቀነስ ከእድሜ መጨመር ጋር ተያይዞ ይፈጠራል” ይላሉ በAustin, Texas የሴቶች ስነተዋልዶ ጤና ዶክተር የሆኑት John Thoppil, MD፡፡ እርግጥ ነው የ29 አለያም የ39 ዓመት ልደትዎን ካከበሩ በኋላ የወሲብ ፍላጎትዎን የሚያነቃቃው ቅመም እየቀነሰ መሄዱን ላያስተውሉት ይችላሉ፡፡ ምክንያቱም ይህን ችግር እንዲከሰቱ ከሚያደርጉ ምክንያቶች መካከል እንደ ሆርሞን ለውጥ፣ እርግዝና እና የቤተሰብ ሃላፊነቶች መጨመር ከ20ዎቹ የእድሜ ክልል ወደ አርባዎቹ ሲሸጋገሩ የሚከሰቱ ጉዳዮች በመሆናቸው ነው፡፡ ☑️ የወሲብ ፍላጎትዎን የሚያነቃቃው ምንድን ነው? አንደ ባዮሎጂያዊ፣ ሥነ-ልቦናዊ ጉዳዮች ያሉ በርካታ ምክንያቶች የወሲብ ስሜትዎ በማንኛውም ጊዜ ዝግጁ አልያም የሆነ ዘመን ላይ ተገትሮ እንዲቀር ተጽዕኖ ያሳድራሉ፡፡ በOrlando, Florida BodyLogicMD የሴቶች ስነተዋልዶ ጤና ዶክተርና የህክምና ባለሙያዎች አለቃ የሆነችው Jennifer Landa “ጭንቀት ዋነኛው የወሲብ ፍላጎት ገዳይ ነው” ስትል Dr. Thoppil በበኩላቸው “ጭንቀት እና ድብርት እንዲሁ የወሲብ ፍላጎትን ገደል ከሚከቱት ውስጥ ይቀመጣሉ፡፡ በሚያሳዝን ሁኔታ ደግሞ እነዚህን በሽታዎች የሚያድኑ ብዙ ፀረ-ድብርት መድኃኒቶች እንዲሁም ሌሎች መድኃኒቶች የጾታ ስሜትንም የመግታት የጎንዮሽ ጉዳትም አላቸው፡፡” ይላሉ፡፡ ዶክተሩ አክለውም “በርግጥ ለተጓዳኝዎና ስለፍቅር ግንኙነትዎ ያለዎት ስሜትም የወሲብ ፍላጎትዎን በደንብ ይጎዳሉ፡፡ በተለይ ወሲብን ቅድሚያ የሚያስቀምጥ ጠንካራ ግንኙነት ያላቸው ሰዎች የወሲብ ፍላጎታቸውን የሚያነቃቃውን ቅመም ስራውን በደንብ እንዲሰራ ያደርጉታል፡፡” ብለዋል፡፡ ዶክተር Landa በበኩሏ “የእርስዎ የአኗኗር ዘይቤ. ጤናማ ልምዶች፣ የተመጣጠነ ምግብ መመገብ፣ አዘውትሮ መሥራት እና በቂ እረፍት ማግኘት በስሜትዎ እንዲሁም በአጠቃላይ ጤናዎ ላይ ተጽዕኖ ያሳድራሉ፡፡ ሌላው ሆሮሞኖች በወሲብ ፍላጎት መቀነስ ላይ ትልቁን ድርሻ ይወስዳሉ፡፡ ሴቶች በጥቂቱም ቢሆን ያላቸው ቴስቴስተሮንን ጀምሮ ኢስትሮጂን፣ ፕሮጄስትሮን የመሳሰሉ በወሲብ ፍላጎት፣ መነቃቃትና እርካታ ላይ ትልቅ ተፅዕኖ የሚያሳድሩ ሆርሞኖች ወደ ሀያዎቹ ሲዘልቁ በተፈጥሮ እየቀነሱ ይሄዳሉ፡፡” ትላለች፡፡ በፊላደልፊያ ነዋሪ የሆነው የግንኙነት ቴራፒስት እና ደራሲ ሻዲን ፍራንሲስ “ወሲብ ስለ ማንነታችን፣ ስሜታችን፣ ፍላጎታችን እና ድርጊታችን የተብራራ ኮክቴል ነው” ሲል ይናገራል፡፡ ምንም “መደበኛ” ባይኖርም የተወሰኑ ሊገመቱ የሚችሉ አዝማሚያዎች ግን ወደ 20ዎቹ፣ 30ዎቹ እና 40ዎቹ የእድሜ ክልል የመሄድ ዝንባሌ አላቸው፡፡ ☑️ የወሲብ ፍላጎትዎ በ20ዎቹ የእድሜ ክልል ልክ እንደሌላው የሰውነትዎ ክፍል ፍላጎትና ተግባራት ሁሉ ዕድሜዎ 21 ወይም 28 ሲሆን የወሲብ ፍላጎትዎ በጣም ጠንካራ ነው፡፡ ዶክተር Landa ይህን ስታብራራ እንዲህ ትላለች “በተለያዩ ምክንያቶች ለምሳሌ ግንኙነቱ ገና አዲስ በመሆኑ አልያም ለመራባት ያለ ባዮሎጂካዊ ምክንያት የተነሳ በ20ዎቹ እድሜ ውስጥ ያለ የወሲብ ፍላጎት አጅግ ከፍተኛ ነው፡፡” ዶክተር Landa በ20ዎቹ ውስጥ ለሚያደርጉት ጥሩ ወሲባዊ ግንኙነት እንዲህ በማለት ትመክራለች “ምናልባት የወሲብ ፍላጎትዎ ዝቅተኛ ከሆነ ምናልባት በወሊድ መቆጣጠሪያ ምክንያት የተከሰተ ሊሆን ይችላል፡፡ በርግጥ ይህ በሁሉም ሰው ላይ ላይከሰት ይችላል፣ ነገር ግን አንዳንድ ሴቶች በክኒኑ ላይ ዝቅተኛ የወሲብ ቴስትስተሮን መጠን ይታይባቸዋል፣ ይህም ወደ ዝቅተኛ የወሲብ አነቃቂ ቅመም መፈጠርና አልፎ ተርፎም በአንዳንድ ወጣት ሴቶች ላይ ወደ ብልት መድረቅ ሊያስከትል ይችላል፡፡ ለዚህ ደግሞ መፍትሄው ሌላ የጤና ችግርን መኖሩን መመርምርና አማራጭ የወሊድ መቆጣጠሪያ ዘዴ መምረጥ ተገቢ ነው፡፡" ትላለች፡፡ ☑️ የወሲብ ፍላጎትዎ በ30ዎቹ የእድሜ ክልል በዚህ እድሜ ውስጥ ለአካላዊ ቅርርብ ያለዎት ፍላጎትዎ ከቀነሰ፣ አይደነቁ፡፡ ለጀማሪዎች በዚህ እድሜ ቴስቴስትሮን እየቀነሰ ይሄዳል፡፡ በዚህ ጉዳይ ላይ ዶክተር Landa “ይህ በተፈጥሮ የጾታ ፍላጎትዎንም እንዲቀንስ ሊያደርግ ይችላል፡፡ 30ዎቹ የእድሜ ክልል ማለት አብዛኛውን ጊዜ ለሴቶች ሥራ የበዛበት አስር ዓመት ማለት ነው፡፡ ስራን በማጠናከር፣ ወጣት ልጆችን መንገድ በማስያዝ፣ እንደ ህፃናት ልጆች አስተዳደግ ያሉ ኃላፊነቶች የሚደራረቡበት አድካሚ ወቅት ስለሆነ ብዙ ሴቶች ማታ ማታ ወሲብ ከማድረግ ይልቅ ጥቅልል ብለው እንቅልፋቸውን መተኛት ይመርጣሉ” ይላሉ። ስለ አስተዳደግ ስናወራ፣ 30ዎቹ የእደሜ ክልሎች ህፃናትን በወጉ የምንቀርፅባቸው የመጀመሪያዎቹ አስርት ዓመታት ናቸው፡፡ በእያንዳንዱ ሶስት ወር እና ከዚያ በኋላ ጡት በምናጠባበት ማጥባት ወቅት የሚከሰት የሆርሞን ለውጥ እንዲሁ የፍላጎት እጥረት ያስከትላል፡፡ ☑️ በ30ዎቹ ዕድሜ ውስጥ ለሚደረጉ ወሲባዊ ግንኙነቶች ምክር ምንም እንኳን በእነዚያ ምሽቶች በእጅ ከመተሻሸት ያለፈ ነገር ማደርግ በማይፈለጉባቸው ምሽተች ጊዜ እንኳን ከጓደኛዎ ጋር በግልጽ በመነጋገር፣ ፍላጎቶችዎን መግለጽ እና መደራደር መቻልና የሚስጥሩን ቋጠሮ በመፍታት አጠቃላይ ግንኙነትዎን የጠበቀ እንዲሆን ማደረግ ይገባዎታል፡፡ ምክንያቱም በዚህ እድሜ የወሲብ ፍላጎትዎ ከተቀየረ ለእርስዎ እና ለባልደረባዎ ግራ የሚያጋባ ሊሆን ይችላልና፡፡ እንዲሁም ጭንቀት በጠበቀ ቅርበት ውስጥ ሊገባ የሚችል ሊፈጥረው የሚችለውን ተጽዕኖን ዝቅ አድርገው አያስቡት፡፡ “ውጥረት ቴስትሮንሮን ሊያጠፋ እና ቴስቶስትሮን ውስጥ ጣልቃ የሚገባውን ኮርቲሶል ከፍ ያደርገዋል” የምትለው ሊንዳ ውጥረትን ለመቀነስ እንደመጀመሪያ ደረጃ መፍትሄ ዮጋ እና ሜዲቴሽን ያሉ ነገሮችንም እንድንሞክር ትመክራለች፡፡ ሌላው በ20 ዎቹ ዕድሜዎ ውስጥ ያደርጉት እንደነበረው ያለ የግብረ ሥጋ ግንኙነት የማይፈጽሙ ከሆነ ብዙ መሥራት አለመፈለግም ብልህነት ነው፡፡ በ 30 ዎቹ ዕድሜዎ ውስጥ ከሚረጋጋ አጋር ጋር የመረጋጋት ዕድሉ ሰፊ ነው፡፡ ምንም እንኳን የወሲብ ግንኙነት ብዙም ተደጋጋሚ ባያደርጉም፣ ጥራት እና ጥልቀት ባለው ግንኙነት ማካካስ ይችላሉ፡፡ ☑️ የወሲብ ፍላጎትዎ በ40ዎቹ የእድሜ ክልል ይህ ጊዜ የሴቶች የማረጫ ወቅት በመሆኑ ከፍተኛ የሆርሞን ለውጥን ያስከትላል፡፡ በዚህ ጊዜ የሆርሞንዎ መቀነስ የተለመደ ነው፡፡ ከማረጥዎ አምስት ወይንም አስር አመታት ባለው ጊዜ ውስጥ ኦቫሪዎ ኢስትሮጂን ማምረቱን ቀስበቀስ ያቆማል፡፡ እነዚህ ተለዋዋጭ ሆርሞኖች በጾታዊ ስሜትዎ፣ በስሜትዎ፣ እና በወሲብ ስሜትም ሆነ በአካል ምን ላይ ተጽዕኖ ያሳድራሉ፡፡ ምክንያቱም የኢስትሮጅንን ምርት በሚቀንስበት ጊዜ ተፈጥሮአዊው የሴት ብልት ቅባትዎ እንዲሁ ሊቀንስ ይችላል፡፡ ይህም በወሲብ ጊዜ ህመም ያስከትላል፡፡ ሌላው ዶክተር Landa “የሚያረጋጋ” ሆርሞን ብለው የሚጠሩት የፕሮጄስትሮን መጠን መቀነስም “ከባድ የወር አበባዎች፣ ክብደት መጨመር፣ ስሜታዊነት፣ እንቅልፍ ማጣት እና ብስጭት ያስከትላል” ትላለች፡፡

እርጉዝ ለመሆን ምን ያህል ጊዜ የግብረ ሥጋ ግንኙነት ማድረግ አለብዎት? ምናልባት እድለኛ ከሆኑ በመጀመሪያ ሙከራዎ ሊያረግዙ ይችላሉ። ነገር ግን ለአንዳንድ ጥንዶች ተጨማሪ ጊዜ ሊጠይቅ ይችላል። ታዲያ በሚያስገርም ሁኔታ ሳይንስ ጥንዶች በተደጋጋሚ ወሲብ ቢፈፅሙ የማርገዝ እድላቸውን ማስፋት ይችላሉ ይለናል። ለመፀነስ እየሞከሩ ነው? እንግዲያውስ እርጉዝ የመሆን እድልን ሊጨምሩ ወይም ሊቀንሱ የሚችሉ አንዳንድ ምክንያቶች አሉ። ቶሎ ማርገዝ ከፈለጉ፤ መቼ እና ምን ያህል ጊዜ የግብረ ሥጋ ግንኙነት ማድረግ እንዳለብዎ ማወቅ አስፈላጊ ነው ይላሉ ባለሙያዎች። ጥናቱ እንደሚለው ከሆነ ሰውነትዎ ለመፀነስ ዝግጁ በሆነበት ጊዜ ተደጋጋሚ ወሲቦችን መፈፀም የማርገዝ እድልን ይጨምራል። ጥናቱ እንዳመለከተው ባለትዳሮች በመጨረሻ ውጤቱን ከማግኘታቸው በፊት በአማካይ 78 ጊዜ የግብረ ሥጋ ግንኙነት ይፈጽማሉ። ይሄ ቁጥር ከ158 ቀናት አልያም 6 ወራት ድረስ ይችላል። ባለሙያዎች በጥናት አገኘነው ያሉት መረጃ አብዛኞቹ ባለትዳሮች ለመፀነስ ሲሞክሩ በወር 13 ጊዜ የግብረ ሥጋ ግንኙነት እንደፈፀሙ ያሳያል። ሆኖም ግን ይላሉ ባለሙያዎቹ፤ ሆኖም ግን በዙ ጊዜ የግብረስጋ ማድረግ እንደሚታሰበው ያክል አስደሳች አይደለም ይልቁንስ አንዳንድ ባለትዳሮች ለማርገዝ ተብለው የሚደረጉ የግብረስጋ ግንኙነትን እንደስራ እንደሚቆጥሯቸው አምነዋል። ይባስ ብሎ አንዳንድ ባለትዳሮች መፀነስ እንደማይችሉ በመፍራት እንደ ግፊት ይወስዱታል። ለዚህም ሳይሆን አይቀርም ባለሙያዎቹ ምንም እንኳን ልጅ ለማግኘት እየሞከራችሁ ቢሆንም አንዳችሁ ስለአንዳችሁ ግን ማሰብ ማቆም የለባችሁም በማለት የሚመክሩት። ☑️ ወሲብ ለመፈፀም የወሩ ተመራጭ ጊዜ የማርገዣ ወቅት ማለት ሴቶች ፅንስ ለመያዝ ዝግጁ የሚሆኑበት ወቅት ሲሆን በዚህ ጊዜ የሚደረግ ወሲብም እርግዝናን የመፍጠር እድሉ ሰፊ ነው፡፡ ይህ የመዳበር ወቅት እንቁላል ከሚፈጠርባቸው አምስት ቀናት ቀደም ብሎ አልያም የእንቁላል መፈጠሪያ ቀንን ያጠቃልላል። ከእንቁላል ማምረት ቀን ሁለት አልያም 3 ቀናት ቀደም ብሎ ወይንም በአንቁላል መመረቻ ቀን ወሲብ መፈፀም እርግዝና የመፈጠር እድሉን ከፍተኛ ያደርገዋል። እንቁላል ከኦቫሪ ከተለቀቀ በኋላ እንቁላሉ ከ12 እስከ 24 ሰዓታት ውስጥ ብቻ ነው ማዳበር የሚችለው። በሌላ በኩል የወንዱ ዘር በሴት የመራቢያ ሥርዓት ውስጥ እስከ አምስት ቀናት ሊቆይ ይችላል። እርጉዝ ለመሆን በሚሞክሩበት ጊዜ ሳይሆን ከዚያም በፊት ባለሙያዎች የግብረ ሥጋ ግንኙነት ማድረግ አለብዎት የሚሉበት ምክንያትም ይህ ነው። ☑️ ግብረ-ሥጋ የመፈፀሚያ መንገድ ጥቂት ሰዎች ወሲብ የሚፈፀምበት መንገድ በራሱ እርጉዝ የመሆን እድልን ሊወስን ይችላል ብለው ያምናሉ። በበርካታ ጥንዶች የሚታወቁት ወሲብ የመፈፀሚያ መንገዶች መካከል ወንድ ከሴቷ ላይ አልያም ከኋላ ሆኖ የሚፈፅምባቸው ዘዴዎች እጅግ ይታወቃሉ። ጥንዶችም እንደሚሉት ከሆነ እነዚህ ወሲብ የመፈፀሚያ መንገዶች የወንድ ዘር በሴቷ የመራቢያ አካል ውስጥ ተጉዘው የዳበሩ እንቁላሎችን እንዲያገኙ በማስቻል ደረጃ የሚወዳደራቸው የለም። ነገር ግን እነዚህ ወሲብ የመፈፀሚያ መንገዶች በሳይንስ የተረጋገጠ አለመሆናቸውን ልብ ይሏል። በነገራችን ላይ እስካሁን ካስነበብናች በሚፃረር መልኩ አንዳንድ ባለሙያዎች በቀን ከአንድ በላይ ወሲብ መፈፀም የወንድ ዘር ወሲብ የመፈፀም አቅሙን ያዳክመዋል ብለው ያስባሉ። ባለሙያዎቹ እንደሚሉት ከሆነ ማርገዝ የፈለጉ ጥንዶች በሳምን ቢያንስ 3 አልያም 4 ጊዜ ወሲብ ለመፈፀም ቢያልሙ አወንታዊ ለውጥ ሊያዩ ይችላሉ፡፡ በበርካታ ጥናቶች መሠረት በየሁለት ቀኑ የግብረ ሥጋ ግንኙነት የሚፈጽሙ ጥንዶች ከፍተኛ የመፀነስ እድል አላቸው። መልካም ጤንነት!! ወቅታዊ እና የተሟሉ የጤና መረጃ ለማግኘት፤ @DrSofonias

የብጉር መነሻ የሚያባብሱ ሁኔታዎችና መከላከያቸው ብጉር የቆዳ ችግር ሲሆን ዘይት/ቅባት እና የቆዳችን የሞቱ ሴሎች የቆዳ ቀዳዳዎችን በሚደፍኑበት ጊዜ ይፈጠራል። ጥቂት ቀያይ ነጠብጣቦች በቆዳዎ ላይ በሚኖሩበት ጊዜ ብጉር እየጀመርዎት ነው ማለት ነው። ከባድ ብጉር የሚባለው በመቶዎች የሚቆጠሩ ነጠብጣቦች (ጠቃጠቆ) በፊት፣ አንገት፣ ደረትና ጀርባዎ ላይ ሲከሰቱና እነዚህ ነጠብጣቦች ትልቅ፣ ደረቅና በጣም ህመም ያለው ቀይ እብጠት ሊሆን ይችላል። ብጉር በወጣትነት/ጉርምስና እድሜ ክልል ውስጥ ያሉትን በከፍተኛ ሁኔታ ያጠቃል። ከወጣትነት ዕድሜ በኋላ ይጠፋል/ይቀንሳል። ☑️ ብጉር እንዴት ይከሰታል? የተለያየ የብጉር አይነቶች አሉ በጣም የተለመደው ግን በወጣትነት ዕድሜ ላይ የሚከሰተው ነው። ለአቅመ አዳም እና ሄዋን ስንደርስ የሆርሞናችን መጠን ይጨምራል በተለይ ቴስቴስትሮን። ይህ የሆርሞን ለውጥ የቆዳችን ዕጢ ብዙ ዘይት(ሴበም) እንዲያመርት ያደርገዋል። በቆዳችን ቀዳዳ የሚወጣው ዘይት ዋናው ጥቅሙ ቆዳችን ጤናማ ወዝ እንዲኖረው ማድረግ ነው። ብጉር የሚጀምረው ዘይት ከሞቱ የቆዳ ሴሎች ጋር ይቀላቀልና የቆዳችንን ቀዳዳ ይዘጉታል በዚህ ውህደት ውስጥ ባክቴሪያ ያገባና ያድጋል። ይህ ውህድ ከጐን ወዳለው የቆዳ ስጋ በማፈትለክ እብጠት፣ መቅላት እና መግል ይፈጥራል። አንዳንድ መድሃኒቶች ለምሳሌ ኮርቲኮስቴሮይድ ወይም ሊቲየም ብጉሩ እንዲባባስ/እንዲያድግ ያደርጉታል። በብጉር የሚጠቁት ወጣቶች ብቻ አይደሉም አንዳንድ ጊዜ ገና የተለወደ ህፃን ብጉር ሊኖራቸው ይችላል ምክንያቱም ህፃናቶቹ ከመወለዳቸው በፊት የህፃኑ እናት ሆርሞን ወደ ህፃኑ ስለምታስተላልፍበት ነው። አንዳንድ የኢንዶክራይን ስርዓት ችግሮች ለምሳሌ ፓሊሲስቲክ ኦቫሪያን ሲንድረም(polycystic ovary syndrome) እና ኩሺንግ ሲንድረም(Cushing syndrome) በብጉር እንድንወረር የሚያደርጉ በሽታዎች ናቸው። ☑️ በብጉር የመጠቃት እድልን የሚጨምሩ ሁኔታዎች በብጉር ለመጠቃት የዘር ሀረግ ወይም ከቤተሰብ ጋር ይያያዛል ወላጅዎ ከባድ ብጉር ካለባቸው እርስዎም በብጉር የመያዝ እድልዎ ከፍተኛ ነው። በብጉር የመጠቃት እድላችን ከፍ የሚለው በጉርምስና እና በመጀመሪያው የወጣትነት ዕድሜ ላይ ነው። የወር አበባ በሚታይበት ዕድሜ ክልል ላይ የምትገኝ ሴት በብጉር የመጠቃት ዕድል አላቸው። አብዛኛዎቹ ሴቶች የወር አበባ ከምትይበት ቀን በፊት ባሉት ቀኖች ላይ በጣም ትናንሽ የብጉር እባጮች ይኖራቸዋል። ☑️ የሚከተሉት ብጉርን የሚያባብሱ ሁኔታዎች ናቸው፦ 🍀 ቆዳን የሚፈገፍጉ/የሚፈትጉ ነገሮች ለምሳሌ፦ ቀበቶ፣ ታይት፣ ሄልመንት፣ እጅ ላይ የሚታሰሩ ነገሮችና የመሳሰሉትን መጠቀም። 🍀 የፀጉርና ቆዳ መጠበቂያ ውጤቶች በተለይ በውስጣቸው የሞያሳክክ ንጥረ ነገር የያዙ 🍀 ፊትዎን ዘወትር/በተደጋጋሚ መታጠብ እና ፊትዎን ሲታጠቡ በጣም ማሸት። 🍀 ሸካራ ሳሙና መጠቀም እና በጣም የሞቀ ውሃ መጠቀም እንዲባባስ ያደርገዋል። 🍀 ጭንቀት ሲኖር 🍀 ፊትን በተደጋጋሚ መንካት 🍀 ላብ በብዛት ሲያልበን 🍀 በፊት ላይ በዛ ያለ ፀጉር መኖር የፊት ቆዳ ዘይት/ቅባት እንዲኖረው ያደርጋል። 🍀 አንዳንድ መድሃኒቶች መውሰድ(ኮርቲኮስቴሮይድ፣ ባርቢቱሬትስ ወይም ሊትየም) 🍀 በዘይት እና ኬሚካል ማምረቻዎች አካባቢ መስራት 🍀 አትሌቶችና ሰውነታቸውን የሚገነቡ ስፓርተኞች ስቴሮይድ ስለሚወስድ በብጉር የመጠቃት ዕድል አላቸው። ☑️ የብጉር መከላከያ መንገዶች ብጉርን መከላከል አይቻልም ነገር ግን እንዳይባባስ የሚወሰድ እርምጃዎችና ጥንቃቄዎች አሉ ከነዚህም መካከል፦ 🔹በዝግታ ወይም በጣም ሳይሹ መታጠብ ለቆዳዎ ጤንነት አስፈላጊ ነው። በጣም ማሸት፣ መጥረግ፣ መፈተግ ወይም መፈግፈግ ተገቢ አይደለም። 🔹በጣም እንዳያልብዎ መጠንቀቅ። ላብ እንዲያልበን የሚያደርጉ እንቅስቃሴዎች ካደረግን በኋላ ወዲያው መታጠብ። 🔹ፀጉርዎ ቅባት ካለው ወይም ከበዛበት መታጠብ። 🔹አንዳንድ የፀጉር መንከባከቢያ ምርቶችን መጠቀም ማቆም ለምሳሌ፦ ጄል፣ ክሬምና የመሳሰሉት 🔹ፊትዎን ቶሎ ቶሎ ከመንካት መቆጠብ 🔹ለስላሳ የኮተን ልብሶችን መጠቀም በተለይ ከቆዳ ጋር ንክኪ ያላቸው። 🔹ከቅባት እና ኬሚካል ጋር ያለዎትን ግንኙነት መቀነስ/ማቆም ለምሳሌ ፔትሮሊየም። መልካም ጤንነት!! ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ የጤና መረጃ ለማግኘት፤ በፌስቡክ 👇 https://www.facebook.com/DrSoffonias በቴሌግራም 👇 @DrSofonias

ስለ ከፍተኛ ኮሌስትሮል ማወቅ ያለብን ነገሮች ከፍተኛ የኮሌስትሮል መጠን በሰውነት ውስጥ የመገኘት ችግር በስፋት የሚያጋጥም ነው። ይህ ለጤና ጠንቅ የሆነ ጉዳይ በሀኪም ምርመራ እስኪደረግልን ድረስ እንዳጋጠመን ላናውቅ እንችላለን። ምልክቶችም ላይኖሩት ይችላሉ። ☑️ ኮሌስትሮል ምንድነው? ኮሌስትሮል ጉበታችን የሚያመርተው ለሴል ሜምብሬን ግንባታ፣ ለተወሰኑ ሆርሞሞች እና ለቪታሚን ዲ መመረት ወሳኝ የሆነ ቅባት (lipid) ነው። ይህ ቅባት በባህሪው ውሃ ውስጥ የሚሟሟ ስላልሆነ በቀላሉ በደማችን ውስጥ መጓጓዝ አይችልም። በዚህም ምክንያት ጉበታችን ለኮሌስትሮል ማጓጓዣ የሚረዳ ሊፖፕሮቲን (lipoprotein) ያዘጋጃል። ይህ ሊፖፕሮቲን ነው ኮሌስትሮልን ጨምሮ triglycerides የተባለውን ሌላ ቅባት በደማችን ውስጥ የሚያጓጉዘው። ሊፖፕሮቲን ሁለት የተለያዩ መልኮች አሉት። low density lipoprotein (LDL) እና high density lipoprotein (HDL) ይባላሉ። በዚህ መሰረት በLDL የሚጓጓዘው ኮሊስትሮል LDL ኮሊስትሮል ተብሎ ይጠራል። አንድ ሰው በደም ውስጥ የዚህ አይነቱ ኮሌስትሮል በከፍተኛ ደረጃ ሲገኝ ነው ከፍተኛ የኮሌስትሮል መጠን አለበት የሚባለው። LDL ኮሌስትሮል “bad cholesterol ” ተብሎም ይጠራል። ይህ የሆነበት ዋነኛ ምክንያት ይህ አይነቱ ኮሌስትሮል ወደ ደም ቧንቧችን ገብቶ ግድግዳው ላይ ስለሚለጠፍ ነው። ይህም cholesterol plaque የሚባለውን ንጣፍ በደም ቧንቧ ግድግዳ ላይ እንዲፈጠር ያደርጋል። ይህ ንጣፍ (cholesterol plaque) የድም ቧንቧችን እንዲጠብ ስለሚያደርግ የደም መርጋት (blood clotting) ይከሰታል። ይህም በተራው ለልብ ህመም ወይም ስትሮክ መከሰት ምክንያት ይሆናል። አንድ ሰው ከፍተኛ የኮሌስትሮል መጠን ኖሮበት በአግባቡ ህክምና ካልተደረገለት ቀስ በቀስ ነገሩ ለሌሎች የጤና ችግሮች መንስዔ ሊሆን ይችላል። ከነዚህም መካከል የልብ በሽታ እና ስትሮክ የመሳሰሉት ተጠቃሽ ናቸው። ከፍተኛ ኮሌስትሮል ሲከሰት ብዙዉን ጊዜ ምልክቶች ላይኖሩት ይችላሉ፣ስለዚህ የሚመከረው ነገር በየጊዜው በሰውነት ውስጥ ያለንን የኮሌስትሮል መጠን በምርመራ ማወቅ ነው። ☑️ ከፍተኛ ኮሌስትሮል እንዴት ይከሰታል? የኮሌስትሮል መጠናቸው ከፍ ያሉ ቅባታማ (fatty) ምግቦችን አብዝቶ መመገብ ለኮሌስትሮል መጠን መጨመር አንዱ ምክንያት ሊሆን ይችላል። ከዚህም በተጨማሪ ከመጠን ያለፈ ክብደትን (obesity) ብጊዜ አለማስተካከል የኮሌስትሮል መጠናችን ከፍ እንዲል ሊያደርግ የሚችልበት እድል ሰፊ ነው። ሌላው ሲጋራ ማጨስ እና ስፖርታዊ እንቅስቃሴ አለማድረግ ነው። ከላይ ከጠቀስናቸው ምክንያቶች በተለየ ለኮሌስትሮል ችግር ምክንያት ሊሆን የሚችለው ጄኔትክ የሆነው ችግር ነው። ከቤተሰብ መካከል ይህ አይነቱ ችግር ያለበት ሰው ካለ ሰውነታችን ኮሌስትሮልን የሚያስተናግድበት ኮድ በዘር (genetically) የሚተላለፍበት እድል አለ። ☑️ እንዴት መከላከል ይቻላል? የሚከተሉትን መንገዶች መከተል በከፍተኛ ኮሌስትሮል መጠን ሊደርስብን ከሚችለው መከላከያ ሊሆነን ይችላል። 🔹 የኮሌስትሮል መጠናቸው ዝቅተኛ የሆኑ ምግቦችን መመገብ፦ ከነዚህም መካከል አቮካዶ፣ አጃ፣ ገብስ፣ ፍራፍሬዎች ተጠቃሽ ናቸው። 🔹 ተመጣጣኝ ክብደት ይኑርዎት 🔹 የምንወስደውን የአልኮል መጠን መቀነስ 🔹 ማጨስ መቀነስ (ከተቻለም ማቆም) 🔹 መደበኛ ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎችን ማድረግ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ የጤና መረጃ ለማግኘት፤ @DrSofonias

30ን የተሻገሩ ወንዶች መውሰድ ያለባቸው ማዕድናት እና አስፈላጊ ንጥረ ነገሮች 30 የእድሜ ክልልን ሲሻገሩ ሰውነትዎ ተጨማሪ ማዕድናት ይፈልጋልና የህክምና ባለሙያ ቢያማክሩ መልካም ነው፡፡ ታዲያ ለወንዶችና ለሴቶች የሚያስፈልጓቸው ሚኒራሎች ግን የተለያዩ ናቸው። ወንዶች ከፕሮስቴት ጋር የተያያዙ ችግሮችን ለመፍታት ዚንክ ሲያስፈልጋቸው ሴቶቹ ደግሞ የሄሞግሎቢን ችግርን ለመቅረፍ ብረት ሊፈልጉ ይችላሉ፡፡ የሆነው ሆኖ 30ን የተሻገሩ ወንዶች የሚያስፈልጓቸውን ተጨማሪ ሚኒራሎችን እንንገርዎ፡፡ 🔹 ፖታሲየም ፖታሲየም የደም ግፊት ከፍ እንዳይል ትልቅ ሚና የሚጫወት ሲሆን አጥረቱ ከተከሰተ ደግሞ ለኩላሊት ጠጠር፣ ለስትሮክ እንዲሁም ለሃይፖካሊሚያ የመጋለጥ እድል ይኖራል። በሃይፖካሊሚያ ጊዜ በደም ውስጥ ያለው የፖታሲየም መጠን ዝቅተኛ ይሆናል ይህ ደግሞ የድካም ስሜት፣ የጡንቻ መንቀጥቀጥ እንደሁም የጡንቻ መኮማተር የሚያስከትል ሲሆን ከፍ ሲልም ሽባ እስከመሆን ያደርሳል፡፡ በነገራችን ላይ የፖታሲየም ማነስ ችግር እንዳለው ሁሉ መብዛትም ልብ ድካምና ሞት ሊያስከትል ይችላል፡፡ 🔹 ቦሮን ከ 30 አመት በላይ የሆናቸው ወንዶች በአመጋገባቸው ውስጥ ሊያካትቱት ከሚገባቸው በጣም ጠቃሚ ማዕድናት አንዱ ቦሮን ነው። ቦሮን የኢስትራዶይል እና ቴስቶስትሮን ምርት ውስጥ ወሳኝ ሚና ይጫወታል። ወሲባዊ ጤንነት ጥሩ እንዲሆን ትልቅ ሚና የሚጫወቱትን ማዕድናት እና ንጥረ ነገሮች መጥጦ በማስቀረት በኩልም ጠቃሚ ነው፡፡ 🔹 ኦሜጋ 3 ኦሜጋ 3ትን የሚጠቀሙ ሰዎች በልብ ድካም በሽታ የመሞታቸው አድል ዝቅተኛ ስለሆነ 30 የሞላቸው ወንዶች ይህን ማዕድን እንዲወስዱ ባለሙያዎች ይመክራሉ፡፡ ጧት ጧት የሚከሰት ሰውነት ግትር የማለትና የህመም ስሜትንም ይቀንሳል። በኦሜጋ 3 የበለፀገ የአሳ ዘይት ከካልሲየም እና ፕሪምሮዝ ዘይት ጋር ተደባልቆ ቢወሰድ የአጥንትን ውፍረት ይጨምራል፡፡ በአረጋውያን ላይ እንኳን ሳይቀር ኦስቲዮፖሮሲስን ይከላከላል። እንዲሁም የሰባ ዓሳ የአዕምሮ ጤናን ለማሻሻል እና እንደ የመርሳት በሽታ እንዲሁም የማስታወስ ችሎታ ማጣት ያሉ በሽታዎችን ለመከላከል ይረዳል። 🔹 ዚንክ በወንዶች ወሲባዊ ጤና ላይ ሚናው ከፍተኛ የሆነው ዚንክ እንደ ፕሮላቲን እና ቴስቶስትሮን ያሉ የወሲብ ሆርሞኖች እንዲፈጠሩ ቁልፍ ሚና ይጫወታል። በተጨማሪም በፕሮቲን ውህደት ውስጥ የራሱ ጉልህ ድርሻ ስላለው ቁስሎችን ለመፈወስ እና የቁስል መመረዝን ለመቋቋም ይረዳል፡፡ 🔹 ካልሲየም 30ዎቹን እድሜ የተሻገሩ ወንዶች የጡንቻቸውንና የአጥንት ጤንነታቸውን መጠበቅ ከፈለጉ ካልሲየምን እንዲወስዱ ይመከራሉ። ካልሲየም አጥንትን እና ጥርስን በመመገብ ረገድ ወሳኝ ሚና የሚጫወት ሲሆን እንደ መዝናናት እና መኮማተር ያሉ የጡንቻ ተግባራትን ለመቆጣጠርም ይረዳል። የሆነው ሆኖ ግን 30 አመትን የተሻገረ የትኛውም ወንድ ምንም አይነት ማዕድን አልያም ቫይታሚኖች ከመውሰዱ በፊት የግድ ባለሙያ ማማከር አለበት፡፡ @DrSofonias

4️⃣ ጥራጥሬዎች፡- ባቄላ የዶክተር ሃርላን ተመራጭ የፕሮቲንና የበሽታ ተከላካይ ቫይታሚኖች መገኛ ነው። ባቄላ፣ ሽምራ፣ አተር እና የመሳሰሉት የጥራጥሬ አይነቶች ጠቃሚዎች ናቸው። ‹‹ቆዳችን ከፕሮቲን የተሰራ ነው፡፡ ጥራት ያላቸው በቂ ፕሮቲኖች የማያገኙ ከሆነ ችግሩ ቆዳዎ ላይ ይንፀባረቃል ይላሉ። ጂያን ኮሊም ባቄላና አሳ የቆዳን ውበት እንደሚያሳምሩ ይገልፃሉ›› 5️⃣ አጃ፡- ጥናቶች እንደ አጃ፣ ዳቦ፣ ፓስቲ፣ ቡናማ ሩዝ ያሉት የእህል አይነቶች የመጉረብረብ ስሜትን እንደሚቀንሱ ገልፀዋል። ‹‹እነዚህ ምግቦች ለቆዳችን ጠቃሚ የሆኑትን እንደ ታሚንና ራይቦ ፍላቪን ያሉትን የቫይታሚን ቢ ዝርያዎችን ይዘዋል። የእነዚህ እጥረት በቆዳችን ላይ ሽፍታ እንዲወጣና ቆዳችንም ወዝ አልባ እንዲሆን ያደርገዋል›› መልካም ጤንነት!! ወቅታዊ እና የተሟሉ የጤና መረጃ ለማግኘት፤ @DrSofonias

የሚያስረጁ እና የማያስረጁ ምግቦች የአመጋገብ እቅድዎ በውስጥና በውጭ ወጣት ሆነው እንዲቆዩ የማድረግ ብቃት አለው፡፡ በጠዋት ተነስተው መስተዋት ፊት ሲቆሙ የሚያስቡት “ዋው! አምሮብኛል?” አሊያም “መቼ ነው እንዲህ ያረጀሁት?” ብለው ነው? ሁለተኛውን የሚሉ ከሆነ ፍሪጅዎን፣ ማዕድ ቤትዎና የምግብ ጠረጴዛዎ ላይ የሚያኖሩትን ምግብ ይጠራጠሩ። እርጅና በሁላችንም የመጣና ማቆም የማይቻል ቢሆንም አዘውትረን የምንመገባቸው አንዳንድ ምግቦች ያለ ዕድሜያችን አርጅተን እንድንታይ ያደርጋሉ። የእነዚህ ምግቦች ጉዳት በውጫዊ እኛነታችን ላይ ብቻ የሚገደብ አይደለም። ውስጣዊ ጉዳትም ያደርሳሉ። ☑️ ጥራት ወሳኝነት አለው (Quality Counts) “በቅባትና በስብ የተጥለቀለቁ ምግቦችን መመገብ ሰውነታችንን እንዲቆጣ ያደርገዋል” ይላሉ Just tell me what you eat! የሚለው መፅሐፍ ደራሲና በቱሌን ዩኒቨርሲቲ የህክምና ትምህርት ቤት ረዳት ፕሮፌሴር የሆኑት ቲሞቲ ሃርላን፡፡ “የጥራትና የጠቃሚ ንጥረ ነገሮች ይዘታቸው ዝቅተኛ የሆነ Trans fats (ስብ የበዛባቸው ምግቦች) የሰውነታችንን የመቆጣት ስሜት ያነሳሳሉ፡፡ እርጅና ደግሞ መሰረታዊ የሆነ የሰውነት የመጉረብረብ ሁኔታ ነው፡፡ ‹ክራብ የተሰኘውን ከባህር የሚገኝ ምግብ በመመገቤ የተነሳ ከዕድሜዬ በላይ ያረጀቡ እመስላለሁ› ብለው ቢጠይቁኝ መልሴ አዎ! የሚል ይሆናል” ይላሉ ዶክተሩ፡፡ “ለምሳሌ በጣም ብዙ ስኳርና በፋብሪካ ሂደት ውስጥ ያለፈ ካርቦሃይድሬትስ ያላቸው ምግቦች (processed carbohydrates); AGE (Advanced Glycation End) የተሰኘው ጎጂ ንጥረ ነገር እንዲፈጠር ምክንያት ይሆናሉ፡፡ ይህ ንጥረ ነገር ለበርካታ ጎጂ በሽታዎች ያጋለጣል፡፡ ከእነዚህ የልብና የስኳር በሽታዎች ዋነኞቹ ናቸው። ከዚህ በተጨማሪም በጅማቶችና በቆዳ ፋይበሮች ላይ ጉዳት ያደርሳሉ” ባይ ናቸው የካሊፎርኒያ የህዝብ ጤና ማዕከል አማካሪና የአሜሪካ የስነ ምግባር ማህበር ቃል አቀባይ የሆኑት አንድሪያ ጂያን ኮሊ። ጎጂ ተብለው የሚመደቡ ምግቦችን መመገብ የሚያደርሰው ጉዳት በአካላዊ አቋማችን የተወሰነ አይደለም፡፡ ከእነዚህ ምግቦች አብዝቶ መመገብ የመቆጣትና መጉረብረብ ስሜትን ይጨምራል፡፡ የደም ቅዳዎች ደም እንዲረጋባቸው ያደርጋል፡፡ ክብደት እንድንጨምርም ምክንያት ይሆናሉ፡፡ ይህ ደግሞ ከፀጉራችን እስከ ጥፍራችን ድረስ ላለው ጤና መጥፎ ዜና ነው፡፡ ☑️ ሊቀንሷቸው የሚገቡ ምግቦች ወዝና ቁመናዎን ጠብቀው ከዕድሜዎ ጋር ሲተያይ ወጣት መስለውና ሆነው መታየት ከፈለጉ የእነዚህን አምስት ምግቦችና መጠጦች አወሳሰድዎን ይቀንሱ፡፡ 1. የድንች ጥብስና በቅባት የተነከረ የድንች ጥብስ በዘይት እየተነከረ የሚጠበስ ማንኛውም ምግብ በጎጂ ንጥረ ነገሮች በትራንስ ፋት (Trans Fates) የታጨቁ ናቸው። ይህም በመላው አካላችን ውስጥ የመጉረብረብ ስሜትን ይፈጥራል። በዕለታዊ ማዕድዎ ላይ የድንች ጥብስ መጠንዎን ከ1% በታች እንዲያደርጉ የአሜሪካ የልብ ማህበር ይመክራል። 2. ዶናት እና በስኳር የተሞሉ ፓስቴዎች እነዚህ ምግቦች የተለያዩ አይነት ጎጂ ንጥረ ነገሮችን ይዘዋል። በአብዛኛው ትራንስ ፋት (Trans fates) በከፍተኛ መጠን ይገኙባቸዋል። በስኳር የተሞሉም ናቸው። በፊታችን ላይ መጨማደድና ሽብሽባትን የሚያስከትለው AGE መገኛዎችም ናቸው። 3. ሃት ዶግና ቋሊሟ የትኛውም በፋብሪካ ፕሮሰስ ተደረገ ሥጋ፣ የአሳማ ሥጋና የመሳሰሉው በቅባት ያበደ ጥብሳ ጥብስ ከጥቅሙ ጉዳቱ እጅግ ያመዘነ ነው። ሳቹሬትድ (saturated) የተሰኘው ጎጂ የስብ አይነት በከፍተኛ መጠን ይገኝባቸዋል። የመለብለብና የመቆጥቆጥ ስሜትን የሚያባብሱት ናይትሬትስ የተሰኙ ንጥረ ነገሮች እንዲከማቹም ያደርጋሉ። 4. ቀይ ሥጋም ቢሆን በጥቂቱ ይመገቡ ጎጂ ስብ በሰውነታችን እንዳይከማች ቀላ ያሉ (ስብ ያልያዙ) ሥጋዎችን እንደንመገብ ይመከራል፡፡ ይህም ቢሆን ለደም ቆዳዎች (arteries) አስደሳች ሁኔታን አይፈጥርም። የአሜሪካ የስነ ምግብ ማህበር እ.ኤ.አ በ2010 ባወጣው መመሪያ ላይ የተለያዩ በፕሮቲን የበለፀጉ ምግቦችን መመገብ (ቀይ ሥጋን ያጠቃልላል) ጠቃሚ እንደሆነ ይገልፃል፡፡ የአሜሪካ የልብ ማህበር በበኩሉ ጎጂ ኮሌስትሮልን የያዙ ምግቦችን እንድናስወገድ ካልተሳካልን ደግሞ ዕለታዊ ፍጆታችንን ከ7% በታች እንዳደርግ ይመክራል፡፡ 5. አልኮል አንዳንድ የአልኮል አይነቶች ለእርስዎ ጠቃሚ ሊሆኑ ይችላሉ። ነገር ግን የበዛ የአልኮል አወሳሰድ በእርግጠንነት ያለ ዕድሜዎ ያረጁ ሊያስመስልዎ ይችላል። ለሴት በቀን አንድ (አንድ ብርጭቆ ወይን ወይም ቢራ) ሲመከር ለወንዶች የሴቷን እጥፍ ቢወስዱ አይጎዳም። በቀን በአማካይ አንድ ወይም ሁለት መለኪያ አልኮል ቢጎነጩ ለልብዎ ጠቃሚ ሊሆን ይችላል። ከዚያ ካለፈ ግን የእርጅና ሂደትዎን ያፋጥናል፤ እንደ ጉበት እና አንዳንድ የካንሰር ህመሞች ያሉ ተያያዥ በሽታዎችንም ያስከትላል። የማይጠጡ ከሆነ የጤና ባለሙያዎች እንዲጠጡ አይመክሩዎትም። የሚጠጡ ከሆነ ግን ለዶክተርዎ ከመናገር አይቆጠቡም። የሚያሳስበዎ የጤና ችግሮች ከእርስዎ የአልኮል አወሳሰድ ጋር ግንኙነት እንዳላቸው ሊነግርዎ ይችላል። ‹‹ከሁሉም በላይ ይላሉ…›› ዶ/ር ሃርላን ‹‹ተገቢውን ማዕድንና ቫይታሚን የያዙ፣ ከፍተኛ ጥራት ያላቸውን ምግቦች መመገብ የሚፈጠረውን የመጉረብረብ ስሜት ይቀንሳል። በጥሩ ውስጣዊና ውጫዊ አቋም ላይ እንዲገኙ ያደርጋል። የሜዲትራኒያን የአበላል ዘዴ የሚሰኘው የአመጋገብ ባህል ከእርጅና ጋር ተያይዘው የሚመጡትን ካንሰር፣ አልዛይመርና የልብ ህመሞችን ያስወግዳል›› ☑️ ልናዘወትራቸው የሚገቡ ምግቦች ሃርላን እና ጂያን ኮሊ ጥቅማቸው ከፍተኛ የሆኑትን፣ ወጣት የሚያስመስሉትንና ጤናማ የሚያደርጉትን (super foods) እንድናዘወትር ይመክራሉ። “ይህ ሲባል ግን የተወሰኑ ምግቦችን መርጣችሁ እነሱ ላይ ማተኮር ማለት አይደለም። ይህ ሁኔታ ትልቁን ምስል እንዳትመለከቱት ያደርጋል›› አሳ ወይንም ፍራፍሬዎችን ብቻ ሳይሆን አበባ ጎመን፣ ስኳር ድንች፣ ሳልመን (አሳ)፣ ሽምብራ እና የዶሮ ሥጋን መመገብ ለአጠቃላይ ጤንነት ይጠቅማል” ይላሉ ዶክተር ሃርላን። ሁለቱም ኤክስፐርቶች ለጤናችን በጣም ጠቃሚ ነው ያሉትን የሜዲትራንያን የአመጋገብ ዘዴ እንድናዘወትር ይመክራሉ። የመረጧቸውን አምስት ከማዕዳችን ላይ መጥፋት የሌለባቸው ምግቦች የሚከተሉት ናቸው። 1️⃣ ሰላጣ፡- ሰላጣ በሽታ ተከላካይ ቫይታሚኖች ተብለው በሚጠሩት በቫይታሚን ኤ እና ሲ የበለፀጉ ሲሆን የመቆጣትና የመጉረብረብ ስሜትን ይዋጋሉ። ሌሎች ጥቁር አረንጓዴ ቀለም ያላቸው እንደ አበባ ጎመንና ስፒናች ያሉትን በማዕዳችን ላይ ማካተት ያስፈልጋል። 2️⃣ ቲማቲም፡- እንደ ሃብሃብ፣ ወይን፣ ዘይቱን፣ አስፓራገስ፣ ቀይ ጎመን ሁሉ ቲማቲም በበሽታ ተከላካዮች የበለፀገውን Lycopene ያስገኝልናል። 3️⃣ ሳልመን፡- እንደ የባህር አሳዎች ቱና እና ሄሪንግ (herring) ሁሉ ሳልመን በኦሜጋ 3 ፋቲ አሲድ የበለፀገ ነው። የሰውነት መመረዝን ይከላከላል።

ደም ለማን ይስጡ? ከማንስ ይቀበሉ? ☑️ የደም አይነት: A+ 🔸 ለማን ይሰጣል ለ A+, AB+ ይሰጣል። 🔸 ከማን ይቀበላል ከ A+, A-, O+ እና O- ይቀበላል። ☑️ የደም አይነት: O+ 🔹 ለማን ይሰጣል ለ O+, A+, B+, AB+ ይሰጣል። 🔹 ከማን ይቀበላል ከ O+, O- ይቀበላል። ☑️ የደም አይነት: B+ 🔸 ለማን ይሰጣል ለ B+, AB+ ይሰጣል። 🔸 ከማን ይቀበላል ከ B+, B-, O+ እና O- ይቀበላል። ☑️ የደም አይነት: AB+ 🔹 ለማን ይስጥ፦ ለ AB+ ብቻ ይሰጣል። 🔹 ከማን ይቀበል፦ ከሁሉም ይቀበላል። ☑️ የደም አይነት: A- 🔸 ለማን ይስጥ፦ ለ A+, A-, AB+, AB- ይሰጣል። 🔸 ከማን ይቀበል፦ ከ A-, O- ይቀበላል። ☑️ የደም አይነት: O- 🔹 ለማን ይስጥ፦ ለሁሉም ይሰጣል። 🔹 ከማን ይቀበል፦ ከ O- ይቀበላል። ☑️ የደም አይነት: B- 🔸 ለማን ይስጥ፦ ለ B+, B-, AB+, AB- ይሰጣል። 🔸 ከማን ይቀበል፦ ከ B-, O- ይቀበላል። ☑️ የደም አይነት: AB- 🔹 ለማን ይስጥ፦ ለ AB+, AB- ይሰጣል። 🔹 ከማን ይቀበል፦ ከ AB-, A-, B- እና O- ይቀበላል። መልካም ጤንነት!! ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ የጤና መረጃ ለማግኘት፤ @DrSofonias

የግብረ-ሥጋ ግንኙነት የጤና ጥቅሞች 🔸 የተሻለ የደም ግፊት እንዲኖረን ያደርጋል፡፡ 🔸 ጭንቀትን ይቀንሳል ወይም ያስወግዳል፡፡ 🔸 የተሻለ በራስ መተማመን እንዲኖረን ያደርጋል፡፡ 🔸 የተሻለ እን
የግብረ-ሥጋ ግንኙነት የጤና ጥቅሞች 🔸 የተሻለ የደም ግፊት እንዲኖረን ያደርጋል፡፡ 🔸 ጭንቀትን ይቀንሳል ወይም ያስወግዳል፡፡ 🔸 የተሻለ በራስ መተማመን እንዲኖረን ያደርጋል፡፡ 🔸 የተሻለ እንቅልፍ እንድንተኛ ያደርጋል፡፡ 🔸 የልብ ጤንነት እንዲሻሻል ያደርጋል፡፡ 🔸 በሽታ የመከላከል አቅማችንን ይጨምራል፡፡ 🔸 ከህመም እንድናገገም ይረዳል፡፡ 🔸 ሸንቀጣ ሰውነት እንዲኖረን ያደርገናል፡፡ 🔸 ደስታን ያጐናጽፋል/ይጨምራል፡፡ 🔸 በፕሮስቴት ካንሰር የመያዝ እድልን ይቀንሳል፡፡ 🔸 መቀራረብን ወይም ቁርኝትን ይጨምራል፡፡ መልካም ጤንነት!! ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ የጤና መረጃ ለማግኘት፤ @DrSofonias